Ethiopiaየዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጽንስ ማቋረጥን ህገ መንግሥታዊ መብት ያደረገውን ታሪካዊ ውሳኔ ሻረው

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለሀገሪቱ ሴቶች የፅንስ የማቋረጥ ህገ መንግሥታዊ መብት የሰጠውን እአአ የ1973ቱን ሮ ቪ ዌድ ተብሎ የሚጠራውን ውሳኔ በዛሬ
የአሜሪካ ድምፅ

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጽንስ ማቋረጥን ህገ መንግሥታዊ መብት ያደረገውን ታሪካዊ ውሳኔ ሻረው

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለሀገሪቱ ሴቶች የፅንስ የማቋረጥ ህገ መንግሥታዊ መብት የሰጠውን እአአ የ1973ቱን ሮ ቪ ዌድ ተብሎ የሚጠራውን ውሳኔ በዛሬው ዕለት ሽሮታል። በዚህ በዛሬው ውሳኔውም ፍርድ ቤቱ ላለፉት ሃምሳ ዐመታት በህግ የተፈቀደ ሆኖ የኖረውን ጽንስን ማቋረጥን የመፍቀድ ወይም የመከልከል ስልጣን የየክፍላተ ሀገሩ (የስቴቶቹ) ፋንታ አድርጎታል። ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ወግ አጥባቂ ዳኞች አንዱ የሆኑት ዳኛ ሳሙኤል አሊቶ ባቀረቡት እና ሌሎች አራት ወግ አጥባቂ ዳኞች በደገፉት የውሳኔ አስተያየታቸው «ህገ መንግሥቱ ስለ ፅንስ ማስወረድ የሚናገረው ነገር የለም። እንዲህ ያለውን መብት በተዘዋዋሪ የሚያስጠብቅ አንዳችም የህገ መንግሥት አንቀጽም የለም።» ብለዋል። የዚህ የዳኛ አሊቶ የውሳኔ አስተያየት ረቂቅ ከሁለት ወራት ገደማ በፊት በድብቅ አንድ የዜና አውታር እጅ መድረሱን ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ የጽንስ ማቋረጥ መብት ተሟጋቾች ተቃውሞ ሲያሰሙበት ቆይተዋል። በዕርግጥ እአአ በ1973 ጀመሮ ፀንቶ የቆየውን ሮ ቪ ዌድ ተብሎ የሚጠራውን የራሱን ውሳኔ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መቀልበሱ ፅንስ ማቋረጥን አያግድም።  ይሁን እንጂ በመላ ሀገሪቱ ጉዳዩን በሚመለከቱ ህግጋት ላይ  አንድምታው ሳይውል ሳያድር መምጣቱ የማይቀር ነው። ገትማከር ኢንስቲቲዩት የተባለው የሴቶች የጽንስ ማቋረጥ መብት ደጋፊ የምርምር ተቋም እንደሚለው አብዛኞቹ በደቡብ እና በማእከላዊ ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስ ያሉ ሀያ ስድስት ክፍላተ ሀገር (ስቴቶች) ሮ ቪ ዌድን ከሚሰርዘው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ ጽንስ ማስወረድን በህግ እንደሚከለክሉ አመልክቷል። ያ ሲሆን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሴቶች ጽንስ የማቋረጥ መብታቸው ወደሚከበርበት የሀገሪቱ አካባቢ ለመጉዋዝ ይገደዳሉ። ለዘብተኞቹ ወይም ሊብራሎቹ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች ዳኛ ስቴፈን ብራየር፥ ሶኒያ ሶቶማዮር እና ኤሌና ኬገን የወግ አጣባቂዎቹን ዳኞች ውሳኔ አጥብቀው የተቃወሙ ሲሆን "ይህ የዛሬው ውሳኔ በርግጠኝነት አንድ ውጤት ይኖረዋል። ያም ሴቶችን በዜግነት የሚገባቸውን ነጻነት እና ዕኩልነት የሚገፍፋቸው መሆኑ ነው።' ብለዋል።

የመተማ አርሶ አደሮች «የሱዳን ታጣቂዎች አፈናቀሉን፤» አሉ

- «246 ባለሀብቶች ሥራ አቁመዋል» /የዞኑ አስተዳዳሪ/ ከሱዳን ጋራ በሚዋሰነው የምዕራብ ጎንደር ዞን መተማወረዳ፣ ሽመት መገዱቃ በተባለ ቀበሌ፣ ባለፈው ሳ
የአሜሪካ ድምፅ

የመተማ አርሶ አደሮች «የሱዳን ታጣቂዎች አፈናቀሉን፤» አሉ

- «246 ባለሀብቶች ሥራ አቁመዋል» /የዞኑ አስተዳዳሪ/ ከሱዳን ጋራ በሚዋሰነው የምዕራብ ጎንደር ዞን መተማወረዳ፣ ሽመት መገዱቃ በተባለ ቀበሌ፣ ባለፈው ሳምንት በሱዳን መንግሥታዊ ታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት፣ የግብርና እንቅስቃሴያቸው እየተስተጓጎለባቸው እንደኾነ፣ በዘርፉ የተሠማሩ ባለሀብቶች እና የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታወቁ። በአካባቢው ላይ እየተፈጸመ በሚገኘው ተደጋጋሚ ጥቃት፣ በአንድ ዓመት ውስጥ በእርሻ ሥራ ላይየተሰማሩ 246 ባለሀብቶች ሥራቸውን እንዳቆሙ፣ የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቄ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ የጠየቃቸው የሱዳን ጦር ቃልአቀባይ ኮሎኔል ናቢልአብደላ፣ ትናንት ለብዙኀን መገናኛ መረጃ መስጠታቸውን አውስተው፣ ተጨማሪ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልኾኑ ገልጸዋል። ቃለ አቀባዩ የሰጡትን ምላሽ እንድንመለከት የጠቆሙን «ሱዳን ፕላስ» የተሰኘ የዜና አውታር፣ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ናቢል፤ የሱዳን ኃይሎች በድንበር አካባቢ መደበኛ ቅኝት እንደሚያደርጉ ፤ አልፎ አልፎ ግን ከኢትዮጵያ የሚሊሺያ ኃይሎች ጋራ ግጭት እንደሚያጋጥም መናገራቸውን ዘግቧል። /ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ/  

አብዛኛዎቹ የቶሌ ጥቃት ተጎጂዎች ከአንድ በላይ የቤተሰብ አባሎቻቸውን ማጣታቸውን ገለጹ

 - ምክር ቤቱ አጣሪ ቡድኖችን አሠማራ በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ በተባለ ቀበሌ ከተፈጸመው ትጥቃዊ ጥቃት የተረፉ ተፈናቃዮች፣ የቤተሰ
የአሜሪካ ድምፅ

አብዛኛዎቹ የቶሌ ጥቃት ተጎጂዎች ከአንድ በላይ የቤተሰብ አባሎቻቸውን ማጣታቸውን ገለጹ

 - ምክር ቤቱ አጣሪ ቡድኖችን አሠማራ በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ በተባለ ቀበሌ ከተፈጸመው ትጥቃዊ ጥቃት የተረፉ ተፈናቃዮች፣ የቤተሰብ አባሎቻቸው በጅምላ ጥቃት እንደተገደሉባቸው ገለጹ።  ቤተሰቦቻቸውን በግድያው እንደተነጠቁ የተናገሩትን ተፈናቃዮች በስልክ ያነጋገርናቸው ሲኾን፣ አብዛኛዎቹ ከአንድ በላይ እንዳጡ ይናገራሉ። ባለቤቷ እና የኹለት ዓመት ልጇ በጥቃቱ እንደተገደሉባት የገለጸችልን አንዲት እናት፣ በእቅፏ የነበረችን የኹለት ዓመት ልጇንም በግድያው ማጣቷን አስታውቃለች። አምስት የቤተሰባቸውን አባላት እንዳጡ የገለጹ ሌላ ግለሰብም፣ «በአጥፊዎች ላይ ርምጃ ይውሰድ፤» ሲሉ አሳስበዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ፣ ከምክር ቤት አባላት የተውጣጡ ኹለት ቡድኖችን በማቋቋም፣ በጋምቤላ ክልል እና በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ውስጥ፣ በንጹሐን ዜጎች ላይ የተፈጸሙ ግፎችን እንዲያጣሩ ስምሪት እንደሰጡ ታውቋል።  በሌላ በኩል፣ የምዕራብ ወለጋ ዞን ቡሳ ጎኖፋ፣ በጊምቢ ወረዳ ውስጥ ባለፈው ሳምንት በተፈጸመው ጥቃት የተጎዱ ሰዎችን በመርዳት ላይ እንደሚገኝ ጠቅሶ፣ ድጋፉ ግን በቂ እንዳልኾነ አስታውቋል። የዞኑ ጸጥታ እና አስተዳደር ጽ/ቤት በበኩሉ፣ «የጸጥታ ኃይሉ በአካባቢው ተሠማርቶ ጥበቃ እያደረገ ነው፤» ብሏል። ጥቃቱ እንዲፈጸም መረጃ በመስጠት ተባብረዋል በሚል የተጠረጠሩ በቁጥር ያልገለጻቸው ግለሰቦችም ተይዘው ምርመራ እየተካሔደባቸው እንደሚገኝ ጨምሮ አስታውቋል።  /ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/  

VOA60 World - U.S. Supreme Court overturns Roe v. Wade, landmark 1973 ruling legalizing abortion

VOA60 World - U.S. Supreme Court overturns Roe v. Wade, landmark 1973 ruling legalizing abortion
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - U.S. Supreme Court overturns Roe v. Wade, landmark 1973 ruling legalizing abortion

VOA60 World - U.S. Supreme Court overturns Roe v. Wade, landmark 1973 ruling legalizing abortion

ምግብን እንደጦር መሣሪያ መጠቀምን የሴኔቱ ኮሚቴ አወገዘ

ምግብን እንደ ጦር መሣሪያ የሚጠቀሙ ኃይሎችን ዩናይትድ ስቴትስ በተጠያቂነት እንድትይዝ የሚያሳስብ የውሣኔ ሃሳብ የህግ መወሰኛ ምክር ቤቷ የውጭ ጉዳዮች ኮሚ
የአሜሪካ ድምፅ

ምግብን እንደጦር መሣሪያ መጠቀምን የሴኔቱ ኮሚቴ አወገዘ

ምግብን እንደ ጦር መሣሪያ የሚጠቀሙ ኃይሎችን ዩናይትድ ስቴትስ በተጠያቂነት እንድትይዝ የሚያሳስብ የውሣኔ ሃሳብ የህግ መወሰኛ ምክር ቤቷ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አሳለፈ። ለምግብ ዋስትና መጥፋት ዋናው ምክንያት ግጭት መሆኑን የኮሚቴው አባላት ከመነሻቸው ጠቁመዋል። ኮሚቴው ትናንት ያሳለፈውን የሁለቱንም ፓርቲዎች ድጋፍ ያገኘው የውሣኔ ሃሳብ የተረቀቀውና የተመከረበት በሪፐብሊካኑ የአይዳሆ፣ የኦሬገን፣ የኢንዲያና የደቡብ ዳኮታ እንደራሴዎች ጂም ራይሽ፣ ጄፍ መርክሊ፣ ቶድ ያንግ እና ጃን ትዩን፤ እንዲሁም በዴሞክራቶቹ ኮሪ ቡከር እና ባብ ሜኔንዴዝ ነው። የሌሎች ባልደረቦቻቸውን ሃሳብ የተቀላቀሉት የኮሚቴው አጋር መሪ ሴናተር ራይሽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ “ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶሪያና የመን ውስጥ እየተዋጉ ያሉ ኃይሎች የግብርና ግብዓቶችና ውጤቶችንና መዋቅሮችን ሆን ብለው እንደሚያወድሙ፣ ገበያውን መረጋጋት እንደሚያሳጡ፣ በሰብዓዊ አቅርቦት ተቋማትና ሠራተኞች ላይ የፀጥታና የአሠራር መደናቅፎችን እንደሚደቅኑ” ተናግረዋል። “በዚህም በሲቪሎች ላይ ታልሞ የተቀነባበረ የረሃብ ቸነፈር ያደርሳሉ” ብለዋል ራይሽ። ሩሲያንም “በዓለም ላይ የበረታ ረሃብን በመዝራት ዘመቻ” ከስሰዋል። የሴኔቱ ኮሚቴ ያሳለፈው የውሣኔ ሃሳብ ረሃብን ሆን ብሎ እንደ ጦር መሣሪያ መጠቀምን አውግዞ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥትና አጋሮቿም የአድራጎቱን አቀናባሪዎች ፈጥነው በተጠያቂነት እንዲይዙ ጠይቋል። “የምግብ እርዳታ፤ አቅርቦቱ በብርቱ የሚያስፈልጋቸውን ሲቪሎች ለመጉዳት ጉዳይ አለመዋሉን ለማረጋገጥ ያሉንን መሣሪያዎች ሁሉ መጠቀም አለብን” ሴናተር ራይሽ ባሰፈሩት ሃሳባቸው። ሌሎቹም እንደራሴዎች ተደጋጋፊና ተመሳሳይ መልክዕክቶችን አስፍረዋል።

በኢትዮጵያ የምግብ እጥረት መባባሱንና የእርዳታ አቅርቦት መሟጠጡን ተ.መ.ድ አስታወቀ

በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ግጭት እና በደቡብ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው ድርቅ ምክንያት ከ20 ሚሊየን በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ የደረሰው የረሃ
የአሜሪካ ድምፅ

በኢትዮጵያ የምግብ እጥረት መባባሱንና የእርዳታ አቅርቦት መሟጠጡን ተ.መ.ድ አስታወቀ

በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ግጭት እና በደቡብ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው ድርቅ ምክንያት ከ20 ሚሊየን በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ የደረሰው የረሃብ አደጋ እየጠነከረ መሄዱን ያስታወቀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ አፋጣኝ እርዳታ ካልተገኘ ለእርዳታ የተዘጋጀው ምግብ በሚቀጥለው ወር ሊያልቅ እንደሚችል አስጠንቅቋል። የተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ተቋም ትላንት ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ለ19 ወራት የተካሄደው ግጭት በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የሚኖሩ 13 ሚሊየን ሰዎችን ሰብዓዊ ርዳታ ጠባቂ አድርጓቸዋል። በደቡብ እና በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ ደግሞ ለአራት ተከታታይ ወቅቶች ዝናብ ባለመዝነቡ ወደ 7.4 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በየእለቱ ከረሃብ ጋር ቀናቸውን ይጀምራሉ።  ግጭቱ እና ድርቁ ተዳምሮ የዋጋ ግሽበት እንዲባባስ ማድረጉንም የገለፀው የዓለም ምግብ ድርጅት፣ የምግብ ዋጋ ባለፈው አመት ሚያዚያ ወር ከነበረበት በ43 ከመቶ የጨመረ ሲሆን በተለይ የምግብ ዘይት ዋጋ 89 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል።  «በተለይ በዩክሬን እየተካሄደ ያለው ጦርነት በኢትዮጵያ የምግብ እጥረትን ሊያብብሰው ይችላል» ያለው የድርጅቱ ሪፖርት፣ የምግብ ተቋሙም ሆነ መንግስት ሶስት አራተኛ ስንዴ የሚያገኙት የነበረው ከዩክሬን እና ከራሽያ በመሆኑ የስንዴ እና የማዳበሪያ ዋጋ ገበሬዎች ከሚችሉት አቅም በላይ ሊሆን እንደሚችል፣ ይሄ ደግሞ የዚህ አመት ምርትን አደጋ ላይ እንደሚጥለው አስጠንቅቋል።    እስካሁን በትግራይ ክልል 800 ሺህ ሰዎች፣ እንዲሁም በአፋር እና አማራ ክልሎች 163 ሚሊየን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደተደረገላቸው የገለፀው የመንግስታቱ ድርጅት ተቋም፣ በሀገሪቱ ለሚገኙ 700 ሺህ ስደተኞች ይሰጥ የነበረውን የምግብ ርዳታ ግን በገንዘብ እጥረት ምክንያት ከግማሽ በላይ ማቋረጡን አስታውቋል። ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት በሀገሪቱ ሊመግባቸው የሚገባ 11 ሚሊየን ሰዎችን ለመድረስም 470 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ርዳታ እንደሚያስፈልገው ግለፆ ለእርዳታ ሰጪዎች ጥሪ አቅርቧል።  

የዩክሬን ኃይሎች ሲቪዬሮዳኔትስክን ለቀው ሊወጡ ነው

የዩክሬን ኃይሎች ከተከበበቸው የሲቪዬሮዳኔትስክ ለቀው እንደሚወጡ በክልሉ የዩክሬን ወታደራዊ አዛዥ አስታወቁ፡፡“በሩሲያ ኃይሎች ያለማቋረጥ በወራት የምት
የአሜሪካ ድምፅ

የዩክሬን ኃይሎች ሲቪዬሮዳኔትስክን ለቀው ሊወጡ ነው

የዩክሬን ኃይሎች ከተከበበቸው የሲቪዬሮዳኔትስክ ለቀው እንደሚወጡ በክልሉ የዩክሬን ወታደራዊ አዛዥ አስታወቁ፡፡“በሩሲያ ኃይሎች ያለማቋረጥ በወራት የምትደበደበውን ከተማ ይዞ መቆየቱ ትርጉም አይሰጥም” ብለዋል አዛዡ ጨምረው በሰጡት መግለጫ፡፡  በሌላም በኩል የአውሮፓ ፓርላማ በትናንት ሀሙስ ስብሰባው በጦርነት ውስጥ የምትገኘውን ዩክሬንን የአውሮፓ ህብረት አባል እጩነት እንድትሆን በሙሉ ድምጽ ተቀብሏል፡፡  ውሳኔው አራት ወራት የዘለቀውን የሩሲያን ወረራ በመመክት ላይ ለምትገኘው ዩክሬን፣ ግዙፍ የጦር መሳሪያዎችን በመደገፍ ላይ ወደሚገኘው የምዕራቡ ዓለም ለመቀላቀል የመጀመሪያው እምርጃ ነው ተብሏል፡፡  ፓርላማው የዩክሬንን እጩነት የተቀበለው 525 ለ45 በሆነ ልዩነትና በ14 የተአቅቦ ድምጽ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ውሳኔውን አስመልክተው ባስተላለፉት የትዊት መልዕክት “ይህ ወቅት በዩክሬን አውሮፓ ግንኙነት ልዩና ታሪካዊ ነው... የዩክሬን የወደፊት ተስፋ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ነው” ብለዋል፡፡ በሌላኛው የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ኢንስታግራም ላይ ባስተላለፉት መልዕክትም “የእጩነትን ደረጃ አሁን አግኝተናል፡፡ ይህ ድላችን ነው” ብለዋል፡፡ ዩክሬክን የህብረቱ አባል ሆና የመታጨቱ ዜና የተሰማው ዩናይትድ ስቴትስ፣ ከአንድ ሳምንት በፊት ይፋ ካደረገችው የአንድ ቢሊዮን ዶላሩ ድጋፍ ሌላ፣ አንዳንድ ተጨማሪ የመካከለኛ ርቀት ሮኬቶችን ጨምሮ፣ የ450ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ወታደራዊ ድጋፍ ለዩክሬን እየላከች መሆኑን ባስታወቀችበት ወቅት ነው፡፡ የዩክሬን ፓርላማ ሊቀመንበር ሩስላን ስቴፋንቸክ በፌስ ቡክ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት “ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባል አገር ነች፣ ለዚህ መብት ደግሞ በጦር ሜዳ ብቻ ሳይሆን በህጉም መድረክ እንፋለማን” በማለት የአውሮፓ ህብረት ህግ አውጭዎች ስለሰጡት ድጋፍ አመስግነዋል፡፡   ለአውሮፓ ህብረት የታጩ እነዚህ አገራት 27 አባላት ወዳሉት ህብረት ለመቀላቀል ጠንክራ የሆኑ የፖለቲካና የማህበራዊ ለውጦችን ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡ የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳን ኡርሱላ ቫን ደር ሌይን “ዩክሬን ከወዲሁ 70 ከመቶ የሚሆኑትን የአውሮፓ ህብረት ህግጋት፣ ሥርዐቶችና መስፈርቶችን አሟልታለች” ያሉ ሲሆን “ይሁን እንጂ የህግ የበላይነት፣ የአገዛዙን ከበርቴዎችና ጸረ ሙስናን እንዲሁም መሠራታዊ መብቶችን በሚመለከት ብዙ መሠራት ይኖርበታል” ብለዋል፡፡ የ27ቱንም የአውሮፓ ህብረት መንግሥታት መሪዎችን የሚያካትተው የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት በዩክሬን አባልነት ላይ የመጨረሻውን ድምጽ ይሰጣል፡፡ የሚሰጠው ድምጽ ሙሉ ሙሉ መሆን ይኖርበታል፡፡ ዲፕሎማቶች እንደሚሉት ሂደቱ አስርት ዓመታትን ሊፈጅ ይችላል፡፡ “ዩክሬናውያን የአውሮፓውያን ቤተሰብ ናቸው፡፡ የዩክሬናውያን የወደፊት ተስፋ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ነው” ያሉት የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል “ዛሬ አብረን የምንጓዘው ረጅሙ ጉዞ የተጀመረበት እለት ነው” ብለዋል፡፡ በብራስልስ የተሰበሰቡት የአውሮፓ ህብረት መሪዎች በዩክሬን ያለው ጦርነት፣ በዓለም የምግብ ደህንነት ላይ በሚያሳድረው ተጽእኖና፣ እንዲሁም በአውሮፓ ተጨማሪ የኢኮኖሚ፣ ወታደራዊና ሰብአዊ ድጋፍ ላይ መነጋገራቸው ተመልክቷል፡፡   በሌላም በኩል የዩክሬን ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን ዶናባስ ግዛት ከባድ የአየርና የመድፍ ድብደባዎችን ያካሄደች መሆኑን ገልጸው፣ ዓላማው “ቀስ በቀስ ጠቅላላውን ዶናባስ ለማውደም” ነው ብለዋል፡፡  የሩሲያውን ጥቃት ለመቋቋም የሳቸው ኃይሎች ተመጣጣኝ የጦር መሳሪያዎችን በአፋጣኝ እንዲያገኙም የዩክሬኑ መሪ ተናግረዋል፡፡

ቡርጅ የተፈፀመው ጥቃት በሽማግሌዎች እስኪፈታ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ተቋርጧል

ከሁለት ሳምንት በፊት በቡርጂ ልዩ ወረዳ ሶየማ ከተማ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የተፈጠረውን ውጥረት ለመፍታት የሀገር ሽማግ
የአሜሪካ ድምፅ

ቡርጅ የተፈፀመው ጥቃት በሽማግሌዎች እስኪፈታ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ተቋርጧል

ከሁለት ሳምንት በፊት በቡርጂ ልዩ ወረዳ ሶየማ ከተማ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የተፈጠረውን ውጥረት ለመፍታት የሀገር ሽማግሌዎች በጥረት ላይ መሆናቸው ተነግሯል። አባ ገዳ ጅሎ መንዶ ከአካባቢው ማኅበረሰብ የተውጣጡ የተለያዩ ሰዎችን ተቀብለው ማነጋገራቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የቡርጂ ልዩ ወረዳ አስተዳደር ጥቃቱን ተከትሎ ወስጃለው ባለው እርምጃ ከሰባ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ውሎ ለፍርድ እያቀረበ መሆኑን ቢገልፅም ነዋሪዎቹ ግን አሁንም በአካባቢው ውጥረት እንዳለ ይገልፃሉ። /ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ/  

VOA60 World - Aid agencies say they are struggling to meet the needs of Afghan earthquake survivors

VOA60 World - Aid agencies say they are struggling to meet the needs of Afghan earthquake survivors
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Aid agencies say they are struggling to meet the needs of Afghan earthquake survivors

VOA60 World - Aid agencies say they are struggling to meet the needs of Afghan earthquake survivors

ሳን ሱ ኪ ወደ ዋናው ከተማ እስር ቤት ተዛወሩ

ከሥልጣናቸው ተወግደው በእስር የሚገኙት የማያንማር መሪ ሳን ሱ ኪ ዛሬ ረቡዕ በአገሪቱ ዋና ከተማ ወደሚገኘው እስር ቤት መዛወራቸው ተነገረ፡፡ የተመሰረተባቸው
የአሜሪካ ድምፅ

ሳን ሱ ኪ ወደ ዋናው ከተማ እስር ቤት ተዛወሩ

ከሥልጣናቸው ተወግደው በእስር የሚገኙት የማያንማር መሪ ሳን ሱ ኪ ዛሬ ረቡዕ በአገሪቱ ዋና ከተማ ወደሚገኘው እስር ቤት መዛወራቸው ተነገረ፡፡ የተመሰረተባቸውን ክስ የሚያስችለውም ችሎት ከፍርድ ቤት ወደ እስር ቤት መዛወሩ ተመልክቷል፡፡ ሳን ሱ ኪ በወታደራዊ መንግሥት ተነስተው በቁጥጥር ስር ከዋሉበት እኤአ 2021 መጀመሪያ አንስቶ ቢያንስ ወደ 20 በሚጠጉ ወንጀሎች ተከሰዋል፡፡ ሳንሱኪ ሁሉንም አስተባበዋል፡፡ ምዕራባውያን አገሮች በአስችኳይ እንዲፈቱ የጠየቁ ሲሆን ወታደራዊ መንግሥቱ ጉዳያቸው በገለልተኛ ፍርድ ቤት እየታየ ነው ብሏል፡፡ በሌላም በኩል የማያንማር ወታደራዊ ገዥዎች በሚቀጥለው ዓመት ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ለማድረግ የገቡት ቃል “ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ የዋለ ሀሰተኛ መረጃ ነው፤ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዚህ ፕሮፖጋንዳ መታለል የለበትም” ሲሉ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ባለሙያ ተናግረዋል፡፡ በማይንማር የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ የተካኑት የመንግሥታቱ ድርጅት ባለሙያው ቶን አንድሩ ለአሶሼይትድ ፕሬስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የወታደራዊ መንግሥቱ የምርጫ ወሬ፣ የሳንሱ ኪን መንግሥትን በኃይል ከገለበጠ በኋላ ህጋዊነትን ለማግኘት የሚያደርገው ጥረት አካል ነው ብለዋል፡፡ ባለሙያው አያይዘው “ተቃዋሚዎችህን በሞት ችሎት አስቀምጠህ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ልታደርግ አትችልም” ማለታቸው ተዘግቧል፡፡ ወታደራዊ መንግሥቱ ሥልጣን ከያዘው ወዲህ እስካሁን ከ2007 በላይ ተቃዋሚዎችን መግደሉ ተመልክቷል፡፡

በምዕራብ ወለጋ ዞን የተፈፀመው የጅምላ ግድያ በአስቸኳይ እንዲጣራ ተመድ ጠየቀ

በምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ፈጣን፣ ገለልተኛ እና ጥንቃቄ የተሞላበት ምርመ
የአሜሪካ ድምፅ

በምዕራብ ወለጋ ዞን የተፈፀመው የጅምላ ግድያ በአስቸኳይ እንዲጣራ ተመድ ጠየቀ

በምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ፈጣን፣ ገለልተኛ እና ጥንቃቄ የተሞላበት ምርመራ እንዲያካሂድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሸሌት አሳሰቡ። ባሸሌት ዛሬ ባወጡት መግለጫ «ቶሌ በተሰኘው መንደር በደረሰ ጥቃት የተፈፀመው ትርጉም የማይሰጥ ግድያ እና ሰዎች በግዳጅ ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸው አሰቅቆኛል» ብለዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ የዓይን እማኞችን አነጋግሮ ባሰባሰበው መረጃ፣ ሰኔ አስራ አንድ ቀን ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት አካባቢ የታጠቁ ሰዎች፣ በአብዛኛው የአማራ ተወላጆች በሚኖሩበት ቶሌ መንደር በመሄድ በዘፈቀደ ባካሄዱት ተኩስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ፣ አብዛኞቹ ሴቶች እና ህፃናት ናቸው። በተጨማሪም ቢያንስ 2ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መኖሪያቸውን ጥለው ተሰደዋል። አራት ሰዓት በፈጀው በዚህ ጥቃት ታጣቂዎቹ በርካታ መኖሪያ ቤቶችንም አቃጥለዋል። ባሸሌት በመግለጫቸው «የኢትዮጵያ መንግሥት ጥቃቱን ለማጣራት ፈጣን እርምጃ በመውሰድ ጥቃት የደረሰባቸው እና ቤተሰቦቻቸው እውነቱን እንዲያውቁ ማድረግ፣ ፍትህ እና ካሳ ማግኘታቸውን እንዲሁም አጥፊዎቹ ተጠያቂ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለበት» ብለዋል። በተጨማሪም ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች በጥቃቱ ወቅት ታግተው መወሰዳቸውንና እስካሁን ያሉበት እንደማይታወቅ ያስታወቁት ከፍተኛ ኮሚሽነሯ «ባለሥልጣናት አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ የታገቱት ሰዎች ነፃነታቸውን እንዲያገኙ እንዲያደርጉ» ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች እየጨመረ የመጣውን ውጥረት እና ሁከት ትከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ህብረተሰቡ ለመኖር ያለውን መብት እንዲያረጋግጥ ሲሉ ከፍተኛ ኮሚሽነሯ ጨምረው አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ የስደተኞችን ደህንነት ለማስጠበቅ ምን እየሰራች ነው?

በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ ከ800 ሺ በላይ ስደተኞችን በግዛቷ በማስጠለል ፣ በብዛት ስደተኞችን ከአስተና
የአሜሪካ ድምፅ

ኢትዮጵያ የስደተኞችን ደህንነት ለማስጠበቅ ምን እየሰራች ነው?

በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ ከ800 ሺ በላይ ስደተኞችን በግዛቷ በማስጠለል ፣ በብዛት ስደተኞችን ከአስተናገዱ የአፍሪካ ሀገራት ሶስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሀገር ናት። ሀገሪቱ በቅርብ ጊዜያት በርስበርስ ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል። ።የጦርነቱ ጉዳት በዜጎቿ ላይ ብቻ ሳይሆን የተሻለ ህይወት ፈልገው በግዛቷ ለተጠለሉት ስደተኞችም መትረፉን የተለያዩ ሪፖርቶች ያሳያሉ ። የመጠለያ ጣቢያዎች ውድመት፣ የጭካኔ ተግባራት እና ሞት በስደተኞች ላይ ደርሰዋል ከተባሉት በደሎች መካከል ናቸው። የዓለም ስደተኞች ቀን በሚከበርበት ዕለት ኢትዮጵያ የስደተኞችን ደህንነት ለማስጠበቅ ምን እየሰራች ነው ስንል ጠይቀናል? ለዚህ እና ለሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች መልስ የሰጡን ደግሞ የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት የኮሚኒኬሽን እና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ በአካል ንጉሴ ናቸው። ያነጋገራቸው ሀብታሙ ስዩም ነው።(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡት።)

የሰማዕታት ዕለት በትግራይ

በትግራይ የሰማዕታት ዕለት ለ34ኛ ግዜ ዛሬ ታስቦ መዋሉን ክልሉን እያስተዳደሩ ያሉት ባለሥልጣናት ተናግረዋል። መቀሌ ላይ ዛሬ የወጣው መግለጫ ዕለቱ ከ34 ዓመት
የአሜሪካ ድምፅ

የሰማዕታት ዕለት በትግራይ

በትግራይ የሰማዕታት ዕለት ለ34ኛ ግዜ ዛሬ ታስቦ መዋሉን ክልሉን እያስተዳደሩ ያሉት ባለሥልጣናት ተናግረዋል። መቀሌ ላይ ዛሬ የወጣው መግለጫ ዕለቱ ከ34 ዓመት በፊት በዚሁ ዕለት ሃውዜን ገበያ ላይ በተፈፀመ የአየር ድብደባ የተገደሉ፣ የሃገሪቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም የነበሩትና ከሦስት ዓመት በፊት የተገደሉት ጄኔራል ሰዓረ መኮንና አብረዋቸው የተገደሉት ሜጄር ጄነራል ገዛኢ አበራ፣ እንዲሁም “ከአንድ ዓመት በፊት በዚሁ ዕለት በቶጎጋ ለገበያ በተሰበሰበ ህዝብ ላይ ተፈፅሟል” ሲል በጠቆመው የአየር ድብደባ ለተገደሉና “ባለፉት 47 ዓመታት ውስጥ ለትግራይ ህዝብ ሰብአዊ መብቶች መከበርና ሰላም መስዋዕት የከፈሉ የሚታሰቡበት መሆኑን አመልክቷል። ዕለቱ ሻማ በማብራት፣ የጥበብ ሥራዎችን በማቅረብና ውይይቶችን በማካሄድ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ታስቦ መዋሉን ሪፖርተራችን ሙሉጌታ አፅብሃ ከመቀሌ ዘግቧል።

ከምዕራብ ወለጋ ጥቃት የተረፉ አሁንም ሥጋት ውስጥ መሆናቸውን ገለፁ

በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የተፈናቀሉ ተጎጂዎች አሁንም ለደህንነታቸው እንደሚሰጉ እና በመንግሥት የሚወሰደው
የአሜሪካ ድምፅ

ከምዕራብ ወለጋ ጥቃት የተረፉ አሁንም ሥጋት ውስጥ መሆናቸውን ገለፁ

በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የተፈናቀሉ ተጎጂዎች አሁንም ለደህንነታቸው እንደሚሰጉ እና በመንግሥት የሚወሰደው እርምጃ አጥጋቢ እንዳልሆነ ገለፁ። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት የቅዳሜውን የጊምቢ ወረዳ ጥቃት ጨምሮ ሰሞኑን የተፈጸሙ ጥቃቶች መንግሥት “ሸኔ” በሚለው እና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ቡድን መፈጸማቸውን ገልጸው፣ ጥቃቱ በተፈጸመበት ሥፍራ በቡድኑ ላይ ጠንካራ እርምጃ እየተወሰደ ነው ብለዋል፡፡ የሰራዊቱ ቃል አቀባይ ግን ጥቃቱ የተፈጸመው በራሱ በመንግሥት ሚሊሺያዎች መሆኑንና ገለልተኛ ምርመራ እንዲካሄድ ጠይቀዋል። ኦነግ እና ኦፌኮ ዛሬ ባወጧቸው መግለጫዎች ጥቃቱን በተመለከተ በገለልተኛ አካል ምርመራ እንዲካሔድ ጠይቀዋል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ በንጹኃን ላይ የተፈጸመው የጅምላ ግድያ በጽኑ እንዳሳሰባት አስታውቃለች፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡት።  

ደቡብ ኮሪያ የራሷን መንኩራኩር ተጠቅማ ሳታላይት ወደ ሕዋ አመጠቀች

ደቡብ ኮሪያ አገር ውስጥ በተሰራ የጠፈር መንኮራኩር ተጠቅማ ሳተላይት ወደ ምህዋር ለማምጠቅ ያደረገችው ሁለተኛ ሙከራ መሳካቱን ባለሥልጣናት ዛሬ አስታወቁ። ይ
የአሜሪካ ድምፅ

ደቡብ ኮሪያ የራሷን መንኩራኩር ተጠቅማ ሳታላይት ወደ ሕዋ አመጠቀች

ደቡብ ኮሪያ አገር ውስጥ በተሰራ የጠፈር መንኮራኩር ተጠቅማ ሳተላይት ወደ ምህዋር ለማምጠቅ ያደረገችው ሁለተኛ ሙከራ መሳካቱን ባለሥልጣናት ዛሬ አስታወቁ። ይህም ደቡብ ኮሪያ በጠፈር እንቅስቃሴው ራሷን የቻለች አገር ለመሆን ለአላት ትልቅ እቅድ ቁልፍ እርምጃ ተደርጎ ታይቷል። «ኑሪ» የተሰኘው ባለ ሦስት እርከን መንኩራኩር በደቡብ ምዕራብ ጎሄንግ ጠረፍ አካባቢ ካለች ትንሽ ደሴት ከሚገኘው የጠፈር ማዕከሏ ከመጠቀ በኋላ በርካታ ሳተላይቶችን ወደ ምህዋር አሰማርታለች” ሲሉ የጠፈር ሚኒስትሯ ሊ ጆንግ ሆ አረጋግጠዋል። ያሁኑ የስኬት ዜና የተሰማው የ”ኑሪ” የመጀመሪያ ሙከራ ካሁን ቀደም ከተሰናከለበት ድንገት ስምንት ወራት በኋላ ነው። ከዛሬው የተሳካ ሙከራዋ በኋላ ደቡብ ኮሪያ መንኩራኩር ወደ ህዋ በማምጠቅ አስረኛዋ ሃገር ሆናለች። ይህ ችሎታ እና ልምድ የመንኩራኩር ማምጠቂያ መሳሪያዎች እና የቦለስቲክ ሚሳዮሎች በርካታ የሚጋሯቸው ገፅታዎች ስላሏቸው ጦር መሳሪያ ለመስራትም ያግዛል።

ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ውስጥ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ

ባለፈው ቅዳሜ በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር በመጨመር ላይ መሆኑን፣ ከጥቃቱ የተረፉ የአካባቢው ነዋሪዎ
የአሜሪካ ድምፅ

ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ውስጥ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ

ባለፈው ቅዳሜ በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር በመጨመር ላይ መሆኑን፣ ከጥቃቱ የተረፉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ የተለያዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ጥቃቱን በማውገዝ ባወጧቸው መግለጫዎች፣ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በተካሔደ 6 ቢሊዮን ችግኝ የመትከል ዘመቻ ማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ መከላከያ ሰራዊት ከትናንት ጀምሮ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገልጸው መላው ኅብረተሰብም እንዲተባበር ጠይቀዋል፡፡ /ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/

በጋምቤላ ከተማ የተፈፀመው ጥቃት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ኦፌኮ ጠየቀ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ በቅርቡ በጋምቤላ ከተማ በንጹሃን ዜጎችላይ ተፈፀመ ያለው ጥቃት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቋል
የአሜሪካ ድምፅ

በጋምቤላ ከተማ የተፈፀመው ጥቃት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ኦፌኮ ጠየቀ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ በቅርቡ በጋምቤላ ከተማ በንጹሃን ዜጎችላይ ተፈፀመ ያለው ጥቃት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቋል። በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን እየተዘዋወረ ያለው በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እንደተፈፀመ የሚያሳየው ግድያ እንዲጣራ እና ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ አሳስቧል። የጋምቤላ ክልል መንግሥት ክልሉን ከታጣቂዎች ለመከላከል ተካሄደ ባሉት ጦርነት መሰል የተኩስ ልውውጥ 17 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የጋምቤላን ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ የፀጥታ ኃይሎች ሕይወት ሊያጠፋ ከሚችል ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡና በተወሰዱ እርምጃዎች ላይ ማጣራት እንዲያደረግ ጥሪ አቅርቧል። በሌላ በኩል በነቀምቴ ከተማ ባለፈው ሳምንት ውስጥ አንድ ወጣት በጸጥታ ኃይሎች መገደሉን ከሟች ቤተሰቦች መካከል ገልጸዋል። በዚህ ዙሪያ ከከተማውም ሆነ ኦሮምያ ክልል ባለሥልጣናት ለማጣራት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። /ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/

ጋምቤላ ከተማ የክልል ጸጥታ ኃይሎች ሲቪሎችን ገድለዋል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

የክልሉ ልዩ ኃይሎችና መደበኛ የፖሊስ አባላት «ኦነግ ሸኔ» ናችሁ በሚል ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል ሲሉ ተናገሩ። የክልሉ መንግሥት ሰኔ 7/2014 ዓ.ም በመንግሥ
የአሜሪካ ድምፅ

ጋምቤላ ከተማ የክልል ጸጥታ ኃይሎች ሲቪሎችን ገድለዋል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

የክልሉ ልዩ ኃይሎችና መደበኛ የፖሊስ አባላት «ኦነግ ሸኔ» ናችሁ በሚል ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል ሲሉ ተናገሩ። የክልሉ መንግሥት ሰኔ 7/2014 ዓ.ም በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎችና ሸማቂዎች መካከል በተደረገው የተኩስ ልውውጥ በሸማቂዎቹ ላይ እርምጃ መወሰዱን በመግለጽ በግጭቱ መካከል የተለያየ ብሔር ተወላጅ የሆኑ 17 ሲቪሎች መገደላቸውን ጨምሮ አስታውቋል። በክልሉ መደበኛ ሥራና ከአዲስ አበባ ወደ ጋምቤላ የሚደረገው የአየር በረራ መጀመሩን የገለፁት የክልሉ ኮሙኒኬሽንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡጌቱ አዲንግ አካባቢው መረጋጋቱን ተናግረዋል። /ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/

የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሚገባቸው መጠን ድጋፍ እንደማያገኙ ተገለፀ

የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሚገባቸው መጠን ድጋፍ እንዳያገኙ የሚያደናቅፉ በርካታ የግብአት ውስንነቶች መኖራቸውን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኛች ድርጅት (አይኦኤ
የአሜሪካ ድምፅ

የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሚገባቸው መጠን ድጋፍ እንደማያገኙ ተገለፀ

የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሚገባቸው መጠን ድጋፍ እንዳያገኙ የሚያደናቅፉ በርካታ የግብአት ውስንነቶች መኖራቸውን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኛች ድርጅት (አይኦኤም) አስታውቋል። በኢትዮጵያ የድርጅቱ የአስቸኳይ ጊዜና የቀውስ ማግስት ፕሮግራም አስተባባሪ ኤስቴር ሩይስደ አስዋ እንዳሉት ከተፈናቃዮች ከሚደርሷቸው የአቅርቦት ጥያቄዎች 42 በመቶው ምላሽ አያገኙም። በኢትዮጵያ ካሉት 4.5 ሚሊዮን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች 81 ከመቶዎቹ የተፈናቀሉት በግጭት ምክንያት መሆኑንም ጠቁመዋል። /አስተባባሪዋን በአዲስ አበባ ያነጋገራቸው የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ እስክንድር ፍሬው ነው። ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።/

የእንግሊዝ የባቡር ትራንስፖርት ሠራተኞች ዛሬ የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ

የብሪታንያ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ሠራተኞች በአስርት ዓመታት ውስጥ ያልታየ ነው የተባለ ግዙፍ የሥራ ማቆም አድማ ዛሬ ጀመሩ። የድርጅቱ ሥራ አመራር
የአሜሪካ ድምፅ

የእንግሊዝ የባቡር ትራንስፖርት ሠራተኞች ዛሬ የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ

የብሪታንያ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ሠራተኞች በአስርት ዓመታት ውስጥ ያልታየ ነው የተባለ ግዙፍ የሥራ ማቆም አድማ ዛሬ ጀመሩ። የድርጅቱ ሥራ አመራር እና የባቡር፣ የባህር እና የመንገድ ትራንስፖርት ሰራተኞች ማህበር በሠራተኞች የደሞዝ ክፍያ መጠን እና ከሥራ ዋስትና ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት እና የሥራ ማቆም አድማውን ለማስቀረት በታለመ ጥረት ትናንት ሰኞ ያደረጉት የመጨረሻ ደቂቃ ውይይት ሳይሰምር ቀርቷል። እንደ ሠራተኛ ማኅበራት መሪዎቹ ገለጣም የሠራተኞች ደሞዝ የዋጋ ከተፈጠረው የዋጋ ግሽበት ጋር ሊሄድ አልቻለም። የብሪታንያው የትራንስፖርት ሚኒስትር ግራንት ሻፕስ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት “አድማው መጠነ ሰፊ ማስተጓጎል ይፈጥራል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ከ40ሺህ በላይ አባላት ያሉት አንድ ሌላ የሠራተኛ ማኅበር የፊታችን ሃሙስ እና ቅዳሜ ተመሳሳይ የሥራ ማቆም አድማ ለማድረግ ማቀዱ ታውቋል።

በታይዋን ጉዳይ የዩናይትድ ስቴትስ እና የቻይና ጦርነት ገጽታዎችን የገመገመ አዲስ መጽሃፍ

ዋናው መቀመጫውን በዋሽንግተን ያደረገ አንድ ታዋቂ የፖሊሲ ጥናት ተቋም እንዳለው ቻይና ታይዋንን ከወረረች በሚል “የተሳሳሳተ ስሌት” ዩናይትድ ስቴትስ ሊቀሰ
የአሜሪካ ድምፅ

በታይዋን ጉዳይ የዩናይትድ ስቴትስ እና የቻይና ጦርነት ገጽታዎችን የገመገመ አዲስ መጽሃፍ

ዋናው መቀመጫውን በዋሽንግተን ያደረገ አንድ ታዋቂ የፖሊሲ ጥናት ተቋም እንዳለው ቻይና ታይዋንን ከወረረች በሚል “የተሳሳሳተ ስሌት” ዩናይትድ ስቴትስ ሊቀሰቀስ ለሚችል ግጭት እየተዘጋጀች ነው ብሏል። የአሜሪካ ኢንተርፕራይዝ ኢንስቲትዩት የተባለው ይህ የጥናት ተቋም “ለታይዋን መከታ ማበጀት” በሚል ርዕስ ለንባብ ባበቃው አዲስ መጽሃፍ ዋሽንግተን፣ ቻይና በታይዋን ላይ ወረራ የፈጸመች እንደሁ ሊቀሰቀስ የሚችለውን ጦርነት አጭር እና በዚያው ተገድቦ የሚካሄድ አድርጎ የማየት የሚል የተሳሳተ ትንበያ ነው የያዘችው ሲል ይከራከራል። የተቋሙ አጥኝዎች እንደሚሉት ግን የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር የፔንታጎን እቅድ “ረጅም ጊዜ ሊዘልቅ በሚችል ግጭት ዙሪያ የሚያተኩር መሆን አለበት።” የአሜሪካ ኢንተርፕራይዝ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የጥናት ባለሞያዎች ሃል ብራንድስ እና ማይክል ቤክሊ እንደተናገሩት ሊደርሱ ከሚችሉት እና እንደ አሳሳቢነት ከሚታዩ ሁኔታዎች በአንዱ ቤጂንግ የታይዋንን መከላከያ በሚሳይል መደብደብ ብቻ ሳይሆን፤ በምዕራብ ፓስፊክ ከሚገኙ ጥቂት ነገር ግን ግዙፍ የሆኑ የጦር ሰፈሮች የዩናይትድ ስቴትስ የባህር እና የአየር ኃይሎችም ኢላማ ሊሆኑ ይችላሉ። አክለውም በምዕራባዊ ፓስፊክ ሊቀሰቀስ የሚችል የዩናይትድ ስቴትስ እና ቻይና ግጭት ፈጥኖ አይበርድም ብለዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ስታራምድ የቆየችው ፖሊሲ በታይዋን የባህር ወሽመጥ ወታደራዊ ግጭት እንዳይቀሰቀስ በብቃት ያስቀረች ሲሆን በአንጻሩ ጥቃት ቢቀሰቀስ ለሚያስፈልገው ስትዘጋጅ ቆይታለች። የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ቤጂንግ ታይዋንን አስመልክቶ እያሳየች ያለችው፣ «እያደረ እየጨመረ የመጣው ጠብ ቀስቃሽ ንግግር እና እንቅስቃሴ» ከፍተኛ ሥጋት እንዳሳደረባቸው አመልክተዋል። ካሁን ቀደም ሲቪል መሪዎች የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ሰራዊት ታይዋንን ከቻይና ጥቃት መከላከል የሚያስችል አዋጭ እቅዶች እንዲነድፉ ለጦር ባለሥልጣናት መመሪያ መስጠታቸውን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር የውስጥ ሰነድ አመልክቷል። በቅርቡ፣ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ከፍተኛ ባለሥልጣናት በቤጂንግ ያለውን ሁኔታ ለመለወጥ የምትወስደውን የኃይል እርምጃ ደጋግመው አስጠንቅቀዋል።

ሩሲያዊው ጋዜጠኛ ለጨረታ ያቀረበው የኖቤል ሽልማት ሜዳይ 103.5 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ

ከሩሲያ የመጨረሻዎቹ ነፃ ጋዜጦች የአንዱ ዋና አዘጋጅ የነበረው ዲሚትሪ ሙራቶቭ እአአ በ2021 የተቀበለው የኖቤል የሰላም ሽልማት አካል የሆነውን ሜዳይ በጦርነቱ
የአሜሪካ ድምፅ

ሩሲያዊው ጋዜጠኛ ለጨረታ ያቀረበው የኖቤል ሽልማት ሜዳይ 103.5 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ

ከሩሲያ የመጨረሻዎቹ ነፃ ጋዜጦች የአንዱ ዋና አዘጋጅ የነበረው ዲሚትሪ ሙራቶቭ እአአ በ2021 የተቀበለው የኖቤል የሰላም ሽልማት አካል የሆነውን ሜዳይ በጦርነቱ ሳቢያ ከቀያቸው የተፈናቀሉትን የዩክሬን ህፃናት ለመርዳት በያዘው ዕቅድ መሰረት ጨረታ ላይ ካዋለው በኋላ ነው ሪከርድ የሰበረ በተባለ ዋጋ በ103 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር የተሸጠው። ጨረታውን ያዘጋጀው ‘Heritage Auctions’ አስተባባሪዎች የጨረታውን አሸናፊ ማንነት ይፋ አላደረጉም። ዕለቱ ትናንት ከታሰበው የስደተኞች ቀን ጋር ተገጣጥሟል። ከጨረታው ሽያጭ የተገኘው ገንዘብ ተፈናቃዩን የዩክሬን ህፃናት  ለመርዳት ጥረት እያደረገ ላለው በተባበሩት መንግሥታት የዓለም ህፃናት መርጃ ድርጅት/ዩኒሴፍ/ እንደሚሰጥ ተገልጧል። ሙራቶቭ እና ፊሊፒናዊቱ ጋዜጠኛ ማሪያ ረሳ በየሃገሮቻቸው የንግግር ነፃነት እንዲከበር ላደረጉት ጥረት የ2021ዱ የኖቤል የሰላም ሽልማት የጋራ ተሸላሚዎች መሆናቸው ይታወሳል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2014 በተመሳሳይ ለጨረታ የዋለ የኖቤል ሽልማት ሜዳይ 4.76 ሚሊዮን ዶላር ነበር የተሸጠው። ሙራቶቭ ትናንት ጨረታው ከተጠናቀቀ በኋላ በሰጠው አስተያየት “ከፍ ያለ የትብብር መንፈስ ይንጸባረቅ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጌ ነበር፤ ሆኖም ግን ይህን ያህል እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ አልተበቅኩም ነበር” ብሏል።

የፓናማው ፕሬዚዳንት የደም በሽታ

የፓናማ ፕሬዚዳንት ላውረንቲኖ ኮርቲዞ ያልተለመደ ዓይነት የደም በሽታ እንዳለባቸው ትናንት ሰኞ አስታወቁ። የ69 ዓመቱ ኮርቲዞ በሰጡት መግለጫ «የአሳሳቢነ
የአሜሪካ ድምፅ

የፓናማው ፕሬዚዳንት የደም በሽታ

የፓናማ ፕሬዚዳንት ላውረንቲኖ ኮርቲዞ ያልተለመደ ዓይነት የደም በሽታ እንዳለባቸው ትናንት ሰኞ አስታወቁ። የ69 ዓመቱ ኮርቲዞ በሰጡት መግለጫ «የአሳሳቢነት ደረጃው መካከለኛ» የሚባል ማይሎ-ዲስ-ፕላስቲክ ሲንድረም እንዳለባቸው የታወቀው ባለፈው የግንቦት ወር መደበኛ የጤና ምርመራ ባደረጉበት ወቅት የሂሞግሎቢን እና የነጭ የደም ሴል ቆጠራ መቀነስ አሳይቷል። ማይሎዳይስፕላስቲክ ሲንድረም በአጥንት መቅኒ ውስጥ ደም የሚፈጥሩ ሕዋሳት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። የአሜሪካ የካንሰር ማኅበር ማይሎዳይስፕላስቲክ ከካንሰር ህመሞች አንዱ አድርጎ ይወስደዋል። በዘገባው እንደተጠቆመው ኮርቲዞ እአአ ሃምሌ 1 ለአገራቸው ብሄራዊ ምክር ቤት ዓመታዊ ንግግራቸውን ካሰሙ በኋላ ተጨማሪ የልዩ ባለ ሞያ አስተያየት ለማግኘት ባለሙያተኛ ሁለተኛ አስተያየት ወደ ሂዩስተን፣ ቴክሳስ ያቀናሉ።

ግብርናን ለማዘመን ስላለመው «ለእርሻ » አገልግሎት ጥቂት ነገሮች

ከህዝቧ መካከል አብዛኛው በግብርና መስክ በተሰማራባት ኢትዮጵያ ፣ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን ያለሙ የተለያዩ አገልግሎቶች እየተበራከቱ ይገኛሉ። «ለእ
የአሜሪካ ድምፅ

ግብርናን ለማዘመን ስላለመው «ለእርሻ » አገልግሎት ጥቂት ነገሮች

ከህዝቧ መካከል አብዛኛው በግብርና መስክ በተሰማራባት ኢትዮጵያ ፣ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን ያለሙ የተለያዩ አገልግሎቶች እየተበራከቱ ይገኛሉ። «ለእርሻ» የተሰኘው በግሪን አግሮ ሶሉሽን ተቋም የተገነባው አገልግሎት አንዱ ነው። ገበሬዎች ለእርሻ የሚፈልጓቸውን ግብዓቶችን የሚያዝዙበት፣ ሙያዊ ምክር የሚያገኙበት አገልግሎት ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት እና አንጋፋ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እያደረገ ስለመሆኑ ስለ ተነገረለት አገልግሎት የበለጠ ለማወቅ ሀብታሙ ስዩም ፣የተቋሙን ኃላፊ አቶ አብርሃም እንድሪያስን በስልክ መስመር አግኝቷቸዋል። አገልግሎቱን ለመጀመር ያበቁ ምክንያቶችን ቀድሞ ያስረዳሉ።

በኦሮሚያ ክልል በተፈፀመ ጥቃት በትንሹ 260 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ቁጥራቸው የበዛ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ከጥቃቱ አመለጥን
የአሜሪካ ድምፅ

በኦሮሚያ ክልል በተፈፀመ ጥቃት በትንሹ 260 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ቁጥራቸው የበዛ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ከጥቃቱ አመለጥን ያሉ የዐይን እማኞች እና የሟቾቹ ቤተሰቦች ተናገሩ። ነዋሪዎቹ ጥቃቱ የደረሰባቸው “አማራ” በመሆናቸው ብቻ መሆኑን ገልፀው በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር የተለያየ መሆኑን ይናገራሉ። ማምሻውን በዚህ ጉዳይ ላይ ዘገባ ያወጣው ሮይተር የዜና ወኪል ነዋሪዎቹ ጠቅሶ የሟቾች ቁጥር 260 መሆኑን አስነብቧል።

በኢትዮጵያ በሺሆች የሚቆጠሩ ስደተኞች በግጭት ምክንያት አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል

በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞችን ከሚያስጠልሉ ሀገራት አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ ከአንድ ዓመት በላይ ለሚሆን ግዜ በዘለቁ ግጭቶች ምክንያት በትግራይ
የአሜሪካ ድምፅ

በኢትዮጵያ በሺሆች የሚቆጠሩ ስደተኞች በግጭት ምክንያት አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል

በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞችን ከሚያስጠልሉ ሀገራት አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ ከአንድ ዓመት በላይ ለሚሆን ግዜ በዘለቁ ግጭቶች ምክንያት በትግራይ፣ በአፋር እና ቤኒሻንጉል ክልሎች ተጠልለው የነበሩ ኤርትራዊ፣ ደቡብ ሱዳናዊ እና ሱዳናዊ ስደተኞች ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ማማዱ ባልዴ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል። በከተማ የሚገኙ ስደተኞች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ 70 ሺህ መድረሱን የገለፁት ዶክተር ባልዴ ተቋሙ ስደተኞችን እና የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ለመርዳት ከጠየቀው የገንዘብ ድጋፍ 19 ከመቶውን ብቻ ማግኘቱ የሰብዓዊ ርዳታ ጥረቱን አዳጋች እንዳደረገውም አስረድተዋል። /ሙሉ ዘገባውን ከተያይዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/

Get more results via ClueGoal