Ethiopia



VOA60 Africa - Kenya's deputy president pleads not guilty in impeachment process

The house last week voted to charge Rigathi Gachagua on 11 counts, including abuse of power and corruption

የአማራ ክልል ግጭት ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ማስከተሉ ተገለፀ

ከአንድ ዓመት በላይ የቀጠለው የአማራ ክልል ግጭት ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት ማስከተሉን ጥናት ማመልከቱን የክልሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም አስታውቋል። ፎ
የአሜሪካ ድምፅ

የአማራ ክልል ግጭት ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ማስከተሉ ተገለፀ

ከአንድ ዓመት በላይ የቀጠለው የአማራ ክልል ግጭት ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት ማስከተሉን ጥናት ማመልከቱን የክልሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም አስታውቋል። ፎረሙ ይሄንን ያስታወቀው፣«የሰብዓዊ ምላሽ ስልት በግጭት በተጎዱ የአማራ ክልል አካባቢዎች» በሚል ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር ባዘጋጀው እና ትላንት ይፋ ባደረገው ሰነድ ነው። ሰነዱ አክሎም “ግጭቱን ተከትሎ በድምሩ ከ 15 ሺህ በላይ ሰዎች የሞት፣ የመቁሰል፣ የአዕምሮና ማሕበራዊ ቀውስ እንደዚሁም የፆታዊ ጥቃት ሰለባ ሆነዋል” በማለት ጠቅሷል። የፎረሙን ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ታፈረ መላኩን ዘጋቢያችን አነጋግራለች።

«የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪው፣ በኑሯችን ላይ ጫና ይፈጥራ» የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች

“በአዲስ አበባ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው፣ አዲሱ የትራንስፖርት ክፍያ ጭማሪ፣ ኑሯችንን ያከብደዋል” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ አን
የአሜሪካ ድምፅ

«የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪው፣ በኑሯችን ላይ ጫና ይፈጥራ» የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች

“በአዲስ አበባ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው፣ አዲሱ የትራንስፖርት ክፍያ ጭማሪ፣ ኑሯችንን ያከብደዋል” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡ ስለ ጉዳዩ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡ አንድ የኢኮኖሚ ባለሙያ ደግሞ፣ የትራንስፖርት ክፍያን ጨምሮ፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየጨመሩ ያሉት የአገልግሎት ክፍያዎች፣ በተለይም የታችኛውን የህብረተሰብ ክፍል ኑሮ እንደሚጎዱ ገልፀዋል፡፡ መንግስት፣ ኑሮን የሚያረጋጉ እና ጫናውን ለመቋቋም የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንዲወስድም ባለሙያው ጠይቀዋል፡፡ ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ምላሽና አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻ ሽያጭ ዛሬ መጀመሩን ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አስታወቁ  

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻ ሽያጭ  ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል አስጀምረዋል ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአክሲዮን ሽ
የአሜሪካ ድምፅ

የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻ ሽያጭ ዛሬ መጀመሩን ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አስታወቁ  

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻ ሽያጭ  ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል አስጀምረዋል ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአክሲዮን ሽያጭ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ በቀጣይነት ኢትዮቴሌኮምን ጨምሮ የሌሎች ኩባንያዎች የድርሻ ሽያጭ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፣ ለህዝብ የሚሸጠው በድምሩ ወደ 30 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለውን 100 ሚሊዮን አክሲዮን እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ የአንድ አክሲዮን ዋጋ 300 ብር ሲሆን፣ መግዛት የሚቻለው ከ33 እስከ 3 ሺህ 333  እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

በቦንብ ፍንዳታ ሕይወታቸው ያለፈው የደሴ ፍ/ቤት ዳኛ ቀብር ተፈጸመ

ከትላንት በስቲያ ሰኞ ፣ ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ሲያሽከረክሩት በነበረው መኪና ላይ በፈነዳ ቦንብ ሕይወታቸው ማለፉ በፖሊስ የተገለጸው፣ የደሴ ከተማ አስተዳደር
የአሜሪካ ድምፅ

በቦንብ ፍንዳታ ሕይወታቸው ያለፈው የደሴ ፍ/ቤት ዳኛ ቀብር ተፈጸመ

ከትላንት በስቲያ ሰኞ ፣ ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ሲያሽከረክሩት በነበረው መኪና ላይ በፈነዳ ቦንብ ሕይወታቸው ማለፉ በፖሊስ የተገለጸው፣ የደሴ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ዳኛ ሙሉጌታ ከበደ ቀብር ሥነ- ሥርዓት ትላንት መፈፀሙን ወዳጆቻቸው ገለፁ። ጥቃቱ በማን እንደተፈፀመ እስካኹን አለመታወቁን ፖሊስ ገለጿል።

VOA60 World - At least 140 people killed in tanker explosion in Nigeria

Nigeria: At least 140 people, including children, were killed and dozens were injured in the in northern Jigawa State after an overturned gasoline tanker truck exploded in flames while they were trying to scoop up fuel pouring from the vehicle, emergency serv
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - At least 140 people killed in tanker explosion in Nigeria

Nigeria: At least 140 people, including children, were killed and dozens were injured in the in northern Jigawa State after an overturned gasoline tanker truck exploded in flames while they were trying to scoop up fuel pouring from the vehicle, emergency services said Wednesday.

VOA60 America - US tells Israel to increase humanitarian aid reaching Gaza or risk weapons funding

The Biden administration has warned Israel that it must increase the amount of humanitarian aid reaching Gaza within the next 30 days, or it could risk losing access to U.S. weapons funding.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - US tells Israel to increase humanitarian aid reaching Gaza or risk weapons funding

The Biden administration has warned Israel that it must increase the amount of humanitarian aid reaching Gaza within the next 30 days, or it could risk losing access to U.S. weapons funding.

እስራኤል በሌባኖስ ባደረሰችው የአየር ጥቃት 21 ሞቱ

እስራኤል በሌባኖስ በርካታ ቦታዎች ባደረገችው የአየር ድብደባ ቢያንስ 21 ሰዎች መሞታቸውን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል። በደቡብ ሌባኖስ በእስራኤል
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል በሌባኖስ ባደረሰችው የአየር ጥቃት 21 ሞቱ

እስራኤል በሌባኖስ በርካታ ቦታዎች ባደረገችው የአየር ድብደባ ቢያንስ 21 ሰዎች መሞታቸውን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል። በደቡብ ሌባኖስ በእስራኤል ድብደባ ከተገደሉት ውስጥ የከተማዋ ከንቲባ እንደሚገኙበት ታውቋል። ድብደባው የዕርዳታ ሥራዎችን ለማስተባበር የተሰየመ ስብሰባ ላይ የነበሩ ሰዎችን መምታቱን የሌባኖስ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። እስራኤል  በማዘጋጃ ቤቱ ሲካሄድ የበረውንና በዕርዳታ ማስተባበር ላይ ያተኮረውን ስብሰባ “ሆን ብላ ኢላማ አድርጋለች” ሲሉ የሌባኖስ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ሚካቲ ክስ አሰምተዋል። ትላንት ምሽት ደቡባዊዋን የቃና ከተማ የመታውን የአየር ድብደባ በተመለከተ እስራኤል ያለችው የለም። እ.አ.አ በ1996፣ ከ28 ዓመታት በፊት፣ እስራኤል በቃና ከተማ በሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ቅጥር ግቢ ላይ በፈጸመችው የከባድ መሣሪያ ድብደባ የተ መ ድ የሠላም አስከባሪ ኃይሎችን ጨምሮ ቢያንስ 100 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል። በርካቶችም ቆስለዋል።

የኬንያ ምክትል ፕሬዝደንት የቀረበባችውን ክስ አስተባበሉ

የኬንያ ምክትል ፕሬዝደንት ሪጋቲ ጋቻጉዋ ሙስናን ጨምሮ ፈፀሙ በተባለው ወንጀል ዛሬ በሃገሪቱ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት ቀርበው ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።
የአሜሪካ ድምፅ

የኬንያ ምክትል ፕሬዝደንት የቀረበባችውን ክስ አስተባበሉ

የኬንያ ምክትል ፕሬዝደንት ሪጋቲ ጋቻጉዋ ሙስናን ጨምሮ ፈፀሙ በተባለው ወንጀል ዛሬ በሃገሪቱ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት ቀርበው ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል። ምክትል ፕሬዝደንቱ “በመንግሥት ላይ ለተደረጉት የተቃውሞ ሰልፎች ድጋፍ ሰጥተዋል፣ ሙስና ፈጽመዋል እንዲሁም በጎሳዎች መካከል ክፍፍል ለመፍጠር ሞክረዋል” የሚል ውንጀላ ቀርቦባቸዋል። ሪጋቲ ጋቻጉዋ ክሱ ፖለቲካዊ መሆኑን አመልክተዋል። በኬንያ በወንጀል ተጠያቂ የሚሆኑ የመጀመሪያው ምክትል ፕሬዚደንት ሊያደርጋቸው ይችላል ተብሏል። ክሱ በተጨማሪም በእርሳቸውና በፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ መካከል ያለውን መልካም ያልሆነ ግንኙነት ያመለከታል ተብሏል። ሩቶ የኡሁሩ ኬንያታ ምክትል በነበሩበት ጊዜ ተመሳሳይ የሆነ አለመግባባት ውስጥ የነበሩ ሲሆን፣ ወደ ፕሬዚደንትንነት ሥልጣን ከመጡ በኋላ ተመሳሳይ ችግር እንደማይፈጠር ቃል ገብተው ነበር። ፓርላማው ክሱን መስማት እንዲቀጥል ፍርድ ቤት በመወሰኑ፣ ፓርላማው በመስማማት ጉዳዩን ወደ ሕግ መወሰኛው ም/ቤት (ሴኔት) አስተላልፏል።

በናይጄሪያ የነዳጅ ቦቴ ተገልብጦ በመቃጠሉ በርካቶች ሞቱ

በሰሜን ናይጄሪያ አንድ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ተገልብጦ በመፈንዳቱ አንድ መቶ የሚሆኑ ሰዎች ሲሞቱ 50 የሚሆኑ ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሷል። አብዛኞቹ ሰዎች ሕይወታ
የአሜሪካ ድምፅ

በናይጄሪያ የነዳጅ ቦቴ ተገልብጦ በመቃጠሉ በርካቶች ሞቱ

በሰሜን ናይጄሪያ አንድ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ተገልብጦ በመፈንዳቱ አንድ መቶ የሚሆኑ ሰዎች ሲሞቱ 50 የሚሆኑ ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሷል። አብዛኞቹ ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡት ከተገለበጠው ቦቴ ላይ ከሚፈሰው ነዳጅ በመውሰድ ላይ ሳሉ ቦቴው በእሳት ተያይዞ በመፈንዳቱ ነው። የነዳጅ ቦቴው ከሌላ ተሽከርካሪ ጋራ እንዳይጋጭ  ለመራቅ ሲሞክር  መገልበጡን ፖሊስ አመልክቷል።  94 ሰዎች መሞታቸው መረጋገጡንና እንዲሁም 50 የሚሆኑ መጎዳታቸውን ፖሊስ ጨምሮ አስታውቋል። ቦቴው መገልበጡን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች ከሚፈሰው ነዳጅ ላይ ለመውሰድ ጥረት ሲያደርጉ ፖሊስ ለመከላከል ቢሞክርም ከአቅም በላይ እንደሆነበት ተመልክቷል። በአስክፊ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ በምትገኘው ናይጄሪያ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። በነዳጅ አመላላሽ ቦቴዎች ላይ በተደጋጋሚ አደጋ የሚስተዋል ሲሆን፣ ባለፈው ወር አንድ የነዳጅ አመላላሽ ከሕዝብ ማመላለሻ ጋራ ተጋጭቶ 59 ሰዎች ሞተዋል።

እንግሊዝ በሶማሊያ ለተሰማራው ልዑክ ተጨማሪ ገንዘብ መደበች

እንግሊዝ በሶማሊያ ለተሰማራው የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ልዑክ ተጨማሪ 10 ሚሊዮን ዶላር መመደቧን አስታውቃለች፡፡ የእንግሊዝ መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ
የአሜሪካ ድምፅ

እንግሊዝ በሶማሊያ ለተሰማራው ልዑክ ተጨማሪ ገንዘብ መደበች

እንግሊዝ በሶማሊያ ለተሰማራው የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ልዑክ ተጨማሪ 10 ሚሊዮን ዶላር መመደቧን አስታውቃለች፡፡ የእንግሊዝ መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ተጨማሪ ድጋፉ ባለፉት ሦስት ዓመታት ለአትሚስ እና አሚሶም የተሰጠውን ገንዘብ መጠን 100 ሚሊዮን ዶላር ያደርሰዋል። “አትሚስ የሶማሊያን ፀጥታ፣ ቁልፍ ሥፍራዎችንና የአቅርቦት ሰንሰለቶችን እንዲሁም መሠረት ልማቶችን በማስጠበቅ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል” ብሏል የእንግሊዝ መንግሥት በመግለጫው። “የሶማሊያ ብሔራዊ ሠራዊት ከሌሎች ጋራ በመተባበር ለሚያካሂደው ዘመቻ፣ የሰብዓዊ ዕርዳታን ለማሳለጥ፣ ምርጫና የፖለቲካ ሂደቶችን በሰላም እንዲከናወኑ ለማስቻል የሚደረገውን ጥረት የእንግሊዝ መንግሥት መደገፉን ይቀጥላል” ሲል አክሏል መግለጫው። ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ጂቡቲ፣ ዩጋንዳ፣ እና ቡሩንዲ በሶማሊያ ለተሰማራው የኅብረቱ ልዑክ ወታደሮቻቸውን አሰማርተዋል። ‘የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍና የማረጋጋት ልዑክ የተሰኘ አዲስ ኃይል በመጪው ጥር ሥራውን ከአትሚስ እንደሚረከብ ይጠበቃል፡፡ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋራ የተፈራረመችውን የመግባቢያ ሥምምነት ተከትሎ በተነሳው ቅሬታ ምክንያት በአዲሱ ልዑክ ውስጥ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍ እንደማትፈልግ ሶማሊያ አስታውቃለች፡፡

ኢትዮጵያውያን ታዋቂ እንስቶች የከበሩበት ምሽት

በስፖርት ስነ ጥበብና ስራ ፈጠራ ዘርፎች በሙያቸው ማህበረሰብን የጠቀሙ አፍሪካውያንን የሚሸልመው የዘንድሮው የአፍሪካ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ሽልማት ስነ ስርዓት
የአሜሪካ ድምፅ

ኢትዮጵያውያን ታዋቂ እንስቶች የከበሩበት ምሽት

በስፖርት ስነ ጥበብና ስራ ፈጠራ ዘርፎች በሙያቸው ማህበረሰብን የጠቀሙ አፍሪካውያንን የሚሸልመው የዘንድሮው የአፍሪካ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ሽልማት ስነ ስርዓት በሜሪላንድ ተካሂዷል:: ታዋቂዋ የዘመናዊ ሙዚቃ አቀንቃኟ አስቴር አወቀና ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩን ጨምሮ አምስት ኢትዮጵያውያትም የዘንድሮው ተሸላሚ ሁነዋል፡፡  ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ለፍልስጤም ነፃነት ህዝባዊ ግንባር ገንዘብ ያሰባስባል ባለችው 'የይስሙላ የበጎ አድራጎት ድርጅት' ላይ ማዕቀብ ጣለች

ዩናይትድ ስቴትስ ህዝባዊ ግንባር ለፍልስጤም ነጻነት (ፒኤፍኤልፒ) ለተባለው ፣ ዋሺንግተን በሽብርተኝት ለፈረጀችው ተቋም፣ ቁልፍ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማሰባሰ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩናይትድ ስቴትስ ለፍልስጤም ነፃነት ህዝባዊ ግንባር ገንዘብ ያሰባስባል ባለችው 'የይስሙላ የበጎ አድራጎት ድርጅት' ላይ ማዕቀብ ጣለች

ዩናይትድ ስቴትስ ህዝባዊ ግንባር ለፍልስጤም ነጻነት (ፒኤፍኤልፒ) ለተባለው ፣ ዋሺንግተን በሽብርተኝት ለፈረጀችው ተቋም፣ ቁልፍ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማሰባሰብያ ነው ባለችው አውታር ላይ ማዕቀብ ጣለች። የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት፣ ከካናዳ ጋር በወሰደው እርምጃ፣ ለፒኤፍኤልፒ ድርጅት «ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማሰባሰብያ ሆኖ የሚያገለግል የይስሙላ በጎ አድራጎት ድርጅት” ሲል በከሰሰው የሳሚዶውን የፍልስጤም እስረኞች አንድነት አውታረ መረብ ላይ ማዕቀብ ጥሏል። ጋዛ ውስጥ ከእስራኤል ጋር በተደረገው ውጊያ ላይ የተሳተፈው ህዝባዊ ግንባር ለፍልስጤም ነጻነት የውጭ አሸባሪ ድርጅት እንዲሁም እና በልዩ ሁኔታ የተበየነ ዓለም አቀፍ አሸባሪ በሚል በጥቅምት 1997 እና በጥቅምት 2001 ዓመተ ምህረት በዩናይትድ ስቴትስ ተፈርጇል። የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤቱ “ፒኤፍኤልፒ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ ገንዘብ ለማሰባሰብ ሳሚዶን አውታርን ይጠቀማል” ብሏል። የቡድኑ እንቅስቃሴ ባለፈው ዓመት በጀርመን ታግዶ ነበር። “እንደ ሳሚዶን ያሉ ድርጅቶች ለተቸገሩት ሰብዓዊ ድጋፍ እናደርጋለን የሚሉ የበጎ አድራጎት ተቋማት ቢመስሉም ፣በእጅጉ አስፈላጊ የሆነውን የገንዘብ ድጋፍ አሸባሪዎችን ለማገዝ ያውሉታል» ሲሉ፣ የግምጃ ቤቱ የሽብርተኝነት እና ፋይናንስ ደህንነት ተጠባባቂ ጸሐፊ ብራድሊ ስሚዝ በመግለጫቸው ላይ አስታውቀዋል። የሳሚዶን የፍልስጤም እስረኞች አንድነት አውታረ መረብ አስተያየት እንዲሰጥ ከሮይተርስ ላቀረበለት ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም ።

በደራ ወረዳ “በቀጠለው ግጭት ሰባት ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል” ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

በኦሮሚያ ክልል ፣ሰሜን ሸዋ ዞን፣ደራ ወረዳ፣በመንግሥት ኃይሎችና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እንደዚሁም በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከመስከረ
የአሜሪካ ድምፅ

በደራ ወረዳ “በቀጠለው ግጭት ሰባት ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል” ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

በኦሮሚያ ክልል ፣ሰሜን ሸዋ ዞን፣ደራ ወረዳ፣በመንግሥት ኃይሎችና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እንደዚሁም በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከመስከረም 27 ቀን 2017 ዓ/ም በቀጠለው ግጭት ሰባት ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል። ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት እነዚሁ ነዋሪዎች እንዳሉት የሟቾቹ አስከሬን የተገኘው ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ/ም. ነው። የአሜሪካ ድምፅ ስለጉዳዩ ካነጋገራቸው ሁለት የዞንና የወረዳ ባለስልጣናት አንዱ “ምንም ውጊያ የለም” በማለት ሲያስተባብሉ፣ ሌላው በበኩላቸው ወረዳው “ከፀጥታ ችግር ውጭ ሆኖ አያውቅም” ብለዋል።

መንግሥት በኮሬ ዞን የቀጠለውን ጥቃት እንዲያስቆም ጥሪ ቀረበ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ኮሬ ዞን፣ ጎርካ ወረዳ፣ ከረዳ እና ዳኖ ቀበሌዎች፣ ባለፈው እሁድና ሰኞ ጠዋት በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት አምስት ሰዎች ተገድለዋል ሲ
የአሜሪካ ድምፅ

መንግሥት በኮሬ ዞን የቀጠለውን ጥቃት እንዲያስቆም ጥሪ ቀረበ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ኮሬ ዞን፣ ጎርካ ወረዳ፣ ከረዳ እና ዳኖ ቀበሌዎች፣ ባለፈው እሁድና ሰኞ ጠዋት በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት አምስት ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ ነዋሪዎችና የተጎጂ ቤተሰቦች ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቁ። የዞኑ የሰላም እና የፀጥታ መምሪያም የሰዎቹን መገደል ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጦ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርጓል። ከአካባቢው የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች በበኩላቸው መንግሥት በኮሬ ዞን የቀጠለውን ጥቃት እንዲያስቆም ጥሪ አቅርበዋል ። ከጥቃቱ ጋር ስሙ ከተነሳው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከዚህ በፊት ለተመሳሳይ ውንጀላ በሰጠው ምላሽ ታጣቂዎቹ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ እንደማያደርጉ በመግለፅ ውንጀላውን አስተባብሏል።

የአፍሪካ መከላከያ ሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ ተጀምሯል

የአፍሪካ መከላከያ ሚኒስትሮች በአዲስ አበባ ስለአህጉሪቱ ሰላምና ፀጥታ በመወያየት ላይ ናቸው፡፡ ለአህጉሪቱ የመከላከያ ሚኒስትሮች የመጀመሪያ መሆኑ የተነ
የአሜሪካ ድምፅ

የአፍሪካ መከላከያ ሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ ተጀምሯል

የአፍሪካ መከላከያ ሚኒስትሮች በአዲስ አበባ ስለአህጉሪቱ ሰላምና ፀጥታ በመወያየት ላይ ናቸው፡፡ ለአህጉሪቱ የመከላከያ ሚኒስትሮች የመጀመሪያ መሆኑ የተነገረውን ይህን ስብሰባ ኢትዮጵያ እንዳዘጋጀች ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ አፍሪካ በውስብስብ የፀጥታ ችግር ዉስጥ መሆኗን ተናግረዋል። የስብሰባው ተሳታፊዎች በተለይ የአፍሪካ ተጠባባቂ ሠራዊት ኃይል ትግበራ ወደ ኋላ መጎተት፣ አገራት “በአህጉሪቱ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ወደ ውጭ እንዲመለከቱ አድርጓል” ይላሉ፡፡

ወደ ሪፐብሊካኖች ታጋድል የነበረችው አሪዞና እንዴት ዋዣቂ 'ስዊንግ ስቴት' ልትሆን ቻለች?

ዩናይትድ ስቴትስ 50 ግዛቶች ቢኖራትም፣ ብርቱ ፍልሚያ የሚደረግባቸው ሰባቱ ግዛቶች እ.አ.አ በ2024 የሚካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ይወስናሉ ተብሎ ይጠበቃ
የአሜሪካ ድምፅ

ወደ ሪፐብሊካኖች ታጋድል የነበረችው አሪዞና እንዴት ዋዣቂ 'ስዊንግ ስቴት' ልትሆን ቻለች?

ዩናይትድ ስቴትስ 50 ግዛቶች ቢኖራትም፣ ብርቱ ፍልሚያ የሚደረግባቸው ሰባቱ ግዛቶች እ.አ.አ በ2024 የሚካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ይወስናሉ ተብሎ ይጠበቃል። በደቡብ ምዕራብ አሜሪካ የምትገኘው አሪዞና ለረጅም ጊዜ ሪፐብሊካኖችን ስትመርጥ የቆየች ቢሆንም እ.አ.አ በ2020 በተደረገው ምርጫ ዲሞክራቱ ጆ ባይደን አሸንፈዋል። ዘንድሮም የግዛቷን መራጮችድምፅ ለማሸነፍ ብርቱ ፉክክር ይደረጋል። የአሜሪካ ድምጿ ዶራ ሜክዋር በዚህ ዙሪያ ያደረሰችንን ዘገባ፣ ስመኝሽ ወደ አማርኛ መልሳዋለች።  

መወሰን ያልቻሉ ድምፅ ሰጪዎች በፕሬዝደንታዊ ምርጫው ላይ ያላቸው ተጽእኖ

በአሜሪካ፤ ፕሬዝደንታዊው ምርጫ ከወር ያነሰ ጊዜ በቀረው በዚህ ወቅት፣ ዶናልድ ትረምፕ እና ካመላ ሄሪስ፣ እስከ አሁን የትኛውን ወገን መምረጥ እንዳለባቸው ያ
የአሜሪካ ድምፅ

መወሰን ያልቻሉ ድምፅ ሰጪዎች በፕሬዝደንታዊ ምርጫው ላይ ያላቸው ተጽእኖ

በአሜሪካ፤ ፕሬዝደንታዊው ምርጫ ከወር ያነሰ ጊዜ በቀረው በዚህ ወቅት፣ ዶናልድ ትረምፕ እና ካመላ ሄሪስ፣ እስከ አሁን የትኛውን ወገን መምረጥ እንዳለባቸው ያልወሰኑትን እና አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን አሜሪካውያን ትኩረት ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው። የቪኦኤው ስካት ስተርንስ እነዚህን እስከ አሁን መወሰን ያልቻሉ ድምፅ ሰጪዎች ሁኔታ ያስቃኘናል። እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።

VOA60 Africa - Kenya relocates 50 elephants to larger park

A landmark operation has begun to relocate 50 elephants from the overcrowded Mwea National Reserve to the more spacious Aberdare National Park, in a bid to ease environmental pressure and reduce human-wildlife conflict.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Kenya relocates 50 elephants to larger park

A landmark operation has begun to relocate 50 elephants from the overcrowded Mwea National Reserve to the more spacious Aberdare National Park, in a bid to ease environmental pressure and reduce human-wildlife conflict.

VOA60 America - Dozens of pro-Palestinian protesters arrested outside New York Stock Exchange

Police in New York City arrested more than 200 pro-Palestinian demonstrators who had staged a sit-in outside the New York Stock Exchange Monday, protesting the war in Gaza. The protesters demanded an end to U.S. support for Israel.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Dozens of pro-Palestinian protesters arrested outside New York Stock Exchange

Police in New York City arrested more than 200 pro-Palestinian demonstrators who had staged a sit-in outside the New York Stock Exchange Monday, protesting the war in Gaza. The protesters demanded an end to U.S. support for Israel.

VOA60 World - Over 8.5 million people affected by Central and West African floods

Residents of Chad, Mali, and Niger waded through flood waters or used boats along submerged streets in recent weeks. They are among 6.6 million people affected by West and Central Africa’s monsoon. Over 8.5 million people were affected across 20 countries
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Over 8.5 million people affected by Central and West African floods

Residents of Chad, Mali, and Niger waded through flood waters or used boats along submerged streets in recent weeks. They are among 6.6 million people affected by West and Central Africa’s monsoon. Over 8.5 million people were affected across 20 countries, according to the U.N. aid agency OCHA.

ተመድ ፣ እስራኤል በሰሜን ሊባኖስ የመኖሪያ ሕንፃ ላይ በፈጸመችው ጥቃት ዙሪያ ምርመራ እንዲካሄድ አሳሰበ

በሰሜን ሊባኖስ ቢያንስ 22 ሰዎችን በገደለው የእስራኤል የአየር ጥቃት ላይ ምርመራ እንዲካሄድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ቢሮ ዛሬ ማክሰኞ ጥ
የአሜሪካ ድምፅ

ተመድ ፣ እስራኤል በሰሜን ሊባኖስ የመኖሪያ ሕንፃ ላይ በፈጸመችው ጥቃት ዙሪያ ምርመራ እንዲካሄድ አሳሰበ

በሰሜን ሊባኖስ ቢያንስ 22 ሰዎችን በገደለው የእስራኤል የአየር ጥቃት ላይ ምርመራ እንዲካሄድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ቢሮ ዛሬ ማክሰኞ ጥሪ አድርጓል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት  ቢሮ ቃል አቀባይ ጄርሚ ሎሬንስ በጄኔቫ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በ«አይቶ»  መንደር በሰኞ ዕለቱ ጥቃት ከተገደሉት መካከል 12 ሴቶች እና 2 ህጻናት እንደሚገኙበት  ተቋማቸው መረጃዎች እንደደረሱት አስታውቀዋል። «ጥቃት የደረሰበት ባለ አራት ፎቅ የመኖሪያ ህንጻ መሆኑን ተረድተናል ። እነዚህን ነገሮች በአእምሯችን ይዘን፣ የጦርነት ሕጎች፣ የልዩነት እና ተመጣጣኝነት መርሆዎችን  ከሚመለከተው  ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ጋር በተያያዘ ተጨባጭ  ስጋቶች አሉን »  ብለዋል። ይህ በእንዲህ እያለ ፣ ከሊባኖስ ወደ እስራኤል የተወነጨፉትን  በርካታ ተተኮሾች የሀገሪቱ የአየር መቃወሚያ ባመከነበት  አፍታ ፣  በሀይፋ ክልል የአደጋ ጊዜ ማንቂያ ደወል  እንዲሰማ እንደተደረገ  የእስራኤል ጦር አስታውቋል።   የእስራኤል መከላከያ ኃይሎች ፣  በደቡብ ሊባኖስ በሚገኙ የሂዝቦላ ኢላማዎች ላይ ባደረሱት  የአየር ድብደባ  በርካታ ተዋጊዎችን እንደገደሉ ይፋ አድርገዋል።  የእስራኤሉ ጠቅላይ  ሚኒስትር ቤኒጃሚን ኔትኒያሁ  ሰኞ ዕለት ፣ « (እስራኤል) ቤሩትን ጨምሮ ፣ በሁሉም የሊባኖስ ክፍሎች ሂዝቦላህን  ካለ ርህራሄ  ትመታለች» ሲሉ ዝተዋል።  እስራኤል ፣ ኢራን ላይ የምትፈጽመው የአጸፋ ጥቃት ፣የነዳጅ ዘይት ወይም ኒውክሌር ተቋሞች  ላይ ሳይሆን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ብቻ ያነጣጠረ  እንደሚሆን  ኔታንያሁ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እንደተናገሩ ፣  የአሜሪካ ባለስልጣናት  ይፋ አድርገዋል። ባለስልጣናቱን የጠቀሱት ፣ዋሽንግተን ፖስት እና ዎል ስትሪት ጆርናል  ትናንት ሰኞ አመሻሽ ላይ እንደዘገቡት  ፣ ኔታንያሁ ይሄንን  ቃል የገቡት ባለፈው ሳምንት በመሪዎች መካከል በተደረገ የስልክ  ውይይት ላይ ነው። የኔታንያሁ ጽህፈት ቤት ማክሰኞ በሰጠው መግለጫ «የዩናይትድ ስቴትስን አስተያየት እናዳምጣለን ፣ ነገር ግን  የመጨረሻ ውሳኔያችን የምናስተላልፈው  ብሔራዊ ጥቅማችንን  ላይ  መሰረት አድርገን ይሆናል »  ብሏል። ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት ያደረሰችው ፣በእስራኤል እና በሂዝቦላ መካከል በተፈጠረው ግጭት  መባባስን ተከትሎ ፣ በኢራን የሚደገፈው የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን መሪ ሀሰን ናስራላህ ላይ እስራኤል  ለፈጸመችው ግድያ ምላሽ  ነው ። እስራኤል ለኢራን ጥቃት አጸፋ ለመስጠት የዛተች ሲሆን ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እስራኤልን ለመከላከል የአየር መቃዋሚያ ስርዓት እና ስርዓቱን የሚዘውሩ ወታደሮችን እንደምትልክ አስታውቃለች።  ( ቪኦኤ በዚህ ዘገባ ውስጥ ከአሶሼትድ ፕሬስ፣ ከአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እና ከሮይተርስ የተገኙ ግብዓቶች ተጠቅሟል ።)

የስድስተኛው የታላቁ የአፍሪካ ሩጫ ቅኝት

በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ ትውልደ አፍሪካዊያን፣ የአህጉሪቱን የአትሌቲክስ ስኬት እና ታሪክ  እየዘከሩ፣ አብሮነታቸውን ያድሱበት ዘንድ ያለመው
የአሜሪካ ድምፅ

የስድስተኛው የታላቁ የአፍሪካ ሩጫ ቅኝት

በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ ትውልደ አፍሪካዊያን፣ የአህጉሪቱን የአትሌቲክስ ስኬት እና ታሪክ  እየዘከሩ፣ አብሮነታቸውን ያድሱበት ዘንድ ያለመው  ዓመታዊው «ታላቁ የአፍሪካ ሩጫ» በሳምንቱ መገባደጃ በአሌክሳንድሪያ ቨርጂኒያ ተከናውኗል። ከስፖርት መድረክነት ባሻገር ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ሰብዓዊ ተልዕኮዎች ውስጥ ፊት መሪ እንዲሆኑ የሚያበረታታው መርሐ ግብር የተከናወነው ለስድስተኛ ጊዜ ነው።

Get more results via ClueGoal