Ethiopia



በኬንያ እና በዩጋንዳ ለታቀደው ከሶማሊያ ጋራ የማሸማገል ርምጃ ኢትዮጵያ አዎንታዊ ምላሽ ሰጠች

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው፣ ዛሬ ኅዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የኬንያን እ
የአሜሪካ ድምፅ

በኬንያ እና በዩጋንዳ ለታቀደው ከሶማሊያ ጋራ የማሸማገል ርምጃ ኢትዮጵያ አዎንታዊ ምላሽ ሰጠች

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው፣ ዛሬ ኅዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የኬንያን እና የዩጋንዳን የሽምግልና እቅድ በተመለከተ ከጋዜጠኞች ተጠይቀው በሰጡኢት ከሶማሊያ ጋራ ለሚደረግ ድርድር ኢትዮጵያ ዝግጁ መኾኗን አስታውቀዋል። የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ “የቀጣናውን መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥል” ያሉትን በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ከዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋራ ጥረት እንደሚያደርጉ ቅዳሜ ዕለት ተናግረዋል። ለዚህ የጥረት ዕቅድ የኢትዮጵያ ምላሽ ምን እንደኾነ የተጠየቁት አምባሳደር ነቢያት፣ ኢትዮጵያ ችግሩን ለመፍታት ለሚደረጉ ድርድሮች ዝግጁ እንደኾነች ገልፀዋል፡፡ “ኢትዮጵያ ከመጀመሪያውም ጀምሮ ማናቸውም ዐይነት ልዩነቶች በውይይት እና በሰላም ድርድር እንደሚፈቱ ፅኑ እምነቷ ነው” ያሉት ቃል አቀባዩ፣ “ለዚህም ነው በተለያዩ መድረኮች ላይ ቀርባ አቋሟን በማስረዳት፣ ዘላቂ ለሆነ፣ ሁለቱንም ሀገራት ሊያስማማ ወደሚችል አቅጣጫ ለመሄድ አጋዥ ሚና ስትጫወት የቆየችው” ሲሉ አክለዋል፡፡ “ስለዚህ ኢትዮጵያ ከሰላም መድረኮች የሸሸችበት አጋጣሚ የለም” በማለትም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም “የተለያዩ የሰላም ሂደቶች ተነስተዋል፣ የአንካራው ተነስቷል፣ አሁንም ፖቴንሺያሊ ሊነሱ የሚችሉ አሉ” ብለዋል፡፡  የሶማሊያ መንግሥት በኬንያ እና ኡጋንዳ የሽምግልና ጉዳይ ላይ ስላለው አቋም በይፋ የገለፀው ነገር የለም፡፡ የኬንያው ፕሬዝደንት፣ ከኡጋንዳው አቻቸው ጋራ ኢትዮጵያን እና ሶማሊያን ለማሸማገል እንደሚጥሩ የተናገሩት፣ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ 24ኛ መደበኛ የመሪዎች ጉባኤውን ባካሄደበት ታንዛኒያ፣ አሩሻ ላይ  ባደረጉት ንግግር ነው። የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት በወቅቱ ባወጣው መግለጫ፣ ፕሬዝደንት መሀሙድ፣ ሩቶ እና ሙሴቬኒ በጉባዔው ላይ ተገናኝተው መነጋገራቸውን ቢገልፅም ከኢትዮጵያ ጋራ ስላለው ውጥረት ሽምግልና ሊኖር እንደሚችል ግን አልጠቀሰም። የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ ሞአሊም ፊቂ፣ ከዚህ ቀደም ለተደረጉ ሽምግልናዎች አለመሳካት ኢትዮጵያን ተጠያቂ ማድረጋቸውን የገለፀው ሮይተርስ፣ ስለቀጣይ የሽምግልና ጥረቶች ያሉት ነገር ስለመኖሩ ግን በዘገባው አላካተተም፡፡ ኢትዮጵያ፣ ራሷን ነጻ አገር አድርጋ ከምትቆጥረው ከተገንጣይዋ ሶማሊላንድ ጋራ በተፈራረመችው አወዛጋቢ የባሕር በር የመግባቢያ ሰምምነት ምክንያት በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ከዚህ ቀደም የተደረጉ ጥረቶች ተጨባጭ ውጤት አላስገኙም፡፡ ቱርክ ፣ ችግሩን ለመፍታት በሐምሌ እና ነሐሴ ወራት ሁለት ስብሰባዎችን በአንካራ ላይ አመቻችታ የነበረ ሲኾን፣ የሁለቱ አገራት ልዑካን ፊት ለፊት ሳይገናኙ በተናጥል ባደረጉት ውይይት መግባባት አልቻሉም፡፡ የሶማሊያ ባለሥልጣናት፣ የመግባቢያ ሰነዱ እስካልተሰረዘ ድረስ ከኢትዮጵያ ጋር ምንም አይነት ቀጥተኛ ንግግር እንደማይኖር አጽንኦት ሲሰጡ ሰንብተዋል። ከዚህም ባለፈ፣ ኢትዮጵያ በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ውስጥ እንደማትሳተፍ ሶማሊያ አቋም ይዛለች፡፡ ይህን ተከትሎ፣ ነባሩ የአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ ተልዕኮ ስምሪት ሲያበቃ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ለቆ ሊወጣ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡ በዛሬው መግለጫ ላይ ስለዚህ ጉዳይ የተጠየቁት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነቢያት ጌታቸው፣ ስለጦሩ መውጣት አስተያየት ባይሰጡም የፀረ አልሻባብ ውጊያው ግን እንደሚቀጥል በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡ ቃል አቀባዩ “ከሶማሌ አካባቢ …በርካታ ተንኳሽ እና ኃላፊነት የጎደላቸው ንግግሮች ቢሰሙም፣ ኢትዮጵያ በኃላፊነት ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ከመስራት ወደኋላ ሳትል እሱኑ ተከትላ እየሰራች ነው የምትገኘው” ብለዋል፡፡ “በቀጣይም ኢትዮጵያ በቀጣናው የሚኖራት ተሳትፎ ለቀጣናው ብቻ ሳይሆን፣ ከቀጣናውም ተሸጋሪ የሆኑ የሰላምና አለመረጋጋት ምንጮችን ማድረቅ የሚቻልበት ሂደት ላይ ከሌሎች አጋሮች ጋር ሆና ቁልፍ ሚና መጫወቷን ትቀጥላለች” ሲሉም አክለዋል፡፡ ምክንያቱም “በአካባባው አሸባሪው አልሻባብ ኬሎች መሰል ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት፣ በሚገኘው ክፍተት ሁሉ ከቀጣናው ባለፈ ለዓለም ስጋት እንደሚሆን ስለሚታወቅ ነው” ብለዋል ቃል አቀባዩ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት በዛሬው መግለጫቸው በሌሎች ጉዳዮችም ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ “በሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተታለው ወደ ሚያንማር የገቡ እና ለችግር የተጋለጡ ኢትዮጵያውያንን ለማስለቀቅ፣ ጃፓን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሚያንማር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ጋራ የኦንላይን ስብሰባዎች አካሂዷል” ብለዋል፡፡ መሰል ችግር ያጋጠማቸው የሌሎች 18 አገራት ኤምባሲዎችም በውይይቱ መሳተፋቸውን ገልጸዋል፡፡ በሊባኖስ ለደኅንነታቸው አስጊ በሆነ ኹኔታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማስመለስ የሚደረገው ጥረትም እንደቀጠለ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ 2 ሺህ ዜጎች እንደሚመለሱ፣ ከነዚህም ውስጥ 200ው ከሳምንት በኋላ ወደ አገራቸው እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡

ካልፎርንያ የትረምፕ ፖሊሲዎችን ለመገዳደር ዝግጅት ጀምራለች

በአሜሪካ የካልፎርንያ ግዛት፣ የሚከተለው ተራማጅ ፖሊሲዎችን ከመጪው የትረምፕ አስተዳደር ሊመጣ ከሚችል ተግዳሮት ለመከላከል መነሻ ርምጃዎችን ወስዷል። የ
የአሜሪካ ድምፅ

ካልፎርንያ የትረምፕ ፖሊሲዎችን ለመገዳደር ዝግጅት ጀምራለች

በአሜሪካ የካልፎርንያ ግዛት፣ የሚከተለው ተራማጅ ፖሊሲዎችን ከመጪው የትረምፕ አስተዳደር ሊመጣ ከሚችል ተግዳሮት ለመከላከል መነሻ ርምጃዎችን ወስዷል። የቪኦኤው ማት ዲብል ከግዛቲቱ መዲና ሳክራሜንቶ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የትግራይ ክልል ወርቅ ለሀብት ዝርፊያ ተጋልጧል

የትግራይ ክልል በአሰቃቂው ጦርነት እና ረሃብ ከደረሰበት ጉዳት ለማገገም እየታገለ ባለበት በአኹኑ ወቅት፣ ለሃብት ዝርፊያ መጋለጡን እና የወርቅ ማዕድን ለማው
የአሜሪካ ድምፅ

የትግራይ ክልል ወርቅ ለሀብት ዝርፊያ ተጋልጧል

የትግራይ ክልል በአሰቃቂው ጦርነት እና ረሃብ ከደረሰበት ጉዳት ለማገገም እየታገለ ባለበት በአኹኑ ወቅት፣ ለሃብት ዝርፊያ መጋለጡን እና የወርቅ ማዕድን ለማውጣት ጥቅም ላይ ለሚውሉ አደገኛ ኬሚካሎች የመጋለጥ ዕጣ የተጋረጠበት መሆኑን ነዋሪዎች እና ባለሥልጣናት ተናገሩ። በማዕድን ማውጫው አቅራቢያ የሚኖሩ ነዋሪዎች ኬሚካሉ በሰውና በእንስሳት ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ ኬሚካሉ የላሞችን ቆዳ እያበላሸ እና መሬት እያራቆተ መሆኑን የዐይን እማኞችና ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።

ብልባላ ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት መነኩሴ እናታቸው እንደተገደሉባቸው አንድ የአካባቢው ነዋሪ ተናገሩ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ፣ ብልባላ ከተማ ላይ ኅዳር 23 እኩለ ሌሊት ላይ ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት የ83 ዓመት አዛውንት መነኩሴ እናታቸው መገደ
የአሜሪካ ድምፅ

ብልባላ ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት መነኩሴ እናታቸው እንደተገደሉባቸው አንድ የአካባቢው ነዋሪ ተናገሩ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ፣ ብልባላ ከተማ ላይ ኅዳር 23 እኩለ ሌሊት ላይ ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት የ83 ዓመት አዛውንት መነኩሴ እናታቸው መገደላቸውን የሟች ቤተሰብ ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ። ተሰነዘረ በተባለው ጥቃት ሁለት የህክምና ባለሞያዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱንም የአካባቢው ነዋሪዎችና አንድ የጤና ባለሞያ ተናግረዋል። በሌላ በኩል ኅዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም. በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ ዙሪያና አካባቢው በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ለሰዓታት የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ደረሰ ስለተባለው የህይወትና የአካል ጉዳት ከክልሉ፣ ከአካባቢው ባለሥልጣናት፣ ከጤና ተቋማት ኃላፊዎች መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በኦሮሚያ ክልል ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎች ለመከላከያ ሠራዊት አባልነት በግዳጅ እየተመለመሉ ነው ሲል ኢሰመኮ  አስታወቀ

በኦሮሚያ ክልል፣ ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎች ከሕግ አግባብ ውጪ ለመከላከያ ሠራዊት አባልነት በግዳጅ እየተያዙ መኾናቸውን እና የተያዙትን ለማስለቀቅ ቤተሰቦቻቸው
የአሜሪካ ድምፅ

በኦሮሚያ ክልል ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎች ለመከላከያ ሠራዊት አባልነት በግዳጅ እየተመለመሉ ነው ሲል ኢሰመኮ  አስታወቀ

በኦሮሚያ ክልል፣ ሕፃናትን ጨምሮ ሰዎች ከሕግ አግባብ ውጪ ለመከላከያ ሠራዊት አባልነት በግዳጅ እየተያዙ መኾናቸውን እና የተያዙትን ለማስለቀቅ ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ እንዲከፍሉ መገደዳቸውን፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ሐሙስ፣ ኅዳር 26፣ 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። ኮሚሽኑ ከኅዳር 4 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ጅማ እና ሻሸመኔ ከተሞች እንዳካሄደ በገለጸው ክትትል እና ምርመራ፣ «የመከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀሉ» በሚል ሕፃናትንና የአእምሮ ህሙማንን ጨምሮ የክልሉ ነዋሪዎች በግዳጅ መያዛቸውን አመልክቷል። ኮሚሽኑ በሻሸመኔ ባካሄደው ክትትል እና ምርመራ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች መኾናቸውን የገለጹ ሕፃናት፣ ወደ ወታደራዊ ሥልጠና ለሚገቡ ሰዎች በተዘጋጁ የማቆያ አዳራሾች ውስጥ ማግኘቱን ገልጾ፣ በተለይም ሁሩፋ ክፍለ ከተማ፣ ሀሌሉ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ የማቆያ አዳራሽ ውስሽ ውስጥ ካነጋገራቸው 32 ሰዎች መካከል 14ቱ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 16 ዓመት መሆኑን አመልክቷል። በተጨማሪም አንድ የ11 ዓመት ሕፃን ማግኘቱንም አስታውቋል። ለመከላከያ ሠራዊት አባልነት በግዳጅ ተመልምለው የተያዙ ሰዎችን ለማስለቀቅ ቤተሰቦቻቸው ከ20 እስከ 100 ሺሕ ብር እንዲከፍሉ እንደሚገደዱ ማረጋገጡን ያመለከተው የሰብአዊ መብት ኮሚሽኑ፣ ቤተሰቦቻቸው የተጠየቁትን ገንዘብ ካልከፈሉ ልጆቻቸው 'ለወታደራዊ ሥልጠና' እንደሚላኩ እንደሚነገራቸውም አብራርቷል። ኢሰመኮ ባወጣው መግለጫ ዙሪያ ስመኝሽ የቆየ የኮሚሽኑን ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ወይዘሮ ራኬብ መሰለን አነጋግራለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

VOA60 World - Syrian rebels capture crucial city of Hama

The Syrian military said it has withdrawn its forces from the central city of Hama after intense fighting with insurgent forces, marking another major defeat for President Bashar al-Assad in the country’s ongoing civil war.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Syrian rebels capture crucial city of Hama

The Syrian military said it has withdrawn its forces from the central city of Hama after intense fighting with insurgent forces, marking another major defeat for President Bashar al-Assad in the country’s ongoing civil war.

VOA60 America - Trump asks Georgia appeals court to end criminal case against him

U.S. President-elect Donald Trump asked a Georgia Appeals Court Wednesday to end the criminal case against him in that state for attempting to overturn his 2020 election loss. Trump pleaded not guilty.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Trump asks Georgia appeals court to end criminal case against him

U.S. President-elect Donald Trump asked a Georgia Appeals Court Wednesday to end the criminal case against him in that state for attempting to overturn his 2020 election loss. Trump pleaded not guilty.

VOA60 Africa - Local non-profit puts death toll from Guinea soccer crowd crush to at least 135

Guinea: At least 135 people were killed in a crush at a soccer stadium in the southeastern city of Nzérékoré, a local human rights group said, more than doubling the official death toll.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Local non-profit puts death toll from Guinea soccer crowd crush to at least 135

Guinea: At least 135 people were killed in a crush at a soccer stadium in the southeastern city of Nzérékoré, a local human rights group said, more than doubling the official death toll.

አቶ ታዬ ደንደአ ዛሬ ከእስር ተፈቱ 

ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዋስ እንዲፈቱ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ከእስር ቤት ሲወጡ በድጋሚ ተይዘው የነበሩት፣የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ድኤታ አ
የአሜሪካ ድምፅ

አቶ ታዬ ደንደአ ዛሬ ከእስር ተፈቱ 

ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዋስ እንዲፈቱ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ከእስር ቤት ሲወጡ በድጋሚ ተይዘው የነበሩት፣የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ድኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ዛሬ ሐሙስ ኅዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም እኩለ ቀን ላይ ፣ ከእስር ተፈተው ከቤተሰቦቻቸው ጋራ መቀላቀላቸውን ባለቤታቸው ወይዘሮ ስንታየኹ አለማየኹ ለአሜርካ ድምጽ ተናግረዋል። ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ፌደራል ፖሊስ መምርያ ዛሬ ሄደው ጠይቀውት እንደነበር የገለጹት፣ ወይዘሮ ስንታየኹ፣ «እዚያ ከደረስን በኋላ የሆኑ ሰዎች፣ »እሱ እዚህ የለም” አሉን፡፡ ሌሎች ደግሞ እዛ እንደነበረ ነገሩን፡፡ በመጨረሻም፣ አግኝተነው ምግብ ሰጥተነው ጊቢውን ለቅቀን ወጣን። በኋላ አቶ ታዬ ራሱ ደውሎ መውጣቱን ነገረን፡፡ በቅርብ ለነበረ የቤተሰብ አባል ቶሎ እንዲሔድለት ነገርን። ከዛም ይዞት መጣ፣ ገና አሁን ነው ቤት የደረሱት" ብለዋል። አቶ ታዬ ተመልሰው ለምን በቁጥጥር ስር እንደዋሉ እስካኹን እንዳልነገሯቸው ወ/ሮ ስንታየው አክለው ተናግረዋል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የአቶ ታዬን ጉዳይ ሲከታተል መቆየቱን፣ በኮሚሽኑ የክትትልና የምርመራ ሪጅናል ዲሬክተር ሰላማዊት ግርማይ ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል። አቶ ታዬ ደንደአ ለፍርድ ቤት ባቀረቡዋቸው አቤቱታዎች ዙርያ፣ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽኑ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የገለፁት ሰላማዊት ግርማይ፣ ምርመራው እንደተጠናቀቀም ውጤቱም ይፋ ይደረጋል ብለዋል። ባለፈው አመት፣ ታህሳስ ወር ላይ በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ድኤታ አቶ ታዬ ደንደአ፣ በመጀመሪያ በሦስት ጉዳዮች ተከሰው ነበር፡፡ በሒደት ግን ሁለቱ ክሶች ውድቅ ተደርገው፣ በሦስተኛው ጉዳይ ማለትም “ህገወጥ የጦር መሳርያ ይዞ በመገኘት” በሚለው ክስ ታኅሳስ 3፣ 2017 ዓ.ም. በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጨማሪ የመከላከያ ምስክሮችን ለማሰማት ተቀጥረዋል፡፡

ህንድ የብሪክስ ሀገራት የጋራ መገበያያ ገንዘብ ሐሳብ አትከተልም ተባለ

ህንድ ለብሪክስ አባል ሀገራት የጋራ መገበያያ ገንዘብ የመፍጠርን ሐሳብ እንደማትደግፍ ኒው ዲልሂ የሚገኙ ተንታኞች ተናገሩ፡፡ ዘጠኝ አባል ሀገራት ያሉት ብሪክ
የአሜሪካ ድምፅ

ህንድ የብሪክስ ሀገራት የጋራ መገበያያ ገንዘብ ሐሳብ አትከተልም ተባለ

ህንድ ለብሪክስ አባል ሀገራት የጋራ መገበያያ ገንዘብ የመፍጠርን ሐሳብ እንደማትደግፍ ኒው ዲልሂ የሚገኙ ተንታኞች ተናገሩ፡፡ ዘጠኝ አባል ሀገራት ያሉት ብሪክስ የጋራ መገበያያ ገንዘብ እንዲፈጥሩ ይቀረበውን ሐሳብ ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ አጥብቀው ተቃውመውታል፡፡ ተንታኞቹ እንዳሉት ህንድ በራሷ ገንዘብ መናገድን በማበረታታት ላይ ነች፡፡ ትረምፕ የብሪክስ ሃገራት ዶላርን የሚተካ የራሳቸው መገበያያ ገንዘብ የሚፈጥሩ ከሆነ መቶ በመቶ ታሪፍ እንደሚጠብቃቸው ዝተዋል፡፡ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ የመሠረቱት የብሪክስ ቡድን በዚህ ዓመት ኢራንን፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን፣ ኢትዮጵያ እና ግብጽን ጨምሮ ተስፋፍቷል፡፡ ትረምፕ ትሩዝ ሶሻል በተባለው ማኅበራዊ መገናኛቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ «እነዚህ ሀገራት አዲስ የብሪክስ ገንዘብ እንደማይፈጥሩ ወይም ኃያሉ የአሜሪካ ዶላር በሌላ መገበያያ እንዲተካ እንደማይደግፉ ቃል እንዲገቡ እንፈልጋለን» ብለዋል፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 በዩናይትድ ስቴትስ  የተመራ ማዕቀብ በሩሲያ ላይ ከተጣለ እና በቻይና እና በምዕራቡ ዓለም መካከል ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ውጥረቶች እየተባባሱ መምጣታቸውን ተከትሎ ብሪክስ “አዲስ የመገበያያ ገንዘብ ይፍጠር” የሚለው ሐሳብ በይበልጥ ተንቀሳቅሷል፡፡ ሩሲያ እና ቻይና ላለው ዓለም አቀፍ የንግድ ልውውጥ ከዶላር ሌላ በተለያዩ ገንዘቦች ሰፋ ብሎ እንዲካሄድ ለማድረግ የሚቻልበትን መንገድ ለመቃኘት ፍላጎት እንዳላቸው በይፋ ገልጸዋል፡፡ ኒው ዴልሂ  ግን ከአሜሪካ ዶላር መገበያየቷን ለመተው  ፍላጎት እንደሌላት የሕንድ ወጪ ንግድ ድርጅቶች ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር አጃይ ሳሃይ ለቪኦኤ ገልጸዋል፡፡

የትረምፕ የመከላከያ ዕጩ ፒት ሄግሴት ሹመታቸውን ለማስጸደቅ እየታገሉ መኾናቸውን ተናገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለመከላከያ ሚኒስትርነት የመረጧቸው ፒት ሄግሴት፣ ሹመታቸውን የሕግ መወሰኛ ምክርቤቱ እንዲያጸድቅላቸ
የአሜሪካ ድምፅ

የትረምፕ የመከላከያ ዕጩ ፒት ሄግሴት ሹመታቸውን ለማስጸደቅ እየታገሉ መኾናቸውን ተናገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለመከላከያ ሚኒስትርነት የመረጧቸው ፒት ሄግሴት፣ ሹመታቸውን የሕግ መወሰኛ ምክርቤቱ እንዲያጸድቅላቸው መታገላቸውን እንደሚቀጥሉ ትላንት ረቡዕ ተናገሩ፡፡ ሆኖም ትረምፕ ለቦታው  ሌላ ሰው ለመምረጥ እያሰቡ መሆናቸውን የሚጠቁሙ ዘገባዎች እየወጡ ነው፡፡ የአርባ አራት ዓመቱ የቀድሞው የጦር መኮንን እና የፎክስ ኒውስ የውይይት አቅራቢ ሄግሴት ሹመታቸው በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት መጽደቅ ያለበት ሲሆን «ጾታዊ ጥቃት ፈጽመዋል እንዲሁም ካለመጠን ይጠጣሉ» ከሚሉ ውንጀላዎች ጋራ  በተያያዘ ጥያቄዎች እንደሚጠብቋቸው ተገልጿል፡፡ ሄግሴት በወታደራዊም ኾነ በንግድ ዘርፍ ትልልቅ ድርጅቶችን የመምራት ምንም ዓይነት ልምድ የላቸውም፡፡ በመኾኑም  በዓለም ዙሪያ  ያለውን 2.9 ሚሊዮን የሚደርስ በሥራ ላይ ያለና ተጠባባቂ ሠራዊት እንዲሁም 700 ሺሕ ሲቪል ሠራተኞች የያዘ ተቋም እንዲመሩ መመረጣቸው ያልተለመደ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ በርካታ የአሜሪካ ዜና ማሰራጫዎች ትረምፕ ለቦታው ሌላ ሰው ሊያጩ እያሰቡ መኾናቸውን ዘግበዋል፡፡ ምናልባትም የፍሎሪዳው ሃገረ ገዥ ሮን ዲሳንተስን ወይም  የቀድሞዋን የጦር መኮንን የአይዋ  ሴኔተር ጆኒ አርነስትን በዕጩነት ያቀርቡ ይሆናል ብለዋል፡፡  ያም ሆኖ ሄግሴት ሹመታቸውን ለማስጸደቅ ከመታገል ወደኋላ እንደማይሉ ተናግረዋል፡፡ ትረምፕ በሄግሴት ምትክ ይመርጧቸው ይሆናል የተባሉት የፍሎሪዳው አገረ ገዥ ዲሳንትስ  የባሕር ኅይል አባል የነበሩ ሲሆኑ በዘንድሮው ምርጫ ለሪፐብሊካን ፓርቲው ፕሬዝደንታዊ ዕጩነት የትረምፕ ተቀናቃኝ ኾነው ቀርበው  ሳይሳካላቸው ቀርቶ ከፉክክሩ  ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወሳል፡፡

እስራኤል በሊባኖስ ላይ በምታካሂደው ጥቃት ቢያንስ አምስት ኢትዮጵያኖች ተገድለዋል - በጎ አድራጎት ተቋም

እስራኤል በሊባኖስ የሚገኘውን የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን ለማጥፋት ከመስከረም ወር ጀምሮ እያካሄደች ባለችው የአየር ጥቃት ቢያንስ አምስት ኢትዮጵያውያን መገደ
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል በሊባኖስ ላይ በምታካሂደው ጥቃት ቢያንስ አምስት ኢትዮጵያኖች ተገድለዋል - በጎ አድራጎት ተቋም

እስራኤል በሊባኖስ የሚገኘውን የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን ለማጥፋት ከመስከረም ወር ጀምሮ እያካሄደች ባለችው የአየር ጥቃት ቢያንስ አምስት ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን፣ ቤይሩት የሚገኝ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል። እኛ ለእኛ በስደት የተሰኘው በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች ባንቺ ይመር ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ እስራኤል ጥቃቱን አጠናክራ በቀጠለችበት ወቅትም አዳዲስ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ቤይሩት መግባት መቀጠላቸውን አመልክተው፣ የኢትዮጵያ መንግስት አዲስ የተደረሰውን የተኩስ ማቆም ስምምነት ተጠቅሞ ዜጎቹን ከሊባኖስ እንዲያስወጣ እና ወደ ሊባኖስ የሚያቀኑ አዳዲስ ስደተኞችን እንዲያስቆም ጠይቀዋል።  (ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ፋይል ያገኛሉ)  

በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች አለመግባባት ምክኒያት የመቐለ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ታሽገ 

የህወሓት አመራሮች መከፋፈል እየተባባሰ በመምጣቱ፣የመቐለ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ላለፉት ሦስት ቀናት «ታሽጓል» የሚል ጽሑፍ ተለጥፎበታል። ሁለቱም
የአሜሪካ ድምፅ

በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች አለመግባባት ምክኒያት የመቐለ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ታሽገ 

የህወሓት አመራሮች መከፋፈል እየተባባሰ በመምጣቱ፣የመቐለ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ላለፉት ሦስት ቀናት «ታሽጓል» የሚል ጽሑፍ ተለጥፎበታል። ሁለቱም ቡድኖች «የየራሳቸው ከንቲባ ሾመዋል» በሚል እርስ በእርስ እየተወቃቀሱ ነው። ሁለቱም ለከተማዋ ከንቲባ ሾመዋል።  

ባይደን የአንጎላን የሎቢቶ ወደብ ጎበኙ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ዛሬ ረቡዕ የአንጎላን የሎቢቶን ወደብ ጎብኝተዋል፡፡ የሎቢቶ ወደብ ወጪው በዩናይትድ ስቴትስ ወጪ የሚሸፈነው እና ከህ
የአሜሪካ ድምፅ

ባይደን የአንጎላን የሎቢቶ ወደብ ጎበኙ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ዛሬ ረቡዕ የአንጎላን የሎቢቶን ወደብ ጎብኝተዋል፡፡ የሎቢቶ ወደብ ወጪው በዩናይትድ ስቴትስ ወጪ የሚሸፈነው እና ከህንድ ውቂያኖስ እስከአትላንቲክ ተሻጋሪ ንግድ እንቅስቃሴዎችን ያጠናክራል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ረጅም የባቡር መስመር መዳረሻ ነው፡፡ ባይደን በቆይታቸው የአንጎላን ብሔራዊ የባሪያ ፍንገላ ዘመን መታሰቢያ ቤተ መዘክር ጎብኝተዋል፡፡ በሃሩን ማሩፍ የተጠናቀረው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፡፡ ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች፡፡    

ሰበር ሰሚ በዋስትና የለቀቃቸው አቶ ታዬ ደንደአ ከቂሊንጦ በር ላይ መያዛቸውን ባለቤታቸው ተናገሩ 

ከትላንት በስቲያ ሰኞ ኅዳር 23 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዋስትና እንዲፈቱ ትዕዛዝ የሰጠላቸው፣ አቶ ታዬ ደንደአ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በድጋሚ
የአሜሪካ ድምፅ

ሰበር ሰሚ በዋስትና የለቀቃቸው አቶ ታዬ ደንደአ ከቂሊንጦ በር ላይ መያዛቸውን ባለቤታቸው ተናገሩ 

ከትላንት በስቲያ ሰኞ ኅዳር 23 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዋስትና እንዲፈቱ ትዕዛዝ የሰጠላቸው፣ አቶ ታዬ ደንደአ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በድጋሚ መያዛቸውን ባለቤታቸው ገለጹ፡፡ አቶ ታዬ የዋስትና ማስያዣቸውን ጨርሰው ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ከተለቀቁ በኋላ፣ በፀጥታ ኅይሎች ተይዘው መወሰዳቸውን ባለቤታቸው ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

ባይደን ለልጃቸው የሰጡት  ምህረት በፕሬዚደንታዊ ስልጣን ላይ ክርክር አስነስቷል

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ለልጃቸው ለሀንተር ባይደን ምህረት ሰጥተዋል፡፡ ይህም የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላትን ለዓመታት የከፋፈ
የአሜሪካ ድምፅ

ባይደን ለልጃቸው የሰጡት  ምህረት በፕሬዚደንታዊ ስልጣን ላይ ክርክር አስነስቷል

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ለልጃቸው ለሀንተር ባይደን ምህረት ሰጥተዋል፡፡ ይህም የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላትን ለዓመታት የከፋፈለው የፖለቲካ ትርምስ እንዲያበቃ ምክኒያት ሆኗል። በፕሬዚደንት ስልጣን መገባደጃ የሚደረጉት የምህረት አሰጣጥ ሂደቶች ሁልጊዜም አከራካሪ መሆናቸውን ጠቅሳ፣ የአሜሪካ ድምፅ የምክር ቤት ዘጋቢ ካትሪን ጂፕሰን ያደረሰችንን ዘገባ ስመኝሽ የቆየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች።

በትግራይ ክልል የኤች አይ ቪ  ስርጭት ከጦርነቱ በኋላ በእጥፍ መጨመሩ ተገለጸ

በትግራይ ክልል የኤችአይቪ ስርጭት ከጦርነቱ በኋላ በእጥፍ መጨመሩን፣ በክልሉ የተካሄደ ጥናት ጠቅሶ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። ለቫይረሱ ስርጭት መጨመር፡
የአሜሪካ ድምፅ

በትግራይ ክልል የኤች አይ ቪ  ስርጭት ከጦርነቱ በኋላ በእጥፍ መጨመሩ ተገለጸ

በትግራይ ክልል የኤችአይቪ ስርጭት ከጦርነቱ በኋላ በእጥፍ መጨመሩን፣ በክልሉ የተካሄደ ጥናት ጠቅሶ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። ለቫይረሱ ስርጭት መጨመር፡ የሴቶች መደፈር፣ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች መበራከት እና የነዋሪዎች ከቀዬ መፈናቀል በምክንያትነት ተጠቅሰዋል። የቫይረሱ ስርጭት በተለይ በከተሞች እና በተፈናቃዮች መጠለያ ማእከላት ከፍተኛ እንደሆነም ተገልጿል።

ናሚቢያ የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዝደነት መረጠች

በናሚቢያ አወዛጋቢ በነበረውና ባለፈው ሳምንት በተከናወነው ምርጫ ገዢው ስዋፖ ፓርቲ አሸናፊ እንደኾነ በመታወጁ ደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር የመጀመሪያዋን ሴት ፕ
የአሜሪካ ድምፅ

ናሚቢያ የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዝደነት መረጠች

በናሚቢያ አወዛጋቢ በነበረውና ባለፈው ሳምንት በተከናወነው ምርጫ ገዢው ስዋፖ ፓርቲ አሸናፊ እንደኾነ በመታወጁ ደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዝደንት መርጣለች፡፡ በምክትል ፕሬዝደንትነት ሲያገለግሉ የነበሩት  የስዋፖ ፓርቲው ኔቱምቦ ናንዲ 57 በመቶ ድምጽ በማግኘት ሲያሸንፉ፣ የዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ደግሞ 25.5 በመቶ በማግኘት ሁለተኛ ኾነዋል። የተቃዋሚው ፓርቲ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበል አስታውቋል። የ72 ዓመቷ ኔቱምቦ ናንዲ በማዕድን ሃብቷ በምትታወቀው ደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ናሚቢያ የተመረጡ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝደንት ሲሆኑ፣ ፓርቲያቸው ‘የደቡብ ምዕራብ አፍሪካ ሕዝባዊ ድርጅት’ ወይም በምጻሩ ስዋፖ፣ ናሚቢያ በአፓርታይድ ሥር ከነበረችው ደቡብ አፍሪካ ነፃ ከወጣችበት ከእ.አ.አ 1990 ጀምሮ ሀገሪቱን በማስተዳደር ላይ ይገኛል። ባለፈው ረቡዕ የተደርገው ምርጫ ለ34 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየውን ስዋፖ የተፈታተነ ሲሆን ‘ገለልተኛ አርበኞች ለለውጥ’ ወይም አይፒሲ የተሰኘው ተቃዋሚው ፓርቲ የሥራ አጥነትና እኩልነት ያለመኖር ያሰቆጣቸውን ወጣት ድምፅ ሰጪዎች ድጋፍ ያገኘበት ነበር ተብሏል።

የደቡብ ኮሪያን ፕሬዝደንት ለመክሰስ ለፓርላማው ሐሳብ ቀረበ

የደቡብ ኮሪያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሀገሪቱን ፕሬዝደንት ዩን ሶክ ዮል ለመክሰስ ለፓርላማው ሐሳብ አቅርበዋል። ፕሬዝደንቱ በአጭሩ የተቀጨውን ወታደራዊ ሕግ ማ
የአሜሪካ ድምፅ

የደቡብ ኮሪያን ፕሬዝደንት ለመክሰስ ለፓርላማው ሐሳብ ቀረበ

የደቡብ ኮሪያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሀገሪቱን ፕሬዝደንት ዩን ሶክ ዮል ለመክሰስ ለፓርላማው ሐሳብ አቅርበዋል። ፕሬዝደንቱ በአጭሩ የተቀጨውን ወታደራዊ ሕግ ማወጃቸውን ተከትሎ ሥልጣን እንዲለቁ ግፊት ጨምሯል። ዩን ሶክ ዩል ትላንት ወታደራዊ ሕግ እንዳወጁ፣ እንደራሴዎች ዐዋጁን ውድቅ እንዳያደርጉ የፀጥታ ኃይሎች ፓርላማውን ከበው ነበር። ፕሬዝደንቱ ሥልጣን እንዲለቁ እና ወታደራዊ ሕጉንም በአስቸኳይ እንዲሽሩ በፓርላማው ዓባላትና በሕዝቡም የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዶ ነበር። ዩን ወታደራዊ ዐዋጁን ባስታወቁበት ማክሰኞ ምሽት፣ «ፀረ መንግሥት» ብለው የጠሯቸውን ኃይላት እንደሚያጠፉ ዝተው፣ ባለቤታቸውን ጨምሮ ቁልፍ የመንግስት ባለሥልጣናት ፈጽመዋል በሚባሉት ወንጀል ለመክሰስ የሚያደርገውን ሙከራ ነቅፈዋል። ፕሬዝደንቱን ለመክሰስ የፓርላማውን ሁለት ሦስተኛ ድምጽና የሕገ መንግስታዊውን ፍርድ ቤት ቢያንስ ስድስት ዳኞች ድጋፍ ማግኘት አለበት፡፡ በዋናው ተቃዋሚ የዲሞክራቲክ ፓርቲና በአምስት አነስተኛ ፓርቲዎች የቀረበው ፕሬዝደንቱን የመክሰስ ሐሳብ፣ ዓርብ ወይም ከዛ በኋላ ባሉት ቀናት ለድምጽ ሊቀርብ ይችላል ተብሏል። የዩን ከፍተኛ አማካሪዎች እና ሐሃፊዎቻቸው በአንድነት ሥራ ለመልቀቅ ያመለከቱ ሲሆን፣ የመከላከያ ምኒስትራቸውን ጨምሮ የካቢኔ አባሎቻቸው ደግሞ ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ተጠይቋል።

 የሩሲያው ቫግነር ቡድን ከምሪው ሞት በኋላም ሥራውን ቀጥሏል

እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር በ2023 ዓ.ም. የሩሲያ ቅጥር ወታደራዊ ቡድን የኾነው ቫግነር መሪ የነበሪይ ቭጌኒ ፕሪጎዥን ሕይወት ካለፈ በኋላም የቡድኑ እንቅ
የአሜሪካ ድምፅ

 የሩሲያው ቫግነር ቡድን ከምሪው ሞት በኋላም ሥራውን ቀጥሏል

እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር በ2023 ዓ.ም. የሩሲያ ቅጥር ወታደራዊ ቡድን የኾነው ቫግነር መሪ የነበሪይ ቭጌኒ ፕሪጎዥን ሕይወት ካለፈ በኋላም የቡድኑ እንቅስቃሴ ንቁ ኾኖ ቀጥሏል። የሩሲያ ጉዳይ ተንታኞች ቡድኑ ወደ ክሬምሊን የኃይል መዋቅሮች ይበልጥ መጠጋቱን  እና አሁንም ድረስ  የሞስኮን ጥቅም በዓለም ዙሪያ ለማስፋፍት እየጣረ ነው ይላሉ፡፡   ዘገባው የማቲው ኩፕፈር ነው ኤደን ገረመው ወደ አማርኛ መልሳዋለች። 

የፕሬዚደንት ባይደን አንጎላን ጉብኝት

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አንጎላን በመጎብኘት ላይ ናቸው። በአፍሪካ የመጀመሪያቸው ለኾነው እና በእርግጥም እንደፕሬዚደንት የመጨረሻቸው ለሚ
የአሜሪካ ድምፅ

የፕሬዚደንት ባይደን አንጎላን ጉብኝት

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አንጎላን በመጎብኘት ላይ ናቸው። በአፍሪካ የመጀመሪያቸው ለኾነው እና በእርግጥም እንደፕሬዚደንት የመጨረሻቸው ለሚሆነው ጉብኝት አንጎላ የገቡት ፕሬዝደንት ባይደን በፕሬዝደንታዊው ቤተ መንግሥት የሞቀ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ባይደን ዩናይትድ ስቴትስ እና አፍሪካ ባላቸው ግንኙነት እንደሚኮሩ ተናግረዋል። የቪኦኤዋ የኋይት ሐውስ ዘጋቢ አኒታ ፓወል ከአንጎላ ዋና ከተማ ከሉዋንዳ የላከችው ዘገባ ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች።

ደቡብ ደላንታ ዞን ግጭት መቀጠሉን ነዋሪዎች ገለጹ

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው ግጭት ምክኒያት ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳቶች መድረሳቸው
የአሜሪካ ድምፅ

ደቡብ ደላንታ ዞን ግጭት መቀጠሉን ነዋሪዎች ገለጹ

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው ግጭት ምክኒያት ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳቶች መድረሳቸውን ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡ በተለይ “ጸሐይ መውጫ” በተባለው አካባቢ ለአምስት ቀናት የዘለቀና በከባድ መሳሪያ የታገዘ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን ነዋሪዎቹ አመልክተው ከደረሰው ሰብአዊ ጉዳት በተጨማሪ የአርሶ አደሮች ቤትና የደረሱ ሰብሎች መቃጠላቸውን ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በአፍሪካ የሚካሄዱ ምርጫዎች በድምጽ ሰጪዎች ላይ የሚደቅኑት የጤና ስጋት

በአፍሪካ የሚካሄዱ ምርጫዎች በአብዛኛው ከፍተኛ ፉክክር እንዲሁም ውጥረት የሚታይባቸው ናቸው። ይህም ለድምጽ ሰጪዎች ጤና መልካም እንዳልኾነ ተነግሯል። በጋ
የአሜሪካ ድምፅ

በአፍሪካ የሚካሄዱ ምርጫዎች በድምጽ ሰጪዎች ላይ የሚደቅኑት የጤና ስጋት

በአፍሪካ የሚካሄዱ ምርጫዎች በአብዛኛው ከፍተኛ ፉክክር እንዲሁም ውጥረት የሚታይባቸው ናቸው። ይህም ለድምጽ ሰጪዎች ጤና መልካም እንዳልኾነ ተነግሯል። በጋና የሚገኙና በተለያዩ ዘርፎች ላይ የተሠማሩ ባለሞያዎች እንደሚሉት፣ የምርጫ ዘመቻዎች፣ የመራጮች መዳከምና መሰላቸት፣ እንዲሁም የፖለቲካ ውጥረትና ሁከት ይመጣል የሚል ፍራቻ መኖር እስከ ሞት የሚያደርሱ ሁኔታዎችን ሊፈጥሩ ይችላሉ። ሰናኑ ቶድ ከአክራ ጋና የላከውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።

በኢትዮጵያ ተባብሶ የቀጠለው ግጭትና ሁከት

በኢትዮጵያ፣ በተለይም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በአማጽያን እና በፌዴራል ኃይሎች መካከል ተባብሶ የቀጠለው ግጭት፣ በሺሕ ለሚቆጠሩ ሲቪሎች ሞትና በሚሊዮኖ
የአሜሪካ ድምፅ

በኢትዮጵያ ተባብሶ የቀጠለው ግጭትና ሁከት

በኢትዮጵያ፣ በተለይም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በአማጽያን እና በፌዴራል ኃይሎች መካከል ተባብሶ የቀጠለው ግጭት፣ በሺሕ ለሚቆጠሩ ሲቪሎች ሞትና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ደግሞ መፈናቀል ምክንያት ኾኗል። ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ በሥልጣን በቆዩባቸው ባለፉት አምስት ከመንፈቅ ዓመታት፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይና በአማራ ክልሎች የተካሄዱ ግጭቶችንና ተግባራዊ ያልሆኑ የሰላም ጥሪዎችን ወደኋላ የሚመለከተው በሃሩን ማሩፍ የተዘጋጀ ትንታኔ ነው። እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።

የባይደን አፍሪካ ጉብኝት በባለሞያ እይታ

የሥልጣን ዘመናቸው ሊያበቃ አንድ ወር የሚጠጋ ጊዜ የቀራቸው የዩናይድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ወደ አፍሪካ ሀገር አቅንተዋል ። በዛሬው ዕለት ከአንጎላው
የአሜሪካ ድምፅ

የባይደን አፍሪካ ጉብኝት በባለሞያ እይታ

የሥልጣን ዘመናቸው ሊያበቃ አንድ ወር የሚጠጋ ጊዜ የቀራቸው የዩናይድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ወደ አፍሪካ ሀገር አቅንተዋል ። በዛሬው ዕለት ከአንጎላው ፕሬዝደንት ጋራ ሉዋንዳ ላይ ተገናኝተው መክረዋል። የባይደን የአፍሪካ ጉዞን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ አንድምታ እንዲያስረዱን ባለሞያ ጋብዘናል። በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ እና እስያ ጥናት እና ምርምር ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑትና በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ በሚገኘው ዱኬን ዩንቨርስቲ በአፍሪካ ጥናት ማዕከል ተጋባዥ ፕሮፌሰር ዶ/ር ሳሙዔል ተፈራ ጉብኝቱ ወቅታዊና ተገቢ ነው ያሉበትን ምክኒያት አብራርተዋል።  

VOA60 America - Biden seeking additional $24B to support Ukraine, replenish US weapons stockpiles

President Joe Biden has asked Congress for an additional $24 billion to support Ukraine and replenish U.S. weapons stockpiles, two U.S. officials tell VOA. Some Republicans are already opposing the request.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Biden seeking additional $24B to support Ukraine, replenish US weapons stockpiles

President Joe Biden has asked Congress for an additional $24 billion to support Ukraine and replenish U.S. weapons stockpiles, two U.S. officials tell VOA. Some Republicans are already opposing the request.

VOA60 World - South Korean parliament votes to revoke martial law declaration by president

Parliament voted to revoke a martial law declaration by President Yoon Suk Yeol, just hours after he addressed the nation and accused the country’s opposition of controlling the parliament, sympathizing with North Korea and paralyzing the government with an
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - South Korean parliament votes to revoke martial law declaration by president

Parliament voted to revoke a martial law declaration by President Yoon Suk Yeol, just hours after he addressed the nation and accused the country’s opposition of controlling the parliament, sympathizing with North Korea and paralyzing the government with anti-state activities.

VOA60 Africa - More than 2,600 people killed in Sudan in October

More than 2,600 people were killed in Sudan in October, according to the Armed Conflict Location and Event Data Project, which called it the bloodiest month of the country’s war.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - More than 2,600 people killed in Sudan in October

More than 2,600 people were killed in Sudan in October, according to the Armed Conflict Location and Event Data Project, which called it the bloodiest month of the country’s war.

ትግራይ ክልል በትኬት ዋጋ መናር ጉዳይ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ማብራሪያ ጠየቀ

የትግራይ ክልል ትራንስፖርትና መገናኛ ቢሮ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ አክሱም ለሚከበረው ኅዳር ጽዮን ማርያም ክብረ በዓል ተጓዦች ላይ «የተጋነነ» የ
የአሜሪካ ድምፅ

ትግራይ ክልል በትኬት ዋጋ መናር ጉዳይ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ማብራሪያ ጠየቀ

የትግራይ ክልል ትራንስፖርትና መገናኛ ቢሮ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ አክሱም ለሚከበረው ኅዳር ጽዮን ማርያም ክብረ በዓል ተጓዦች ላይ «የተጋነነ» የትኬት ዋጋ ጭማሪ አድርጓል በማለት ወቀሳ አቅርቧል፡፡ በተጓዦች ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ፣ “አየር መንገዱ ለትግራይ ሕዝብ «ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚጥል» እንደኾነና “ውሳኔው ፖለቲካዊ ይዘት እንዳለው” ቢሮው ገልጿል። በጉዳዩ ላይ ለአሜሪካ ድምጽ ማብራሪያ የሰጡት የቢሮው ኃላፊ አቶ ታደለ መንግሥቱ፣ አየር መንገዱ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀናል ብለዋል፡፡ የአክሱም ከተማ የባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ዘረዳዊት ፀጋይ በበኩላቸው፣ የቲኬት ዋጋ ጭማሪው በጎብኝዎች ላይ ቅሬታ መፍጠሩን ገልጸው ተጓዦቹ ከአዲስ አበባ አክሱም ለደርሶ መልስ ጉዞ እስከ 42 ሺሕ ብር መክፈላቸውን ተናግረዋል፡፡ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽን ኃላፊዎች አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። በጉዳዩ ላይ የጹሑፍ መግለጫ እንደሚያወጡ ገልጸውልናል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትሱ የብረታ ብረት አምራች ኩባንያ ለጃፓኑ ኒፖን ስቲል የመሸጡን ዕቅድ «አግዳለሁ» አሉ

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትሱ የብረታ ብረት ኩባንያ - ‘ዩኤስ ስቲል’ ያለበትን ዕዳ በሙሉ ክፍያ በመፈጸም፤ በ14.9 ቢሊዮን ዶላር ወጭ ወ
የአሜሪካ ድምፅ

ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትሱ የብረታ ብረት አምራች ኩባንያ ለጃፓኑ ኒፖን ስቲል የመሸጡን ዕቅድ «አግዳለሁ» አሉ

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትሱ የብረታ ብረት ኩባንያ - ‘ዩኤስ ስቲል’ ያለበትን ዕዳ በሙሉ ክፍያ በመፈጸም፤ በ14.9 ቢሊዮን ዶላር ወጭ ወደ ጃፓኑ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ‘ኒፖን ስቲል’ ለማዛወር የተያዘውን ዕቅድ እንደሚያግዱ አስታወቁ። ትራምፕ በትላንትናው ዕለት ‘ትሩዝ ሶሻል’ በተባለው የማኅበራዊ ሚዲያ መልዕክት መላላኪያቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ በአንድ ወቅት “ገናና እና ብርቱ የነበረው ‘ዩኤስ ስቲል’” የውጭ አገር ኩባንያ በሆነው በጃፓኑ ‘ኒፖን ስቲል’ የመገዛቱን ዕድል ሙሉ በሙሉ እቃወማለሁ« ሲሉ ጽፈዋል። አያይዘውውም »በተከታታይ የሚፈጸሙ የግብር ማበረታቻዎችን እና ቀረጥ ነክ ርምጃዎችን በመውሰድ ‘ዩኤስ ስቲል ዳግም ገናና እና ጠንካራነቱን እንዲጎናጸፍ እናደርገዋለን’ ያሉት ትራምፕ፤ ‘ይህም በፍጥነት እውን ይደረጋል፣ እንደ ፕሬዝዳንትም ስምምነቱ ተግባራዊ እንዳይሆን አደርጋለሁ« ሲሉ አቁማቸውን ገልጸዋል። ከኒፖን ስቲል ጋራ የደረሰው የሽያጭ ስምምነት ‘ሞን ቫሊ ፔንስልቬንያ’ በሚገኘው ፋብሪካው ላይ በቂ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ያስችለኛል’ ሲል የተከራከረው ‘ዩኤስ ስቲል’ በበኩሉ “ሽያጩ ከታገደ ግን ፋብሪካውን ለመዝጋት እገደዳለሁ” ብሏል። ገዥው ‘ኒፖን ስቲል’ በፊናው ከትራምፕ አስተያየት በኋላ ባወጣው መግለጫ፤ “የዩናይትድ ስቴትስን ኢንዱስትሪ ዘርፍ፣ የሀገር ውስጥ የአቅርቦት ስርአቷን ፈታኝ ሁኔታዎችን የመቋቋም አቅም እና የአሜሪካን ብሄራዊ ደህንነት በሚያጠናክር መልኩ ዩኤስ ስቲል’ን ተንከባክቦ ለመያዝ እና ለማሳደግ ቁርጠኝስ ነኝ” ብሏል። “በማኅበር የተደራጁ ሠራተኞች ባሉት ‘ዩኤስ ስቲል’ ኩባንያ ላይ ከ2.7 ቢሊዮን ዶላር ያላነሰ መዋዕለ ንዋይ ወጭ እናደርጋለን። ዓንምለም አቀፍ ደረጃው የተጠበቀ የቴክኖሎጂ ፈጠራ አቅማችንን ተጠቅመንም በዩኤስ ስቲል ውስጥ የሚገኙ አሜሪካውያን የብረታብረት ሰራተኞች ለአሜሪካውያን ደንበኞቻቸው ጥራታቸው እጅግ የላቀ የብረታ ብረት ምርቶችን እንዲያመርቱ እናስችላቸዋለን» ሲል የጃፓኑ ኩባንያ እቅዱን ዘርዝሯል። የሽያጭ ስምምነቱን ተከትሎም የባለቤትነት ይዞታ ዝውውሩ የያዝነው የአውሮፓውያኑ 2024 ዓ.ም. ከመጠናቀቁ አስቀድሞ፣ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሥልጣን ላይ እያሉ ይጠናቀቃል’ ሲል ‘ኒፖን ስቲል’ ባለፈው ወር በተካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ ምርጫ ማግስት ነበር ይህንኑ እቅዱን ይፋ ያደረገው። ይሁን እንጂ ባይደንም ’ዩኤስ ስቲል’ “በአገር ውስጥ ኩባንያ ባለቤትነት የሚተዳደር፣ የአሜሪካ ብረታ-ብረት ኩባንያ ሆኖ መቀጠሉ አስፈላጊ ነው” ሲሉ ስምምነቱን እንደሚቃወሙ ገልጸዋል። በሌላ በኩል የትራምፕ በዓለ ሲመት እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ጥር 20 ይፈጸማል።

ከ«ሕግ ሲዳኝ» መጽሐፍ ደራሲ ጋራ የተደረገ ቆይታ

«ሕግ ሲዳኝ» በሕግ ባለሞያው ሙሉጌታ አረጋዊ በቅርቡ የተጻፈ ሐሳብ ወለድ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ በሕግ ጉዳዮች ላይ ያተኮረና አኹናዊ የኢትዮጵያን የሕግ ሥ
የአሜሪካ ድምፅ

ከ«ሕግ ሲዳኝ» መጽሐፍ ደራሲ ጋራ የተደረገ ቆይታ

«ሕግ ሲዳኝ» በሕግ ባለሞያው ሙሉጌታ አረጋዊ በቅርቡ የተጻፈ ሐሳብ ወለድ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ በሕግ ጉዳዮች ላይ ያተኮረና አኹናዊ የኢትዮጵያን የሕግ ሥርዐት አቅርቦ ለመመልከት የሚጋብዝ ነው። «መጽሐፉ ሁላችንም አለን የምንለውን እምነት ደግመን እንድናይ ይጋብዛል» የሚሉት ደራሲው ሙሉጌታ አረጋዊ፣ «መታሰቢያነቱም እምነታቸውን ደግመው ለመጠየው ፈቃደኛ ለኾኑ ብየዋለኹ» ብለውናል። ኢትዮጵያ ውስጥ “ልክ ነኝ” ብሎ የማመን ችግር እንዳለ መረዳታቸውን የገለጹት አቶ ሙሉጌታ፣በመጽሐፉ ውስጥ የተሳሉት ገጸ ባሕሪያትም «ልክ ነኝ» የሚል መከራከሪያ ይዘው ሙግት እንደሚገጥሙ ይናገራሉ። ፖሊስ፣ ዐቃቤ ሕግ ፣ ዳኛ በፍትሕ ሥርዐቱ ውስጥ ቁልፍ ሚና ያላቸው ባለሞያዎች ወደ እራሳቸው ተመልክተው «ትንሽ ተሳስቼ ሊኾን ይችላል» በሚል በመጠራጠር ቢያስቡ የተሸላ ሕይወት የመኖር ዕድል ይኖራል ብለው እንደሚያምኑ አቶ ሙሉጌታ ተናግረዋል። ይሕንን አስተሳሰባቸውን ከሕግ ፍልስፍና ጋራ በማዋሐድ በመጽሐፋቸው ውስጥ እንዲንጸባረቅ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። በመጽሐፉ ይዘት ዙሪያ አነጋግረናቸዋል። ውይይቱን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ሎስ አንጀለስ ለስደተኞች ከለላ የሚሰጥ ድንጋጌ አጸደቀች

በካሊፎርኒያ ግዛት የምትገኘው ሎስ አንጀለስ ከተማ ለስደተኞች ከለላ የሚሰጥ ድንጋጌ አጽድቃለች። ውሳኔው የተላለፈው፣ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ
የአሜሪካ ድምፅ

ሎስ አንጀለስ ለስደተኞች ከለላ የሚሰጥ ድንጋጌ አጸደቀች

በካሊፎርኒያ ግዛት የምትገኘው ሎስ አንጀለስ ከተማ ለስደተኞች ከለላ የሚሰጥ ድንጋጌ አጽድቃለች። ውሳኔው የተላለፈው፣ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጥር ወር ሥልጣን ሲረከቡ ስደተኞችን በጅምላ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ነው። ድንጋጌው የፌደራል ባለሥልጣናት ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞች ከማባረር ማገድ ባይችልም፣ ከተማዋ ለስደተኛ ነዋሪዎቿ ከለላ ለመስጠት የገባችውን ቃል እንደሚያጠናክር ተገልጿል። አንጄሊና ባግዳሳሪያን በዚህ ዙሪያ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰላም ጥሪና የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት

የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በትጥቅ ትግል ላይ ለሚገኙ ኃይሎች በድጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያቀርቡ፣ አስተያየት የሰጡን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች “መ
የአሜሪካ ድምፅ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰላም ጥሪና የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት

የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በትጥቅ ትግል ላይ ለሚገኙ ኃይሎች በድጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያቀርቡ፣ አስተያየት የሰጡን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች “መንግሥት ቁርጠኝነት ይጎድለዋል” ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ በፓርቲያቸው አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ዝግጅት ላይ በአማራና በኦሮሚያ ክልል ላሉ የትጥቅ ታጋዮች ባስተላለፉት መልዕክት “አንድ ሺህ ዓመት ቢታገሉ ስለማያሸንፉን፣ ወደሰላም እንዲመጡ ጥሪ አቀርብላቸዋለሁ” ሲሉ ተናግረዋል። አስተያየታቸውን የሰጡን ሦስት ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች በበኩላቸው፣ በመንግሥት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎች ቢቀርቡም፣ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ግን አይስተዋልም ብለዋል፡፡ ተፋላሚ ወገኖች ለሰላም ድርድር የየራሳቸው ኃላፊነት ቢኖርባቸውም፣ መንግሥት የመሪነቱን ሚና መወጣት እንዳለበትም ይመክራሉ፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ዛሬ አንጎላን ይጎበኛሉ 

ባይደን የደቡብ ምዕራባዊ አፍሪካዋን ሀገር በመጎብኘት የመጀመሪያ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ናቸው። ጉብኝታቸው በዋናነት ከአፍሪካ አህጉር የሚወጡ ውድ ማዕድኖች
የአሜሪካ ድምፅ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ዛሬ አንጎላን ይጎበኛሉ 

ባይደን የደቡብ ምዕራባዊ አፍሪካዋን ሀገር በመጎብኘት የመጀመሪያ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ናቸው። ጉብኝታቸው በዋናነት ከአፍሪካ አህጉር የሚወጡ ውድ ማዕድኖች እየተስፋፋ ወደሚገኘው የአንጎላ ወደብ የሚያጓጉዘው የባቡር መሥመር ላይ ያተኮረ እንደሚሆንም ተመልክቷል። በተጨማሪም የአህጉሪቱ ዕድገት አውታሮች ይጠናከሩ ዘንድ ዲሞክራሲ እና መረጋጋት እንደሚያስፈልግ  ያሰምሩበታል፡፡  የቪኦኤዋ የኋይት ሐውስ ዘጋቢ አኒታ ፓወል ከዋሽንግተን ያጠናቀረችው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

በዐድዋ ከተማ አንዲት አዳጊን አግተው በመግደል ጥፋተኛ የተባሉ ሁለት ተከሳሾች  ሞትና ዕድሜ ልክ ተፈረደባቸው 

ትግራይ ክልል ውስጥ ዐድዋ ከተማ፣ አንዲት አዳጊን አግተው በመውሰድ መግደላቸው በፍርድ ቤት ተረጋግጦ “ጥፋተኛ” የተባሉ ሁለት ተከሳሾች፣ አንደኛው በሞት አን
የአሜሪካ ድምፅ

በዐድዋ ከተማ አንዲት አዳጊን አግተው በመግደል ጥፋተኛ የተባሉ ሁለት ተከሳሾች  ሞትና ዕድሜ ልክ ተፈረደባቸው 

ትግራይ ክልል ውስጥ ዐድዋ ከተማ፣ አንዲት አዳጊን አግተው በመውሰድ መግደላቸው በፍርድ ቤት ተረጋግጦ “ጥፋተኛ” የተባሉ ሁለት ተከሳሾች፣ አንደኛው በሞት አንደኛው ደግሞ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ፣ ዛሬ ኅዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም. የዋለው ችሎት ፈረደ። በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን ዐድዋ ከተማ መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ ከቤት ወጥታ የቋንቋ ትምሕርት ወደ ምትከታተልበት ትምሕርት ቤት በማምራት ላይ የነበረችን አንዲት አዳጊ፣ በተለምዶ ባጃጅ ተብሎ በሚጠራ ባለ ሦስት እግር ተሽከካሪ በመጠቀም አግተው ወስደዋታል፣ በኋላም ገድለዋታል በሚል ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት ተከሳሾች ዛሬ ተፈርዶቻቸዋል። የመቐለ ዞን ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኞ ኅዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም. በዋለው ችሎት፣ የ16 ዓመት አዳጊ ማኅሌት ተኽላይን በመግደል ተከሰውና ጥፋተኛ ተብለው የፍርድ ውሳኔያቸውን ለመጠባበቅ ለዛሬ ተቀጥረው ከነበሩት ሁለት ተከሳሾች፣ አንደኛው የ24 ዓመት ዓወት ነጋሲ ሓጎስ ሞት ሲፈረድበት፣ ሁለተኛው የ20 ዓመቱ ናሆም ፍፁም ኃይሉ ደግሞ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Get more results via ClueGoal