Ethiopia



የኢራቅ ሚሊሻዎች መንግሥት በአማፂያን ላይ የሚያካሂደውን  አጸፋዊ ጥቃት ለመደገፍ በሶሪያ ተሰማርተዋል

በኢራን የሚደገፉት የኢራቅ ታጣቂዎች  የሶሪያ መንግሥት ትልቋን የአሌፖ ከተማ በያዙት ታጣቂዎች ድንገተኛ ግሥጋሤ ላይ የሚያካሂደውን የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ለ
የአሜሪካ ድምፅ

የኢራቅ ሚሊሻዎች መንግሥት በአማፂያን ላይ የሚያካሂደውን  አጸፋዊ ጥቃት ለመደገፍ በሶሪያ ተሰማርተዋል

በኢራን የሚደገፉት የኢራቅ ታጣቂዎች  የሶሪያ መንግሥት ትልቋን የአሌፖ ከተማ በያዙት ታጣቂዎች ድንገተኛ ግሥጋሤ ላይ የሚያካሂደውን የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ለመደገፍ ወደሶሪያ ዘምተዋል ሲሉ አንድ የታጣቂዎቹ ባለስልጣን እና የሶሪያ  የጦርነት ተከታታይ አካል  አመልክተዋል፡፡ በጂሃዳዊው ሃያት ታህሪር አልሻም ቡድን የሚመሩት ሰርጎ ገቦቹ ባለፈው ሳምንት አሌፖ ላይ ከሁለት አቅጣጫ ጥቃት አድርሰው ወደ ገጠራማዎቹ ኢድሊብ እና ሃማ ግዛቶች ተሻግረዋል፡፡ የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አርጋቺ ከሶሪያው ፕሬዘዳንት በሽር አሳድ ጋር ትላንት እሁድ ደማስቆ ላይ የተገናኙ ሲሆን፤ ቴህራን ለሶሪያ መንግሥት ሙሉ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቀዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ትላንቱኑ በመቀጠል  ከአማጺያኑ ዋና ደጋፊ ጋር ለመወያየት ወደ ቱርክ አንካራ ተጉዘዋል፡፡ መቀመጫውን በብሪታንያ ያደረገው የተቃዋሚዎች  የሶሪያ የሰብዓዊ መብት ተከታታይ ቡድን  ወደ 200 የሚጠጉ ኢራቃውያን ታጣቂዎች በአነስተኛ የጭነት መኪናዎች ወደ ሶሪያ ማቅናታቸውን አስታውቋል። የሶሪያ ጦር  የአማጺያኑን ጥቃት  በመመከት በሚያካሂደው ውጊያ ለማገዝ  አሌፖ ላይ  ይሰፍራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አክሎ አስታውቋል፡፡

ጀርመን ቻይና ሩሲያን መደገፏን እንድታቆም ጠየቀች

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቤርቦክ ቤጂንግ ለሞስኮ የምታደርገውን ድጋፍ ግንኙነታቸውን እንደሚያሻክር በመግለጽ ቻይና የዩክሬንን ግጭት ለማስቆም
የአሜሪካ ድምፅ

ጀርመን ቻይና ሩሲያን መደገፏን እንድታቆም ጠየቀች

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቤርቦክ ቤጂንግ ለሞስኮ የምታደርገውን ድጋፍ ግንኙነታቸውን እንደሚያሻክር በመግለጽ ቻይና የዩክሬንን ግጭት ለማስቆም እንድታግዝ የቻይና አቻቸውን አስጠንቅቀዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ይሄንን ያሉት በቤጂንግ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡ አናሌና ከአንድ ሺህ ቀናት በላይ የፈጀው ጦርነት አለምን ሁሉ እየጎዳ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በጦር ሜዳ ያላቸውን ሚና እና በግጭቱ በቻይና የተሰሩ ድሮኖች ጥቅም ላይ መዋላቸውን አውግዘዋል፡፡ አናሊና ቤርቦክ “ዛሬ ቻይና ያለሁት ለዚሁ ነው” ያሉ ሲሆን ሁሉም የመንግስታቱ ድርጅት ቋሚ የጸጥታው ምክርቤት አባል “ለአለም ሰላም እና ደህንነት ሃላፊነት አለበት” በማለት ተናግረዋል፡፡ በርሊን ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከቻይና ጋር የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር በምታደርገው ጥረት የጀርመኗ ከፍተኛ ዲፕሎማት ከአቻቸው ዋንግ ዪ ጋር “ስልታዊ ውይይት” ለማድረግ ተገናኝተዋል። ዋንግ ለጀርመን አቻቸው “የዓለም ሁለተኛ እና ሦስተኛ ትልቅ ምጣኔ ሃብት ባለቤት” እንዲሁም “በነውጥ ውስጥ ባለው ዓለም አቀፍ ሁኔታ ውስጥ እንደ ታላላቅ ኃያላን" ሃገራት ቻይና እና ጀርመን ግንኙነታቸውን ማሻሻል አለባቸው ብለዋል፡፡  

VOA60 America - President Biden pardons son Hunter

President Joe Biden announced Sunday he pardoned his son Hunter, who was facing sentencing this month in two federal cases. Biden had previously pledged not to take such action, but in a statement Sunday he said the move was in response to what he called sele
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - President Biden pardons son Hunter

President Joe Biden announced Sunday he pardoned his son Hunter, who was facing sentencing this month in two federal cases. Biden had previously pledged not to take such action, but in a statement Sunday he said the move was in response to what he called selective and unfair prosecution.

VOA60 Africa - Guinea stadium crush kills 56 people

A disputed penalty call sparked violence and a stampede at a soccer match in southeast Guinea, killing at least 56 people according to a provisional toll, the government said on Monday. An investigation is under way, authorities said.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Guinea stadium crush kills 56 people

A disputed penalty call sparked violence and a stampede at a soccer match in southeast Guinea, killing at least 56 people according to a provisional toll, the government said on Monday. An investigation is under way, authorities said.

VOA60 World - Georgia: Police say 224 people detained during pro-EU protests

Police say 224 people were detained «over the past few days» of ongoing opposition mass protests following the government’s decision to suspend negotiations to join the European Union. Georgia's interior ministry said Monday that 21 police offic
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Georgia: Police say 224 people detained during pro-EU protests

Police say 224 people were detained «over the past few days» of ongoing opposition mass protests following the government’s decision to suspend negotiations to join the European Union. Georgia's interior ministry said Monday that 21 police officers were injured on Sunday.

የጡት ካንሰር ህክምና ጥረቶች በአፍሪካ

የጡት ካንሰር በጡት ውስጥ የሚገኙ ህዋሳቶቻችን ከተገቢ መጠን በላይ እራሳቸውን ማባዛት ሲጀመሩ የሚከሰት የጤና ችግር ነው፡፡ ይህን መሰሉ የህዋሳት መባዛት በ
የአሜሪካ ድምፅ

የጡት ካንሰር ህክምና ጥረቶች በአፍሪካ

የጡት ካንሰር በጡት ውስጥ የሚገኙ ህዋሳቶቻችን ከተገቢ መጠን በላይ እራሳቸውን ማባዛት ሲጀመሩ የሚከሰት የጤና ችግር ነው፡፡ ይህን መሰሉ የህዋሳት መባዛት በጊዜ ህክምና ካልተደረገለት እስከ ህይወት ማለፍ ድረስ የሚደርስ የጤና ተግዳሮት ነው፡፡ ለመሆኑ በበሽታው ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ምን ይመስላሉ?

አማፅያን እና አጋሮቻቸው አብዛኛውን የአሌፖ ክፍል መቆጣጠራቸውን የሶሪያን ጦርነት በቅርብ የሚያጠና ተቋም አስታወቀ

የሶሪያ አማፂ ተዋጊዎች ከ2016 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሶሪያን ግዙፍ ከተማ አሌፖን መቆጣጠራቸውን የሶሪያን ጦርነት የሚከታተለው ተቋም በዛሬው ዕለት አስታውቋ
የአሜሪካ ድምፅ

አማፅያን እና አጋሮቻቸው አብዛኛውን የአሌፖ ክፍል መቆጣጠራቸውን የሶሪያን ጦርነት በቅርብ የሚያጠና ተቋም አስታወቀ

የሶሪያ አማፂ ተዋጊዎች ከ2016 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሶሪያን ግዙፍ ከተማ አሌፖን መቆጣጠራቸውን የሶሪያን ጦርነት የሚከታተለው ተቋም በዛሬው ዕለት አስታውቋል ። ጦርነቱ በቀጠለበት በአሁኑ ሰዓት የመንግስት ሃይሎች እና የሩሲያ የጦር አውሮፕላኖች  በከተማይቱ የተለያዩ ስፍራዎች ላይ የአየር ጥቃት መፈጸማቸው ተገልጿል። በጦርነት በተመሰቃቀለችው ሀገር ዙሪያ ጥናቶችን የሚያከናውነው ተመራማሪዎችን ያቀፈው የሶሪያ የሰብዓዊ መብቶች ታዛቢ የተሰኘው ተቋም እንዳስታወቀው በአልቃይዳ የቀድሞ የሶሪያ ቅርንጫፍ የሚመራው የጂሃዲስት ህብረት እና አጋር አንጃዎች የአሌፖን ከተማ አብዛኛው ክፍልን ፣ የመንግስት ማዕከላትን እና ማረሚያ ቤቶችን ተቆጣጥረዋል። የአማፂ ኃይሎች ከሶሪያው ፕሬዝዳንት ባሻር አል አሳድ መንግስት ታማኝ ኃይሎች ጋር ከታዋጉ በኃላ አርብ ዕለት ወደ በከተማይቱ አንዳንድ ክፍሎች መግባታቸውን ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ በአሌፖ የሚገኙ እማኞች ለቪኦኤ አረጋግጠዋል። የሶሪያ የሰብዓዊ መብቶች ታዛቢ ተቋም ከረቡዕ ጀምሮ በተቀሰቀሰው ግጭት 277 ሰዎች መሞታቸውን እና አብዛኞቹ አማፂያን እና የሶሪያ ወታደሮች እንደሆኑ አስታውቋል። ይሁን እንጂ የተባበሩት መንግስታት የሶሪያ ቀውስ ምክትል የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ዴቪድ ካርደን በትናንትናው ዕለት እንደተናገሩት በጦርነቱ ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 27 ንፁሀን ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል። የሶሪያ ጦር አርብ ባወጣው መግለጫ ፣በአሌፖ እና ኢድሊብ ገጠራማ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱት ሀይሎቹ በአሸባሪ ድርጅቶች የተሰነዘረውን ከባድ ጥቃት መመከት መቀጠላቸውን አስታውቋል ። ጦር ሰራዊቱ በአሌፖ ከተማ ስላለው ሁኔታ የሰጠው መግለጫ የለም።

ውጥረትን ለመቀነስ ከሶማሊያ፣ ኢትዮጵያ እና ዩጋንዳ መሪዎች ጋር ስብሰባ መታቀዱን የኬንያው ፕሬዚደንት አስታወቁ

የሶማሊያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳ መሪዎች የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውጥረቶችን «ለመቀነስ» ስብሰባ ለማድረግ ማቀዳቸውን የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊ
የአሜሪካ ድምፅ

ውጥረትን ለመቀነስ ከሶማሊያ፣ ኢትዮጵያ እና ዩጋንዳ መሪዎች ጋር ስብሰባ መታቀዱን የኬንያው ፕሬዚደንት አስታወቁ

የሶማሊያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳ መሪዎች የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውጥረቶችን «ለመቀነስ» ስብሰባ ለማድረግ ማቀዳቸውን የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ትናንት አርብ አስታውቀዋል። ሩቶ ይህንን የተናገሩት የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ 24ኛ መደበኛ የመሪዎች ጉባኤውን ባካሄደበት ታንዛኒያ፣ አሩሻ ባደረጉት ንግግር ነው። የማህበረሰቡ አዲስ ሊቀመንበር ሩቶ ፣ ስብሰባው የሚደረግበትን ቀን ይፋ አላደረጉም ።ስብሰባው እርግጥ ከሆነ ፣አዲስ አበባ እና ሶማሌላንድ አወዛጋቢውን የመግባቢያ ሰነድ በአውሮፓዊያኑ ጥር 1 ፣2024 ከተፈራረሙ ወዲህ በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል የሚደረግ የመጀመሪያ የፊት ለፊት ስብሰባ ይሆናል። የሶማሊያ መሪዎች የመግባቢያ ሰነዱ እስካልተሰረዘ ድረስ ከኢትዮጵያ መሪዎች ጋር ምንም አይነት ቀጥተኛ ንግግር እንደማይኖር አጽንኦት ሲሰጡ ሰንብተዋል። ቱርክ ቀደም ሲል ፣ በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል በሐምሌ እና ነሐሴ ወራት ሁለት ስብሰባዎችን በአንካራ ላይ አመቻችታ ነበር ።በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ ልዑካኑ ፊት ለፊት ባለመገናኘታቸው ተጨባጭ እድገት ሳይገኝ ቀርቷል። በአውሮፓዊያኑ መስከረም 17 ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ሶስተኛው ዙር ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል። ሶማሊያ የምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ 8ኛ አባል ሀገር ሆና የተቀላቀለችው በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ነው። «የቀጠናችንን ሰላም ለማስጠበቅ ፣ ለቀጠናችን ፀጥታና መረጋጋት መዋለ ነዋይ ለማፍሰስ የጋራ ጥረት (ያሻል) » ፣ በማለት ጥሪ ያቀረቡት ሩቶ ፣ በንግግራቸው ወቅት ሰላምና መረጋጋትን ማስጠበቅ ፣ በቀጠናው የመዋለ ነዋይ ፍሰትን እንደሚያሳድግ ገልጸዋል። «በተጨማሪም ፣ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ውጥረት ለመቀነስ በፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ፣ በራሴ፣ በወንድሜ ሀሰን ሼክ እና በጠቅላይ ሚንስትር አብይ መካከል ምክክር ለማድረግ አቅደናል ።ምክንያቱም የሶማሊያ ደህንነት እና መረጋጋት ፣ ለቀጠናው መረጋጋት ፣ ለንግድ ሰዎች ፣ ለመዋለ ነዋይ አፍሳሾች እና ስራ ፈጣሪዎች እመርታ በእጅጉ አስተዋጽኦ አለው ” ሲሉም አክለዋል። ኬንያ በደቡብ ሱዳን የሰላም ጥረቶች ውስጥ እየሰራች መሆኗን የተናገሩት ሩቶ ፣ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማረጋገጥ ከሌሎች አጋር መንግስታት ጋር እየሰራች መሆኗን እስታውቀዋል። “የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሶማሊያ መረጋጋት ለቀጠናው ብልጽግና ቁልፍ ሚና አለው » ሲሉ ሩቶ በትናንትናው ዕለት በኤክስ አውታር ላይ አጋርተዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዚደንት ፣ የኔቶ አባልነት «የጋለውን ጦርነት ምዕራፍ » ሊያስቆም እንደሚችል ተናገሩ 

  የዩክሬኑ ፕሬዚደንት ቮሎድሜር ዜለንስኪ ፣ ሀገራቸው የሰሜን አትላንቲክ  የጦር ቃልኪዳን ድርጅት -ኔቶን  ተቀባይነት ማግኘት ከቻለች  «የጋለ ጦርነት ም
የአሜሪካ ድምፅ

የዩክሬኑ ፕሬዚደንት ፣ የኔቶ አባልነት «የጋለውን ጦርነት ምዕራፍ » ሊያስቆም እንደሚችል ተናገሩ 

  የዩክሬኑ ፕሬዚደንት ቮሎድሜር ዜለንስኪ ፣ ሀገራቸው የሰሜን አትላንቲክ  የጦር ቃልኪዳን ድርጅት -ኔቶን  ተቀባይነት ማግኘት ከቻለች  «የጋለ ጦርነት ምዕራፍ» ሲሉ የጠሩትትን በሩሲያ የታወጀጦርነት ለማስቆም እንደሚቻል ተናገሩ።  በትናንትናው ዕለት  ከስካይ ኒውስ ቴሌቭዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት  ቃለ ምልልስ ዜለንስኪ የሀገሪቱ ያልተያዙ ግዛቶች በኔቶ ከለላ ስር ከዋሉ  እና ህብረቱን ለመቀላቀል በቀረበው ጥሪ መሰረት የዩክሬን ዓለም አቀፍ ድንበሮች ዕውቅና ካገኙ፣ ሀገራቸው ተኩስ አቁምን  ለማጤን ፍቃደኛ መሆኗን ተናግረዋል ። በአውሮፓዊያኑ  2014 ሩሲያ የዩክሬን ግዛት የነበረችው  የክራይሚያን ባሕረ ገብ መሬት በኃይል ወደ ግዛቷ ከመቀላቀሏ በተጨማሪ ፣ በየካቲት 2022  ሙሉ ወረራ በማወጅ  ከአጠቃላይ የዩክሬን ግዛት  20 በመቶውን ተቆጣጥራለች። «የጋለውን የጦርነት ምዕራፍ መቋጨት ከፈለግን ፣በእጃችን ያሉ የዩክሬን ግዛቶችን በኔቶ ጥላ ስር ማድረግ  አስፈላጊ ነው» ያሉት ዘለንስኪ በሩሲያ ቁጥጥር ስር ያሉ የሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍሎች  «በዲፕሎማሲያዊ መንገድ» ሊመለስ እንደሚችሉ አክለዋል። የእሳቸው ንግግር የተሰማው ፣ የአሜሪካ አዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያ ወረራ ከጀመረች ወዲህ  ዩናይትድ ስቴትስ ዩክሬንን ለመደገፍ  ያፈሰሰችውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በተመለከተ ትችት በሰነዘሩ ማግስት ነው።  ትራምፕ ዋይት ሀውስን መልሰው ከተረከቡ በኃላ  በ24 ሰዓታት ውስጥ ጦርነቱን ማቆም እንደሚችሉም ገልጸዋል ። ይህ  መግለጫ ዩክሬን አሁን ላይ  በሩሲያ  የተያዙባትን ግዛቶች አሳልፋ መስጠት  እንዳለባት አመላካች ተደርጎ  ተተርጉሟል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ትራምፕ የዩክሬን እና የሩስያ ልዩ መልዕክተኛ ይሆኑ ዘንድ በመከላከያ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ አማካሪ ሆነው ያገለገሉትን ፣ጡረተኛውን ሌተናል ጄኔራል ኪት ኬሎግን  በእጩነት አቅርበዋል ።  ኬሎግ ዩክሬናውያን ወደ ድርድር ጠረጴዛው ካልመጡ የአሜሪካ ድጋፍ እንደሚያከትም የተናገሩ ሲሆን ፣  ለሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደግሞ  ወደ ጠረጴዛው ካልመጡ ዩናይትድ ስቴትስ ሩሲያዊያንን በጦርነት አውድማ ለመግደል የሚስችል ማናቸውንም ድጋፍ ለዩክሬናውያን እንደምትሰጥ ተናግረዋል። ላለፉት በርካታ ወራት ሩሲያ  ከጊዜ ወደ ጊዜ እያለ በመጣ ሁኔታ    ሰው አልባ አውሮፕላኖች፣ ሚሳኤል እና ተንሸራታች ቦምቦችን በመጠቀም የዩክሬይን ከተሞን  በኃያሉ እየደበደበች ትገኛለች። ይህም ህዝቦችን ተጎጂ ከማድረግ በተጨማሪ ፣ ቀዝቃዛው ወቅት እየተንሰራፋ  በመጣባት በአሁኑ  ጊዜ ለኃይል መሠረተ ልማቶች ውድመት ምክንያት ሆኗል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣን ሮዝሜሪ ዲካርሎ ሞስኮ እያካሄደች ያለችው በዩክሬን የኃይል መሠረተ ልማት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ክረምቱን  «ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከነበሩት ሁሉ በጣም የከበደ  ሊያደርገው ይችላል » ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ዩክሬን ከሩሲያ ወረራ ጋር በምታደርገው ውጊያ የሀገሪቱ  ከፍተኛ የውጭ ደጋፊ ሆኖ የሰነበተው  የዩኤስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር እና የኪየቭ አውሮፓውያን አጋሮች ፣ ሩሲያ ውስጥ ባሉ ኢላማዎች ላይ የረጅም ርቀት ሚሳኤሎች ለጥቅም እንዲውሉ ከፈቀዱ ወዲህ  ዩክሬን የበረታ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ጀምራለች።

ግድያ ሲፈጸም ያሳያሉ የተባሉ በማኅበራዊ ሚዲያ የተለቀቁ ቪዲዮች “በመንግሥት የተቀነባበሩ ናቸው” ሲል ከፋኖ ቡድኖች አንዱ ክስ አሰማ

ግድያ ሲፈጸም ያሳያሉ የተባሉ እና በቅርቡ በሶሻል ሚዲያ የተለቀቁ ቪኦኤ ያላረጋገጣቸው የቪዲዮ ክሊፖችን በተመለከተ የፋኖ ታጣቂ ቡድን እጁ እንደሌለበት አስታ
የአሜሪካ ድምፅ

ግድያ ሲፈጸም ያሳያሉ የተባሉ በማኅበራዊ ሚዲያ የተለቀቁ ቪዲዮች “በመንግሥት የተቀነባበሩ ናቸው” ሲል ከፋኖ ቡድኖች አንዱ ክስ አሰማ

ግድያ ሲፈጸም ያሳያሉ የተባሉ እና በቅርቡ በሶሻል ሚዲያ የተለቀቁ ቪኦኤ ያላረጋገጣቸው የቪዲዮ ክሊፖችን በተመለከተ የፋኖ ታጣቂ ቡድን እጁ እንደሌለበት አስታውቋል። የፌዴራል እና የክልል ባለሥልጣናት ግን “የጭካኔ ድርጊት” ብለው የገለጹትንና በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ተገድሏል የተባለውን ወጣት በተመለከተ ባለፈው ሐሙስ ዕለት በጽኑ አውግዘዋል። በአማራ ክልል የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ከሚገኙት ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው ‘የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት’ መሪ እንደሆኑ የነገሩን አቶ እስክንድር ነጋ፣ በቪዲዮ ላይ ግድያ ያሳያል የተባለውን ድርጊት በተመለከተ ቡድኑ ተጠያቂ እንዳልሆነ አስታውቀዋል።

በነሃሴው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት 24 ሰዎችን ገድሏል ሲል አምነስቲ የናይጄሪያን ፖሊስ ከሰሰ

ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል በትላንትናው ዕለት ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ የነሀሴ ወር የናይጄሪያን መንግሥት በመቃወም የ
የአሜሪካ ድምፅ

በነሃሴው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት 24 ሰዎችን ገድሏል ሲል አምነስቲ የናይጄሪያን ፖሊስ ከሰሰ

ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል በትላንትናው ዕለት ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ የነሀሴ ወር የናይጄሪያን መንግሥት በመቃወም የተካሄዱ ሰልፎች ተከትሎ ባደረገው ምርመራ ባለሥልጣናቱ በወሰዷቸው ርምጃዎች ተቃዋሚዎችን ገድለዋል፤ ከ1 ሺሕ 200 በላይ ሰዎችን ደግሞ አስረዋል ብሏል። የአምነስቲ ምርመራ ውጤት የተሰማው በናይጄሪያ ዜጎች መብታቸውን የሚገልጡባቸው መንገዶች እየጠበቡ የመምጣታቸው ስጋት እየያለ በመጣበት ወቅት ነው። ቲሞቲ ኦቢዙ ከአቡጃ ያደረሰንን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በርካታ የኒው ዮርክ ነዋሪዎች ከምግብ ዋስትና እጦት ጋራ እየታገሉ ነው

ዛሬ በሚከበረው የምስጋና ቀን በርካታ አሜሪካውያን በማዕድ ዙሪያ ይሰበሰባሉ። በቅርቡ የወጣ ሪፖርት እንዳመለከተው ግን በአሜሪካ ትልቋ ከተማ የሚገኙ በርካታ
የአሜሪካ ድምፅ

በርካታ የኒው ዮርክ ነዋሪዎች ከምግብ ዋስትና እጦት ጋራ እየታገሉ ነው

ዛሬ በሚከበረው የምስጋና ቀን በርካታ አሜሪካውያን በማዕድ ዙሪያ ይሰበሰባሉ። በቅርቡ የወጣ ሪፖርት እንዳመለከተው ግን በአሜሪካ ትልቋ ከተማ የሚገኙ በርካታ ነዋሪዎች የምግብ ዋስትና እጦት ገጥሟቸዋል። በኒው ዮርክ ከተማ የሚገኙ የነፃ ምግብ ማደያዎች ተጠቃሚያቸው እየጨመረ መጥቷል። ከነዚኽም ውስጥ የመተዳደሪያ ሥራ ያላቸውም ይገኙበታል። የቪኦኤዋ ቲና ትሪን የላከችው ዘገባ ነው እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል፡፡

በናሚቢያ የምርጫ ጣቢያዎች በድጋሚ ተከፍተዋል

በምርጫ ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ለሁለተኛ ጊዜ የምርጫ ሂደቱን ባራዘመችው ናሚቢያ፣ ዛሬ 36 የምርጫ ጣቢያዎች በድጋሚ ተከፍተው ምርጫ ተካሂዷል። ረቡዕ እለት
የአሜሪካ ድምፅ

በናሚቢያ የምርጫ ጣቢያዎች በድጋሚ ተከፍተዋል

በምርጫ ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ለሁለተኛ ጊዜ የምርጫ ሂደቱን ባራዘመችው ናሚቢያ፣ ዛሬ 36 የምርጫ ጣቢያዎች በድጋሚ ተከፍተው ምርጫ ተካሂዷል። ረቡዕ እለት የተጀመረው የምርጫ ሂደት ባለፉት ሁለት ቀናት በገጠሙ የቴክኒክ ችግሮች ምክንያት፣ የተረጋጋች እና ሰላማዊ ሀገር በመሆን በምትታወቀው ደቡባዊቷ የአፍሪካ አገር ውጥረት ፈጥሯል። ተቃዋሚዎችም የምርጫውን መዘግየት “አሳፋሪ” ብለውታል፡፡ አንዳንድ መራጮች ፕሬዘዳንታቸውንና፣ ህግ አውጭ አባላትን ለመምረጥ እስከ 12 ሰዓት በምርጫ መስጫ ጣቢያዎች ሰልፍ ላይ ማሳለፋቸው ተገልጿል፡፡ ይህም ናሚቢያ ከደቡብ አፍሪካ ነፃ ከወጣች እ.ኤ.አ. በ1990 ወዲህ፣ በስልጣን ላይ ላለው የደቡብ ምዕራብ አፍሪካ ህዝቦች ድርጅት (ስዋፖ) ፓርቲ የገጠመው በጣም ከባድ ክስ እንደሆነ ተገልጿል። መራጮን መመዝገቢያ ታብሌቶች በትክክል አለመስራትና የምርጫ ወረቀቶች እጥረት ምርጫው በተጀምረ እለት የገጠሙ ቴክኒካዊ ችግሮች እንደነበሩ ተገልጿል፡፡ ይህን ተከትሎ በመራጮችና ፓርቲዎች ነቀፋ የደረሰበት የሃገሪቱ ምርጫ ኮምሽንም፣ ምርጫውን ለሁለተኛ ጊዜ በማራዘም እስከነገ ቅዳሜ ምሽት ድረስ እንዲካሄድ እንዲወስን አስገድዶታል፡፡ ሁኔታው የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ቁጣ ያስነሳ ሲሆን አንዳንዶች የምርጫው ሂደት እንዲቆም ጠይቀዋል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዛሬ ተገናኝተው የጋራ መግለጫ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘው እንደነበረም ገለልተኛ አርበኞች ለለውጥ (IPC) ፓርቲ ተወካይ ክሪስቲን አኦቻመስ ተናግረዋል፡፡ የወጣቶች ሥራ አጥነት እና ከነጻነት በኋላ የተወለዱ አዲስ ትውልድ መፈጠር እ.አ.አ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ሲገዛ ለነበረው ስዋፖ ፓርቲ የነበረውን ድጋፍ ፈታኝ አድርጎበታል፡፡ በናሚቢያ ከተመዘገቡት መራጮች መካከል 42 በመቶ ያህሉ ከ35 ዓመት በታች ዕድሜ እንደሆኑም የምርጫ ባለስልጣን ገልጸዋል፡፡ ናሚቢያ ዋና የዩራኒየም እና የአልማዝ ላኪ ሀገር ብትሆንም ከሦስት ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ህዝቧ በመሠረተ ልማት እና የስራ እድሎች ተጠቃሚ እንዳልሆነ ተንታኞች ይናገራሉ።

ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለማባረር ቃል የገቡት የሶማሊያ ከንቲባ ከምርጫ በኋላ አቋማቸውን አለሳለሱ 

በቅርቡ በሶማሊያ በተካሄደው ምርጫ፣ በተለይ በፑንትላንድ ክልል የስደተኞች ጉዳይ የዘመቻው ቁልፍ አካል ነበር። በተለይ በሥልጣን ላይ ያሉት የከተማዋ ከንቲባ
የአሜሪካ ድምፅ

ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለማባረር ቃል የገቡት የሶማሊያ ከንቲባ ከምርጫ በኋላ አቋማቸውን አለሳለሱ 

በቅርቡ በሶማሊያ በተካሄደው ምርጫ፣ በተለይ በፑንትላንድ ክልል የስደተኞች ጉዳይ የዘመቻው ቁልፍ አካል ነበር። በተለይ በሥልጣን ላይ ያሉት የከተማዋ ከንቲባ፣ ኢትዮጵያውያንን ሰብስበው ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ሲያስፈራሩ ቆይተዋል። አንዳንዶች ይህ ንግግራቸው የአካባቢውን ምክር ቤት አባላት ድጋፍ ለማግኘት የተጠቀሙበት ነው ሲሉ፣ ሌሎች ደግሞ አቋማቸውን፣ በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ አሸናፊ ከሆኑት ዶናልድ ትራምፕ ጋራ ያመሳስሏቸዋል። የአፍሪካ ቀንድ ዘጋቢ ሀሩን ማሩፍ በዚህ ዙሪያ ያጠናቀረውን ዘገባ፣ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

በእስራኤል ጥቃት 30 ሰዎች ጋዛ ውስጥ መገደላቸውን የህክምና ባለሞያዎች ገለጹ

እስራኤል በጋዛ ባካሄደችው ወታደራዊ ጥቃት ቢያንስ 30 ሰዎች መገደላቸውንና አብዛኞቹ በከበባ ስር በሚገኘው ኑሴይራት መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የነበሩ መሆናቸውን የ
የአሜሪካ ድምፅ

በእስራኤል ጥቃት 30 ሰዎች ጋዛ ውስጥ መገደላቸውን የህክምና ባለሞያዎች ገለጹ

እስራኤል በጋዛ ባካሄደችው ወታደራዊ ጥቃት ቢያንስ 30 ሰዎች መገደላቸውንና አብዛኞቹ በከበባ ስር በሚገኘው ኑሴይራት መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የነበሩ መሆናቸውን የህክምና ባለሙያዎች አስታወቁ፡፡   የህክምና ባለሞያዎች ይህን ያሉት አካባቢውን ወረው የነበሩት የእስራኤል ታንኮች አርብ እለት ካፈገፈጉ በኃላ ነው። የጤና ባለሞያዎቹ አክለው፣ ከሩሴይራት በስተሰሜን በሚገኙ አካባቢዎችም የ19 ፍልስጤማውያን አስክሬኖችን ማግኘታቸውን ተናግረዋል። የእስራኤል ታንኮች አሁንም ከመጠለያ ጣቢያው በስተምዕራብ መኖራቸውን የገለጸው የፍልስጤም የሲቪል የአደጋ ጊዜ አገልግሎት፣ ቡድኑ ከዛ አካባቢ ለሚደርሰው የእርዳታ ጥሪዎች ምላሽ ለመስጠት አለመቻላቸውንም ጨምሮ ገልጿል፡፡ ጥቃቱን አስመልክቶ በእስራኤል ጦር በኩል እስካሁን የተሰጠ አዲስ ምላሽ ባይኖርም፣ ሠራዊቱ «በጋዛ ሠርጥ ውስጥ የሚያካሄደው ዘመቻ አካል የሆኑ የሽብር ዒላማዎችን መምታቱን» ቀጥሏል ሲል ትላንት ሃሙስ አስታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ባለስልጣናት ባለፉት ወራት በጋዛ ባካሄዱት ጥቃት ይዘዋቸው የነበሩ ሰላሳ ፍልስጤማውያንን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡ የህክምና ባለሙያዎችም የተለቀቁት ሰዎች በደቡባዊ ጋዛ ከሚገኝ ሆስፒታል ለህክምና ምርመራ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል፡፡ በጦርነቱ ወቅት የታሰሩ ፍልስጤማውያን ከእስር ከተፈቱ በኋላ በእስር ወቅት በእስራኤላውያን እንግልት እና የማሰቃየት ተግባር እንደሚፈጸምባቸው ተናግረዋል። እስራኤል ግን ይህንን የማሰቃየት ውንጀላ አትቀበልም፡፡ ለወራቶች በጋዛ የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲደርሰ ሲደረጉ የነበሩ ውይይቶች እምብዛም ለውጥ ያላሳዩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ድርድሮቹ ቆመዋል። በእስራኤል እና የሐማስ አጋር በሆነው የሊባኖሱ ሂዝቦላህ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ከረቡዕ ማለዳ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን፣ ከቅርብ ወራት ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ የነበረውንና የጋዛን ግጭት ሸፍኖት የነበረውን ጦርነት ማስቆም መቻሉ ተገልጿል፡፡

ቻይና 3ሺህ ኪሎሜትር በሚረዝመው ትልቁ በረሃዋ ያካሄደችውን 'የአረንጓዴ መቀነት' ፕሮጀክት ማጠናቀቋን አስታወቀች

ቻይና በረሃማነትን እና ሀገሪቱን ለጉዳት የዳረገውን የአሸዋ አውሎ ነፋስ የመከላከል ብሔራዊ ጥረቷ አካል የሆነውን እና 46 ዓመታትን የፈጀውን፣ በትልቁ የሀገሪ
የአሜሪካ ድምፅ

ቻይና 3ሺህ ኪሎሜትር በሚረዝመው ትልቁ በረሃዋ ያካሄደችውን 'የአረንጓዴ መቀነት' ፕሮጀክት ማጠናቀቋን አስታወቀች

ቻይና በረሃማነትን እና ሀገሪቱን ለጉዳት የዳረገውን የአሸዋ አውሎ ነፋስ የመከላከል ብሔራዊ ጥረቷ አካል የሆነውን እና 46 ዓመታትን የፈጀውን፣ በትልቁ የሀገሪቱ በረሃማ ስፍራ ዛፎችን የመትከል ዘመቻ ማጠናቀቋን የመንግሥት ሚዲያዎች አስታወቁ።  ከዢንጂአንግ ግዛት በስተሰሜን ምዕራብ የተካሄደው እና «አረንጓዴ ቀበቶ» የሚል ስያሜ የተሰጠው 3 ሺህ ኪሎሜትር የሚሸፍነውን በረሃ በዛፎች የመሸፈን ዘመቻ ሐሙስ ዕለት የተጠናቀቀው፣ የመጨረሻው 100 ሜትር ላይ  የዛፍ ተከላ ከተካሄደ በኋላ ነው።  በረሃውን አረንጓዴ ለማድረግ የተደረገው ጥረት የተጀመረው፣ እ.አ.አ በ1978 «የሦስቱ-ሰሜን መጠለያ» ወይም በተለምዶ «ታላቁ አረንጓዴ ግርግዳ» ተብሎ በሚጠራው ፕሮጀክት ነው። ከዛን ጊዜ ጀምሮም ከ30 ሚሊዮን ሄክታር በላይ በሚሆን የበርሃው ክፍል ዛፎች ተተክለዋል።  ደረቅ በነበረው ሰሜን ምዕራብ አካባቢ የተካሄደው ይህ የዛፍ ተከላም፣ ባለፈው አመት መጨረሻ ቻይና አጠቃላይ የደን ሽፋኗን እ.አ.አ በ1949 ከነበረው 10 ከመቶ ወደ፤ ከ25 በመቶ በላይ እንድታሳድግ አስችሏታል።  ሆኖም ተቺዎች፣ ዛፎቹ የመፅደቅ እድላቸው በጣም ዝቅተኛ መሆኑንና በተደጋጋሚ በዋና ከተማዋ ቤጂንግ የሚደርሰውን የአሸዋ አውሎ ነፋስ አደጋን በመቀነስ ረገድ ውጤታማ አለመሆናቸውን ይገልጻሉ።  የዚንጂያንግ የደን ልማት ባለስልጣን ዡ ሊዶንግ ሰኞ እለት በቤጂንግ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ግን፣ ቻይና በረሃማነት ለመከላከል በታክላማካን ዙሪያ እፅዋትን እና ዛፎችን መትከሏን ትቀጥላለች ሲሉ ተናግረዋል።  ቻይና ዛፎችን የመትከል ጥረቶችን ብታደርግም ከአጠቃላይ የመሬቷ ክፍል 26.8 ከመቶ የሚሆነው አሁንም “በረሃማ” መሆኑን ከሀገሪቱ የደን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ሆኖም ከአስር አመት በፊት ከነበረው 27.2 በመቶ አሃዝ ጋር ሲነፃፀር፣ በረሃማነቱ በመጠኑ ዝቅ ማለቱ ተመልክቷል፡፡     

ፑቲን ኪየቭን በአዲስ እጅግ ፈጣን ተውዘግዛጊ ሚሳኤል እንደሚመቱ አስፈራሩ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ዋና ከተማ፣ ኪየቭ የሚገኙትን “የውሳኔ መሰጫ ማዕከላት” ኦርሸኒክ በተሰኙ፣ ከድምፅ የፈጠኑ የሩሲያ ተውዘግዛ
የአሜሪካ ድምፅ

ፑቲን ኪየቭን በአዲስ እጅግ ፈጣን ተውዘግዛጊ ሚሳኤል እንደሚመቱ አስፈራሩ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ዋና ከተማ፣ ኪየቭ የሚገኙትን “የውሳኔ መሰጫ ማዕከላት” ኦርሸኒክ በተሰኙ፣ ከድምፅ የፈጠኑ የሩሲያ ተውዘግዛጊ ሚሳኤሎች እንደሚመቱ ትላንት ዝተዋል። ፑቲን ይህን የተናገሩት በዩክሬን የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት በማድረስ በመላ አገሪቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ለሚኾኑ ሰዎች ኃይል ካቋረጡ በኋላ ነው፡፡ ፑቲን በካዛክ መዲና፣ አስታና ከተማ ትራንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ኦርሽኒክን በሠራዊቱ፣ በወታደራዊ ተቋማት ወይም ኪየቭ የሚገኙትን ጨምሮ በውሳኔ ሰጪ ማዕከላት ላይ ከመጠቀም ወደ ኃላ እንደማይሉ መናገራቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። ሐሙስ እለት በዩክሬን በኃይል አመንጪ መሠረተ ልማቶች ላይ በሰው አልባ አውሮፕላንና በሚሳኤል ጥቃት ያደረሱትም፣ ዩክሬን የዩናይትድ ስቴስን መካከለኛ ርቀት ተተኳሽ ሚሳኤልን ተጠቅማ፣ በሩስያ ላይ ላደረሰችው ጥቃት ምላሽ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህ ጥቃት በዚህ ወር ውስጥ በኃይል መሠረተ ልማት ላይ የደረሰ ሁለተኛው ጥቃት ሲሆን ከመጋቢት ወር ወዲህ ደግሞ አስራ አንደኛው መሆኑን ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው፣ ሞስኮ ተውዘግዛጊ ሚሳኤሎችን እና በአንድ ጊዜ በርካታ ፈንጂዎችን በአየር ላይ የሚጥሉ መሳሪያዎችን በመጠቀም ጦርነቱን «ወደ ከፋ መባባስ» አስገብተውታል ሲሉ ከሰዋል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፑቲን በኪየቭ የመንግስት ማዕከላት ላይ ላነጣጠረ ዛቻቸው ምላሽ እንዲሰጥም፣ ዩክሬን በውጭ ጉዳይ መስሪያቤቷ በኩል ጠይቃለች፡፡ በጥቃቱ ምክንያት የኤለክትሪክ ሃይል ካጡ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ነባሩ የመብራት መቆራረጥ ተባብሶባቸዋል፡፡ ሩሲያ በጥቃቱ 91 ሚሳኤሎችን እና 97 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መጠቀሟን የዩክሬን አየር ሃይል ያስታወቀ ሲሆን ዒላማቸውን ከመቱ አስራ ሁለት ጥቃቶች መካከል አብዛኞቹ በኃይል ተቋማት እና በነዳጅ ማከማቻዎች ላይ ማረፋቸውን፣ እንዲሁም በውሃ አገልግሎት ላይም ተጽዕኖ ማድረሱን ገልጿል፡፡    

ዓዲግራት ከተማ ሁለት ከንቲባ ተሾመባት 

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከትላንት በስቲያ ለዓዲግራት ከተማ «ከንቲባ» የሾመ ሲኾን፣ በዶ.ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ዛሬ
የአሜሪካ ድምፅ

ዓዲግራት ከተማ ሁለት ከንቲባ ተሾመባት 

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከትላንት በስቲያ ለዓዲግራት ከተማ «ከንቲባ» የሾመ ሲኾን፣ በዶ.ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ዛሬ ባካሄደው የምክር ቤት ጉባኤ ደግሞ ሌላ «ከንቲባ» ለከተማዋ መሾሙን አስታውቋል። በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሾሙት አቶ ዓለም አረጋዊ ሲኾኑ፣ በዶ.ር. ደብረጽዮን የተሾሙት ደግሞ አቶ ረዳኢ ገብረእግዚኣብሄር ናቸው። ሁለቱንም ተሿሚዎች አነጋግረናል።

ሦስት በመብት ላይ የሚሠሩ ድርጅቶች መታገድ ትችት አስከተለ

ሁለት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሦስት ታዋቂ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶችን ማገዱን አጥብቀው ተቃወሙ። አምነስቲ
የአሜሪካ ድምፅ

ሦስት በመብት ላይ የሚሠሩ ድርጅቶች መታገድ ትችት አስከተለ

ሁለት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሦስት ታዋቂ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶችን ማገዱን አጥብቀው ተቃወሙ። አምነስቲና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል በተናጥል ባወጧቸው መግለጫዎች፣ በሰብአዊ መብት ዙርያ በሚሠሩ የሲቪል ማኅበራት ላይ የመንግሥት ዛቻና ማስፈራርያ መበርታቱን ተናግረዋል። አምነስቲ መንግሥት እግዱን እንዲያነሳ ጠይቋል። የማዕከል ዋና ዲሬክተር አቶ ያሬድ ሃይለማርያም፣ ድርጅቶቹ ከመታገዳቸው አስቀድሞም ቢኾን በሰብአዊ መብት ዙርያ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበራትና አመራሮቻቸው ላይ በመንግሥት የጸጥታ አካላት ዛቻና ማስፈራርያ ይደርስ እንደነበር ጠቁመዋል። ከኢትዮጵያ መንግሥት ምላሽ አላገኘንም።

ሥራ አቋርጠው የነበሩ የህክምና ባለሞያዎችና ሠራተኞች ወደ ሥራ መመለሳቸውን ገለጹ

በታጠቁ ዘራፊዎች ምክኒያት የደኅንነት ስጋት ስለገባቸው ባለፈው ሳምንት ሰኞ ሥራ ማቆማቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸው የነበሩ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝ ሆስፒታ
የአሜሪካ ድምፅ

ሥራ አቋርጠው የነበሩ የህክምና ባለሞያዎችና ሠራተኞች ወደ ሥራ መመለሳቸውን ገለጹ

በታጠቁ ዘራፊዎች ምክኒያት የደኅንነት ስጋት ስለገባቸው ባለፈው ሳምንት ሰኞ ሥራ ማቆማቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸው የነበሩ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የህክምና ባለሞያዎችና ሠራተኞች ሙሉ ለሙሉ ወደ መደበኛ ሥራቸውን ከተመለሱ አንድ ሳምንት እደኾናቸው ገለጹ። ከዩኒቨርስቲውና ከኮሌጁ አመራሮች ጋራ በተደረገ ውይይት የሆስፒታሉን ጥበቃ ለማጠናከር ስምምነት ላይ በመደረሱ ሥራ መጀመራቸውን ተናግረዋል። ከሆስፒታሉ አመራሮች ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

አዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራውያን ከለላ ጠያቂዎች አፋር ክልል ሊሰፍሩ ነው ተባለ

አዲስ አበባ የሚገኙ ከለላ ጠያቂ ኤርትራውያንን በመመዝገብ፣ አፋር ክልል ውስጥ በሚዘጋጅ መጠለያ ጣቢያ ለማስፈር ማቀዱን የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገ
የአሜሪካ ድምፅ

አዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራውያን ከለላ ጠያቂዎች አፋር ክልል ሊሰፍሩ ነው ተባለ

አዲስ አበባ የሚገኙ ከለላ ጠያቂ ኤርትራውያንን በመመዝገብ፣ አፋር ክልል ውስጥ በሚዘጋጅ መጠለያ ጣቢያ ለማስፈር ማቀዱን የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት አስታወቀ። የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው አዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራውያን፣ ሕጋዊ ሰነድ ማቅረብ ባለመቻላቸው ለእስር መዳረጋቸውን ተናግረዋል። ኤርትራውያን ከለላ ተያቂዎች፣ ለዘፈቀደ እስር መዳረጋቸውን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ከሀገር የመባረር አደጋ እንደተጋረጠባቸውም ጠቁሟል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

VOA60 Africa - At least 30 feared dead after landslides in eastern Uganda

Uganda: The government issued a national disaster alert Thursday after days of heavy rains caused flooding and landslides. Local officials say at least 30 people are feared dead after landslides Wednesday in Masugu village in eastern Bulambuli district.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - At least 30 feared dead after landslides in eastern Uganda

Uganda: The government issued a national disaster alert Thursday after days of heavy rains caused flooding and landslides. Local officials say at least 30 people are feared dead after landslides Wednesday in Masugu village in eastern Bulambuli district.

VOA60 America - Wrongfully detained Americans return from China

Three American citizens imprisoned for years by China have been released. The three were designated by the U.S. government as wrongfully detained. China announced Thursday that the United States had returned four people to China including three Beijing says w
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Wrongfully detained Americans return from China

Three American citizens imprisoned for years by China have been released. The three were designated by the U.S. government as wrongfully detained. China announced Thursday that the United States had returned four people to China including three Beijing says were «wrongfully imprisoned.»

VOA60 World - Israeli military strikes kill at least 17 Palestinians across Gaza Strip

Israeli military strikes killed at least 17 Palestinians across the Gaza Strip on Thursday, medics said, as forces stepped up aerial bombardments on central areas and pushed tanks deeper into the north and south of the enclave.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Israeli military strikes kill at least 17 Palestinians across Gaza Strip

Israeli military strikes killed at least 17 Palestinians across the Gaza Strip on Thursday, medics said, as forces stepped up aerial bombardments on central areas and pushed tanks deeper into the north and south of the enclave.

የማህሙድ አህመድ የስልሳ ዓመታት የሙዚቃ ሕይወት ጉዞ

ገና በአፍላ ዕድሜው ያደረበትን የሙዚቃ ፍቅር ይዞ አደባባይ የወጣው አንጋፋው ድምጻዊ ማህሙድ አህመድ ትውልድ ተሻግረው ዛሬም ድረስ እንደ አዲስ የሚሰሙ ሙዚቃ
የአሜሪካ ድምፅ

የማህሙድ አህመድ የስልሳ ዓመታት የሙዚቃ ሕይወት ጉዞ

ገና በአፍላ ዕድሜው ያደረበትን የሙዚቃ ፍቅር ይዞ አደባባይ የወጣው አንጋፋው ድምጻዊ ማህሙድ አህመድ ትውልድ ተሻግረው ዛሬም ድረስ እንደ አዲስ የሚሰሙ ሙዚቃዎችን እየተጫወተ እዚኽ ደርሷል። የኢትዮጵያን የሙዚቃ ባህል በዓለም አቀፍ የሙዚቃ መድረኮች ማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን፤ ሙዚቃውን የሚጫወቱ ቁጥራቸው የበዙ አውሮፓውያን እና አሜሪካውያን ሙዚቀኞችም አፍርቷል። ዩናይትድ ስቴትስን እና ካናዳን ጨምሮ በአንዳንድ ሀገሮች ዛሬ የሚከበረውን የምስጋና ቀን ክብረ በዓል ምክኒያት በማድረግ፣ በዋሽንግተን እና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን “ለዕድሜ ዘመን አገልግሎትህ፣ በድንቅ ሙዚቃ ሥራዎችህ ለሰጠኽን ደስታ እና ብሎም የባሕል አምባሳደር ሆነህ አገር ላስተዋወቅክበት ውለታህ እናመሰግናለን” ሊሉት ተሰናድተዋል። ማህሙድ እስካኹን ከኖረበት ዕድሜ፣ አብላጫው ያገለገለበትን መድረክ የሚሰናበትበት ይህን ልዩ ዝግጅት ‘አክብረን እንከበር’ የሚል ሥያሜ ሰጥተውታል። አቶ ፍስሃ ወልዴ የሥነ ሥርዐት አስተባባሪ ናቸው። ለዝግጅቱ መነሻ የሆናቸውን አጋጣሚ ጨምረው በመድረኩ የታሰበውን በመጠኑ ያጋሩናል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ጁባላንድ ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋራ ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን አስታወቀች

በሶማሊያ አንድ የፌዴራሉ ዓባል የሆነ ግዛት ከማዕከላዊ መንግሥት ጋራ ያለውን ግንኙነት ማቋረጡን ተከትሎ በሃገሪቱ የሚታየው የፖለቲካ ቀውስ ተባብሷል። በሶ
የአሜሪካ ድምፅ

ጁባላንድ ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋራ ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን አስታወቀች

በሶማሊያ አንድ የፌዴራሉ ዓባል የሆነ ግዛት ከማዕከላዊ መንግሥት ጋራ ያለውን ግንኙነት ማቋረጡን ተከትሎ በሃገሪቱ የሚታየው የፖለቲካ ቀውስ ተባብሷል። በሶማሊያ ከሚገኙ ስድስት የፌዴራሉ ዓባል ግዛቶች ውስጥ አንዷ የሆነችው በደቡብ የምትገኘው ጁባላንድ ከፌዴራል መንግሥቱ ጋራ ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን በይፋ አስታውቃለች፡፡  ይላል የግዛቲቱ ካቢኔ ስብሰባን ተከትሎ ዛሬ ከኪሲማዮ የወጣው መግለጫ፣ “ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋራ ያላትን የሥራ ግንኙነት ማቋረጧን ጁባላንድ ታስታውቃለች” ይላል።  ፑንትላንድም ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ከፌዴራል መንግሥቱ ጋራ ያላትን ግንኙነት ማቋረጧ ይታወሳል። ጁባላንድ መነጠሏን ያስታወቀችው፣ በሞቃዲሹ የሚገኝ ፍርድ ቤት በጁባላንድ መሪ ላይ የመያዢያ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ተከትሎ ነው። መሪዉ አህመድ ሞሃመድ ኢስላም ወይም አህመድ ማዶቤ የሃገሪቱን መረጃ ለውጪ ሃገር አሳልፈው ሠጥተዋል በሚል “የሃገር ክህደት” እና ሕገ መንግስቱን የሚፃረር ተግባር በመፈጸም ክስ ቀርቦባቸዋል። ጁባላንድ ባወጣችው መግለጫ የሶማሊያውን ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ “ሥልጣንን ካለ አግባብ በመጠቀም” ከሳለች፡፡ ፍርድ ቤቱም “ገለልተኝነት ይጎድለዋል”  ብላለች፡፡ ውዝግቡ የጀመረው ባለፈው ወር ሞቃዲሹ ላይ በተካሄደ ብሔራዊ የምክክር ስብሰባ ላይ ነበር። በስብሰባውም የፌዴራል መንግስት እና አንዳንድ ግዛቶች በመጪው ሰኔ 2017 የአካባቢ ምርጫ ለማካሄድ፣ በመስከረም ደግሞ የግዛቶች እና የፓርላማ ምርጫ ለማድረግ ተስማምተው ነበር። የጁባላንዱ መሪ ግን ምርጫውን በዛ ወቅት ለማካሄድ የሥልጣን ዘመንን ማራዘም ይጠይቃል በሚል ተቃውመዋል። አህመድ ማዶቤ በጁባላንድ ባለፈው ሰኞ በግዛቲቱ ፓርላማ በድጋሚ መሪ ሆነው ተመርጠዋል። የፌዴራል መንግስት ግን ድርጊቱን በማውገዝ በድጋሚ መመረጣቸውን እውቅና እንደማይሰጥ አስታውቋል። በሁለቱ ወገኖች መካከል ውጥረቱ ባየለበት ሁኔታ የፌዴራል መንግስቱ ወደ ጁባላንድ ሠራዊቱን ልኳል። በጁባላንድ የአፍሪካ ኅብረት ኃይል አካል የሆኑ የኢትዮጵያ እና የኬንያ ወታደሮች ይገኛሉ።

በዩጋንዳ በተከሰተ የመሬት ናዳ ቢያንስ 30 ሰዎች ሞተዋል ተባለ

በምሥራቃዊ ዩጋንዳ በተከሰተ የመሬት ናዳ ቢያንስ 30 የሚሆኑ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ባለሥልጣናቱ አክለውም የሟቾቹ ቁጥር ከተጠቀ
የአሜሪካ ድምፅ

በዩጋንዳ በተከሰተ የመሬት ናዳ ቢያንስ 30 ሰዎች ሞተዋል ተባለ

በምሥራቃዊ ዩጋንዳ በተከሰተ የመሬት ናዳ ቢያንስ 30 የሚሆኑ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ባለሥልጣናቱ አክለውም የሟቾቹ ቁጥር ከተጠቀሰውም ሊበልጥ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል። ላለፉት ጥቂት ቀናት በሀገሪቱ ከባድ ዝናብ ሲጥል የነበረ ሲሆን፣ ጎርፍ እና የመሬት ናዳ መከሰታቸውን የሚያሳዩ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ መንግሥት ብሔራዊ የአደጋ ማስጠንቀቂያ አውጇል። ከመዲናዋ ካምፓላ የአምስት ሰዓት ርቀት ላይ የምትገኘው ማሱጉ መንደር ትላንት ረቡዕ የመሬት ናዳው ከተከሰተባቸው መንደሮች አንዷ ስትሆን፣ በማኅበራዊ ሚዲያ የተጋሩ ምስሎች የአደጋውን አስከፊነት አሳይተዋል። የወርዳው ኮሚሽነር 30 ሰዎች ኅይወታቸው እንዳለፈ አስታውቀዋል። እስከአሁን የአንድ ሕፃንን ጨምሮ ስድስት አስከሬኖች መገኘታቸውንም ተናግረዋል። የአደጋውን ከባድነትና የሸፈነውን ስፋት በመመልከት በርካታ ሰዎች የደረሱበት እንደማይታወቅና ምናልባትም ናዳው ሥር ተቀብረው ሊሆን እንደሚችልም ስጋታቸውን ገልጸዋል። የዩጋንዳው ቀይ መስቀል ቃል አቀባይ በበኩሉ 13 አስከሬኖችን ማግኘታቸውንና አደጋውም በበርካታ መንደሮች መከሰቱን አስታውቀዋል።

«አቶ ጌታቸው ረዳ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ናቸው» - አቶ አማኑኤል አሰፋ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በእነ ዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራው ቡድን ባካሄደው ጉባኤ ከሥልጣን የተነሱ በመኾናቸው ፕሬዝደን
የአሜሪካ ድምፅ

«አቶ ጌታቸው ረዳ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ናቸው» - አቶ አማኑኤል አሰፋ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በእነ ዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራው ቡድን ባካሄደው ጉባኤ ከሥልጣን የተነሱ በመኾናቸው ፕሬዝደንትነታቸውን እንደማይቀበል፣ በቅርቡ በተካሄደው አወዛጋቢ የህወሓት ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ኾነው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ ተናገሩ። አቶ አማኑኤል ዛሬ መቐሌ ላይ በሰጡት መግለጫ አቶ ጌታቸውን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሲሉ ጠርተዋቸዋል። «የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት እና ወደ ኅበረተሰቡ የማቀላቀል ሥራ፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እየተሠራ አይደለም» ያሉት አቶ አማኑኤል ሂደቱን ተቃውመውታል። አቶ አማኑኤል ዛሬ ረቡዕ ኅዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ለብዙኀን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ህወሓትን በአመፅ ለመበተን ወጣቶች እያሰለጠኑ ናቸው ሲሉ ወንጅለዋል። በጉዳዩ ላይ ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ኮምዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ሆኖም የአስተዳደሩ ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ በቅርቡ፣ በሰጡት መግለጫ፣ በዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመራ የህወሓት ቡድን፣ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ሥራውን እንዳያከናውን ከማድረግ በተጨማሪ የወረዳ ምክር ቤቶች በመጠቀም በመንግሥት የተመደቡ አስተዳዳሪዎች እንዲነሱ እያደረገ ነው ፣ «ይህ መፈንቅለ መንግሥት” ነው » ሲሉ ከሰው ነበር። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ዕድሜ ጠገቡ የኒውዮርክ የምስጋና ቀን ሰልፍ ትዕይንት

አሜሪካውያን  በየዓመቱ አንድ መቶ ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በየዓመቱ በሚዘጋጀው የሜሲስ ምስጋና ቀን የሰልፍ ትዕይንት  ሲደሰቱ ኖረዋል። በነዚህ ዓመታት ውስጥ የ
የአሜሪካ ድምፅ

ዕድሜ ጠገቡ የኒውዮርክ የምስጋና ቀን ሰልፍ ትዕይንት

አሜሪካውያን  በየዓመቱ አንድ መቶ ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በየዓመቱ በሚዘጋጀው የሜሲስ ምስጋና ቀን የሰልፍ ትዕይንት  ሲደሰቱ ኖረዋል። በነዚህ ዓመታት ውስጥ የተቋረጠው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ብቻ ነበር። «ሜሲስ» በተባለው ታዋቂ ግዙፍ መደብር የሚዘጋጀው  ትዕይንት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሸማቾችን «የኛ» በሚል ስሜት ከመደብሩ ጋር ለማስተሳሰር ያለመ ዓመታዊ  በዓል ነው። የቪኦኤ ዘጋቢ ዶራ መኳር በኒው ዮርክ የሰልፉን ዝግጅት ተመልክታለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

ጭቆና እና ጥቃትን ተቋቁመው የሠሩ ጋዜጠኞች እውቅና ተሰጣቸው

ግጭቶችን ለተመለከቱ ዘገባዎች ከመሰማራት አንስቶ እስከ ሕጋዊ እንቅፋቶችና እሥራቶች፣ በመላው ዓለም በፕሬስ ነፃነት ላይ የተደቀነው አደጋ  እየጨመረ መጥቷል
የአሜሪካ ድምፅ

ጭቆና እና ጥቃትን ተቋቁመው የሠሩ ጋዜጠኞች እውቅና ተሰጣቸው

ግጭቶችን ለተመለከቱ ዘገባዎች ከመሰማራት አንስቶ እስከ ሕጋዊ እንቅፋቶችና እሥራቶች፣ በመላው ዓለም በፕሬስ ነፃነት ላይ የተደቀነው አደጋ  እየጨመረ መጥቷል። በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ የሠሩ አራት ጋዜጠኞች ባለፈው ሐሙስ በዓመታዊው ዓለም አቀፍ የፕረስ ነፃነት ሽልማት ላይ  እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ሊያም ስካት ከኒው ዮርክ የላከውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

በአፍሪካ የተፈናቃዮች ቁጥር በሦስት እጥፍ መጨመሩ ተገለጸ

በአፍሪካ የተፈናቃዮች ሰዎች ቁጥር በሦስት እጥፍ መጨመሩን እና 35 ሚሊዮን መድረሱን ዓለም አቀፉ የሀገር ውስጥ ተናቃዮች ተከታታይ ማዕከል ይፋ ያደረገው ዐዲስ
የአሜሪካ ድምፅ

በአፍሪካ የተፈናቃዮች ቁጥር በሦስት እጥፍ መጨመሩ ተገለጸ

በአፍሪካ የተፈናቃዮች ሰዎች ቁጥር በሦስት እጥፍ መጨመሩን እና 35 ሚሊዮን መድረሱን ዓለም አቀፉ የሀገር ውስጥ ተናቃዮች ተከታታይ ማዕከል ይፋ ያደረገው ዐዲስ ሪፖርት አመለከተ። ከእነዚህም ውስጥ ቁጥራቸው 32.5 ሚሊዮን የሚደርሱት በግጭት እና ሁከት ሳቢያ ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ የተገደዱ ናቸው። ትላንት ማክሰኞ የታተመው ሪፖርት አያይዞም፤ በአህጉሪቱ ያለውን በሃገር ውስጥ የመፈናቀል ፈተና ለመፍታት መንግሥታት የሚያደርጉትን ጥረት የሚበረታታ ቢሆንም፤ ‘በቂ አይደለም’ ብሏል። መሀመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ ያደረሰን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ታስረው የነበሩ መምህራን መፈታታቸውን ተናገሩ 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ በእስር ላይ የነበሩና 66 ይኾናሉ የተባሉ መምህራን መፈታታቸውን የዞኑ መምህራን ማኅበር ለአሜሪካ ድምጽ አስታወቀ
የአሜሪካ ድምፅ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ታስረው የነበሩ መምህራን መፈታታቸውን ተናገሩ 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ በእስር ላይ የነበሩና 66 ይኾናሉ የተባሉ መምህራን መፈታታቸውን የዞኑ መምህራን ማኅበር ለአሜሪካ ድምጽ አስታወቀ። የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ከእስር የተለቀቁ መምህራን፣ በእስር ላይ በነበሩበት ወቅት ድብደባ እንደተፈጸመባቸንና ሕክምና ተከልክለው እንደነበር ገለጹ። በኮሬ ዞን የሳርማሌ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ፣ ታሰሩ የተባሉ መምህራን ቁጥር በጣም አነስተኛ እንደነበር ገልጸው፣ «ሁሉም ከእስር ተለቀዋል» ብለዋል። ድብደባ ተፈጸመ የተባለውም ከ«እውነት የራቀ ነው» ብለዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

አፋር ክልል የሚገኙ መምህራን የሥራ ማቆም አድማ ላይ መኾናቸውን ተናገሩ

ክልሉ የተቋረጠ ሥራ የለም ሲል አስተባብሏ በአፋር ክልል ሃሪረሱ ዞን ዳዌ ወረዳ የደሞዝ ክፍያ እንደዘገየባቸውና ጥቅማ ጥቅም እንዳልተከፈላቸው ለአሜሪካ ድ
የአሜሪካ ድምፅ

አፋር ክልል የሚገኙ መምህራን የሥራ ማቆም አድማ ላይ መኾናቸውን ተናገሩ

ክልሉ የተቋረጠ ሥራ የለም ሲል አስተባብሏ በአፋር ክልል ሃሪረሱ ዞን ዳዌ ወረዳ የደሞዝ ክፍያ እንደዘገየባቸውና ጥቅማ ጥቅም እንዳልተከፈላቸው ለአሜሪካ ድምጽ የተናገሩ መምህራን፣ የሥራ ማቆም አድማ ላይ መኾናቸውን ተናገሩ። አድማ የተደረገው በ18 መደበኛ እና ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ባልታወቀ አማራጭ ት/ቤቶች ላይ መሆኑን የወረዳው መምህራን ማኅበር አስታውቋል። ክልሉ መጠነኛ የደመወዝ መዘግየት አጋጥሞት እንደነበር ለቪኦኤ ምላሽ የሰጠው፣ የአፋር ክልል መንግሥት የኮምዩኒኬሽንስ ቢሮ ፣ የወረዳ አመራሮች ከመምህራኑ ጋራ ውይይት ካደረጉ በኋላ የተቋረጠው የማማር ማስተማር እንቅስቃሴ ጥያቄው ከተነሳበት ከኅዳር 16 ቀን 2017ዓ.ም ጀምሮ ቀጥሏል ብሏል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን በተጓዳኝ ሥራዎች ላይ እየተሰማሩ ነው

በደመወዝ አለመከፈል፣ መዘግየትና መቆረጥ የተነሳ ችግር ውስጥ መግባታቸውን ለአሜሪካ ድምጽ የተናገሩ መምህራን፣ ኑሯቸውን ለመደጎም ጫማ መጥረግን ጨምሮ፣ ከ
የአሜሪካ ድምፅ

የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን በተጓዳኝ ሥራዎች ላይ እየተሰማሩ ነው

በደመወዝ አለመከፈል፣ መዘግየትና መቆረጥ የተነሳ ችግር ውስጥ መግባታቸውን ለአሜሪካ ድምጽ የተናገሩ መምህራን፣ ኑሯቸውን ለመደጎም ጫማ መጥረግን ጨምሮ፣ ከዘርፋቸው ውጪ በሆኑ ሌሎች ሥራዎች ላይ እየተሰማሩ መኾኑን ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ። ሦስት ዐዳዲስ ክልሎች ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ፣ ችግሮች እያጋጠሟቸው እንደሚገኙ ያረጋገጠው ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ፣ ችግሩ በበጀት እጥረት ምክንያት የተፈጠረ መኾኑን ለአሜሪካ ድምጽ አስታውቋል። የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበርም በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ መምህራን ችግር ላይ መኾናቸውን ጠቅሶ፣ መፍትሔ ለመፈለግም ከክልሎቹ ኃላፊዎች ጋራ መነጋገሩን አመልክቷል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

አውስትራሊያ አዳጊዎች ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ ልታደርግ ነው

የአውስትራሊያ የተወካዮች ም/ቤት ከ16 ዓመት በታች ያሉ አዳጊዎች ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚያግድ ሕግ አጸደቀ። ሕጉ በመቀጠል በሃገሪቱ የእንደራሴዎች
የአሜሪካ ድምፅ

አውስትራሊያ አዳጊዎች ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ ልታደርግ ነው

የአውስትራሊያ የተወካዮች ም/ቤት ከ16 ዓመት በታች ያሉ አዳጊዎች ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚያግድ ሕግ አጸደቀ። ሕጉ በመቀጠል በሃገሪቱ የእንደራሴዎች ም/ቤት (ሴኔት) ከጸደቀ በዓለም የመጀመሪያው ይሆናል። የተወካዮች ም/ቤቱ በ102 ድጋፍ እና 13 ተቃውሞ ድምጽ አጽድቆታል። በሃገሪቱ የሚገኙ ዋና ፓርቲዎች የደገፉት ሕግ፤ ቲክቶክ፣ ፌስቡክ፣ ስናፕቻት፣ ሬዲት፣ X እና ኢንስታግራም የመሰሉ መድረኮች አዳጊዎች ተጠቃሚ እንዳይሆኑ የማይከላከሉ ከሆነ እስከ 33 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ሕጉ በዚህ ሳምንት በሴኔቱም የሚጸድቅ ከሆነ፣ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎቹ የዕድሜ ገደቡን ተፈጻሚ የሚያደርጉበትን መላ ለመዘየድ አንድ ዓመት ይሰጣቸዋል። ከአንድ ዓመት ጊዜ በኋላ ግን ቅጣቱ ተፈጻሚ ይሆናል። የሃገሪቱ ዋና ዋና ፓርቲዎች ሕጉን በመደገፋቸው፣ በእንደራሴዎች ምክር ቤት  ሊጸድቅ እንደሚችል ይጠበቃል።

Get more results via ClueGoal