ትረምፕ የመጀመሪያዋን ሴት የኋይት ሃውስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሰየሙ
newsare.net
ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለድል ያበቃቸውን የምርጫ ቅስቅሳ ዘመቻቸውን በዋና ሥራ አስኪያጅነት የመሩትን ሱዚ ዊልስን ኋይት ሃውስ ጽ/ቤት ኃላፊ አድርትረምፕ የመጀመሪያዋን ሴት የኋይት ሃውስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሰየሙ
ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለድል ያበቃቸውን የምርጫ ቅስቅሳ ዘመቻቸውን በዋና ሥራ አስኪያጅነት የመሩትን ሱዚ ዊልስን ኋይት ሃውስ ጽ/ቤት ኃላፊ አድርገው ሰይሟቸዋል፡፡ ሱዚ ዊልሰን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ተደማጭነት ያለውን ቦታ እንዲመሩ የተመደቡ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነዋል። ዊልሰን ትረምፕ ሥረዓት ያለው የምርጫ ቅስቀሳ እንዲያካሂዱ በማድረግ ባማረ ውጤት የተጠናቀቀውን ምርጫ በመምራት ለትረምፕ ቅርበት ባለቸው በብዙዎቹ የውስጥም ሆነ የውጭ ሰዎች ዘንድ የተደነቁ መሆናቸው ተነግሯል፡፡ ይሁን እንጂ ትረምፕ ባላፈው ረቡዕ ጧት ድላቸውን ሲያከብሩ ማይክራፎኑን ይዞ በመናገር ለመታየት እንኳ ፍላጎት አላሳዩም ተብሏል፡፡ የዊልሰን ሹመት እንደ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ለትረምፕ የመጀመሪያቸው ትልቅ ውሳኔ ሲሆን የመጭውን አስተዳደር ወሳኝ ፈተና ሊያመልክት የሚችል ውሳኔ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ዊልሰን ይዘው የሚመጡት ፌደራል መንግስት የሥራ ልምድ ባይኖራቸውም ከተመራጩ ፕሬዝዳንት ጋር የቀረበ ግንኙነት እንዳላቸው ተነግሯል፡፡ Read more