እስራኤል ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት በኢራን ላይ ማድረሷን አስታወቀች
newsare.net
እ.አ.አ ጥቅምት 1 ኢራን በባሊስቲክ ሚሳኤል በእስራኤል ላይ ላደረሰችው ጥቃት ምላሽ በሆነው በዚህ የአጸፋ ጥቃት የጦር አውሮፕላኖች በመላ ኢራን ወታደራዊ ጣቢያእስራኤል ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት በኢራን ላይ ማድረሷን አስታወቀች
እ.አ.አ ጥቅምት 1 ኢራን በባሊስቲክ ሚሳኤል በእስራኤል ላይ ላደረሰችው ጥቃት ምላሽ በሆነው በዚህ የአጸፋ ጥቃት የጦር አውሮፕላኖች በመላ ኢራን ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ለብዙ ሰዓታት ድብደባ ማካሄዳቸውን የእስራኤል ጦር አስታውቋል፡፡ ከአንድ አመት በላይ በዘለቀው ጦርነት በኢራን ላይ ያደረሰችውን ከባድ ጥቃት ማጠናቀቋንም እስራኤል ገልጻለች፡፡ የኢራን አጋር የሆነው ሃማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ካደረሰ በኋላ ወደ ብዙ የግጭት ግንባሮች ተስፋፍቶ ቴህራንና ሌሎች ቀጠናዊ አጋሮቿን የጦርነቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ ሁነዋል፡፡ የእስራኤል መከላከያ ሃይል ዛሬ ረፋድ ላይ በሰጠው መግለጫ የጦር አውሮፕላኖቹ «በኢራን ውስጥ ባሉ በርካታ አካባቢዎች በወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ያነጣጠሩና ትክክለኛ ጥቃቶችን ካደረሱ በኋላ በሰላም ወደ አገራቸው ተመልሰዋል» ብሏል። ይህ መግለጫ የወጣውም ኢራን ውስጥ የመጀመርያው ፍንዳታ ከተሰማ ከአራት ሰዓታት በኋላ ነው፡፡ የእስራኤል መከላከያ ሃይል ቃል አቀባይ ሪየር አድሚራል ዳንኤል ሃጋሪ ለጋዜጠኞች የእስራኤል የአየር ድብደባ አላማቸውን ያሳኩ እንደነበሩ የገለጹ ቢሆንም ማስረጃ ግን ወዲያውኑ አላቀረቡም። የኢራን መንግስት የዜና ጣቢያ የሀገሪቱ የአየር መከላከያ ድርጅትን ጠቅሶ እንደዘገበው እስራኤል በቴህራን እና በምዕራባዊው ኩዝስታን እና ኢላም አውራጃዎች በሚገኙ ወታደራዊ ማዕከላት ላይ ጥቃት አድርሳለች ብሏል። የኢራን ሃይሎች አብዛኛውን ጥቃት “በስኬት” ማክሸፍ መቻላቸውንና “ውስን ጉዳት” ብቻ መድረሱንም ጨምሮ ገልጿል፡፡ የኢራን ባለስልጣናት የእስራኤል የአየር ጥቃት ማክሸፍ ሰለመቻላቸውም ሆነ ስላደረሰው ጉዳት ማስረጃ ማቅረብ አልቻሉም። ነገር ግን የመንግስት ሚዲያ የኢራን ጦርን ጠቅሶ እንደዘገበው በእስራኤል ጥቃት ሁለት ወታደሮች ተገድለዋል። አንድ የአሜሪካ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ደግሞ እስራኤል “በኢራን ህዝብ ከሚኖርባቸው ወጣ ባሉ አካባቢዎች በሚገኙ በርካታ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ትክክለኛ የአየር ድብደባ አድርጋለች'' ብለዋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስም ስለእስራኤል ወታደራዊ ርምጃ ገለፃ ተደርጎላቸዋል ሲል ዋይት ሀውስ ትላንት አስታውቋል። ያሉትን ለውጦችን በቅርበት እየተከታተሉ መሆናቸውንም ተገልጿል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ባለስልጣን ለቪኦኤ ሲናገሩ “በጥቃቱ ዙርያ ቅድሚያ አሳውቀውን ነበር” ነገር ግን እኛ አልተሳተፍንም ብለዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ከእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ጋር ዛሬ የተነጋገሩ ሲሆን የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በኢራን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ስላደረሰው ጥቃት አዳዲስ መረጃዎችን እንዳጋሯቸው ፔንታጎን ንግግራቸውን በተመለከተ ካወጣው ጽሁፍ ታውቋል፡፡ ኦስቲን ዩናይትድ ስቴትስ ለእስራኤል ደህንነት እና ራስን የመከላከል መብት ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ ማረጋገጣቸውም ተገልጿል፡፡ Read more