የዩናይትድ ስቴትሱ የምርጫ ጣቢያ የቦምብ ጥቃት ስጋት ምንጭ ሩሲያ ናት ተባለ
newsare.net
በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የሚሰነዘሩ ተከታታይ የቦምብ ጥቃት ዛቻዎች ከሩሲያ እንደሚመጡ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌደራል እና የግዛት ባለስልጣየዩናይትድ ስቴትሱ የምርጫ ጣቢያ የቦምብ ጥቃት ስጋት ምንጭ ሩሲያ ናት ተባለ
በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የሚሰነዘሩ ተከታታይ የቦምብ ጥቃት ዛቻዎች ከሩሲያ እንደሚመጡ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌደራል እና የግዛት ባለስልጣናት አስታወቁ። ማክሰኞ ጠዋት የደረሰው የመጀመሪያው የቦምብ ዛቻ በጆርጂያ ግዛት፣ ደቡብ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኙ አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ለተወሰነ ጊዜ ድምፅ መስጠት እንዲቆም አስገድዷል። የግዛቱ ባለስልጣናት ግን ዛቻው እውነተኛ መሆኑን በማረጋገጣቸው ድምፅ መስጠቱ ቀጥሏል። የጆርጂያ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ብራድ ራፌንስበርገር ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል «ምንጩን ለይተን ከሩሲያ መሆኑን አውቀናል» ብለዋል። ራፌንስበርገር አክለው «የሆነ ተንኮል ለመስራት እየሞከሩ ነው። ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና ትክክለና ምርጫ እንድናደርግ የማይፈልጉ ይመስላል» ያሉ ሲሆን «እርስ በርሳችን እንድንጋጭ የሚያደርጉ ይመስላቸዋል። ያንን እንደድል ሊቆጥሩት ይችላሉ» ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስን ምርጫ ለማደናቀፍ የሚደረገው ጥረት ግን ከዛም የሰፋ ይመስላል። የአሜሪካ ፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) ዛሬ ማክሰኞ ባወጣም መግለጫ «በበርካታ ግዛቶች በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የቦምብ ስጋት መኖሩን እናውቃለን» ያለ ሲሆን አብዛኞቹ ዛቻዎች ከሩሲያ ኢሜይሎች እንደመጡ አመልክቷል። አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣንም፣ ከጆሪጂያ በተጨማሪ በሚቺጋን እና በዊስኮንሰን በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ላይም የቦምብ ጥቃት ዛቻዎች እንደተሰነዘሩ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ኤፍ ቢ አይ በበኩሉ «ሁሉም ዛቻዎች እውነተኛ አለመሆናቸው ተረጋግጧል» ያለ ሲሆን፣ በምርጫዎች ላይ ለሚሰነዘሩ ዛቻዎች ምላሽ ለመስጠት እና አሜሪካኖች የመምረጥ መብታቸውን ሲያረጋግጡ ደህንነታቸውን ለመጠበቅ፣ ከግዛቶች እና የአካባቢ ሕግ አስከባሪዎች ጋር በቅርበት እንደሚሰራም አረጋግጧል። ማክሰኞ ጠዋት አብዛኛው የአሜሪካ መራጭ ድምፁን ሊሰጥ በተዘጋጀበት ወቅት፣ የቢሮውን ተመሳሳይ ስያሜ በመጠቀም ሀሰተኛ ትርክት ለማሰራጨት የተደረጉ ሁለት ሙከራዎች መኖራቸውን ኤፍ ቢ አይ አስጠንቅቆ ነበር። እንደምሳሌም፣ የሽብር ጥቃት ዛቻ እየጨመረ በመምጣቱ አሜሪካውያን በርቀት ድምፅ እንዲሰጡ የሚያበረታታ ሀሰተኛ ዜና መሰራጨቱን ጠቁሟል። በተጨማሪም በአሜሪካ የሚገኙ አምስት እስር ቤቶች በድምፅ ስርቆት ውስጥ ተሳትፈዋል የሚል በቪዲዮ የተቀነባበረ ሀሰተኛ ዜና በማህበራዊ ሚዲያዎች መሰራጨታቸውንም ጠቁሟል። ቪድዮዎቹን ማን እንዳሰራጨ ግን ኤፍ ቢ አይ አልገለጸም። ሆኖም ከዚህ በፊት የድምፅ አሰጣጥ ጉድለቶችን አስመልክቶ በተመሳሳይ ሁኔታ በሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች ሩሲያ እጇ እንዳለበት ቢገለፅም፣ ሩሲያ ክሱን አትቀበለውም። Read more