ጆርጂያውያን ሲመርጡ ውለዋል
newsare.net
ጆርጂያውያን ዛሬ ወደ አውሮፓ ህብረት ወይም ወደ ሩሲያ ምህዋር ሊወስድ በሚችል ምርጫ ላይ ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል፡፡ ገዥው ፓርቲ የሩስያ ደጋፊነት ስጋት ከጊዜጆርጂያውያን ሲመርጡ ውለዋል
ጆርጂያውያን ዛሬ ወደ አውሮፓ ህብረት ወይም ወደ ሩሲያ ምህዋር ሊወስድ በሚችል ምርጫ ላይ ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል፡፡ ገዥው ፓርቲ የሩስያ ደጋፊነት ስጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣባት ጆርጂያ የተካሄደው ምርጫ የአውሮፓን ምኞት የሚወስን እንደሆነም ተገልጿል፡፡ የፓርላማ ምርጫው ዲሞክራሲን በማፈን ወደ ሩሲያ አዘንብሏል ተብሎ ከተከሰሰው ገዥው ፓርቲ በተቃራኒ የተሰለፉት የምዕራቡ ዓለም ደጋፊ የሆኑ የተቃዋሚ ሃይሎች ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታውቅ ሁኔታ ህብረት ያሳዩበት ነው ተብሏል። ብራሰልስ ምርጫው የአውሮፓ ህብረት እጩ የሆነችው ጆርጅያን ወደ ህብረቱ የመቀላቀል እድሏን እንደሚወስን አስጠንቅቋል። ብዙዎች የሃገሬው ሰዎችም ምርጫው በሕይወታቸው ውስጥ በጣም ወሳኝ ድምጽ ሊሆን እንደሚችል ያምናሉ፡፡ ጆርጂያ ወደ አውሮፓ ህብረት አባልነት መመለሱን ወይም አምባገነንነትን ተቀብላ ወደ ሩሲያ ምህዋር መግባቷን የሚወሰንበት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ Read more