በፕሬዝዳንትነት ለመመረጥ የመመዘኛ መስፈርቶች
newsare.net
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ሆኖ ለመመረጥ የሚያስፈልጉት መስፈርቶች ምንድን ናቸው?በፕሬዝዳንትነት ለመመረጥ የመመዘኛ መስፈርቶች
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ሆኖ ለመመረጥ የሚያስፈልጉት መስፈርቶች ምንድን ናቸው? Read more
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ሆኖ ለመመረጥ የሚያስፈልጉት መስፈርቶች ምንድን ናቸው? Read more
በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት በሰላማዊና ፓለቲካዊ መንገድ ለመፍታት ቃል መገባቱን በትግራይ ክልል የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት ገለጹ። በትግራይ ክልል በቅርቡ የራሳቸው ሲኖዶስ የመሰረቱት ሊቃነ ጳጳሳት፣ በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩንት ለመፍታት የክልልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታችው ረዳ ና ዶክተር የፓርቲው ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በዛሬው ዕለት ፊት ለፊት እንዲገናኙ እንዳደረጉ ገለጸዋል። ፖለቲከኞቹ በቅርቡ ተገናኝተው እንደሚወያዩ ሊቀጳጳሳቱ ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደቡብ አፍሪካ፣ ፕሪቶሪያ ላይ የተካሄደው ተኩስን በዘላቂነት የማቆም ስምምነት ነገ ሁለተኛ ዓመቱን የሚደፍን ሲኾን፣ ስምምነቱን አስመልክቶ በመቐለ ከተማ የነዋሪዎች አስተያየት ጠይቀናል። ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
በኢትዮጵያ ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ 7.3 ሚሊዮን ሰዎች በወባ መያዛቸውንና 1ሺሕ 157 በበሽታው መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በኢትዮጵያ 75 ከመቶ የሚሆነው መሬት ለወባ ትንኝ ተጋላጭ በመሆኑ ለሃገሪቱ ከፍተኛ የጤና ተግዳሮት እንደደቀነም ድርጅቱ አስታውቋል። በእነዚህ አካባባዎች ከሚኖሩት ውስጥ 69 በመቶ የሚሆኑት በወባ የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ሲሆን፣ ከአምስት ዓመት በታች ሳሉ ከሚሞቱት ሕፃናት ውስጥ 20 በመቶ የሚሆኑት ሕይወታቸው የሚያልፈው በወባ ምክንያት መሆኑንም ዓለም አቀፉ የጤና ተቋም አስታውቋል። በተለይም ግጭት ባለባቸው ሥፍራዎች የጤና አገልግሎት ማዳረሡ አስቸጋሪ እንደሆነም የጤና ድርጅቱ ጠቁሟል። የሌሎች በሽታዎች መዛመትም ሁኔታውን ይበልጥ አስቸጋሪ እንዳደረገው ድርጅቱ አስታውቋል።
የቦትስዋናው ፕሬዝደንት ሞከዌትሲ ማሲሲ በምርጫ መሸነፋቸውን አምነዋል። የምርጫው ውጤት ገና ባይታወጅም ሃገሪቱ ከእንግሊዝ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 58 ዓመታት በሥልጣን ላይ የከረመው ፓርቲያቸው ‘የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ’ እስከ አሁን በተገኘው ውጤት በአራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ‘አምብሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ’ በከፍተኛ ድምጽ እየመራ ሲሆን፣ የፓርቲው እጩ ዱማ ቦኮ በዓለም ከፍተኛ አልማዝ አምራች ከሆኑት ሃገራት ውስጥ አንዷ የሆነችው ደቡብ አፍሪካዊቷ ሃገር ፕሬዝደንት የመሆን ዕድል አላቸው ተብሏል። ማሲሲ ለቦኮ ስልክ በመደወል በምርጫው መሸነፋቸውን እንደነገሯቸው አስታውቀዋል። “በዲሞክራሲ ሂደቱ ኩራት ተሰምቶኛል። ለሁለተኛ የሥልታን ዘመን መመረጥ ብሻም፣ ገለል ብዬ በሥልጣን ሽግግሩ ተሳትፎ አደርጋለሁ” ብለዋል ማሲሲ። ቦትስዋና በአፍሪካ የተረጋጋ ዲሞክራሲ ካላቸው ሃገራት ውስጥ ነች በሚል ስትሞካሽ፣ በዓለም ከሩሲያ በመቀጠል ሁለተኛ የአልማዝ አምራች ሃገር ነች፡፡
በአንግሊዝኛ የምህጻር ስማቸው ኤስ.ኤም.አር ተብለው የሚጠሩት ትናንሽ የኒውክሊየር ኅይል ማመንጫዎች ከበርቴ ላልኾኑት ሀገሮች በንጽጽር በርካሽ ወጪ የኒውክሊየር ኅይል እንደሚያስገኙ የጉዳዩ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ SMR ምንድናቸው? ጠቃሚነታቸውን የሚናገሩት ወገኖች አብዝቶ ያስደሰታቸው ምንድነው? የቪኦኤው ሄንሪ ሪጅዌል ከለንደን ያጠናቀረው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
በአሜሪካ ለፕሬዝደንትነት የሚወዳደሩት የሁለቱ ፓርቲ እጩዎች፣ በዚህ ከምርጫው በፊት ባለው የመጨረሻው ሳምንት፣ “የመዝጊያ ሙግት” በሚል የሚገለፀውን ንግግራቸውን በየፊናቸው አድርገዋል። የቪኦኤ ከፍተኛ የዋሽንግተን ዘጋቢ ካሮሊን ፕረሱቲ ዘገባዋን ልካለች።ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
በእስራኤል እና በኢራን በሚደገፈው የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላህ መካከል የሚካሄደውን ጦርነት ለማርገብ፣ የዩናይትድ ስቴትስ አሸማጋዮች የ60 ቀናት ተኩስ ማቆምም ስምምነት ለማስጀመር እየጣሩ መሆኑን ሁለት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሮይተርስ አስታወቁ። ስለድርድሩ ገለጻ የተደረገላቸው አንድ ግለሰብ እና በሊባኖስ የሚሠሩ አንድ ከፍተኛ ዲፕሎማት እንዳመለከቱት፣ ለሁለት ወራት የሚቆየው የተኩስ ማቆም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት፣ እ.አ.አ በ2006 ደቡባዊ ሊባኖስን ከጦር መሳሪያ ነፃ ለማድረግ ያሳለፈውን '1701' የተሰኘ የውሳኔ ሐሳብ ተግብራዊ ለማድረግ ይጠቅማል ብለዋል። በቤይሩት የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ቃል አቀባይ ሳማ ሐቢብ ስለ ውሳኔ ሐሳቡ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ «የውሳኔ ሐሳብ 1701ን ተግባራዊ የሚያደርግ እና የእስራኤል እና የሊባኖስ ዜጎችን ወደየቤታቸው የሚመልስ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንፈልጋለን» ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የተጀመረው እስራኤል በሊባኖስ የምታደርገው ዘመቻ እየሰፋ ባለበት ወቅት ሲሆን ለሦስት ተከታታይ ቀናት ደቡባዊ የሊባኖስ ከተማ በሆነችው ኪያም አቅራቢያ ከፍተኛ ውጊያ መደረጉን ሂዝቦላህ አስታውቋል። በአዲሱ የተኩስ አቁም ሀሳብ ላይ እየሰሩ ያሉት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ልዩ መልዕክተኛ አሞስ ሆችስቴይን በዚህ ወር መጀመሪያ ቤይሩት ለሚገኙ ጋዜጠኞች በሰጡት ቃል፣ እስራኤልም ሆነች ሊባኖስ የፀጥታ ምክርቤቱን የውሳኔ ሐሳብ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው የተሻሉ የማስፈጸሚያ ዘዴዎች እንደሚያስፈልጉ ተናግረው ነበር።
ዩናይትድ ስቴትስ ሩሲያን ዒላማ ያደረጉ በመቶዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ማዕቀቦች መጣሏን ረቡዕ እለት አስታውቃለች። ማዕቀቦቹ ሩሲያ የሚጣሉባትን ማዕቀቦች ለማለፍ የምታደርገውን ጥረት ለመመከት አሜሪካ ቁርጠኛ መሆኗን እንደሚያሳይ ተመልክቷል። የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ባወጡት መግለጫ፣ ወደ 400 የሚጠጉ ተቋማት እና የተለያየ አገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ መጣላቸውን ገልጸዋል። ማዕቀቡ ከተጣለባቸው መካከል በርካታ የቻይና፣ ሆንግ ኮንግ እና ህንድ ኩባንያዎች እንደሚገኙበትም አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን ለሮይተርስ ተናግረዋል። በተጨማሪም በሩሲያ፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ በቱርክ፣ በታይላንድ፣ በማሌዥያ፣ በስዊዘርላንድ እና በሌሎች ሀገራት የሚገኙ ተቋማት ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል። ጥቃቅን ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ጨምሮ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ህብረት የላቁ ያሏቸውን እና ሩሲያ ለዩክሬን ወረራ ልትጠቀምባቸው የሚችላቸውን ምርቶች፣ ሀገራት ለሩሲያ እንዳያቀርቡ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በተደጋጋሚ ስታስጠነቅቅ ቆይታለች። ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ባለስልጣን፣ ማዕቀቡ «ለመንግስታትም ሆነ በነዚህ ሀገራት ለሚገኙ የግል ኢኮኖሚ ዘርፎች፣ ሩሲያ የሚጣልባትን ማዕቀብ ለመሸሽ የምታደርጋቸውን ጥረቶች ለመመከት ቁርጠኛ መሆናችንን የሚያሳይ መልዕክት ሊያስተላልፍ ይገባል» ብለዋል። ማዕቀቡ ዒላማ ካደረጋቸው ተቋማት መካከል መቀመጫውን ህንድ ያደረገው 'ፉትሬቮ' አንዱ ሲሆን፣ ሩሲያ ለሚገኘው የሰው ሰራሽ አውሮፕላን (ድሮን) አምራች ኩባንያ እጅግ ተፈላጊ የሆኑ ቁሶችን በማቀርብ ክስ ቀርቦበታል።
Botswana: Voters headed to the polls Wednesday in southern Africa's diamond-rich nation to cast ballots in the general election. The ruling party seeks to extend its nearly six-decade rule and hand a second term to President Mokgweetsi Masisi.
More than 53 million Americans already have voted in the election, according to Election Hub at the University of Florida on Tuesday.
Dozens of people have died after flash floods swept away cars, turned village streets into rivers and disrupted rail lines and highways in Spain’s Valencia region. Rainstorms on Tuesday caused flooding in a wide swath of southern and eastern Spain, stretching from Malaga to Valencia.
በመጪው ማክሰኞ ኅዳር 5 ቀን 2024 ዓ.ም. ለሚካሄደው ምርጫ «የቅድሚያ ምርጫ ድምጽ» እየተሰጠ ነው። ከምርጫው ቀን አስቀድሞ ድምጽ እንዲሰጥ የሚፈቅዱ ክፍለ ግዛቶች የተለያዩ ደንቦች እና የጊዜ ሰሌዳዎችን ይከተላሉ። ከወዲሁ ድምጽ መስጠት የሚፈቅዱ ክፍለ ግዛቶችም አሉ። በአንዳንድ ክፍለ ግዛቶች አስቀድሞ ድምጽ ለመስጠት የተቀመጠው የመመዝገቢያ ቀነ ገደብ ያበቃ ሲኾን፣ በአንዳንዶቹ ክፍለ ግዛቶች ደግሞ አሁን እየተጀመረ ነው። በዚህ ሂደት ድምጽ መስጠት ጠቃሚ መሆኑን ድምጻቸውን የሰጡ መራጮችና የምርጫ ባለሞያዎች ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። /ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/
በምስራቅ ሊባኖስ ቤካ ሸለቆ አቅራቢያ በሚገኙ የሂዝቦላ ዒላማዎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንደምትወስድ ያስጠነቀቀችው እስራኤል፣ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላልፋለች። የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ቃል አቀባይ ባስተላለፉት መልዕክት በአልቤክ፣ አይን ቦርዴይ እና ዶውሪስ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው መውጣት አለባቸው ብለዋል። የእስራኤል ባለሥልጣናት የሚያስተላልፏቸው ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያዎችን ተከትሎ እስራኤል የአየር ድብደባዎችን የምታካሂድ ሲሆን፣ የጥቃቱ ዓላማ ሂዝቦላህን ከእስራኤልና ሊባኖስ ድንበር ለመግፋት መሆኑን ባለስልጣናቱ ይገልጻሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ፣ እስራኤል የፍልስጤም ስደተኞችን የሚደግፈውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለማገድ ባወጣችው አዲስ ሕግ ዙሪያ ስጋታቸውን ገልጸው ለእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ደብዳቤ ጽፈዋል። የደብዳቤውን ይዘት አስመልክተው የመንግስታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ «ሕጉ ተግባራዊ ከሆነ በከበባ ስር በሚገኘው ግዛት የሚኖሩት ፍልስጤማውያን ሰብዓዊ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስ ግልፅ ነው» ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል ማክሰኞ እለት በሰሜናዊ ጋዛ በሚገኝ ባለአምስት ፎቅ የመኖሪያ ህንፃ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 70 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤም የጤና ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
በአሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሚሳተፉት ወጣቶቹ መራጮች «ጄን ዚ» በሚል መጠሪያ ይታወቃሉ። ከ18 እስከ 27 ባለው የዕድሜ ክልል ገዳማ ውስጥ ይገኛሉ። እንዴት መምረጥ እንደሚችሉ ከመማር ጀምሮ ከቤት ቤት እየዞሩ ድጋፍ ማሰባበሰብ ተግባራት ድረስ፣ ብዙዎች የምርጫው የሲቪክ ሂደት አካል እየሆኑ ነው። ላውሬል ቦውማን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
ትላንት ማክሰኞ ዕለት በደቡብ እና ምስራቅ የስፔን አካባቢዎች የጣለው አውሎ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ባስከተለው ድንገተኛ ጎርፍ የ51 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የስፔን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። አውሮፓ ውስጥ በቅርብ ጊዜ ተከስቶ የማያውቅ የከፋ የተፈጥሮ አደጋ መሆኑ የተገለጸው ይህ ጎርፍ መኪናዎችን ጠራርጎ መውሰዱን፣ አውራ ጎዳናዎችን ወደ ወንዝነት መቀየሩን እና የባቡር መሥመሮችን ማስተጓጎሉንም አመልክተዋል። ማላጋ በተሰኘው ከተማ አቅራቢያ 300 ሰዎችን አሳፍሮ በፍጥነት ይጓዝ የነበረ ባቡርም ከመስመር ውጪ የወጣ ሲሆን የተጎዳ ሰው ግን እንደሌለ ባለሥልጣናቱ አመልክተዋል። በፍጥነት የሚጓዘው የጭቃ ቀለም ያለው የጎርፍ ውሃ መኪናዎችን እያላጋ ሲወስድም ታይቷል። ፖሊስ እና የነፍስ አድን አገልግሎት ሠራተኞች ሄሊኮፕተሮችን በመጠቀም ሰዎችን ከቤታቸው እና ከመኪናዎቻቸው ያወጡ ቢሆንም በርካታ ሰዎች እስካሁን የደረሱበት እንደማይታወቅ ባለሥልጣናቱ ማክሰኞ ማታ አስታውቀው ነበር። የስፔን የአደጋ ጊዜ ምላሽ አባል የሆኑ ከ1ሺህ በላይ ወታደሮች በአደጋው ወደተጎዱ አካባቢዎች ተሰማርተው ፍለጋ በቀጠሉበት ወቅት፣ የሟቾቹ ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ ተገልጿል።
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጥር ኅዳር አምስት የነገ ሳምንት ማክሰኞ የሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ተቃርቧል። የምረጡኝ ዘመቻውም ተጧጡፏል፡፡ በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቀው ኬኒያ ውስጥ የሚኖሩ አሜሪካዊያንም ባሉበት ሆነው በምርጫው መሳተፋቸውን ቀጥለዋል፡፡ የአሜሪካ ድምጹ ዘጋቢ ጁማ ማጃንጋ ናይሮቢ የሚኖሩ አሜሪካዊያንን በሀገራቸው ፖለቲካ ስለሚያደርጉት ተሳትፎ አነጋግሮ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
በተያዘው ዓመት በአሜሪካ ምርጫ ለመሳተፍ ዝግጅት ላይ የሚገኙት የሃገሪቱ ገበሬዎች፣ ኢኮኖሚው ከበድ ብሏቸዋል ተብሏል። የታሪፍ ጉዳይና የድጎማ መቋረጥ ከሚያሳስቧቸው ጉዳዮች ውስጥ ናቸው። የቪኦኤው ኬን ፋርቦ ገበሬዎችን አነጋግሮ ከኢሊኖይ ግዛት ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
ሶማልያ በሞቃዲሾ የሚሰሩት የኢትዮጵያ ዲፕሎማት እውቅና የላቸውም አለች፡፡ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ፣ ዲፕሎማቱ ከዲፕሎማሲያዊ ሚናቸው ጋር የማይጣጣሙ ተግባራትን ፈጽመዋል ሲል ከሷል። ሞቃዲሾ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አማካሪ የሆኑት ዲፕሎማት አሊ ሞሃመድ አዳን ትዕዛዙ በደረሳቸው 72 ሰዓታት ውስጥ ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡም ተነግሯዋል። ሶማሊያ በአሊ ተፈጽሟል የተባለውን ድርጊት በዝርዝር ባትገልጽም፣ የሚኒስቴሩ መግለጫ ውሳኔው የተላለፈው “የቪየናን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስምምነት በመጣሳቸው” መሆኑን አመልክቷል፡፡ የአሜሪካ ድምፅ ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው ወዲያውኑ ምላሽ ማግኘት አልቻለም። አዲስ አበባ ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመች በኋላ፣ ሶማሊያ ስምምነቱ ሉዓላዊነቷን የጣሰ አድርጋ በመቁጠሯ፣ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ የከረረ ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል፡፡ ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ በበኩላቸው “የባህር በር-ለእውቅና” የተባለውን የመግባቢያ ስምምነት ተገቢነት በመግለፅ ተከላክለዋል።
በ2016 ዓም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 684 ሺህ 205 ተማሪዎች ያለፉት 5.4 በመቶ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር። በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ውስጥ የሚገኝ አንድ የግል ትምህርት ቤት ግን ያስፈተናቸውን 35 ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ በማሳለፍ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል። የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ዝቅተኛ በሆነበት የሶማሌ ክልል፣ ትምህርት ቤቱ ተማሪዎቹን እንዴት ለዚህ ስኬት ሊያበቃ ቻለ?
ምክትል ፕሬዝደንት ካመላ ሃሪስ ዩናይትድ ስቴትስ የግጭቶች አያያዝን አጋርነቶችን እየገነባች መምራት እንዳለባት እንደሚያምኑ ይናገራሉ። የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በበኩላቸው ጥንካሬን የሚያሳዩ በመሆናቸው እና ቀጣይ እርምጃቸው ምን እንደሚሆን ስለማያሳውቁ ጦርነትን ከመጀመሩ በፊት ማስቆም እንደሚችሉ ይናገራሉ፡፡ የቪኦኤ የኋይት ሐውስ ቢሮ ዋና ዘጋቢ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ በመካከለኛው ምሥራቅ እና በአውሮፓ ጦርነቶች እየተካሄዱ ባሉበት በዚህ ወቅት ግጭቶችን ለመቀነስ የተሻለ የሚሆነው የትኛው የውጭ ፖሊሲ እንደሆነ የጉዳዩን አዋቂ ባለሞያዎች ጠይቃ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
በአሜሪካ የሚደረገው ምርጫ በብዙ መልኩ ለየት ያለና ታሪካዊ ነው። በካልፎርኒያ ግዛት በምትገኘው ኦክላንድ ከተማ፣ አንድ ትውልደ ኤርትራ አሜሪካዊና እንዲኹም ትውልደ ናይጄሪያ አሜሪካዊ ለከተማዋ ምክር ቤት አባልነት ለመወዳደር የምርጫ ዘመቻ ላይ ናቸው። የቪኦኤ የትግርኛ ክፍል ባልደረባ ተወልደ ወልደገብርኤል የስደተኞች ተሟጋች የሆኑትን ትውልደ ኤርትራው አቶ ሜሮን ሰመዳር እና የንግድ ማኅበረሰቡ ድምጽ መሆን የሚሹትንና የንግድ ድርጅቶች ባለቤት የሆኑትን ትውልደ ናይጄሪያው ባባ አፎላቢ አነጋግሮ ተከታዩን አጠናቅሯል።
እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2020 ዓ.ም. ከተካሄደው ምርጫ ወዲህ ቁጥራቸው 3.5 ሚሊዮን የሚደርስ በመራጭነት ዕድሜ የሚገኙ ሰዎች የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ ለመሆን በቅተዋል’ ሲል ለስደተኞች መብት የሚሟገተው ‘ብሔራዊ ፓርትነርሺፕ ፎር ኒው አሜሪካንስ’ በመባል የሚታወቀው ተቋም አመልክቷል። እንደ አንዳንድ ተንታኞችም እይታ ይህ ቁጥሩ እያደገ የመጣ ቡድን የምርጫውን ውጤት በመወሰኑ ረገድ ትልቅ ሚና ሊጫወት ይችላል። የአሜሪካ ድምጿ የኢሚግሬሽን ጉዳዮች ዘጋቢ አሊን ባሮስ ያደረሰችንን ዘገባ አሉላ ከበደ እንደሚከተለው ያቀርበዋል።
በኢትዮጵያ በትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ በግብርና እና በሌሎች ዘርፎች አዳዲስ የስራ ፈጠራ ሃሳቦች ያሏቸው ወጣቶች እየተበራከቱ ስለመምጣታቸው ይገለጻል፡: ይሁንና እነዚህ በሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ወጣቶቹ፤ ያላቸውን ርዕይ ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚችሉበት የተመቻቸ ሃገራዊ ሁኔታ አለመኖሩን ስራ ፈጣሪዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ መንግስት በበኩሉ ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች የተመቻቸ ሁኔታ እንዲኖር ትኩረት ሰጥቶ እየስራ እንደሚገኝ ይገልጻል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
በ19 ዓመቷ ሥራ ፈጣራ ውስጥ የገባችው ሳሚያ አብዱልቃድር፣ ወጣቶች የሥራ ፈጠራ ሀሳባቸውን ተግባራዊ ለማድረግ በሚገጥሟቸውን እንቅፋቶች በማለፏ፣ ከአራት አመት በፊት የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበርን መሰረተች። ላለፉት አራት አመታትም፣ ማህበሩ የወጣት ስራ ፈጣሪዎችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስራ ፈጣራ ጥቅሞችን በመደገፍ፣ በማበረታታት እና በማስተዋወቅ በርካታ ሥራዎችን ሰርቷል። (ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ዘገባ ያገኛሉ)
የትላንቱ የእስራኤል ጥቃት ከኢራን የቀድሞ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ምርምር እና ከአሁኑ የባሊስቲክ ሚሳይል መርሃ ግብሮች ጋር ግንኙነት ያላቸውን ፓርቺን እና ክሆጂር የተባሉትን ሁለት ሚስጥራዊ የኢራን ጦር ሰፈሮች እንዳወደመ ተነግሯል። ዛሬ እሁድ በአሶሲየትድ ፕሬስ የተተነተኑ የሳተላይት ምስሎች በፓርቺን የጦር ሠፈር የወደሙ ተቋማትን አሳይተዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል ኢራን ቀደም ሲል የኒውክሌር ፍንዳታ ሊያስከትሉ የሚችሉ ፈንጂዎችን እንደሞከረችበት የሚጠረጠር ሥፍራ እንደሚገኝበት ተመልክቷል፡፡ ወድመዋል ከተባሉት መካከል “ታሌጋን 2” ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ በዩራኒየም የበለጸጉ ከፍተኛ የፍንዳታ መሣሪያዎች ግብአቶችን የያዘ ህንጻ ሊኖር እንደሚችል ቢገመትም በውስጡ ምን እንዳለ በግልጽ አልታወቀም፡፡ ዓለም አቀፉን የኒውክሌር ኃይል ተቋም የሚመሩት ራፌል ማሪኖ ግሮሲ በኤክስ የማህበራዊ መድረካቸው “የኢራን ኒውክሌር ተቋማት ምንም ጉዳት አልደረሰባቸውም” ብለዋል፡፡ የሳተላይት ፎቶግራፍ ምስሎች የሚሳይል ማምረቻ ተቋማትን እና የመሬት ውስጥ ለውስጥ ዋሻ መስመር እንዳለው በሚታመንበት በክሆጂር ተቋም ላይ የደረሰውንም ጉዳት እንደሚያሳዩ ዘገባው አመልክቷል። ተንታኞች ይህ ጥቃት ኢራን አዳዲስ ባለስቲክ ሚሳይሎችን የማምረት አቅም እንደሚያሳጣት ገምተዋል፡፡ ኢራን ሁለት ወታደሮች ብቻ ሲሞቱባት አብዛኛውን የእስራኤል ጥቃት “በተሳካ ሁኔታ” ማክሸፍ መቻሏን “ውስን ጉዳት” ብቻ መድረሱንም ገልጻለች፡፡ ይሁን እንጂ ባለሥልጣናቱን ስለደረሰው ጉዳትም ሆነ የኢራን ጦር ስለሰጠው ምላሽ ማስረጃ አላቀረቡም፡፡ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጥቃቱ ኢራንን “በከፍተኛ ጉዳት አድርሶበታል” ጥቃቱም “ዓላማውን ሁሉ አሳክቷል”ብለዋል፡፡ የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ ካሜኒ ግን ዛሬ እሁድ እንደተናገሩት የእስራኤሉ ጥቃት “ብዙ መጋነንም ሆነ ዝቅ ተደርጎ ሊታይ የሚችል መሆን አይገባውም” ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ኢራን ልትሰጠው ስለሚገባው ምላሽ ምንም አልተናገሩም፡፡ የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ተቋም፣ ምዕራባውያን የመረጃ ምንጮች እና ሌሎች፣ ቴህራን እኤአ ከ2003 ጀምሮ የልዩ ጦር መሣሪያ ግንባታ መርሃግብሮችን እንደምታካሂድ ይናገራሉ፡፡
በሰሜን ጋዛ ዛሬ እሁድ በተፈጸመ የእስራኤል የአየር ድብደባ አብዛኞቹ ህጻናትና ሴቶች የሚገኙበት ቢያንስ 22 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ እስራኤል ጥቃቱ በታጣቂዎች ላይ ያነጣጠረ ነው ስትል የተዘገበውንም የሟቾችን ቁጥር አስተባብላለች። ለሶስት ተከታታይ ሳምንታት ሰሜን ጋዛን በመነጠል የሚካሄዱት የእስራኤል ጥቃቶች እየጨመሩ በመምጣታቸው በጋዛ ሰሜናዊ ክፍል ያለው የሰብአዊነት ሁኔታ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን የረድኤት ድርጅቶች ተናግረዋል፡፡ ቀይ መስቀል ነዋሪዎች የሚያገኟቸው የምግብ፣ የውሃ እና የህክምና አቅርቦት ውስን ሲሆን በአካባቢው የተረፉት ጥቂት ሆስፒታሎች እየተጨናነቁ መምጣታቸውን አስታውቋል፡፡ በሰሜን ጋዛ በግጭቱ መካከል መውጫ አጥተው የሚገኙ ሰላማዊ ሰዎች የህክምና እንክብካቤ በማጣት የሚደርስባቸውን ዘግናኝ ሁኔታዎች ያሳሰበው መሆኑንም ቀይ መስቀል ጨምሮ ገልጿል፡፡ በተያያዘ ሌላ ዜና ፣ ዛሬ እሁድ በቴል አቪቭ ከተማ አካባቢ ወደሚገኝ የአውቶብስ ማቆሚያ ደርምሶ በገባ አንድ ከባድ መኪና 35 ሰዎች መቁሰላቸውን የእስራኤል የአደጋ ጊዜ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡ በእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ ዋና መሥሪያ ቤት አቅራቢያ የደረሰውን አደጋ ባለሥልጣናት ሆን ተብሎ የተፈጸመ እንደሆነ ጠርጥረዋል፡፡ ስለ አሸከርካሪውና ዓላማው የገለጹት ዝርዝር ነገር የለም፡፡ አሽከርካሪው ወዲያውኑ ርምጃ እንደተወሰደበት ተነግሯል፡፡
የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ከዋና ከተማይቱ ካርቱም በስተደቡብ በአል-ጃዚራ ግዛት ውስጥ ባሉ መንደሮች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 50 ሰዎች ሲገደሉ ከ200 በላይ መቁሰላቸውን የመብት ተሟጋቾች ተናገሩ፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው በግዛቲቱ የነበሩ አንድ ወታደራዊ አዛዥና የተወሰኑ ወታደሮቻቸው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ከድተው የሱዳን ሠራዊትን መቀላቀላቸው ከተነገረ በኋላ መሆኑን ተሟጋቾቹ ገልጸዋል፡፡ ካለፈው ዓርብ ጀምሮ “የአል ሳሪሃ እና አዝራቅ መንደሮች ጥቃት ደርሶባቸዋል” ሲሉ በሱዳን የረድኤት ሥራዎችን የሚያስተባበሩ የበጎ ፈቃድ ቡድኖች ለኤኤፍፒ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ አካባቢው በከባድ መሣሪያ ድብደባ ሥር የሚገኝና የግንኙነት መስመሮችም የተቋረረጡ በመሆናቸው ቁስለኞችን ለማውጣት አስቸጋሪ መሆኑን መግለጫቸው አመልክቷል፡፡ ከትላንት በስቲያ ዓርብ የሱዳን የዶክተሮች ህብረት “በፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች ለዘር ማጥፋት አደጋ ተጋልጣዋል” የተባሉትን ንጽሃን ዜጎች ከተከበበው አካባቢ እንዲወጡ የሰብአዊ ኮሪደር እንዲያስከፍት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ተማጽኗል፡፡ “የሱዳን ሠራዊት ሰላማዊ ዜጎችን የመከላከል ብቃት የሌለው በመሆኑ” የነፍስ አድን ሥራው የማይቻል ሆኗል ሲል የዶክተሮቹ ህብረት አክሏል፡፡ በሱዳን የሚካሄደው ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መግደሉ ሲነገር፣ አንዳንዶቹ የሟቾቹን ቁጥር እስከ 150, 000 እንደሚያደርሷቸው ዘገባው አመልክቷል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከ7ሚሊዮን በላይ ሰዎች የተፈናቀሉ መሆናቸውን በመግለጽ “በዓለም ትልቁ የተፈናቃዮች ቀውስ” ሲል ጠርቶታል፡፡ የዓለም የገንዘብ ድርጅት ቀውሱ ለሱዳን አጎራባች ሀገራት የሚተርፍ መሆኑን አመልክቷል፡፡ አካባቢዎቹን ለኢኮኖሚ ችግር፣ የጸጥታ ጉዳዮች እና ከተፈናቃዮች ጋር ተያይዘው ለሚመጡ ሌሎች ፈተናዎች እንደሚጋልጣቸው በማስጠንቀቅ “የግጭቱ ቀጣናዊ ተጽእኖ እጅግ ከባድ ነው” ብሏል፡፡
በፊሊፒንስ «ትራሚ» የሚል ስያሜ በተሰጠው ከባድ አውሎ ንፋስ እና ዝናብ ባስከተለው አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 110 ደርሷል ሲሉ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ዛሬ እሁድ ተናገሩ ። እስካሁን 42 የሚሆኑ ሰዎች ደብዛቸው እንደጠፋ ሲሆን የነፍስ አድን ሠራተኞች ፍለጋቸውን ቀጥለዋል፡፡ ባላፈው ሀሙስ እኤአ ጥቅምት 24 ፊሊፒንስን የመታው ትራሚ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን ከመኖሪያ እና ቀያቸው አፈናቅሏል፡፡ ፊሊፒንስን ደቁሶ ወደ ቬትናም የገሠገሠው ትራሚ በማዕከላዊ የሀገሪቱ ክፍል ዛሬ እሁድ ከባድ ዝናብ እንዲሁም በሰዓት 70 ኪሎሜትሮች የሚፈጥን ነፋስ ማስተከተሉ ተነግሯል፡፡ የትራሚ ከባዱ አውሎ ነፋስ፣ ቬትናም ከመድረሱ በፊት፣ ባለሥልጣናት የጀልባና የባህር ላይ እንቅስቃሴዎችን በማገድ ፣ 25ሺ ሰዎችም አካባቢያቸውን ለቀው እንዲቆዩ ማድረጋቸው ተመልክቷል፡፡ የአየር ትንበያ ባለሥልጣናት፣ በአካባቢ አየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ሳቢያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእስያ ፓስፊክ ክልል የሚታዩ አውሎ ነፋሶች ከባህር ላይ ወደ ምድር ዳርቻ ተጠናክረው እየተጠጉ መንፈስ መያዛቸውና በየብስ ላይ ለረጅም ጊዜ መቆየታቸው በጥናት መረጋገጡን ተናግረዋል፡፡
ጆርጂያውያን ዛሬ ወደ አውሮፓ ህብረት ወይም ወደ ሩሲያ ምህዋር ሊወስድ በሚችል ምርጫ ላይ ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል፡፡ ገዥው ፓርቲ የሩስያ ደጋፊነት ስጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣባት ጆርጂያ የተካሄደው ምርጫ የአውሮፓን ምኞት የሚወስን እንደሆነም ተገልጿል፡፡ የፓርላማ ምርጫው ዲሞክራሲን በማፈን ወደ ሩሲያ አዘንብሏል ተብሎ ከተከሰሰው ገዥው ፓርቲ በተቃራኒ የተሰለፉት የምዕራቡ ዓለም ደጋፊ የሆኑ የተቃዋሚ ሃይሎች ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታውቅ ሁኔታ ህብረት ያሳዩበት ነው ተብሏል። ብራሰልስ ምርጫው የአውሮፓ ህብረት እጩ የሆነችው ጆርጅያን ወደ ህብረቱ የመቀላቀል እድሏን እንደሚወስን አስጠንቅቋል። ብዙዎች የሃገሬው ሰዎችም ምርጫው በሕይወታቸው ውስጥ በጣም ወሳኝ ድምጽ ሊሆን እንደሚችል ያምናሉ፡፡ ጆርጂያ ወደ አውሮፓ ህብረት አባልነት መመለሱን ወይም አምባገነንነትን ተቀብላ ወደ ሩሲያ ምህዋር መግባቷን የሚወሰንበት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ለታይዋን ባጸደቀችው የ2 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ ጥቅል ውስጥ በዩክሬን የተሞከረው የላቀ የአየር መከላከያ ሚሳኤል ጭምር መካተቱንና ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ደሴቷ የሚላክ መሆኑን ፔንታጎን ትላንት አርብ አስታውቋል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ በቻይና ይገባኛል ጥያቄ ከምታነሳባት ታይዋን ጋር ምንም እንኳን መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ባይኖራትም ራሷን እንድትከላከል የሚያስችል ድጋፍ ለመስጠት በህግ ትገደዳለች፤ ይህ ደግሞ የቤጂንግ የሁልጊዜ ቁጣ ነው። ቻይና ያለፈውን ሳምንት ጨምሮ በታይዋን ላይ የምታካሄዳቸው ወታደራዊ ጫናዎች እየጨመረ ሲሆን ይህም በግንቦት ወር ላይ ቺንግ-ቴ የታይዋን ፕሬዝዳንት ሆነው ስልጣን ከያዙ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ያካሄደችው ወታደራዊ እንቅስቃሴነው፡፡ የፔንታጎን የመከላከያ ደህንነት ትብብር ኤጀንሲ እንዳስታወቀው አዲሱ ሽያጭ 828 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ዋጋ ያላቸው 1.16 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ የሚሳኤል እና ራዳር ስርዓት መሳርያዎችን ያካተተ ነው። የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር መግለጫውን በደስታ እንደተቀበለው አስታውቋል፣ የአየር መከላከያዎቹ በቻይና የሚደረጉ ተደጋጋሚ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከልና የታይዋን የአየር መከላከያ አቅም ለማሳደግ ያግዛል ብሏል፡፡ የታይዋን ጦር ከቻይና የሚደርስ ማንኛውንም ጥቃት በተሻለ ሁኔታ ለመቋቋም ወሳኝ የባህር ሃይል መከላከያ የራሱን ሰርጓጅ መርከብ መገንባትን ጨምሮ ትጥቁን እያጠናከረ ይገኛል።
ሩስያ ባደረሰችው የሚሳኤል ጥቃት በዩክሬን ዲኒፕሮ ከተማ አንድ ህፃን ጨምሮ ሶስት ሰዎችን ሲገደሉ በኪየቭ እና አካባቢው ላይ በደረሰው ጥቃት ደግሞ ታዳጊን ጨምሮ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን ባለስልጣናቱ ዛሬ አስታውቀዋል፡፡ የማዕከላዊ ዲኒፕሮ ፔትሮቭስክ ክልል ገዥ ሰርጊ ሊሳክ እንዳሉት በዲኒፕሮ ላይ በአንድ ሌሊት በደረሰ ጥቃት 19 ሰዎች ጉዳት የደርሰባቸው ሲሆን በርካታ ሕንፃዎች ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡ ባለ ሁለት ፎቅ የመኖሪያ ሕንፃ መውደሙንም ገልጸዋል፡፡ በሩሲያ ወረራ ኪየቭን ጨምሮ የዩክሬን ከተሞች የሰው አልባ አውሮፕላኖች እና የሚሳኤል ጥቃቶች በተደጋጋሚ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ ሞስኮ በኤሌክትሪክ ሃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት እየፈፀመች ባለችበት በአሁኑ ወቅት ኪየቭ ገና ከባዱ ክረምት ከመግባቱ በፊት ከአጋሮቿ ተጨማሪ የአየር መከላከያ እንዲላክላት እየጠየቀች ነው፡፡
እ.አ.አ ጥቅምት 1 ኢራን በባሊስቲክ ሚሳኤል በእስራኤል ላይ ላደረሰችው ጥቃት ምላሽ በሆነው በዚህ የአጸፋ ጥቃት የጦር አውሮፕላኖች በመላ ኢራን ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ለብዙ ሰዓታት ድብደባ ማካሄዳቸውን የእስራኤል ጦር አስታውቋል፡፡ ከአንድ አመት በላይ በዘለቀው ጦርነት በኢራን ላይ ያደረሰችውን ከባድ ጥቃት ማጠናቀቋንም እስራኤል ገልጻለች፡፡ የኢራን አጋር የሆነው ሃማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ካደረሰ በኋላ ወደ ብዙ የግጭት ግንባሮች ተስፋፍቶ ቴህራንና ሌሎች ቀጠናዊ አጋሮቿን የጦርነቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ ሁነዋል፡፡ የእስራኤል መከላከያ ሃይል ዛሬ ረፋድ ላይ በሰጠው መግለጫ የጦር አውሮፕላኖቹ «በኢራን ውስጥ ባሉ በርካታ አካባቢዎች በወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ያነጣጠሩና ትክክለኛ ጥቃቶችን ካደረሱ በኋላ በሰላም ወደ አገራቸው ተመልሰዋል» ብሏል። ይህ መግለጫ የወጣውም ኢራን ውስጥ የመጀመርያው ፍንዳታ ከተሰማ ከአራት ሰዓታት በኋላ ነው፡፡ የእስራኤል መከላከያ ሃይል ቃል አቀባይ ሪየር አድሚራል ዳንኤል ሃጋሪ ለጋዜጠኞች የእስራኤል የአየር ድብደባ አላማቸውን ያሳኩ እንደነበሩ የገለጹ ቢሆንም ማስረጃ ግን ወዲያውኑ አላቀረቡም። የኢራን መንግስት የዜና ጣቢያ የሀገሪቱ የአየር መከላከያ ድርጅትን ጠቅሶ እንደዘገበው እስራኤል በቴህራን እና በምዕራባዊው ኩዝስታን እና ኢላም አውራጃዎች በሚገኙ ወታደራዊ ማዕከላት ላይ ጥቃት አድርሳለች ብሏል። የኢራን ሃይሎች አብዛኛውን ጥቃት “በስኬት” ማክሸፍ መቻላቸውንና “ውስን ጉዳት” ብቻ መድረሱንም ጨምሮ ገልጿል፡፡ የኢራን ባለስልጣናት የእስራኤል የአየር ጥቃት ማክሸፍ ሰለመቻላቸውም ሆነ ስላደረሰው ጉዳት ማስረጃ ማቅረብ አልቻሉም። ነገር ግን የመንግስት ሚዲያ የኢራን ጦርን ጠቅሶ እንደዘገበው በእስራኤል ጥቃት ሁለት ወታደሮች ተገድለዋል። አንድ የአሜሪካ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ደግሞ እስራኤል “በኢራን ህዝብ ከሚኖርባቸው ወጣ ባሉ አካባቢዎች በሚገኙ በርካታ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ትክክለኛ የአየር ድብደባ አድርጋለች'' ብለዋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስም ስለእስራኤል ወታደራዊ ርምጃ ገለፃ ተደርጎላቸዋል ሲል ዋይት ሀውስ ትላንት አስታውቋል። ያሉትን ለውጦችን በቅርበት እየተከታተሉ መሆናቸውንም ተገልጿል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ባለስልጣን ለቪኦኤ ሲናገሩ “በጥቃቱ ዙርያ ቅድሚያ አሳውቀውን ነበር” ነገር ግን እኛ አልተሳተፍንም ብለዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ከእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ጋር ዛሬ የተነጋገሩ ሲሆን የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በኢራን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ስላደረሰው ጥቃት አዳዲስ መረጃዎችን እንዳጋሯቸው ፔንታጎን ንግግራቸውን በተመለከተ ካወጣው ጽሁፍ ታውቋል፡፡ ኦስቲን ዩናይትድ ስቴትስ ለእስራኤል ደህንነት እና ራስን የመከላከል መብት ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ ማረጋገጣቸውም ተገልጿል፡፡
ወርሃ ጥቅምት የአለም አቀፉ የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር በመባል ይታወቃል። በአለም ላይ ከስምንት ሴቶች አንዷ በጡት ካንሰር እንደምትያዝ በዩናይትድ ስቴትስ በካንሰር ዙሪያ የሚሰራው ገባሬ ሰናዩ የአሜሪካ የካንሰር ማኅበረሰብ አማካኝነት የተሰሩ ጥናቶች ያመላክታሉ። በኢትዮጵያም በበሽታው ዙሪያ ያለው ግንዛቤ እና እንዲሁም የህክምናው ተደራሽነት አነስተኛ መሆኑን ታካሚዎች እና የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ።
ሶማሌ ክልል ውስጥ በተቃዋሚ ፓርቲነት የሚታወቀው፣ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብግ) በቅርቡ በክልሉ የአጀንዳ ልየታ ማጥናቀቁን ባስታወቀው፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋቋመው፣ የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለልተኝነት ላይ ጥያቄ አነሳ። የኮሚሽኑ የተሳታፊዎች መረጣ በክልሉ ገዢ ፓርቲ ብልጽግና ተጽዕኖ ሥር የወደቀ መኾኑን ፓርቲው በማኅበራዊ ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽነር መስፍን አርአያ፣ ተቋማቸው ግጭት ያለባቸውን ክልሎች ጨምሮ በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች ምክክሩን ለማካሄድ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸው፣ የቀረበው ወቀሳ አስተባብለዋል። በሌላ በኩል የፓርቲውን ስጋት የተጋሩት ዋና መቀመጫውን ጄኔቭ ያደረገው፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ሃይለማርያም፣ እንዲህ ዐይነት የገለልተኝነት ጥያቄ ሲነሳ የመጀመሪያ አለመኾኑን ጠቅሰው፤ ኮሚሽኑ አሳታፊ መኾን እንደሚገባው መክረዋል።
በዘንድሮው የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ሴት መራጮች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይጠበቃል፡፡ በቅርብ ዓመታት በመራጭነት የሚመዘገቡም ኾነ ድምጽ የሚሰጡ ሴቶች ቁጥር ከወንዶቹ እየበለጠ መጥቷል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020 ዓ.ም ምርጫ የሴቶቹ መራጮች ቁጥር ከወንዶቹ ቁጥር በብዙ ሚሊዮኖች የበለጠ እንደነበር ታውቋል፡፡ የሴቶቹ መራጮች የምርጫ ተሳትፎ አንድ ወጥ አይሁን እንጂ በድምጽ አሰጣጣቸው በአመዛኙ ወደ አንደኛው ፓርቲ እንደሚያጋድሉ የታወቀ ነው፡፡ የአሜሪካ ድምጿ ዶራ መኳዋር ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር ለዓመታት ሰብአዊ ተግባራትን ያከናወነው «ወገኔ ኢትዮጵያ» የሰብአዊ ተቋም የእንቅስቃሴውን 24ኛ ዓመት ከሰሞኑ አክብሯል። የሰብአዊ ተቋሙ፣ በኢትዮጵያውያን ሕይወት ላይ ለውጥ ያመጡ ተግባራቱን ለተሳታፊዎች ከማስተዋወቅ በተጨማሪ፣ ለቀጣይ የግብረ ሠናይ እንቅስቃሴው የሚረዱ መርሐ ግብሮችንም አስተዋውቋል። በስፕሪንግ ፊልድ ቨርጅኒያ የተካሔደውን ሥነ ሥርዐት በተመለከተ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።