newsare.net
ፍልስጤም አሜሪካዊት ጋዜጠኛ ሽሪን አቡ አክሌህ አስክሬንን ተሸክመው ይጓዙ የነበሩ ሰዎች ላይ ድብደባ ባደረሱ የእስራኤል ፖሊሶች ላይ ዩናይትድ ስቴትስ እና የየእስራኤል ፖሊሶች በአልጄዚራዋ ጋዜጠኛ ቀብር ስነስርዓት ላይ የፈጸሙት ድብደባ ተወገዘ
ፍልስጤም አሜሪካዊት ጋዜጠኛ ሽሪን አቡ አክሌህ አስክሬንን ተሸክመው ይጓዙ የነበሩ ሰዎች ላይ ድብደባ ባደረሱ የእስራኤል ፖሊሶች ላይ ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ሕብረት ዓለም አቀፍ ተቃውሞ አደረጉ። የእስራኤል ፖሊሶች ባደረጉት ድብደባ የጋዜጠኛዋ አስክሬን ሊወድቅ ነበር። ታዋቂዋ የአልጄዚራ ጋዜጠኛ በዌስት ባንክ ከተገደለች ከሁለት ቀናት ትላንት አርብ በቀብር ስነስርዓቷ ላይ ለመታደም እጅግ በዙ ሰዎች በእየሩሳሌም ጥንታዊው ከተማ ተግኝተዋል። በቴሌቪዥን የተላለፉ ምስሎች እንደሚያሳዩት ከሆነ የእስራኤል ፖሊሶች የፍልስጤም ባንዲራ ከያዙ ለቀስተኞች ላይ ለመቀማት ሲሞክሩ እና አስክሬኑን የተሸከሙ ሰዎችን በቆመጥ ሲመቱ የታየ ሲሆን በዚህ የተነሳም የአስክሬን ሳጥኑ ከእጃቸው አምልጦ ሊወድቅ ሲል ታይቷል። ዩናይትድ ስቴትስ ሁኔታውን ‘እጅግ የሚረብሽ’ ስትል የአውሮፓ ሕብረት ደግሞ ፖሊሶቹ በተጠቀሙት ‘አላስፈላጊ ጉልበት ተደናግጫለሁ’ ብሏል። በሁኔታው በቦታው የነበሩ 33 ሰዎች ሲጎዱ ሌሎች ስድስት ሰዎች ደግሞ ሆስፒታል መግባታቸውን የእየሩሳሌም ቀይ ጨረቃ አስታውቋል። Read more