ኢራን ሞት የተፈረደበት እስረኛ ከመገደሉ በፊት ሞቶ መገኘቱን አስታወቀች
newsare.net
የሞት ፍርድ የተፈደበት ኢራናዊው-ጀርመናዊው ጃምሺድ ሻርማህድ የሞት ቅጣት ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት አስድሞ ሞቶ መገኘቱን አንድ የኢራን ባለሥልጣን ዛሬ ማክሰኞኢራን ሞት የተፈረደበት እስረኛ ከመገደሉ በፊት ሞቶ መገኘቱን አስታወቀች
የሞት ፍርድ የተፈደበት ኢራናዊው-ጀርመናዊው ጃምሺድ ሻርማህድ የሞት ቅጣት ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት አስድሞ ሞቶ መገኘቱን አንድ የኢራን ባለሥልጣን ዛሬ ማክሰኞ አስታወቁ፡፡ ባለሥልጣኑ አስተያየት የኢራን ባለሥልጣናት ቀደም ሲል እኤአ ጥቅምት 28 የሞት ቅጣቱ የተፈጸመበት መሆኑን ካስታወቁበት መግለጫ ጋር የሚቃረን መሆኑ ተገልጿል፡፡ የፍርድ ቤቱ ባለሥልጣኑ አሽጋር ጃሃንጊር አስተያየት የተሰማው ጀርመን የሞት ፍርዱን በመቃወም በበርሊን የሚገኘውን የኢራን ኢምባሲ ብቻ በመተው ሶስት የኢራን ቆንስላ ጽ/ቤቶችን መዝጋቷን ካስታወቀች በኋላ ነው፡፡ ባለሥልጣኑ “ሻርማህድ ሞት የተረፈደበት ነው ቅጣቱ ተፈጻሚ ሊሆን በዝግጅት ላይ ነበር፡፡ ከዚያ በፊት ግን ሞቶ ተገኘ” ሲሉ መናገራቸውን የፍርድ ቤቱ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡ ዝርዝር አሟሟቱ አልተገለጸም፡፡ ጀርመን የባለስልጣኑን መግለጫ በመቃወም የሻርማህድ ግድያ አስቀድሞ የተፈጸመ መሆኑን በመጥቀስ ኢራንን ተጠያቂ አድርጋለች፡፡ አስክሬኑ ለቤተሰቡ እንዲሰጥ ሲያግባቡ የቆዩት የጀርመን ባለሥልጣናት “የሻርማህድ ሞት በኢራን በኩል አሁን የተረጋገጠ” ሆኗል ብለዋል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ የመኖሪያ ፍቃድ ያለው ሻርማህድ እኤአ በ2023 በኢራን እስላማዊ ህግጋት ውስጥ እንደ ትልቅ ወንጀል ነው በተባለውና የአምላክን ትዕዛዝ መተላለፍ በሚያመልከተው «ምድራዊ ኃጢአት» ክስ የሞት ቅጣት እንደተፈረደበት ተገልጿል፡ የ69 ዓመቱ ሻርማህድ ኢራን ውስጥ የዘውድ ሥርዐት ደጋፊ ቡድንን በመምራት እ.ኤ.አ.በ2008 የ12 ሰዎች ሞትና 100 ሰዎች የቆሰሉበትን አደጋ ባስተከለው የቦምብ ፍንዳታ እና እንዲሁም በሀገሪቱ ውስጥ ሌሎች ጥቃቶችን በማቀድ መከሰሱ ይታወሳል፡፡ Read more