ፑቲን ኪየቭን በአዲስ እጅግ ፈጣን ተውዘግዛጊ ሚሳኤል እንደሚመቱ አስፈራሩ
newsare.net
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ዋና ከተማ፣ ኪየቭ የሚገኙትን “የውሳኔ መሰጫ ማዕከላት” ኦርሸኒክ በተሰኙ፣ ከድምፅ የፈጠኑ የሩሲያ ተውዘግዛፑቲን ኪየቭን በአዲስ እጅግ ፈጣን ተውዘግዛጊ ሚሳኤል እንደሚመቱ አስፈራሩ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ዋና ከተማ፣ ኪየቭ የሚገኙትን “የውሳኔ መሰጫ ማዕከላት” ኦርሸኒክ በተሰኙ፣ ከድምፅ የፈጠኑ የሩሲያ ተውዘግዛጊ ሚሳኤሎች እንደሚመቱ ትላንት ዝተዋል። ፑቲን ይህን የተናገሩት በዩክሬን የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት በማድረስ በመላ አገሪቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ለሚኾኑ ሰዎች ኃይል ካቋረጡ በኋላ ነው፡፡ ፑቲን በካዛክ መዲና፣ አስታና ከተማ ትራንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ኦርሽኒክን በሠራዊቱ፣ በወታደራዊ ተቋማት ወይም ኪየቭ የሚገኙትን ጨምሮ በውሳኔ ሰጪ ማዕከላት ላይ ከመጠቀም ወደ ኃላ እንደማይሉ መናገራቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። ሐሙስ እለት በዩክሬን በኃይል አመንጪ መሠረተ ልማቶች ላይ በሰው አልባ አውሮፕላንና በሚሳኤል ጥቃት ያደረሱትም፣ ዩክሬን የዩናይትድ ስቴስን መካከለኛ ርቀት ተተኳሽ ሚሳኤልን ተጠቅማ፣ በሩስያ ላይ ላደረሰችው ጥቃት ምላሽ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህ ጥቃት በዚህ ወር ውስጥ በኃይል መሠረተ ልማት ላይ የደረሰ ሁለተኛው ጥቃት ሲሆን ከመጋቢት ወር ወዲህ ደግሞ አስራ አንደኛው መሆኑን ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው፣ ሞስኮ ተውዘግዛጊ ሚሳኤሎችን እና በአንድ ጊዜ በርካታ ፈንጂዎችን በአየር ላይ የሚጥሉ መሳሪያዎችን በመጠቀም ጦርነቱን «ወደ ከፋ መባባስ» አስገብተውታል ሲሉ ከሰዋል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፑቲን በኪየቭ የመንግስት ማዕከላት ላይ ላነጣጠረ ዛቻቸው ምላሽ እንዲሰጥም፣ ዩክሬን በውጭ ጉዳይ መስሪያቤቷ በኩል ጠይቃለች፡፡ በጥቃቱ ምክንያት የኤለክትሪክ ሃይል ካጡ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ነባሩ የመብራት መቆራረጥ ተባብሶባቸዋል፡፡ ሩሲያ በጥቃቱ 91 ሚሳኤሎችን እና 97 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መጠቀሟን የዩክሬን አየር ሃይል ያስታወቀ ሲሆን ዒላማቸውን ከመቱ አስራ ሁለት ጥቃቶች መካከል አብዛኞቹ በኃይል ተቋማት እና በነዳጅ ማከማቻዎች ላይ ማረፋቸውን፣ እንዲሁም በውሃ አገልግሎት ላይም ተጽዕኖ ማድረሱን ገልጿል፡፡