በሰሜን ሸዋ ዞን የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ 48 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ
newsare.net
በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ወጫሌ ወረዳ፣ ልዩ ስሙ ካራ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ፈጸሙት በተባለ ጥበሰሜን ሸዋ ዞን የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ 48 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ
በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ወጫሌ ወረዳ፣ ልዩ ስሙ ካራ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ፈጸሙት በተባለ ጥቃት ፣የወረዳውን አስተዳዳሪ፣ እንደዚሁም የአካባቢውን ሚሊሻዎችና ፖሊሶች ጨምሮ 48 ሰዎች መገደላቸውን የሚገልጽ መረጃ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ የጅማ ቅንጫፍ ኃላፊ አቶ በዳሳ ለሜሳ ተቋማቸው ሁኔታውን እያጣራ መሆኑንም ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል። የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪ የአቶ ንጉሱ ኮሩ ታናሽ ወንድም፣ አቶ ሞስሳ ኮሩ ጥቅምት 22 ቀን 2017ዓ.ም. በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጣቂዎች መካከል ውጊያ እንደነበር ጠቅሰው፣ ወንድማቸው የተገደሉት ተጨማሪ ኃይል ይዘው ወደ አካባቢ እያቀኑ ባሉበት ሰዓት መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አማካሪ መኾናቸውን የተናገሩት፣ አቶ ጅሬኛ ጉደታ ታጣቂዎቻቸው ጥቃት መፈጸማቸውን አረጋግጠዋል። ከሰሜን ሸዋ ዞን፣ ከወጫሌ ወረዳ እና ከክልሉ መንግሥት ባለሥልጣናት ማብራሪያ ለማግኝነት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። Read more