Ethiopia



የስደተኞች ጉዳይ ለትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካዊ መራጮች ቁልፍ ጉዳይ ነው

ከሁለት ቀናት በኃላ በዩናይትድ ስቴትስ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መራጮች ትኩረት ከሚሰጡባቸው ቁልፍ ፖሊሲዎች አንዱ የስደተኞች ጉዳይ ነው። የአሜሪካ ድ

ቲም ዋልዝ ማናቸው?

'የነብራስካው መልካም ሰው' የገጠሪቱን አሜሪካ ድምጽ ያገኙ ይሆን? ቲም ዋልዝ ከካመላ ሄሪስ ጎን ሆነው ለምክትል ፕሬዝደንትነት እንዲወዳደሩ ከመታጨታቸው በፊ
የአሜሪካ ድምፅ

ቲም ዋልዝ ማናቸው?

'የነብራስካው መልካም ሰው' የገጠሪቱን አሜሪካ ድምጽ ያገኙ ይሆን? ቲም ዋልዝ ከካመላ ሄሪስ ጎን ሆነው ለምክትል ፕሬዝደንትነት እንዲወዳደሩ ከመታጨታቸው በፊት፣ ለሚንሶታ አገረ ገዢነት ሁለት ጊዜ ተመርጠዋል። በምርጫ ዘመቻ ጉዟቸው ላይ፤ በነብራስካ ማደጋቸው፣ እንዴት ስብእናቸውን እንደቀረጸውና፣ አሁን ለታጩበት ሥራም ሆነ ለሃገረ ገዢነት ሃላፊነት ለመብቃት እንዴት እንደረዳቸው ይናገራሉ። የነብራስካ ሰዎች ስለ ቲም ዋልዝ ምን እንደሚያስታውሱ እንዲሁም አሁን ስለ እርሳቸው ምን እንደሚሰማቸው ለማወቅ የቪኦኤዋ ናታሻ ሞዝጎቫያ ግዛቲቱን ጎብኝታ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የሪፐብሊካኑ እጩ ምክትል ፕሬዘዳንት ተወዳዳሪ ጄዲ ቫንስ ማናቸው?

የሪፐብሊካኑ እጩ ምክትል ፕሬዘዳንት ተወዳዳሪ ጄዲ ቫንስ የሕይወት ታሪክ “የአንድ የትንሽ ከተማ ብላቴና መልካም ሲገጥመው” የሚለውን ሀረግ ሊጠቃለል ይችላል
የአሜሪካ ድምፅ

የሪፐብሊካኑ እጩ ምክትል ፕሬዘዳንት ተወዳዳሪ ጄዲ ቫንስ ማናቸው?

የሪፐብሊካኑ እጩ ምክትል ፕሬዘዳንት ተወዳዳሪ ጄዲ ቫንስ የሕይወት ታሪክ “የአንድ የትንሽ ከተማ ብላቴና መልካም ሲገጥመው” የሚለውን ሀረግ ሊጠቃለል ይችላል፡፡ ጄዲ በተራራማው አፓላችን ነው ያደጉት፤ በኋላም አይቪ ሊግ ተብለው ከሚታወቁት ልዩ የሆነ ክብር ካላቸው ዩኒቨርስቲዎች መካከል በዬል ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ በዬል የህግ ትምህርት ቤት ቆይታቸውም ከአሁኗ ባለቤታቸው ኡሻ ቺሉኩሪ ጋር ሊተዋወቁ ችለዋል፡፡ ጄዲ ቫንስ ውልደታቸው በሚድል ታውን ኦሃዮ ቢሆንም፤  ነገር ግን ቤቴ ብለው የሚጠሩት ጃክሰን ኬንተኪን ነው፡፡ በልጅነት ህይወታቸው ብሎም በአስተሳሰባቸው ላይ ሚማው ብለው የሚጠሯቸው ሴት አያታቸው ትልቅ ሚና አላቸው፡፡ የጄዲ ቫንስ የመጀመሪያ እውቅና የመነጨው በጎርጎሮሳዊያኑ 2016 በታተመው የአሜሪካ የሰራተኛውን መደብ ሕይወት በሚያስቃኘው ‘ሂልቢሊ ኤልጊ’ ብለው በጻፉት እና በኋላም ወደ ፊልምነት በተቀየረው መጽሓፋቸው ነው፡፡ በፖለቲካ ርዕዮተ ዓለማቸው  ቀድሞ ትራምፕን ያወግዙ የነበሩት ጄዲ ቫንስ አሁን ላይ የትግል አጋራቸው በመሆን የጎሮጎርሳዊያኑ 2024 ምርጫን ለማሸነፍ እየሰሩ ነው፡፡ መጭው የአውሮፓውያኑ ኅዳር አምስት በሚድረገው ምርጫ ካሸነፉም በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ወጣት ከሆኑ ምክትል ፕሬዘዳንቶች መካከል አንዱ በመሆን በታሪክ ሊመዘገቡ ይችላሉ፡፡  የአሜሪካ ድምጿ ከፍተኛ ዘጋቢ ኬሮላይን ፔርሱቲን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የአሜሪካ መራጮች «ከፍ ያለ እና ተለዋዋጭ» የደህንነት ሥጋቶች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል

ነገ ማክሰኞ በዩናይትድ ስቴትስ የሚካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በሀገሪቱ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማያውቅ እንደሚሆን ተነግሮለታል፡፡ የሀገሪቱ የጸጥታ እና የደህ
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ መራጮች «ከፍ ያለ እና ተለዋዋጭ» የደህንነት ሥጋቶች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል

ነገ ማክሰኞ በዩናይትድ ስቴትስ የሚካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በሀገሪቱ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማያውቅ እንደሚሆን ተነግሮለታል፡፡ የሀገሪቱ የጸጥታ እና የደህንነት ባለስልጣናትም መራጮች ድምጻቸውን የሚሰጡት ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጪ የተቀኑ አደጋዎች እጅግ ከፍተኛ እና ተለዋዋጭ የሆነ የስጋት ድባብ በፈጠሩበት ሁኔታ እንደሆነ ይናገራሉ። የብሔራዊ ጸጥታ ጉዳዮች ዘጋቢ ጄፍ ሴልድን ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ቆይታ ከኤፓክ ተወካይ ጋራ - በዩ ኤስ ምርጫ ኢትዮጵያ - አሜሪካውያን ድምጽ

«የተለያዩ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ማኅበረሰብ አባላት ለዘንድሮው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለውሳኔያቸው ምን ዓይነት ጉዳዮችን መሰረት ያደር
የአሜሪካ ድምፅ

ቆይታ ከኤፓክ ተወካይ ጋራ - በዩ ኤስ ምርጫ ኢትዮጵያ - አሜሪካውያን ድምጽ

«የተለያዩ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ማኅበረሰብ አባላት ለዘንድሮው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለውሳኔያቸው ምን ዓይነት ጉዳዮችን መሰረት ያደርጉ ይሆን?» ችችችችበሚል ላነሳነው ጥያቄ፣ ማብራሪያ እንዲሰጡን የአሜሪካ-ኢትዮጵያውያን የሕዝብ ጉዳዮች ኮሚቴ (ኤፓክ) ዋና ጸሐፊ አቶ ዮም ፍሰሃን ጋብዘናል። ከተቋቋመ ሦስት ዓመት ተኩል የሆነው ኤፓክ፣ ሁለቱ ዕጩዎች በየበኩላቸው ከላኳቸው አራት የምርጫ ዘመቻ ተወካዮች ጋራ አባሎቻቸው ውይይት እንዲያደርጉ በቅርቡ መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። አቶ ዮም ማኅበራቸው ስላሰናዳው ስለዚህ መድረክም አስረድተውናል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ከነብዩ መሃመድ የካርቱን ስዕል ጋር የተያያዘው የሽብር ጥቃት ወንጀል ጉዳይ መታየት ጀመረ

ፈረንሳይ ውስጥ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎቹን ስለ ንግግር ነፃነት በሚያስተምርበት ወቅት የነቢዩ መሃመድን የካርቱን ምስል ካሳየ በኋላ በአንድ እስላማዊ ጽንፈኛ
የአሜሪካ ድምፅ

ከነብዩ መሃመድ የካርቱን ስዕል ጋር የተያያዘው የሽብር ጥቃት ወንጀል ጉዳይ መታየት ጀመረ

ፈረንሳይ ውስጥ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎቹን ስለ ንግግር ነፃነት በሚያስተምርበት ወቅት የነቢዩ መሃመድን የካርቱን ምስል ካሳየ በኋላ በአንድ እስላማዊ ጽንፈኛ በስለት ተቀልቶ በተገደለው መምሕር ሳሙኤ ፓቲ ላይ በተፈጸመው ወንጀል ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ ስምንት ሰዎች ጉዳይ መታየት ጀመረ። የዛሬውም የችሎት ውሎ በርካታ ፖሊሶች በተሰማሩበት ጥብቅ ፍተሻ እና ቁጥጥር መከናወኑ ተዘግቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ ከሚገኙት ተጠርጣሪዎች መካከል አምስቱ ከሰፊ የመስታወት ሳጥን ውስጥ እንዲቀመጡ ሲደረግ፤ የተቀሩት ሶስቱ እግሞ ተከሳሾቹ ከሚቀመጡበት ሥፍራ በቁጥጥር ስር ሆነው ቀርበዋል። ከተከሳሾቹ አራቱ የጂሃድ መልዕክት ሲያስተላልፉ በነበሩ የማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከነብሰ ገዳዩ ጋር ይወያዩ ነበር በሚል የሽብር ወንጀል ነው የተከሰሱት። ይሁንና መምምህሩን ለመግደል የተፈጸመውን ሴራ በተመለከተ የምናውቀው ነገር አልነበረም ሲሉ አስተባብለዋል። በሌላ በኩል ከፓሪስ ከተማ ወጣ ብሎ ከሚገኘው ትምሕርት ቤቱ አቅራቢያ የተፈጸመውን መምህር ፓቲ’ን አስደንጋጭ ግድያ ተከትሎም በርካታ ትምሕርት ቤቶች ለመታሰቢያው በስሙ ተሰይመዋል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ጥቅምት 16, 2020 መምሕሩን የገደለው ከሩስያዋ የቸቸን ክፍለ ግዛት የሆነው የ18 ዓመቱ ነብሰ ገዳይ በጊዜው በፖሊስ ጥይት ተደብድቦ መገደሉ ይታወሳል።

ትረምፕ እና ሃሪስ ከምርጫው ቀን አስቀድሞ የመጨረሻውን የምረጡኝ ዘመቻ ጥረታቸውን ቀጥለዋል

አሜሪካውያን ቀጣዩን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ በነገው ዕለት ድምጻቸውን በሚሰጡበት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ፤ የሁለቱ ዋና ዋና ፓርቲ ዕጩዎቹ ዶናልድ ትረምፕ እና
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ እና ሃሪስ ከምርጫው ቀን አስቀድሞ የመጨረሻውን የምረጡኝ ዘመቻ ጥረታቸውን ቀጥለዋል

አሜሪካውያን ቀጣዩን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ በነገው ዕለት ድምጻቸውን በሚሰጡበት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ፤ የሁለቱ ዋና ዋና ፓርቲ ዕጩዎቹ ዶናልድ ትረምፕ እና ካማላ ሃሪስ አሁንም እንደተናነቁ መሆናቸውን አዲስ የወጡ ትንበያዎች እያመላከቱ ነው። ካማላ ሃሪስ የመጨረሻ ቀን ዘመቻቸውን ወሳኝ ከሚባሉት ሰባት ግዛቶች አንዷ በሆነችው የሚቺጋን ክፍለ ግዛት ሲያደርጉ፤ ትረምፕ በበኩላቸው በፔንሲልቫንያ፣ ሰሜን ካሮላይና እና በጆርጂያ ክፍለ ግዛቶች አድርገዋል።

VOA60 Africa - Botswana: Outgoing President Masisi hands over power to incoming President Boko

Botswana: Outgoing President Mokgweetsi Masisi handed over power to incoming President Duma Boko on Monday. Masisi conceded defeat Friday after his party lost its parliamentary majority by an unexpected landslide ending nearly six decades in power.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Botswana: Outgoing President Masisi hands over power to incoming President Boko

Botswana: Outgoing President Mokgweetsi Masisi handed over power to incoming President Duma Boko on Monday. Masisi conceded defeat Friday after his party lost its parliamentary majority by an unexpected landslide ending nearly six decades in power.

VOA60 World - At least 35 dead in India bus crash

India: At least 35 people are dead after a bus veered off the road and plunged into a deep gorge in the northern mountainous state of Uttarakhand, officials said on Monday.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - At least 35 dead in India bus crash

India: At least 35 people are dead after a bus veered off the road and plunged into a deep gorge in the northern mountainous state of Uttarakhand, officials said on Monday.

VOA60 America - Trump criticizes US election voting procedures

Republican presidential nominee Donald Trump visited three battleground states on Sunday, Pennsylvania, North Carolina and Georgia. Trump repeatedly criticized the U.S. election process.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Trump criticizes US election voting procedures

Republican presidential nominee Donald Trump visited three battleground states on Sunday, Pennsylvania, North Carolina and Georgia. Trump repeatedly criticized the U.S. election process.

የጀርመኗ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በኪየቭ ጉብኝታቸው ዩክሬንን መደገፋቸውን እንደሚቀጥሉ ተናገሩ

ከዩክሬን መሪዎች ጋር ተገናኝተው ለመነጋገር በዛሬው ዕለት ወደ ኪቭ ያቀኑት የጀርመኗ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አናሌና ቤርቦክ ሃገራቸው ዩክሬንን መደገፏን እንደ
የአሜሪካ ድምፅ

የጀርመኗ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በኪየቭ ጉብኝታቸው ዩክሬንን መደገፋቸውን እንደሚቀጥሉ ተናገሩ

ከዩክሬን መሪዎች ጋር ተገናኝተው ለመነጋገር በዛሬው ዕለት ወደ ኪቭ ያቀኑት የጀርመኗ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አናሌና ቤርቦክ ሃገራቸው ዩክሬንን መደገፏን እንደምትቀጥል በመግለጽ ቃል ገቡ።ባርቦክ አክለውም ‘የሩስያ የአየር ድብደባ አይሎ ወደ ክረምቱ በዘለቀበት እና ሰሜን ኮሪያ ለሞስኮ የምትሰጠው ወታደራዊ ድጋፍ ተጨማሪ ስጋት እየደቀነ ባለበት ወቅት ዩክሬይን ከመቼውም የበለጠ ድጋፍ ያስፈልጋታል’ ብለዋል። ‘ዩክሬናውያን እየተፈጸመባቸውን የጭካኔ ድርጊት በሰብአዊነት እና በምንሰጠው ድጋፍ እየመከትን፤ ክረምቱን መሻገር ብቻ ሳይሆን አገራቸውም እንዲያተርፉ ጭምር እናግዛቸዋለን። በድፍን አውሮፓ ለምንገኝ ለሁላችንንም ነጻነት እየታገሉ ነውና” ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩስያ ኃይሎች ለሊቱን በበርካታ የዩክሬይን አካባቢዎች ላይ ካነጣጠሯቸው ቁጥራቸው 80 የሚደርሱ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ውስጥ ሃምሳ ያህሉን የዩክሬን አየር መከላከያ መትቶ መጣሉን የሃገሪቱ ጦር ሠራዊት አስታውቋል። ሰው አልባ አውሮፕላኖቹ ተመተው የወደቁት በቼርካሲ፣ ቼርኒሂቭ፣ ኬርሰን፣ ኪሮቮራድ፣ ኪቭ፣ ሚኮላይቭ፣ ኦዴሳ፣ ሱሚ እና ዚሂቶሚር መሆኑንም የዩክሬን አየር ኃይል አክሎ አመልክቷል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ በዛሬው ዕለት ‘ከሩስያ ድንበር አቅራቢያ ከሚገኘው የቤልጎሮድ ግዛት አቅራቢያ አንድ የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላን መትቼ’ ጥያለሁ ብሏል።

«ለምን ይመርጣሉ?» የኢትዮጵያ - አሜሪካውያን ድምጽ

ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካውያን ነገ  በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከሁለቱ ዕጩ ተፎካካሪዎች አንዳቸውን ለመምረጥ፣  ለውሳኔያቸው መሰረት የሚያደርጓቸውን ጉ
የአሜሪካ ድምፅ

«ለምን ይመርጣሉ?» የኢትዮጵያ - አሜሪካውያን ድምጽ

ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካውያን ነገ  በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከሁለቱ ዕጩ ተፎካካሪዎች አንዳቸውን ለመምረጥ፣  ለውሳኔያቸው መሰረት የሚያደርጓቸውን ጉዳዮች ይናገራሉ። “በግልም ሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ ለውሳኔያችሁ ቅድሚያ የምትሰጡት ምንድነው?” የሚል ጥያቄ  ለተለያዩ የማኅበረሰብ ድርጅት ተወካዮች አንስተናል። ሰላምና ፍትሕ ለትግራይ ተወላጆች ዓለም አቀፍ ማኅበር ምክትል ሰብሳቢ  አቶ ፒተር ሃጎስ ገብረ  ለዚኽና ለሌሎች ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተውናል። አቶ ፒተር እንደ ዜጋ ሕወታቸውን ከሚመለከቱ አበይት ጉዳዮች፣ የተለየ ዋጋ እስከሚሰጧቸው ሌሎች እሴቶች ድረስ ቁልፍ ናቸው የሚሏቸውን ጉዳዮች ያነሳሉ።  ቃለ ምልልሱን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

በዘንድሮው የአሜሪካ ምርጫ ላለመሳተፍ የወሰኑ መራጮች

ማክሰኞ በሚካሄደው የአሜሪካ ምርጫ የሚወዳደሩትን እጩ ፕሬዘዳንቶች እየመረጡ ና ለመምረጥ የተዘጋጁ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቢኖሩም አንዳንዶቹ ግን በዘንድሮ
የአሜሪካ ድምፅ

በዘንድሮው የአሜሪካ ምርጫ ላለመሳተፍ የወሰኑ መራጮች

ማክሰኞ በሚካሄደው የአሜሪካ ምርጫ የሚወዳደሩትን እጩ ፕሬዘዳንቶች እየመረጡ ና ለመምረጥ የተዘጋጁ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቢኖሩም አንዳንዶቹ ግን በዘንድሮው ምርጫ ላለመሳተፍ የወሰኑም አሉ፡፡ ለዚህም የተለያየ ምክንያት አላቸው፡፡ የህግ ባለሙያና የዩስ አፍሪካ ኢንስቲትዩት ፕሬዘዳንት ዶክተር ታዲዮስ በላይ ግን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተሰሚነታቸውን ለማሳደግ በመራጭነትና ተመራጭነት የሚያደርጉትን ተሳትፎ ማጠናከር ይኖርባቸዋል ይላሉ፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡  

ቱርክ ከአፍሪካ ጋር ግንኙነቷን በማጥበቅ ላይ ትገኛለች

ዛሬ እሁድ በጅቡቲ እየተካሄደ ባለው የቱርክ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ቱርክ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እና ፍልስጤማዊያንን በዲፕሎማሲ ለመ
የአሜሪካ ድምፅ

ቱርክ ከአፍሪካ ጋር ግንኙነቷን በማጥበቅ ላይ ትገኛለች

ዛሬ እሁድ በጅቡቲ እየተካሄደ ባለው የቱርክ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ቱርክ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እና ፍልስጤማዊያንን በዲፕሎማሲ ለመደገፍ ጥሪ አድርጋለች።   ሀገሪቱ ባለፉት ቅርብ ዓመታት በከፍተኛ ሁኔታ በአፍሪካ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሰች ሲሆን፤ የቱርኩ መሪ ረጂብ ጣይብ ኤርዶዋንም ሥልጣን ላይ በቆዩባቸው አስርት ዓመታት ፤  በ31 የአፍሪካ ሀገራት 50 የሚደርሱ ጉብኝቶችን አድርገዋል።   በአሁን ሰዓት በጂቡቲ እየተካሄደ በሚገኘው የቱርክ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ አንጎላ፣ ቻድ፣ ኮሞሮስ፣ ኮንጎ ሪፐሊክ፣ ግብጽ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ጋና፣ ሞሪታኒያ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዛምቢያ እና ዚምባቡዌን ጨምሮ 14 የአፍርካ ሀገራት እየተሳተፉ ይገኛሉ።   በጉባኤው ላይ የተሳተፉት የቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ባድር አብዲላቲ ሀገራቸው ከአፍሪካ ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ባለፈው የጎርጎርሳዊያኑ ዓመት 35 ቢሊየን ዶላር እንደነበረ ገልጸው፤ ሀገራቸው በአፍሪካ ላይ በቀጥታ የምታፈሰው መዋዕለ ንዋይም ሰባት ቢልየን ዶላር ደርሷል በማለት ተናግረዋል።   በተጨማሪም ቱርክ በሰሃራ በስተደቡብ ባሉ ሀገራት የታጠቁ ሃይሎችን በማሰልጠን እና መሳሪያ በማስታጠቅ በአህጉሪቱ አራተኛዋ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገር ሆናለች። ባለፉት ቅርብ ወራትም በኢትዮጵያን እና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለማስታረቅ እንዲሁም በኒጀር የመዓድን ስምምነት ውሎችን እንዲካሄዱ ማገዟ ይታወሳል።   ቀጣዩ የቱርክ አፍሪካ ጉባኤ በጎሮጎሮሳዊያኑ 2026 እንደሚደረግ ተገልጿል።

የፕሪቶሪያ የተኩስ አቁም ስምምነት ሁለተኛ ዓመቱን ያዘ

የትግራይ ክልል አመራሮች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በፕሪቶሪያ በተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የሰፈሩ ቁልፍ ጉዳዮች በመንግስት በኩል እስካሁን ድረስ
የአሜሪካ ድምፅ

የፕሪቶሪያ የተኩስ አቁም ስምምነት ሁለተኛ ዓመቱን ያዘ

የትግራይ ክልል አመራሮች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በፕሪቶሪያ በተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የሰፈሩ ቁልፍ ጉዳዮች በመንግስት በኩል እስካሁን ድረስ ተፈጻሚ አልሆኑም አሉ።   የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ስምምነቱን ተፈጻሚ አለማድረግ በኢትዮጵያ ብሎም በቀጠናው “ሊንሰራፋ የሚችል” ያሉትን አሉታዊ ውጤት እንደሚያስከትል ተናግረዋል።  “ህገ-መንግስታዊ እውቅና የተሰጣቸውን የትግራይግዛቶች ወደ ነበሩበት መመለስ ላይ እብዛም ለውጥ አልታየም። መላው ምዕራብ ትግራይ አሁንም በአማራ ኃይሎችቁጥጥር ስር  ሲሆን በአንጻሩ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች  በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ” በማለት በኤክስ ማኅበራዊ ድረ ገጻቸው ላይ ትላንት ቅዳሜ አስፍረዋል።   አቶ ጌታቸው ረዳ አክለውም “የኤርትራ ኃይሎች በሰሜን ምዕራብ እና በምሥራቅ ትግራይ የያዟቸውን አንዳንድ ቦታዎች እንደያዙ ቀጥለዋል። በእነዚህ አካባቢዎችም በሰዎች ላይ ግፍ መፈጸሙ የተለመደ ነው። በዚህ ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች በማይታሰብ አስከፊ ሁኔታ በሀገር ውስጥ ተፈናቃይ መጠለያ ካምፖች ውስጥ እየማቀቁ ይገኛሉ” ብለዋል።   በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ የአማራ ክልል ቃል አቀባይ አቶ መንገሻ ፈንታውን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የኢትዮጵያ መንግስት ለአቶ ጌታቸው ረዳ አስተያየት በቀጥታ ምላሽ አልሰጠም። ይሁን እንጂ የፕሪቶሪያው የተኩስ አቁም ስምምነትን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ መንግስት ‘አወዛጋቢ አካባቢዎች’ ብሎ በሚጠራቸው ምዕራባዊ ትግራይ ዙሪያ ውሳኔ ለመስጠት የአካባቢው ተወላጆች የራሳቸውን እድል በራሳቸውን እንዲወስኑ መሻቱን አስታውቋል።   በሌላ በኩል ኤርትራ ሰራዊቶቿ በትግራይ ክልል ውስጥ እንደማይገኙ አስታውቃለች። “ለእነዚህ የውሸት እና አሳሳችውንጀላዎች ከረጅም ጊዜ በፊት ምላሽ ሰጥተናል” በማለት የኤርትራው የመረጃ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ዛሬ እሁድ ተናግረዋል።     “ሰሜናዊ እና ምሥራቃዊ ትግራይ ተብለው እየተጠቀሱ ያሉት ባድሜና ሌሎች የኤርትራ  ሉዓላዊ ግዛቶች  ሲሆኑ፤ በኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን በኩል የኤርትራ ሉዓላዊ ግዛት ተብለው የተካተቱ፤ አለም አቀፍ ህግን በመጣስ ለሃያዓመታት ያህል በወረራ ተይዘው የቆዩ ስፍራዎች ናቸው” በማለት ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።   በሌላ በኩል አቶ ጌታቸው ረዳ የፕሪቶሪያው የተኩስ አቁም ስምምነት በትግራይ ክልል ላለፉት ሁለት ዓመታት ሰላምን በማምጣት ውጤታማ ሆኗል ሲሉም ተናግረዋል።   አያይዘውም የኢትዮጵያ መንግስት የባንክ፣ የቴሌኮሚኒኬሽን፣ የምድር እና የአየር መጓጓዣ አገልግሎቶችን በመመለሱ ረገድ እርምጃዎች መውሰዱን ተናግረዋል።   ይህ በእንዲህ እንዳለ ዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ መንግስት በተሳለጠ መልኩ በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ የትግራይ ክልል ዜጎች ወደ መኖሪያ ቀያቸው እንዲመለሱ እንዲያደርግ ጠይቃለች። የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የፕሪቶሪያውን የተኩስ አቁም ስምምነት ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያ በማስመልከት ባወጣው መግለጫ “መንግስት በትግራይ ክልል ከሀገሪቱ ሰራዊት ውጭ ያሉ ኃይሎችን በሙሉ እንዲያሰወጣ” አሳስቧል።   በጎርጎርሳዊያኑ ህዳር ሁለት 2022 በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል በፕሪቶሪያ የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት “በዋናነት በትግራይ ክልል የመሳሪያ ድምጾች ጸጥ ብለዋል፣ የቆሙ አገልግሎቶች በድጋሚ ተጀምረዋል፤ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችም ተመልሰዋል” በማለት ዩናይትድ ስቴትስ ሂደቱን በመልካም ተቀብላዋለች ሲል የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመግለጫው አስታውቋል፡   በተጨማሪም ዩናይትድ ስቴትስ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ግጭቶች በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረጉ ውይይቶች እንዲፈቱ ጥሪ አድርጋለች።

የአሜሪካ ቢ-52 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች መካከለኛው ምሥራቅ ገቡ

ኢራን በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ ከፈጸመችው ዛቻ አንድ ቀን በኋላ ትላንት ቅዳሜ የአሜሪካ ቢ-52 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ መድረሳቸውን
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ ቢ-52 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች መካከለኛው ምሥራቅ ገቡ

ኢራን በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ ከፈጸመችው ዛቻ አንድ ቀን በኋላ ትላንት ቅዳሜ የአሜሪካ ቢ-52 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ መድረሳቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ጦር አስታውቋል። የመካከለኛው ምሥራቅ አና አካባቢው የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ እዝ “ፈንጂ ጣይ አውሮፕላኖቹ ከሚኖ የአየር ኃይል አምስተኛ ክንፍ ደርሰዋል” በማለት በማኅበራዊ ድረገጹ ላይ አስፍሯል።    የፔንታጎን ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ፓት ራይደር “ኢራን፣ አጋሮቿ ወይም በአካባቢቢዎቿ፤ በመካከለኛው ምሥራቅ ያሉ አሜሪካዊያንን ሰራተኞችን ወይም ፍላጎቶችን ለማጥቃት ይህንን ወቅት ይጠቀሙበታል” ያሉ ሲሆን አይይዘውም “ዩናይትድ ስቴትስ ህዝቦቿን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ትወስዳለች” ብለዋል ።

የኦሮሞ ነጻነት ተዋጊዎች የሰሜን ሸዋ ዞን ባለሥልጣንን ገደሉ

በኢትዮጵያ የሰሜን ሸዋ ዞን ባለሥልጣናት አርብ ዕለት በተፈጸም ጥቃት አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን መገደላቸውን አስታውቀዋል። ባለሥልጣቱ የውጫሌ ወረዳ ዋ
የአሜሪካ ድምፅ

የኦሮሞ ነጻነት ተዋጊዎች የሰሜን ሸዋ ዞን ባለሥልጣንን ገደሉ

በኢትዮጵያ የሰሜን ሸዋ ዞን ባለሥልጣናት አርብ ዕለት በተፈጸም ጥቃት አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን መገደላቸውን አስታውቀዋል። ባለሥልጣቱ የውጫሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ኮሩ ጉርሙ በታጠቁ ኃይሎች መገደላቸውን አስታውቀዋል። የግድያው ዜና በአካባቢው የብልጽግና ፓርቲ የፌስቡክ ገጽ ላይ ነው የሰፈረው። መግለጫው አቶ ንጉሴ “የተገደሉት” በካራ አካባቢ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ለመጎብኘት በተንቀሳቀሱበት ወቅት ነው በማለት አስፍሯል። ፓርቲው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት/ኦነግን ለጥቃቱ ተጠያቂ አድርጓል። በጥቃቱ በመንግስት ኃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል በተፈጠረ ግጭት ሌሎች በርካታ ሰዎችመቁሰላቸውን እና መገደላቸውን የሚያመላክቱ ዘገባዎች አሉ።   ‘አቶ ንጉሴ የህዝብ ፍላጎትን እና ጥቅምን ለማስከበር ቁርጠኝነት የነበራቸውና በህዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩ በከፍተኛ ፍላጎት ህዝባቸውን የመሩ ናቸው’ በማለት የፓርቲው መግለጫ አስፍሯል።  የአሜሪካ ድምጽ የውጫሌ ዞን የአካባቢ አመራሮች እና ከሰሜን ሸዋ አመራሮችን አግኝቶ ለማነጋገር ያደረገው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አማካሪ የሆኑት ጂሬኚ ጉደታ በውጫሌ ወረዳ የተደረገው ጥቃት በኦነግ መፈጸሙን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ በጥቃቱ እስካሁን ድረስ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ አላስታወቁም።

በኦሮሚያ ክልል በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 38 ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ በሚገኙ፣ ቢርቢሳ ጋሌ እና ደረባ በተሰኙ ሁለት ቀበሌዎች ውስጥ ረቡዕ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት ላይ በታጣቂዎች
የአሜሪካ ድምፅ

በኦሮሚያ ክልል በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 38 ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ በሚገኙ፣ ቢርቢሳ ጋሌ እና ደረባ በተሰኙ ሁለት ቀበሌዎች ውስጥ ረቡዕ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት ላይ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ። ወላጆቻቸውን በጥቃቱ ያጡ ቤተሰቦችን ጨምሮ ለአሜሪካ ድምጽ ስለጉዳዩ የተናገሩ ስድስት ሰዎች፣ በዕለቱ በተፈፀመው ጥቃት ቢያንስ 38 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል። ቁጥሩን እስከ አርባ ያደረሱት ነዋሪዎችም አሉ። በወረዳው ቢርቢሳ ጋሌ ቀበሌ ነዋሪ የኾኑት አቶ አሸናፊ ቦጋለ፤ ለሥራ ጉዳይ ከቤት ውጭ እንደነበሩ ገልጸው፣ በጥቃቱ ነፍሰጡር ባለቤታቸውን ጨምሮ አራት ቤተሰብ እንደተገደለባቸው ተናግረዋል።    “እናቴን፣ ልትወልድ ተቃርባ የነበረች  ባለቤቲንና  ልጄን በአንድ ጊዜ አጣሁ። አንደኛዋ ሴት ልጄ ህይወቷን ለማትረፍ ስትሮጥ በተተኮሰባት ጥይት ተመታ ቆስላለች” ይቺ በሕይወት የተረፈችው ልጃቸው አዳማ ሆስፒታል እንደምትገኝ አቶ አሸናፊ አክለው ገልጸዋል። ሌላው በዱግዳ ወረዳ፣ ቢርቢሳ ቀበሌ ነዋሪ የኾኑት አቶ ደጀኔ ጥላሁን ፣ የ77 ዓመት አዛውንት አባታቸው በጥቃቱ እንደተገደሉባቸው ገልጸዋል።   “በዕለቱ ማታ ቤት ውስጥ ሁለት ወንድሞቼ፣ ሁለት ሠራተኞችና አባቴ ነበርን። እንደ አጋጣሚ እናታችን ቤት አልነበረችም። ታጣቂዎቹ መጀመሪያ አካባቢውን የሚጠብቁ ይለስሉ ነበር። በኋላ “ወሪ ኩን” እያሉ በኦሮመኛ እየጮሁ ወደ ጊቢያችን ገቡ” በወቅቱ እርሻ ውስጥ መደበቃቸውን የሚናገሩት አቶ አሸናፊ፣ ታጣቂዎቹ የሳር ቤቶቹን አቃጥለው ትልቁን ቤት ለማቃጠል ሲሄዱ አባት ለልመና ከተደበቁበት ወተው ወደ ታጣቂዎቹ ማምራታቸውን ተናግረዋል። “እለምናቸዋለሁ ብሎ ሲሄድ ነው የተጎዳው። እናታችን ነች አስክሬኑን ያነሳችው። እጁን በስለት ተወግቷል፣ ደረቱንም በጥይት ተመቷል። ሥርዓተ ቀብሩም፣ ሐሙስ በዱግዳ ወረዳ ቢርቢሳ ጋሌ ቀበሌ መድሃኒያለም ቤተክርስትያን ተፈጽሟል።” ኩሼ ጌታቸው የተባለች ሌላ ጎረቤታቸውም መገደሏን የጠቆሙት አቶ ደጀኔ፣ “ነፍሰጡር እናትና ማየት የማይችሉ አዛውንት ጭምር ተገድለዋል። ጥቃቱ ዘግናኝ ነው። እንዲህ ያለ ዘግናኝ ድርጊት የፈጸሙት የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው ይባላል። እኛ ምን እናውቃለን። ግራ የሚያጋባ ነው።” ብለዋል። አቶ ደጀኔ ቀበሌዉ ከሶዶ ወረዳ ጋራ እንደሚዋሰን ገልጸው፣ በጥቃቱ ዋና ዋነኛ ተጎጂዎቹ የጉራጌ እና የአማራ ብሔር ተወላጆች መኾናቸውን ተናግረዋል። ሟች አባታቸው የአማራ ብሔረሰብ ተወላጅ መኾናቸውን ጠቅሳው፣ እናታቸው ደግሞ የጉራጌ የወላጅ መኾናቸውን ተናግረዋል።  ጥቃቱ ሲፈፀም ማንም የፀጥታ ኃይል ወደ አካባቢው አለመምጣቱን የተናገሩት አቶ ደጀኔ፣ አኹን የአካባቢው ሰላም አስተማማኝ ባለመኾኑ፣ የአባታቸው ቤተሰብ ቀያቸውን መልቀቃቸውን ገልጸዋል። አቶ ገመቹ አራባ የተባሉ ሌላ የደረባ ቀበሌ ነዋሪ፣ ቤተሰቦቻቸው እንደተገደሉ ተናግረዋል። “የደረሰብን ጥቃት በጣም አስደንጋጭ እና ከባድ አደጋ ነው። ለመግለፅ ቃላት የለኝም። ወንድ አያቴ እና ሁለት የአጎቴ ልጆች ተገድለውብኛል። ቤቶቻችን ተቃጥሎብናል። እንደምንም ብዬ ነው ቤተሰቦቼን ያተረፍኳቸው። የተገደሉትን ቀብረናቸው ተቀምጠናል። አሁን ራሱ ሜዳ ላይ ነው ያለነው።” አቶ ገመቹ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ተፈጸመ ባሉት ጥቃት፣ ከ40 ሰዎች በላይ መገደላቸውን ተናግረዋል። ከአንድ ቤተሰብ አምስት እና ስደስት የተገደለበት አለ። በጣክ አሳዛኝ ጥቃት የተፈፀመው መንግሥትን ትደግፋላችሁ፤ መሳሪያ ታጥቃችኃል በሚል ነው። ጥቃቱን የፈፀሙትም የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው” ብለዋል።  በጥቃቱ ቤታቸው ውስጥ የነበሩ ሕጻናት፣ ሴቶችና አቅመ ደካሞች ጭምር መጎዳታቸውን የተናገሩት አቶ ገመቹ  “አብዛኛው የተገደሉት የሶዶ ጉራጌ ተወላጆች ናቸው። በአከባቢው የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ቦራ የፀጥታ ኃይሎች በቅርብ ርቀት ቢኖሩም ጥቃቱን ማስቆም አልቻሉም። ከዚህ በፊትም በወረዳው ሰዎች እየታገቱ ገንዘብ እየተከፈለ ይለቀቁ ነበር።” ብለዋል። ጤሮ ተስፋ የተባሉ ሌላ የቢርቢርሳ ቀበሌ ነዋሪ በበኩላቸው በአካባቢ ዘግናኝ ያሉት ጥቃት በተደራጀ ኃይል መፈጸሙን ይናገራሉ። አቶ ጤሮ ስለግድያው ዘግናኝነት በዝርዝር አስረድተዋል። “ማየት የተሳናቸው፣ ሴቶች፣ ሕጻናት፣ ወንዶች በአጠቃላይ ወደ 40 የሚኾኑ ሰዎች ተገድለዋል። ግድያውን የፈጸመው ሸኔ የተባለ ቡድን ነው። ድርጊቱ ለአዕምሮ የሚከብድ ነው። ሰዎችን መለየት አልቻልንም ዝም ብለን አፍሰን ቀብረናቸዋል። በጥቃቱ የተጎዳው አብዛኛው የጉራጌ ማኅበረሰብ ተወላጅ ሲኾን ነዋሪው አኹን ወደ መቂና ጉራጌ እየሸሸ ነው” ብለዋል።   የዱግዳ ወረዳ ቢርቢሳ ጋሌ ቀበሌ ነዋሪ የኾኑና ለደኅንነታቸው ስለሚሰጉ ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ ነዋሪ በዕለቱ ዝናብ እየዘነበ እንደነበር ገልጸው ምሽት አካባቢ ጩኸት መስማታቸውን ይናገራሉ። “ከዚያ ቤት ሲቃጠል ነው የተመለከትነዉ፣ ጥቃቱ የጀመረው ማታ አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ ሲኾን እየጎላ የመጣው ግን ወደ ሁለት ሰዓት ነው። እናም እስከ ምሽቱ ስድስት ሰዓት ድረስ ግድያው ቀጠለ።  ጥቃቱን ያደረሱት ኦሮምኛ ይናገራሉ አሉን። እኛ በጊዜው ተደብቀን ነበር።  ኦነግ ሸኔ ናቸው የሚል ነገር ነው የተነገረን። በዚህ ጥቃት በሚያሳዝን መልኩ፣ ሕፃናት፣ አዛውንቶች፣ ነፍሰጡር ሴቶች ጭምር ቤት ውስጥ ተቃጥለዋል። በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው የተከሰተው።” በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዓት ዱግዳ ወረዳ መፈጸሙን ተናግረዋል። “ የ38 ሟቸው ቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጽሟል። ከደረባ 24፣ ከኩሬ 17፣ ከቢጥሲ ደግሞ ሁለት ነበሩ። የወረዳዉ መንግሥት ባለሥልጣናት ባሉበት ነው ከተቃጠለው ቤት አስክሬን ወጥቶ ኩሬ ስላሴ ቤተክርስትያን የተቀበረው። ፈጣሪ ይርዳን እንጂ አሁን አብሮ ሲኖር የነበረ ሰው እርስ በርሱ በጥርጣሬ ዐይን እየተያየ ነው። መንግሥትም ይህን እንዴት እንደተመለከተው አላውቅም።” ነዋሪው አክለው ጥቃቱ ሲፈጸም የነበረው እስከ እኩለ ለሊት ቢኾንም፣ የፀጥታ አካላት የደረሱት ግን ማለዳ ላይ ነው ብለዋል። በጥቃቱ የኦሮሞ ተወላጅ ማኅበረሰብ አባላትም መጎዳታቸውን ተናግረዋል። “ኦሮሞ ኾኖ ቤቱ የተቃጠለበትና የተገደለም አለ። ለምሳሌ ከደረባ መኮንን የሚባለው ሰው ከተገደሉት አንዱ ነው።  እሱ ኦሮሞ ነዉ፣ ሌላ የአያቴ ባል ጎሳዬ የሚባልም ተገድሏል። ነገር ግን በዚህ ጥቃት የተጎዱት አብዛኛው የጉራጌ ተወላጆች ናቸው።” ሲሉ ነዋሪው ኹኔታውን አስረድተዋል። የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ ተካልኝ ንጉሴ የተፈፀመው ጥቃት ዘግናኝ መኾኑን ተናግረዋል። ነገር ግን ተገደሉ የተባሉ ሰዎችን ቁጥር ማረጋገጥ እንደማይችሉ ገልጸዋል። ሰዎቹ የተገደሉት በመኖሪያ በታቸው እሳት ተለቀቆባቸው እና መሳሪያ ተተኩሶባቸው እንደኾነ አስረድተዋል። ሴቶች፣ አረጋዊያን፣ አቅመ ደካሞች በእሳት ተቃጥለው መሞታቸውን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የክልሎቹ የፀጥታ ሃይሎች አከባቢውን ለማረጋጋት ወደ ስፍራው መግባታቸውን ያስታወቁት አቶ ተካልኝ ተጎጂዎችን ለመርዳት በሁለቱም አስተዳደር በኩል ጥረት መጀመሩን ተናግረዋል።  ነዋሪዎቹና የተጎጂ ቤተሰቦች ኦነግ ሸኔ ሲሉ የጠሯቸውን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርገዋል። ኖርዌይና አፍሪካ ውስጥ እንደሚኖሩ የገለጹት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አማካሪ መኾናቸውን የተናገሩት፣ አቶ ጅሬና ጉደታ ስለጉዳዩ መስማታቸውን ገልፀው፣ ታጣቂዎቹ ከጥቃቱ ጀርባ እንደሌሉና በመናገር አስተባብለዋል። ታጣቂዎቻቸው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት እንደማይፈጽሙም ገልጸዋል።  አቶ ጅሬና ማስተባበላቸውን ገልጸን አስተያያት እንዲሰጡ የጠየቅናቸው የተጎጂ ቤተሰብ አቶ ገመቹ አራባ፣ ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች ታጣቂዎቹ  ይታወቁባቸዋል ያሏቸውን መለያዎች መናገራቸውን ገልጸዋል። “ከጥቃቱ የተረፉ እና የቆሰሉ ሰዎችም  አይተዋቸዋል። ሌላው ነገር ቢቀር በሹሩባቸው እንለያቸዋለን። ራሳቸው ናቸው ሰላማዊ ሰዎችን የገደሉት። ከዚህ በፊትም ራሳቸው እየመጡ ሦስት አራት ጊዜ ሞክረው አልተሳካላቸውም ነበር።” በጉዳዩ ላይ ከኦሮሚያ ክልል እና ከአካባቢው ባለሥልጣናት መረጃን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

የኢራን መንፈሳዊ መሪ እስራኤልና አሜሪካ ከባድ ምላሽ እንደሚጠብቃቸው ዛቱ

የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ ዛሬ ቅዳሜ ባሰሙት ንግግር በኢራን እና አጋሮችዋ ላይ ለሚደርሰው ጥቃት “ከባድ ምላሽ” እንደሚሰጡ በመግለጽ እስራኤል
የአሜሪካ ድምፅ

የኢራን መንፈሳዊ መሪ እስራኤልና አሜሪካ ከባድ ምላሽ እንደሚጠብቃቸው ዛቱ

የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ ዛሬ ቅዳሜ ባሰሙት ንግግር በኢራን እና አጋሮችዋ ላይ ለሚደርሰው ጥቃት “ከባድ ምላሽ” እንደሚሰጡ በመግለጽ እስራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ ላይ ዝተዋል፡፡ የካሜኒ ንግግር የተሰማው፣ እስራኤል እ.ኤ.አ ጥቅምት 26  በኢራን ወታደራዊ ሰፈሮች እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ባነጣጠረ ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎችን መግደሏን ተከትሎ የኢራን ባለስልጣናት ሌላ ምላሽ እንደሚሰጡ ያሰሙት ዛቻ እየጨመረ ከመጣ በኋላ ነው፡፡ ከሁለቱም ወገኖች የሚሰነዘር ተጨማሪ ጥቃት ሰፊውን መካከለኛ ምስራቅ ሊያካልል ይችላል የሚል ስጋት አሳድሯል፡፡  በጋዛ ሰርጥ በእስራኤልና ሀማስ ጦርነት፣ እንዲሁም እስራኤል ሂዝቦላን ለማጥቃት ሊባኖስ ላይ በምታካሂደው ወረራ ሳቢያ በተለይ ችግር ውስጥ ያለውን ቀጠና ወደባሰ ክልላዊ ግጭት እንዳያስገባ ተሰግቷል፡፡  ይህ ስጋት የተሰማው በተለይ ማክሰኞ ከሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት መሆኑም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡ ካሜኒ «ጠላቶች የጽዮናዊው መንግስትም ይሁን የዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ፣ በኢራን ህዝብ እና የተቃውሞ ግንባሩ ላይ እያደረጉት ላሉት ነገር በርግጠኝነት ከባድ ምላሽ ይሰጣቸዋል »በማለት ሲናገሩ የኢራን መንግስት በመገናኛ ብዙሃን በለቀቀው ቪዲዮ አሳይቷል። መንፈሳዊ መሪው በዛቻው ስለተገለጸው ጥቃት ዓይነት፣ ጥቃቱ ሰለሚፈጸምበት ጊዜ እና ቦታ ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡም።  የዩናይትድ ስቴትስ ጦር በመላው መካከለኛ ምስራቅ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን አንዳንድ ወታደሮችም እስራኤል ውስጥ ከውጭ የሚመጡ ጥቃቶችን ከሚመክት የጸረ ሚሳይል መሣሪያ ታጣቂ ቡድን ጋር እንደሚሰሩ ተመልክቷል፡፡   የ85 አመቱ ካሜኒ ቀደም ሲል በሰጡት አስተያየት “ባለስልጣናት የኢራንን ምላሽ ይመዝናሉ” ያሉ ሲሆን የእስራኤል ጥቃት “መጋነን ወይም በቀላሉ መታየት የለበትም” ሲሉ የበለጠ ጥንቃቄ የተሞላበት አካሄድን መርጠዋል። ካሜኒ በቴህራን ዩኒቨርሲቲ የሻህ አገዛዝን በተቃወሙ ተማሪዎች ላይ የኢራን ወታደሮች የተኩስ እሩምታ የከፈቱበትንና እኤአ ህዳር 4 ቀን 1978 የሚከበረውን  ቀን አስመልክቶ ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጋር ዛሬ ቅዳሜ ተገናኝተዋል። ጥቃቱ በርካታ ተማሪዎችን የገደለ እና ያቆሰለ ሲሆን፣  በወቅቱ ኢራንን አስጨንቆ የነበረውን ውጥረት የበለጠ  በማባባስ በመጨረሻም ሻህ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡና እኤአ የ1979 የእስልምና አብዮት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡ በስብሰባው ቦታ ካሜኒን የተቀበሉ ታዳሚዎች “ በደም ሥራችን ውስጥ ያለው ደም ለመሪያችን የተሰጠ ስጦታ ነው” የሚል መፈክር እያሰሙ በደማቅ አቀባበል እንደተቀበሏቸው አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ አንዳንዶቹም የተገደሉት የሂዝቦላህ መሪ ሃሰን ናስራላህ እኤአ በ2020 የአሜሪካ ወታደሮች “ በሬሣ ሳጥን ይመለሳሉ” ሲሉ በዛቱበት ንግግር ያሳዩትን የእጅ ምልክት አሳይተዋል፡፡  ኢራን የአሜሪካ ኤምባሲው የታጋቾች ቀውስ የተፈጸመበትን 45ኛ ዓመት ነገ እሁድ ታከብራለች።  እ.ኤ.አ. ህዳር 4 ቀን 1979 እስላማዊ ተማሪዎች ኤምባሲው ላይ ያደረሱት ጥቃት ለ444 ቀናት የቆየ ቀውስ አስከትሏል፡፡ ይህ ቀውስ በቴህራን እና በዋሽንግተን መካከል ለአስርት አመታት የዘለቀውን ጠላትነት አጠናክሮ ቀጥሏል።  

ሩሲያ ሰዓታት በፈጀ የድሮን ጥቃት ኪቭን ዒላማ አደረገች

ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ በአንድ ሌሊት የፈፀመች የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት እስከ ማለዳ ድረስ የዘለቀ እና ቢያንስ አንድ ሰው ማቁሰሉን የ
የአሜሪካ ድምፅ

ሩሲያ ሰዓታት በፈጀ የድሮን ጥቃት ኪቭን ዒላማ አደረገች

ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ በአንድ ሌሊት የፈፀመች የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት እስከ ማለዳ ድረስ የዘለቀ እና ቢያንስ አንድ ሰው ማቁሰሉን የከተማዋ ባለስልጣናት ዛሬ ቅዳሜ ተናገሩ። «የድሮኖቹ ስብርባሪዎች ስድስት የከተማ ወረዳዎች ላይ ሲወድቁ አንድ የፖሊስ መኮንን ቆስለዋል» ያሉት የከተማው ወታደራዊ አስተዳዳሪ ሰርሂ ፖፕኮ፣ በጥቃቱ የመኖሪያ ሕንፃዎች መውደማቸውንና እና የእሳት ቃጠሎ መነሳቱን ተናግረዋል ። የከተማዪቱ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ ቀደም ብለው በሰጡት መግለጫ ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውን ተናግረዋል። ፖፕኮ በማህበራዊ ሚዲያ መድረካቸው ላይ «ሌላ ምሽት፣ ሌላ የአየር ወረራ፣ ሌላ የማንቂያ ደወል፣ ሌላ ሰው አልባ ጥቃት፣ የሩስያ ፌዴሬሽን የታጠቁ ኃይሎች በቀድሞው እና በተለመደው ስልታቸው ኪቭ ላይ በድጋሚ ሌላ ጥቃት ሰንዝረዋል» ሲሉ ጽፈዋል፡፡ ፖፕኮ አክለውም “ኪቭ ላይ ያነጣጠሩ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በሙሉ ተመተው ወድቀዋል” ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ “ግን በአሁኑ ጊዜ ከከተማዋ ውጭ ባለው የአየር ክልል ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ድሮኖች ወደ ዋና ከተማዋ ሊዞሩ ይችላሉ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የሮይተርስ ዘጋቢዎች ከአምስት ሰዓታት በላይ በፈጀው የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ውስጥ በከተማው እና በአካባቢው ፍንዳታዎችን መስማታቸውን ዘግበዋል። የኪቭ ጦር ትላንት አርብ እንዳስታወቀው የሞስኮ ጦር በጥቅምት ወር ብቻ በዩክሬን በሚገኙ የሲቪል እና ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ “ከ2,000 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለጥቃት አሰማርቷል” ብሏል። ሩሲያ ጥቃቶችዋ በሲቪሎች ላይ ያነጣጠሩ ናቸው የሚለውን ስትቃወም “ የኃይል ማመንጫዎች የዩክሬን ወታደራዊ መሠረተ ልማት አካል ሲሆኑ ህጋዊ ዒላማዎች ናቸው” ብላለች ።

ጦርነት ጋዜጠኞችን የሚገድሉትን አካላት ተጠያቂነት አስቸጋሪ ያደርገዋል ተባለ

ጋዜጠኞች ዒላማ ለተደረጉበት ግድያ ፍትህን ማስፈን በተለይ በጦርነት ጊዜ የበለጠ የተወሳሰበ ከባድ ስራ መሆኑን ዓለም አቀፍ ተቋማትና ባለሙያዎች ገለጹ፡፡ በ
የአሜሪካ ድምፅ

ጦርነት ጋዜጠኞችን የሚገድሉትን አካላት ተጠያቂነት አስቸጋሪ ያደርገዋል ተባለ

ጋዜጠኞች ዒላማ ለተደረጉበት ግድያ ፍትህን ማስፈን በተለይ በጦርነት ጊዜ የበለጠ የተወሳሰበ ከባድ ስራ መሆኑን ዓለም አቀፍ ተቋማትና ባለሙያዎች ገለጹ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ በዓለም ላይ «85 በመቶው የጋዜጠኞች ግድያ አሁንም መፍትሄ አላገኘም» ሲል ዩኔስኮ ቅዳሜ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል።  እ.ኤ.አ. በ2013 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እኤአ ህዳር 2ን በጋዜጠኞች ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ያለመከሰስ መብትን የማስቆም ዓለም አቀፍ ቀን ብሎ አውጇል። የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ ወይም ሲፒጄ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጆዲ ጊንስበርግ “በጋዜጠኞች ግድያ ላይ ያለመከሰስ መብት ከረዥም ጊዜ ጀምሮ የተለመደ እና በተለይም እየተካሄደ ያለ ግጭት ችግሩን ያባብሰዋል” ብለዋል፡፡ እኤአ ከ2006 ጀምሮ በጋዜጠኞች ላይ ለደረሱ ግድያዎች 85 ከመቶ የሚሆኑት መፍትሄ ያላገኙ መሆናቸው በዘገባው ተጠቅሷል፡፡ እንደ እስራኤል-ጋዛ፣ ዩክሬን፣ ምያንማር እና ሄይቲ ያሉ ጦርነት እና ግጭቶች በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን ይጨምራሉ፣ ምርመራዎችን እና የህግ ተጠያቂነትንም ያወሳስባሉ ተብሏል፡፡ በጋዛ 134፣ ባብዛኛው ፍልስጤማውያን የሆኑ ጋዜጠኞች የተገደሉ ሲሆን፣ እስራኤል ተጠያቂነት በማጣት ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ዘገባው አመልክቷል። እ.ኤ.አ. ጥቅምት 13 ቀን 2023 የሊባኖሱ የሮይተርስ ጋዜጠኛ ኢሳም አብደላህ የተገደለ ሲሆን ሌሎች 6 ጋዜጠኞችም ቆስለዋል፡፡ ዩክሬን ውስጥ ያለው የሩሲያ ጦርነት ቢያንስ 15 ጋዜጠኞች እንዲሞቱ አድርጓል፡፡ ዩኔስኮ እንደዘገበው በየአራት ቀኑ አንድ ጋዜጠኛ እንደሚሞት ገልጾ እነዚህን በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ ወንጀሎች ለመግታት የፕሬስ ነጻነት ማስከበርና ህጋዊ እምርጃ እንዲወሰድ አሳስቧል፡፡  

የተከፋፈሉት የህወሓት አመራሮች ፖለቲካዊ ውይይት ለመጀመር ቃል መግባታቸው ተገለጸ

በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት በሰላማዊና ፓለቲካዊ መንገድ ለመፍታት ቃል መገባቱን በትግራይ ክልል የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት ገለጹ። በትግራ
የአሜሪካ ድምፅ

የተከፋፈሉት የህወሓት አመራሮች ፖለቲካዊ ውይይት ለመጀመር ቃል መግባታቸው ተገለጸ

በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት በሰላማዊና ፓለቲካዊ መንገድ ለመፍታት ቃል መገባቱን በትግራይ ክልል የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት ገለጹ። በትግራይ ክልል በቅርቡ የራሳቸው ሲኖዶስ የመሰረቱት ሊቃነ ጳጳሳት፣ በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩንት ለመፍታት የክልልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታችው ረዳ ና ዶክተር የፓርቲው ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በዛሬው ዕለት ፊት ለፊት እንዲገናኙ እንዳደረጉ ገለጸዋል። ፖለቲከኞቹ በቅርቡ ተገናኝተው እንደሚወያዩ ሊቀጳጳሳቱ ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደቡብ አፍሪካ፣ ፕሪቶሪያ ላይ የተካሄደው ተኩስን በዘላቂነት የማቆም ስምምነት ነገ ሁለተኛ ዓመቱን የሚደፍን ሲኾን፣ ስምምነቱን አስመልክቶ በመቐለ ከተማ የነዋሪዎች አስተያየት ጠይቀናል። ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በወባ ተጠቅተዋል ተባለ

በኢትዮጵያ ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ 7.3 ሚሊዮን ሰዎች በወባ መያዛቸውንና 1ሺሕ 157 በበሽታው መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በኢትዮጵያ 75 ከመቶ የሚ
የአሜሪካ ድምፅ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በወባ ተጠቅተዋል ተባለ

በኢትዮጵያ ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ 7.3 ሚሊዮን ሰዎች በወባ መያዛቸውንና 1ሺሕ 157 በበሽታው መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በኢትዮጵያ 75 ከመቶ የሚሆነው መሬት ለወባ ትንኝ ተጋላጭ በመሆኑ ለሃገሪቱ ከፍተኛ የጤና ተግዳሮት እንደደቀነም ድርጅቱ አስታውቋል። በእነዚህ አካባባዎች ከሚኖሩት ውስጥ 69 በመቶ የሚሆኑት በወባ የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ሲሆን፣ ከአምስት ዓመት በታች ሳሉ ከሚሞቱት ሕፃናት ውስጥ 20 በመቶ የሚሆኑት ሕይወታቸው የሚያልፈው በወባ ምክንያት መሆኑንም ዓለም አቀፉ የጤና ተቋም አስታውቋል። በተለይም ግጭት ባለባቸው ሥፍራዎች የጤና አገልግሎት ማዳረሡ አስቸጋሪ እንደሆነም የጤና ድርጅቱ ጠቁሟል። የሌሎች በሽታዎች መዛመትም ሁኔታውን ይበልጥ አስቸጋሪ እንዳደረገው ድርጅቱ አስታውቋል።

የቦትስዋናው ፕሬዝደንት በምርጫ መሸነፋቸውን አመኑ

የቦትስዋናው ፕሬዝደንት ሞከዌትሲ ማሲሲ በምርጫ መሸነፋቸውን አምነዋል። የምርጫው ውጤት ገና ባይታወጅም ሃገሪቱ ከእንግሊዝ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉ
የአሜሪካ ድምፅ

የቦትስዋናው ፕሬዝደንት በምርጫ መሸነፋቸውን አመኑ

የቦትስዋናው ፕሬዝደንት ሞከዌትሲ ማሲሲ በምርጫ መሸነፋቸውን አምነዋል። የምርጫው ውጤት ገና ባይታወጅም ሃገሪቱ ከእንግሊዝ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 58 ዓመታት በሥልጣን ላይ የከረመው ፓርቲያቸው ‘የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ’ እስከ አሁን በተገኘው ውጤት በአራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ‘አምብሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ’ በከፍተኛ ድምጽ እየመራ ሲሆን፣ የፓርቲው እጩ ዱማ ቦኮ  በዓለም ከፍተኛ አልማዝ አምራች ከሆኑት ሃገራት ውስጥ አንዷ የሆነችው ደቡብ አፍሪካዊቷ ሃገር ፕሬዝደንት የመሆን ዕድል አላቸው ተብሏል። ማሲሲ ለቦኮ ስልክ በመደወል በምርጫው መሸነፋቸውን እንደነገሯቸው አስታውቀዋል። “በዲሞክራሲ ሂደቱ ኩራት ተሰምቶኛል። ለሁለተኛ የሥልታን ዘመን መመረጥ ብሻም፣ ገለል ብዬ በሥልጣን ሽግግሩ ተሳትፎ አደርጋለሁ” ብለዋል ማሲሲ። ቦትስዋና በአፍሪካ የተረጋጋ ዲሞክራሲ ካላቸው ሃገራት ውስጥ ነች በሚል ስትሞካሽ፣ በዓለም ከሩሲያ በመቀጠል ሁለተኛ የአልማዝ አምራች ሃገር ነች፡፡

ታዳጊ ሀገሮችን ለኒውክሊየር ኃይል ተጠቃሚነት ያበቃል የተባለለት አዲሱ የኤሌክትሪክ ኅይል ማመንጫ ቴክኖሎጂ

በአንግሊዝኛ የምህጻር ስማቸው ኤስ.ኤም.አር ተብለው የሚጠሩት ትናንሽ የኒውክሊየር ኅይል ማመንጫዎች ከበርቴ ላልኾኑት ሀገሮች በንጽጽር በርካሽ ወጪ የኒውክሊ
የአሜሪካ ድምፅ

ታዳጊ ሀገሮችን ለኒውክሊየር ኃይል ተጠቃሚነት ያበቃል የተባለለት አዲሱ የኤሌክትሪክ ኅይል ማመንጫ ቴክኖሎጂ

በአንግሊዝኛ የምህጻር ስማቸው ኤስ.ኤም.አር ተብለው የሚጠሩት ትናንሽ የኒውክሊየር ኅይል ማመንጫዎች ከበርቴ ላልኾኑት ሀገሮች በንጽጽር በርካሽ ወጪ የኒውክሊየር ኅይል እንደሚያስገኙ የጉዳዩ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ SMR ምንድናቸው? ጠቃሚነታቸውን የሚናገሩት ወገኖች አብዝቶ ያስደሰታቸው ምንድነው? የቪኦኤው ሄንሪ ሪጅዌል ከለንደን ያጠናቀረው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በፕሬዝዳንትነት ለመመረጥ የመመዘኛ መስፈርቶች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ሆኖ ለመመረጥ የሚያስፈልጉት መስፈርቶች ምንድን ናቸው?
የአሜሪካ ድምፅ

በፕሬዝዳንትነት ለመመረጥ የመመዘኛ መስፈርቶች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ሆኖ ለመመረጥ የሚያስፈልጉት መስፈርቶች ምንድን ናቸው?

ፕሬዝደንታዊ እጩዎቹ ‘የመዝጊያ ሙግታቸውን’ አቀረቡ

በአሜሪካ ለፕሬዝደንትነት የሚወዳደሩት የሁለቱ ፓርቲ እጩዎች፣ በዚህ ከምርጫው በፊት ባለው የመጨረሻው ሳምንት፣ “የመዝጊያ ሙግት” በሚል የሚገለፀውን ንግግ
የአሜሪካ ድምፅ

ፕሬዝደንታዊ እጩዎቹ ‘የመዝጊያ ሙግታቸውን’ አቀረቡ

በአሜሪካ ለፕሬዝደንትነት የሚወዳደሩት የሁለቱ ፓርቲ እጩዎች፣ በዚህ ከምርጫው በፊት ባለው የመጨረሻው ሳምንት፣ “የመዝጊያ ሙግት” በሚል የሚገለፀውን ንግግራቸውን በየፊናቸው አድርገዋል። የቪኦኤ ከፍተኛ የዋሽንግተን ዘጋቢ ካሮሊን ፕረሱቲ ዘገባዋን ልካለች።ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ዩናይትድ ስቴትስ በሊባኖስ የ60 ቀናት ተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲደረግ እየጣረች መሆኑ ተገለጸ

በእስራኤል እና በኢራን በሚደገፈው የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላህ መካከል የሚካሄደውን ጦርነት ለማርገብ፣ የዩናይትድ ስቴትስ አሸማጋዮች የ60 ቀናት ተኩስ ማ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩናይትድ ስቴትስ በሊባኖስ የ60 ቀናት ተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲደረግ እየጣረች መሆኑ ተገለጸ

በእስራኤል እና በኢራን በሚደገፈው የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላህ መካከል የሚካሄደውን ጦርነት ለማርገብ፣ የዩናይትድ ስቴትስ አሸማጋዮች የ60 ቀናት ተኩስ ማቆምም ስምምነት ለማስጀመር እየጣሩ መሆኑን ሁለት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሮይተርስ አስታወቁ። ስለድርድሩ ገለጻ የተደረገላቸው አንድ ግለሰብ እና በሊባኖስ የሚሠሩ አንድ ከፍተኛ ዲፕሎማት እንዳመለከቱት፣ ለሁለት ወራት የሚቆየው የተኩስ ማቆም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት፣ እ.አ.አ በ2006 ደቡባዊ ሊባኖስን ከጦር መሳሪያ ነፃ ለማድረግ ያሳለፈውን '1701' የተሰኘ የውሳኔ ሐሳብ ተግብራዊ ለማድረግ ይጠቅማል ብለዋል። በቤይሩት የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ቃል አቀባይ ሳማ ሐቢብ ስለ ውሳኔ ሐሳቡ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ «የውሳኔ ሐሳብ 1701ን ተግባራዊ የሚያደርግ እና የእስራኤል እና የሊባኖስ ዜጎችን ወደየቤታቸው የሚመልስ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንፈልጋለን» ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የተጀመረው እስራኤል በሊባኖስ የምታደርገው ዘመቻ እየሰፋ ባለበት ወቅት ሲሆን ለሦስት ተከታታይ ቀናት ደቡባዊ የሊባኖስ ከተማ በሆነችው ኪያም አቅራቢያ ከፍተኛ ውጊያ መደረጉን ሂዝቦላህ አስታውቋል። በአዲሱ የተኩስ አቁም ሀሳብ ላይ እየሰሩ ያሉት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ልዩ መልዕክተኛ አሞስ ሆችስቴይን በዚህ ወር መጀመሪያ ቤይሩት ለሚገኙ ጋዜጠኞች በሰጡት ቃል፣ እስራኤልም ሆነች ሊባኖስ የፀጥታ ምክርቤቱን የውሳኔ ሐሳብ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው የተሻሉ የማስፈጸሚያ ዘዴዎች እንደሚያስፈልጉ ተናግረው ነበር።   

ሩሲያ የሚጣሉባትን ማዕቀቦች እንዳታስተጓጉል አሜሪካ አዲስ እርምጃ ወሰደች  

ዩናይትድ ስቴትስ ሩሲያን ዒላማ ያደረጉ በመቶዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ማዕቀቦች መጣሏን ረቡዕ እለት አስታውቃለች። ማዕቀቦቹ ሩሲያ የሚጣሉባትን ማዕቀቦች ለማለ
የአሜሪካ ድምፅ

ሩሲያ የሚጣሉባትን ማዕቀቦች እንዳታስተጓጉል አሜሪካ አዲስ እርምጃ ወሰደች  

ዩናይትድ ስቴትስ ሩሲያን ዒላማ ያደረጉ በመቶዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ማዕቀቦች መጣሏን ረቡዕ እለት አስታውቃለች። ማዕቀቦቹ ሩሲያ የሚጣሉባትን ማዕቀቦች ለማለፍ የምታደርገውን ጥረት ለመመከት አሜሪካ ቁርጠኛ መሆኗን እንደሚያሳይ ተመልክቷል። የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ባወጡት መግለጫ፣ ወደ 400 የሚጠጉ ተቋማት እና የተለያየ አገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ መጣላቸውን ገልጸዋል። ማዕቀቡ ከተጣለባቸው መካከል በርካታ የቻይና፣ ሆንግ ኮንግ እና ህንድ ኩባንያዎች እንደሚገኙበትም አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን ለሮይተርስ ተናግረዋል። በተጨማሪም በሩሲያ፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ በቱርክ፣ በታይላንድ፣ በማሌዥያ፣ በስዊዘርላንድ እና በሌሎች ሀገራት የሚገኙ ተቋማት ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል። ጥቃቅን ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ጨምሮ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ህብረት የላቁ ያሏቸውን እና ሩሲያ ለዩክሬን ወረራ ልትጠቀምባቸው የሚችላቸውን ምርቶች፣ ሀገራት ለሩሲያ እንዳያቀርቡ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በተደጋጋሚ ስታስጠነቅቅ ቆይታለች። ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ባለስልጣን፣ ማዕቀቡ «ለመንግስታትም ሆነ በነዚህ ሀገራት ለሚገኙ የግል ኢኮኖሚ ዘርፎች፣ ሩሲያ የሚጣልባትን ማዕቀብ ለመሸሽ የምታደርጋቸውን ጥረቶች ለመመከት ቁርጠኛ መሆናችንን የሚያሳይ መልዕክት ሊያስተላልፍ ይገባል» ብለዋል። ማዕቀቡ ዒላማ ካደረጋቸው ተቋማት መካከል መቀመጫውን ህንድ ያደረገው 'ፉትሬቮ' አንዱ ሲሆን፣ ሩሲያ ለሚገኘው የሰው ሰራሽ አውሮፕላን (ድሮን) አምራች ኩባንያ እጅግ ተፈላጊ የሆኑ ቁሶችን በማቀርብ ክስ ቀርቦበታል።  

VOA60 Africa - Botswana votes with ruling party seeking to extend six decades of power

Botswana: Voters headed to the polls Wednesday in southern Africa's diamond-rich nation to cast ballots in the general election. The ruling party seeks to extend its nearly six-decade rule and hand a second term to President Mokgweetsi Masisi.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Botswana votes with ruling party seeking to extend six decades of power

Botswana: Voters headed to the polls Wednesday in southern Africa's diamond-rich nation to cast ballots in the general election. The ruling party seeks to extend its nearly six-decade rule and hand a second term to President Mokgweetsi Masisi.

VOA60 America - More than 53 million Americans already have voted

More than 53 million Americans already have voted in the election, according to Election Hub at the University of Florida on Tuesday.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - More than 53 million Americans already have voted

More than 53 million Americans already have voted in the election, according to Election Hub at the University of Florida on Tuesday.

VOA60 World - Dozens dead in flash floods in Spain’s Valencia region

Dozens of people have died after flash floods swept away cars, turned village streets into rivers and disrupted rail lines and highways in Spain’s Valencia region. Rainstorms on Tuesday caused flooding in a wide swath of southern and eastern Spain, stretchi
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Dozens dead in flash floods in Spain’s Valencia region

Dozens of people have died after flash floods swept away cars, turned village streets into rivers and disrupted rail lines and highways in Spain’s Valencia region. Rainstorms on Tuesday caused flooding in a wide swath of southern and eastern Spain, stretching from Malaga to Valencia.

ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካውያን ከምርጫው ቀን በፊት ድምጻቸውን እየሰጡ ነው

በመጪው ማክሰኞ ኅዳር 5 ቀን 2024 ዓ.ም. ለሚካሄደው ምርጫ «የቅድሚያ ምርጫ ድምጽ» እየተሰጠ ነው። ከምርጫው ቀን አስቀድሞ ድምጽ እንዲሰጥ የሚፈቅዱ ክፍለ ግ
የአሜሪካ ድምፅ

ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካውያን ከምርጫው ቀን በፊት ድምጻቸውን እየሰጡ ነው

በመጪው ማክሰኞ ኅዳር 5 ቀን 2024 ዓ.ም. ለሚካሄደው ምርጫ «የቅድሚያ ምርጫ ድምጽ» እየተሰጠ ነው። ከምርጫው ቀን አስቀድሞ ድምጽ እንዲሰጥ የሚፈቅዱ ክፍለ ግዛቶች የተለያዩ ደንቦች እና የጊዜ ሰሌዳዎችን ይከተላሉ። ከወዲሁ ድምጽ መስጠት የሚፈቅዱ ክፍለ ግዛቶችም አሉ። በአንዳንድ ክፍለ ግዛቶች አስቀድሞ ድምጽ ለመስጠት የተቀመጠው የመመዝገቢያ ቀነ ገደብ ያበቃ ሲኾን፣ በአንዳንዶቹ ክፍለ ግዛቶች ደግሞ አሁን እየተጀመረ ነው። በዚህ ሂደት ድምጽ መስጠት ጠቃሚ መሆኑን ድምጻቸውን የሰጡ መራጮችና የምርጫ ባለሞያዎች ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። /ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

እስራኤል የምስራቅ ሊባኖስ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

በምስራቅ ሊባኖስ ቤካ ሸለቆ አቅራቢያ በሚገኙ የሂዝቦላ ዒላማዎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንደምትወስድ ያስጠነቀቀችው እስራኤል፣ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል የምስራቅ ሊባኖስ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

በምስራቅ ሊባኖስ ቤካ ሸለቆ አቅራቢያ በሚገኙ የሂዝቦላ ዒላማዎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንደምትወስድ ያስጠነቀቀችው እስራኤል፣ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላልፋለች። የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ቃል አቀባይ ባስተላለፉት መልዕክት በአልቤክ፣ አይን ቦርዴይ እና ዶውሪስ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው መውጣት አለባቸው ብለዋል። የእስራኤል ባለሥልጣናት የሚያስተላልፏቸው ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያዎችን ተከትሎ እስራኤል የአየር ድብደባዎችን የምታካሂድ ሲሆን፣ የጥቃቱ ዓላማ ሂዝቦላህን ከእስራኤልና ሊባኖስ ድንበር ለመግፋት መሆኑን ባለስልጣናቱ ይገልጻሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ፣ እስራኤል የፍልስጤም ስደተኞችን የሚደግፈውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለማገድ ባወጣችው አዲስ ሕግ ዙሪያ ስጋታቸውን ገልጸው ለእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ደብዳቤ ጽፈዋል። የደብዳቤውን ይዘት አስመልክተው የመንግስታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ «ሕጉ ተግባራዊ ከሆነ በከበባ ስር በሚገኘው ግዛት የሚኖሩት ፍልስጤማውያን ሰብዓዊ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስ ግልፅ ነው» ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል ማክሰኞ እለት በሰሜናዊ ጋዛ በሚገኝ ባለአምስት ፎቅ የመኖሪያ ህንፃ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 70 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤም የጤና ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ወጣት መራጮች

በአሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሚሳተፉት ወጣቶቹ መራጮች «ጄን ዚ» በሚል መጠሪያ ይታወቃሉ። ከ18 እስከ 27 ባለው የዕድሜ ክልል ገዳማ ውስጥ ይገኛሉ። እንዴ
የአሜሪካ ድምፅ

ወጣት መራጮች

በአሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሚሳተፉት ወጣቶቹ መራጮች «ጄን ዚ» በሚል መጠሪያ ይታወቃሉ። ከ18 እስከ 27 ባለው የዕድሜ ክልል ገዳማ ውስጥ ይገኛሉ። እንዴት መምረጥ እንደሚችሉ ከመማር ጀምሮ ከቤት ቤት እየዞሩ ድጋፍ ማሰባበሰብ ተግባራት ድረስ፣ ብዙዎች የምርጫው የሲቪክ ሂደት አካል እየሆኑ ነው። ላውሬል ቦውማን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በስፔን የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 51 ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ

ትላንት ማክሰኞ ዕለት በደቡብ እና ምስራቅ የስፔን አካባቢዎች የጣለው አውሎ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ባስከተለው ድንገተኛ ጎርፍ የ51 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የስፔ
የአሜሪካ ድምፅ

በስፔን የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 51 ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ

ትላንት ማክሰኞ ዕለት በደቡብ እና ምስራቅ የስፔን አካባቢዎች የጣለው አውሎ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ባስከተለው ድንገተኛ ጎርፍ የ51 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የስፔን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። አውሮፓ ውስጥ በቅርብ ጊዜ ተከስቶ የማያውቅ የከፋ የተፈጥሮ አደጋ መሆኑ የተገለጸው ይህ ጎርፍ መኪናዎችን ጠራርጎ መውሰዱን፣ አውራ ጎዳናዎችን ወደ ወንዝነት መቀየሩን እና የባቡር መሥመሮችን ማስተጓጎሉንም አመልክተዋል። ማላጋ በተሰኘው ከተማ አቅራቢያ 300 ሰዎችን አሳፍሮ በፍጥነት ይጓዝ የነበረ ባቡርም ከመስመር ውጪ የወጣ ሲሆን የተጎዳ ሰው ግን እንደሌለ ባለሥልጣናቱ አመልክተዋል። በፍጥነት የሚጓዘው የጭቃ ቀለም ያለው የጎርፍ ውሃ መኪናዎችን እያላጋ ሲወስድም ታይቷል። ፖሊስ እና የነፍስ አድን አገልግሎት ሠራተኞች ሄሊኮፕተሮችን በመጠቀም ሰዎችን ከቤታቸው እና ከመኪናዎቻቸው ያወጡ ቢሆንም በርካታ ሰዎች እስካሁን የደረሱበት እንደማይታወቅ ባለሥልጣናቱ ማክሰኞ ማታ አስታውቀው ነበር። የስፔን የአደጋ ጊዜ ምላሽ አባል የሆኑ ከ1ሺህ በላይ ወታደሮች በአደጋው ወደተጎዱ አካባቢዎች ተሰማርተው ፍለጋ በቀጠሉበት ወቅት፣ የሟቾቹ ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ ተገልጿል።

Get more results via ClueGoal