Ethiopia



አሜሪካ ለምን የሁለት ፓርቲ ሥርዓት ኖራት?

አሜሪካ በታሪኳ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ብታስተናግድም፣ ዲሞክራቶች እና ሪፐብሊካኖች የገነኑበት የሁለት ፓርት ሥርዓት የፖለቲካ ሂደቱን በበላይነት ይመ

VOA60 Africa - Uganda: Death toll in fuel tanker explosion rises to at least 15

The death toll rose to at least 15 on Wednesday, a day after a fuel tanker exploded in a northern Kampala suburb. The victims had gathered to scoop up fuel after the tanker overturned on a road connecting Kampala and the northern city of Gulu.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Uganda: Death toll in fuel tanker explosion rises to at least 15

The death toll rose to at least 15 on Wednesday, a day after a fuel tanker exploded in a northern Kampala suburb. The victims had gathered to scoop up fuel after the tanker overturned on a road connecting Kampala and the northern city of Gulu.

VOA60 America - New evidence China, Russia and Iran targeting US elections

China, Iran and Russia are aggressively expanding their efforts to influence American voters to potentially sway the result of the upcoming U.S. elections, according to two threat intelligence reports Wednesday.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - New evidence China, Russia and Iran targeting US elections

China, Iran and Russia are aggressively expanding their efforts to influence American voters to potentially sway the result of the upcoming U.S. elections, according to two threat intelligence reports Wednesday.

VOA60 World - At least 16 killed, including children, in Israeli airstrike on school in Nuseirat camp

At least 16 Palestinians were killed, including children, and 32 others wounded in an Israeli airstrike on a school in the Nuseirat refugee camp on Thursday, officials at Nuseirat's Al-Awda Hospital said.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - At least 16 killed, including children, in Israeli airstrike on school in Nuseirat camp

At least 16 Palestinians were killed, including children, and 32 others wounded in an Israeli airstrike on a school in the Nuseirat refugee camp on Thursday, officials at Nuseirat's Al-Awda Hospital said.

በሞዛምቢክ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የገዢው ፓርቲ እጩ አሸነፉ

በሞዛምቢክ ከሁለት ሳምንት በፊት በተደረገውና አጨቃጫቂ በሆነው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የገዢው ፍሬሊሞ ፓርቲ እጩ ዳንኤል ቻፖ ማሸነፋቸውን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚ
የአሜሪካ ድምፅ

በሞዛምቢክ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የገዢው ፓርቲ እጩ አሸነፉ

በሞዛምቢክ ከሁለት ሳምንት በፊት በተደረገውና አጨቃጫቂ በሆነው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የገዢው ፍሬሊሞ ፓርቲ እጩ ዳንኤል ቻፖ ማሸነፋቸውን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ አስታውቋል። ላለፉት ሃምሳ ዓመታት በስልጣን ላይ የቆየው የፍሬሊሞ ፓርቲ እጩው ዳንኤል ቻፖ 71 በመቶውን ድምጽ ሲያገኙ፣ የተቀናቃኙ ፖዴሞስ ፓርቲ ወኪሉ ቬናንሲዮ ሞንዳኔ ደግሞ 20 በመቶ ድምጽ እንዳገኙ ብሔራዊ የምርጫ ኮሚሽኑ አስታውቋል። ተቀናቃኙ የምርጫውን ውጤት አለመቀበል ብቻ ሳይሆን አሸናፊው እርሳቸው መሆናቸውን በማስታወቃቸው እና ባለፈው ቅዳሜ ጠበቃቸውና አንድ ሌላ የተቃዋሚ አንቂ በመገደላቸው በሃገሪቱ ውጥረት መስፈኑ ተነገሯል፡፡ ጠበቃው ኤልቪኖ ዲያስ እና የማኅበራዊ አንቂው ፓውሎ ጉዋምቤ የተቃዋሚውን እጩ በመወከል የምርጫውን ውጤት በሕግ ለመሞገት በዝግጅት ላይ ነበሩ። ተቃዋሚው ቬናንሲዮ ሞንዳኔ ለግድያው የፀጥታ ኃይሎችን ተጠያቂ አድርገው፣ ቀጣዩ ዒላማ ምናልባትም እርሳቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል። ሞንዳኔ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረገ ጥሪ ሲያደርጉ፣ ተሰናባቹ ፕሬዝደንት ፊሊፔ ኒዩሲ፣ «ኃይል የተቀላቀለበት የተቃውሞ ጥሪ ማድረግ የወንጀል ድርጊት ነው» ሲሉ አስጠንቅቀዋል። አዲስ የተመረጡትና በመጪው ጥር ስልጣናቸውን የሚረከቡት ዳንኤል ቻፖ፣ ሞዛምቢክ ከፖርቹጋል ነፃ ከወጣች ወዲህ ተወልደው ፕሬዝደንት የሆኑ የመጀመሪያው ፖለቲከኛ ይሆናሉ። 

ቻይና፣ ሩሲያና ኢራን በአሜሪካ ምርጫ ተጽእኖ የማድረግ ጥረታቸውን ጨምረዋል ተባለ

ቻይና፣ ሩሲያና ኢራን በአሜሪካ የሚደረገውን ምርጫ ውጤት ለመቀየር የተለያዩ የሳይበር ጥቃቶችን በመሞከር ላይ መሆናቸውን የሚያመለክቱ አዳዲስ መረጃዎች መገ
የአሜሪካ ድምፅ

ቻይና፣ ሩሲያና ኢራን በአሜሪካ ምርጫ ተጽእኖ የማድረግ ጥረታቸውን ጨምረዋል ተባለ

ቻይና፣ ሩሲያና ኢራን በአሜሪካ የሚደረገውን ምርጫ ውጤት ለመቀየር የተለያዩ የሳይበር ጥቃቶችን በመሞከር ላይ መሆናቸውን የሚያመለክቱ አዳዲስ መረጃዎች መገኘታቸው ታውቋል። ማይክሮሶፍት እና ‘ሪኮርድድ ፊውቸር’ የተሰኘው የሳይበር ደህንነት ኩባንያ እንዳስታወቁት፣ ከሃገራቱ ጋራ ግኑኝነት ያላቸው ተዋንያን የምክር ቤት አባላትን የኮምፒውተር ሥርዓት ዒላማ አድርገዋል። በተጨማሪም በማኅበራዊ ሚዲያ የመራጮችን ሃሳብ ለማስቀየር ሞክረዋል፣ በምርጫው እንዳይሳተፉም ቅስቀሳ አድርገዋል ተብሏል። ማይክሮሶፍት እንዳስታወቀው፣ ከቻይና ጋራ ግንኙነት ያላቸው የሳይበር ተዋንያን ቢያንስ አራት የሪፐብሊካን ፓርቲ የምክር ቤት ዓባላትን ዒማላ አድርገዋል። አባላቱ የቻይናን መንግስት በመንቀፍ የሚታወቁ ናቸው። ዋሽንግተን የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ የማይክሮሶፍትን ውንጀላ ተቃውሟል። የተወካዮች ም/ቤት አባላቱ ከቻይና ወገን የሳይበር ጥቃት ሙከራ መጨመሩ እንዳላስገረማቸው አስታውቀዋል። ቻይና ብቻ ሳትሆን ከሩሲያ እና ኢራን ጋራ ግንኙነት ያላቸው የሳይበር ተዋንያን አንዳንድ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ዒላማ በማድረግ በአሜሪካ በሚደረገው ምርጫ ላይ ተጽእኖ ለማሳረፍ እየሞከሩ ነው ተብሏል። ማይክሮሶፍት ጨምሮ እንደገለጸው “የሩሲያ የሳይበር ተዋንያን ከቴሌግራም ወደ X ማኅበራዊ ሚዲያ በመሸጋገር ተጨማሪ ድምፅ ሰጪዎችን ለማግኘትና መልዕክቶቻቸውን ለማዳረስ ችለዋል” ብሏል።

እስራኤል በተፈናቃዮች መጠለያ ባደረሰችው የአየር ጥቃት 17 ተገድለዋል ተባለ

እስራኤል ተፈናቃዮች በተጠለሉበት አንድ ት/ቤት ላይ ባደረሰችው የአየር ጥቃት 17 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤማውያን የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። በጥቃቱ
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል በተፈናቃዮች መጠለያ ባደረሰችው የአየር ጥቃት 17 ተገድለዋል ተባለ

እስራኤል ተፈናቃዮች በተጠለሉበት አንድ ት/ቤት ላይ ባደረሰችው የአየር ጥቃት 17 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤማውያን የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። በጥቃቱ ሌሎች 42 ስዎች መጎዳታቸውም ታውቋል። የእስራኤል ሠራዊት በበኩሉ የሃማስ ታጣቂዎች ትምህርት ቤቱን እንደ ማዘዣ ጣቢያ ሲጠቀሙበት ነበር ብሏል። ሠራዊቱ ለዚህ ማስረጃ እንዳላቀረበ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል። ለለፉት ሁለት ሳምንታት እስራኤል በምድርና ከአየር በምትፈጽመው ድብደባ ምክንያት አሳሳቢ የሰብዓዊ ሁኔታ ተፈጥሯል ሲሉ የጤና ሠራተኞች እያስጠነቀቁ ነው። በዛሬው የአየር ጥቃት ከተገደሉት ውስጥ 13 ሕፃናትና 18 ሴቶች እንደሚገኙበት የሆስፒታል ሰነዶች አመልክተዋል። እስራኤል ላለፉት ጥቂት ወራት በተፈናቃይ መጠለያነት በማገልገል ላይ ባሉ ትምህርት ቤቶች ላይ ጥቃቷን የጨመረች ሲሆን ትምህርት ቤቶቹ ለሐማስ የማዘዣ ጣቢያነት እያገለገሉ ነው ብላለች፡፡ እስራኤል ለዚህ ማስረጃ እንዳላቀርበችና ጥቃቶቹ በአብዛኛው ሴቶችና ሕፃናትን እንደሚገድሉ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

ብሊንከን ከዓረብ ሃገራት መሪዎች ጋር ምክክራቸውን ቀጥለዋል

በጋዛ እና ሊባኖስ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በሚቆምበት ሁኔታ ላይ ለመነጋገር በቀጠናው የሚገኙት የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ፣ ዛሬ ሐ
የአሜሪካ ድምፅ

ብሊንከን ከዓረብ ሃገራት መሪዎች ጋር ምክክራቸውን ቀጥለዋል

በጋዛ እና ሊባኖስ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በሚቆምበት ሁኔታ ላይ ለመነጋገር በቀጠናው የሚገኙት የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ፣ ዛሬ ሐሙስ ከካታሩ መሪ ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ጋራ ተገናኝተው ተወያይተዋል። ብሊንከን በተጨማሪም ከካታሩ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሃመድ አል ታኒ ጋራ እንደሚገናኙ ታውቋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ብሊንከን ነገ ዓርብ በለንደን ከዓረብ ሃገራት ባለሥልጣናት ጋራ ስብሰባ እንደሚቀመጡም ታውቋል። ብሊንከን ከያዙት አጀንዳ ውስጥ ዋነኛው በጋዘ ለሚገኙ ፍልስጤማውያን የሚሰጠው ሰብዓዊ ዕርዳታ መጨመርን የሚመለከተው ነው፡፡ ፈረንሳይ በበኩሏ እስራኤል ከሄዝቦላ ጋራ ሊባኖስ ውስጥ በምታደርገው ውጊያ ችግር ላይ ለወደቁ ሰዎች የሚውል ገንዘብ ለማሰባሰብ ዛሬ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ አስተናግዳለች፡፡ ፈረንሣይ 108 ሚሊዮን ዶላር ቃል ስትገባ፣ ጀርመን በበኩሏ 103 ሚሊዮን ዶላር እንደምታዋጣ አስታውቃለች፡፡ በፓሪሱ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በድምሩ 1 ቢሊዮን ዶላር ቃል እንደተገባ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር በ100 ዓመታቸው መረጡ

የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር በ100 ዓመታቸው ለ2024ቱ ምርጫ ድምጻቸውን በፖስታ ሰጥተዋል። ጂሚ ካርተር 100 ዓመት የሞላቸው የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬ
የአሜሪካ ድምፅ

ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር በ100 ዓመታቸው መረጡ

የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር በ100 ዓመታቸው ለ2024ቱ ምርጫ ድምጻቸውን በፖስታ ሰጥተዋል። ጂሚ ካርተር 100 ዓመት የሞላቸው የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሲኾኑ፣ ለቤተሰባቸው የገለጹትን ምኞታቸውን ማሳካት ችለዋል። በኬን ፋራቦህ ከጆርጂያ የተላከውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በአማራ ክልል በሦስት ወር ውስጥ 37 ሰዎች በወባ በሽታ ሕይወታቸው ማለፉን ከልሉ አስታወቀ

በአማራ ክልል በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት አስፈላጊ ቁጥጥር እና ክትትል ባለመደረጉ፣ በሦስት ወራት ውስጥ 37 ሰዎች በወባ መሞታቸውን፣ በአንድ ሳምንት ብ
የአሜሪካ ድምፅ

በአማራ ክልል በሦስት ወር ውስጥ 37 ሰዎች በወባ በሽታ ሕይወታቸው ማለፉን ከልሉ አስታወቀ

በአማራ ክልል በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት አስፈላጊ ቁጥጥር እና ክትትል ባለመደረጉ፣ በሦስት ወራት ውስጥ 37 ሰዎች በወባ መሞታቸውን፣ በአንድ ሳምንት ብቻ ደግሞ ከ64 ሺሕ ሰዎች መያዛቸውን ክልሉ አስታወቀ። በኢንስቲትዩት የወባ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንከር ለቪኦኤ እንደተናገሩት፣ ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ከ600 ሺሕ በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ተናግረዋል። የወባ ወረርሽኙ በብዛት ተከስቶባቸዋል በተባሉት ምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢ ጠህናን ወረዳና በባህር ዳር ዙሪያ የሚገኙ ነዋሪዎችና የአካባቢው ባለሥልጣናት፣ ወረርሽኙ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን ስጋታቸውን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በቅርቡ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት አስተያየት የወረርሽኙ 70 በመቶ የሚኾነው ስርጭት በ222 ወረዳዎች መኾኑን ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመምህራን ደመወዝ በመቋረጡ የትምህርት ሥራ መታጎሉ ተገለጸ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የመምህራን ደመወዝ በመቋረጡ የተነሳ እስከ አኹን በአንዳንድ ትምሕር ቤቶች ትምሕርት አለመጀመሩን ቪኦኤ ያነጋገራቸው
የአሜሪካ ድምፅ

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመምህራን ደመወዝ በመቋረጡ የትምህርት ሥራ መታጎሉ ተገለጸ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የመምህራን ደመወዝ በመቋረጡ የተነሳ እስከ አኹን በአንዳንድ ትምሕር ቤቶች ትምሕርት አለመጀመሩን ቪኦኤ ያነጋገራቸው ወላጆች ገለጹ። ከግል እና አንዳንድ የመንግሥት ትምሕርት ቤቶች ውጪ አብዛኞቹ እንዳልተከፈቱ፣ ቢከፈቱም ከሁለት በላይ መመሕራን ስለማይገቡ ትምሕርት አለመጀመሩን የተናገሩ ወላጆች፣ ስጋታቸውን አጋርተዋል። የክልሉ መምሕራን ማኅበር በወላይታ ዞን፣ በጋሞ ዞን፣ በኮንሶ ዞን እና በጎፋ ዞኖች የሚገኙ 28 ወረዳዎች የሚገኙ በሺሕዎች የሚቆጠሩ መምህራን ደመወዝ በወቅቱ እንደማይከፈል አስታውቋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

“ተቀናቃኝ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ሸቀጣሸቀጥ ዳሶች የፖለቲካውን ውጥረት ለማርገብ እየሞከሩ ነው”

በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ፣ የካማላ ኻሪስ እና የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎችን የሚያስሟሟቸው ጉዳዮች በብዛት የሉም። ደቡብ ካሊፎርኒያ የምት
የአሜሪካ ድምፅ

“ተቀናቃኝ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ሸቀጣሸቀጥ ዳሶች የፖለቲካውን ውጥረት ለማርገብ እየሞከሩ ነው”

በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ፣ የካማላ ኻሪስ እና የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎችን የሚያስሟሟቸው ጉዳዮች በብዛት የሉም። ደቡብ ካሊፎርኒያ የምትገኘው ዘጋቢያችን ጄኒያ ዱሎት ግን የተቀናቃኝ ምርጫ ዘመቻ ሸቀጣሸቀጥ የሚሸጡ ሁለት ግለሰቦች የፖለቲካውን ውጥረት ለማርገብ እያደረጉት ያለውን አስተዋፅኦ ቃኝታ ያደረሰችንን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

በሸንጎው ጥፋተኛ የተባሉት የኬንያው ም/ፕሬዝደንት ለደህነታቸው እንደሚሰጉ ተናገሩ

በኬንያ፤ በሃገሪቱ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት በተለያዩ ወንጀሎች ጥፋተኛ የተባሉት ምክትል ፕሬዝደንት ሪጋቲ ጋቻጉዋ የደህንነት ጠባቂዎቻቸው በመነሳታቸው ለራሳቸ
የአሜሪካ ድምፅ

በሸንጎው ጥፋተኛ የተባሉት የኬንያው ም/ፕሬዝደንት ለደህነታቸው እንደሚሰጉ ተናገሩ

በኬንያ፤ በሃገሪቱ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት በተለያዩ ወንጀሎች ጥፋተኛ የተባሉት ምክትል ፕሬዝደንት ሪጋቲ ጋቻጉዋ የደህንነት ጠባቂዎቻቸው በመነሳታቸው ለራሳቸውም ኾነ ለቤተሰባቸው ሕይወት እንደሚሰጉ አስታውቀዋል። ችግር የሚደርስባቸው ከኾነም ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ተናግረዋል። ጁማ ማጃንጋ ከናይሮቢ የላከው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ሶማሊያ «በቀጣዩ የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ ማን እንደሚሳተፍ የምወስነው እኔ ነኝ» አለች

የሶማሊያ መንግሥት እአአ በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ በሀገሯ ሥራ እንዲጀምር ለታቀደው የአፍሪካ ኅብረት አረጋጊ ተልእኮ (አውሶም) ወታደር የሚያዋጡ ሀገሮ
የአሜሪካ ድምፅ

ሶማሊያ «በቀጣዩ የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ ማን እንደሚሳተፍ የምወስነው እኔ ነኝ» አለች

የሶማሊያ መንግሥት እአአ በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ በሀገሯ ሥራ እንዲጀምር ለታቀደው የአፍሪካ ኅብረት አረጋጊ ተልእኮ (አውሶም) ወታደር የሚያዋጡ ሀገሮችን እንደሚመርጥ አረጋግጧል። የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ ሶማሊያ የተልእኮውን አቅጣጫ «ትኩረቱን በግልጽ ሉዓላዊነት ላይ» ባደረገ መንገድ ትመራዋለች ብሏል፡፡ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የደረሰችው ስምምነት  ሉዓላዊነቴን የሚጥስ ነው ስትል ሶማሊያ ትከራከራለች። «ከሶማሊያ ሰሜናዊ ክልል ጋር የተደረገውን ስምምነት ጨምሮ፣ ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜያት የወሰደቻቸው የተናጠል እርምጃዎች ሉዓላዊነታችንን የሚጥስ እና ለሰላም ማስከበር አስፈላጊ የሆነውን አመኔታ የሚሸረሽር ነው።» ሲል መግለጫው አመልክቷል። መግለጫው የወጣው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ሶማሊያ ውስጥ ጦር ባላቸው አራት ሀገራት፣ ማለትም ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ቡሩንዲ እና ጅቡቲ ያደረጉትን ጉብኝት ካጠናቀቁ በኋላ ነው። መሀሙድ ሶማሊያ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ቢኖራትም ኢትዮጵያን አልጎበኙም፡፡ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተያየቱን እንዲሰጥ ከቪኦኤ ለቀረበለት ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠም። ኢትዮጵያ  የአውሶም አካል ሆና ለመሳተፍ ፈቃደኛ መሆኗን አመላክታለች። ባለፈው ነሀሴ ኢትዮጵያ ወደ አዲሱ የአውሶም (AUSSOM) ተልዕኮ የሚደረገው ሽግግር “አካባቢው ላይ አደጋ ደቅኗል” ስትል አስጠንቅቃለች። ኢትዮጵያ አዲሱን ተልዕኮ የማዘጋጀት ኃላፊነት የተጣለባቸው አካላት "የቀጠናውን ሀገራት እና ሠራዊት ያዋጡ ሀገራትን ተገቢ ስጋት ከግምት ማስገባት አለባቸው” በማለት አሳስባለች፡፡ ሽግግሩ እየተዘጋጀ ባለበት በዚህ ወቅት ክልሉ “ወደ ማይታወቅ አደጋ እየገባ ነው” ስትልም ኢትዮጵያ ያላትን ስጋት አመልክታለች። “ኢትዮጵያ የጥላቻ መግለጫዎችን እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የከፈለውን መስዋእትነት ችላ መባሉን በዝምታ እንድታልፈው እየተጠበቀ ነው” ስትልም ኢትዮጵያ በመግለጫዋ አክላለች፡፡

«የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሩሲያ ውስጥ መኖራቸውን የሚያሳይ ማስረጃ አለ» የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስትን

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን “የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሩሲያ ውስጥ መኖራቸውን የሚያሳይ ማስረጃ አለ” ሲሉ ተናገሩ፡፡ ሚኒስትሩ ት
የአሜሪካ ድምፅ

«የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሩሲያ ውስጥ መኖራቸውን የሚያሳይ ማስረጃ አለ» የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስትን

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን “የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሩሲያ ውስጥ መኖራቸውን የሚያሳይ ማስረጃ አለ” ሲሉ ተናገሩ፡፡ ሚኒስትሩ ትላንት ረቡዕ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል “ቀሪው ነገር” እዚያ ምን እንደሚሠሩ ማየቱ ነው ብለዋል። ኦስትን ይህን ያሉት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ሁለት የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ክፍሎች ሩሲያ ውስጥ ለዩክሬኑ ጦርነት ሊውል የሚችል ሥልጠና እየወሰዱ መሆኑን መንግሥታቸው መረጃ እንዳለው ከተናገሩ አንድ ቀን በኋላ ነው፡፡ ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ «የተጠናከረ ግንኙነት» አላቸው ያሉት ኦስትን ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ የጦር መሣሪያ እንደሰጠች ጠቁመዋል፡፡ «ግንባር ከፈጠሩ፣ አላማቸው በዚህ ጦርነት ሩሲያን ወክለው ለመሳተፍ ከሆነ፣ ያ በጣም፣ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው፣ በአውሮፓ ብቻ ሳይሆን በህንድ እና ፓሲፊክ ውቅያኖስ አካባቢ (ኢንዶ-ፓሲፊክ) ባሉ ጉዳዮችም ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል» ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ኦስትን ሩሲያ እ.ኤ.አ. በ2022 መጀመሪያ ላይ ዩክሬንን ሙሉ በሙሉ በመውረር በከፈተችው ጦርነት ሰለባ ስለሆኑ ሩሲያውያን ገልፀው፣ የሰሜን ኮሪያ እዚህ ውስጥ መጨመር የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን “ብዙ ሰዎች ከሚያስቡት በላይ የበለጠ ችግር ውስጥ ሊሆኑ እንደሚችሉ አመላካች ነው” ብለዋል። ዜሌነስኪ «ሰሜን ኮሪያ በአውሮፓ ጦርነት ውስጥ ጣልቃ መግባት ከቻለች፣ በዚህ አገዛዝ ላይ የሚደረገው ጫና በእርግጠኝነት በቂ አይደለም ማለት ነው» በማለት ዩክሬን ከዓለም ጠንካራና ተጨባጭ ምላሽ ትጠብቃለች” ብለዋል፡፡

VOA60 Africa - Uganda: Fuel truck explosion near Kampala kills at least 10 people

A fuel truck that ran out of control and exploded into flames near the capital, Kampala, killed at least 10 people, police said Tuesday. Last week a fuel tanker exploded in northern Nigeria, killing more than 170 people.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Uganda: Fuel truck explosion near Kampala kills at least 10 people

A fuel truck that ran out of control and exploded into flames near the capital, Kampala, killed at least 10 people, police said Tuesday. Last week a fuel tanker exploded in northern Nigeria, killing more than 170 people.

VOA60 America - Blinken visits Saudi Arabia amid push for Middle East ceasefire

U.S. Secretary of State Antony Blinken arrived in Saudi Arabia from Israel on Wednesday. Blinken said in Israel that Israel’s killing of Hamas leader Yahya Sinwar presents a “real opportunity” to free the remaining hostages being held by Hamas in Gaza a
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Blinken visits Saudi Arabia amid push for Middle East ceasefire

U.S. Secretary of State Antony Blinken arrived in Saudi Arabia from Israel on Wednesday. Blinken said in Israel that Israel’s killing of Hamas leader Yahya Sinwar presents a “real opportunity” to free the remaining hostages being held by Hamas in Gaza and end the Israel-Hamas war.

VOA60 World - Israeli jets struck multiple buildings in the Lebanese coastal city of Tyre

Israeli jets struck multiple buildings in the coastal city of Tyre on Wednesday, sending large clouds of black smoke into the air. The state-run National News Agency reported that an Israeli airstrike on the nearby town of Maarakeh killed three people.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Israeli jets struck multiple buildings in the Lebanese coastal city of Tyre

Israeli jets struck multiple buildings in the coastal city of Tyre on Wednesday, sending large clouds of black smoke into the air. The state-run National News Agency reported that an Israeli airstrike on the nearby town of Maarakeh killed three people.

ብሊንከን የሃማስ መሪ ከተገደሉ በኋላ ታጋቾቹን ለማስለቀቅ «እውነተኛ ዕድል ይኖራል» አሉ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ እስራኤል የሃማሱን መሪ ያህያ ሲንዋርን መግደሏ አሁንም ጋዛ ውስጥ በታጣቂው ቡድን እጅ ያሉትን ቀ
የአሜሪካ ድምፅ

ብሊንከን የሃማስ መሪ ከተገደሉ በኋላ ታጋቾቹን ለማስለቀቅ «እውነተኛ ዕድል ይኖራል» አሉ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ እስራኤል የሃማሱን መሪ ያህያ ሲንዋርን መግደሏ አሁንም ጋዛ ውስጥ በታጣቂው ቡድን እጅ ያሉትን ቀሪዎቹን ታጋቾች የሚያስለቅቅ ስምምነት ላይ ለመድረስ  እውነተኛ እድል ማምጣቱን ተናገሩ። ብሊንክን ይህን የተናገሩት፣ ዛሬ ረቡዕ ከቴል አቪቭ ወደ ሳኡዲ አረብያ ከመብረራቸው በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው። «እስራኤል ሃማስ ላይ በምታካሂደው ጦርነት  ወታደራዊ ዓቅሙን ማዳከም ጨምሮ ብዙ ስኬት አግኝታለች» ያሉት ብሊንከን  «የቀረው ታጋቾቹን ማስለቀቅ እና ጦርነቱን ማጠናቀቅ ነው» ብለዋል።  ጦርነቱ ሃማስን ከጋዛ በሚያስወጣ እና የእስራኤል ወታደሮችም እዚያ እንዳይቆዩ በሚያደርግ መንገድ መጠናቀቅ እንዳለበትም ብሊንክን አሳስበዋል። ከጦርነቱ በኋላ ለጋዛ የሚኖረው እቅድ አስተዳደር፣ ደህንነት፣ መልሶ ግንባታ፣ እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ፍልስጤማውያንን ለመርዳት ማድረግ የሚችለውን ጨምሮ በሚቀጥሉት ቀናት ከአረብ አገሮች ጋራ የሚወያዩበት ርዕስ እንደሚሆን ብሊንከን ተናግረዋል፡፡ ብሊንከን ነገ ሐሙስ ወደካታር ይሄዱ እና አርብ በለንደን ከአረብ ሀገራት አቻዎቻቸው ጋራ  እንደሚገናኙ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ብሊንከን እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስተን እስራኤል ወደጋዛ የሚገባውንን የሰብአዊ ርዳታ መጠን እንድትጨምር፣ አለዚያ  የአሜሪካን ወታደራዊ ርዳታ እንደምታጣ የሚያስጠነቅቅ ደብዳቤ ከላኩ አንድ ሳምንት በኋላ ሁኔታዎች መሻሻል ቢያሳዩም ብዙ እንደሚቀረውና ቀጣይነት እንደሚያስፈልገው የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትላንት ረቡዕ በሰጡት መግለጫቸው ተናግረዋል፡፡ አምና የሰጡትን ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ እስራኤል ወዲያውኑ የሰብአዊ ርዳታ አቅርቦቱ መጠን እንዲጨምር ብታደርግም እንዳልቀጠለ ብሊንከን አውስተዋል። አዲሱ ማስጠንቀቂያ «ባዶ ማስፈራሪያ» ይሆን እንደሆን የተጠየቁት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ « በሕጉ  መሠረት ለመሥራት ቁርጠኛ ነኝ» ብለዋል፡፡ ብሊንከን ከአንድ ዓመት በፊት ከተቀሰቀሰው የእስራኤል እና የሃማስ ጦርነት ወዲህ ባደረጉት 11ኛ ጉብኘታቸው ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እና ሌሎች ባለሥልጣናት ጋራ ትላንት ማክሰኞ ተገናኝተው ተወያይተዋል። የሃማሱ መሪ ሲንዋርን ግድያ ተከትሎ ዩናትይትድ ስቴትስ ወደ አካባቢው ተመልሳ የተኩስ አቁም ጥረቱን እንድትገፋበት መልካም አጋጣሚ የተከፈተላት መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ኅይሎች ዛሬ ረቡዕ የሊባኖስ ደቡባዊ የወደብ ከተማ ታይር ላይ የአየር ጥቃት አካሂደዋል፡፡ ጥቃቱን ያደረሱት ነዋሪዎች ከተማዋን ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ከሰጡ ከሰዓታት በኋላ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ሌሊቱን ቤይሩት ውስጥ ያሉ ከሄዝቦላህ ጋር ግንኙነት ያላቸውን አካባቢዎች ደብድበናል ስትል እስራኤል አስታውቃለች፡፡ ዛሬ ረቡዕ ቤይሩትን የጎበኙት የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አናሌና ቤርቦክ ለሊባኖሱ ጦርነት ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሕክምና የበጎ አድራጎት አገልግሎቶች የሃያ አምስት ዓመታት ጉዞ

ዋና መቀመጫውን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው “ፒፕል ቱ ፒፕል” ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብላ በምትገኘው የአርሊንግተን ዋና ከተማ የተመሰረ
የአሜሪካ ድምፅ

በሕክምና የበጎ አድራጎት አገልግሎቶች የሃያ አምስት ዓመታት ጉዞ

ዋና መቀመጫውን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው “ፒፕል ቱ ፒፕል” ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብላ በምትገኘው የአርሊንግተን ዋና ከተማ የተመሰረተበትን ሃያ አምስተኛ ዓመት መታሰቢያ በማድረግ ዓመታዊ የሕክምና ሳይንስ ጉባኤው አካሂዷል። አብዛኞቹ አባላቱ ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሞያዎች ቢሆኑም፤ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ከፍተኛ እውቅና ያላቸው የሕክምና ባለ ሞያዎችም ለዓመታት ተሳትፈውበታል። ከሕክምና አገልግሎቶች እና የህክምና ትምሕርት ተሳትፎዎቹ በተጨማሪም በሌሎች ርዳታ የሚሹ ማኅበራዊ ጉዳዮች አስተዋጽኦ ሲያደርግ የቆየ ድርጅት ነው። ይህንኑ መነሻ በማድረግ ከድርጅቱ አመራር አባላት ጋራ ውይይት አካሂደናል። ውይይቱን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በምዕራብ ወለጋ ግጭት ውስጥ ያልተሳተፉ ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ፣ በመንግሥት ኃይሎች እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው ግጭት፣ ሲቪ
የአሜሪካ ድምፅ

በምዕራብ ወለጋ ግጭት ውስጥ ያልተሳተፉ ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ፣ በመንግሥት ኃይሎች እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው ግጭት፣ ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ። የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች «ለታጣቂዎቹ ታገለግላላችኹ» ፣ ታጣቂዎቹ ደግሞ «ለመንግሥት ትሠራላችኹ» በሚል ከሁለቱም በኩል ጉዳት እየደረሰባቸው እንደኾነ፣ ለቪኦኤ አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጉዳቱ ደርሶበታል የተባለው፣ የቆንዳላ ወረዳ አስተዳዳር፣ ተገደሉ ስለተባሉ ሲቪሎች መረጃ እንደሌለው አስታውቋል። መንግሥት በሲቪሎች ላይ ጥቃት እንደማያደርስም የወረዳው አስተዳዳሪ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በአካባቢው ይፈፀማል የተባለው ጥቃት ሪፖርት እንደደረሰው አስታውቋል። /ዝርዝርሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

ስፔን ከአፍሪካ የሚመጣውን ፍልሰት እንደ መልካም የኢኮኖሚ አጋጣሚ ትመለከታለች

ለቀኝ ዘመም ወግ አጥባቂ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰጠው ድጋፍ እየጨመረ በመጣበት የአውሮፓ ኅብረት፣ ዓባል ሃገራቱ ፍልሰት እንዲቆም ጥሪ በማድረግ ላይ ናቸው።
የአሜሪካ ድምፅ

ስፔን ከአፍሪካ የሚመጣውን ፍልሰት እንደ መልካም የኢኮኖሚ አጋጣሚ ትመለከታለች

ለቀኝ ዘመም ወግ አጥባቂ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰጠው ድጋፍ እየጨመረ በመጣበት የአውሮፓ ኅብረት፣ ዓባል ሃገራቱ ፍልሰት እንዲቆም ጥሪ በማድረግ ላይ ናቸው። ስፔን ግን ከዚህ በተቃራኒ በመቆም፣ በአውሮፓ ዕድሜያቸው የገፉ አዛውንቶች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ፣ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ቁጥጥር የሚደረግበት ፍልሰት አስፈላጊ ነው ትላለች። ሄንሪ ሪጅዌል ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የአሜሪካ ምርጫ ወጪ 

ሃገራት በምርጫ ወቅት ከፍተኛ ገንዘብ ያወጣሉ። የአሜሪካ የምርጫ ወጪ ከሌሎች ሃገራት ጋራ ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው። ይህንንኑ የተመለከተውን  ገላጭ ዘገባ ከተያ
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ ምርጫ ወጪ 

ሃገራት በምርጫ ወቅት ከፍተኛ ገንዘብ ያወጣሉ። የአሜሪካ የምርጫ ወጪ ከሌሎች ሃገራት ጋራ ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው። ይህንንኑ የተመለከተውን  ገላጭ ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የሠራተኛ ማኅበራት ድጋፍ በዩናይትድ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ያለው ከፍተኛ ሚና

በመላዋ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ14 ሚሊዮን የሚሆኑት መራጮች መብታቸውን ለማስከበር በተቋቋሙ ማኅበራት የተደራጁ ሠራተኞች ናቸው። ከአጠቃላዩ መራጭ ቁጥር አኳያ
የአሜሪካ ድምፅ

የሠራተኛ ማኅበራት ድጋፍ በዩናይትድ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ያለው ከፍተኛ ሚና

በመላዋ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ14 ሚሊዮን የሚሆኑት መራጮች መብታቸውን ለማስከበር በተቋቋሙ ማኅበራት የተደራጁ ሠራተኞች ናቸው። ከአጠቃላዩ መራጭ ቁጥር አኳያ ሲታይ ቁጥራቸው አነስተኛ ቢሆንም ፕሬዚደንታዊ ዕጩ ተፎካካሪዎች ድጋፋቸውን በእጅጉ ይፈልጉታል። የአሜሪካ ድምጿ የምክር ቤታዊ ጉዳዮች ዘጋቢ ካትሪን ጂፕሰን በዘንድሮ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የሠራተኛ ማኅበራት ድምጽ ትልቅ ሚና የሚጫወትባት ከሆነችው ከኔቫዳ ክፍለ ግዛት ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የአይ ኤም ኤፍ እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ

ዓመታዊው የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤም ኤፍ)ና የዓለም ባንክ ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ ተጀምሯል።  ኢትዮጵያን ጨምሮ የአባል ሃገራቱ የገንዘብ ሚንስት
የአሜሪካ ድምፅ

የአይ ኤም ኤፍ እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ

ዓመታዊው የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤም ኤፍ)ና የዓለም ባንክ ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ ተጀምሯል።  ኢትዮጵያን ጨምሮ የአባል ሃገራቱ የገንዘብ ሚንስትሮችና የብሄራዊ ባንክ ገዥዎች የሚሳተፉበት ነው። የኢኮኖሚና ኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ያሬድ ሃይለመስቀል ይህ ጉባኤ የዓለም ኢኮኖሚ በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ጦርነቶች እየተፈተነ ባለበት ወቅት የሚካሄድ ነው ይላሉ። /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/ 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 11 ፓርቲዎችን በጊዜያዊነት አገደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ "በጠቅላላ ጉባኤ፣ በኦዲት እና በሴት አባላት አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋራ በተያያዘ፣ 11 የፖለቲካ ፓርቲዎችን በጊዜያ
የአሜሪካ ድምፅ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 11 ፓርቲዎችን በጊዜያዊነት አገደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ "በጠቅላላ ጉባኤ፣ በኦዲት እና በሴት አባላት አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋራ በተያያዘ፣ 11 የፖለቲካ ፓርቲዎችን በጊዜያውነት ማገዱን ትላንት ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. በጻፈው እና በፌስቡክ ገጹ ይፋ ባደረገው ደብዳቤ አስታውቋል። ቦርዱ የእግድ ውሳኔ ካሳለፈባቸው ፓርቲዎች መካከል የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የጌዲኦ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የሐረዲ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የገዳ ሥርዓት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ፣ የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ የጋምቤላ ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ኅብረት እና አገው ለፍትህና ዲሞክራሲ ፓርቲ ይገኙበታል።  ፓርቲው እግዱን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋር ምክር ቤት በጻፈው በዚሁ ደብዳቤ፣ ቦርዱ የተለየ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ፣ ፓርቲዎቹ ከማንኛውም ሕጋዊ እንቅስቃሴ ታቅበው እንዲቆዩ ትዕዛዝ አስተላልፏል።  በመሆኑም የተዘረዘሩት ፓርቲዎች የተጣለባቸው የእግድ ውሳኔ እስከሚነሳ ድረስ፣ በማናቸውም የጋራ ምክር ቤቱ የሚያዘጋጃቸው ጉባኤዎች ላይ ሊገኙ፣ ሊመርጡ፣ ሊመረጡ ወይም በተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ ሊያገለግሉ እንደማይችሉ ቦርዱ ጨምሮ ገልጿል።  እስካሁን ስማቸው ከተጠቀሰው ፓርቲዎች በኩል የወጣ መግለጫም ሆነ የተሰጠ አስተያየት የለም።

ኡጋንዳ  16 ተቃዋሚዎችን በ’ሀገር ክህደት’ ወነጀለች

የኡጋንዳ ወታደራዊ ፍርድ ቤት «በሕግ ወጥ መንገድ ፈንጂ ይዞ በመገኘት እና የሀገር ክህደት በመፈጸም» በተወነጀሉ 16 የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ በትላንት
የአሜሪካ ድምፅ

ኡጋንዳ  16 ተቃዋሚዎችን በ’ሀገር ክህደት’ ወነጀለች

የኡጋንዳ ወታደራዊ ፍርድ ቤት «በሕግ ወጥ መንገድ ፈንጂ ይዞ በመገኘት እና የሀገር ክህደት በመፈጸም» በተወነጀሉ 16 የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ በትላንትናው እለት የጥፋተኝነት ብይን ማሳለፉን አንድ የተከሳሾች ተከላካይ ጠበቃ አስታወቁ። የችሎቱን ውሳኔም ‘አጠያያቂ’ ብለውታል። አቃቤ ሕግ 16’ቱን የተቃዋሚው ይብሔራዊ አንድነት መድረክ ፓርቲ አባላት እና እስከአሁን  አልተያዙም ያላቸውን ሌሎች ግለሰቦች እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በሕዳር 2020 እና በግንቦት 2021 መካከል ባለው ጊዜ በሃገሪቱ ምርጫ እየተካሄደ ሳለ የተባሉትን ወንጀሎች ‘ፈጽመዋል’ ሲል ነው የከሰሳቸው።   ሻሚም ማሌንዴ የተባሉ የተከሳሾች ተከላካይ ጠበቃ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት፤ «ካሁን ቀደም ወንጀሉን አልፈጸምንም” ሲሉ ክሱን ያስተባበሉት ተከሳሾች አሁን ጥፋተኝነታቸውን አምነዋል የተባለበትን ሁኔታ “አጠያያቂ ነው» ብለውታል። ‘ባቢ ዋይን’ በሚል የመድረክ ስም የሚታወቀው  የቀድሞ ድምጻዊ  ሮበርት ኪያጉላኒ የተባለው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል፤ ቡድኑ ጥፋተኛነቱን አምኖ ፕሬዝዳንታዊ ይቅርታ እንዲጠይቅ መገደዱን ተናግሯል። 16ቱ ተከሳሾች አራት ዓመታት በእስር ላይ የቆዩ ሲሆኑ፤ ነገ ረቡዕ ችሎቱ ዘንድ ይቀርባሉ። ጋዜጠኞች ሥነ ስርአቱን እንዳይከታተሉ ታግደዋል። ምሥራቅ አፍሪቃዊቱ አገር ኡጋንዳ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ1986 አንስቶ በዩዌሪ ሙሴቬኒ ስትመራ መቆየቷ ይታወቃል።  

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያውያንን በእግር ኳስ አንድ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ካፍ አስታወቀ

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ያቀረበችውን ጥያቄ ካፍ እንዲያፀድቀው ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በአዲስ አበባ በተካሔደው የካፍ 46ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላ
የአሜሪካ ድምፅ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያውያንን በእግር ኳስ አንድ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ካፍ አስታወቀ

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ያቀረበችውን ጥያቄ ካፍ እንዲያፀድቀው ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በአዲስ አበባ በተካሔደው የካፍ 46ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ጠየቁ።  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “ኢትዮጵያውያንን በእግር ኳስ አንድ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው” የተናገሩት የካፍ ፕሬዝደንት ፓትሪስ ሞትሴፔ፣ የኢትዮጵያ ጥያቄ በካፍ አሠራር መሰረት ታይቶ ምላሽ እንደሚሰጠው ተናግረዋል፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በመጪው 2029 ዓ.ም. የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት 13 አገራት መጠየቃቸውንም አስታውቀዋል።  የፊፋ ፕሬዝደንት ጂያኒ እኢንፋንቲኖ በበኩላቸው፣ በፊፋ የዓለም ዋንጫ የሚሳተፉ የአፍሪካ አገራት ቁጥር ከቀጣዩ ውድድር ጀምሮ በእጥፍ እንደሚጨምር፣ በአዲስ አበባው የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል፡፡ /ዝርዝርሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/ 

የኤሌክቶራል ኮሌጅ ሂደት

ኤሌክቶራል ኮሌጅ (Electoral College) የአሜሪካ ዜጎች ፕሬዝዳንታቸውን የሚመርጡበት ሂደት ነው። በስተመጨረሻ አሸናፊውን የሚመስኑት የኤሌክቶራል ኮሌጅ አባላት ናቸ
የአሜሪካ ድምፅ

የኤሌክቶራል ኮሌጅ ሂደት

ኤሌክቶራል ኮሌጅ (Electoral College) የአሜሪካ ዜጎች ፕሬዝዳንታቸውን የሚመርጡበት ሂደት ነው። በስተመጨረሻ አሸናፊውን የሚመስኑት የኤሌክቶራል ኮሌጅ አባላት ናቸው።  ሂደቱ እንዴት እንደሚካሄድ ከተያያዘው መግለጫ ይከታተሉ። 

ለትግራይ ክልል ተረጂዎች ገቢ ማሰባሰብ ተጀመረ

በትግራይ ክልል 4.5 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው፣ «አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ» የተባለ ኮሚቴ አስታወቀ። ኮሚቴው ተጎጂዎቹን
የአሜሪካ ድምፅ

ለትግራይ ክልል ተረጂዎች ገቢ ማሰባሰብ ተጀመረ

በትግራይ ክልል 4.5 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው፣ «አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ» የተባለ ኮሚቴ አስታወቀ። ኮሚቴው ተጎጂዎቹን ለመርዳት ዛሬ ባስጀመረው የገቢ ማሰባሰቢያ 130 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን እና፣ ፌደራል መንግሥቱ 130 ሚሊዮን ብር ለመስጠት ቃል መግባቱ ታውቋል። /ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

በትረምፕ እና ሀሪስ ምርጫ ዘመቻ “የውስጥ ጠላት” እና “ያልተረጋጋ” መባባሉ ተባብሷል

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ልንታገለው የሚገባን «የውስጥ ጠላት» አለን የሚለው ንግግር በተቃዋሚዎቻቸው ውስጥ ትልቅ የ
የአሜሪካ ድምፅ

በትረምፕ እና ሀሪስ ምርጫ ዘመቻ “የውስጥ ጠላት” እና “ያልተረጋጋ” መባባሉ ተባብሷል

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ልንታገለው የሚገባን «የውስጥ ጠላት» አለን የሚለው ንግግር በተቃዋሚዎቻቸው ውስጥ ትልቅ የትችት ማዕበል አስነስቷል፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱ የሪፐብሊካን እና የዴሞክራቲክ እጩዎች በምርጫ ዘመቻው ቅስቀሳቸው የሚጠቀሙባቸው የጋሉ ንግግሮች “ዋይት ሀውስን የማሸነፍ ዕድላቸውን ሊጎዳ ይችላል” በሚል የተንታኞችን ማስጠንቀቂያ አስከትሏል፡፡ የቪኦኤ ቬሮኒካ ባልደራስ ኤግልሲያስ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።    

በታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት 19 ሚሊሽያ አባላት ኦሮሚያ ውስጥ መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ፣ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት፣ 19 ሚሊሽያ አባላት መገደላቸውን ቤተሰቦች እና የአካባቢ
የአሜሪካ ድምፅ

በታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት 19 ሚሊሽያ አባላት ኦሮሚያ ውስጥ መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ፣ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት፣ 19 ሚሊሽያ አባላት መገደላቸውን ቤተሰቦች እና የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ምላሽ ማግኘት አልቻልንም። /ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

ደቡብ ሱዳን  ያለዕድሜ መዳርን ለማስወገድ የያዘችው አዲስ ጥረት

ደቡብ ሱዳን በትምሕርት ቤት ፣በሴቶች እና ሴቶች ተማሪዎች ብዛት ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ትልቅ ጥረት በማድረግ ላይ ነች። መፍትሄ ይሆን ዘንድ ልጅ ያላቸው ታዳ
የአሜሪካ ድምፅ

ደቡብ ሱዳን  ያለዕድሜ መዳርን ለማስወገድ የያዘችው አዲስ ጥረት

ደቡብ ሱዳን በትምሕርት ቤት ፣በሴቶች እና ሴቶች ተማሪዎች ብዛት ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ትልቅ ጥረት በማድረግ ላይ ነች። መፍትሄ ይሆን ዘንድ ልጅ ያላቸው ታዳጊ ልጃገረዶችን ትምሕርት ቤት እንዲገቡ በማድረግ የተያያዘችው ጥረት ትልቅ ውጤት እያመጣ መሆኑ ተነግሯል። ይህ የደቡብ ሱዳን አዲስ መርሐ ግብር በልጅነት የልጅ እናት ሆነው ትምሕርታቸው የተሰናከለባቸውን ትምሕርታቸውን እንዲቀጥሉ ለማስቻል ተነስቷል። ሺላ ፖኒ ከጁባ ያጠናቀረችው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ጉቴሬዥ ኢትዮጵያ ገብተዋል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጀት ዋና ፀሐፊ  አንቶኒዮ ጉተሬዥ በተመድ እና የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ለመገኘት አዲስ አበባ ገብተዋል።  ለ
የአሜሪካ ድምፅ

ጉቴሬዥ ኢትዮጵያ ገብተዋል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጀት ዋና ፀሐፊ  አንቶኒዮ ጉተሬዥ በተመድ እና የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ለመገኘት አዲስ አበባ ገብተዋል።  ለጉቴሬዥ አቀባበል ያደረጉት ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ በቀጠናዊና በሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ላይ እንደተወያዩ በ X ማኅበራዊ መድረክ ላይ ባጋሩት መልዕክት አስታውቀዋል። ጉቴሬዥ በተጨማሪም ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋራ ተነጋግረዋል። በሠላምና ፀጥታ፣ በዘላቂ ልማት እንዲሁም በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ ባሉ ተግዳሮቶችና ልምዶች ላይ መነጋገራቸውን ሙሳ ፋኪ ማሃማት አስታውቀዋል።

ፑቲን የብሪክስን ጉባኤ ያስተናግዳሉ

የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በመጪዎቹ ቀናት የዓለም መሪዎችን በመቀበል የብሪክስን ጉባኤ ያስተናግዳሉ። የቻይና፣ የሕንድ፣ የቱርክ፣ እንዲሁም የኢ
የአሜሪካ ድምፅ

ፑቲን የብሪክስን ጉባኤ ያስተናግዳሉ

የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በመጪዎቹ ቀናት የዓለም መሪዎችን በመቀበል የብሪክስን ጉባኤ ያስተናግዳሉ። የቻይና፣ የሕንድ፣ የቱርክ፣ እንዲሁም የኢራንን ጨምሮ በርካታ የዓለም መሪዎች የሚገኙበትና በሩሲያዋ ካዛን ከተማ የሚካሄደው ጉባኤ፤ በዩክሬን በሚካሄደው ጦርነትና በወጣባቸው የእስር የመያዣ ትዕዛዝ ምክንያት ከዓለም መድረክ ይገለላሉ ሲባሉ የነበሩት ፑቲን፣ አሁንም ተሰሚነት እንዳላቸው ማሳያ ነው ተብሏል። ሩሲያ የብሪክስን ጉባኤ በማስተናገድ፣ ከምዕራቡ ዓለም  ጋራ ውጥረቱ እየቀጠለ ቢመጣም ከአጋሮቿ ጋራ መቆሟን ለማመልከት የምትጠቀምበትና የጦርነት ኢኮኖሚዋን ለመደገፍ ስምምነትና ድርድር የምታደርግበት መድረክ መሆኑን ተንታኞች በመናገር ላይ ናቸው። ለሌሎቹ ለተሳታፊ ሃገራት ደግሞ ትርክቶቻቸውን አጉልቶ ለማሰማት ዕድል የሚሰጥ መድረክ ነው ተብሏል። ነገ ማክሰኞ ጉባኤውን የሚጀምረውና በማደግ ላይ ያሉ ኢኮኖሚዎች ስብስብ የሆነው ብሪክስ፤ በምዕራቡ ዓለም የሚመራውን የዓለም ሥርዓት ለመገዳደር በሚል ሲጀመር በአምስት ሃገራት የተቋቋመ ሲሆን፣ በያዝነው ዓመት ግን ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሃገራት ተቀላቅለዋል። ሌሎች በርካታ ሃገራትም ለመቀላቀል ጥያቄ በማቅረብ ላይ ናቸው።

በጫሞ ሓይቅ የጀልባ አደጋ የሞቱት ሰዎች አስከሬን ተገኘ

ባለፈው ሳምንት በደቡብ ኢትዮጵያ በጋሞ ዞን በሚገኘው የጫሞ ሓይቅ በደረሰ የጀልባ አደጋ ሕይወታቸው ካለፈው 13 ሰዎች ውስጥ የአስራ ሁለቱን አስከሬን ማግኘታቸው
የአሜሪካ ድምፅ

በጫሞ ሓይቅ የጀልባ አደጋ የሞቱት ሰዎች አስከሬን ተገኘ

ባለፈው ሳምንት በደቡብ ኢትዮጵያ በጋሞ ዞን በሚገኘው የጫሞ ሓይቅ በደረሰ የጀልባ አደጋ ሕይወታቸው ካለፈው 13 ሰዎች ውስጥ የአስራ ሁለቱን አስከሬን ማግኘታቸውን የካባቢው ባለሥልታናት አስታውቀዋል። ባለፈው ሐሙስ አደጋው ሲደርስ ጀልባው 16 ሰዎችን አሳፍሮ እንደነበር ያስታውቀው የአካባቢው አስተዳደር፣ ሶስት ሰዎችን ወዲያውኑ ከአደጋው መታደግ እንደተቻለ ገልጿል። የጀልባዋ ተሳፋሪዎችም “የቀን ሠራተኞች” እንደሆኑ ተገልጿል። የዞኑ ፖሊስ ቃል አቀባይ የሆኑት ኮማንደር ረታ ተክሉ ለቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ ክፍል እንደተናገሩት፣ ጀልባው ቆሬ ዞን ከሚገኘው አቡሎ አርፊቾ አውራጃ ወደ ዞኑ መዲና አርባምንጭ በመጓዝ ላይ ነበር።

Get more results via ClueGoal