2 የኢራን ወታደራዊ ጦር ሠፈሮች በእስራኤል ጥቃት መውደማቸውን የሳተላይት ምስሎች አሳዩ
newsare.net
የትላንቱ የእስራኤል ጥቃት ከኢራን የቀድሞ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ምርምር እና ከአሁኑ የባሊስቲክ ሚሳይል መርሃ ግብሮች ጋር ግንኙነት ያላቸውን ፓርቺን እና2 የኢራን ወታደራዊ ጦር ሠፈሮች በእስራኤል ጥቃት መውደማቸውን የሳተላይት ምስሎች አሳዩ
የትላንቱ የእስራኤል ጥቃት ከኢራን የቀድሞ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ምርምር እና ከአሁኑ የባሊስቲክ ሚሳይል መርሃ ግብሮች ጋር ግንኙነት ያላቸውን ፓርቺን እና ክሆጂር የተባሉትን ሁለት ሚስጥራዊ የኢራን ጦር ሰፈሮች እንዳወደመ ተነግሯል። ዛሬ እሁድ በአሶሲየትድ ፕሬስ የተተነተኑ የሳተላይት ምስሎች በፓርቺን የጦር ሠፈር የወደሙ ተቋማትን አሳይተዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል ኢራን ቀደም ሲል የኒውክሌር ፍንዳታ ሊያስከትሉ የሚችሉ ፈንጂዎችን እንደሞከረችበት የሚጠረጠር ሥፍራ እንደሚገኝበት ተመልክቷል፡፡ ወድመዋል ከተባሉት መካከል “ታሌጋን 2” ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ በዩራኒየም የበለጸጉ ከፍተኛ የፍንዳታ መሣሪያዎች ግብአቶችን የያዘ ህንጻ ሊኖር እንደሚችል ቢገመትም በውስጡ ምን እንዳለ በግልጽ አልታወቀም፡፡ ዓለም አቀፉን የኒውክሌር ኃይል ተቋም የሚመሩት ራፌል ማሪኖ ግሮሲ በኤክስ የማህበራዊ መድረካቸው “የኢራን ኒውክሌር ተቋማት ምንም ጉዳት አልደረሰባቸውም” ብለዋል፡፡ የሳተላይት ፎቶግራፍ ምስሎች የሚሳይል ማምረቻ ተቋማትን እና የመሬት ውስጥ ለውስጥ ዋሻ መስመር እንዳለው በሚታመንበት በክሆጂር ተቋም ላይ የደረሰውንም ጉዳት እንደሚያሳዩ ዘገባው አመልክቷል። ተንታኞች ይህ ጥቃት ኢራን አዳዲስ ባለስቲክ ሚሳይሎችን የማምረት አቅም እንደሚያሳጣት ገምተዋል፡፡ ኢራን ሁለት ወታደሮች ብቻ ሲሞቱባት አብዛኛውን የእስራኤል ጥቃት “በተሳካ ሁኔታ” ማክሸፍ መቻሏን “ውስን ጉዳት” ብቻ መድረሱንም ገልጻለች፡፡ ይሁን እንጂ ባለሥልጣናቱን ስለደረሰው ጉዳትም ሆነ የኢራን ጦር ስለሰጠው ምላሽ ማስረጃ አላቀረቡም፡፡ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጥቃቱ ኢራንን “በከፍተኛ ጉዳት አድርሶበታል” ጥቃቱም “ዓላማውን ሁሉ አሳክቷል”ብለዋል፡፡ የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ ካሜኒ ግን ዛሬ እሁድ እንደተናገሩት የእስራኤሉ ጥቃት “ብዙ መጋነንም ሆነ ዝቅ ተደርጎ ሊታይ የሚችል መሆን አይገባውም” ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ኢራን ልትሰጠው ስለሚገባው ምላሽ ምንም አልተናገሩም፡፡ የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ተቋም፣ ምዕራባውያን የመረጃ ምንጮች እና ሌሎች፣ ቴህራን እኤአ ከ2003 ጀምሮ የልዩ ጦር መሣሪያ ግንባታ መርሃግብሮችን እንደምታካሂድ ይናገራሉ፡፡ Read more