Ethiopia



እስራኤል የምስራቅ ሊባኖስ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

በምስራቅ ሊባኖስ ቤካ ሸለቆ አቅራቢያ በሚገኙ የሂዝቦላ ዒላማዎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንደምትወስድ ያስጠነቀቀችው እስራኤል፣ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው

ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካውያን ከምርጫው ቀን በፊት ድምጻቸውን እየሰጡ ነው

በመጪው ማክሰኞ ኅዳር 5 ቀን 2024 ዓ.ም. ለሚካሄደው ምርጫ «የቅድሚያ ምርጫ ድምጽ» እየተሰጠ ነው። ከምርጫው ቀን አስቀድሞ ድምጽ እንዲሰጥ የሚፈቅዱ ክፍለ ግ
የአሜሪካ ድምፅ

ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካውያን ከምርጫው ቀን በፊት ድምጻቸውን እየሰጡ ነው

በመጪው ማክሰኞ ኅዳር 5 ቀን 2024 ዓ.ም. ለሚካሄደው ምርጫ «የቅድሚያ ምርጫ ድምጽ» እየተሰጠ ነው። ከምርጫው ቀን አስቀድሞ ድምጽ እንዲሰጥ የሚፈቅዱ ክፍለ ግዛቶች የተለያዩ ደንቦች እና የጊዜ ሰሌዳዎችን ይከተላሉ። ከወዲሁ ድምጽ መስጠት የሚፈቅዱ ክፍለ ግዛቶችም አሉ። በአንዳንድ ክፍለ ግዛቶች አስቀድሞ ድምጽ ለመስጠት የተቀመጠው የመመዝገቢያ ቀነ ገደብ ያበቃ ሲኾን፣ በአንዳንዶቹ ክፍለ ግዛቶች ደግሞ አሁን እየተጀመረ ነው። በዚህ ሂደት ድምጽ መስጠት ጠቃሚ መሆኑን ድምጻቸውን የሰጡ መራጮችና የምርጫ ባለሞያዎች ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። /ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

ወጣት መራጮች

በአሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሚሳተፉት ወጣቶቹ መራጮች «ጄን ዚ» በሚል መጠሪያ ይታወቃሉ። ከ18 እስከ 27 ባለው የዕድሜ ክልል ገዳማ ውስጥ ይገኛሉ። እንዴ
የአሜሪካ ድምፅ

ወጣት መራጮች

በአሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሚሳተፉት ወጣቶቹ መራጮች «ጄን ዚ» በሚል መጠሪያ ይታወቃሉ። ከ18 እስከ 27 ባለው የዕድሜ ክልል ገዳማ ውስጥ ይገኛሉ። እንዴት መምረጥ እንደሚችሉ ከመማር ጀምሮ ከቤት ቤት እየዞሩ ድጋፍ ማሰባበሰብ ተግባራት ድረስ፣ ብዙዎች የምርጫው የሲቪክ ሂደት አካል እየሆኑ ነው። ላውሬል ቦውማን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በስፔን የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 51 ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ

ትላንት ማክሰኞ ዕለት በደቡብ እና ምስራቅ የስፔን አካባቢዎች የጣለው አውሎ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ባስከተለው ድንገተኛ ጎርፍ የ51 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የስፔ
የአሜሪካ ድምፅ

በስፔን የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 51 ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ

ትላንት ማክሰኞ ዕለት በደቡብ እና ምስራቅ የስፔን አካባቢዎች የጣለው አውሎ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ባስከተለው ድንገተኛ ጎርፍ የ51 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የስፔን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። አውሮፓ ውስጥ በቅርብ ጊዜ ተከስቶ የማያውቅ የከፋ የተፈጥሮ አደጋ መሆኑ የተገለጸው ይህ ጎርፍ መኪናዎችን ጠራርጎ መውሰዱን፣ አውራ ጎዳናዎችን ወደ ወንዝነት መቀየሩን እና የባቡር መሥመሮችን ማስተጓጎሉንም አመልክተዋል። ማላጋ በተሰኘው ከተማ አቅራቢያ 300 ሰዎችን አሳፍሮ በፍጥነት ይጓዝ የነበረ ባቡርም ከመስመር ውጪ የወጣ ሲሆን የተጎዳ ሰው ግን እንደሌለ ባለሥልጣናቱ አመልክተዋል። በፍጥነት የሚጓዘው የጭቃ ቀለም ያለው የጎርፍ ውሃ መኪናዎችን እያላጋ ሲወስድም ታይቷል። ፖሊስ እና የነፍስ አድን አገልግሎት ሠራተኞች ሄሊኮፕተሮችን በመጠቀም ሰዎችን ከቤታቸው እና ከመኪናዎቻቸው ያወጡ ቢሆንም በርካታ ሰዎች እስካሁን የደረሱበት እንደማይታወቅ ባለሥልጣናቱ ማክሰኞ ማታ አስታውቀው ነበር። የስፔን የአደጋ ጊዜ ምላሽ አባል የሆኑ ከ1ሺህ በላይ ወታደሮች በአደጋው ወደተጎዱ አካባቢዎች ተሰማርተው ፍለጋ በቀጠሉበት ወቅት፣ የሟቾቹ ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ ተገልጿል።

ኬኒያ የሚኖሩ አሜሪካዊያን ለምርጫ እየተዘጋጁ ናቸው

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጥር ኅዳር አምስት የነገ ሳምንት ማክሰኞ የሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ተቃርቧል። የምረጡኝ ዘመቻውም ተጧጡፏል፡፡  በብዙ ሺ
የአሜሪካ ድምፅ

ኬኒያ የሚኖሩ አሜሪካዊያን ለምርጫ እየተዘጋጁ ናቸው

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጥር ኅዳር አምስት የነገ ሳምንት ማክሰኞ የሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ተቃርቧል። የምረጡኝ ዘመቻውም ተጧጡፏል፡፡  በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቀው ኬኒያ ውስጥ የሚኖሩ አሜሪካዊያንም ባሉበት ሆነው በምርጫው መሳተፋቸውን ቀጥለዋል፡፡  የአሜሪካ ድምጹ ዘጋቢ ጁማ ማጃንጋ ናይሮቢ የሚኖሩ አሜሪካዊያንን በሀገራቸው ፖለቲካ ስለሚያደርጉት ተሳትፎ አነጋግሮ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የአሜሪካ ገበሬዎች የታሪፍ ጉዳይና የድጎማ መቋረጥ አሳስቧቸዋል

በተያዘው ዓመት በአሜሪካ ምርጫ ለመሳተፍ ዝግጅት ላይ የሚገኙት የሃገሪቱ ገበሬዎች፣ ኢኮኖሚው ከበድ ብሏቸዋል ተብሏል። የታሪፍ ጉዳይና የድጎማ መቋረጥ ከሚያ
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ ገበሬዎች የታሪፍ ጉዳይና የድጎማ መቋረጥ አሳስቧቸዋል

በተያዘው ዓመት በአሜሪካ ምርጫ ለመሳተፍ ዝግጅት ላይ የሚገኙት የሃገሪቱ ገበሬዎች፣ ኢኮኖሚው ከበድ ብሏቸዋል ተብሏል። የታሪፍ ጉዳይና የድጎማ መቋረጥ ከሚያሳስቧቸው ጉዳዮች ውስጥ ናቸው። የቪኦኤው ኬን ፋርቦ ገበሬዎችን አነጋግሮ ከኢሊኖይ ግዛት ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ሶማሊያ በሞቃድሾ የሚሠሩትን የኢትዮጵያ ዲፕሎማት እውቅና ነሳች

ሶማልያ በሞቃዲሾ የሚሰሩት የኢትዮጵያ ዲፕሎማት እውቅና የላቸውም አለች፡፡ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ፣ ዲፕሎማቱ ከዲፕሎማ
የአሜሪካ ድምፅ

ሶማሊያ በሞቃድሾ የሚሠሩትን የኢትዮጵያ ዲፕሎማት እውቅና ነሳች

ሶማልያ በሞቃዲሾ የሚሰሩት የኢትዮጵያ ዲፕሎማት እውቅና የላቸውም አለች፡፡ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ፣ ዲፕሎማቱ ከዲፕሎማሲያዊ ሚናቸው ጋር የማይጣጣሙ ተግባራትን ፈጽመዋል ሲል ከሷል። ሞቃዲሾ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አማካሪ የሆኑት ዲፕሎማት አሊ ሞሃመድ አዳን ትዕዛዙ በደረሳቸው 72 ሰዓታት ውስጥ ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡም ተነግሯዋል። ሶማሊያ በአሊ ተፈጽሟል የተባለውን ድርጊት በዝርዝር ባትገልጽም፣ የሚኒስቴሩ መግለጫ ውሳኔው የተላለፈው “የቪየናን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስምምነት በመጣሳቸው” መሆኑን አመልክቷል፡፡ የአሜሪካ ድምፅ ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው ወዲያውኑ ምላሽ ማግኘት አልቻለም። አዲስ አበባ ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመች በኋላ፣ ሶማሊያ ስምምነቱ ሉዓላዊነቷን የጣሰ አድርጋ በመቁጠሯ፣ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ የከረረ ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል፡፡ ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ በበኩላቸው “የባህር በር-ለእውቅና” የተባለውን የመግባቢያ ስምምነት ተገቢነት በመግለፅ ተከላክለዋል።

ተማሪዎቹን ለከፍተኛ ውጤት ያበቃው የጠረፍ ከተማ ትምህርት ቤት

በ2016 ዓም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 684 ሺህ 205 ተማሪዎች ያለፉት 5.4 በመቶ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር። በ
የአሜሪካ ድምፅ

ተማሪዎቹን ለከፍተኛ ውጤት ያበቃው የጠረፍ ከተማ ትምህርት ቤት

በ2016 ዓም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 684 ሺህ 205 ተማሪዎች ያለፉት 5.4 በመቶ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር። በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ውስጥ የሚገኝ አንድ የግል ትምህርት ቤት ግን ያስፈተናቸውን 35 ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ በማሳለፍ  ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል። የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ዝቅተኛ በሆነበት የሶማሌ ክልል፣ ትምህርት ቤቱ ተማሪዎቹን እንዴት ለዚህ ስኬት ሊያበቃ ቻለ? 

ጦርነቶቹን ለማስቆም የሚያስችል ፖሊሲ ያላቸው ትረምፕ ናቸው ወይስ ሃሪስ?

ምክትል ፕሬዝደንት ካመላ ሃሪስ ዩናይትድ ስቴትስ የግጭቶች አያያዝን  አጋርነቶችን እየገነባች  መምራት እንዳለባት እንደሚያምኑ ይናገራሉ። የቀድሞ ፕሬዝደን
የአሜሪካ ድምፅ

ጦርነቶቹን ለማስቆም የሚያስችል ፖሊሲ ያላቸው ትረምፕ ናቸው ወይስ ሃሪስ?

ምክትል ፕሬዝደንት ካመላ ሃሪስ ዩናይትድ ስቴትስ የግጭቶች አያያዝን  አጋርነቶችን እየገነባች  መምራት እንዳለባት እንደሚያምኑ ይናገራሉ። የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በበኩላቸው  ጥንካሬን የሚያሳዩ  በመሆናቸው እና ቀጣይ እርምጃቸው ምን እንደሚሆን ስለማያሳውቁ  ጦርነትን ከመጀመሩ በፊት ማስቆም እንደሚችሉ ይናገራሉ፡፡ የቪኦኤ የኋይት ሐውስ ቢሮ ዋና ዘጋቢ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ  በመካከለኛው ምሥራቅ እና በአውሮፓ ጦርነቶች እየተካሄዱ ባሉበት በዚህ ወቅት  ግጭቶችን ለመቀነስ  የተሻለ የሚሆነው የትኛው የውጭ ፖሊሲ እንደሆነ የጉዳዩን አዋቂ ባለሞያዎች  ጠይቃ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

ለኦክላንድ ከተማ ምክር ቤት የሚወዳደሩት አፍሪካውያን

በአሜሪካ የሚደረገው ምርጫ በብዙ መልኩ ለየት ያለና ታሪካዊ ነው። በካልፎርኒያ ግዛት በምትገኘው ኦክላንድ ከተማ፣ አንድ ትውልደ ኤርትራ አሜሪካዊና እንዲኹም
የአሜሪካ ድምፅ

ለኦክላንድ ከተማ ምክር ቤት የሚወዳደሩት አፍሪካውያን

በአሜሪካ የሚደረገው ምርጫ በብዙ መልኩ ለየት ያለና ታሪካዊ ነው። በካልፎርኒያ ግዛት በምትገኘው ኦክላንድ ከተማ፣ አንድ ትውልደ ኤርትራ አሜሪካዊና እንዲኹም ትውልደ ናይጄሪያ አሜሪካዊ ለከተማዋ ምክር ቤት አባልነት ለመወዳደር የምርጫ ዘመቻ ላይ ናቸው። የቪኦኤ የትግርኛ ክፍል ባልደረባ ተወልደ ወልደገብርኤል የስደተኞች ተሟጋች የሆኑትን ትውልደ ኤርትራው አቶ ሜሮን ሰመዳር እና የንግድ ማኅበረሰቡ ድምጽ መሆን የሚሹትንና የንግድ ድርጅቶች ባለቤት የሆኑትን ትውልደ ናይጄሪያው ባባ አፎላቢ አነጋግሮ ተከታዩን አጠናቅሯል።

አዲሶቹ አሜሪካውያን በ2024’ቱ ምርጫ ከፍ ያለ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ ተነገረ

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2020 ዓ.ም.  ከተካሄደው ምርጫ ወዲህ ቁጥራቸው 3.5 ሚሊዮን የሚደርስ በመራጭነት ዕድሜ የሚገኙ ሰዎች የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ
የአሜሪካ ድምፅ

አዲሶቹ አሜሪካውያን በ2024’ቱ ምርጫ ከፍ ያለ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ ተነገረ

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2020 ዓ.ም.  ከተካሄደው ምርጫ ወዲህ ቁጥራቸው 3.5 ሚሊዮን የሚደርስ በመራጭነት ዕድሜ የሚገኙ ሰዎች የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ ለመሆን በቅተዋል’ ሲል ለስደተኞች መብት የሚሟገተው ‘ብሔራዊ ፓርትነርሺፕ ፎር ኒው አሜሪካንስ’ በመባል የሚታወቀው ተቋም አመልክቷል። እንደ አንዳንድ ተንታኞችም እይታ ይህ ቁጥሩ እያደገ የመጣ ቡድን የምርጫውን ውጤት በመወሰኑ ረገድ ትልቅ ሚና ሊጫወት ይችላል። የአሜሪካ ድምጿ የኢሚግሬሽን ጉዳዮች ዘጋቢ አሊን ባሮስ ያደረሰችንን ዘገባ አሉላ ከበደ እንደሚከተለው ያቀርበዋል።

ኢትዮጵያ ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች ምን ያህል ምቹ ናት?

 በኢትዮጵያ በትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ በግብርና እና በሌሎች ዘርፎች አዳዲስ የስራ ፈጠራ ሃሳቦች ያሏቸው ወጣቶች እየተበራከቱ ስለመምጣታቸው ይገለጻል፡: ይሁ
የአሜሪካ ድምፅ

ኢትዮጵያ ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች ምን ያህል ምቹ ናት?

 በኢትዮጵያ በትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ በግብርና እና በሌሎች ዘርፎች አዳዲስ የስራ ፈጠራ ሃሳቦች ያሏቸው ወጣቶች እየተበራከቱ ስለመምጣታቸው ይገለጻል፡: ይሁንና እነዚህ በሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ወጣቶቹ፤ ያላቸውን ርዕይ ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚችሉበት የተመቻቸ ሃገራዊ ሁኔታ አለመኖሩን ስራ ፈጣሪዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ መንግስት በበኩሉ ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች የተመቻቸ ሁኔታ እንዲኖር ትኩረት ሰጥቶ እየስራ እንደሚገኝ ይገልጻል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች የሚገጥሟቸው ፈተናዎች እና እድሎች

በ19 ዓመቷ ሥራ ፈጣራ ውስጥ የገባችው ሳሚያ አብዱልቃድር፣ ወጣቶች የሥራ ፈጠራ ሀሳባቸውን ተግባራዊ ለማድረግ በሚገጥሟቸውን እንቅፋቶች በማለፏ፣ ከአራት አመ
የአሜሪካ ድምፅ

ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች የሚገጥሟቸው ፈተናዎች እና እድሎች

በ19 ዓመቷ ሥራ ፈጣራ ውስጥ የገባችው ሳሚያ አብዱልቃድር፣ ወጣቶች የሥራ ፈጠራ ሀሳባቸውን ተግባራዊ ለማድረግ በሚገጥሟቸውን እንቅፋቶች በማለፏ፣ ከአራት አመት በፊት የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበርን መሰረተች። ላለፉት አራት አመታትም፣ ማህበሩ የወጣት ስራ ፈጣሪዎችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስራ ፈጣራ ጥቅሞችን በመደገፍ፣ በማበረታታት እና በማስተዋወቅ በርካታ ሥራዎችን ሰርቷል።  (ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ዘገባ ያገኛሉ)

2 የኢራን ወታደራዊ ጦር ሠፈሮች በእስራኤል ጥቃት መውደማቸውን የሳተላይት ምስሎች አሳዩ

የትላንቱ የእስራኤል ጥቃት ከኢራን የቀድሞ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ምርምር እና ከአሁኑ የባሊስቲክ ሚሳይል መርሃ ግብሮች ጋር ግንኙነት ያላቸውን ፓርቺን እና
የአሜሪካ ድምፅ

2 የኢራን ወታደራዊ ጦር ሠፈሮች በእስራኤል ጥቃት መውደማቸውን የሳተላይት ምስሎች አሳዩ

የትላንቱ የእስራኤል ጥቃት ከኢራን የቀድሞ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ምርምር እና ከአሁኑ የባሊስቲክ ሚሳይል መርሃ ግብሮች ጋር ግንኙነት ያላቸውን ፓርቺን እና ክሆጂር የተባሉትን ሁለት ሚስጥራዊ የኢራን ጦር ሰፈሮች እንዳወደመ ተነግሯል። ዛሬ እሁድ በአሶሲየትድ ፕሬስ የተተነተኑ የሳተላይት ምስሎች በፓርቺን የጦር ሠፈር የወደሙ ተቋማትን አሳይተዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል ኢራን ቀደም ሲል የኒውክሌር ፍንዳታ ሊያስከትሉ የሚችሉ ፈንጂዎችን እንደሞከረችበት የሚጠረጠር ሥፍራ እንደሚገኝበት ተመልክቷል፡፡  ወድመዋል ከተባሉት መካከል “ታሌጋን 2” ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ በዩራኒየም የበለጸጉ ከፍተኛ የፍንዳታ መሣሪያዎች ግብአቶችን የያዘ ህንጻ ሊኖር እንደሚችል ቢገመትም በውስጡ ምን እንዳለ በግልጽ አልታወቀም፡፡ ዓለም አቀፉን የኒውክሌር ኃይል ተቋም የሚመሩት ራፌል ማሪኖ ግሮሲ በኤክስ የማህበራዊ መድረካቸው “የኢራን ኒውክሌር ተቋማት ምንም ጉዳት አልደረሰባቸውም” ብለዋል፡፡   የሳተላይት ፎቶግራፍ ምስሎች የሚሳይል ማምረቻ ተቋማትን እና የመሬት ውስጥ ለውስጥ ዋሻ መስመር እንዳለው በሚታመንበት በክሆጂር ተቋም ላይ የደረሰውንም ጉዳት እንደሚያሳዩ ዘገባው አመልክቷል።  ተንታኞች ይህ ጥቃት ኢራን አዳዲስ ባለስቲክ ሚሳይሎችን የማምረት አቅም እንደሚያሳጣት ገምተዋል፡፡ ኢራን ሁለት ወታደሮች ብቻ ሲሞቱባት አብዛኛውን የእስራኤል ጥቃት “በተሳካ ሁኔታ” ማክሸፍ መቻሏን “ውስን ጉዳት” ብቻ መድረሱንም ገልጻለች፡፡ ይሁን እንጂ ባለሥልጣናቱን ስለደረሰው ጉዳትም ሆነ የኢራን ጦር ስለሰጠው ምላሽ ማስረጃ አላቀረቡም፡፡ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጥቃቱ ኢራንን “በከፍተኛ ጉዳት አድርሶበታል” ጥቃቱም “ዓላማውን ሁሉ አሳክቷል”ብለዋል፡፡ የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ ካሜኒ ግን ዛሬ እሁድ እንደተናገሩት የእስራኤሉ ጥቃት “ብዙ መጋነንም ሆነ ዝቅ ተደርጎ ሊታይ የሚችል መሆን አይገባውም” ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ኢራን ልትሰጠው ስለሚገባው ምላሽ ምንም አልተናገሩም፡፡ የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ተቋም፣ ምዕራባውያን የመረጃ ምንጮች እና ሌሎች፣ ቴህራን እኤአ ከ2003 ጀምሮ የልዩ ጦር መሣሪያ ግንባታ መርሃግብሮችን እንደምታካሂድ ይናገራሉ፡፡  

በሰሜን ጋዛ የእስራኤል ጥቃት 22 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤም ባለሥልጣናት ተናገሩ

በሰሜን ጋዛ ዛሬ እሁድ በተፈጸመ የእስራኤል የአየር ድብደባ አብዛኞቹ ህጻናትና ሴቶች የሚገኙበት ቢያንስ 22 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር
የአሜሪካ ድምፅ

በሰሜን ጋዛ የእስራኤል ጥቃት 22 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤም ባለሥልጣናት ተናገሩ

በሰሜን ጋዛ ዛሬ እሁድ በተፈጸመ የእስራኤል የአየር ድብደባ አብዛኞቹ ህጻናትና ሴቶች የሚገኙበት ቢያንስ 22 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ እስራኤል ጥቃቱ በታጣቂዎች ላይ ያነጣጠረ ነው ስትል የተዘገበውንም የሟቾችን ቁጥር አስተባብላለች። ለሶስት ተከታታይ ሳምንታት ሰሜን ጋዛን በመነጠል የሚካሄዱት የእስራኤል ጥቃቶች እየጨመሩ በመምጣታቸው በጋዛ ሰሜናዊ ክፍል ያለው የሰብአዊነት ሁኔታ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን የረድኤት ድርጅቶች ተናግረዋል፡፡  ቀይ መስቀል ነዋሪዎች የሚያገኟቸው የምግብ፣ የውሃ እና የህክምና አቅርቦት ውስን ሲሆን በአካባቢው የተረፉት ጥቂት ሆስፒታሎች እየተጨናነቁ መምጣታቸውን አስታውቋል፡፡ በሰሜን ጋዛ በግጭቱ መካከል መውጫ አጥተው የሚገኙ ሰላማዊ ሰዎች የህክምና እንክብካቤ በማጣት የሚደርስባቸውን ዘግናኝ ሁኔታዎች ያሳሰበው መሆኑንም ቀይ መስቀል ጨምሮ ገልጿል፡፡ በተያያዘ ሌላ ዜና ፣ ዛሬ እሁድ በቴል አቪቭ ከተማ አካባቢ ወደሚገኝ የአውቶብስ ማቆሚያ ደርምሶ በገባ አንድ ከባድ መኪና 35 ሰዎች መቁሰላቸውን የእስራኤል የአደጋ ጊዜ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡  በእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ ዋና መሥሪያ ቤት አቅራቢያ የደረሰውን አደጋ ባለሥልጣናት ሆን ተብሎ የተፈጸመ እንደሆነ ጠርጥረዋል፡፡ ስለ አሸከርካሪውና ዓላማው የገለጹት ዝርዝር ነገር የለም፡፡ አሽከርካሪው ወዲያውኑ ርምጃ እንደተወሰደበት ተነግሯል፡፡  

በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር 50 ሰዎች ተገድለዋል ከ200 በላይ ቆስለዋል ተባለ

የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ከዋና ከተማይቱ ካርቱም በስተደቡብ በአል-ጃዚራ ግዛት ውስጥ ባሉ መንደሮች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 50 ሰዎች ሲገደሉ ከ200 በላይ መቁ
የአሜሪካ ድምፅ

በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር 50 ሰዎች ተገድለዋል ከ200 በላይ ቆስለዋል ተባለ

የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ከዋና ከተማይቱ ካርቱም በስተደቡብ በአል-ጃዚራ ግዛት ውስጥ ባሉ መንደሮች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 50 ሰዎች ሲገደሉ ከ200 በላይ መቁሰላቸውን የመብት ተሟጋቾች ተናገሩ፡፡  ጥቃቱ የተፈጸመው በግዛቲቱ የነበሩ አንድ ወታደራዊ አዛዥና የተወሰኑ ወታደሮቻቸው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ከድተው የሱዳን ሠራዊትን መቀላቀላቸው ከተነገረ በኋላ መሆኑን ተሟጋቾቹ ገልጸዋል፡፡ ካለፈው ዓርብ ጀምሮ “የአል ሳሪሃ እና አዝራቅ መንደሮች ጥቃት ደርሶባቸዋል” ሲሉ በሱዳን የረድኤት ሥራዎችን የሚያስተባበሩ የበጎ ፈቃድ ቡድኖች ለኤኤፍፒ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡  አካባቢው በከባድ መሣሪያ ድብደባ ሥር የሚገኝና የግንኙነት መስመሮችም የተቋረረጡ በመሆናቸው ቁስለኞችን ለማውጣት አስቸጋሪ መሆኑን መግለጫቸው አመልክቷል፡፡ ከትላንት በስቲያ ዓርብ የሱዳን የዶክተሮች ህብረት “በፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች ለዘር ማጥፋት አደጋ ተጋልጣዋል” የተባሉትን ንጽሃን ዜጎች ከተከበበው አካባቢ እንዲወጡ የሰብአዊ ኮሪደር እንዲያስከፍት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ተማጽኗል፡፡  “የሱዳን ሠራዊት ሰላማዊ ዜጎችን የመከላከል ብቃት የሌለው በመሆኑ” የነፍስ አድን ሥራው የማይቻል ሆኗል ሲል የዶክተሮቹ ህብረት አክሏል፡፡ በሱዳን የሚካሄደው ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መግደሉ ሲነገር፣ አንዳንዶቹ የሟቾቹን ቁጥር እስከ 150, 000 እንደሚያደርሷቸው ዘገባው አመልክቷል፡፡   የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከ7ሚሊዮን በላይ ሰዎች የተፈናቀሉ መሆናቸውን በመግለጽ “በዓለም ትልቁ የተፈናቃዮች ቀውስ” ሲል ጠርቶታል፡፡ የዓለም የገንዘብ ድርጅት ቀውሱ ለሱዳን አጎራባች ሀገራት የሚተርፍ መሆኑን አመልክቷል፡፡ አካባቢዎቹን ለኢኮኖሚ ችግር፣ የጸጥታ ጉዳዮች እና ከተፈናቃዮች ጋር ተያይዘው ለሚመጡ ሌሎች ፈተናዎች እንደሚጋልጣቸው በማስጠንቀቅ “የግጭቱ ቀጣናዊ ተጽእኖ እጅግ ከባድ ነው” ብሏል፡፡  

በፊሊፒንስ ትራሚ አውሎ ነፋስ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 110 ደረሰ

በፊሊፒንስ «ትራሚ» የሚል ስያሜ በተሰጠው ከባድ አውሎ ንፋስ እና ዝናብ ባስከተለው አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 110 ደርሷል ሲሉ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ዛሬ
የአሜሪካ ድምፅ

በፊሊፒንስ ትራሚ አውሎ ነፋስ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 110 ደረሰ

በፊሊፒንስ «ትራሚ» የሚል ስያሜ በተሰጠው ከባድ አውሎ ንፋስ እና ዝናብ ባስከተለው አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 110 ደርሷል ሲሉ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ዛሬ እሁድ ተናገሩ ።  እስካሁን 42 የሚሆኑ ሰዎች ደብዛቸው እንደጠፋ ሲሆን የነፍስ አድን ሠራተኞች ፍለጋቸውን ቀጥለዋል፡፡ ባላፈው ሀሙስ እኤአ ጥቅምት 24 ፊሊፒንስን የመታው ትራሚ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን ከመኖሪያ እና ቀያቸው አፈናቅሏል፡፡  ፊሊፒንስን ደቁሶ ወደ ቬትናም የገሠገሠው ትራሚ በማዕከላዊ የሀገሪቱ ክፍል ዛሬ እሁድ ከባድ ዝናብ እንዲሁም በሰዓት 70 ኪሎሜትሮች የሚፈጥን ነፋስ ማስተከተሉ ተነግሯል፡፡   የትራሚ ከባዱ አውሎ ነፋስ፣ ቬትናም ከመድረሱ በፊት፣ ባለሥልጣናት የጀልባና የባህር ላይ እንቅስቃሴዎችን በማገድ ፣ 25ሺ ሰዎችም አካባቢያቸውን ለቀው እንዲቆዩ ማድረጋቸው ተመልክቷል፡፡ የአየር ትንበያ ባለሥልጣናት፣ በአካባቢ አየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ሳቢያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእስያ ፓስፊክ ክልል የሚታዩ አውሎ ነፋሶች ከባህር ላይ ወደ ምድር ዳርቻ ተጠናክረው እየተጠጉ መንፈስ መያዛቸውና በየብስ ላይ ለረጅም ጊዜ መቆየታቸው በጥናት መረጋገጡን ተናግረዋል፡፡  

ጆርጂያውያን ሲመርጡ ውለዋል 

ጆርጂያውያን ዛሬ ወደ አውሮፓ ህብረት ወይም ወደ ሩሲያ ምህዋር ሊወስድ በሚችል ምርጫ ላይ ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል፡፡  ገዥው ፓርቲ የሩስያ ደጋፊነት ስጋት ከጊዜ
የአሜሪካ ድምፅ

ጆርጂያውያን ሲመርጡ ውለዋል 

ጆርጂያውያን ዛሬ ወደ አውሮፓ ህብረት ወይም ወደ ሩሲያ ምህዋር ሊወስድ በሚችል ምርጫ ላይ ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል፡፡  ገዥው ፓርቲ የሩስያ ደጋፊነት ስጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣባት ጆርጂያ የተካሄደው ምርጫ የአውሮፓን ምኞት የሚወስን እንደሆነም ተገልጿል፡፡ የፓርላማ ምርጫው ዲሞክራሲን በማፈን ወደ ሩሲያ አዘንብሏል ተብሎ ከተከሰሰው ገዥው ፓርቲ በተቃራኒ የተሰለፉት የምዕራቡ ዓለም ደጋፊ የሆኑ የተቃዋሚ ሃይሎች ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታውቅ ሁኔታ ህብረት ያሳዩበት ነው ተብሏል።  ብራሰልስ ምርጫው የአውሮፓ ህብረት እጩ የሆነችው ጆርጅያን ወደ ህብረቱ የመቀላቀል እድሏን እንደሚወስን አስጠንቅቋል።  ብዙዎች የሃገሬው ሰዎችም ምርጫው በሕይወታቸው ውስጥ በጣም ወሳኝ ድምጽ ሊሆን እንደሚችል ያምናሉ፡፡ ጆርጂያ ወደ አውሮፓ ህብረት አባልነት መመለሱን ወይም አምባገነንነትን ተቀብላ ወደ ሩሲያ ምህዋር መግባቷን የሚወሰንበት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ 

ዩናይትድ ስቴትስ ለታይዋን የ2 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ አጸደቀች 

ዩናይትድ ስቴትስ ለታይዋን ባጸደቀችው የ2 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ ጥቅል ውስጥ በዩክሬን የተሞከረው የላቀ የአየር መከላከያ ሚሳኤል ጭምር መካተቱን
የአሜሪካ ድምፅ

ዩናይትድ ስቴትስ ለታይዋን የ2 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ አጸደቀች 

ዩናይትድ ስቴትስ ለታይዋን ባጸደቀችው የ2 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ ጥቅል ውስጥ በዩክሬን የተሞከረው የላቀ የአየር መከላከያ ሚሳኤል ጭምር መካተቱንና ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ደሴቷ የሚላክ መሆኑን ፔንታጎን ትላንት አርብ አስታውቋል፡፡  ዩናይትድ ስቴትስ በቻይና ይገባኛል ጥያቄ ከምታነሳባት ታይዋን ጋር ምንም እንኳን መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ባይኖራትም ራሷን እንድትከላከል የሚያስችል ድጋፍ ለመስጠት በህግ ትገደዳለች፤ ይህ ደግሞ የቤጂንግ የሁልጊዜ ቁጣ ነው።  ቻይና ያለፈውን ሳምንት ጨምሮ በታይዋን ላይ የምታካሄዳቸው ወታደራዊ ጫናዎች እየጨመረ ሲሆን ይህም በግንቦት ወር ላይ ቺንግ-ቴ የታይዋን ፕሬዝዳንት ሆነው ስልጣን ከያዙ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ያካሄደችው ወታደራዊ እንቅስቃሴነው፡፡  የፔንታጎን የመከላከያ ደህንነት ትብብር ኤጀንሲ እንዳስታወቀው አዲሱ ሽያጭ 828 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ዋጋ ያላቸው 1.16 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ የሚሳኤል እና ራዳር ስርዓት መሳርያዎችን ያካተተ ነው።    የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር መግለጫውን በደስታ እንደተቀበለው አስታውቋል፣ የአየር መከላከያዎቹ በቻይና የሚደረጉ ተደጋጋሚ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከልና የታይዋን የአየር መከላከያ አቅም ለማሳደግ ያግዛል ብሏል፡፡   የታይዋን ጦር ከቻይና የሚደርስ ማንኛውንም ጥቃት በተሻለ ሁኔታ ለመቋቋም ወሳኝ የባህር ሃይል መከላከያ የራሱን ሰርጓጅ መርከብ መገንባትን ጨምሮ  ትጥቁን እያጠናከረ ይገኛል። 

ሩስያ በማዕከላዊ ዩክሬን ባደረሰችው ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ 

ሩስያ ባደረሰችው የሚሳኤል ጥቃት በዩክሬን ዲኒፕሮ ከተማ አንድ ህፃን ጨምሮ ሶስት ሰዎችን ሲገደሉ  በኪየቭ እና አካባቢው ላይ በደረሰው ጥቃት ደግሞ ታዳጊን ጨ
የአሜሪካ ድምፅ

ሩስያ በማዕከላዊ ዩክሬን ባደረሰችው ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ 

ሩስያ ባደረሰችው የሚሳኤል ጥቃት በዩክሬን ዲኒፕሮ ከተማ አንድ ህፃን ጨምሮ ሶስት ሰዎችን ሲገደሉ  በኪየቭ እና አካባቢው ላይ በደረሰው ጥቃት ደግሞ ታዳጊን ጨምሮ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን ባለስልጣናቱ ዛሬ አስታውቀዋል፡፡  የማዕከላዊ ዲኒፕሮ ፔትሮቭስክ ክልል ገዥ ሰርጊ ሊሳክ እንዳሉት በዲኒፕሮ ላይ በአንድ ሌሊት በደረሰ ጥቃት 19 ሰዎች ጉዳት የደርሰባቸው ሲሆን በርካታ ሕንፃዎች ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡ ባለ ሁለት ፎቅ የመኖሪያ ሕንፃ መውደሙንም ገልጸዋል፡፡  በሩሲያ ወረራ ኪየቭን ጨምሮ የዩክሬን ከተሞች የሰው አልባ አውሮፕላኖች እና የሚሳኤል ጥቃቶች በተደጋጋሚ ተፈጽሞባቸዋል፡፡  ሞስኮ በኤሌክትሪክ ሃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት እየፈፀመች ባለችበት በአሁኑ ወቅት ኪየቭ ገና ከባዱ ክረምት ከመግባቱ በፊት ከአጋሮቿ ተጨማሪ የአየር መከላከያ እንዲላክላት እየጠየቀች ነው፡፡   

እስራኤል ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት በኢራን ላይ ማድረሷን አስታወቀች 

እ.አ.አ ጥቅምት 1 ኢራን በባሊስቲክ ሚሳኤል በእስራኤል ላይ ላደረሰችው ጥቃት ምላሽ በሆነው በዚህ የአጸፋ ጥቃት የጦር አውሮፕላኖች በመላ ኢራን ወታደራዊ ጣቢያ
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት በኢራን ላይ ማድረሷን አስታወቀች 

እ.አ.አ ጥቅምት 1 ኢራን በባሊስቲክ ሚሳኤል በእስራኤል ላይ ላደረሰችው ጥቃት ምላሽ በሆነው በዚህ የአጸፋ ጥቃት የጦር አውሮፕላኖች በመላ ኢራን ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ለብዙ ሰዓታት ድብደባ ማካሄዳቸውን የእስራኤል ጦር አስታውቋል፡፡  ከአንድ አመት በላይ በዘለቀው ጦርነት በኢራን ላይ ያደረሰችውን ከባድ ጥቃት ማጠናቀቋንም እስራኤል  ገልጻለች፡፡ የኢራን አጋር የሆነው ሃማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ካደረሰ በኋላ ወደ ብዙ የግጭት ግንባሮች ተስፋፍቶ ቴህራንና ሌሎች ቀጠናዊ አጋሮቿን የጦርነቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ ሁነዋል፡፡  የእስራኤል መከላከያ ሃይል ዛሬ ረፋድ ላይ በሰጠው መግለጫ የጦር አውሮፕላኖቹ «በኢራን ውስጥ ባሉ በርካታ አካባቢዎች በወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ያነጣጠሩና ትክክለኛ ጥቃቶችን ካደረሱ በኋላ በሰላም ወደ አገራቸው ተመልሰዋል» ብሏል። ይህ መግለጫ የወጣውም ኢራን ውስጥ የመጀመርያው ፍንዳታ ከተሰማ ከአራት ሰዓታት በኋላ ነው፡፡  የእስራኤል መከላከያ ሃይል ቃል አቀባይ ሪየር አድሚራል ዳንኤል ሃጋሪ ለጋዜጠኞች የእስራኤል የአየር ድብደባ አላማቸውን ያሳኩ እንደነበሩ የገለጹ ቢሆንም ማስረጃ ግን ወዲያውኑ አላቀረቡም።  የኢራን መንግስት የዜና ጣቢያ የሀገሪቱ የአየር መከላከያ ድርጅትን ጠቅሶ እንደዘገበው እስራኤል በቴህራን እና በምዕራባዊው ኩዝስታን እና ኢላም አውራጃዎች በሚገኙ ወታደራዊ ማዕከላት ላይ ጥቃት አድርሳለች ብሏል። የኢራን ሃይሎች  አብዛኛውን ጥቃት “በስኬት” ማክሸፍ መቻላቸውንና “ውስን ጉዳት” ብቻ መድረሱንም ጨምሮ ገልጿል፡፡  የኢራን ባለስልጣናት የእስራኤል የአየር ጥቃት ማክሸፍ ሰለመቻላቸውም ሆነ ስላደረሰው ጉዳት ማስረጃ ማቅረብ አልቻሉም። ነገር ግን የመንግስት ሚዲያ የኢራን ጦርን ጠቅሶ እንደዘገበው በእስራኤል ጥቃት ሁለት ወታደሮች ተገድለዋል።  አንድ የአሜሪካ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ደግሞ እስራኤል “በኢራን ህዝብ ከሚኖርባቸው ወጣ ባሉ አካባቢዎች በሚገኙ በርካታ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ትክክለኛ  የአየር ድብደባ አድርጋለች'' ብለዋል።  ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስም ስለእስራኤል ወታደራዊ ርምጃ ገለፃ ተደርጎላቸዋል ሲል ዋይት ሀውስ ትላንት አስታውቋል። ያሉትን ለውጦችን በቅርበት እየተከታተሉ መሆናቸውንም ተገልጿል፡፡  የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ባለስልጣን ለቪኦኤ ሲናገሩ “በጥቃቱ ዙርያ ቅድሚያ አሳውቀውን ነበር” ነገር ግን እኛ አልተሳተፍንም ብለዋል፡፡   የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ከእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ጋር ዛሬ የተነጋገሩ ሲሆን የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በኢራን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ስላደረሰው ጥቃት አዳዲስ  መረጃዎችን እንዳጋሯቸው ፔንታጎን ንግግራቸውን በተመለከተ ካወጣው ጽሁፍ ታውቋል፡፡  ኦስቲን ዩናይትድ ስቴትስ ለእስራኤል ደህንነት እና ራስን የመከላከል መብት ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ ማረጋገጣቸውም ተገልጿል፡፡ 

የጡት ካንሰርን ማሸነፍ ቆይታ ከበሽታው ካገገሙት ዶ/ር ፍሬሕይወት ደርሶ ጋር

ወርሃ ጥቅምት የአለም አቀፉ የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር በመባል ይታወቃል። በአለም ላይ ከስምንት ሴቶች አንዷ በጡት ካንሰር እንደምትያዝ በዩናይትድ
የአሜሪካ ድምፅ

የጡት ካንሰርን ማሸነፍ ቆይታ ከበሽታው ካገገሙት ዶ/ር ፍሬሕይወት ደርሶ ጋር

ወርሃ ጥቅምት የአለም አቀፉ የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር በመባል ይታወቃል። በአለም ላይ ከስምንት ሴቶች አንዷ በጡት ካንሰር እንደምትያዝ በዩናይትድ ስቴትስ በካንሰር ዙሪያ የሚሰራው ገባሬ ሰናዩ የአሜሪካ የካንሰር ማኅበረሰብ አማካኝነት የተሰሩ ጥናቶች ያመላክታሉ። በኢትዮጵያም በበሽታው ዙሪያ ያለው ግንዛቤ እና እንዲሁም የህክምናው ተደራሽነት አነስተኛ መሆኑን ታካሚዎች እና የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ።

ኦብነግ በምክክር ኮሚሽኑ ገለልተኝነት ላይ ጥያቄ አነሳ፣ ኮሚሽኑ አልተቀበለውም

ሶማሌ ክልል ውስጥ በተቃዋሚ ፓርቲነት የሚታወቀው፣ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብግ) በቅርቡ በክልሉ የአጀንዳ ልየታ ማጥናቀቁን ባስታወቀው፣ በሕዝብ
የአሜሪካ ድምፅ

ኦብነግ በምክክር ኮሚሽኑ ገለልተኝነት ላይ ጥያቄ አነሳ፣ ኮሚሽኑ አልተቀበለውም

ሶማሌ ክልል ውስጥ በተቃዋሚ ፓርቲነት የሚታወቀው፣ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብግ) በቅርቡ በክልሉ የአጀንዳ ልየታ ማጥናቀቁን ባስታወቀው፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋቋመው፣ የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለልተኝነት ላይ ጥያቄ አነሳ። የኮሚሽኑ የተሳታፊዎች መረጣ በክልሉ ገዢ ፓርቲ ብልጽግና ተጽዕኖ ሥር የወደቀ መኾኑን ፓርቲው በማኅበራዊ ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽነር መስፍን አርአያ፣ ተቋማቸው ግጭት ያለባቸውን ክልሎች ጨምሮ በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች ምክክሩን ለማካሄድ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸው፣ የቀረበው ወቀሳ አስተባብለዋል። በሌላ በኩል የፓርቲውን ስጋት የተጋሩት ዋና መቀመጫውን ጄኔቭ ያደረገው፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ሃይለማርያም፣ እንዲህ ዐይነት የገለልተኝነት ጥያቄ ሲነሳ የመጀመሪያ አለመኾኑን ጠቅሰው፤ ኮሚሽኑ አሳታፊ መኾን እንደሚገባው መክረዋል።

 የአሜሪካ ሴት መራጮች

በዘንድሮው የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ሴት መራጮች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይጠበቃል፡፡  በቅርብ ዓመታት  በመራጭነት የሚመዘገቡም ኾነ  ድምጽ የሚሰጡ ሴቶ
የአሜሪካ ድምፅ

 የአሜሪካ ሴት መራጮች

በዘንድሮው የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ሴት መራጮች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይጠበቃል፡፡  በቅርብ ዓመታት  በመራጭነት የሚመዘገቡም ኾነ  ድምጽ የሚሰጡ ሴቶች ቁጥር ከወንዶቹ እየበለጠ መጥቷል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020 ዓ.ም ምርጫ የሴቶቹ መራጮች ቁጥር ከወንዶቹ ቁጥር በብዙ ሚሊዮኖች የበለጠ እንደነበር ታውቋል፡፡  የሴቶቹ መራጮች  የምርጫ ተሳትፎ አንድ ወጥ  አይሁን እንጂ በድምጽ አሰጣጣቸው በአመዛኙ ወደ አንደኛው ፓርቲ እንደሚያጋድሉ  የታወቀ ነው፡፡ የአሜሪካ ድምጿ ዶራ መኳዋር ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

የ«ወገኔ ኢትዮጵያ» የርኅራኄ ምሽት 

በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር ለዓመታት ሰብአዊ ተግባራትን ያከናወነው «ወገኔ ኢትዮጵያ» የሰብአዊ ተቋም የእንቅስቃሴው
የአሜሪካ ድምፅ

የ«ወገኔ ኢትዮጵያ» የርኅራኄ ምሽት 

በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር ለዓመታት ሰብአዊ ተግባራትን ያከናወነው «ወገኔ ኢትዮጵያ» የሰብአዊ ተቋም የእንቅስቃሴውን 24ኛ ዓመት ከሰሞኑ አክብሯል። የሰብአዊ ተቋሙ፣ በኢትዮጵያውያን ሕይወት ላይ ለውጥ ያመጡ ተግባራቱን ለተሳታፊዎች ከማስተዋወቅ በተጨማሪ፣ ለቀጣይ የግብረ ሠናይ እንቅስቃሴው የሚረዱ መርሐ ግብሮችንም አስተዋውቋል። በስፕሪንግ ፊልድ ቨርጅኒያ የተካሔደውን ሥነ ሥርዐት በተመለከተ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

VOA60 Africa - LRA rebel commander in Uganda sentenced to 40 years in prison for war crimes

Uganda: A court on Friday sentenced Thomas Kwoyelo, a mid-level commander in the Lord's Resistance Army (LRA) rebel group, to 40 years in prison for war crimes. The court found Thomas Kwoyelo guilty in August, in the first domestic trial of a senior member o
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - LRA rebel commander in Uganda sentenced to 40 years in prison for war crimes

Uganda: A court on Friday sentenced Thomas Kwoyelo, a mid-level commander in the Lord's Resistance Army (LRA) rebel group, to 40 years in prison for war crimes. The court found Thomas Kwoyelo guilty in August, in the first domestic trial of a senior member of the LRA.

VOA60 World - Philippines: Tropical storm Trami leaves at least 46 people dead

Philippines: Tropical storm Trami left at least 46 people dead after extensive flooding, and forecasters are warning of the possibility that the storm could make a U-turn next week as it is pushed back by high-pressure winds in the South China Sea.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Philippines: Tropical storm Trami leaves at least 46 people dead

Philippines: Tropical storm Trami left at least 46 people dead after extensive flooding, and forecasters are warning of the possibility that the storm could make a U-turn next week as it is pushed back by high-pressure winds in the South China Sea.

VOA60 America - Blinken meets Lebanese Prime Minister to discuss Israel’s strikes on the country

U.S. Secretary of State Antony Blinken met in London with Lebanon's caretaker Prime Minister Najib Mikati to discuss Israel’s strikes on the country. He also met separately with Jordanian Foreign Minister Ayman Safadi.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Blinken meets Lebanese Prime Minister to discuss Israel’s strikes on the country

U.S. Secretary of State Antony Blinken met in London with Lebanon's caretaker Prime Minister Najib Mikati to discuss Israel’s strikes on the country. He also met separately with Jordanian Foreign Minister Ayman Safadi.

በኢትዮጵያ የርዳታ እህል ምዝበራ እስከ አሁን ባሉ መረጃዎች የሚታወቀው

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት(USAID) በዓለም የምግብ ፕሮግራም(WFP) አማካይነት በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል የሚያሰራጨው የርዳ
የአሜሪካ ድምፅ

በኢትዮጵያ የርዳታ እህል ምዝበራ እስከ አሁን ባሉ መረጃዎች የሚታወቀው

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት(USAID) በዓለም የምግብ ፕሮግራም(WFP) አማካይነት በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል የሚያሰራጨው የርዳታ እህል፣ በተገቢው መንገድ “ለተረጂው ባለመድረሱ”፣ የርዳታ ዕደላው እንዲቋረጥ ማድረጉን፣ በግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. አስታውቆ ነበር።  ይኸው የርዳታ እህል ምዝበራ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ «ግዙፉ» እንደኾነ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅቱ አመልክቷል። ምንም እንኳን፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቱ፣ በኢትዮጵያ ያቋረጠው የምግብ ርዳታ በድጋሚ እንዲሰጥ ቢፈቅድም፤ በአገሪቱ የርዳታ እህል ምዝበራ የረጅም ዓመታት ዕድሜ እንዳለው አውስቷል። የዓለም የምግብ መርሐ ግብር(WFP) እና የዩናይትድ ስቴትሱ ዓለም አቀፍ የልማት ተራዶኦ (USAID)፣ ከዚኽ ምዝበራ ጀርባ ማን እንዳለ ምርመራ እያደረጉ መኾናቸውን ቢያስታውቁም፣ በመካከላቸው ያለው ግንኙነት መሻከሩ ተጠቁሟል። ሮይተርስ የዜና ወኪል፣ በትግራይ ክልል ተዘዋውሮ፣ የርዳታ እህሉ በማን እንደተዘረፈ እስከ አሁን ድረስ የታወቁት መረጃዎች ምን እንደሚመስሉ፣ የሁለቱን ዓለም አቀፍ ተቋማት ባልደረቦች እና በክልሉ ያሉ ባለድርሻ አካላትን አነጋግሮ ያጠናቀረውን ዘገባ፣ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

ብሊንከን በተባባሰው ጦርነት ከሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋራ ተወያዩ

ዋሽንግተን የቤይሩት መንግሥት በሂዝቦላ ላይ ክስ እንዲመሰርት ግፊት በምታደርግበት በአኹኑ ወቅት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
የአሜሪካ ድምፅ

ብሊንከን በተባባሰው ጦርነት ከሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋራ ተወያዩ

ዋሽንግተን የቤይሩት መንግሥት በሂዝቦላ ላይ ክስ እንዲመሰርት ግፊት በምታደርግበት በአኹኑ ወቅት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ እስራኤል በሀገሪቱ ላይ ስላደረሰችው ጥቃት ከሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ዛሬ ዓርብ ውይይት አድርገዋል። ብሊንከን ከአንድ ቀን በፊት በሊባኖስ ጉዳይ ፓሪስ ላይ በተካሄደው ጉባኤ ተካፋይ ከነበሩት ከሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ነጂብ ሚካቲ ጋር ለንደን ውስጥ የተገናኙት ከመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት ሲመለሱ  ነው። ሁለቱ በካሜራዎች ፊት ፈገግ ሲሉ ቢታዩም ምንም አስተያየት አልሰጡም። የእስራኤል ዋነኛ የፖለቲካ እና ወታደራዊ አጋር የሆነችው አሜሪካ እስራኤል ሊባኖስ ውስጥ በኢራን በሚደገፈው የሂዝቦላ ሚሊሻ ላይ ያነጣጠረ የአንድ ወር የቦምብ ጥቃት ባደረሰች ጊዜ አፋጣኝ የተኩስ አቁም ጥሪ አላቀረበችም። ይሁን እንጂ ብሊንከን ለአፋጣኛ የዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ጥሪ አድርገዋል፡፡ ብሊንከን «ይህ ወደ ተራዘመ ዘመቻ እንዳያመራ ፣ሊያመራም እንደማይገባ እና እስራኤል በሰለማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ አለባት፣ የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ሃይሎችን ወይም የሊባኖስን ጦር ሃይሎችን አደጋ ላይ እንዳይጥል ማድረግም ይኖርባታል» ሲሉ ትላንት ሐሙስ ዶሃ ውስጥ ተናግረዋል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ ለረጅም ጊዜ የዋለለውን የሊባኖስ ማዕከላዊ መንግሥት፣ ደህንነቱን የማስጠብቅ ኃላፊነት እንዲወስድ እና የራሱ የሆነ ጦር የመሰረተውን በኢራን የሚደገፈውን የሺዓ ንቅናቄ አራማጅ ሂዞቦላህን ትጥቅ እንዲያስፈታ ጥሪ አቅርባለች፡፡ እ.ኤ.አ ጥቅምት 7 ቀን 2023፣ የፍልስጤም ታጣቂዎች ያደረሱት ጥቃት፣ ያስከተለውን መጠነ ሰፊ የእስራኤል ወታደራዊ ጥቃት ተከትሎ፣ ሂዝቦላህ አጋርነቱን ለመግለጽ፣ ሚሳይሎችን ወደ እስራኤል ሲተኩስ ቆይቷል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ለእስራኤል አቻቸው ዮአቭ ጋላንት ባስተላለፉት ጥሪ ቢያንስ 11 የሊባኖስ ወታደሮችን የገደለው የእስራኤል ጦር ጥቃት እንዳሳሰባቸው ገልጿል።

በአማራ ክልል የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ለጥቃት መጋለጣቸውን ማኅበሩ አስታወቀ

በአማራ ክልል በቀጠለው ግጭት ሳቢያ አራት የጤና ባለሞያዎች መገደላቸውንና በርካቶች መታሰራቸውን የአማራ ክልል የጤና ባለሞያዎች ማኅበር አስታወቀ። “በተለ
የአሜሪካ ድምፅ

በአማራ ክልል የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ለጥቃት መጋለጣቸውን ማኅበሩ አስታወቀ

በአማራ ክልል በቀጠለው ግጭት ሳቢያ አራት የጤና ባለሞያዎች መገደላቸውንና በርካቶች መታሰራቸውን የአማራ ክልል የጤና ባለሞያዎች ማኅበር አስታወቀ። “በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚገኙ የጤና አገልግሎት ባለሞያች የሞያ ነፃነት አጥተዋል” ያሉት የአማራ ክልል ጤና ባለሞያዎች ማኅበር ጸሀፊ “ባለሞያዎች የታጠቁ ኃይሎች በሚሰነዝሩት ጥቃት ይገደላሉ፣ ይታሰራሉ፤” ብለዋል:: ከሁለት ሳምንት ወዲህ በምዕራብና ሰሜን ጎጃም ዞኖች የሚኖሩ ሁለት ፋርማሲስት ሲገደሉ በባሕር ዳር ከተማ አንዲት ነርስ በትላንትናው ዕለት ምሽት ላይ ሥራ ላይ እያለች ባልታወቁ ታጣቂዎች በጥይት ተመትታ መቁሰሏን የማኅበሩ ጸሐፊ ተናግረዋል። ለደህንነቱ በመስጋት ስሙም ኾነ የሚሠራበት የሕክምና ተቋም እንዳይጠቀስ የጠየቀ አንድ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚኖር የሕክምና ባለሞያ መተማ አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ የሚሠሩ ሁለት የሞያ አጋሮቹ እንዲሁም በጎንደር ከተማ የሚገኘው የአይራ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ‘ከፋኖ ጋራ ግንኙነት አላችሁ” በሚል መታሰራቸውን ነግረውናል። በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡን የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ የእጅ ስልክ ላይ ብንደውልም ስልኩ ባለ መስራቱ ምክንያት አስተያየታቸውን ማካተት አልቻልንም። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

ብርቱ ፍልሚያ የሚደረግባቸው የ2024ቱን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት የሚወስኑት ግዛቶች

በየአራት ዓመቱ የሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፉክክር ትኩረቱን አንድ ጊዜ የአንደኛው ፓርቲ በሌላ ጊዜ ደሞ የተፎካካሪው ፓርቲ እጩ በመፈራ
የአሜሪካ ድምፅ

ብርቱ ፍልሚያ የሚደረግባቸው የ2024ቱን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት የሚወስኑት ግዛቶች

በየአራት ዓመቱ የሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፉክክር ትኩረቱን አንድ ጊዜ የአንደኛው ፓርቲ በሌላ ጊዜ ደሞ የተፎካካሪው ፓርቲ እጩ በመፈራረቅ ወደሚያሸንፉባቸው ግዛቶች ይመልሳል። እነዚህ ብርቱ ፍልሚያው የሚካሄድባቸው ግዛቶች፣ በተደጋጋሚ የአንዱ ፓርቲ ደጋፊ በቁጥር አይሎ ከሚታይባቸው የሚበዙት ግዛቶች በተለየ መልኩ የምርጫውን ውጤት ወደ አሸናፊው በማድረግ ወደ ዋይት ሀውስ ገብቶ አገሪቱን በፕሬዝዳንትነት የመምራት እጣ የሚገጥመው ሰው ማን እንደሚሆን ይወስናሉ። ይህን መሰል ግዙፍ ተጽዕኖ የማሳደር ዕድል ያላቸው ጥቂት ግዛቶች እንደመሆናቸው የምርጫ ዘመቻዎች መጠኑ የበዛ ገንዘብ በእነኚህ ወሳኝ ግዛቶች ውስጥ ለሚያካሂዷቸው የምረጡኝ ዘመቻዎቻቸው ወጭ ያደርጋሉ። በተደጋጋሚ እንደታየውም ለእነኚህ ግዛቶች አሸናፊ የተመደቡት ድምጾች አጠቃላዩን የምርጫ ውጤት ስለሚወስኑ የምርጫ ዘመቻዎቹ ጠንካራ የምረጡኝ ቅስቀሳ ትኩረት ያደርጋቸዋል።

VOA60 Africa - Uganda: Death toll in fuel tanker explosion rises to at least 15

The death toll rose to at least 15 on Wednesday, a day after a fuel tanker exploded in a northern Kampala suburb. The victims had gathered to scoop up fuel after the tanker overturned on a road connecting Kampala and the northern city of Gulu.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Uganda: Death toll in fuel tanker explosion rises to at least 15

The death toll rose to at least 15 on Wednesday, a day after a fuel tanker exploded in a northern Kampala suburb. The victims had gathered to scoop up fuel after the tanker overturned on a road connecting Kampala and the northern city of Gulu.

VOA60 America - New evidence China, Russia and Iran targeting US elections

China, Iran and Russia are aggressively expanding their efforts to influence American voters to potentially sway the result of the upcoming U.S. elections, according to two threat intelligence reports Wednesday.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - New evidence China, Russia and Iran targeting US elections

China, Iran and Russia are aggressively expanding their efforts to influence American voters to potentially sway the result of the upcoming U.S. elections, according to two threat intelligence reports Wednesday.

VOA60 World - At least 16 killed, including children, in Israeli airstrike on school in Nuseirat camp

At least 16 Palestinians were killed, including children, and 32 others wounded in an Israeli airstrike on a school in the Nuseirat refugee camp on Thursday, officials at Nuseirat's Al-Awda Hospital said.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - At least 16 killed, including children, in Israeli airstrike on school in Nuseirat camp

At least 16 Palestinians were killed, including children, and 32 others wounded in an Israeli airstrike on a school in the Nuseirat refugee camp on Thursday, officials at Nuseirat's Al-Awda Hospital said.

በሞዛምቢክ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የገዢው ፓርቲ እጩ አሸነፉ

በሞዛምቢክ ከሁለት ሳምንት በፊት በተደረገውና አጨቃጫቂ በሆነው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የገዢው ፍሬሊሞ ፓርቲ እጩ ዳንኤል ቻፖ ማሸነፋቸውን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚ
የአሜሪካ ድምፅ

በሞዛምቢክ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የገዢው ፓርቲ እጩ አሸነፉ

በሞዛምቢክ ከሁለት ሳምንት በፊት በተደረገውና አጨቃጫቂ በሆነው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የገዢው ፍሬሊሞ ፓርቲ እጩ ዳንኤል ቻፖ ማሸነፋቸውን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ አስታውቋል። ላለፉት ሃምሳ ዓመታት በስልጣን ላይ የቆየው የፍሬሊሞ ፓርቲ እጩው ዳንኤል ቻፖ 71 በመቶውን ድምጽ ሲያገኙ፣ የተቀናቃኙ ፖዴሞስ ፓርቲ ወኪሉ ቬናንሲዮ ሞንዳኔ ደግሞ 20 በመቶ ድምጽ እንዳገኙ ብሔራዊ የምርጫ ኮሚሽኑ አስታውቋል። ተቀናቃኙ የምርጫውን ውጤት አለመቀበል ብቻ ሳይሆን አሸናፊው እርሳቸው መሆናቸውን በማስታወቃቸው እና ባለፈው ቅዳሜ ጠበቃቸውና አንድ ሌላ የተቃዋሚ አንቂ በመገደላቸው በሃገሪቱ ውጥረት መስፈኑ ተነገሯል፡፡ ጠበቃው ኤልቪኖ ዲያስ እና የማኅበራዊ አንቂው ፓውሎ ጉዋምቤ የተቃዋሚውን እጩ በመወከል የምርጫውን ውጤት በሕግ ለመሞገት በዝግጅት ላይ ነበሩ። ተቃዋሚው ቬናንሲዮ ሞንዳኔ ለግድያው የፀጥታ ኃይሎችን ተጠያቂ አድርገው፣ ቀጣዩ ዒላማ ምናልባትም እርሳቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል። ሞንዳኔ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረገ ጥሪ ሲያደርጉ፣ ተሰናባቹ ፕሬዝደንት ፊሊፔ ኒዩሲ፣ «ኃይል የተቀላቀለበት የተቃውሞ ጥሪ ማድረግ የወንጀል ድርጊት ነው» ሲሉ አስጠንቅቀዋል። አዲስ የተመረጡትና በመጪው ጥር ስልጣናቸውን የሚረከቡት ዳንኤል ቻፖ፣ ሞዛምቢክ ከፖርቹጋል ነፃ ከወጣች ወዲህ ተወልደው ፕሬዝደንት የሆኑ የመጀመሪያው ፖለቲከኛ ይሆናሉ። 

Get more results via ClueGoal