በአማራ ክልል የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ለጥቃት መጋለጣቸውን ማኅበሩ አስታወቀ
newsare.net
በአማራ ክልል በቀጠለው ግጭት ሳቢያ አራት የጤና ባለሞያዎች መገደላቸውንና በርካቶች መታሰራቸውን የአማራ ክልል የጤና ባለሞያዎች ማኅበር አስታወቀ። “በተለበአማራ ክልል የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ለጥቃት መጋለጣቸውን ማኅበሩ አስታወቀ
በአማራ ክልል በቀጠለው ግጭት ሳቢያ አራት የጤና ባለሞያዎች መገደላቸውንና በርካቶች መታሰራቸውን የአማራ ክልል የጤና ባለሞያዎች ማኅበር አስታወቀ። “በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚገኙ የጤና አገልግሎት ባለሞያች የሞያ ነፃነት አጥተዋል” ያሉት የአማራ ክልል ጤና ባለሞያዎች ማኅበር ጸሀፊ “ባለሞያዎች የታጠቁ ኃይሎች በሚሰነዝሩት ጥቃት ይገደላሉ፣ ይታሰራሉ፤” ብለዋል:: ከሁለት ሳምንት ወዲህ በምዕራብና ሰሜን ጎጃም ዞኖች የሚኖሩ ሁለት ፋርማሲስት ሲገደሉ በባሕር ዳር ከተማ አንዲት ነርስ በትላንትናው ዕለት ምሽት ላይ ሥራ ላይ እያለች ባልታወቁ ታጣቂዎች በጥይት ተመትታ መቁሰሏን የማኅበሩ ጸሐፊ ተናግረዋል። ለደህንነቱ በመስጋት ስሙም ኾነ የሚሠራበት የሕክምና ተቋም እንዳይጠቀስ የጠየቀ አንድ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚኖር የሕክምና ባለሞያ መተማ አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ የሚሠሩ ሁለት የሞያ አጋሮቹ እንዲሁም በጎንደር ከተማ የሚገኘው የአይራ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ‘ከፋኖ ጋራ ግንኙነት አላችሁ” በሚል መታሰራቸውን ነግረውናል። በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡን የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ የእጅ ስልክ ላይ ብንደውልም ስልኩ ባለ መስራቱ ምክንያት አስተያየታቸውን ማካተት አልቻልንም። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡ Read more