Ethiopia



የቡድን ሰባት መከላከያ ሚንስትሮች ጉባኤ ተጀመረ

በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ግጭት እየተባባሰ እና የዩክሬን ጦርነት ሦስተኛ ክረምቱን እየያዘ ባለበት በዚህ የውጥረት ወቅት የቡድን ሰባት አባል ሀገራት መከላከ

በምዕራብ ወለጋ ግጭት ውስጥ ያልተሳተፉ ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ፣ በመንግሥት ኃይሎች እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው ግጭት፣ ሲቪ
የአሜሪካ ድምፅ

በምዕራብ ወለጋ ግጭት ውስጥ ያልተሳተፉ ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ፣ በመንግሥት ኃይሎች እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው ግጭት፣ ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ። የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች «ለታጣቂዎቹ ታገለግላላችኹ» ፣ ታጣቂዎቹ ደግሞ «ለመንግሥት ትሠራላችኹ» በሚል ከሁለቱም በኩል ጉዳት እየደረሰባቸው እንደኾነ፣ ለቪኦኤ አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጉዳቱ ደርሶበታል የተባለው፣ የቆንዳላ ወረዳ አስተዳዳር፣ ተገደሉ ስለተባሉ ሲቪሎች መረጃ እንደሌለው አስታውቋል። መንግሥት በሲቪሎች ላይ ጥቃት እንደማያደርስም የወረዳው አስተዳዳሪ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በአካባቢው ይፈፀማል የተባለው ጥቃት ሪፖርት እንደደረሰው አስታውቋል። /ዝርዝርሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

ስፔን ከአፍሪካ የሚመጣውን ፍልሰት እንደ መልካም የኢኮኖሚ አጋጣሚ ትመለከታለች

ለቀኝ ዘመም ወግ አጥባቂ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰጠው ድጋፍ እየጨመረ በመጣበት የአውሮፓ ኅብረት፣ ዓባል ሃገራቱ ፍልሰት እንዲቆም ጥሪ በማድረግ ላይ ናቸው።
የአሜሪካ ድምፅ

ስፔን ከአፍሪካ የሚመጣውን ፍልሰት እንደ መልካም የኢኮኖሚ አጋጣሚ ትመለከታለች

ለቀኝ ዘመም ወግ አጥባቂ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰጠው ድጋፍ እየጨመረ በመጣበት የአውሮፓ ኅብረት፣ ዓባል ሃገራቱ ፍልሰት እንዲቆም ጥሪ በማድረግ ላይ ናቸው። ስፔን ግን ከዚህ በተቃራኒ በመቆም፣ በአውሮፓ ዕድሜያቸው የገፉ አዛውንቶች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ፣ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ቁጥጥር የሚደረግበት ፍልሰት አስፈላጊ ነው ትላለች። ሄንሪ ሪጅዌል ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የአሜሪካ ምርጫ ወጪ 

ሃገራት በምርጫ ወቅት ከፍተኛ ገንዘብ ያወጣሉ። የአሜሪካ የምርጫ ወጪ ከሌሎች ሃገራት ጋራ ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው። ይህንንኑ የተመለከተውን  ገላጭ ዘገባ ከተያ
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ ምርጫ ወጪ 

ሃገራት በምርጫ ወቅት ከፍተኛ ገንዘብ ያወጣሉ። የአሜሪካ የምርጫ ወጪ ከሌሎች ሃገራት ጋራ ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው። ይህንንኑ የተመለከተውን  ገላጭ ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የሠራተኛ ማኅበራት ድጋፍ በዩናይትድ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ያለው ከፍተኛ ሚና

በመላዋ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ14 ሚሊዮን የሚሆኑት መራጮች መብታቸውን ለማስከበር በተቋቋሙ ማኅበራት የተደራጁ ሠራተኞች ናቸው። ከአጠቃላዩ መራጭ ቁጥር አኳያ
የአሜሪካ ድምፅ

የሠራተኛ ማኅበራት ድጋፍ በዩናይትድ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ያለው ከፍተኛ ሚና

በመላዋ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ14 ሚሊዮን የሚሆኑት መራጮች መብታቸውን ለማስከበር በተቋቋሙ ማኅበራት የተደራጁ ሠራተኞች ናቸው። ከአጠቃላዩ መራጭ ቁጥር አኳያ ሲታይ ቁጥራቸው አነስተኛ ቢሆንም ፕሬዚደንታዊ ዕጩ ተፎካካሪዎች ድጋፋቸውን በእጅጉ ይፈልጉታል። የአሜሪካ ድምጿ የምክር ቤታዊ ጉዳዮች ዘጋቢ ካትሪን ጂፕሰን በዘንድሮ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የሠራተኛ ማኅበራት ድምጽ ትልቅ ሚና የሚጫወትባት ከሆነችው ከኔቫዳ ክፍለ ግዛት ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የአይ ኤም ኤፍ እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ

ዓመታዊው የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤም ኤፍ)ና የዓለም ባንክ ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ ተጀምሯል።  ኢትዮጵያን ጨምሮ የአባል ሃገራቱ የገንዘብ ሚንስት
የአሜሪካ ድምፅ

የአይ ኤም ኤፍ እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ

ዓመታዊው የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤም ኤፍ)ና የዓለም ባንክ ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ ተጀምሯል።  ኢትዮጵያን ጨምሮ የአባል ሃገራቱ የገንዘብ ሚንስትሮችና የብሄራዊ ባንክ ገዥዎች የሚሳተፉበት ነው። የኢኮኖሚና ኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ያሬድ ሃይለመስቀል ይህ ጉባኤ የዓለም ኢኮኖሚ በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ጦርነቶች እየተፈተነ ባለበት ወቅት የሚካሄድ ነው ይላሉ። /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/ 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 11 ፓርቲዎችን በጊዜያዊነት አገደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ "በጠቅላላ ጉባኤ፣ በኦዲት እና በሴት አባላት አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋራ በተያያዘ፣ 11 የፖለቲካ ፓርቲዎችን በጊዜያ
የአሜሪካ ድምፅ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 11 ፓርቲዎችን በጊዜያዊነት አገደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ "በጠቅላላ ጉባኤ፣ በኦዲት እና በሴት አባላት አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋራ በተያያዘ፣ 11 የፖለቲካ ፓርቲዎችን በጊዜያውነት ማገዱን ትላንት ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. በጻፈው እና በፌስቡክ ገጹ ይፋ ባደረገው ደብዳቤ አስታውቋል። ቦርዱ የእግድ ውሳኔ ካሳለፈባቸው ፓርቲዎች መካከል የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የጌዲኦ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የሐረዲ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የገዳ ሥርዓት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ፣ የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ የጋምቤላ ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ኅብረት እና አገው ለፍትህና ዲሞክራሲ ፓርቲ ይገኙበታል።  ፓርቲው እግዱን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋር ምክር ቤት በጻፈው በዚሁ ደብዳቤ፣ ቦርዱ የተለየ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ፣ ፓርቲዎቹ ከማንኛውም ሕጋዊ እንቅስቃሴ ታቅበው እንዲቆዩ ትዕዛዝ አስተላልፏል።  በመሆኑም የተዘረዘሩት ፓርቲዎች የተጣለባቸው የእግድ ውሳኔ እስከሚነሳ ድረስ፣ በማናቸውም የጋራ ምክር ቤቱ የሚያዘጋጃቸው ጉባኤዎች ላይ ሊገኙ፣ ሊመርጡ፣ ሊመረጡ ወይም በተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ ሊያገለግሉ እንደማይችሉ ቦርዱ ጨምሮ ገልጿል።  እስካሁን ስማቸው ከተጠቀሰው ፓርቲዎች በኩል የወጣ መግለጫም ሆነ የተሰጠ አስተያየት የለም።

ኡጋንዳ  16 ተቃዋሚዎችን በ’ሀገር ክህደት’ ወነጀለች

የኡጋንዳ ወታደራዊ ፍርድ ቤት «በሕግ ወጥ መንገድ ፈንጂ ይዞ በመገኘት እና የሀገር ክህደት በመፈጸም» በተወነጀሉ 16 የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ በትላንት
የአሜሪካ ድምፅ

ኡጋንዳ  16 ተቃዋሚዎችን በ’ሀገር ክህደት’ ወነጀለች

የኡጋንዳ ወታደራዊ ፍርድ ቤት «በሕግ ወጥ መንገድ ፈንጂ ይዞ በመገኘት እና የሀገር ክህደት በመፈጸም» በተወነጀሉ 16 የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ በትላንትናው እለት የጥፋተኝነት ብይን ማሳለፉን አንድ የተከሳሾች ተከላካይ ጠበቃ አስታወቁ። የችሎቱን ውሳኔም ‘አጠያያቂ’ ብለውታል። አቃቤ ሕግ 16’ቱን የተቃዋሚው ይብሔራዊ አንድነት መድረክ ፓርቲ አባላት እና እስከአሁን  አልተያዙም ያላቸውን ሌሎች ግለሰቦች እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በሕዳር 2020 እና በግንቦት 2021 መካከል ባለው ጊዜ በሃገሪቱ ምርጫ እየተካሄደ ሳለ የተባሉትን ወንጀሎች ‘ፈጽመዋል’ ሲል ነው የከሰሳቸው።   ሻሚም ማሌንዴ የተባሉ የተከሳሾች ተከላካይ ጠበቃ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት፤ «ካሁን ቀደም ወንጀሉን አልፈጸምንም” ሲሉ ክሱን ያስተባበሉት ተከሳሾች አሁን ጥፋተኝነታቸውን አምነዋል የተባለበትን ሁኔታ “አጠያያቂ ነው» ብለውታል። ‘ባቢ ዋይን’ በሚል የመድረክ ስም የሚታወቀው  የቀድሞ ድምጻዊ  ሮበርት ኪያጉላኒ የተባለው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል፤ ቡድኑ ጥፋተኛነቱን አምኖ ፕሬዝዳንታዊ ይቅርታ እንዲጠይቅ መገደዱን ተናግሯል። 16ቱ ተከሳሾች አራት ዓመታት በእስር ላይ የቆዩ ሲሆኑ፤ ነገ ረቡዕ ችሎቱ ዘንድ ይቀርባሉ። ጋዜጠኞች ሥነ ስርአቱን እንዳይከታተሉ ታግደዋል። ምሥራቅ አፍሪቃዊቱ አገር ኡጋንዳ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ1986 አንስቶ በዩዌሪ ሙሴቬኒ ስትመራ መቆየቷ ይታወቃል።  

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያውያንን በእግር ኳስ አንድ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ካፍ አስታወቀ

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ያቀረበችውን ጥያቄ ካፍ እንዲያፀድቀው ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በአዲስ አበባ በተካሔደው የካፍ 46ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላ
የአሜሪካ ድምፅ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያውያንን በእግር ኳስ አንድ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ካፍ አስታወቀ

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ያቀረበችውን ጥያቄ ካፍ እንዲያፀድቀው ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በአዲስ አበባ በተካሔደው የካፍ 46ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ጠየቁ።  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “ኢትዮጵያውያንን በእግር ኳስ አንድ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው” የተናገሩት የካፍ ፕሬዝደንት ፓትሪስ ሞትሴፔ፣ የኢትዮጵያ ጥያቄ በካፍ አሠራር መሰረት ታይቶ ምላሽ እንደሚሰጠው ተናግረዋል፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በመጪው 2029 ዓ.ም. የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት 13 አገራት መጠየቃቸውንም አስታውቀዋል።  የፊፋ ፕሬዝደንት ጂያኒ እኢንፋንቲኖ በበኩላቸው፣ በፊፋ የዓለም ዋንጫ የሚሳተፉ የአፍሪካ አገራት ቁጥር ከቀጣዩ ውድድር ጀምሮ በእጥፍ እንደሚጨምር፣ በአዲስ አበባው የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል፡፡ /ዝርዝርሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/ 

የኤሌክቶራል ኮሌጅ ሂደት

ኤሌክቶራል ኮሌጅ (Electoral College) የአሜሪካ ዜጎች ፕሬዝዳንታቸውን የሚመርጡበት ሂደት ነው። በስተመጨረሻ አሸናፊውን የሚመስኑት የኤሌክቶራል ኮሌጅ አባላት ናቸ
የአሜሪካ ድምፅ

የኤሌክቶራል ኮሌጅ ሂደት

ኤሌክቶራል ኮሌጅ (Electoral College) የአሜሪካ ዜጎች ፕሬዝዳንታቸውን የሚመርጡበት ሂደት ነው። በስተመጨረሻ አሸናፊውን የሚመስኑት የኤሌክቶራል ኮሌጅ አባላት ናቸው።  ሂደቱ እንዴት እንደሚካሄድ ከተያያዘው መግለጫ ይከታተሉ። 

ለትግራይ ክልል ተረጂዎች ገቢ ማሰባሰብ ተጀመረ

በትግራይ ክልል 4.5 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው፣ «አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ» የተባለ ኮሚቴ አስታወቀ። ኮሚቴው ተጎጂዎቹን
የአሜሪካ ድምፅ

ለትግራይ ክልል ተረጂዎች ገቢ ማሰባሰብ ተጀመረ

በትግራይ ክልል 4.5 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው፣ «አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ» የተባለ ኮሚቴ አስታወቀ። ኮሚቴው ተጎጂዎቹን ለመርዳት ዛሬ ባስጀመረው የገቢ ማሰባሰቢያ 130 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን እና፣ ፌደራል መንግሥቱ 130 ሚሊዮን ብር ለመስጠት ቃል መግባቱ ታውቋል። /ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

በትረምፕ እና ሀሪስ ምርጫ ዘመቻ “የውስጥ ጠላት” እና “ያልተረጋጋ” መባባሉ ተባብሷል

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ልንታገለው የሚገባን «የውስጥ ጠላት» አለን የሚለው ንግግር በተቃዋሚዎቻቸው ውስጥ ትልቅ የ
የአሜሪካ ድምፅ

በትረምፕ እና ሀሪስ ምርጫ ዘመቻ “የውስጥ ጠላት” እና “ያልተረጋጋ” መባባሉ ተባብሷል

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ልንታገለው የሚገባን «የውስጥ ጠላት» አለን የሚለው ንግግር በተቃዋሚዎቻቸው ውስጥ ትልቅ የትችት ማዕበል አስነስቷል፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱ የሪፐብሊካን እና የዴሞክራቲክ እጩዎች በምርጫ ዘመቻው ቅስቀሳቸው የሚጠቀሙባቸው የጋሉ ንግግሮች “ዋይት ሀውስን የማሸነፍ ዕድላቸውን ሊጎዳ ይችላል” በሚል የተንታኞችን ማስጠንቀቂያ አስከትሏል፡፡ የቪኦኤ ቬሮኒካ ባልደራስ ኤግልሲያስ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።    

በታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት 19 ሚሊሽያ አባላት ኦሮሚያ ውስጥ መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ፣ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት፣ 19 ሚሊሽያ አባላት መገደላቸውን ቤተሰቦች እና የአካባቢ
የአሜሪካ ድምፅ

በታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት 19 ሚሊሽያ አባላት ኦሮሚያ ውስጥ መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ፣ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት፣ 19 ሚሊሽያ አባላት መገደላቸውን ቤተሰቦች እና የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ምላሽ ማግኘት አልቻልንም። /ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

ደቡብ ሱዳን  ያለዕድሜ መዳርን ለማስወገድ የያዘችው አዲስ ጥረት

ደቡብ ሱዳን በትምሕርት ቤት ፣በሴቶች እና ሴቶች ተማሪዎች ብዛት ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ትልቅ ጥረት በማድረግ ላይ ነች። መፍትሄ ይሆን ዘንድ ልጅ ያላቸው ታዳ
የአሜሪካ ድምፅ

ደቡብ ሱዳን  ያለዕድሜ መዳርን ለማስወገድ የያዘችው አዲስ ጥረት

ደቡብ ሱዳን በትምሕርት ቤት ፣በሴቶች እና ሴቶች ተማሪዎች ብዛት ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ትልቅ ጥረት በማድረግ ላይ ነች። መፍትሄ ይሆን ዘንድ ልጅ ያላቸው ታዳጊ ልጃገረዶችን ትምሕርት ቤት እንዲገቡ በማድረግ የተያያዘችው ጥረት ትልቅ ውጤት እያመጣ መሆኑ ተነግሯል። ይህ የደቡብ ሱዳን አዲስ መርሐ ግብር በልጅነት የልጅ እናት ሆነው ትምሕርታቸው የተሰናከለባቸውን ትምሕርታቸውን እንዲቀጥሉ ለማስቻል ተነስቷል። ሺላ ፖኒ ከጁባ ያጠናቀረችው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ጉቴሬዥ ኢትዮጵያ ገብተዋል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጀት ዋና ፀሐፊ  አንቶኒዮ ጉተሬዥ በተመድ እና የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ለመገኘት አዲስ አበባ ገብተዋል።  ለ
የአሜሪካ ድምፅ

ጉቴሬዥ ኢትዮጵያ ገብተዋል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጀት ዋና ፀሐፊ  አንቶኒዮ ጉተሬዥ በተመድ እና የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ለመገኘት አዲስ አበባ ገብተዋል።  ለጉቴሬዥ አቀባበል ያደረጉት ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ በቀጠናዊና በሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ላይ እንደተወያዩ በ X ማኅበራዊ መድረክ ላይ ባጋሩት መልዕክት አስታውቀዋል። ጉቴሬዥ በተጨማሪም ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋራ ተነጋግረዋል። በሠላምና ፀጥታ፣ በዘላቂ ልማት እንዲሁም በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ ባሉ ተግዳሮቶችና ልምዶች ላይ መነጋገራቸውን ሙሳ ፋኪ ማሃማት አስታውቀዋል።

ፑቲን የብሪክስን ጉባኤ ያስተናግዳሉ

የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በመጪዎቹ ቀናት የዓለም መሪዎችን በመቀበል የብሪክስን ጉባኤ ያስተናግዳሉ። የቻይና፣ የሕንድ፣ የቱርክ፣ እንዲሁም የኢ
የአሜሪካ ድምፅ

ፑቲን የብሪክስን ጉባኤ ያስተናግዳሉ

የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በመጪዎቹ ቀናት የዓለም መሪዎችን በመቀበል የብሪክስን ጉባኤ ያስተናግዳሉ። የቻይና፣ የሕንድ፣ የቱርክ፣ እንዲሁም የኢራንን ጨምሮ በርካታ የዓለም መሪዎች የሚገኙበትና በሩሲያዋ ካዛን ከተማ የሚካሄደው ጉባኤ፤ በዩክሬን በሚካሄደው ጦርነትና በወጣባቸው የእስር የመያዣ ትዕዛዝ ምክንያት ከዓለም መድረክ ይገለላሉ ሲባሉ የነበሩት ፑቲን፣ አሁንም ተሰሚነት እንዳላቸው ማሳያ ነው ተብሏል። ሩሲያ የብሪክስን ጉባኤ በማስተናገድ፣ ከምዕራቡ ዓለም  ጋራ ውጥረቱ እየቀጠለ ቢመጣም ከአጋሮቿ ጋራ መቆሟን ለማመልከት የምትጠቀምበትና የጦርነት ኢኮኖሚዋን ለመደገፍ ስምምነትና ድርድር የምታደርግበት መድረክ መሆኑን ተንታኞች በመናገር ላይ ናቸው። ለሌሎቹ ለተሳታፊ ሃገራት ደግሞ ትርክቶቻቸውን አጉልቶ ለማሰማት ዕድል የሚሰጥ መድረክ ነው ተብሏል። ነገ ማክሰኞ ጉባኤውን የሚጀምረውና በማደግ ላይ ያሉ ኢኮኖሚዎች ስብስብ የሆነው ብሪክስ፤ በምዕራቡ ዓለም የሚመራውን የዓለም ሥርዓት ለመገዳደር በሚል ሲጀመር በአምስት ሃገራት የተቋቋመ ሲሆን፣ በያዝነው ዓመት ግን ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሃገራት ተቀላቅለዋል። ሌሎች በርካታ ሃገራትም ለመቀላቀል ጥያቄ በማቅረብ ላይ ናቸው።

በጫሞ ሓይቅ የጀልባ አደጋ የሞቱት ሰዎች አስከሬን ተገኘ

ባለፈው ሳምንት በደቡብ ኢትዮጵያ በጋሞ ዞን በሚገኘው የጫሞ ሓይቅ በደረሰ የጀልባ አደጋ ሕይወታቸው ካለፈው 13 ሰዎች ውስጥ የአስራ ሁለቱን አስከሬን ማግኘታቸው
የአሜሪካ ድምፅ

በጫሞ ሓይቅ የጀልባ አደጋ የሞቱት ሰዎች አስከሬን ተገኘ

ባለፈው ሳምንት በደቡብ ኢትዮጵያ በጋሞ ዞን በሚገኘው የጫሞ ሓይቅ በደረሰ የጀልባ አደጋ ሕይወታቸው ካለፈው 13 ሰዎች ውስጥ የአስራ ሁለቱን አስከሬን ማግኘታቸውን የካባቢው ባለሥልታናት አስታውቀዋል። ባለፈው ሐሙስ አደጋው ሲደርስ ጀልባው 16 ሰዎችን አሳፍሮ እንደነበር ያስታውቀው የአካባቢው አስተዳደር፣ ሶስት ሰዎችን ወዲያውኑ ከአደጋው መታደግ እንደተቻለ ገልጿል። የጀልባዋ ተሳፋሪዎችም “የቀን ሠራተኞች” እንደሆኑ ተገልጿል። የዞኑ ፖሊስ ቃል አቀባይ የሆኑት ኮማንደር ረታ ተክሉ ለቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ ክፍል እንደተናገሩት፣ ጀልባው ቆሬ ዞን ከሚገኘው አቡሎ አርፊቾ አውራጃ ወደ ዞኑ መዲና አርባምንጭ በመጓዝ ላይ ነበር።

VOA60 Africa - Mozambique: Riot police fired tear gas to disperse protesters

Mozambique: Riot police fired tear gas to disperse a small crowd in Maputo after two of opposition leader Venancio Mondlane’s associates were shot dead over the weekend. Mondlane had called for a general strike to contest early results showing the ruling Fr
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Mozambique: Riot police fired tear gas to disperse protesters

Mozambique: Riot police fired tear gas to disperse a small crowd in Maputo after two of opposition leader Venancio Mondlane’s associates were shot dead over the weekend. Mondlane had called for a general strike to contest early results showing the ruling Frelimo party ahead.

VOA60 America - US envoy in Beirut for talks with Lebanese officials

U.S. envoy Amos Hochstein visited Lebanon on Monday amid Biden administration efforts to halt the fighting between Israel and Hezbollah.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - US envoy in Beirut for talks with Lebanese officials

U.S. envoy Amos Hochstein visited Lebanon on Monday amid Biden administration efforts to halt the fighting between Israel and Hezbollah.

VOA60 World - Gulen, powerful cleric accused by Turkey of orchestrating a Turkish coup, dies

Turkish Muslim preacher Fethullah Gulen, who Ankara says was behind a 2016 failed coup against Turkish leader Tayyip Erdogan, has died at the age of 83 in the United States. The cleric had lived in the United States since 1999, when he came to seek medical tr
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Gulen, powerful cleric accused by Turkey of orchestrating a Turkish coup, dies

Turkish Muslim preacher Fethullah Gulen, who Ankara says was behind a 2016 failed coup against Turkish leader Tayyip Erdogan, has died at the age of 83 in the United States. The cleric had lived in the United States since 1999, when he came to seek medical treatment.

በጀርመን እስራኤል ኤምባሲ ላይ ጥቃት ለማድረስ በማሴር የተጠረጠረ ሊቢያዊ በቁጥጥር ስር ዋለ

በርሊን በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ላይ ጥቃት ለማድረስ አቅዷል ተብሎ የተጠረጠረ እና ከእስላማዊ መንግስት ቡድን ጋር ግንኙነት እንዳለው የተገለጸው ሊቢያዊ
የአሜሪካ ድምፅ

በጀርመን እስራኤል ኤምባሲ ላይ ጥቃት ለማድረስ በማሴር የተጠረጠረ ሊቢያዊ በቁጥጥር ስር ዋለ

በርሊን በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ላይ ጥቃት ለማድረስ አቅዷል ተብሎ የተጠረጠረ እና ከእስላማዊ መንግስት ቡድን ጋር ግንኙነት እንዳለው የተገለጸው ሊቢያዊ ተጠርጣሪ እሁድ ፍርድቤት እንደሚቀርብ የጀርመን አቃብያነ ህጎች አስታወቁ።  ስሙ ኦማር ኤ. እንደሆነ የተገለጸው ተጠርጣሪ፣ ቅዳሜ ምሽት በቁጥጥር ስር የዋለው፣ ከጀርመን ዋና ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው በርናው ከተማ መኖሪያ ቤቱ ውስጥ መሆኑን የፌደራል አቃቢያነ ህጎች ቢሮ አመልክቷል።  ቢሮው አክሎ፣ ኦማር ኤ. በርሊን በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ላይ «በጦር መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ ጥቃት ለማድረስ አቅዷል» የሚል ክስ እንደተመሰረተበት አመልክቷል። የእስላማዊ መንግስት ርዕዮተ ዓለም ደጋፊ መሆኑን የገለጸው አቃቤ ህግ፣ ለጥቃቱ ዝግጅት በሚያደርግበት ወቅትም «ከእስላማዊ መንግስት አባላት ጋር በማህበራዊ ሚዲያ መልዕክት ተለዋውጧል» ብሏል።  በርሊን የሚገኙት የእስራኤል አምባሳደር ሮን ፕሮሶር በኤክስ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት «የሙስሊም ፀረ-ሴማዊነት፣ ትርክት ብቻ ሳይሆን በዓለም ዙሪያ የሽብር ድርጊቶችን የሚያበረታታ እና የሚያነሳሳ ነው» ብለዋል። አክለውም የእስራኤል ኤምባሲዎች «በዲፕሎማሲው ጦር ሜዳ ግንባር ተሰላፊ ናቸው» ሲሉም አመልክተዋል።  የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ናንችይ ፌዘር በበኩላቸው፣ በጀርመን የሚገኙ አይሁዳውያንን እና የእስራኤል ተቋማትን መጠበቅ «ከምንም በላይ ቅድሚ የምንሰጠው ነው» ያሉ ሲሆን፣  የሕግ አስከባሪ አካላት ማንኛውንም እስላማዊ፣ ፀረ-ሴማዊ እና ፀረ-እስራኤል ጥቃቶችን ለመከላከል ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረጉ መሆናቸውን ጨምረው ገልጸዋል።

እስራኤል በባህር ኃይል የንግድ ትርዒት እገዳ ምክንያት በማክሮን ላይ ህጋዊ እርምጃ ልትወስድ ነው

በፓሪስ በሚካሄደው ወታደራዊ የባህር ኃይል የንግድ ትርዒት ላይ የእስራኤል ተቋማት እንዳይሳተፉ መታገዳቸውን ተከትሎ፣ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስ
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል በባህር ኃይል የንግድ ትርዒት እገዳ ምክንያት በማክሮን ላይ ህጋዊ እርምጃ ልትወስድ ነው

በፓሪስ በሚካሄደው ወታደራዊ የባህር ኃይል የንግድ ትርዒት ላይ የእስራኤል ተቋማት እንዳይሳተፉ መታገዳቸውን ተከትሎ፣ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ፣ መስሪያቤታቸው በፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ላይ ክስ እንዲመሰርቱ ማዘዛቸውን እሁድ እለት አስታውቀዋል።  የእስራኤል ተቋማትን የማገድ ውሳኔው፣ እስራኤል በጋዛ እና ሊባኖን እያካሄደችው ባለው ጦርነት ምክንያት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተባባሰ የሄደው የማክሮን መንግስት ቅሬታ አካል ነው። እ.አ.አ ከህዳር 4 -7 በፓሪስ የሚካሄደው የባህር ኃይል የንግድ ትርዒት አዘጋጅ ኢዩሮናቫል ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ፣ የፈረንሳይ መንግስት፣ የእስራኤል ልዑካን በትርዒቱ ላይ መሳተፍም ሆነ መሳሪያዎቻቸውን ማሳየት እንደማይችሉ ማሳወቁን አመልክቷል። ውሳኔው ሰባት ተቋማት ላይ ተፅእኖ ማሳደሩንም ጠቅሷል።   ውሳኔውን ተከትሎ ካትዝ በኤክስ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈረው መልዕክት «የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት፣ በመጪው ወር ፓሪስ ላይ በሚካሄደው የባህር ኃይል የንግድ ትርዒት ላይ የእስራኤል ተቋማት ምርቶቻቸውን እንዳያሳዩ በመከልከላቸው፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሕጋዊ እና ዲፕሎማሲያዊ እርምጃ እንዲወስድ መመሪያ ሰጥቻለሁ» ብለዋል።  ካትዝ አክለው «ለሁለተኛ ጊዜ በእስራኤል ተቋማት ላይ የተጣለው እቀባም ሆነ ተቀባይነት የሌላቸው ቅድመ ሁኔታዎች ዲሞራሲያዊ ያልሆኑ ከመሆናቸውም በላይ፣ በሁለት ወዳጅ ሀገሮች መካከል ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው» ያሉ ሲሆን ፕሬዝዳንት ማክሮን ውሳኔያቸውን ሙሉ ለሙሉ እንዲሰርዙ አሳስበዋል። 

እስራኤል በጋዛ ጥቃት 73 ሰዎችን ስትገድል፣ በቤይሩት ላይ የምታካሂደውን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላለች

እስራኤል በሊባኖስ ዋና ከተማ የሂዝቦላህ «የትዕዛዝ ማዕከል» ነው ባለችው ዒላማ ላይ ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ ጦርነቱ እሁድ እለት በሁለት ግንባር የተካሄ
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል በጋዛ ጥቃት 73 ሰዎችን ስትገድል፣ በቤይሩት ላይ የምታካሂደውን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላለች

እስራኤል በሊባኖስ ዋና ከተማ የሂዝቦላህ «የትዕዛዝ ማዕከል» ነው ባለችው ዒላማ ላይ ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ ጦርነቱ እሁድ እለት በሁለት ግንባር የተካሄደ ሲሆን፣ በጋዛ ባካሄደችው የአየር ጥቃትም 73 ሰዎች መገደላቸውን የነፍስ አድን ሰራተኞች አስታውቀዋል።  የሂዝቦላህ ጠንካራ ይዞታ በሆነው ደቡባዊ ቤይሩት ላይ ጥቃቱ የተካሄደው፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በኢራን የሚደገፈው ቡድን መኖሪያ ቤታቸውን ዒላማ በማድረግ ሊገድሏቸው እንደሞከረ ገልጸው ከከሰሱ በኃላ ነው።  የእስራኤል ጥቃት ሃረት ሄሪክ ውስጥ በአንድ መስጊድ እና ሆስፒታል አቅራቢያ የሚገኝ የመኖሪያ ህንፃ መምታቱን የሊባኖስ ብሐራዊ የዜና ማሰራጫ አስታውቋል።  የእስራኤል ጦር በበኩሉ በቤይሩት የሚገኘውን «የሂዝቦላህ የስለላ ድርጅት ዋና ማዕከል» እና የምድር ውስጥ ጦር መሳሪያ ማከማቻ መምታቱን እና በሌሎች ጥቃቶች ደግሞ ሦስት የሂዝቦላህ ታጣቂዎች መግደሉን አስታውቋል።  እስራኤል ጥቃቱን ካደረሰች ደቂቃዎች በኃላ፣ ከሊባኖስ አቅጣጫ 70 ሚሳይሎች ወደ እስራኤል መተኮሳቸውን እና ሁሉንም አየር ላይ እንዳሉ ማክሸፋቸውንም ጦሩ ጨምሮ ገልጿል።  በሌላ በኩል እስራኤል በጋዛ ሰሜናዊ ግዛት ቤይት ላሃ በተሰኘ አካባቢ፣ መኖሪያ ቤቶች አቅራቢያ በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ 73 ፍልስጠማውያን መገደላቸውን የጋዛ ሲቪል መከላከያ ኤጀንሲ አስታውቋል።  

ከስልጣናቸው የተባረሩት የኬንያ ምክትል ፕሬዝዳንት አለቃቸውን 'ጨካኝ' ሲሉ ከሰሷቸው

ከስልጣናቸው የተባረሩት የኬንያ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ጋቻጉዋ እሁድ እለት፣ አለቃቸውን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ «ጨካኝ» እና «አረመኔ» ሲሉ በ
የአሜሪካ ድምፅ

ከስልጣናቸው የተባረሩት የኬንያ ምክትል ፕሬዝዳንት አለቃቸውን 'ጨካኝ' ሲሉ ከሰሷቸው

ከስልጣናቸው የተባረሩት የኬንያ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ጋቻጉዋ እሁድ እለት፣ አለቃቸውን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ «ጨካኝ» እና «አረመኔ» ሲሉ በመንቀፍ፣ ህይወታቸው አደጋ ላይ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።  ጋቻጉዋ ሐሙስ እለት በህግ መወሰኛ ምክርቤት ፊት ከተከሰሱባቸው 11 ክሶች አምስቱ ተቀባይነት በማግኘታቸው ከስልጣናቸው የተነሱ ሲሆን፣ በምትካቸው ሌላ የመሾሙን ሂደት ግን የፍርድ ቤት ውሳኔ አግዶታል።  «ፕሬዝዳንት እንዲሆን የረዳሁት፣ ያመንኩት እና እሱን በመደገፌ የተሳደድኩበት ሰው እንዴት በእኔ ላይ ይህን ላክል ጨካኝ ሊሆን እንደቻለ አስደንግጦኛል» ብለዋል ጋቻጉዋ። የ59 ዓመቱ አዛውንት የተመደቡላቸው የፀጥታ አካላት መነሳታቸውን እና ሁሉም ሰራተኞቻቸው አስገዳጅ እረፍት እንዲወጡ መደረጋቸውንም ገልጸው «በእኔ ላይ ወይም በቤተሰቤ ላይ የሆነ ነገር ቢደርስ፣ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ተጠያቂ መሆን አለባቸው» ሲሉ ተናግረዋል።  ጋቻጉዋ ይህንን ንግግር ያደረጉት፣ በደረታቸው ላይ ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ሲታከሙበት ከነበረው ሆስፒታል ከወጡ በኃላ ነው።  «ይህን አይነት መጠን ያለው ጭካኔ አይገባኝም» ያሉት ጋቻጉዋ «አንድ ሰው በህይወቱ እጅግ በጣም መጥፎ ሁኔታ ውስጥ ባለበት ወቅት እና በህይወት ለመቆየት በሚፍጨረጨርበት ወቅት፣ ሆን ተብሎ እንደዚህ አይነት ጭካኔ ይፈፀምበታል» ብለዋል። 

በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት ተቃጣ

የኢራኑ መሪ ባለፈው ዓመት በጎሮጎርሳዊያኑ ጥቅምት ሰባት ሀማስ የፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት ዋናየእቅዱ መስራች የሆኑት የሀማሱ መሪ መገደላቸውን ተከትሎ፤ ሀማስ ከ
የአሜሪካ ድምፅ

በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት ተቃጣ

የኢራኑ መሪ ባለፈው ዓመት በጎሮጎርሳዊያኑ ጥቅምት ሰባት ሀማስ የፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት ዋናየእቅዱ መስራች የሆኑት የሀማሱ መሪ መገደላቸውን ተከትሎ፤ ሀማስ ከእስራኤል ጋር የሚያደርገውንትግል እንደሚቀጥል ቃል በገቡበት ወቅት፤ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ መኖሪያ ቤትን ዒላማ ያደረገ የድሮን ጥቃት ምንም ዓይነት ጉዳት ሳያደርስ መክሸፉን የእስራኤል መንግስት ዛሬቅዳሜ ተናግሯል።   በአንጻሩ በጋዛ፣ የሆስፒታል ባለስልጣናት እና የአሶሺየትድ ፕሬስ ዘጋቢ እንደገለፁት  እስራኤል በፈጸመቻቸው የተለያዩ  ጥቃቶች ህጻናትን ጨምሮ በትንሹ 21 ሰዎች ተገድለዋል።   ዛሬ ቅዳሜ ማለዳ ከሊባኖስ አቅጣጫ የመጣውን የሰው አልባ ድሮን ጥቃት የሚያስጠነቅቁ ድምጾች በእስራኤል በከፍተኛ ሁኔታ ሲጮሁ ነበር ያለው የእስራኤል መንግስት ቃል አቀባይ  መግለጫ፤  ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት በቂሳሪያ በሚገኘው የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት እሳቸውም ሆኑ ባለቤታቸው እንዳልነበሩ አስታውቆ  በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ብሏል።    በመስከረም ወር የየመን ሁቲ አማፂያን የኔታኒያሁ አይሮፕላን በቴል አቪቭ በሚገኘው ቤን ጉሪዮን አየርማረፊያ ሲያርፍ ባሊስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፋቸው ይታወሳል።   የኔታኒያሁ መኖሪያ ቤትን ዒላማ ካደረገው የድሮን ጥቃት  በተጨማሪ ቅዳሜ ማለዳ ላይ በሰሜንእስራኤል ከሊባኖስ የተነሱ ወደ 55 የሚጠጉ ዒላማዎች ላይ መተኮሱን የእስራኤል ጦር አስታውቋል።የተወሰኑት መክነዋል የተባለ ሲሆን፤ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ እስካሁን  የተገለጸ ነገር የለም።

የኬኒያ ፍርድ ቤት የምክትል ፕሬዝዳንት ምርጫውን አገደ

የኬኒያ ህግ አውጭዎች የሀገሪቱን የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ጋቻጓን በከባድ የስነ ምግባርጉድለት እና ፕሬዚዳንቱን በማቃለል ክስ ከስልጣናቸው እንዲነ
የአሜሪካ ድምፅ

የኬኒያ ፍርድ ቤት የምክትል ፕሬዝዳንት ምርጫውን አገደ

የኬኒያ ህግ አውጭዎች የሀገሪቱን የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ጋቻጓን በከባድ የስነ ምግባርጉድለት እና ፕሬዚዳንቱን በማቃለል ክስ ከስልጣናቸው እንዲነሱ በማድረግ፤ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶለተተኪ ምክትል ፕሬዝዳንት እጩ አድርገው ያቀረቧቸውን በማጽደው ድምጽ ከሰጡ ከአንድ ቀንበኋላ የኬንያ ፍርድ ቤት  አዲሱን ምክትል ፕሬዝዳንት አግዷቸዋል።   ሩቶ ምክትል ፕሬዘዳንት ጋቻጉዋ ከስልጣናቸው እንደተነሱ የምክትል ፕሬዝዳንትነቱን ሥልጣንሹመት ለማካሄድ ጊዜ አላጠፉም።   ተተኪ ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ተጨማሪ የ ሁለት ሳምንት ጊዜ የነበራቸው ዊሊያም ሩቶ ምርጫለማድረግ ፣ምክትል ፕሬዝዳንት ጋቻጓን እንዲተኩ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ኪቱሬ ኪንዲኪንበፍጥነት ለእጩነት ያቀረቡ ሲሆን ከሰዓታት በኋላ የኪንዲኪ ሹመት ያለምንም ድምጸ ተዐቅቦ እና ተቃውሞ በ236 የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት ድምጽ ጸድቋል።   ፍርድ ቤቱ አርብ ዕለት በሰጠው ብይን የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ጋቻጓ በመተካታቸው ዙሪያ  የተወሰደውን እርምጃ በመቃወም ያቀረቡት አቤቱታ “የህዝብ ጥቅም ጥያቄዎችን ዙሪያ ጠቃሚየህግ ጥያቄ አስነስቷል” ብሏል።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በሀገራቸው ጸጥታ እያስከበሩ ወደሚገኙ ሀገራቶች ጉብኝት ማድረግ ጀመሩ

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ዛሬ ቅዳሜ ዩጋንዳ ካምፓላ ገብተዋል።  የአሁኑ ጉብኝታቸው በሶማሊያ ጸጥታ በሚያስከብሩ አራት ሀገራት ከሚያደርጉት
የአሜሪካ ድምፅ

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በሀገራቸው ጸጥታ እያስከበሩ ወደሚገኙ ሀገራቶች ጉብኝት ማድረግ ጀመሩ

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ዛሬ ቅዳሜ ዩጋንዳ ካምፓላ ገብተዋል።  የአሁኑ ጉብኝታቸው በሶማሊያ ጸጥታ በሚያስከብሩ አራት ሀገራት ከሚያደርጉት የመጀመሪያው ነው።    ፕሬዝዳንቱ በካምፓላ ከዩጋንዳው አቻቸው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በጋራ ጉዳዮች፣ በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ተልዕኮ ሽግግር አትሚስ ዙሪያ እና ቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋትን በተመለከተ እንደሚወያዩ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ቤተመንግስት መግለጫ አስታውቋል።    ሀሰን ሼክ መሃሙድ በቀጣይ በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ተልዕኮ አባል ሀገራት ወደ ሆኑትን ብሩንዲ፣ ኬኒያ እና ጅቡቲን ይጓዛሉ። የሶማሊያ ፕሬዘዳንት ቃል አቀባይ አብዱልቃድር ዲጌ ለአሜሪካ ድምጽ አፍሪካ ቀንድ ፕሬዘዳንቱ ኢትዮጵያን አይጎበኙም ሲሉ ተናግረዋል።   በሶማሊያ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች ጸጥታ ለማስከበር የተሰማሩ ቢሆንም ነገርግን በጎርጎርሳዊያኑ 2024 መግቢያ ላይ ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችው አጨቃጫቂ ውል ሶማሊያን ሉዓላዊነቴን ጥሳለች በሚል አስቆጥቷታል።   የኢትዮጵያ ሰራዊት በፊታችን ታህሳስ ሙሉ ለሙሉ ከሶማሊያ ለቆ የሚወጣ ሲሆን ሁለት የሶማሊያ ባለስልጣናት ምንጮች ግብጽ በሶማሊያ የአፍሪካ ቀንድ ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ አባል ለመሆን ጥያቄ ማቅረቧን አረጋግጠዋል።  የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ አብዱልቃድር ዲጌ በሶማሊያ ቀጣዩ የሰላም አስከባሪ ማን እንደሚሆን መታየቱ ገና እንደቀጠለ ነው ብለዋል።

በኢንተርኔትን ነፃነት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ትገኛለች

በዲጂታል፣ ወይም በአጠቃላይ በኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ ያለው ነፃነት ለተከታታይ 14 ዓመታት ማሽቆልቆሉን ‘ፍሪደም ሃውስ’ የተሰኘው ተቋም ባወጣው ዓመታዊ ሪ
የአሜሪካ ድምፅ

በኢንተርኔትን ነፃነት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ትገኛለች

በዲጂታል፣ ወይም በአጠቃላይ በኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ ያለው ነፃነት ለተከታታይ 14 ዓመታት ማሽቆልቆሉን ‘ፍሪደም ሃውስ’ የተሰኘው ተቋም ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ላይ አመልክቷል። በጥናቱ ከተካተቱ ሃገራት ውስጥ 41 በሚሆኑት በያዝነው ዓመት ምርጫ የሚካሄድ በመሆኑ ሁኔታውን አሳሳቢ እንደሚያደርገውና፣ ነጻና ክፍት የሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት ዲሞክራሲ እውን እንዲሆን ወሳኝ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች አሳስበዋል። ኢትዮጵያም በጥናቱ ከተካተቱት ሃገራት አንዷ ስትሆን፣ ኢንተርኔት ሆን ተብሎ ከሚቋረጥበት፣ የማኅበራዊ ሚዲያ ወይም ሌሎች የግንኙነት መንገዶች ከሚታገዱበት፣ ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች የመረጃ መረብ ላይ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ምክንያት የአካል ጉዳት ከሚደርስባቸውና ከሚገደሉበት ሃገራት ተርታ ተመድባለች፡፡ ሪፖርቱን የተመለከተው ባልደረባችን እንግዱ ወልዴ፣ ከቪኦኤዋ ቬሮኒካ ባልዴርስ ኤግሌሲያስ ዘገባ ጋራ አጣምሮ ተከታዩን አሰናድቷል።

ድንበር አቋርጠው የሚገቡ ሕገ ወጥ ስደተኞች እና የደኅንነት ጉዳይ

ጥቂት ሳምንታት በቀሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድንበር አቋርጠው የሚገቡ ሕገ ወጥ ስደተኞች እና የደኅንነት ጉዳይ አብይ ትኩረት ሆኖ ቀጥሏል።
የአሜሪካ ድምፅ

ድንበር አቋርጠው የሚገቡ ሕገ ወጥ ስደተኞች እና የደኅንነት ጉዳይ

ጥቂት ሳምንታት በቀሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድንበር አቋርጠው የሚገቡ ሕገ ወጥ ስደተኞች እና የደኅንነት ጉዳይ አብይ ትኩረት ሆኖ ቀጥሏል። የአሜሪካ ድምጿ የኢሚግሬሽን ጉዳዮች ዘጋቢ አሊን ባሮስ ከአሪዞና የዩናይትድ ስቴትስ የድንበር ጠባቂዎችን እና የፍልሰት ጉዳይ አዋቂዎችን አነጋግራ ያደረሰችንን አሉላ ከበደ እንደሚከተለው ያቀርበዋል።

ጫሞ ሃይቅ ላይ ከሰመጠ ጀልባ ላይ 13 ሰዎች የገቡበት አልታወቀም

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከኮሬ ዞን 16 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ አርባምንጭ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ ጫሞ ሃይቅ ውስጥ መስመጡን እና 13 ሰዎች እስካኹን የገቡበት አለመታወቁ
የአሜሪካ ድምፅ

ጫሞ ሃይቅ ላይ ከሰመጠ ጀልባ ላይ 13 ሰዎች የገቡበት አልታወቀም

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከኮሬ ዞን 16 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ አርባምንጭ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ ጫሞ ሃይቅ ውስጥ መስመጡን እና 13 ሰዎች እስካኹን የገቡበት አለመታወቁን፣ የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። ሦስት ሰዎች በህይወት የተገኙ ሲኾን፣ ቀሪዎቹ ደግሞ እየተፈለጉ እንደኾነ የፖሊስ መምሪያው ሕዝብ ግንኙት ድቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ረታ ተክሉ ገልፀዋል። /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

የመንገዶች መዘጋት ለተለያዩ ችግሮች እንዳጋለጣቸው የደራ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ

በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘውን ደራ ወረዳ ከአጎራባች አካባቢዎች የሚያገናኙ መንገዶች ከአንድ ዓመት ለሚበልጥ ጊዜ በታጠቁ ኃይሎች ተዘግተው መቀጠ
የአሜሪካ ድምፅ

የመንገዶች መዘጋት ለተለያዩ ችግሮች እንዳጋለጣቸው የደራ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ

በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘውን ደራ ወረዳ ከአጎራባች አካባቢዎች የሚያገናኙ መንገዶች ከአንድ ዓመት ለሚበልጥ ጊዜ በታጠቁ ኃይሎች ተዘግተው መቀጠላቸውን የገለጹ ነዋሪዎች፣ ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መጋለጣቸውን ገለጹ። በኦሮሚያ ክልል በምትገኘው ፍቼ ወረዳና በአማራ ክልል በሚገኘው መራቤቴ ወረዳ በኩል ወደ አገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ የሚወስዱ መንገዶች፣ “ተጓዦችን ለዝርፊያ፣ለእገታና ለሞት የሚዳርጉ ናቸው” በማለትም ነዋሪዎቹ አማረዋል። ከአንድ ወር በፊት በመራቤቴ ወረዳ በኩል ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበሩ ስምንት የንግድ መኪና አሽከርካሪዎች በፋኖ ታጣቂዎች ከታገቱና የተጠየቁትን የማስለቀቂያ ቤዛ ከከፈሉ በኋላ መገደላቸውን፣ ኹኔታውን በቅርብ እንደሚያውቁ የተናገሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል። “በመራቤቴ በኩል ለመጓዝ የሚሞክሩ አሽከርካሪዎች ገንዘብ እየከፈሉ እንደሚያልፉ አውቃለሁ” ያሉት የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ከፍያለው አደሬ፣ተገደሉ ስለተባሉት ስምንት አሽከርካሪዎች ግን መረጃው እንደሌላቸው ጠቅሰዋል። ዋና አስተዳዳሪው ዛሬ ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም. ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ባደረጉት የስልክ ቃለ ምልልስ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች በዞኑ አምሰት ወረዳዎች ፣ የፋኖ ታጣቂዎች ደግሞ በሦስት ወረዳዎች ውሰጥ እንደሚንቀሳቀሱ ጠቅሰው ለመንገዶቹ መዘጋትና በአካባቢው ላለው የጸጥታ ችግርም ሁለቱን ቡድኖች ተጠያቂ አድርገዋል። የአሜሪካ ድምፅ በስምንት አሽከርካሪዎች ላይ ተፈፀመ የተባለውን እገታና ግድያ እንደዚሁም ለድርጊቱ ተጠያቂ የሆነውን አካል ማንነት ከገለልተኛ ወገን አላረጋገጠም። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትና የፋኖ ታጣቂ ቡድኖች ከዚህ ቀደም ለተመሳሳይ ውንጀላዎች በሰጧቸው ምላሾች፣ ታጣቂዎቻቸው ሰላማዊ ሰዎችን ዒላማ እንደማያደርጉ በመግለፅ በጽኑ አስተባብለዋል።

በስምንት ወራት ውስጥ ከስልሳ በላይ ሰዎች በኮሌራ መሞታቸውን አማራ ክልል አስታወቀ

ባለፉት ስምት ወራት በአማራ ክልል 66 ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ መሞታቸውን የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ከ4 ሺሕ በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ
የአሜሪካ ድምፅ

በስምንት ወራት ውስጥ ከስልሳ በላይ ሰዎች በኮሌራ መሞታቸውን አማራ ክልል አስታወቀ

ባለፉት ስምት ወራት በአማራ ክልል 66 ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ መሞታቸውን የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ከ4 ሺሕ በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ መያዛቸውን ገልጿል። በተቋሙ የበሽታዎች እና የጤና ሁኔታዎች ምላሽ አፈፃፀም ባለሞያ ሲስተር ሰፊ ድርብ፤ ካለፈው ዓመት መጋቢት ወር መጨረሻ ጀምሮ እስከ ትላንት ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በ41 ወረዳዎች በተከሰትው የኮሌራ ወረርሽኝ 66 ሰዎች ሲሞቱ ከ4 ሺ በላይ በወረርሽኙ መያዛቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ ያሏትን ግቦች አደጋ ላይ የጣለው የሶማሊያና የኢትዮጵያ ግንኙነት

ቱርክ ከሶማሊያ ጋር ያላትን ትብብር በማጠናከር ላይ ትገኛለች። በያዝነው ወርም ለኃይል ምንጮች ፍለጋ ያሰማራቻት አሳሽ መርከብ ወደዚያ አቅንታለች። ዶሪያን
የአሜሪካ ድምፅ

ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ ያሏትን ግቦች አደጋ ላይ የጣለው የሶማሊያና የኢትዮጵያ ግንኙነት

ቱርክ ከሶማሊያ ጋር ያላትን ትብብር በማጠናከር ላይ ትገኛለች። በያዝነው ወርም ለኃይል ምንጮች ፍለጋ ያሰማራቻት አሳሽ መርከብ ወደዚያ አቅንታለች። ዶሪያን ጆንስ ከኢስታንቡል ባጠናቀረው ዘገባው እንዳመለከተው በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ውጥረት አንካራ በአፍሪካ ቀንድ ያሏትን ግቦች ለአደጋ እያጋለጠ ነው።

እስራኤል በሊባኖሱ ጥቃት የሂዝቦላህን አዛዥ መግደሏን አስታወቀች

የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ ባካሄደው ጥቃት የሂዝቦላህን የተዋጊ አዛዥ መገደሉን ዛሬ ሐሙስ አስታውቋል። በጥቃቱ የተገደለው የተዋጊ አዛዥ ሁሴን አዋዳ
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል በሊባኖሱ ጥቃት የሂዝቦላህን አዛዥ መግደሏን አስታወቀች

የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ ባካሄደው ጥቃት የሂዝቦላህን የተዋጊ አዛዥ መገደሉን ዛሬ ሐሙስ አስታውቋል። በጥቃቱ የተገደለው የተዋጊ አዛዥ ሁሴን አዋዳ እንደሚባል የገለጸው ጦሩ፣ ወደ እስራኤል ለሚተኮሱ ሚሳይሎች ተጠያቂ መሆኑንም ገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል የሂዝቦላህ ታጣቂዎች ለሚገኙባቸው አካባቢዎች ቅርበት አላቸው ባለቻቸው ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎች አካባቢያቸው ጥለው እንዲወጡ  አዲስ ትዕዛዝ አስተላልፋለች። እስራኤል እንዲህ ያሉ  ትዕዛዞች የምታስተላልፈው የአየር ጥቃቶችን ከማካሄዷ ቀደም ብላ ነው።   እስራኤል ትዕዛዙን ካስተላለፈችባቸው አካባቢዎች ውስጥ፣ በሊባኖስ ቤካ  ሸለቆ አካባቢ የሚገኙት ሳራይን፣ ታምኒን እና ሳፋሪ የተሰኙ አካባቢዎች ይገኙበታል። እስራኤል ትላንት ረቡዕ  በደቡባዊው ከተማ ናባቲህ ባካሄደችው የአየር ጥቃት ከንቲባውን ጨምሮ 16 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ50 በላይ መቁሰላቸውን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።  

ባይደን ዩክሬንን ቀዳሚ አጀንዳቸው በማድረግ ወደ ጀርመን አቅንተዋል

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከባድ ዝናባማው አውሎ ነፋስ (ሄሪኬን ሚልተን) አስቀድሞ የታቀደው ጉዟቸውን ለአንድ ሳምንት ከአስተጓጎለው በኋላ ዛሬ
የአሜሪካ ድምፅ

ባይደን ዩክሬንን ቀዳሚ አጀንዳቸው በማድረግ ወደ ጀርመን አቅንተዋል

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከባድ ዝናባማው አውሎ ነፋስ (ሄሪኬን ሚልተን) አስቀድሞ የታቀደው ጉዟቸውን ለአንድ ሳምንት ከአስተጓጎለው በኋላ ዛሬ ሐሙስ ወደ ጀርመን አቅንተዋል። ባይደን እና የጀርመኑ መሪ፣ ሁለቱም በቅርቡ ለዩክሬን ይፋ ያደረጉት አዲስ የደህንነት እርዳታ እና የሚሰጡትን ድጋፍ አስመልክቶ ከፍተኛ ጫና እያጋጠማቸው ነው። ዩክሬን በመሪዎቹ የመነጋገሪያ አጀንዳ በዋናነት ከተቀመጡት መካከል ናት፡፡ ዋይት ሀውስ ፕሬዚደንት ባይደን ሌላ የ425 ሚሊዮን ዶላር ጥቅል የደህንነት ድጋፍ ይፋ ማድረጋቸውን ትላንት ረቡዕ አስታውቋል።

የአዋሽ ፈንታሌው የመሬት መንቀጥቀጥ እና እስከ አዲስ አበባ የሚሰማው ንዝረት ቀጥሏል

ከአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የተነሳ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች ትላንት ምሽት እና ዛሬ ቀን ላይ ተሰምቷል:: የመሬት መንቀ
የአሜሪካ ድምፅ

የአዋሽ ፈንታሌው የመሬት መንቀጥቀጥ እና እስከ አዲስ አበባ የሚሰማው ንዝረት ቀጥሏል

ከአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የተነሳ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች ትላንት ምሽት እና ዛሬ ቀን ላይ ተሰምቷል:: የመሬት መንቀጥቀጡ መነሻ ከፈንታሌ 10 ኪሎ ሜትር አካባቢ ባለ ርቀት ላይ መሆኑን እና ከከርሰ ምድር አካባቢ የቅልጥ አለት ወደ መሬት እየሰረገ መምጣት ምክንያቱ መሆናቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ ተመራማሪ እና መምህር ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ተናግረዋል፡፡ በተመሳሳይ የዘርፉ ተመራማሪ እና መምህር ዶ/ር መሰለ ኃይሌ፣ አሁን እየተከሰተ ያለው አነስተኛ ሊባል የሚችል የመሬት መንቀጥቀጥ መሆኑን እና ቀስ በቀስ ኃይሉ እየወጣ መሆኑ የተሻለ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ ሁኔታው ለአዲስ አበባ የጎላ ስጋት ይፈጥራል ብለው እንደማይጠብቁ የገለፁት ሁለቱ ምሁራን፣ ሆኖም ቀጣይነቱ እና መጠኑ በግልፅ ሊተነበይ እንደማይችል እና የጥንቃቄ እርምጃዎች መወሰድ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

Get more results via ClueGoal