ብሪታኒያ እና ዩክሬን «ለመቶ ዓመት የሚዘልቅ አጋርነት» ስምምነት
newsare.net
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር የሀገራቸውን እና የዩክሬንን ግንኙነት የሚያጠናክር የ«100 ዓመት ስምምነት» ለመፈራረም ዛሬ ሀሙስ ኪቭ ገብተዋብሪታኒያ እና ዩክሬን «ለመቶ ዓመት የሚዘልቅ አጋርነት» ስምምነት
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር የሀገራቸውን እና የዩክሬንን ግንኙነት የሚያጠናክር የ«100 ዓመት ስምምነት» ለመፈራረም ዛሬ ሀሙስ ኪቭ ገብተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደኪቭ የተጓዙት ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ወደ ዋይት ሀውስ ከመመለሳቸው በፊት የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት እና የጦር ሜዳ ውጥረቶች እያየሉ በመጡበት በዚህ ወቅት ነው፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ወቅት በኪቭ ከፍተኛ ፍንዳታ እና የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደወል ሲጮኽ ተሰምቷል፡፡ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ውስጥ ስልጣን የያዙት ስታርመር ወደዩክሬን ሲጓዙ ይህ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ሲሆን የተጓዙትም የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ትረምፕ በሚቀጥለው ሳምንት አስተዳደራቸውን ከመጀመራቸው በፊት ከዩክሬን አእጋሮች ጋራ በተከታታይ እየተነጋገሩ ባሉበት በዚህ ወቅት መሆኑ ነው፡፡ ስምምነቱ የመከላከያ፣ የጦር ሜዳ ቴክኖሎጂ እና ወደ ውጭ በሚላከው እህል ክትትል ላይ ያተኩራል። ስታርመር ለዩክሬን መልሶ ማቋቋሚያ የ40 ሚሊዮን ፓውንድ ርዳታ ይፋ አድርገዋል። ብሪታኒያ እኤአ ከ 2022 ጀምሮ ለዩክሬን የ12.8 ቢሊዮን ፓውንድ ርዳታ ሰጥታለች። ዘገባው የኤኤፍፒ ነው፡፡