newsare.net
በዓለም ዙሪያ ትናንት ቅዳሜ ብቻ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተመዘገበው ሰዎች ቁጥር እስከዛሬ በሃያ ሰዓት ውስጥ ከተገኙት ሁሉ ከፍተኛው መሆኑ ተገለጸ ሁለትየትናንቱ ዕለታዊ የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ቁጥር ከፍተኛው ነው
በዓለም ዙሪያ ትናንት ቅዳሜ ብቻ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተመዘገበው ሰዎች ቁጥር እስከዛሬ በሃያ ሰዓት ውስጥ ከተገኙት ሁሉ ከፍተኛው መሆኑ ተገለጸ ሁለት መቶ አስራ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ስድስት አዲስ የቫይረስ መመዝገቡን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል ካሁን ቀደም የታየው ከፍተኛ ዕለታዊ የአዲስ ተጋላጮች አሃዝ ባለፈው ሳምንት ዕሁድ አንድ መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሰባ ሰባት እንደነበር ይታወሳል በበሽታው ምክንያት አሁንም በቀን ቁጥሩ አምስት ሺህ ለህልፈት እየተዳረገ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ትናንትና ብቻ ሃምሳ ሁለት ሺህ አራት መቶ ዘጠና ሁለት የቫይረሱ ተጋላጮች የተመዘገቡ ሲሆን አጠቃላዩ ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማኒያ ሺህ አልፏል ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንትየነጻነት ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ በዋይት ሐውስ ባስተናገዱት ዝግጅት ባሰሙት ንግግር በሀገሪቱ በኮቪድ አስራ ዘጠኝ ምክንያት አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን አላነሱም፤ ሃገሪቱ ቫይረሱን መዛመት ለመግታት እየታተረች ቢሆንም ፕሬዚደንቱ የኮቪድ አስራ ዘጠኝ ስትራተጂያችን በጥሩ ሁኔታ እየተራመደ ነው ብለዋል እስከዓመቱ መጨረሻ ባለው ጊዜ ውስጥ ክትባቱን ወይም መድሃኒቱን ማግኘታችን አይቀርም ሲሉም ተናግረዋል በሳይንቲስቶች ዕምነት ግን በዚሁ ዓመት ውስጥ ከተገኘ በሚያስገርም ሁኒታ ከተፋጠነ ብቻ ነው ባዮች ናቸው Read more