Ethiopia



ደስታም ሐዘንም ያስተናገደው የትረምፕ ምርጫ ድል

የአሜሪካውያን ፈቃድ በመሆኑ፣ የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ወደ ዋይት ሃውስ ይመለሳሉ። ለሁለት በተከፈለችው ሃገር፣ ምርጫውን የማሸነፋቸውን ዜና አ

ካምላ ሃሪስ በፕሬዝደንታዊ ምርጫው ትረምፕ ማሸነፋቸው ተቀበሉ

በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ተመራጩን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ዘንድ በስልክ «እንኳን ደስ ያለዎ» ብለዋቸዋል፡፡ ምክትል ፕሬዝደ
የአሜሪካ ድምፅ

ካምላ ሃሪስ በፕሬዝደንታዊ ምርጫው ትረምፕ ማሸነፋቸው ተቀበሉ

በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ተመራጩን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ዘንድ በስልክ «እንኳን ደስ ያለዎ» ብለዋቸዋል፡፡ ምክትል ፕሬዝደንት ካምላ ሃሪስም በምርጫው መሸነፋቸውን ተቀብለዋል፡፡ የኋይት ሀውስ ዘጋቢያችን ፓትሲ  ዊዳኩስዋራ  ሃሪስ ትላንት ረቡዕ ንግግር ካደረጉበት ከዋሽንግተኑ ሐዋርድ ዩኒቨርስቲ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በደቡብ ሶማሊያው ጦርነት ቢያንስ 11 የመንግሥት ኃይሎች ተገደሉ

ሶማሊያ ውስጥ በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል በትላንት  በተደረገ ከባድ ጦርነት ቢያንስ 11 የሶማሌ ክልል እና የፌደራል መንግስት ሃይሎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት አ
የአሜሪካ ድምፅ

በደቡብ ሶማሊያው ጦርነት ቢያንስ 11 የመንግሥት ኃይሎች ተገደሉ

ሶማሊያ ውስጥ በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል በትላንት  በተደረገ ከባድ ጦርነት ቢያንስ 11 የሶማሌ ክልል እና የፌደራል መንግስት ሃይሎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ጦርነቱ የተካሄደው ከጁባላንድ ግዛት ኪስማዮ በስተደቡብ ምዕራብ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዋያንታ አካባቢ የመንግስት ሃይሎች ታጣቂዎቹ ይሰባሰባሉ በተባለበት ቦታ ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ ነው። ከመገናኛ ብዙኃን ጋር መነጋገር ያልተፈቀደላቸውና ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሦስት ባለሥልጣናት፣ 11 የክልልና የመንግሥት ወታደሮች ሲገደሉ ከ20 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል። በግጭቱ ከ20 በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን ከባለስልጣናቱ አንዱ ተናግረዋል። ባለፈው አመት የሶማሊያ ሃይሎች በተመሳሳይ አካባቢ ባደረጉት ዘመቻ የአልሸባብ ምክትል አሚር ነበር የተባለውን ግለሰብ መግደላቸውን የክልሉ ባለስልጣናት ገልጸዋል። አምና በአልሸባብ ታጣቂዎች ላይ በዋይንታ አካባቢ “ራስን በጋራ መከላከል” በተሰኘው የአሜሪካ ጦር የአየር ጥቃት ሶስት ተዋጊዎች ተገድለዋል።  

ትራምፕ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት እንደሚያስቀጥሉ ኢትዮጵያውያን ተስፋ አድርገዋል

በአሜሪካ ምርጫ ውጤት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የተለያዩ አስተያየቶችን አንፀባርቀዋል። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ምርጫን ማሸነፋቸውን
የአሜሪካ ድምፅ

ትራምፕ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት እንደሚያስቀጥሉ ኢትዮጵያውያን ተስፋ አድርገዋል

በአሜሪካ ምርጫ ውጤት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የተለያዩ አስተያየቶችን አንፀባርቀዋል። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ምርጫን ማሸነፋቸውን ተከትሎ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ካነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች መካከል ገሚሱ በውጤቱ ሲደሰቱ የተቀሩት ደግሞ ቅር ተሰኝተዋል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ላይ ያሉ ግጭቶችን ከማስቆም አንጻር ከአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት የተሻለ ጥረት እንደሚጠብቁም ገልፀዋል፡፡ አስተያየቶቹን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

VOA60 America - Harris concedes US presidential election defeat to Trump

U.S. Vice President Kamala Harris on Wednesday conceded her presidential election defeat, phoning former president Donald Trump to congratulate him on his victory
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Harris concedes US presidential election defeat to Trump

U.S. Vice President Kamala Harris on Wednesday conceded her presidential election defeat, phoning former president Donald Trump to congratulate him on his victory

VOA60 Africa - Mozambique: Clashes in Maputo ahead of demonstrations against election results

Riot police fired tear gas and rubber bullets to disperse groups of people gathering in the capital Maputo, ahead of planned demonstrations against October 9 election results.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Mozambique: Clashes in Maputo ahead of demonstrations against election results

Riot police fired tear gas and rubber bullets to disperse groups of people gathering in the capital Maputo, ahead of planned demonstrations against October 9 election results.

VOA60 World - Ukraine: Dozens of Russian drones target Kyiv in eight-hour attack

Ukraine: Dozens of Russian drones targeted the capital of Kyiv in a nighttime attack that lasted eight hours, authorities said Thursday, as Russia kept up its relentless pounding of Ukraine after almost 1,000 days of war.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Ukraine: Dozens of Russian drones target Kyiv in eight-hour attack

Ukraine: Dozens of Russian drones targeted the capital of Kyiv in a nighttime attack that lasted eight hours, authorities said Thursday, as Russia kept up its relentless pounding of Ukraine after almost 1,000 days of war.

ጀርመን ለቻይና በመሰለል የተጠረጠረ አሜሪካዊ መያዝዋን አስታወቀች

ጀርመን ወታደራዊ መረጃዎችን ለቻይና ሰጥቷል በሚል የተጠረጠረውን የአሜሪካ ዜጋ በቁጥጥር ስር አዋለች። ጀርመን በሀገሯ ለሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሲሰራ ያገኘ
የአሜሪካ ድምፅ

ጀርመን ለቻይና በመሰለል የተጠረጠረ አሜሪካዊ መያዝዋን አስታወቀች

ጀርመን ወታደራዊ መረጃዎችን ለቻይና ሰጥቷል በሚል የተጠረጠረውን የአሜሪካ ዜጋ በቁጥጥር ስር አዋለች። ጀርመን በሀገሯ ለሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሲሰራ ያገኘውን የአሜሪካ ወታደራዊ መረጃ ለቻይና በመስጠት የተጠረጠረውን የአሜሪካ ዜጋ በቁጥጥር ስር ማዋሏን፣ የሀገሪቱ ፌደራል አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ዛሬ ሃሙስ ዕለት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። መግለጫ እንዳመልከተው የግል ማንነትን አለመግለጽ በሚፈቅደው የጀርመን ህግ መሰረት ማርቲን ዲ በሚል ስም ብቻ የተገለጸው ግለሰብ ለውጭ የስለላ ድርጅት ወኪል ሆኖ ለመስራት መዘጋጀቱን ተናግሯል ሲል አመልክቷል፡፡ ተከሳሹ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በጀርመን ለአሜሪካ ጦር ሃይሎች ሲሰራ እንደነበር አቃቤ ህግ ተናግሯል። እ.ኤ.አ. በ2024 ከቻይና የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በመገናኘት ለቻይና ጥብቅ መረጃዎችን እንደሚያካፍላቸው ተነግሯል። መረጃውን የሰበሰበው ለውትድርና ባደረገው ስራ ነው ሲል አቃቤ ህግ ተናግሯል። ጀርመን ከቤጂንግ የሚዘረጉ የስለላ መረቦች ሊጨምሩ እንደሚችሉ ያላትን ስጋት በመግለጽ ያስጠነቀቀች ሲሆን በዚህ ዓመት በስለላ ተግባር የተጠረጠሩ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታውቃለች፡፡ ይህ በሚያዝያ ወር ላይ የቻይናን የባህር ሃይል የሚያጠናክር ቴክኖሎጂን አሳልፈው ለመስጠት ሲሰሩ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሶስት ጀርመናውያን እና ከቻይና የስለላ ድርጅት ጋር በመስራት የተከሰሱትን የቀኝ አክራሪ ፖለቲከኛ የአውሮፓ ህብረት ሰራተኛን ያጠቃልላል።

የቻይና እና የታይዋን መሪዎች ለትረምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

የቻይና እና የታይዋን መሪዎች ለወደፊቱ ግንኙነቶች ጥንቃቄ ከተሞላበት ተስፋ ጋራ ፣ ትረምፕ የአሜሪካን ምርጫ በማሸነፋቸው የ”እንኳን ደስ ያለዎት” መልዕክታ
የአሜሪካ ድምፅ

የቻይና እና የታይዋን መሪዎች ለትረምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

የቻይና እና የታይዋን መሪዎች ለወደፊቱ ግንኙነቶች ጥንቃቄ ከተሞላበት ተስፋ ጋራ ፣ ትረምፕ የአሜሪካን ምርጫ በማሸነፋቸው የ”እንኳን ደስ ያለዎት” መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ ቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ «ሁለቱንም ሀገራት እና ሰፊውን ዓለም» ተጠቃሚ ለማድረግ በአዲሱ ዘመን ተስማምተው ለመኖር የሚያስችላቸውን ትክክለኛውን መንገድ እንዲሹ አሳስበዋል፡፡ የቻይናው መሪ ሁለቱ ወገኖች “በመከባበር መርህ፣ አብሮ መኖርና መጠቃቀም ላይ የተመሠረተ ግንኙነቶችን ለማስፋት ውይይትና ግንኙነትን በማጠናከር ልዩነቶችን በአግባቡ እየፈቱ የጋራ ትብብርና ጥቅሞችን ማስፋት ይችላሉ የሚል ተስፋ” እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ ባላፈው ግንቦት ወደ ሥልጣን የመጡት የታይዋን ፕሬዝዳንት ላ ቺንግ-ቴ ለረጅም ጊዜ የዘለቀው በጋራ እሴቶችን እና ፍላጎቶች ላይ የተመሠረተው የታይዋን እና ዩናይትድ ስቴትስ አጋርነት፣ ለክልላዊ መረጋጋት ቁልፍ ጉዳይ ሆኖ እንደሚቀጥል እና ወደ ላቀው ብልጽግና እንደሚያመራ” ሙሉ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ በቻይና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ትረምፕ በቻይና ምርቶች ላይ ከፍተኛ ቀረጥ ሊጥሉ እንደሚችሉ በመገመት የንግድ ጦርነቱ በቻይና ኢኮኖሚ ላይ ምን ያህል ተጽእኖ ሊያሳድር እንደሚችል የተደባለቀ ስሜቶቻቸውን ገልጸዋል፡፡ አንዳንድ የታይዋን ዜጎችም የትረምፕ የግብይት ዘይቤ፣ በተለይም ትረምፕ በምርጫ ዘመቻቸው ስለታይዋን የተናገሩት እና የውጭውን ዓለም የማግለል ፖሊሲያቸው፣ አሜሪካ ለታይዋን የምትሰጠውን ድጋፍ ሊያዳክሙ ይችላሉ ብለው እንደሚጨነቁ ተመልክቷል፡፡ ትረምፕ ባለፈው ሀምሌ ከብሉምበርግ ጋራ ባደረጉት ቃለጠመይቅ ታይዋን ድጋፍ ለሚሰጣት የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ እንድትከፍል የጠየቁ ሲሆን፣ የኮምፒውተር እና የስልክ ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ቁልፍ የሆነውን የ“ቺፕ”ሥራዎችን መቶ መቶ ወስዳብናለች ብለዋል፡፡ ተንታኞች ታይዋን ጠንካራ የመከላከያ ቁርጠኝነት ካላሳየች የትረምፕ ተለዋዋጭ የፖሊሲ እና የማግለል ዝንባሌ የታይዋንን ደህንነት ሊያዛባ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የቻይና ተንታኞች የአሜሪካ እና የታይዋን ወታደራዊ ትብብር መጨመር በተለይም የጦር መሳሪያ ግዢ ውጥረቱን ሊያባብሰው ይችላል ብለው ይጨነቃሉ፡፡

እስራኤል በጋዛ ዘመቻዋን ስታሰፋ በቤይሩት ከባድ የአየር ድብደባ ፈጽማለች

በሊባኖስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የሚገኘውን አካባቢ ጨምሮ በደቡባዊ ቤይሩት አካባቢዎች ዛሬ ሐሙስ ጠዋት ከፍተኛ የአየር ድብደባዎች ተፈጽመ
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል በጋዛ ዘመቻዋን ስታሰፋ በቤይሩት ከባድ የአየር ድብደባ ፈጽማለች

በሊባኖስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የሚገኘውን አካባቢ ጨምሮ በደቡባዊ ቤይሩት አካባቢዎች ዛሬ ሐሙስ ጠዋት ከፍተኛ የአየር ድብደባዎች ተፈጽመዋል፡፡ የእስራኤል ጦር በአካባቢው የሂዝቦላህን መገልገያዎች መኖራቸውን በመጥቀስ ሰዎች አካባቢውን እንዲለቁ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ተጨማሪ ዝርዝሮችን አልሰጠም፡፡ በተጨማሪም የእስራኤል ጦር፣ ከጦርነቱ የመጀመሪያዎቹ ቀናት ጀምሮ ከባድ የቦምብ ድብደባ የተፈፀመባትንና የሀማስ ታጣቂዎች መልሰው እየተቧደኑባት ነው ያላትን ቤት ላሂያ ከተማን በማካተት በሰሜናዊ ጋዛ ለወራት የቆየውን የምድር ዘመቻ ማስፋፋቱን አስታውቋል፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች የተፈጸሙ ከባድ የቦምብ ጥቃቶች ከፍተኛ ጉዳት እና የጅምላ መፈናቀል አድርሰዋል፡፡ የሂዝቦላህ መሪ ናኢም ካሴም፣ የቀድሞ የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህ፣ በቤይሩት ከተገደሉበት ጊዜ አንስቶ ለ40 ቀናት የቆየውን የሃዘን ጊዜ አስመልከተው ትላንት ረቡዕ ባሰሙት ንግግር “የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ለተኩስ አቁም ድርድር ክፍት የሚሆነው አንዴ ነው ፣ ‘ጠላት ጥቃቱን ካቆመ’ ብቻ” ብለዋል። ሄዝቦላህ በጋዛ ሰርጥ ከሚገኘው የሃማስ ታጣቂ ቡድን ጋር በመተባበር እኤአ ከጥቅምት 8፣ 2023 ጀምሮ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ሲተኩስ መቆየቱ ተነግሯል፡፡ ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ፣ “በሊባኖስ ከ3,000 በላይ ሰዎች ሲገደሉ 13,600 የሚያህሉ ቆስለዋል” ሲል የሌባኖስ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዘግቧል። የእስራኤል-ሃማስ ጦርነት የተቀሰቀሰው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7፣ 2023 የፍልስጤም ታጣቂዎች ወደ እስራኤል ዘልቀው በመግባት አብዛኞቹ ሲቪሎች የሆኑትን 1,200 ያህል ሰዎችን ከገደሉ እና ሌሎችን 250 ከጠለፉ በኋላ ነው። እስራኤል በጋዛ በወሰደችው ወታደራዊ ምላሽ ከ43,000 በላይ ሰዎችን መገደላቸውን የፍልስጤም የጤና ባለሥልጣናት ገልጸዋል። በሰላማዊ ሰዎች እና በታጋዮች መካከል ያለውን ልዩነት ባይገልጹም ከተገደሉት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች እና ህጻናት ናቸው ብለዋል።

ሪፐብሊካኖች በትላንቱ ምርጫ የህግ መወሰኛ  ምክር ቤት መቀመጫዎችን ተቆጣጠሩ

 የሪፐብሊካን ፓርቲ ትላንት ማክሰኞ በተካሄደው ምርጫ ከ100 መቀመጫዎች ካሉት የዩናይትድ ስቴትስ የእንደራሴዎች ምክር ቤት (ሴኔት) ቢያንስ የሃምሳ አንዱን ማሸነ
የአሜሪካ ድምፅ

ሪፐብሊካኖች በትላንቱ ምርጫ የህግ መወሰኛ  ምክር ቤት መቀመጫዎችን ተቆጣጠሩ

 የሪፐብሊካን ፓርቲ ትላንት ማክሰኞ በተካሄደው ምርጫ ከ100 መቀመጫዎች ካሉት የዩናይትድ ስቴትስ የእንደራሴዎች ምክር ቤት (ሴኔት) ቢያንስ የሃምሳ አንዱን ማሸነፋቸው ይፋ ተደርጓል። አሁን ሪፕብሊካኖች የሚቆጣጠሩት የተወካዮች ምክር ቤት እጣ ግን  አልለየም።    435 ጠቅላላ መቀመጫዎች ያሉት የተወካዮች ምክር ቤት አባላት በመላዋ ዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ለሁለት ዓመታት ለሚዘልቅ የሥራ ዘመን ሲወዳደሩ፤ በየ6 ዓመቱ አባላቱ ለአዲስ ምርጫ የሚፎካከሩበት የእንደራሴዎች  ምክር ቤት በበኩሉ፤ 34 መቀመጫዎች ብቻ ናቸው ለዘንድሮው ምርጫ የቀረቡት።  የትላንቱ ምርጫ ከመካሄዱ አስቀድሞ ዲሞክራቶች ሴኔቱን (የእንደራሴዎች ምክር ቤቱን) በጠባብ  ብልጫ ሲቆጣጠሩ፤ ሪፐብሊካኖች ደግሞ በተመሳሳይ አነስተኛ ብልጫ (220 መቀመጫዎችን በመያዝ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱን እንደቆጣጠሩ ናቸው። በሌላ በኩል በዌስት ቨርጂኒያ እና ኦሃዮ ክፍለ ግዛቶች የሴኔት መቀመጫዎችን ያሸነፉበት ወሳኝ ድል የሪፐብሊካን ፓርቲያቸውን ዳግም አብላጫ መቀመጫዎች እንዲቆጣጠር አስችሎታል። የካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት ምርጫ ድምጽ ቆጠራ ብዙ ቀናት የሚወስድ መሆኑ፤ አሸናፊው ያልለየባቸው ፉክክሮች ዳግም ምርጫ እና በጣም ተቀራራቢ ውጤቶች የተገኙባቸው ምርጫዎች ዳግም ቆጠራም  ሳምንታት ሊወስዱ የመቻላቸው እጣ ተደማምሮ፤ የተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ውጤት ለበርካታ ቀናት ሳይታወቅ ሊቆይ  እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ የምርጫ ቅስቀሳዎች እየተካሄዱ ሳሉ የተደረጉ የፖለቲካ ግምገማዎች ለሁለቱ ምክር ቤቶች ተመራጮች ያለው ድጋፍ፤ ለፕሬዚደንትነት የተፎካከሩት   ካማላ ሃሪስ እና ዶናልድ ትራምፕ ከዋይት ሃውስ ለመዝለቅ ሲያደርጉት  በነበረው ብርቱ ፉክክር የታየውን የመሰለ የፓርቲ መስመር የተከተለ ሆኖ ታይቷል። በጥቅምት ወር የሮይተርስ የዜና ወኪል እና ኢፕሶስ በጋራ ያካሄዱት የሕዝብ አስተያየት ግምገማ እንዳመለከተው ከጠቅላላው የተመዘገቡ መራጮች 43 በመቶው በየምርጫ ክልሎቻቸው ያሉ ሪፐብሊካን የምክር ቤት አባላትን ሲደግፉ፣ በተመሳሳይ 43 በመቶው መራጮች የዲሞክራት ፓርቲውን እንደሚደግፉ አሳይቷል።

የትራምፕ መመረጥ በሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያለው ተፅእኖ

ትላንት ማክሰኞ በዩናይትድ ስቴትስ በተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ  የሪፐብሊካን ፓርቲው እጩ ዶናልድ ትረምፕ  ከዲሞክራቲክ ፓርቲው ተፎካካሪያቸው ከምክትል
የአሜሪካ ድምፅ

የትራምፕ መመረጥ በሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያለው ተፅእኖ

ትላንት ማክሰኞ በዩናይትድ ስቴትስ በተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ  የሪፐብሊካን ፓርቲው እጩ ዶናልድ ትረምፕ  ከዲሞክራቲክ ፓርቲው ተፎካካሪያቸው ከምክትል ፕሬዚደንት ካምላ ሃሪስ ጋር ብርቱ ፉክክር አድርገው አሸንፈዋል፡፡ መጀመሪያ 45ኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት የነበሩት ትረምፕ በመጪው ጥር ወር 47ኛው ፕሬዚደንት ሆነው በድጋሚ ኋይት ኃውስ ቤተ መንግሥት ይገባሉ፡፡ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ትኩረትን ስቦ የከረመው የአሜሪካ ምርጫ ውጤት በቀጣይ የሀገር ውስጥ ፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ምን አንድምታ ይኖረዋል ስትል ስመኝሽ የቆየ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራንን አነጋግራለች። (ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ፋይል ያገኛሉ)

ዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ 47ኛ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ ፉክክር የተደረገባቸውን እንደ ፔንሴልቫኒያ እና ዊንስኮንሰን ያሉ ወሳኝ ግዛቶች ማሸነፋቸው
የአሜሪካ ድምፅ

ዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ 47ኛ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ ፉክክር የተደረገባቸውን እንደ ፔንሴልቫኒያ እና ዊንስኮንሰን ያሉ ወሳኝ ግዛቶች ማሸነፋቸውን ተከትሎ፣ ረቡዕ ጠዋት የአሜሪካ 47ኛ ፕሬዝዳንት ሆነው ማሸነፋቸውን አረጋግጠዋል። ትራምፕ፣ በግዛቶች ውስጥ በሚደረኩ ፉክክሮች ፈታኝ ፍልስሚያ በሚካሄድበት የዩናይትድ ስቴትስ የምርጫ ስርዓት ውስጥ የተፎካከሯቸውን ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ግልፅ በሆነ አብላጫ ድምፅ ማሸነፋቸው የታወቀው፣ ማክሰኞ እለት የድምፅ አሰጣጥ ሥርዓቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ነው። ትራምፕ ፈታኝ ፉክክር ይደረግባቸው ተብለው የተጠበቁትን ፔንሴልቫኒያ፣ ጆርጂያ እና ሰሜን ካሮላይና ግዛቶች ማሸነፋቸው ሥልጣኑን ለመረከብ ያስፈልጋቸው ከነበረው 270 የመራጮች ድምፅ ቢያንስ 267ቱን እንዲያገኙ ረድቷቸዋል። ዊስኮንሰን ግዛትም ረቡዕ ማለዳ ላይ ትራምፕ ማሸነፋቸውን አስታውቋል። በተጨማሪም ሪፐብሊካኖች 100 መቀመጫ ያለውን የሕግ መወሰኛ ምክርቤት መቆጣጠር የቻሉ ሲሆን፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤቱን ማን እንደሚያሸንፍ እስካሁን አልታወቀም። ትራምፕ ረቡዕ ማለዳ ላይ ፍሎሪዳ ውስጥ ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠው «ይህ ከዚህ በፊት ማንም አይቶት የማያውቀው እንቅስቃሴ ነው። እውነት ለመናገር እስከዛሬ ከተደረገው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሁሉ የላቀ ነው» ሲሉ ተናግረዋል። ትራምፕ በዚሁ ንግግራቸው «ድንበሮችን» እና ሌሎች ጉዳዮችንም እንደሚያስተካክሉ ቃል ገብተዋል። «ጠንካራ፣ አስተማማኝ እና የበለፀገች አሜሪካን» ለህዝቡ ለማቅረብ እንደሚሠሩም አመልክተዋል። የሃሪስ ዘመቻ ባለሥልጣን በበኩላቸው ዋሽንግተን ውስጥ ለተሰበሰቡት ደጋፊዎች ባደረጉት ንግግር ሃሪስ  ንግግር የሚያደርጉት ረቡዕ ጠዋት መሆኑን ገልጸዋል።

ትራምፕ እስካሁን 18 ግዛቶችን ሲያሸንፉ፣ ሃሪስ ዘጠኝ ግዛቶችን ማሸነፋቸውን አረጋግጠዋል

ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የተካሄደው እ.አ.አ የ2024 ሀገር አቀፍ ምርጫ ውጤት በተለያዩ ግዛቶች መታወቅ ጀምሯል። እስካሁን ባለው ውጤት የሪፐብሊካኑ ፕሬዝዳንታዊ እ
የአሜሪካ ድምፅ

ትራምፕ እስካሁን 18 ግዛቶችን ሲያሸንፉ፣ ሃሪስ ዘጠኝ ግዛቶችን ማሸነፋቸውን አረጋግጠዋል

ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የተካሄደው እ.አ.አ የ2024 ሀገር አቀፍ ምርጫ ውጤት በተለያዩ ግዛቶች መታወቅ ጀምሯል። እስካሁን ባለው ውጤት የሪፐብሊካኑ ፕሬዝዳንታዊ እጩ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 18 ግዛቶች ውስጥ ማሸነፋቸውን ሲያረጋግጡ፣ የሪፐብሊካን እጩ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ዘጠኝ ግዛቶችን አሸንፈዋል።  ትራምፕ ማሸነፋቸውን ያረጋገጡባቸው ግዛቶች በተለምዶ ለሪፐሊካን ፓርቲ ድምፃቸውን በመስጠት የሚታወቁት ኢንዲያና፣ ኬንታኪ፣ ዌስት ቨርጂኒያ፣ አላባማ፣ ኦክላሃማ፣ ሚሲሲፒ፣ ቴኔሲ፣ ፍሎሪዳ፣ ደቡብ ካሮላይና፣ አርካንሳ፣ ነብራስካ፣ ሰሜን ዳኮታ፣ ደቡብ ዳኮታ፣ ሉዚያና፣ ዋዮሚንግ፣ ኦሃዮ፣ ቴክሳስ እና ሚዙሪ ናቸው።  ሃሪስ ማሸነፋቸውን ያረጋገጡባቸው በተለምዶ ዲሞክራትን በመምረጥ የሚታወቁት ቨርሞንት፣ ማሳቹሴትስ፣ ሜሪላንድ፣ ከነቲኬት፣ ሮድ አይላንድ፣ ኒው ጀርሲ፣ ዴላዌር፣ ኤሊኖስ እና ኒው ዮርክ ግዛቶች ናቸው።  በዘንድሮ ምርጫ ከፍተኛ ፉክክር እንደሚካሄድባቸው እና የምርጫውን ውጤት ለመለየት ወሳኝ ናቸው ተብለው የሚጠበቁት አሪዞና፣ ጆርጂያ፣ ሚቺጋን፣ ኔቫዳ፣ ሰሜን ካሮላይና፣ ፔንሴልቫኒያ እና ዊስኮንሰን ግዛቶች ውጤት እስካሁን አልታወቀም። 

በአሜሪካ የምርጫ ጣቢያዎች በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ይዘጋሉ

በኢንዲያና እና ኬንተኪ የሚገኙ የተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች በምሥራቅ የሃገሪቱ አቆጣጠር ከምሽቱ 6 ሰዓት ቀድመው ከተዘጉት ውስጥ ሲሆኑ፤ የተቀሩት ደግሞ ከምሽ
የአሜሪካ ድምፅ

በአሜሪካ የምርጫ ጣቢያዎች በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ይዘጋሉ

በኢንዲያና እና ኬንተኪ የሚገኙ የተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች በምሥራቅ የሃገሪቱ አቆጣጠር ከምሽቱ 6 ሰዓት ቀድመው ከተዘጉት ውስጥ ሲሆኑ፤ የተቀሩት ደግሞ ከምሽቱ 7 ሰዓት ተዘግተዋል። 25 የሚሆኑ ግዛቶች ደግሞ ከምሽቱ 8 ሰዓት እንደሚዘጉ ይጠበቃል። በአላስካ ግዛት የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ ከእኩለ ሌሊት በኋላ 1 ሰዓት ላይ ይዘጋሉ። በበርካታዎቹ ግዛቶች የምርጫውን ውጤት ለማወቅ ሰዓታት፣ ምናልባትም ቀናት ሊወስድ ይችላል። ሃሰተኛ የቦምብ ጥቃት ዛቻዎች በሚሺጋን፣ ውስከንስን፣ እና ጆርጂያ መሰማታቸውን የፌዴራል ምርመራ ቢሮ ያስታወቀ ሲሆን፣ የአብዛኛዎቹ ዛቻዎች መነሻ ከሩሲያ የተላኩ ኢሜይሎች መሆናቸውንም ቢሮው ገልጿል። በጆርጂያ የሚገኙ ቢያንስ ሁለት ጣቢያዎች ዛቻውን ተከትሎ ሰዎች ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል። የግዛቲቱ ዋና ፀሃፊ ሩሲያ ጣልቃ ገብታለች ሲሉ ከሰዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ምርጫዋን ከጣልቃ ገብ ጥቃት የተጠበቀ  ለማድረግ ተዘጋጅታለች

በደቡብ ምሥራቅ አሜሪካ በሕዝብ ስብጥራቸው ከሚታወቁት አውራጃዎች መካከል አንዷ የሆነችውና በጆርጂያ የምትገኘው ጉወኔት አውራጃ፣ በአሜሪካ ምርጫ ምሽት ውጤ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩናይትድ ስቴትስ ምርጫዋን ከጣልቃ ገብ ጥቃት የተጠበቀ  ለማድረግ ተዘጋጅታለች

በደቡብ ምሥራቅ አሜሪካ በሕዝብ ስብጥራቸው ከሚታወቁት አውራጃዎች መካከል አንዷ የሆነችውና በጆርጂያ የምትገኘው ጉወኔት አውራጃ፣ በአሜሪካ ምርጫ ምሽት ውጤታቸውን ቀድመው ከሚልኩት አውራጃዎች አንዷ ነች፡፡ የቪኦኤ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ዋና ዘጋቢ ስቲቭ ኽረማን ወደ ሎውረንስ፣ ጆርጂያ ተጉዙና የድምጽ ቆጠራ ሂደቱን ታዝቦ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የዩናይትድ ስቴትሱ የምርጫ ጣቢያ የቦምብ ጥቃት ስጋት ምንጭ ሩሲያ ናት ተባለ

በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የሚሰነዘሩ ተከታታይ የቦምብ ጥቃት ዛቻዎች ከሩሲያ እንደሚመጡ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌደራል እና የግዛት ባለስልጣ
የአሜሪካ ድምፅ

የዩናይትድ ስቴትሱ የምርጫ ጣቢያ የቦምብ ጥቃት ስጋት ምንጭ ሩሲያ ናት ተባለ

በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የሚሰነዘሩ ተከታታይ የቦምብ ጥቃት ዛቻዎች ከሩሲያ እንደሚመጡ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌደራል እና የግዛት ባለስልጣናት አስታወቁ። ማክሰኞ ጠዋት የደረሰው የመጀመሪያው የቦምብ ዛቻ በጆርጂያ ግዛት፣ ደቡብ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኙ አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ለተወሰነ ጊዜ ድምፅ መስጠት እንዲቆም አስገድዷል። የግዛቱ ባለስልጣናት ግን ዛቻው እውነተኛ መሆኑን በማረጋገጣቸው ድምፅ መስጠቱ ቀጥሏል። የጆርጂያ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ብራድ ራፌንስበርገር ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል «ምንጩን ለይተን ከሩሲያ መሆኑን አውቀናል» ብለዋል። ራፌንስበርገር አክለው «የሆነ ተንኮል ለመስራት እየሞከሩ ነው። ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና ትክክለና ምርጫ እንድናደርግ የማይፈልጉ ይመስላል» ያሉ ሲሆን «እርስ በርሳችን እንድንጋጭ የሚያደርጉ ይመስላቸዋል። ያንን እንደድል ሊቆጥሩት ይችላሉ» ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስን ምርጫ ለማደናቀፍ የሚደረገው ጥረት ግን ከዛም የሰፋ ይመስላል። የአሜሪካ ፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) ዛሬ ማክሰኞ ባወጣም መግለጫ «በበርካታ ግዛቶች በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የቦምብ ስጋት መኖሩን እናውቃለን» ያለ ሲሆን አብዛኞቹ ዛቻዎች ከሩሲያ ኢሜይሎች እንደመጡ አመልክቷል። አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣንም፣ ከጆሪጂያ በተጨማሪ በሚቺጋን እና በዊስኮንሰን በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ላይም የቦምብ ጥቃት ዛቻዎች እንደተሰነዘሩ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።  ኤፍ ቢ አይ በበኩሉ «ሁሉም ዛቻዎች እውነተኛ አለመሆናቸው ተረጋግጧል» ያለ ሲሆን፣ በምርጫዎች ላይ ለሚሰነዘሩ ዛቻዎች ምላሽ ለመስጠት እና አሜሪካኖች የመምረጥ መብታቸውን ሲያረጋግጡ ደህንነታቸውን ለመጠበቅ፣ ከግዛቶች እና የአካባቢ ሕግ አስከባሪዎች ጋር በቅርበት እንደሚሰራም አረጋግጧል። ማክሰኞ ጠዋት አብዛኛው የአሜሪካ መራጭ ድምፁን ሊሰጥ በተዘጋጀበት ወቅት፣ የቢሮውን ተመሳሳይ ስያሜ በመጠቀም ሀሰተኛ ትርክት ለማሰራጨት የተደረጉ ሁለት ሙከራዎች መኖራቸውን ኤፍ ቢ አይ አስጠንቅቆ ነበር። እንደምሳሌም፣ የሽብር ጥቃት ዛቻ እየጨመረ በመምጣቱ አሜሪካውያን በርቀት ድምፅ እንዲሰጡ የሚያበረታታ ሀሰተኛ ዜና መሰራጨቱን ጠቁሟል። በተጨማሪም በአሜሪካ የሚገኙ አምስት እስር ቤቶች በድምፅ ስርቆት ውስጥ ተሳትፈዋል የሚል በቪዲዮ የተቀነባበረ  ሀሰተኛ ዜና በማህበራዊ ሚዲያዎች መሰራጨታቸውንም ጠቁሟል።  ቪድዮዎቹን ማን እንዳሰራጨ ግን ኤፍ ቢ አይ አልገለጸም። ሆኖም ከዚህ በፊት የድምፅ አሰጣጥ ጉድለቶችን አስመልክቶ በተመሳሳይ ሁኔታ በሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች ሩሲያ እጇ እንዳለበት ቢገለፅም፣ ሩሲያ ክሱን አትቀበለውም።

አሜሪካ ምርጫ ላይ ነች - የመራጮች አስተያየት

በሚልየን የሚቆጠሩ የአሜሪካ መራጮች፣” ቀጣይ የአሜሪካ መሪ የሚሆኑት ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ወይም የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ?” የሚለውን  
የአሜሪካ ድምፅ

አሜሪካ ምርጫ ላይ ነች - የመራጮች አስተያየት

በሚልየን የሚቆጠሩ የአሜሪካ መራጮች፣” ቀጣይ የአሜሪካ መሪ የሚሆኑት ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ወይም የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ?” የሚለውን  ለመወሰን ዛሬ ማክሰኞ ድምፅ በመስጠት ላይ ናቸው። የተወሰኑትን አስተያየት ጠይቀናል ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በሰሜን ሸዋ የመስጅድ ኢማም ታግተዉ መገደላቸው ተነገረ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከሳምንታት በፊት በታጣቂዎች ታግተው ነበር የተባሉ የኃይማኖት አባት መገደላቸው ተነገረ። በሰሜን ሸዋ ዞ
የአሜሪካ ድምፅ

በሰሜን ሸዋ የመስጅድ ኢማም ታግተዉ መገደላቸው ተነገረ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከሳምንታት በፊት በታጣቂዎች ታግተው ነበር የተባሉ የኃይማኖት አባት መገደላቸው ተነገረ። በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ አረቦ መስጅድ ኢማም ኾነው ሲያገለግሉ ነበሩ የተባሉት ሼክ መከዬ ሰይድ ለሳምንታት ታግተዉ ከተወሰዱ በኋላ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ አስከሬናቸው መምጣቱንና ሥርዓተ ቀብራቸው መፈፀሙ ተነግሯል። የደራ ወረዳ አስተዳደር ድርጊቱ መፈፀሙን አረጋግጧል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንም ስለግድያዉ መረጃ እንደደረሰዉ አስታውቋል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች አማካሪ መኾናቸውን የተናገሩት ጅሬኛ ጉደታ፣ ታጣቂዎቻቸው ጥቃቱን እንዳልፈጸሙ ተናግረዋል።

በሰሜን ሸዋ ዞን የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ 48 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ

በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ወጫሌ ወረዳ፣ ልዩ ስሙ ካራ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ፈጸሙት በተባለ ጥ
የአሜሪካ ድምፅ

በሰሜን ሸዋ ዞን የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ 48 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ

በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ወጫሌ ወረዳ፣ ልዩ ስሙ ካራ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ፈጸሙት በተባለ ጥቃት ፣የወረዳውን አስተዳዳሪ፣ እንደዚሁም የአካባቢውን ሚሊሻዎችና ፖሊሶች ጨምሮ 48 ሰዎች መገደላቸውን የሚገልጽ መረጃ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ የጅማ ቅንጫፍ ኃላፊ አቶ በዳሳ ለሜሳ ተቋማቸው ሁኔታውን እያጣራ መሆኑንም ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል። የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪ የአቶ ንጉሱ ኮሩ ታናሽ ወንድም፣ አቶ ሞስሳ ኮሩ ጥቅምት 22 ቀን 2017ዓ.ም. በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጣቂዎች መካከል ውጊያ እንደነበር ጠቅሰው፣ ወንድማቸው የተገደሉት ተጨማሪ ኃይል ይዘው ወደ አካባቢ እያቀኑ ባሉበት ሰዓት መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አማካሪ መኾናቸውን የተናገሩት፣ አቶ ጅሬኛ ጉደታ ታጣቂዎቻቸው ጥቃት መፈጸማቸውን አረጋግጠዋል። ከሰሜን ሸዋ ዞን፣ ከወጫሌ ወረዳ እና ከክልሉ መንግሥት ባለሥልጣናት ማብራሪያ ለማግኝነት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

VOA60 America - America votes for next president

Millions of U.S. voters cast ballots Tuesday as they decide if Vice President Kamala Harris or former president Donald Trump will be the country’s next leader. Ahead of Election Day more than 81 million Americans cast early ballots, either in person at poll
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - America votes for next president

Millions of U.S. voters cast ballots Tuesday as they decide if Vice President Kamala Harris or former president Donald Trump will be the country’s next leader. Ahead of Election Day more than 81 million Americans cast early ballots, either in person at polling stations or by mail.

VOA60 Africa - Sudan: UN says some 135,000 people displaced in 10 days from Al Jazirah state

The United Nations said this week that some 135,000 people were displaced in just 10 days from the Al Jazirah state in a series of revenge attacks by the paramilitary Rapid Support Forces, with activists reporting violent raids over the past two weeks affecti
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Sudan: UN says some 135,000 people displaced in 10 days from Al Jazirah state

The United Nations said this week that some 135,000 people were displaced in just 10 days from the Al Jazirah state in a series of revenge attacks by the paramilitary Rapid Support Forces, with activists reporting violent raids over the past two weeks affecting at least 65 villages and towns.

VOA60 World - America chooses between former president Donald Trump, Vice President Kamala Harris

Both candidates projected confidence in their own campaigns. Survey polls heading into Election Day indicated a tight race.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - America chooses between former president Donald Trump, Vice President Kamala Harris

Both candidates projected confidence in their own campaigns. Survey polls heading into Election Day indicated a tight race.

ከ50 በላይ ሀገራት ለእስራኤል የመሣሪያ ሽያጭና አቅርቦትን እንዲያስቆም ተመድን ጠየቁ

በሲቪሎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት እና የአከባቢው አለመረጋጋት አሳሳቢ ነው ያሉ ከ50 በላይ ሀገራት ለእስራኤል የሚደረገው የጦር መሣሪያ ሽያጭ በአስቸኳይ እንዲቆ
የአሜሪካ ድምፅ

ከ50 በላይ ሀገራት ለእስራኤል የመሣሪያ ሽያጭና አቅርቦትን እንዲያስቆም ተመድን ጠየቁ

በሲቪሎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት እና የአከባቢው አለመረጋጋት አሳሳቢ ነው ያሉ ከ50 በላይ ሀገራት ለእስራኤል የሚደረገው የጦር መሣሪያ ሽያጭ በአስቸኳይ እንዲቆም ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደብዳቤ ልከዋል፡፡ በቱርክ አስተባባሪነት ለሁለት የተባበሩ መንግሥታት ድርጅት አካላት እና ለድርጅቱ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ የተላከውና ትላንት ሰኞ ማምሻው ላይ አሶሴይት ፕሬስ እጅ የገባው የሀገራቱ ደብዳቤ፣ “በጋዛ እና በሌሎች የፍልስጤም ግዛቶች እንዲሁም በሊባኖስ እና በቀሪው የመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ያለው ዓለም አቀፍ ህጉን የጣሰ ነው” ሲል እስራኤልን ከሷል፡፡ ሀገራቱ በደብዳቤያቸው " ዓለም አቀፍ ህግን በመጣስ እስራኤል እየፈፀመች ባለችው ድርጊት ሳቢያ ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረው አብዛኞቹ ህጻናት እና ሴቶች የሆኑበት አስደንጋጭ የሰላማዊ ሰዎች እልቂት፣ ህሊና የማይቀበለውና የማይታለፍ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ በአካባቢ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ከመጠን ያለፈ ሰብአዊ ስቃይ እና ክልላዊ አለመረጋጋት ለማስቆም አፋጣኝ ርምጃ መውሰድ አለብን” ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ “የተባበሩት መንግሥታት ይህንን ቀውስ ለማስቆም፣ አስቸኳይ የተኩስ ማቆም ማወጅና፣ የሰላማዊ ሰዎችን ህይወት የሚታደግ ርምጃዎችን መውሰድ፣ ተጠያቂነት ማረጋገጥና ለእስራኤል የሚተላለፈው መሣሪያ እንዲቆም ግልጽ ጥያቄ ማቅረብ አለበት ሲል” የሀገራቱ ደብዳቤ ጠይቋል፡፡ በተባበሩት መንግስታት የእስራኤል አምባሳደር ዳኒ ዳኖን የቱርክን ተሳትፎ ውድቅ በማድረግ “በጥፋት ኃይሎች ድጋፍ ግጭትን ለመቀስቀስ ሙከራ ከምታደርግ ሀገር ምን ልንጠብቅ እንችላለን” ብለዋል፡፡ “የእስራኤል ጥቅሞች ከየትኛው ፖለቲካዊ እና ወታደዊ ጥቃት ለመከላከል መታገላችንን እንቀጥላለን “ሲሉም አምባሳደሩ ሀገራቸው ራሷን ለመከላከል ያላትን አቋም ገልጸዋል። ደብዳቤውን ከፈረሙት መካከል የአረብ ሊግ ፣ የእስላማዊ ኮርፖሬሽን፣ ኖርዌ እና ደቡብ አፍሪካ ይገኙበታል፡፡ ደቡብ አፍሪካ በፍልስጤማውያን ላይ የዘር ማጥፋት ተፈጽሟል ስትል እስራኤልን በመክሰስ ጉዳዩን ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ፊት ማቅረቧ ይታወሳል፡፡ በጋዛ የእስራኤል ሀማስ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ከ43ሺ በላይ ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጤም የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ሴቶችና ህጻናት መሆናቸውን ባለሥልጣናቱ ገልጸዋል፡፡ ጦርነቱ የተጀመረው እኤአ ጥቅምት 7 2023 ወደ እስራኤል ዘልቀው የገቡ የሃማስ ታጣቂዎች አብዛኞቹ ሰላማዊ የሆኑ 1ሺ200 ሰዎችን ከገደሉና 250 የሚሆኑትን አግተው ከወሰዱ በኋላ ነው፡፡

ኢራን ሞት የተፈረደበት እስረኛ ከመገደሉ በፊት ሞቶ መገኘቱን አስታወቀች

የሞት ፍርድ የተፈደበት ኢራናዊው-ጀርመናዊው ጃምሺድ ሻርማህድ የሞት ቅጣት ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት አስድሞ ሞቶ መገኘቱን አንድ የኢራን ባለሥልጣን ዛሬ ማክሰኞ
የአሜሪካ ድምፅ

ኢራን ሞት የተፈረደበት እስረኛ ከመገደሉ በፊት ሞቶ መገኘቱን አስታወቀች

የሞት ፍርድ የተፈደበት ኢራናዊው-ጀርመናዊው ጃምሺድ ሻርማህድ የሞት ቅጣት ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት አስድሞ ሞቶ መገኘቱን አንድ የኢራን ባለሥልጣን ዛሬ ማክሰኞ አስታወቁ፡፡ ባለሥልጣኑ አስተያየት የኢራን ባለሥልጣናት ቀደም ሲል እኤአ ጥቅምት 28 የሞት ቅጣቱ የተፈጸመበት መሆኑን ካስታወቁበት መግለጫ ጋር የሚቃረን መሆኑ ተገልጿል፡፡ የፍርድ ቤቱ ባለሥልጣኑ አሽጋር ጃሃንጊር አስተያየት የተሰማው ጀርመን የሞት ፍርዱን በመቃወም በበርሊን የሚገኘውን የኢራን ኢምባሲ ብቻ በመተው ሶስት የኢራን ቆንስላ ጽ/ቤቶችን መዝጋቷን ካስታወቀች በኋላ ነው፡፡ ባለሥልጣኑ “ሻርማህድ ሞት የተረፈደበት ነው ቅጣቱ ተፈጻሚ ሊሆን በዝግጅት ላይ ነበር፡፡ ከዚያ በፊት ግን ሞቶ ተገኘ” ሲሉ መናገራቸውን የፍርድ ቤቱ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡ ዝርዝር አሟሟቱ አልተገለጸም፡፡ ጀርመን የባለስልጣኑን መግለጫ በመቃወም የሻርማህድ ግድያ አስቀድሞ የተፈጸመ መሆኑን በመጥቀስ ኢራንን ተጠያቂ አድርጋለች፡፡ አስክሬኑ ለቤተሰቡ እንዲሰጥ ሲያግባቡ የቆዩት የጀርመን ባለሥልጣናት “የሻርማህድ ሞት በኢራን በኩል አሁን የተረጋገጠ” ሆኗል ብለዋል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ የመኖሪያ ፍቃድ ያለው ሻርማህድ እኤአ በ2023 በኢራን እስላማዊ ህግጋት ውስጥ እንደ ትልቅ ወንጀል ነው በተባለውና የአምላክን ትዕዛዝ መተላለፍ በሚያመልከተው «ምድራዊ ኃጢአት» ክስ የሞት ቅጣት እንደተፈረደበት ተገልጿል፡ የ69 ዓመቱ ሻርማህድ ኢራን ውስጥ የዘውድ ሥርዐት ደጋፊ ቡድንን በመምራት እ.ኤ.አ.በ2008 የ12 ሰዎች ሞትና 100 ሰዎች የቆሰሉበትን አደጋ ባስተከለው የቦምብ ፍንዳታ እና እንዲሁም በሀገሪቱ ውስጥ ሌሎች ጥቃቶችን በማቀድ መከሰሱ ይታወሳል፡፡

በረሃብ ላይ የሚያተኩር ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው

ዘመናዊ የግብርና ዘዴ እና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን መግታት ረሃብን ለማጥፋት ቁልፍ እንደሆኑ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ። ጠ
የአሜሪካ ድምፅ

በረሃብ ላይ የሚያተኩር ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው

ዘመናዊ የግብርና ዘዴ እና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን መግታት ረሃብን ለማጥፋት ቁልፍ እንደሆኑ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ምኒስትሩ አዲስ አበባ ለሶስት ቀናት በሚቆየው “ከረሃብ ነጻ ዓለም” በተሰኘ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በዓለም የሚታየውን የምግብ ችግር ለመቅረፍ ፈጠራ የታከለበት መፍትሄ እንደሚያሻም ጠቁመዋል። “ዘላቂነት ያለው አሰራር፣ የተሻሻለ ዘመናዊ የእርሻ ዘዴ፣ የግርብና ግብአት አቅርቦት ማስፋፋት እና የአየር ንብረት ለውጥ ችግርን መቅረፍ ለምርታማነት መሻሻል አስፈላጊ ናቸው” ሲሉ ጠቅላይ ምኒስትሩ በ'X' ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መልዕክታቸውን አስፍረዋል። የዓለም መሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ እና ተሟጋቾች ፈጠራ የታከለበት መፍትሄ ላይ ውይይት እንዲያደርጉና በአንድነት እንዲሰሩ በማድረግ ረሃብን ለማጥፋትና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ፍሬ እንዲያፈራ ማድረግ ይቻላል ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ከተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት እና ከአፍሪክ ኅብረት ኮሚሽን ጋራ በመተባበር ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ 1ሺሕ 500 የሚሆኑ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ ከተባበሩት መንግስታት የተገኘው መረጃ አመልክቷል።

በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ለምን በማክሰኞ ቀን ይካሄዳል?

ለመሆኑ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ  ሁሌም ለምን በማክሰኞ ቀን እንደሚደረግ አስበው ያውቃሉ? ይህ ፖለቲካዊ ባህል ዩናይትድ ስቴትስ አሁን ካላት ገጽ
የአሜሪካ ድምፅ

በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ለምን በማክሰኞ ቀን ይካሄዳል?

ለመሆኑ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ  ሁሌም ለምን በማክሰኞ ቀን እንደሚደረግ አስበው ያውቃሉ? ይህ ፖለቲካዊ ባህል ዩናይትድ ስቴትስ አሁን ካላት ገጽታ በተለየ መልኩ በነበረችበት ከሁለት መቶ ዓመት በፊት የጀመረ ነው፡፡ ተከታዩ ዘገባ መልሱን ይዟል፡፡

ጉወኔት አውራጃ ለምን የአሜሪካን ምርጫ ውጤት ከሚወስኑት ሥፍራዎች አንዷ ሆነች?

በደቡብ ምሥራቅ አሜሪካ በሕዝብ ስብጥራቸው ከሚታወቁት አውራጃዎች መካከል አንዷ የሆነችውና በጆርጂያ የምትገኘው ጉወኔት አውራጃ፣ በአሜሪካ ምርጫ ምሽት ውጤ
የአሜሪካ ድምፅ

ጉወኔት አውራጃ ለምን የአሜሪካን ምርጫ ውጤት ከሚወስኑት ሥፍራዎች አንዷ ሆነች?

በደቡብ ምሥራቅ አሜሪካ በሕዝብ ስብጥራቸው ከሚታወቁት አውራጃዎች መካከል አንዷ የሆነችውና በጆርጂያ የምትገኘው ጉወኔት አውራጃ፣ በአሜሪካ ምርጫ ምሽት ውጤታቸውን ቀድመው ከሚልኩት አውራጃዎች አንዷ ነች፡፡ የቪኦኤ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ዋና ዘጋቢ ስቲቭ ኽረማን ወደ ሎውረንስ፣ ጆርጂያ ተጉዙና የድምጽ ቆጠራ ሂደቱን ታዝቦ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

ከውጭ ሀገር ቤተሰቦች የተወለዱትና በፕሬዝደንታዊ እጩነት ታሪክ የሠሩት ካምላ ሃሪስ

እጅግ  "የለውጥ አቀንቃኝ ወይም ሊበራል ከሆነ እና ሰፊ  የሕዝብ ስብጥር ካለው የካሊፎርኒያ አካባቢ የተነሱት ካምላ ሃሪስ በብርቱ የሕግ አስከባሪነት እና ተራማ
የአሜሪካ ድምፅ

ከውጭ ሀገር ቤተሰቦች የተወለዱትና በፕሬዝደንታዊ እጩነት ታሪክ የሠሩት ካምላ ሃሪስ

እጅግ  "የለውጥ አቀንቃኝ ወይም ሊበራል ከሆነ እና ሰፊ  የሕዝብ ስብጥር ካለው የካሊፎርኒያ አካባቢ የተነሱት ካምላ ሃሪስ በብርቱ የሕግ አስከባሪነት እና ተራማጅ የለውጥ አቀንቃኝነት አልፈው  ለዲሞክራቲክ ፓርቲው ፕሬዚደንታዊ እጩነት በቅተዋል፡፡ የቪኦኤው ማት ዲብል ከካሊፎርኒያ ኦክላንድ ከተማ የምክትል ፕሬዚደንት ሃሪስን የፖለቲካ ጉዞዎች ያስቃኘበትን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ዶናልድ ትረምፕ ወደ ፕሬዝደንትነት የተጓዙበት ያልተለመደ መንገድ

የቀድሞው፣ ምናልባትም መጪው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ክፍፍሉ እየጨመረ ባለበት ሃገር ውስጥ፣ የሪፐብሊካን ፓርቲውን ቅርጽ ለመቀየር የፈጀባቸ
የአሜሪካ ድምፅ

ዶናልድ ትረምፕ ወደ ፕሬዝደንትነት የተጓዙበት ያልተለመደ መንገድ

የቀድሞው፣ ምናልባትም መጪው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ክፍፍሉ እየጨመረ ባለበት ሃገር ውስጥ፣ የሪፐብሊካን ፓርቲውን ቅርጽ ለመቀየር የፈጀባቸው ከዘጠኝ ዓመት ያህል ነው። ትረምፕ ወደ ፖለቲካ ሥልጣን ለመመለስ የሚያደርጉትን ታሪካዊ ሂደት የቪኦኤዋ ቲና ትሪን ተመልክታዋለች፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

ቲም ዋልዝ ማናቸው?

'የነብራስካው መልካም ሰው' የገጠሪቱን አሜሪካ ድምጽ ያገኙ ይሆን? ቲም ዋልዝ ከካመላ ሄሪስ ጎን ሆነው ለምክትል ፕሬዝደንትነት እንዲወዳደሩ ከመታጨታቸው በፊ
የአሜሪካ ድምፅ

ቲም ዋልዝ ማናቸው?

'የነብራስካው መልካም ሰው' የገጠሪቱን አሜሪካ ድምጽ ያገኙ ይሆን? ቲም ዋልዝ ከካመላ ሄሪስ ጎን ሆነው ለምክትል ፕሬዝደንትነት እንዲወዳደሩ ከመታጨታቸው በፊት፣ ለሚንሶታ አገረ ገዢነት ሁለት ጊዜ ተመርጠዋል። በምርጫ ዘመቻ ጉዟቸው ላይ፤ በነብራስካ ማደጋቸው፣ እንዴት ስብእናቸውን እንደቀረጸውና፣ አሁን ለታጩበት ሥራም ሆነ ለሃገረ ገዢነት ሃላፊነት ለመብቃት እንዴት እንደረዳቸው ይናገራሉ። የነብራስካ ሰዎች ስለ ቲም ዋልዝ ምን እንደሚያስታውሱ እንዲሁም አሁን ስለ እርሳቸው ምን እንደሚሰማቸው ለማወቅ የቪኦኤዋ ናታሻ ሞዝጎቫያ ግዛቲቱን ጎብኝታ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የሪፐብሊካኑ እጩ ምክትል ፕሬዘዳንት ተወዳዳሪ ጄዲ ቫንስ ማናቸው?

የሪፐብሊካኑ እጩ ምክትል ፕሬዘዳንት ተወዳዳሪ ጄዲ ቫንስ የሕይወት ታሪክ “የአንድ የትንሽ ከተማ ብላቴና መልካም ሲገጥመው” የሚለውን ሀረግ ሊጠቃለል ይችላል
የአሜሪካ ድምፅ

የሪፐብሊካኑ እጩ ምክትል ፕሬዘዳንት ተወዳዳሪ ጄዲ ቫንስ ማናቸው?

የሪፐብሊካኑ እጩ ምክትል ፕሬዘዳንት ተወዳዳሪ ጄዲ ቫንስ የሕይወት ታሪክ “የአንድ የትንሽ ከተማ ብላቴና መልካም ሲገጥመው” የሚለውን ሀረግ ሊጠቃለል ይችላል፡፡ ጄዲ በተራራማው አፓላችን ነው ያደጉት፤ በኋላም አይቪ ሊግ ተብለው ከሚታወቁት ልዩ የሆነ ክብር ካላቸው ዩኒቨርስቲዎች መካከል በዬል ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ በዬል የህግ ትምህርት ቤት ቆይታቸውም ከአሁኗ ባለቤታቸው ኡሻ ቺሉኩሪ ጋር ሊተዋወቁ ችለዋል፡፡ ጄዲ ቫንስ ውልደታቸው በሚድል ታውን ኦሃዮ ቢሆንም፤  ነገር ግን ቤቴ ብለው የሚጠሩት ጃክሰን ኬንተኪን ነው፡፡ በልጅነት ህይወታቸው ብሎም በአስተሳሰባቸው ላይ ሚማው ብለው የሚጠሯቸው ሴት አያታቸው ትልቅ ሚና አላቸው፡፡ የጄዲ ቫንስ የመጀመሪያ እውቅና የመነጨው በጎርጎሮሳዊያኑ 2016 በታተመው የአሜሪካ የሰራተኛውን መደብ ሕይወት በሚያስቃኘው ‘ሂልቢሊ ኤልጊ’ ብለው በጻፉት እና በኋላም ወደ ፊልምነት በተቀየረው መጽሓፋቸው ነው፡፡ በፖለቲካ ርዕዮተ ዓለማቸው  ቀድሞ ትራምፕን ያወግዙ የነበሩት ጄዲ ቫንስ አሁን ላይ የትግል አጋራቸው በመሆን የጎሮጎርሳዊያኑ 2024 ምርጫን ለማሸነፍ እየሰሩ ነው፡፡ መጭው የአውሮፓውያኑ ኅዳር አምስት በሚድረገው ምርጫ ካሸነፉም በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ወጣት ከሆኑ ምክትል ፕሬዘዳንቶች መካከል አንዱ በመሆን በታሪክ ሊመዘገቡ ይችላሉ፡፡  የአሜሪካ ድምጿ ከፍተኛ ዘጋቢ ኬሮላይን ፔርሱቲን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የአሜሪካ መራጮች «ከፍ ያለ እና ተለዋዋጭ» የደህንነት ሥጋቶች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል

ነገ ማክሰኞ በዩናይትድ ስቴትስ የሚካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በሀገሪቱ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማያውቅ እንደሚሆን ተነግሮለታል፡፡ የሀገሪቱ የጸጥታ እና የደህ
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ መራጮች «ከፍ ያለ እና ተለዋዋጭ» የደህንነት ሥጋቶች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል

ነገ ማክሰኞ በዩናይትድ ስቴትስ የሚካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በሀገሪቱ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማያውቅ እንደሚሆን ተነግሮለታል፡፡ የሀገሪቱ የጸጥታ እና የደህንነት ባለስልጣናትም መራጮች ድምጻቸውን የሚሰጡት ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጪ የተቀኑ አደጋዎች እጅግ ከፍተኛ እና ተለዋዋጭ የሆነ የስጋት ድባብ በፈጠሩበት ሁኔታ እንደሆነ ይናገራሉ። የብሔራዊ ጸጥታ ጉዳዮች ዘጋቢ ጄፍ ሴልድን ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የስደተኞች ጉዳይ ለትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካዊ መራጮች ቁልፍ ጉዳይ ነው

ከሁለት ቀናት በኃላ በዩናይትድ ስቴትስ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መራጮች ትኩረት ከሚሰጡባቸው ቁልፍ ፖሊሲዎች አንዱ የስደተኞች ጉዳይ ነው። የአሜሪካ ድ
የአሜሪካ ድምፅ

የስደተኞች ጉዳይ ለትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካዊ መራጮች ቁልፍ ጉዳይ ነው

ከሁለት ቀናት በኃላ በዩናይትድ ስቴትስ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መራጮች ትኩረት ከሚሰጡባቸው ቁልፍ ፖሊሲዎች አንዱ የስደተኞች ጉዳይ ነው። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊዎች ወደ አሜሪካ የሚገቡ ሕገወጥ ስደተኞች ቁጥር የሚያሳስባቸው ሲሆን፣ የዲሞክራት ፓርቲ ደጋፊዎች ደግሞ ስደተኞች ሕጋዊ በሆነ መንገድ የሚኖሩበት መንገድ እንዲመቻች ይፈልጋሉ።  (ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ዘገባ ያገኛሉ)

ቆይታ ከኤፓክ ተወካይ ጋራ - በዩ ኤስ ምርጫ ኢትዮጵያ - አሜሪካውያን ድምጽ

«የተለያዩ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ማኅበረሰብ አባላት ለዘንድሮው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለውሳኔያቸው ምን ዓይነት ጉዳዮችን መሰረት ያደር
የአሜሪካ ድምፅ

ቆይታ ከኤፓክ ተወካይ ጋራ - በዩ ኤስ ምርጫ ኢትዮጵያ - አሜሪካውያን ድምጽ

«የተለያዩ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ማኅበረሰብ አባላት ለዘንድሮው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለውሳኔያቸው ምን ዓይነት ጉዳዮችን መሰረት ያደርጉ ይሆን?» ችችችችበሚል ላነሳነው ጥያቄ፣ ማብራሪያ እንዲሰጡን የአሜሪካ-ኢትዮጵያውያን የሕዝብ ጉዳዮች ኮሚቴ (ኤፓክ) ዋና ጸሐፊ አቶ ዮም ፍሰሃን ጋብዘናል። ከተቋቋመ ሦስት ዓመት ተኩል የሆነው ኤፓክ፣ ሁለቱ ዕጩዎች በየበኩላቸው ከላኳቸው አራት የምርጫ ዘመቻ ተወካዮች ጋራ አባሎቻቸው ውይይት እንዲያደርጉ በቅርቡ መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። አቶ ዮም ማኅበራቸው ስላሰናዳው ስለዚህ መድረክም አስረድተውናል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Get more results via ClueGoal