የሊቢያ እሥር ቤቶች
newsare.net
ሊቢያ ውስጥ በሚገኙ ማጎሪያ ቤቶች ያሉት በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ያሉበት ሁኔታ ከገሃነመ እሳት የሚቆጠር ነው ሲሉ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃየሊቢያ እሥር ቤቶች
ሊቢያ ውስጥ በሚገኙ ማጎሪያ ቤቶች ያሉት በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ያሉበት ሁኔታ ከገሃነመ እሳት የሚቆጠር ነው ሲሉ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አሳሰቡ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህን ያሳሰቡት የዛሬ ሰባት ዓመት በዛሬዋ ዕለት ስደተኞች ከሰሜን አፍሪካ በስቃይ ጉዞ አውሮፓ የሚደርሱባትን የጣሊያኑዋን ደሴት ላምፔዱሳን የጎበኙበትን ዕለት ምክንያት በማድረግ ነው። በጉብኝታቸው ከስደተኞች ጋር የተነጋገሩ ሲሆን የእሥር ካምፖቹ እንዲዘጉ ተማጽኖ አሰምተዋል፤ ስለስደተኞች ስቃይ የሰፈነው ዓለምቀፍ ደንታ ቢስነት ይቁም ሲሉ መማጸናቸው ይታወሳል። Read more