Ethiopia



ትራምፕ እስካሁን 18 ግዛቶችን ሲያሸንፉ፣ ሃሪስ ዘጠኝ ግዛቶችን ማሸነፋቸውን አረጋግጠዋል

ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የተካሄደው እ.አ.አ የ2024 ሀገር አቀፍ ምርጫ ውጤት በተለያዩ ግዛቶች መታወቅ ጀምሯል። እስካሁን ባለው ውጤት የሪፐብሊካኑ ፕሬዝዳንታዊ እ

በአሜሪካ የምርጫ ጣቢያዎች በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ይዘጋሉ

በኢንዲያና እና ኬንተኪ የሚገኙ የተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች በምሥራቅ የሃገሪቱ አቆጣጠር ከምሽቱ 6 ሰዓት ቀድመው ከተዘጉት ውስጥ ሲሆኑ፤ የተቀሩት ደግሞ ከምሽ
የአሜሪካ ድምፅ

በአሜሪካ የምርጫ ጣቢያዎች በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ይዘጋሉ

በኢንዲያና እና ኬንተኪ የሚገኙ የተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች በምሥራቅ የሃገሪቱ አቆጣጠር ከምሽቱ 6 ሰዓት ቀድመው ከተዘጉት ውስጥ ሲሆኑ፤ የተቀሩት ደግሞ ከምሽቱ 7 ሰዓት ተዘግተዋል። 25 የሚሆኑ ግዛቶች ደግሞ ከምሽቱ 8 ሰዓት እንደሚዘጉ ይጠበቃል። በአላስካ ግዛት የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ ከእኩለ ሌሊት በኋላ 1 ሰዓት ላይ ይዘጋሉ። በበርካታዎቹ ግዛቶች የምርጫውን ውጤት ለማወቅ ሰዓታት፣ ምናልባትም ቀናት ሊወስድ ይችላል። ሃሰተኛ የቦምብ ጥቃት ዛቻዎች በሚሺጋን፣ ውስከንስን፣ እና ጆርጂያ መሰማታቸውን የፌዴራል ምርመራ ቢሮ ያስታወቀ ሲሆን፣ የአብዛኛዎቹ ዛቻዎች መነሻ ከሩሲያ የተላኩ ኢሜይሎች መሆናቸውንም ቢሮው ገልጿል። በጆርጂያ የሚገኙ ቢያንስ ሁለት ጣቢያዎች ዛቻውን ተከትሎ ሰዎች ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል። የግዛቲቱ ዋና ፀሃፊ ሩሲያ ጣልቃ ገብታለች ሲሉ ከሰዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ምርጫዋን ከጣልቃ ገብ ጥቃት የተጠበቀ  ለማድረግ ተዘጋጅታለች

በደቡብ ምሥራቅ አሜሪካ በሕዝብ ስብጥራቸው ከሚታወቁት አውራጃዎች መካከል አንዷ የሆነችውና በጆርጂያ የምትገኘው ጉወኔት አውራጃ፣ በአሜሪካ ምርጫ ምሽት ውጤ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩናይትድ ስቴትስ ምርጫዋን ከጣልቃ ገብ ጥቃት የተጠበቀ  ለማድረግ ተዘጋጅታለች

በደቡብ ምሥራቅ አሜሪካ በሕዝብ ስብጥራቸው ከሚታወቁት አውራጃዎች መካከል አንዷ የሆነችውና በጆርጂያ የምትገኘው ጉወኔት አውራጃ፣ በአሜሪካ ምርጫ ምሽት ውጤታቸውን ቀድመው ከሚልኩት አውራጃዎች አንዷ ነች፡፡ የቪኦኤ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ዋና ዘጋቢ ስቲቭ ኽረማን ወደ ሎውረንስ፣ ጆርጂያ ተጉዙና የድምጽ ቆጠራ ሂደቱን ታዝቦ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የዩናይትድ ስቴትሱ የምርጫ ጣቢያ የቦምብ ጥቃት ስጋት ምንጭ ሩሲያ ናት ተባለ

በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የሚሰነዘሩ ተከታታይ የቦምብ ጥቃት ዛቻዎች ከሩሲያ እንደሚመጡ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌደራል እና የግዛት ባለስልጣ
የአሜሪካ ድምፅ

የዩናይትድ ስቴትሱ የምርጫ ጣቢያ የቦምብ ጥቃት ስጋት ምንጭ ሩሲያ ናት ተባለ

በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የሚሰነዘሩ ተከታታይ የቦምብ ጥቃት ዛቻዎች ከሩሲያ እንደሚመጡ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌደራል እና የግዛት ባለስልጣናት አስታወቁ። ማክሰኞ ጠዋት የደረሰው የመጀመሪያው የቦምብ ዛቻ በጆርጂያ ግዛት፣ ደቡብ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኙ አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ለተወሰነ ጊዜ ድምፅ መስጠት እንዲቆም አስገድዷል። የግዛቱ ባለስልጣናት ግን ዛቻው እውነተኛ መሆኑን በማረጋገጣቸው ድምፅ መስጠቱ ቀጥሏል። የጆርጂያ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ብራድ ራፌንስበርገር ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል «ምንጩን ለይተን ከሩሲያ መሆኑን አውቀናል» ብለዋል። ራፌንስበርገር አክለው «የሆነ ተንኮል ለመስራት እየሞከሩ ነው። ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና ትክክለና ምርጫ እንድናደርግ የማይፈልጉ ይመስላል» ያሉ ሲሆን «እርስ በርሳችን እንድንጋጭ የሚያደርጉ ይመስላቸዋል። ያንን እንደድል ሊቆጥሩት ይችላሉ» ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስን ምርጫ ለማደናቀፍ የሚደረገው ጥረት ግን ከዛም የሰፋ ይመስላል። የአሜሪካ ፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) ዛሬ ማክሰኞ ባወጣም መግለጫ «በበርካታ ግዛቶች በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የቦምብ ስጋት መኖሩን እናውቃለን» ያለ ሲሆን አብዛኞቹ ዛቻዎች ከሩሲያ ኢሜይሎች እንደመጡ አመልክቷል። አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣንም፣ ከጆሪጂያ በተጨማሪ በሚቺጋን እና በዊስኮንሰን በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ላይም የቦምብ ጥቃት ዛቻዎች እንደተሰነዘሩ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።  ኤፍ ቢ አይ በበኩሉ «ሁሉም ዛቻዎች እውነተኛ አለመሆናቸው ተረጋግጧል» ያለ ሲሆን፣ በምርጫዎች ላይ ለሚሰነዘሩ ዛቻዎች ምላሽ ለመስጠት እና አሜሪካኖች የመምረጥ መብታቸውን ሲያረጋግጡ ደህንነታቸውን ለመጠበቅ፣ ከግዛቶች እና የአካባቢ ሕግ አስከባሪዎች ጋር በቅርበት እንደሚሰራም አረጋግጧል። ማክሰኞ ጠዋት አብዛኛው የአሜሪካ መራጭ ድምፁን ሊሰጥ በተዘጋጀበት ወቅት፣ የቢሮውን ተመሳሳይ ስያሜ በመጠቀም ሀሰተኛ ትርክት ለማሰራጨት የተደረጉ ሁለት ሙከራዎች መኖራቸውን ኤፍ ቢ አይ አስጠንቅቆ ነበር። እንደምሳሌም፣ የሽብር ጥቃት ዛቻ እየጨመረ በመምጣቱ አሜሪካውያን በርቀት ድምፅ እንዲሰጡ የሚያበረታታ ሀሰተኛ ዜና መሰራጨቱን ጠቁሟል። በተጨማሪም በአሜሪካ የሚገኙ አምስት እስር ቤቶች በድምፅ ስርቆት ውስጥ ተሳትፈዋል የሚል በቪዲዮ የተቀነባበረ  ሀሰተኛ ዜና በማህበራዊ ሚዲያዎች መሰራጨታቸውንም ጠቁሟል።  ቪድዮዎቹን ማን እንዳሰራጨ ግን ኤፍ ቢ አይ አልገለጸም። ሆኖም ከዚህ በፊት የድምፅ አሰጣጥ ጉድለቶችን አስመልክቶ በተመሳሳይ ሁኔታ በሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች ሩሲያ እጇ እንዳለበት ቢገለፅም፣ ሩሲያ ክሱን አትቀበለውም።

አሜሪካ ምርጫ ላይ ነች - የመራጮች አስተያየት

በሚልየን የሚቆጠሩ የአሜሪካ መራጮች፣” ቀጣይ የአሜሪካ መሪ የሚሆኑት ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ወይም የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ?” የሚለውን  
የአሜሪካ ድምፅ

አሜሪካ ምርጫ ላይ ነች - የመራጮች አስተያየት

በሚልየን የሚቆጠሩ የአሜሪካ መራጮች፣” ቀጣይ የአሜሪካ መሪ የሚሆኑት ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ወይም የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ?” የሚለውን  ለመወሰን ዛሬ ማክሰኞ ድምፅ በመስጠት ላይ ናቸው። የተወሰኑትን አስተያየት ጠይቀናል ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በሰሜን ሸዋ የመስጅድ ኢማም ታግተዉ መገደላቸው ተነገረ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከሳምንታት በፊት በታጣቂዎች ታግተው ነበር የተባሉ የኃይማኖት አባት መገደላቸው ተነገረ። በሰሜን ሸዋ ዞ
የአሜሪካ ድምፅ

በሰሜን ሸዋ የመስጅድ ኢማም ታግተዉ መገደላቸው ተነገረ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከሳምንታት በፊት በታጣቂዎች ታግተው ነበር የተባሉ የኃይማኖት አባት መገደላቸው ተነገረ። በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ አረቦ መስጅድ ኢማም ኾነው ሲያገለግሉ ነበሩ የተባሉት ሼክ መከዬ ሰይድ ለሳምንታት ታግተዉ ከተወሰዱ በኋላ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ አስከሬናቸው መምጣቱንና ሥርዓተ ቀብራቸው መፈፀሙ ተነግሯል። የደራ ወረዳ አስተዳደር ድርጊቱ መፈፀሙን አረጋግጧል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንም ስለግድያዉ መረጃ እንደደረሰዉ አስታውቋል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች አማካሪ መኾናቸውን የተናገሩት ጅሬኛ ጉደታ፣ ታጣቂዎቻቸው ጥቃቱን እንዳልፈጸሙ ተናግረዋል።

በሰሜን ሸዋ ዞን የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ 48 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ

በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ወጫሌ ወረዳ፣ ልዩ ስሙ ካራ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ፈጸሙት በተባለ ጥ
የአሜሪካ ድምፅ

በሰሜን ሸዋ ዞን የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ 48 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ

በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ወጫሌ ወረዳ፣ ልዩ ስሙ ካራ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ፈጸሙት በተባለ ጥቃት ፣የወረዳውን አስተዳዳሪ፣ እንደዚሁም የአካባቢውን ሚሊሻዎችና ፖሊሶች ጨምሮ 48 ሰዎች መገደላቸውን የሚገልጽ መረጃ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ የጅማ ቅንጫፍ ኃላፊ አቶ በዳሳ ለሜሳ ተቋማቸው ሁኔታውን እያጣራ መሆኑንም ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል። የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪ የአቶ ንጉሱ ኮሩ ታናሽ ወንድም፣ አቶ ሞስሳ ኮሩ ጥቅምት 22 ቀን 2017ዓ.ም. በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጣቂዎች መካከል ውጊያ እንደነበር ጠቅሰው፣ ወንድማቸው የተገደሉት ተጨማሪ ኃይል ይዘው ወደ አካባቢ እያቀኑ ባሉበት ሰዓት መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አማካሪ መኾናቸውን የተናገሩት፣ አቶ ጅሬኛ ጉደታ ታጣቂዎቻቸው ጥቃት መፈጸማቸውን አረጋግጠዋል። ከሰሜን ሸዋ ዞን፣ ከወጫሌ ወረዳ እና ከክልሉ መንግሥት ባለሥልጣናት ማብራሪያ ለማግኝነት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

VOA60 America - America votes for next president

Millions of U.S. voters cast ballots Tuesday as they decide if Vice President Kamala Harris or former president Donald Trump will be the country’s next leader. Ahead of Election Day more than 81 million Americans cast early ballots, either in person at poll
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - America votes for next president

Millions of U.S. voters cast ballots Tuesday as they decide if Vice President Kamala Harris or former president Donald Trump will be the country’s next leader. Ahead of Election Day more than 81 million Americans cast early ballots, either in person at polling stations or by mail.

VOA60 Africa - Sudan: UN says some 135,000 people displaced in 10 days from Al Jazirah state

The United Nations said this week that some 135,000 people were displaced in just 10 days from the Al Jazirah state in a series of revenge attacks by the paramilitary Rapid Support Forces, with activists reporting violent raids over the past two weeks affecti
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Sudan: UN says some 135,000 people displaced in 10 days from Al Jazirah state

The United Nations said this week that some 135,000 people were displaced in just 10 days from the Al Jazirah state in a series of revenge attacks by the paramilitary Rapid Support Forces, with activists reporting violent raids over the past two weeks affecting at least 65 villages and towns.

VOA60 World - America chooses between former president Donald Trump, Vice President Kamala Harris

Both candidates projected confidence in their own campaigns. Survey polls heading into Election Day indicated a tight race.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - America chooses between former president Donald Trump, Vice President Kamala Harris

Both candidates projected confidence in their own campaigns. Survey polls heading into Election Day indicated a tight race.

ከ50 በላይ ሀገራት ለእስራኤል የመሣሪያ ሽያጭና አቅርቦትን እንዲያስቆም ተመድን ጠየቁ

በሲቪሎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት እና የአከባቢው አለመረጋጋት አሳሳቢ ነው ያሉ ከ50 በላይ ሀገራት ለእስራኤል የሚደረገው የጦር መሣሪያ ሽያጭ በአስቸኳይ እንዲቆ
የአሜሪካ ድምፅ

ከ50 በላይ ሀገራት ለእስራኤል የመሣሪያ ሽያጭና አቅርቦትን እንዲያስቆም ተመድን ጠየቁ

በሲቪሎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት እና የአከባቢው አለመረጋጋት አሳሳቢ ነው ያሉ ከ50 በላይ ሀገራት ለእስራኤል የሚደረገው የጦር መሣሪያ ሽያጭ በአስቸኳይ እንዲቆም ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደብዳቤ ልከዋል፡፡ በቱርክ አስተባባሪነት ለሁለት የተባበሩ መንግሥታት ድርጅት አካላት እና ለድርጅቱ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ የተላከውና ትላንት ሰኞ ማምሻው ላይ አሶሴይት ፕሬስ እጅ የገባው የሀገራቱ ደብዳቤ፣ “በጋዛ እና በሌሎች የፍልስጤም ግዛቶች እንዲሁም በሊባኖስ እና በቀሪው የመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ያለው ዓለም አቀፍ ህጉን የጣሰ ነው” ሲል እስራኤልን ከሷል፡፡ ሀገራቱ በደብዳቤያቸው " ዓለም አቀፍ ህግን በመጣስ እስራኤል እየፈፀመች ባለችው ድርጊት ሳቢያ ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረው አብዛኞቹ ህጻናት እና ሴቶች የሆኑበት አስደንጋጭ የሰላማዊ ሰዎች እልቂት፣ ህሊና የማይቀበለውና የማይታለፍ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ በአካባቢ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ከመጠን ያለፈ ሰብአዊ ስቃይ እና ክልላዊ አለመረጋጋት ለማስቆም አፋጣኝ ርምጃ መውሰድ አለብን” ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ “የተባበሩት መንግሥታት ይህንን ቀውስ ለማስቆም፣ አስቸኳይ የተኩስ ማቆም ማወጅና፣ የሰላማዊ ሰዎችን ህይወት የሚታደግ ርምጃዎችን መውሰድ፣ ተጠያቂነት ማረጋገጥና ለእስራኤል የሚተላለፈው መሣሪያ እንዲቆም ግልጽ ጥያቄ ማቅረብ አለበት ሲል” የሀገራቱ ደብዳቤ ጠይቋል፡፡ በተባበሩት መንግስታት የእስራኤል አምባሳደር ዳኒ ዳኖን የቱርክን ተሳትፎ ውድቅ በማድረግ “በጥፋት ኃይሎች ድጋፍ ግጭትን ለመቀስቀስ ሙከራ ከምታደርግ ሀገር ምን ልንጠብቅ እንችላለን” ብለዋል፡፡ “የእስራኤል ጥቅሞች ከየትኛው ፖለቲካዊ እና ወታደዊ ጥቃት ለመከላከል መታገላችንን እንቀጥላለን “ሲሉም አምባሳደሩ ሀገራቸው ራሷን ለመከላከል ያላትን አቋም ገልጸዋል። ደብዳቤውን ከፈረሙት መካከል የአረብ ሊግ ፣ የእስላማዊ ኮርፖሬሽን፣ ኖርዌ እና ደቡብ አፍሪካ ይገኙበታል፡፡ ደቡብ አፍሪካ በፍልስጤማውያን ላይ የዘር ማጥፋት ተፈጽሟል ስትል እስራኤልን በመክሰስ ጉዳዩን ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ፊት ማቅረቧ ይታወሳል፡፡ በጋዛ የእስራኤል ሀማስ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ከ43ሺ በላይ ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጤም የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ሴቶችና ህጻናት መሆናቸውን ባለሥልጣናቱ ገልጸዋል፡፡ ጦርነቱ የተጀመረው እኤአ ጥቅምት 7 2023 ወደ እስራኤል ዘልቀው የገቡ የሃማስ ታጣቂዎች አብዛኞቹ ሰላማዊ የሆኑ 1ሺ200 ሰዎችን ከገደሉና 250 የሚሆኑትን አግተው ከወሰዱ በኋላ ነው፡፡

ኢራን ሞት የተፈረደበት እስረኛ ከመገደሉ በፊት ሞቶ መገኘቱን አስታወቀች

የሞት ፍርድ የተፈደበት ኢራናዊው-ጀርመናዊው ጃምሺድ ሻርማህድ የሞት ቅጣት ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት አስድሞ ሞቶ መገኘቱን አንድ የኢራን ባለሥልጣን ዛሬ ማክሰኞ
የአሜሪካ ድምፅ

ኢራን ሞት የተፈረደበት እስረኛ ከመገደሉ በፊት ሞቶ መገኘቱን አስታወቀች

የሞት ፍርድ የተፈደበት ኢራናዊው-ጀርመናዊው ጃምሺድ ሻርማህድ የሞት ቅጣት ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት አስድሞ ሞቶ መገኘቱን አንድ የኢራን ባለሥልጣን ዛሬ ማክሰኞ አስታወቁ፡፡ ባለሥልጣኑ አስተያየት የኢራን ባለሥልጣናት ቀደም ሲል እኤአ ጥቅምት 28 የሞት ቅጣቱ የተፈጸመበት መሆኑን ካስታወቁበት መግለጫ ጋር የሚቃረን መሆኑ ተገልጿል፡፡ የፍርድ ቤቱ ባለሥልጣኑ አሽጋር ጃሃንጊር አስተያየት የተሰማው ጀርመን የሞት ፍርዱን በመቃወም በበርሊን የሚገኘውን የኢራን ኢምባሲ ብቻ በመተው ሶስት የኢራን ቆንስላ ጽ/ቤቶችን መዝጋቷን ካስታወቀች በኋላ ነው፡፡ ባለሥልጣኑ “ሻርማህድ ሞት የተረፈደበት ነው ቅጣቱ ተፈጻሚ ሊሆን በዝግጅት ላይ ነበር፡፡ ከዚያ በፊት ግን ሞቶ ተገኘ” ሲሉ መናገራቸውን የፍርድ ቤቱ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡ ዝርዝር አሟሟቱ አልተገለጸም፡፡ ጀርመን የባለስልጣኑን መግለጫ በመቃወም የሻርማህድ ግድያ አስቀድሞ የተፈጸመ መሆኑን በመጥቀስ ኢራንን ተጠያቂ አድርጋለች፡፡ አስክሬኑ ለቤተሰቡ እንዲሰጥ ሲያግባቡ የቆዩት የጀርመን ባለሥልጣናት “የሻርማህድ ሞት በኢራን በኩል አሁን የተረጋገጠ” ሆኗል ብለዋል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ የመኖሪያ ፍቃድ ያለው ሻርማህድ እኤአ በ2023 በኢራን እስላማዊ ህግጋት ውስጥ እንደ ትልቅ ወንጀል ነው በተባለውና የአምላክን ትዕዛዝ መተላለፍ በሚያመልከተው «ምድራዊ ኃጢአት» ክስ የሞት ቅጣት እንደተፈረደበት ተገልጿል፡ የ69 ዓመቱ ሻርማህድ ኢራን ውስጥ የዘውድ ሥርዐት ደጋፊ ቡድንን በመምራት እ.ኤ.አ.በ2008 የ12 ሰዎች ሞትና 100 ሰዎች የቆሰሉበትን አደጋ ባስተከለው የቦምብ ፍንዳታ እና እንዲሁም በሀገሪቱ ውስጥ ሌሎች ጥቃቶችን በማቀድ መከሰሱ ይታወሳል፡፡

በረሃብ ላይ የሚያተኩር ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው

ዘመናዊ የግብርና ዘዴ እና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን መግታት ረሃብን ለማጥፋት ቁልፍ እንደሆኑ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ። ጠ
የአሜሪካ ድምፅ

በረሃብ ላይ የሚያተኩር ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው

ዘመናዊ የግብርና ዘዴ እና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን መግታት ረሃብን ለማጥፋት ቁልፍ እንደሆኑ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ምኒስትሩ አዲስ አበባ ለሶስት ቀናት በሚቆየው “ከረሃብ ነጻ ዓለም” በተሰኘ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በዓለም የሚታየውን የምግብ ችግር ለመቅረፍ ፈጠራ የታከለበት መፍትሄ እንደሚያሻም ጠቁመዋል። “ዘላቂነት ያለው አሰራር፣ የተሻሻለ ዘመናዊ የእርሻ ዘዴ፣ የግርብና ግብአት አቅርቦት ማስፋፋት እና የአየር ንብረት ለውጥ ችግርን መቅረፍ ለምርታማነት መሻሻል አስፈላጊ ናቸው” ሲሉ ጠቅላይ ምኒስትሩ በ'X' ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መልዕክታቸውን አስፍረዋል። የዓለም መሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ እና ተሟጋቾች ፈጠራ የታከለበት መፍትሄ ላይ ውይይት እንዲያደርጉና በአንድነት እንዲሰሩ በማድረግ ረሃብን ለማጥፋትና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ፍሬ እንዲያፈራ ማድረግ ይቻላል ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ከተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት እና ከአፍሪክ ኅብረት ኮሚሽን ጋራ በመተባበር ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ 1ሺሕ 500 የሚሆኑ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ ከተባበሩት መንግስታት የተገኘው መረጃ አመልክቷል።

በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ለምን በማክሰኞ ቀን ይካሄዳል?

ለመሆኑ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ  ሁሌም ለምን በማክሰኞ ቀን እንደሚደረግ አስበው ያውቃሉ? ይህ ፖለቲካዊ ባህል ዩናይትድ ስቴትስ አሁን ካላት ገጽ
የአሜሪካ ድምፅ

በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ለምን በማክሰኞ ቀን ይካሄዳል?

ለመሆኑ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ  ሁሌም ለምን በማክሰኞ ቀን እንደሚደረግ አስበው ያውቃሉ? ይህ ፖለቲካዊ ባህል ዩናይትድ ስቴትስ አሁን ካላት ገጽታ በተለየ መልኩ በነበረችበት ከሁለት መቶ ዓመት በፊት የጀመረ ነው፡፡ ተከታዩ ዘገባ መልሱን ይዟል፡፡

ጉወኔት አውራጃ ለምን የአሜሪካን ምርጫ ውጤት ከሚወስኑት ሥፍራዎች አንዷ ሆነች?

በደቡብ ምሥራቅ አሜሪካ በሕዝብ ስብጥራቸው ከሚታወቁት አውራጃዎች መካከል አንዷ የሆነችውና በጆርጂያ የምትገኘው ጉወኔት አውራጃ፣ በአሜሪካ ምርጫ ምሽት ውጤ
የአሜሪካ ድምፅ

ጉወኔት አውራጃ ለምን የአሜሪካን ምርጫ ውጤት ከሚወስኑት ሥፍራዎች አንዷ ሆነች?

በደቡብ ምሥራቅ አሜሪካ በሕዝብ ስብጥራቸው ከሚታወቁት አውራጃዎች መካከል አንዷ የሆነችውና በጆርጂያ የምትገኘው ጉወኔት አውራጃ፣ በአሜሪካ ምርጫ ምሽት ውጤታቸውን ቀድመው ከሚልኩት አውራጃዎች አንዷ ነች፡፡ የቪኦኤ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ዋና ዘጋቢ ስቲቭ ኽረማን ወደ ሎውረንስ፣ ጆርጂያ ተጉዙና የድምጽ ቆጠራ ሂደቱን ታዝቦ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

ከውጭ ሀገር ቤተሰቦች የተወለዱትና በፕሬዝደንታዊ እጩነት ታሪክ የሠሩት ካምላ ሃሪስ

እጅግ  "የለውጥ አቀንቃኝ ወይም ሊበራል ከሆነ እና ሰፊ  የሕዝብ ስብጥር ካለው የካሊፎርኒያ አካባቢ የተነሱት ካምላ ሃሪስ በብርቱ የሕግ አስከባሪነት እና ተራማ
የአሜሪካ ድምፅ

ከውጭ ሀገር ቤተሰቦች የተወለዱትና በፕሬዝደንታዊ እጩነት ታሪክ የሠሩት ካምላ ሃሪስ

እጅግ  "የለውጥ አቀንቃኝ ወይም ሊበራል ከሆነ እና ሰፊ  የሕዝብ ስብጥር ካለው የካሊፎርኒያ አካባቢ የተነሱት ካምላ ሃሪስ በብርቱ የሕግ አስከባሪነት እና ተራማጅ የለውጥ አቀንቃኝነት አልፈው  ለዲሞክራቲክ ፓርቲው ፕሬዚደንታዊ እጩነት በቅተዋል፡፡ የቪኦኤው ማት ዲብል ከካሊፎርኒያ ኦክላንድ ከተማ የምክትል ፕሬዚደንት ሃሪስን የፖለቲካ ጉዞዎች ያስቃኘበትን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ዶናልድ ትረምፕ ወደ ፕሬዝደንትነት የተጓዙበት ያልተለመደ መንገድ

የቀድሞው፣ ምናልባትም መጪው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ክፍፍሉ እየጨመረ ባለበት ሃገር ውስጥ፣ የሪፐብሊካን ፓርቲውን ቅርጽ ለመቀየር የፈጀባቸ
የአሜሪካ ድምፅ

ዶናልድ ትረምፕ ወደ ፕሬዝደንትነት የተጓዙበት ያልተለመደ መንገድ

የቀድሞው፣ ምናልባትም መጪው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ክፍፍሉ እየጨመረ ባለበት ሃገር ውስጥ፣ የሪፐብሊካን ፓርቲውን ቅርጽ ለመቀየር የፈጀባቸው ከዘጠኝ ዓመት ያህል ነው። ትረምፕ ወደ ፖለቲካ ሥልጣን ለመመለስ የሚያደርጉትን ታሪካዊ ሂደት የቪኦኤዋ ቲና ትሪን ተመልክታዋለች፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

ቲም ዋልዝ ማናቸው?

'የነብራስካው መልካም ሰው' የገጠሪቱን አሜሪካ ድምጽ ያገኙ ይሆን? ቲም ዋልዝ ከካመላ ሄሪስ ጎን ሆነው ለምክትል ፕሬዝደንትነት እንዲወዳደሩ ከመታጨታቸው በፊ
የአሜሪካ ድምፅ

ቲም ዋልዝ ማናቸው?

'የነብራስካው መልካም ሰው' የገጠሪቱን አሜሪካ ድምጽ ያገኙ ይሆን? ቲም ዋልዝ ከካመላ ሄሪስ ጎን ሆነው ለምክትል ፕሬዝደንትነት እንዲወዳደሩ ከመታጨታቸው በፊት፣ ለሚንሶታ አገረ ገዢነት ሁለት ጊዜ ተመርጠዋል። በምርጫ ዘመቻ ጉዟቸው ላይ፤ በነብራስካ ማደጋቸው፣ እንዴት ስብእናቸውን እንደቀረጸውና፣ አሁን ለታጩበት ሥራም ሆነ ለሃገረ ገዢነት ሃላፊነት ለመብቃት እንዴት እንደረዳቸው ይናገራሉ። የነብራስካ ሰዎች ስለ ቲም ዋልዝ ምን እንደሚያስታውሱ እንዲሁም አሁን ስለ እርሳቸው ምን እንደሚሰማቸው ለማወቅ የቪኦኤዋ ናታሻ ሞዝጎቫያ ግዛቲቱን ጎብኝታ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የሪፐብሊካኑ እጩ ምክትል ፕሬዘዳንት ተወዳዳሪ ጄዲ ቫንስ ማናቸው?

የሪፐብሊካኑ እጩ ምክትል ፕሬዘዳንት ተወዳዳሪ ጄዲ ቫንስ የሕይወት ታሪክ “የአንድ የትንሽ ከተማ ብላቴና መልካም ሲገጥመው” የሚለውን ሀረግ ሊጠቃለል ይችላል
የአሜሪካ ድምፅ

የሪፐብሊካኑ እጩ ምክትል ፕሬዘዳንት ተወዳዳሪ ጄዲ ቫንስ ማናቸው?

የሪፐብሊካኑ እጩ ምክትል ፕሬዘዳንት ተወዳዳሪ ጄዲ ቫንስ የሕይወት ታሪክ “የአንድ የትንሽ ከተማ ብላቴና መልካም ሲገጥመው” የሚለውን ሀረግ ሊጠቃለል ይችላል፡፡ ጄዲ በተራራማው አፓላችን ነው ያደጉት፤ በኋላም አይቪ ሊግ ተብለው ከሚታወቁት ልዩ የሆነ ክብር ካላቸው ዩኒቨርስቲዎች መካከል በዬል ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ በዬል የህግ ትምህርት ቤት ቆይታቸውም ከአሁኗ ባለቤታቸው ኡሻ ቺሉኩሪ ጋር ሊተዋወቁ ችለዋል፡፡ ጄዲ ቫንስ ውልደታቸው በሚድል ታውን ኦሃዮ ቢሆንም፤  ነገር ግን ቤቴ ብለው የሚጠሩት ጃክሰን ኬንተኪን ነው፡፡ በልጅነት ህይወታቸው ብሎም በአስተሳሰባቸው ላይ ሚማው ብለው የሚጠሯቸው ሴት አያታቸው ትልቅ ሚና አላቸው፡፡ የጄዲ ቫንስ የመጀመሪያ እውቅና የመነጨው በጎርጎሮሳዊያኑ 2016 በታተመው የአሜሪካ የሰራተኛውን መደብ ሕይወት በሚያስቃኘው ‘ሂልቢሊ ኤልጊ’ ብለው በጻፉት እና በኋላም ወደ ፊልምነት በተቀየረው መጽሓፋቸው ነው፡፡ በፖለቲካ ርዕዮተ ዓለማቸው  ቀድሞ ትራምፕን ያወግዙ የነበሩት ጄዲ ቫንስ አሁን ላይ የትግል አጋራቸው በመሆን የጎሮጎርሳዊያኑ 2024 ምርጫን ለማሸነፍ እየሰሩ ነው፡፡ መጭው የአውሮፓውያኑ ኅዳር አምስት በሚድረገው ምርጫ ካሸነፉም በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ወጣት ከሆኑ ምክትል ፕሬዘዳንቶች መካከል አንዱ በመሆን በታሪክ ሊመዘገቡ ይችላሉ፡፡  የአሜሪካ ድምጿ ከፍተኛ ዘጋቢ ኬሮላይን ፔርሱቲን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የአሜሪካ መራጮች «ከፍ ያለ እና ተለዋዋጭ» የደህንነት ሥጋቶች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል

ነገ ማክሰኞ በዩናይትድ ስቴትስ የሚካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በሀገሪቱ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማያውቅ እንደሚሆን ተነግሮለታል፡፡ የሀገሪቱ የጸጥታ እና የደህ
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ መራጮች «ከፍ ያለ እና ተለዋዋጭ» የደህንነት ሥጋቶች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል

ነገ ማክሰኞ በዩናይትድ ስቴትስ የሚካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በሀገሪቱ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማያውቅ እንደሚሆን ተነግሮለታል፡፡ የሀገሪቱ የጸጥታ እና የደህንነት ባለስልጣናትም መራጮች ድምጻቸውን የሚሰጡት ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጪ የተቀኑ አደጋዎች እጅግ ከፍተኛ እና ተለዋዋጭ የሆነ የስጋት ድባብ በፈጠሩበት ሁኔታ እንደሆነ ይናገራሉ። የብሔራዊ ጸጥታ ጉዳዮች ዘጋቢ ጄፍ ሴልድን ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የስደተኞች ጉዳይ ለትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካዊ መራጮች ቁልፍ ጉዳይ ነው

ከሁለት ቀናት በኃላ በዩናይትድ ስቴትስ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መራጮች ትኩረት ከሚሰጡባቸው ቁልፍ ፖሊሲዎች አንዱ የስደተኞች ጉዳይ ነው። የአሜሪካ ድ
የአሜሪካ ድምፅ

የስደተኞች ጉዳይ ለትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካዊ መራጮች ቁልፍ ጉዳይ ነው

ከሁለት ቀናት በኃላ በዩናይትድ ስቴትስ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መራጮች ትኩረት ከሚሰጡባቸው ቁልፍ ፖሊሲዎች አንዱ የስደተኞች ጉዳይ ነው። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊዎች ወደ አሜሪካ የሚገቡ ሕገወጥ ስደተኞች ቁጥር የሚያሳስባቸው ሲሆን፣ የዲሞክራት ፓርቲ ደጋፊዎች ደግሞ ስደተኞች ሕጋዊ በሆነ መንገድ የሚኖሩበት መንገድ እንዲመቻች ይፈልጋሉ።  (ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ዘገባ ያገኛሉ)

ቆይታ ከኤፓክ ተወካይ ጋራ - በዩ ኤስ ምርጫ ኢትዮጵያ - አሜሪካውያን ድምጽ

«የተለያዩ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ማኅበረሰብ አባላት ለዘንድሮው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለውሳኔያቸው ምን ዓይነት ጉዳዮችን መሰረት ያደር
የአሜሪካ ድምፅ

ቆይታ ከኤፓክ ተወካይ ጋራ - በዩ ኤስ ምርጫ ኢትዮጵያ - አሜሪካውያን ድምጽ

«የተለያዩ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ማኅበረሰብ አባላት ለዘንድሮው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለውሳኔያቸው ምን ዓይነት ጉዳዮችን መሰረት ያደርጉ ይሆን?» ችችችችበሚል ላነሳነው ጥያቄ፣ ማብራሪያ እንዲሰጡን የአሜሪካ-ኢትዮጵያውያን የሕዝብ ጉዳዮች ኮሚቴ (ኤፓክ) ዋና ጸሐፊ አቶ ዮም ፍሰሃን ጋብዘናል። ከተቋቋመ ሦስት ዓመት ተኩል የሆነው ኤፓክ፣ ሁለቱ ዕጩዎች በየበኩላቸው ከላኳቸው አራት የምርጫ ዘመቻ ተወካዮች ጋራ አባሎቻቸው ውይይት እንዲያደርጉ በቅርቡ መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። አቶ ዮም ማኅበራቸው ስላሰናዳው ስለዚህ መድረክም አስረድተውናል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ከነብዩ መሃመድ የካርቱን ስዕል ጋር የተያያዘው የሽብር ጥቃት ወንጀል ጉዳይ መታየት ጀመረ

ፈረንሳይ ውስጥ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎቹን ስለ ንግግር ነፃነት በሚያስተምርበት ወቅት የነቢዩ መሃመድን የካርቱን ምስል ካሳየ በኋላ በአንድ እስላማዊ ጽንፈኛ
የአሜሪካ ድምፅ

ከነብዩ መሃመድ የካርቱን ስዕል ጋር የተያያዘው የሽብር ጥቃት ወንጀል ጉዳይ መታየት ጀመረ

ፈረንሳይ ውስጥ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎቹን ስለ ንግግር ነፃነት በሚያስተምርበት ወቅት የነቢዩ መሃመድን የካርቱን ምስል ካሳየ በኋላ በአንድ እስላማዊ ጽንፈኛ በስለት ተቀልቶ በተገደለው መምሕር ሳሙኤ ፓቲ ላይ በተፈጸመው ወንጀል ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ ስምንት ሰዎች ጉዳይ መታየት ጀመረ። የዛሬውም የችሎት ውሎ በርካታ ፖሊሶች በተሰማሩበት ጥብቅ ፍተሻ እና ቁጥጥር መከናወኑ ተዘግቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ ከሚገኙት ተጠርጣሪዎች መካከል አምስቱ ከሰፊ የመስታወት ሳጥን ውስጥ እንዲቀመጡ ሲደረግ፤ የተቀሩት ሶስቱ እግሞ ተከሳሾቹ ከሚቀመጡበት ሥፍራ በቁጥጥር ስር ሆነው ቀርበዋል። ከተከሳሾቹ አራቱ የጂሃድ መልዕክት ሲያስተላልፉ በነበሩ የማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከነብሰ ገዳዩ ጋር ይወያዩ ነበር በሚል የሽብር ወንጀል ነው የተከሰሱት። ይሁንና መምምህሩን ለመግደል የተፈጸመውን ሴራ በተመለከተ የምናውቀው ነገር አልነበረም ሲሉ አስተባብለዋል። በሌላ በኩል ከፓሪስ ከተማ ወጣ ብሎ ከሚገኘው ትምሕርት ቤቱ አቅራቢያ የተፈጸመውን መምህር ፓቲ’ን አስደንጋጭ ግድያ ተከትሎም በርካታ ትምሕርት ቤቶች ለመታሰቢያው በስሙ ተሰይመዋል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ጥቅምት 16, 2020 መምሕሩን የገደለው ከሩስያዋ የቸቸን ክፍለ ግዛት የሆነው የ18 ዓመቱ ነብሰ ገዳይ በጊዜው በፖሊስ ጥይት ተደብድቦ መገደሉ ይታወሳል።

ትረምፕ እና ሃሪስ ከምርጫው ቀን አስቀድሞ የመጨረሻውን የምረጡኝ ዘመቻ ጥረታቸውን ቀጥለዋል

አሜሪካውያን ቀጣዩን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ በነገው ዕለት ድምጻቸውን በሚሰጡበት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ፤ የሁለቱ ዋና ዋና ፓርቲ ዕጩዎቹ ዶናልድ ትረምፕ እና
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ እና ሃሪስ ከምርጫው ቀን አስቀድሞ የመጨረሻውን የምረጡኝ ዘመቻ ጥረታቸውን ቀጥለዋል

አሜሪካውያን ቀጣዩን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ በነገው ዕለት ድምጻቸውን በሚሰጡበት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ፤ የሁለቱ ዋና ዋና ፓርቲ ዕጩዎቹ ዶናልድ ትረምፕ እና ካማላ ሃሪስ አሁንም እንደተናነቁ መሆናቸውን አዲስ የወጡ ትንበያዎች እያመላከቱ ነው። ካማላ ሃሪስ የመጨረሻ ቀን ዘመቻቸውን ወሳኝ ከሚባሉት ሰባት ግዛቶች አንዷ በሆነችው የሚቺጋን ክፍለ ግዛት ሲያደርጉ፤ ትረምፕ በበኩላቸው በፔንሲልቫንያ፣ ሰሜን ካሮላይና እና በጆርጂያ ክፍለ ግዛቶች አድርገዋል።

VOA60 Africa - Botswana: Outgoing President Masisi hands over power to incoming President Boko

Botswana: Outgoing President Mokgweetsi Masisi handed over power to incoming President Duma Boko on Monday. Masisi conceded defeat Friday after his party lost its parliamentary majority by an unexpected landslide ending nearly six decades in power.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Botswana: Outgoing President Masisi hands over power to incoming President Boko

Botswana: Outgoing President Mokgweetsi Masisi handed over power to incoming President Duma Boko on Monday. Masisi conceded defeat Friday after his party lost its parliamentary majority by an unexpected landslide ending nearly six decades in power.

VOA60 World - At least 35 dead in India bus crash

India: At least 35 people are dead after a bus veered off the road and plunged into a deep gorge in the northern mountainous state of Uttarakhand, officials said on Monday.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - At least 35 dead in India bus crash

India: At least 35 people are dead after a bus veered off the road and plunged into a deep gorge in the northern mountainous state of Uttarakhand, officials said on Monday.

VOA60 America - Trump criticizes US election voting procedures

Republican presidential nominee Donald Trump visited three battleground states on Sunday, Pennsylvania, North Carolina and Georgia. Trump repeatedly criticized the U.S. election process.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Trump criticizes US election voting procedures

Republican presidential nominee Donald Trump visited three battleground states on Sunday, Pennsylvania, North Carolina and Georgia. Trump repeatedly criticized the U.S. election process.

የጀርመኗ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በኪየቭ ጉብኝታቸው ዩክሬንን መደገፋቸውን እንደሚቀጥሉ ተናገሩ

ከዩክሬን መሪዎች ጋር ተገናኝተው ለመነጋገር በዛሬው ዕለት ወደ ኪቭ ያቀኑት የጀርመኗ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አናሌና ቤርቦክ ሃገራቸው ዩክሬንን መደገፏን እንደ
የአሜሪካ ድምፅ

የጀርመኗ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በኪየቭ ጉብኝታቸው ዩክሬንን መደገፋቸውን እንደሚቀጥሉ ተናገሩ

ከዩክሬን መሪዎች ጋር ተገናኝተው ለመነጋገር በዛሬው ዕለት ወደ ኪቭ ያቀኑት የጀርመኗ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አናሌና ቤርቦክ ሃገራቸው ዩክሬንን መደገፏን እንደምትቀጥል በመግለጽ ቃል ገቡ።ባርቦክ አክለውም ‘የሩስያ የአየር ድብደባ አይሎ ወደ ክረምቱ በዘለቀበት እና ሰሜን ኮሪያ ለሞስኮ የምትሰጠው ወታደራዊ ድጋፍ ተጨማሪ ስጋት እየደቀነ ባለበት ወቅት ዩክሬይን ከመቼውም የበለጠ ድጋፍ ያስፈልጋታል’ ብለዋል። ‘ዩክሬናውያን እየተፈጸመባቸውን የጭካኔ ድርጊት በሰብአዊነት እና በምንሰጠው ድጋፍ እየመከትን፤ ክረምቱን መሻገር ብቻ ሳይሆን አገራቸውም እንዲያተርፉ ጭምር እናግዛቸዋለን። በድፍን አውሮፓ ለምንገኝ ለሁላችንንም ነጻነት እየታገሉ ነውና” ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩስያ ኃይሎች ለሊቱን በበርካታ የዩክሬይን አካባቢዎች ላይ ካነጣጠሯቸው ቁጥራቸው 80 የሚደርሱ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ውስጥ ሃምሳ ያህሉን የዩክሬን አየር መከላከያ መትቶ መጣሉን የሃገሪቱ ጦር ሠራዊት አስታውቋል። ሰው አልባ አውሮፕላኖቹ ተመተው የወደቁት በቼርካሲ፣ ቼርኒሂቭ፣ ኬርሰን፣ ኪሮቮራድ፣ ኪቭ፣ ሚኮላይቭ፣ ኦዴሳ፣ ሱሚ እና ዚሂቶሚር መሆኑንም የዩክሬን አየር ኃይል አክሎ አመልክቷል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ በዛሬው ዕለት ‘ከሩስያ ድንበር አቅራቢያ ከሚገኘው የቤልጎሮድ ግዛት አቅራቢያ አንድ የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላን መትቼ’ ጥያለሁ ብሏል።

«ለምን ይመርጣሉ?» የኢትዮጵያ - አሜሪካውያን ድምጽ

ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካውያን ነገ  በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከሁለቱ ዕጩ ተፎካካሪዎች አንዳቸውን ለመምረጥ፣  ለውሳኔያቸው መሰረት የሚያደርጓቸውን ጉ
የአሜሪካ ድምፅ

«ለምን ይመርጣሉ?» የኢትዮጵያ - አሜሪካውያን ድምጽ

ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካውያን ነገ  በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከሁለቱ ዕጩ ተፎካካሪዎች አንዳቸውን ለመምረጥ፣  ለውሳኔያቸው መሰረት የሚያደርጓቸውን ጉዳዮች ይናገራሉ። “በግልም ሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ ለውሳኔያችሁ ቅድሚያ የምትሰጡት ምንድነው?” የሚል ጥያቄ  ለተለያዩ የማኅበረሰብ ድርጅት ተወካዮች አንስተናል። ሰላምና ፍትሕ ለትግራይ ተወላጆች ዓለም አቀፍ ማኅበር ምክትል ሰብሳቢ  አቶ ፒተር ሃጎስ ገብረ  ለዚኽና ለሌሎች ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተውናል። አቶ ፒተር እንደ ዜጋ ሕወታቸውን ከሚመለከቱ አበይት ጉዳዮች፣ የተለየ ዋጋ እስከሚሰጧቸው ሌሎች እሴቶች ድረስ ቁልፍ ናቸው የሚሏቸውን ጉዳዮች ያነሳሉ።  ቃለ ምልልሱን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

በዘንድሮው የአሜሪካ ምርጫ ላለመሳተፍ የወሰኑ መራጮች

ማክሰኞ በሚካሄደው የአሜሪካ ምርጫ የሚወዳደሩትን እጩ ፕሬዘዳንቶች እየመረጡ ና ለመምረጥ የተዘጋጁ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቢኖሩም አንዳንዶቹ ግን በዘንድሮ
የአሜሪካ ድምፅ

በዘንድሮው የአሜሪካ ምርጫ ላለመሳተፍ የወሰኑ መራጮች

ማክሰኞ በሚካሄደው የአሜሪካ ምርጫ የሚወዳደሩትን እጩ ፕሬዘዳንቶች እየመረጡ ና ለመምረጥ የተዘጋጁ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቢኖሩም አንዳንዶቹ ግን በዘንድሮው ምርጫ ላለመሳተፍ የወሰኑም አሉ፡፡ ለዚህም የተለያየ ምክንያት አላቸው፡፡ የህግ ባለሙያና የዩስ አፍሪካ ኢንስቲትዩት ፕሬዘዳንት ዶክተር ታዲዮስ በላይ ግን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተሰሚነታቸውን ለማሳደግ በመራጭነትና ተመራጭነት የሚያደርጉትን ተሳትፎ ማጠናከር ይኖርባቸዋል ይላሉ፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡  

ቱርክ ከአፍሪካ ጋር ግንኙነቷን በማጥበቅ ላይ ትገኛለች

ዛሬ እሁድ በጅቡቲ እየተካሄደ ባለው የቱርክ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ቱርክ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እና ፍልስጤማዊያንን በዲፕሎማሲ ለመ
የአሜሪካ ድምፅ

ቱርክ ከአፍሪካ ጋር ግንኙነቷን በማጥበቅ ላይ ትገኛለች

ዛሬ እሁድ በጅቡቲ እየተካሄደ ባለው የቱርክ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ቱርክ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እና ፍልስጤማዊያንን በዲፕሎማሲ ለመደገፍ ጥሪ አድርጋለች።   ሀገሪቱ ባለፉት ቅርብ ዓመታት በከፍተኛ ሁኔታ በአፍሪካ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሰች ሲሆን፤ የቱርኩ መሪ ረጂብ ጣይብ ኤርዶዋንም ሥልጣን ላይ በቆዩባቸው አስርት ዓመታት ፤  በ31 የአፍሪካ ሀገራት 50 የሚደርሱ ጉብኝቶችን አድርገዋል።   በአሁን ሰዓት በጂቡቲ እየተካሄደ በሚገኘው የቱርክ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ አንጎላ፣ ቻድ፣ ኮሞሮስ፣ ኮንጎ ሪፐሊክ፣ ግብጽ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ጋና፣ ሞሪታኒያ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዛምቢያ እና ዚምባቡዌን ጨምሮ 14 የአፍርካ ሀገራት እየተሳተፉ ይገኛሉ።   በጉባኤው ላይ የተሳተፉት የቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ባድር አብዲላቲ ሀገራቸው ከአፍሪካ ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ባለፈው የጎርጎርሳዊያኑ ዓመት 35 ቢሊየን ዶላር እንደነበረ ገልጸው፤ ሀገራቸው በአፍሪካ ላይ በቀጥታ የምታፈሰው መዋዕለ ንዋይም ሰባት ቢልየን ዶላር ደርሷል በማለት ተናግረዋል።   በተጨማሪም ቱርክ በሰሃራ በስተደቡብ ባሉ ሀገራት የታጠቁ ሃይሎችን በማሰልጠን እና መሳሪያ በማስታጠቅ በአህጉሪቱ አራተኛዋ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገር ሆናለች። ባለፉት ቅርብ ወራትም በኢትዮጵያን እና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለማስታረቅ እንዲሁም በኒጀር የመዓድን ስምምነት ውሎችን እንዲካሄዱ ማገዟ ይታወሳል።   ቀጣዩ የቱርክ አፍሪካ ጉባኤ በጎሮጎሮሳዊያኑ 2026 እንደሚደረግ ተገልጿል።

የፕሪቶሪያ የተኩስ አቁም ስምምነት ሁለተኛ ዓመቱን ያዘ

የትግራይ ክልል አመራሮች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በፕሪቶሪያ በተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የሰፈሩ ቁልፍ ጉዳዮች በመንግስት በኩል እስካሁን ድረስ
የአሜሪካ ድምፅ

የፕሪቶሪያ የተኩስ አቁም ስምምነት ሁለተኛ ዓመቱን ያዘ

የትግራይ ክልል አመራሮች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በፕሪቶሪያ በተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የሰፈሩ ቁልፍ ጉዳዮች በመንግስት በኩል እስካሁን ድረስ ተፈጻሚ አልሆኑም አሉ።   የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ስምምነቱን ተፈጻሚ አለማድረግ በኢትዮጵያ ብሎም በቀጠናው “ሊንሰራፋ የሚችል” ያሉትን አሉታዊ ውጤት እንደሚያስከትል ተናግረዋል።  “ህገ-መንግስታዊ እውቅና የተሰጣቸውን የትግራይግዛቶች ወደ ነበሩበት መመለስ ላይ እብዛም ለውጥ አልታየም። መላው ምዕራብ ትግራይ አሁንም በአማራ ኃይሎችቁጥጥር ስር  ሲሆን በአንጻሩ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች  በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ” በማለት በኤክስ ማኅበራዊ ድረ ገጻቸው ላይ ትላንት ቅዳሜ አስፍረዋል።   አቶ ጌታቸው ረዳ አክለውም “የኤርትራ ኃይሎች በሰሜን ምዕራብ እና በምሥራቅ ትግራይ የያዟቸውን አንዳንድ ቦታዎች እንደያዙ ቀጥለዋል። በእነዚህ አካባቢዎችም በሰዎች ላይ ግፍ መፈጸሙ የተለመደ ነው። በዚህ ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች በማይታሰብ አስከፊ ሁኔታ በሀገር ውስጥ ተፈናቃይ መጠለያ ካምፖች ውስጥ እየማቀቁ ይገኛሉ” ብለዋል።   በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ የአማራ ክልል ቃል አቀባይ አቶ መንገሻ ፈንታውን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የኢትዮጵያ መንግስት ለአቶ ጌታቸው ረዳ አስተያየት በቀጥታ ምላሽ አልሰጠም። ይሁን እንጂ የፕሪቶሪያው የተኩስ አቁም ስምምነትን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ መንግስት ‘አወዛጋቢ አካባቢዎች’ ብሎ በሚጠራቸው ምዕራባዊ ትግራይ ዙሪያ ውሳኔ ለመስጠት የአካባቢው ተወላጆች የራሳቸውን እድል በራሳቸውን እንዲወስኑ መሻቱን አስታውቋል።   በሌላ በኩል ኤርትራ ሰራዊቶቿ በትግራይ ክልል ውስጥ እንደማይገኙ አስታውቃለች። “ለእነዚህ የውሸት እና አሳሳችውንጀላዎች ከረጅም ጊዜ በፊት ምላሽ ሰጥተናል” በማለት የኤርትራው የመረጃ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ዛሬ እሁድ ተናግረዋል።     “ሰሜናዊ እና ምሥራቃዊ ትግራይ ተብለው እየተጠቀሱ ያሉት ባድሜና ሌሎች የኤርትራ  ሉዓላዊ ግዛቶች  ሲሆኑ፤ በኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን በኩል የኤርትራ ሉዓላዊ ግዛት ተብለው የተካተቱ፤ አለም አቀፍ ህግን በመጣስ ለሃያዓመታት ያህል በወረራ ተይዘው የቆዩ ስፍራዎች ናቸው” በማለት ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።   በሌላ በኩል አቶ ጌታቸው ረዳ የፕሪቶሪያው የተኩስ አቁም ስምምነት በትግራይ ክልል ላለፉት ሁለት ዓመታት ሰላምን በማምጣት ውጤታማ ሆኗል ሲሉም ተናግረዋል።   አያይዘውም የኢትዮጵያ መንግስት የባንክ፣ የቴሌኮሚኒኬሽን፣ የምድር እና የአየር መጓጓዣ አገልግሎቶችን በመመለሱ ረገድ እርምጃዎች መውሰዱን ተናግረዋል።   ይህ በእንዲህ እንዳለ ዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ መንግስት በተሳለጠ መልኩ በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ የትግራይ ክልል ዜጎች ወደ መኖሪያ ቀያቸው እንዲመለሱ እንዲያደርግ ጠይቃለች። የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የፕሪቶሪያውን የተኩስ አቁም ስምምነት ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያ በማስመልከት ባወጣው መግለጫ “መንግስት በትግራይ ክልል ከሀገሪቱ ሰራዊት ውጭ ያሉ ኃይሎችን በሙሉ እንዲያሰወጣ” አሳስቧል።   በጎርጎርሳዊያኑ ህዳር ሁለት 2022 በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል በፕሪቶሪያ የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት “በዋናነት በትግራይ ክልል የመሳሪያ ድምጾች ጸጥ ብለዋል፣ የቆሙ አገልግሎቶች በድጋሚ ተጀምረዋል፤ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችም ተመልሰዋል” በማለት ዩናይትድ ስቴትስ ሂደቱን በመልካም ተቀብላዋለች ሲል የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመግለጫው አስታውቋል፡   በተጨማሪም ዩናይትድ ስቴትስ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ግጭቶች በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረጉ ውይይቶች እንዲፈቱ ጥሪ አድርጋለች።

የአሜሪካ ቢ-52 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች መካከለኛው ምሥራቅ ገቡ

ኢራን በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ ከፈጸመችው ዛቻ አንድ ቀን በኋላ ትላንት ቅዳሜ የአሜሪካ ቢ-52 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ መድረሳቸውን
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ ቢ-52 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች መካከለኛው ምሥራቅ ገቡ

ኢራን በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ ከፈጸመችው ዛቻ አንድ ቀን በኋላ ትላንት ቅዳሜ የአሜሪካ ቢ-52 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ መድረሳቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ጦር አስታውቋል። የመካከለኛው ምሥራቅ አና አካባቢው የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ እዝ “ፈንጂ ጣይ አውሮፕላኖቹ ከሚኖ የአየር ኃይል አምስተኛ ክንፍ ደርሰዋል” በማለት በማኅበራዊ ድረገጹ ላይ አስፍሯል።    የፔንታጎን ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ፓት ራይደር “ኢራን፣ አጋሮቿ ወይም በአካባቢቢዎቿ፤ በመካከለኛው ምሥራቅ ያሉ አሜሪካዊያንን ሰራተኞችን ወይም ፍላጎቶችን ለማጥቃት ይህንን ወቅት ይጠቀሙበታል” ያሉ ሲሆን አይይዘውም “ዩናይትድ ስቴትስ ህዝቦቿን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ትወስዳለች” ብለዋል ።

የኦሮሞ ነጻነት ተዋጊዎች የሰሜን ሸዋ ዞን ባለሥልጣንን ገደሉ

በኢትዮጵያ የሰሜን ሸዋ ዞን ባለሥልጣናት አርብ ዕለት በተፈጸም ጥቃት አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን መገደላቸውን አስታውቀዋል። ባለሥልጣቱ የውጫሌ ወረዳ ዋ
የአሜሪካ ድምፅ

የኦሮሞ ነጻነት ተዋጊዎች የሰሜን ሸዋ ዞን ባለሥልጣንን ገደሉ

በኢትዮጵያ የሰሜን ሸዋ ዞን ባለሥልጣናት አርብ ዕለት በተፈጸም ጥቃት አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን መገደላቸውን አስታውቀዋል። ባለሥልጣቱ የውጫሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ኮሩ ጉርሙ በታጠቁ ኃይሎች መገደላቸውን አስታውቀዋል። የግድያው ዜና በአካባቢው የብልጽግና ፓርቲ የፌስቡክ ገጽ ላይ ነው የሰፈረው። መግለጫው አቶ ንጉሴ “የተገደሉት” በካራ አካባቢ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ለመጎብኘት በተንቀሳቀሱበት ወቅት ነው በማለት አስፍሯል። ፓርቲው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት/ኦነግን ለጥቃቱ ተጠያቂ አድርጓል። በጥቃቱ በመንግስት ኃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል በተፈጠረ ግጭት ሌሎች በርካታ ሰዎችመቁሰላቸውን እና መገደላቸውን የሚያመላክቱ ዘገባዎች አሉ።   ‘አቶ ንጉሴ የህዝብ ፍላጎትን እና ጥቅምን ለማስከበር ቁርጠኝነት የነበራቸውና በህዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩ በከፍተኛ ፍላጎት ህዝባቸውን የመሩ ናቸው’ በማለት የፓርቲው መግለጫ አስፍሯል።  የአሜሪካ ድምጽ የውጫሌ ዞን የአካባቢ አመራሮች እና ከሰሜን ሸዋ አመራሮችን አግኝቶ ለማነጋገር ያደረገው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አማካሪ የሆኑት ጂሬኚ ጉደታ በውጫሌ ወረዳ የተደረገው ጥቃት በኦነግ መፈጸሙን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ በጥቃቱ እስካሁን ድረስ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ አላስታወቁም።

በኦሮሚያ ክልል በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 38 ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ በሚገኙ፣ ቢርቢሳ ጋሌ እና ደረባ በተሰኙ ሁለት ቀበሌዎች ውስጥ ረቡዕ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት ላይ በታጣቂዎች
የአሜሪካ ድምፅ

በኦሮሚያ ክልል በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 38 ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ በሚገኙ፣ ቢርቢሳ ጋሌ እና ደረባ በተሰኙ ሁለት ቀበሌዎች ውስጥ ረቡዕ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት ላይ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ። ወላጆቻቸውን በጥቃቱ ያጡ ቤተሰቦችን ጨምሮ ለአሜሪካ ድምጽ ስለጉዳዩ የተናገሩ ስድስት ሰዎች፣ በዕለቱ በተፈፀመው ጥቃት ቢያንስ 38 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል። ቁጥሩን እስከ አርባ ያደረሱት ነዋሪዎችም አሉ። በወረዳው ቢርቢሳ ጋሌ ቀበሌ ነዋሪ የኾኑት አቶ አሸናፊ ቦጋለ፤ ለሥራ ጉዳይ ከቤት ውጭ እንደነበሩ ገልጸው፣ በጥቃቱ ነፍሰጡር ባለቤታቸውን ጨምሮ አራት ቤተሰብ እንደተገደለባቸው ተናግረዋል።    “እናቴን፣ ልትወልድ ተቃርባ የነበረች  ባለቤቲንና  ልጄን በአንድ ጊዜ አጣሁ። አንደኛዋ ሴት ልጄ ህይወቷን ለማትረፍ ስትሮጥ በተተኮሰባት ጥይት ተመታ ቆስላለች” ይቺ በሕይወት የተረፈችው ልጃቸው አዳማ ሆስፒታል እንደምትገኝ አቶ አሸናፊ አክለው ገልጸዋል። ሌላው በዱግዳ ወረዳ፣ ቢርቢሳ ቀበሌ ነዋሪ የኾኑት አቶ ደጀኔ ጥላሁን ፣ የ77 ዓመት አዛውንት አባታቸው በጥቃቱ እንደተገደሉባቸው ገልጸዋል።   “በዕለቱ ማታ ቤት ውስጥ ሁለት ወንድሞቼ፣ ሁለት ሠራተኞችና አባቴ ነበርን። እንደ አጋጣሚ እናታችን ቤት አልነበረችም። ታጣቂዎቹ መጀመሪያ አካባቢውን የሚጠብቁ ይለስሉ ነበር። በኋላ “ወሪ ኩን” እያሉ በኦሮመኛ እየጮሁ ወደ ጊቢያችን ገቡ” በወቅቱ እርሻ ውስጥ መደበቃቸውን የሚናገሩት አቶ አሸናፊ፣ ታጣቂዎቹ የሳር ቤቶቹን አቃጥለው ትልቁን ቤት ለማቃጠል ሲሄዱ አባት ለልመና ከተደበቁበት ወተው ወደ ታጣቂዎቹ ማምራታቸውን ተናግረዋል። “እለምናቸዋለሁ ብሎ ሲሄድ ነው የተጎዳው። እናታችን ነች አስክሬኑን ያነሳችው። እጁን በስለት ተወግቷል፣ ደረቱንም በጥይት ተመቷል። ሥርዓተ ቀብሩም፣ ሐሙስ በዱግዳ ወረዳ ቢርቢሳ ጋሌ ቀበሌ መድሃኒያለም ቤተክርስትያን ተፈጽሟል።” ኩሼ ጌታቸው የተባለች ሌላ ጎረቤታቸውም መገደሏን የጠቆሙት አቶ ደጀኔ፣ “ነፍሰጡር እናትና ማየት የማይችሉ አዛውንት ጭምር ተገድለዋል። ጥቃቱ ዘግናኝ ነው። እንዲህ ያለ ዘግናኝ ድርጊት የፈጸሙት የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው ይባላል። እኛ ምን እናውቃለን። ግራ የሚያጋባ ነው።” ብለዋል። አቶ ደጀኔ ቀበሌዉ ከሶዶ ወረዳ ጋራ እንደሚዋሰን ገልጸው፣ በጥቃቱ ዋና ዋነኛ ተጎጂዎቹ የጉራጌ እና የአማራ ብሔር ተወላጆች መኾናቸውን ተናግረዋል። ሟች አባታቸው የአማራ ብሔረሰብ ተወላጅ መኾናቸውን ጠቅሳው፣ እናታቸው ደግሞ የጉራጌ የወላጅ መኾናቸውን ተናግረዋል።  ጥቃቱ ሲፈፀም ማንም የፀጥታ ኃይል ወደ አካባቢው አለመምጣቱን የተናገሩት አቶ ደጀኔ፣ አኹን የአካባቢው ሰላም አስተማማኝ ባለመኾኑ፣ የአባታቸው ቤተሰብ ቀያቸውን መልቀቃቸውን ገልጸዋል። አቶ ገመቹ አራባ የተባሉ ሌላ የደረባ ቀበሌ ነዋሪ፣ ቤተሰቦቻቸው እንደተገደሉ ተናግረዋል። “የደረሰብን ጥቃት በጣም አስደንጋጭ እና ከባድ አደጋ ነው። ለመግለፅ ቃላት የለኝም። ወንድ አያቴ እና ሁለት የአጎቴ ልጆች ተገድለውብኛል። ቤቶቻችን ተቃጥሎብናል። እንደምንም ብዬ ነው ቤተሰቦቼን ያተረፍኳቸው። የተገደሉትን ቀብረናቸው ተቀምጠናል። አሁን ራሱ ሜዳ ላይ ነው ያለነው።” አቶ ገመቹ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ተፈጸመ ባሉት ጥቃት፣ ከ40 ሰዎች በላይ መገደላቸውን ተናግረዋል። ከአንድ ቤተሰብ አምስት እና ስደስት የተገደለበት አለ። በጣክ አሳዛኝ ጥቃት የተፈፀመው መንግሥትን ትደግፋላችሁ፤ መሳሪያ ታጥቃችኃል በሚል ነው። ጥቃቱን የፈፀሙትም የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው” ብለዋል።  በጥቃቱ ቤታቸው ውስጥ የነበሩ ሕጻናት፣ ሴቶችና አቅመ ደካሞች ጭምር መጎዳታቸውን የተናገሩት አቶ ገመቹ  “አብዛኛው የተገደሉት የሶዶ ጉራጌ ተወላጆች ናቸው። በአከባቢው የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ቦራ የፀጥታ ኃይሎች በቅርብ ርቀት ቢኖሩም ጥቃቱን ማስቆም አልቻሉም። ከዚህ በፊትም በወረዳው ሰዎች እየታገቱ ገንዘብ እየተከፈለ ይለቀቁ ነበር።” ብለዋል። ጤሮ ተስፋ የተባሉ ሌላ የቢርቢርሳ ቀበሌ ነዋሪ በበኩላቸው በአካባቢ ዘግናኝ ያሉት ጥቃት በተደራጀ ኃይል መፈጸሙን ይናገራሉ። አቶ ጤሮ ስለግድያው ዘግናኝነት በዝርዝር አስረድተዋል። “ማየት የተሳናቸው፣ ሴቶች፣ ሕጻናት፣ ወንዶች በአጠቃላይ ወደ 40 የሚኾኑ ሰዎች ተገድለዋል። ግድያውን የፈጸመው ሸኔ የተባለ ቡድን ነው። ድርጊቱ ለአዕምሮ የሚከብድ ነው። ሰዎችን መለየት አልቻልንም ዝም ብለን አፍሰን ቀብረናቸዋል። በጥቃቱ የተጎዳው አብዛኛው የጉራጌ ማኅበረሰብ ተወላጅ ሲኾን ነዋሪው አኹን ወደ መቂና ጉራጌ እየሸሸ ነው” ብለዋል።   የዱግዳ ወረዳ ቢርቢሳ ጋሌ ቀበሌ ነዋሪ የኾኑና ለደኅንነታቸው ስለሚሰጉ ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ ነዋሪ በዕለቱ ዝናብ እየዘነበ እንደነበር ገልጸው ምሽት አካባቢ ጩኸት መስማታቸውን ይናገራሉ። “ከዚያ ቤት ሲቃጠል ነው የተመለከትነዉ፣ ጥቃቱ የጀመረው ማታ አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ ሲኾን እየጎላ የመጣው ግን ወደ ሁለት ሰዓት ነው። እናም እስከ ምሽቱ ስድስት ሰዓት ድረስ ግድያው ቀጠለ።  ጥቃቱን ያደረሱት ኦሮምኛ ይናገራሉ አሉን። እኛ በጊዜው ተደብቀን ነበር።  ኦነግ ሸኔ ናቸው የሚል ነገር ነው የተነገረን። በዚህ ጥቃት በሚያሳዝን መልኩ፣ ሕፃናት፣ አዛውንቶች፣ ነፍሰጡር ሴቶች ጭምር ቤት ውስጥ ተቃጥለዋል። በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው የተከሰተው።” በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዓት ዱግዳ ወረዳ መፈጸሙን ተናግረዋል። “ የ38 ሟቸው ቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጽሟል። ከደረባ 24፣ ከኩሬ 17፣ ከቢጥሲ ደግሞ ሁለት ነበሩ። የወረዳዉ መንግሥት ባለሥልጣናት ባሉበት ነው ከተቃጠለው ቤት አስክሬን ወጥቶ ኩሬ ስላሴ ቤተክርስትያን የተቀበረው። ፈጣሪ ይርዳን እንጂ አሁን አብሮ ሲኖር የነበረ ሰው እርስ በርሱ በጥርጣሬ ዐይን እየተያየ ነው። መንግሥትም ይህን እንዴት እንደተመለከተው አላውቅም።” ነዋሪው አክለው ጥቃቱ ሲፈጸም የነበረው እስከ እኩለ ለሊት ቢኾንም፣ የፀጥታ አካላት የደረሱት ግን ማለዳ ላይ ነው ብለዋል። በጥቃቱ የኦሮሞ ተወላጅ ማኅበረሰብ አባላትም መጎዳታቸውን ተናግረዋል። “ኦሮሞ ኾኖ ቤቱ የተቃጠለበትና የተገደለም አለ። ለምሳሌ ከደረባ መኮንን የሚባለው ሰው ከተገደሉት አንዱ ነው።  እሱ ኦሮሞ ነዉ፣ ሌላ የአያቴ ባል ጎሳዬ የሚባልም ተገድሏል። ነገር ግን በዚህ ጥቃት የተጎዱት አብዛኛው የጉራጌ ተወላጆች ናቸው።” ሲሉ ነዋሪው ኹኔታውን አስረድተዋል። የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ ተካልኝ ንጉሴ የተፈፀመው ጥቃት ዘግናኝ መኾኑን ተናግረዋል። ነገር ግን ተገደሉ የተባሉ ሰዎችን ቁጥር ማረጋገጥ እንደማይችሉ ገልጸዋል። ሰዎቹ የተገደሉት በመኖሪያ በታቸው እሳት ተለቀቆባቸው እና መሳሪያ ተተኩሶባቸው እንደኾነ አስረድተዋል። ሴቶች፣ አረጋዊያን፣ አቅመ ደካሞች በእሳት ተቃጥለው መሞታቸውን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የክልሎቹ የፀጥታ ሃይሎች አከባቢውን ለማረጋጋት ወደ ስፍራው መግባታቸውን ያስታወቁት አቶ ተካልኝ ተጎጂዎችን ለመርዳት በሁለቱም አስተዳደር በኩል ጥረት መጀመሩን ተናግረዋል።  ነዋሪዎቹና የተጎጂ ቤተሰቦች ኦነግ ሸኔ ሲሉ የጠሯቸውን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርገዋል። ኖርዌይና አፍሪካ ውስጥ እንደሚኖሩ የገለጹት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አማካሪ መኾናቸውን የተናገሩት፣ አቶ ጅሬና ጉደታ ስለጉዳዩ መስማታቸውን ገልፀው፣ ታጣቂዎቹ ከጥቃቱ ጀርባ እንደሌሉና በመናገር አስተባብለዋል። ታጣቂዎቻቸው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት እንደማይፈጽሙም ገልጸዋል።  አቶ ጅሬና ማስተባበላቸውን ገልጸን አስተያያት እንዲሰጡ የጠየቅናቸው የተጎጂ ቤተሰብ አቶ ገመቹ አራባ፣ ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች ታጣቂዎቹ  ይታወቁባቸዋል ያሏቸውን መለያዎች መናገራቸውን ገልጸዋል። “ከጥቃቱ የተረፉ እና የቆሰሉ ሰዎችም  አይተዋቸዋል። ሌላው ነገር ቢቀር በሹሩባቸው እንለያቸዋለን። ራሳቸው ናቸው ሰላማዊ ሰዎችን የገደሉት። ከዚህ በፊትም ራሳቸው እየመጡ ሦስት አራት ጊዜ ሞክረው አልተሳካላቸውም ነበር።” በጉዳዩ ላይ ከኦሮሚያ ክልል እና ከአካባቢው ባለሥልጣናት መረጃን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

Get more results via ClueGoal