Ethiopia



ትረምፕ ለምንና እንዴት አሸነፉ?

የአሜሪካ ምርጫ በያዝነው ሳምንት ከመደረጉ በፊት የተሰበሰቡ የሕዝብ ፖለቲካዊ አስተያየት መለኪያዎች፣ በቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ እና በምክትል ፕ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በእነ ዶ.ር. ደብረጽዮን የሚመራውን ቡድን በመፈንቅለ መንግሥት ከሰሰ

በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በውይይት እንደሚቋጭ በመሪዎቹ መካከል ቃል መገባቱት በክልል ከሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት ከተነገረ ከዐሥር ቀና
የአሜሪካ ድምፅ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በእነ ዶ.ር. ደብረጽዮን የሚመራውን ቡድን በመፈንቅለ መንግሥት ከሰሰ

በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በውይይት እንደሚቋጭ በመሪዎቹ መካከል ቃል መገባቱት በክልል ከሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት ከተነገረ ከዐሥር ቀናት በኋላ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በእነ ዶ.ር. ደብረጽዮን የሚመራውን ቡድን “ይፋዊ መፈንቅለ መንግሥት እያካሄደ ነው” ሲል ከሷል። አስተዳደሩ ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ በአስተዳደሩ ሥር የሚገኙት የፓርቲው አመራሮች ያለ ቅድመ ኹኔታ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ለውይይት ዝግጁ መኾናቸውን ገልጿል። በመግለጫው ላይ በእነ ዶ.ር. ደብረ ጽዮን ብረሚካኤል ወገን በኩል ምላሽ ለማግኘት በስልክ እና በአካል ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። (ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ)  

ቻይና ውስጥ የመኪና አሽከርካሪ 35 ሰዎች ገጭቶ ገደለ 

ዙሃይ በተባለች የደቡባዊ ቻይና ከተማ አንድ የመኪና አሽከርካሪ በስፖርት ማዕከል  ስፖርት ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች መሃል መኪናውን እየነዳ ገብቶ 35 ሰዎችን ሲገድል
የአሜሪካ ድምፅ

ቻይና ውስጥ የመኪና አሽከርካሪ 35 ሰዎች ገጭቶ ገደለ 

ዙሃይ በተባለች የደቡባዊ ቻይና ከተማ አንድ የመኪና አሽከርካሪ በስፖርት ማዕከል  ስፖርት ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች መሃል መኪናውን እየነዳ ገብቶ 35 ሰዎችን ሲገድል ሌሎች 43 ሰዎች ማቁሰሉን ፖሊስ አስታወቀ።  የስድሳ ሁለት ዓመቱ የመኪናው አሽከርካሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ ትላንት  ሰኞ ማታ አስታውቋል።  ድርጊቱ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ጥቃት ወይም አደጋ ይሁን ለጊዜው አለመታወቁን ፖሊስ አመልክቷል።  ድርጊቱ የተፈጸመው  ከተማዋ በየዓመቱ የቻይና ህዝባዊ ነጻ አውጪ ሠራዊት የአቪየሽን ትርዒት የምታስተናግድ ስትሆን  ትርዒቱ ዛሬ ማክሰኞ ተከፍቷል። 

ለቀድሞ ጦር አካል ጉዳተኞች መቐለ ላይ ቦታ ለመስጠት የቀረበው እቅድ ተቃውሞ ገጠመው

የመቐለ ከተማ አስተዳደር፣ ትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ፣ እስከ ኢትዮጵያ ኤርትራ ጦርነትና ከዛ በፊት በነበሩ ጦርነቶች ላይ ተሳትፈው የአካል ጉዳት ለደረሰባቸ
የአሜሪካ ድምፅ

ለቀድሞ ጦር አካል ጉዳተኞች መቐለ ላይ ቦታ ለመስጠት የቀረበው እቅድ ተቃውሞ ገጠመው

የመቐለ ከተማ አስተዳደር፣ ትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ፣ እስከ ኢትዮጵያ ኤርትራ ጦርነትና ከዛ በፊት በነበሩ ጦርነቶች ላይ ተሳትፈው የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወደ 1ሺሕ 28 የሚደርሱ የቀድሞ የትግራይ ተወላጅ የጦር አባላት የመኖሪያ ቤት ቦታ ሊሰጣቸው መኾኑን ይፋ አድርጓል። ይህንን እቅድ የተቃወመው በአዲስ አበባ  ተመስርቶ በቅርቡ ጽሕፈት ቤቱን መቐለ ከተማ የከፈተው  ሰብዓ እንደርታ ፓርቲ ሲኾን፣  “ለጦር አካል ጉዳተኞች መኖርያ ቤት የሚሆን በሚል ሰበብ የመሬት ወረራ እየተፈፀመ ነው" ሲል አቤቱታውን አሰምቷል።   አስተዳደሩ መሬቱን ለመስጠት ያቀደው  ለትግራይ ጦር አካል ጉዳተኞች ማኅበር መቐለ ቅርንጫፍ አባለት መኾኑን የጠቀሱት  የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አብርሀም ፅጌ ከዚኽ ቀደም ለጦር ጉዳተኞች መሬት መሰጠቱንን መከራከሪያ በማቅረብ የአኹኑን እቅድ ተቃውመዋል። የመቐለ ከተማ የመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ገብረሚካኤል እኑን፣ የጦር አካል ጉዳተኞች የመኖርያ ቤት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚደነግገውን ሕግ መሰረት አድርገው እየሠሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በቅርቡ ለጦር አካል ጉዳተኞች የመኖርያ ቤት መሬት ዕጣ ለማውጣት ታቅዶ የነበረው ተጨማሪ ማጣራት ስላስፈለገው ለሌላ ጊዜ እንደ‍ተራዘመም ተናግረዋል።  (ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ)

ጋዛ ውስጥ 14 ሰዎች ተገደሉ ፣ ቤይሩት ላይ የአየር ድብደባ ተፈጸመ 

እስራኤል ጋዛ  ውስጥ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 14 ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጥኤም ባለስልጣናት ተናገሩ።  በተያያዘ ዜና ደቡባዊ ቤይሩት ዳርቻ በሚገኙ የመኖ
የአሜሪካ ድምፅ

ጋዛ ውስጥ 14 ሰዎች ተገደሉ ፣ ቤይሩት ላይ የአየር ድብደባ ተፈጸመ 

እስራኤል ጋዛ  ውስጥ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 14 ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጥኤም ባለስልጣናት ተናገሩ።  በተያያዘ ዜና ደቡባዊ ቤይሩት ዳርቻ በሚገኙ የመኖሪያ ሠፈሮች የእስራኤል የአየር ኅይል ጥቃት ማድረሱ ተዘግቧል። ነዋሪዎች እንዳሉት የእስራኤል ኅይሎች ነዋሪዎቹ እንዲወጡ ትዕዛዝ ከሰጡ ግማሽ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ሰማዩ በጢስ ተሸፍኗል።  ውጊያው የቀጠለ ሲሆን ዓለም አቀፍ የረድዔት ድርጅቶች ባወጡት ሪፖርት እስራኤል ወደ ጋዛ ሰርጥ ተጨማሪ እርዳታ እንዲገባ እንድትፈቅድ በዩናይትድ ስቴትስ የተቀመጠውን የዛሬ ማክሰኞ ቀነ ገደብ አለማክበሯን ተናግረዋል።  የእስራኤል የጦር ኅይል በበኩሉ በጥቃቱ በዋናነት የሚያተኩርበት ወደ ሆነው ወደ ሰሜናዊ ጋዛ ብዙ መቶ የምግብ አቅርቦት ጥቅሎች እና ውሃ እንዲገባ አድርገናል ሲል አስታውቋል።  ባለፈው እ አ አ ጥቅምት ወር የባይደን አስተዳደር እስራኤል ተጨማሪ የምግብ እርዳታ እና ሌላም አቅርቦት ወደጋዛ እንዲገባ እንድትፈቅድ አለዚያ ወታደራዊ እርዳታ ሊቀነስባት እንደሚችል ማስጠንቀቁ ይታወሳል። 

VOA60 Africa - Senegal PM Sonko calls for vengeance after election campaign clashes

Senegal: Prime Minister Ousmane Sonko on Tuesday called for vengeance following what he described as attacks against supporters of his Pastef party by the opposition during the campaign for Sunday's parliamentary elections.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Senegal PM Sonko calls for vengeance after election campaign clashes

Senegal: Prime Minister Ousmane Sonko on Tuesday called for vengeance following what he described as attacks against supporters of his Pastef party by the opposition during the campaign for Sunday's parliamentary elections.

VOA60 America - President-elect Trump taps Senator Rubio to be Secretary of State

President-elect Donald Trump tapped U.S. Senator Marco Rubio to be his secretary of state, The New York Times reported Monday night. If confirmed, the Republican senator from Florida would become the first Latino to serve as America's top diplomat in the new
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - President-elect Trump taps Senator Rubio to be Secretary of State

President-elect Donald Trump tapped U.S. Senator Marco Rubio to be his secretary of state, The New York Times reported Monday night. If confirmed, the Republican senator from Florida would become the first Latino to serve as America's top diplomat in the new Trump administration.

VOA60 World - At least 35 people were killed in vehicle attack on southern Chinese city

China: People laid floral tributes and lit candles in the southern city of Zhuhai, where a man whom authorities said was upset over his divorce settlement rammed his car into a crowd of people exercising at a sports complex. Authorities say 35 people were kil
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - At least 35 people were killed in vehicle attack on southern Chinese city

China: People laid floral tributes and lit candles in the southern city of Zhuhai, where a man whom authorities said was upset over his divorce settlement rammed his car into a crowd of people exercising at a sports complex. Authorities say 35 people were killed and dozens were severely injured.

ታላላቅ የዓለም መሪዎች ያልተገኙበት የአየር ንብረት ጉባዔ

የዓለም መሪዎች የተሰባሰቡበት የተመድ የአየር ንብረት ጉባዔ  ዛሬማክሰኞ አዘርባይጃን ዋና ከተማ ባኩ ውስጥ ተከፍቷል። ከቀደሙት ጉባዔዎች በተለየ በዘንድሮ
የአሜሪካ ድምፅ

ታላላቅ የዓለም መሪዎች ያልተገኙበት የአየር ንብረት ጉባዔ

የዓለም መሪዎች የተሰባሰቡበት የተመድ የአየር ንብረት ጉባዔ  ዛሬማክሰኞ አዘርባይጃን ዋና ከተማ ባኩ ውስጥ ተከፍቷል። ከቀደሙት ጉባዔዎች በተለየ በዘንድሮው ስብሰባ ላይ ያልተገኙ ታላላቅ ሰዎች እና አገሮች አሉ።  ከዚህ ቀደም የተካሄዱት ጉባዔዎች ከዓለም  ዋንጫ ውድድር በሚስተካከል ደረጃ  ዝነኞች ያሰባሰቡ እንደነበሩ የገለጸው የእሶሲየትድ ፕሬስ ዘገባ በዘንድሮው ጉባዔ የአስራ ሦስቱ ግንባር ቀደም በካይ ካርቦን ዳይክሳይድ  አፍላቂ  ሀገሮች  መሪዎች እንደማይሳተፉ አመልክቷል።   አስራ ሦስቱ ሀገሮች እ አ አ ባለፈው 2023 ዓም  ከተለቀቀው የዓለምን አየር የሚያግል  በካይ ጋዝ  ሰባ ከመቶውን ያፈለቁት መሆናቸውን ዘገባው ጠቁሟል።  የቻይና እና የዩናይትድ ስቴትስ መሪዎች የማይገኙ ሲሆን ህንድ እና ኢንዶኔዢያም መሪዎቻቸውን እንደማይልኩ ተገልጿል።   በመሆኑም ከዓለም  42 ከመቶውን የሕዝብ ብዛት  የያዙት አራት ሀገሮች መሪዎች በጉባዔው ላይ  ንግግር እንደማያደርጉ ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል። 

የቆቦ ከተማ የብልጽግና ጽ/ቤት ሓላፊ በታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ሰዎች ገለጹ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የቆቦ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደርቤ በለጠ ትላንት ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች መገ
የአሜሪካ ድምፅ

የቆቦ ከተማ የብልጽግና ጽ/ቤት ሓላፊ በታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ሰዎች ገለጹ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የቆቦ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደርቤ በለጠ ትላንት ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን በአካባቢው ነበርን ያሉ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ። በአካባቢው ላይ በጥርስ መፋቂያ ንግድ ላይ ተሰማርቶ የነበረ አንድ ወጣት በወቅቱ በደረሰብ ጉዳት ምክኒያት ዛሬ ሕይወቱ ማለፉን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ፣ በአቶ ደርቤ መገደል ማዘናቸውን በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። ለግድያው እስካኹን በይፋ ሓላፊነት የወሰደ አካል የለም። ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ይከታተሉ፡፡

በእስር ላይ የሚገኘው ኤርትራዊ-ስዊድናዊ ጋዜጠኛ ተሸለመ

ኤርትራ ውስጥ ከ23 ዓመታት በላይ ያለምንም ክስ ታስሮ የሚገኘው እና የስዊድን ዜግነት ያለው ትውልደ ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ፣ ሀሳብን በነጻነት ለመግለ
የአሜሪካ ድምፅ

በእስር ላይ የሚገኘው ኤርትራዊ-ስዊድናዊ ጋዜጠኛ ተሸለመ

ኤርትራ ውስጥ ከ23 ዓመታት በላይ ያለምንም ክስ ታስሮ የሚገኘው እና የስዊድን ዜግነት ያለው ትውልደ ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ፣ ሀሳብን በነጻነት ለመግለፅ መብት ላደረገው ትግል ዛሬ ሰኞ ተሸላሚ ሆኗል።  እ.አ.አ በመስከረም 2001 ዓ.ም የኤርትራ መንግስት ባካሄደው ዘመቻ፣ ከፍተኛ የካቢኔ ሚኒስትሮችን፣ የፓርላማ አባላትን እና ነፃ ጋዜጠኞችን ጨምሮ፣ መንግስት ካሰራቸው ከ24 በላይ ሰዎች መካከል ዳዊት አንዱ ነበር።  ሽልማቱን የሰጠው ኤድልስታም የተሰነው ተቋም ሽልማቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፣ ዳዊት 'ኤድልስታም' የተሰኘውን ሽልማት ያገኘው «ሀሳብን በነጻነት ለመግለፅ መብት፣ ለግለሰባዊ እምነት እና ለሰብዓዊ መብት ጥበቃ በመቆም ላደረገው የላቀ አስትዋፅኦ እና ፅናት» መሆኑን አስታውቋል።  አምነትስቲ ኢንተርናሽናል ዳዊትን የህሊና እስረኛ አድርጎ የሚቆጥረው ሲሆን፣ ለፕሬስ ነፃነት የሚሟገተው ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን፣ እሱ እና አብረውት የታሰሩት የስራ ባልደረቦቹ በዓለማችን ለረጅም ጊዜ የታሰሩ ጋዜጠኞች መሆናቸውን አስታውቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመብት ባለሞያዎች በበኩላቸው ኤርትራ በአስቸኳይ ዳውትን ከእስር እንድትፈታ ጠይቋል።  ኤርትራ እስካሁን በዳዊት ዙሪያ መላሽ ሰጥታ የማታውቅ ሲሆን፣ ምናልባትም በህይወት ላይኖር ይችላል የሚል ስጋት አለ። በህይወት ካለ ግን አሁን የ60 አመት እድሜ ይኖረዋል።  ሽልማቱን ሴት ልጁ ቤተልሔም ይስሐቅ ዳዊትን ወክላ በመጪው ሳምንት ስቶክሆልም ውስጥ በሚካሄድ ሥነ ስርዓት ላይ ትቀበላለች።  ዳዊት ከኤርትራ ሸሽቶ ወደ ስዊድን የተሰደደው እ.አ.አ በ1987 ሲሆን፣ የስዊድን ዜግነት ካገኘ በኃላ እ.አ.አ በ2001 በኤርትራ የመጀመሪያ የሆነው የግል ጋዜጣ ሰቲት መሰረተ። ብዙም ሳይቆይ የፖለቲካ ማሻሻያዎችን የሚጠይቁ መጣጥፎች በጋዜጣው መውጣታቸውን ተከትሎ ግን በቁጥጥር ስር ውሏል። 

ትራምፕ ስቴፋኒክን የተባበሩት መንግስታት አምባሳደር እንዲሆኑ መረጡ

የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው በዩናይትድ ስቴትስ ምክርቤት የሚያገለግሉትን ኤሊዝ ስቴፋኒክ፣ የተባበሩ
የአሜሪካ ድምፅ

ትራምፕ ስቴፋኒክን የተባበሩት መንግስታት አምባሳደር እንዲሆኑ መረጡ

የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው በዩናይትድ ስቴትስ ምክርቤት የሚያገለግሉትን ኤሊዝ ስቴፋኒክ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አምባሳደር አድርገው መሾማቸውን አስታወቁ።  ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ሰኞ ለሮይተርስ በላኩት መግለጫ «ኤሊዝ ስቴፋኒክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሆነው እንዲያገለግሉ በመሾሜ ክብር ይሰማኛል። ኤሊዝ በጣም ጠንካራ እና ብልህ የአሜሪካ ተፋላሚ ናቸው» ብለዋል። ኒው ዮርክን ወክለው በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የተመረጡት እና በምክርቤቱ የሪፐብሊካን ኮንፈረንስ ሊቀመንበር የሆኑት ስቴፋኒክ ጠንካራ የትራምፕ አጋር ሲሆኑ ሹመቱን አስመልክቶ አስተያየት እንዲሰጡ ወዲያው ማግኘት አልተቻለም።  ትራምፕ ቅዳሜ እለት በሰጡት መግለጫ በሪፐብሊካን ፓርቲ ለፕሬዝዳንት እጩነት ተፎካካሪያቸው የነበሩትን ኒኪ ሄሊ እና የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው የነበሩትን ማይክ ፖምፔዮ በአዲሱ አስተዳደራቸው እንደማይካተቱ አስታውቀው ነበር።  ሄሊ በቀደመው የትራምፕ አስተዳደር በመንግስታቱ ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።  ትራምፕ እ.አ.አ በጥር 20፣ 2025 ዓ.ም ቃለ መሃላ ፈፅመው ስልጣን ከመረከባቸው በፊት አስተዳደራቸው ውስጥ የሚያገለግሉ ሰዎችን ለመሾም እጩ ሆነው የቀረቡ ሰዎችን እያነጋገሩ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት ቅዳሜ እለት የገንዘብ ሚኒስቴር ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው ከታጩት፣ ታዋቂው ባለሀብት ስኮት ቤሰንት ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል። 

በቦኮ ሃራም ጥቃት 17 የቻድ ወታደሮች እና 96 አማፂያን መገደላቸውን የሀገሪቱ ጦር አስታወቀ

የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ቅዳሜ እና እሁድ በወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ ላይ ባደረሱት ጥቃት 17 የቻድ ወታደሮች መግደላቸውን የቻድ ጦር አስታወቀ። በጥቃቱ ወቅት በተደረ
የአሜሪካ ድምፅ

በቦኮ ሃራም ጥቃት 17 የቻድ ወታደሮች እና 96 አማፂያን መገደላቸውን የሀገሪቱ ጦር አስታወቀ

የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ቅዳሜ እና እሁድ በወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ ላይ ባደረሱት ጥቃት 17 የቻድ ወታደሮች መግደላቸውን የቻድ ጦር አስታወቀ። በጥቃቱ ወቅት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 96 የሚሆኑ አማፂያን መገደላቸውንም ጨምሮ ገልጿል።  የጦሩ ቃል አቀባይ ጀነራል ኢሳክ አቼክ እሁድ ምሽት በሀገሪቱ የቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጡት መግለጫ በቻድ ሐይቅ ክልል ጥቃቱ የተፈፀመው ቅዳሜ ምሽት መሆኑን ተናግረዋል። የቻድ ሐይቅ አካባቢ በዚህ አመት ከቦኮ ሃራም እና የምዕራብ አፍሪካ እስላማዊ መንግስትን ጨምሮ በአማፂያን ተደጋጋሚ ጥቃቶች ደርሶበታል።  ባለፈው ወር በወታደራዊ ካምፕ ላይ በተፈጸመ ጥቃት 40 ወታደሮች መገደላቸውን ተከትሎ፣ ፕሬዝዳንት ማሃማት ዴቢ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎችን ከቻድ ሐይቅ ለማትፋጥ ዘመቻ አካሂደው ነበር።  የምዕራባውያንን የትምህርት አሰጣጥ በመቃወም ያለፉትን አስር አመታት ትጥቅ ትግል ሲያካሂድ የቆየው ቦኮ ሃራም፣ በናይጄሪያ በእስላማዊ ሕግ የሚተዳደር መንግስት ማቋቋም ይፈልጋል። አማፂ ቡድኑ፣ ካሜሩን፣ ኒጀርን እና ቻድን ጨምሮ፣ በምዕራብ አፍሪካ ወደሚገኙ የአፍሪካ አገራትም ተስፋፍቷል።  ወደ 18 ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ ያላት ቻድ፣ በዴቢ ኢትኖ አሸናፊነት ከተጠናቀቀው አወዛጋቢ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት እና በኃላ በፖለቲካዊ ውዥንብር ስትታመስ ቆይታለች። 

ሁቲዎች ወደ እስራኤል ጦር ሰፈር ሚሳይል ተኮሱ

የሁቲ አማፂያን ሰኞ እለት ከየመን ወደ እስራኤል የተኮሱት ሚሳይል እየሩሳሌም አቅራቢያ በከሸፈበት ወቅት አየር ላይ እሳት ያስነሳ ሲሆን፣ አማፂያኑ ጥቃቱን ተ
የአሜሪካ ድምፅ

ሁቲዎች ወደ እስራኤል ጦር ሰፈር ሚሳይል ተኮሱ

የሁቲ አማፂያን ሰኞ እለት ከየመን ወደ እስራኤል የተኮሱት ሚሳይል እየሩሳሌም አቅራቢያ በከሸፈበት ወቅት አየር ላይ እሳት ያስነሳ ሲሆን፣ አማፂያኑ ጥቃቱን ተከትሎ ባወጡት መግለጫ በማዕከላዊ እስራኤል የተሳካ ጥቃት ማካሄዳቸውን ገልጸዋል።  በኢራን የሚደገፈው ታጣቂ ቡድን ባወጣው መግለጫ «ናሃል ሶሬክ የጦር ሰፈር» ላይ ያነጣጠረ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄዱን የገለጸ ሲሆን «ጥቃቱ ኢላማውን መምታቱን እና እሳት ማስነሳቱን» ገልጿል።  ሁኔታውን ተከትሎ የእስራኤል ጦር ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በላከው መግለጫ፣ ከየመን የተወነጨፈው ሚሳይል፣ ከእየሩሳሌም በስተምዕራብ በሚገኝ ቤተ ሸመሽ የተሰኘ አካባቢ የከሸፈ መሆኑን እና ይህ የፈጠረው እሳት በሰማይ ላይ መታየቱን አስታውቋል።  መግለጫው አክሎ የሁቱ ሚሳይል የእስራኤልን ግዛት ዘልቆ አለመግባቱን አመልክቷል።  ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁቲዎች የሚቆጣጠሩት የቴሌቭዥን ማሰራጫ ጣቢያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና እንግሊዝ አምራን እና ሰዓዳ በተሰኙ የየመን አካባቢዎች ላይ ያነጣጠረ ተከታታይ የአየር ድብደባ ማካሄዳቸውን አስታውቋል።  በሌላ ዜና፣ ማዕከላዊ ጋዛ ውስጥ ተፈናቃይ ቤተሰቦች ተጠልለው በሚገኙበት ድንኳን ላይ እስራኤል እሁድ እለት ባካሄደችው ጥቃት ቢያንስ ሦስት ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤም የጤና ባለስልጣናት አስታውቀዋል።  በተመሳሳይ ሁኔታ እስራኤል እሁድ ጠዋት በሴሜናዊ ጋዛ፣ ስደተኞች ተጠልለው የሚገኙበት መጠለያ ጣቢያ ላይ ባካሄደችው የአየር ጥቃት፣ ዘጠኝ ሴቶችን ጨምሮ ቢያንስ 17 ሰዎች መገደላቸውን አል አህሊ የተሰኝ ሆስፒታል አመልክቷል።

ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ልታካሂድ ነው

ከሶማሊያ ተገንጥላ በራስ ገዝ አስተዳደር የምትመራው እና በዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ውስጥ የምትገኘው ሶማሌላንድ፣ በአፍሪካ ቀንድ ውጥረት በነገሰበት ወቅት ረቡ
የአሜሪካ ድምፅ

ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ልታካሂድ ነው

ከሶማሊያ ተገንጥላ በራስ ገዝ አስተዳደር የምትመራው እና በዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ውስጥ የምትገኘው ሶማሌላንድ፣ በአፍሪካ ቀንድ ውጥረት በነገሰበት ወቅት ረቡዕ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች።  እ.አ.አ ከ1991 ጀምሮ እራሷን እንደ ነፃ ሀገር የምትቆጥረው ሶማሌላንድ የራሷ ገንዘብ፣ ፓስፖርት እና የጦር ሠራዊት ቢኖራትም፣ እስካሁን ከዓለም ሀገራት እውቅና አላገኘችም።  አሁን ደግሞ በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ለተነሳው ከፍተኛ ውዝግብ ምክንያት የሆነች ሲሆን፣ አለመረጋጋት በሰፈነበት ቀጠና ግጭት ሊቀሰቅስ ይችላል የሚል ዓለም አቀፍ ስጋት ፈጥሯል።  የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ በጥር ወር ከኢትዮጵያ ጋር በተፈራረሙት ስምምነት፣ 20 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው የቀይ ባህር ዳርቻ የባህር በር ለሌላት ኢትዮጵያ ለመስጠት ቃለ የገቡ ሲሆን፣ በምትኩ ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ እውቅና እንደምትሰጥ ተናግረዋል።  ይህ ስምምነት በአዲስ አበባ በኩል ያልተረጋገጠ ሲሆን፣ የስምምነቱ ሙሉ ዝርዝርም ለህዝብ ይፋ አልተደረገም።  ሆኖም የመግባቢያ ሰነዱ ሶማሊያን ያስቆጣ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ ጋር የሚካሄደው እና እየጨመረ የሄደው የቃላት እና ወታደራዊ ፍጥጫ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ አሳስቧል።  የቡሂ ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡት ፕሬዝዳንታዊ እጩዎች፣ አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ እና ፋይሳል አሊ ዋራቤ፣ መግባቢያ ሰደዱ ላይ ቅሬታ ባያቀረቡም፣ ቡሂ ሶማሌላንድ ውስጥ መከፋፈል በመፍጠር፣ በግጭት እና በዋጋ ንረት ይከሷቸዋል።  

ዮክሬን በሩሲያ መዲና ላይ ግዙፉን የሰው ዐልባ አይሮፕላኖች ጥቃት ፈጸመች

  ዩክሬን ቁጥራቸው ቢያንስ 34 በሚሆን ሰው ዐልባ አይሮፕላኖች  በዛሬው ዕለት ሞስኮ ላይ ጥቃት አደረሰች ።ጦርነቱ ከጀመረበት ከአውሮፓዊያኑ 2022 ወዲህ በሩሲያ
የአሜሪካ ድምፅ

ዮክሬን በሩሲያ መዲና ላይ ግዙፉን የሰው ዐልባ አይሮፕላኖች ጥቃት ፈጸመች

  ዩክሬን ቁጥራቸው ቢያንስ 34 በሚሆን ሰው ዐልባ አይሮፕላኖች  በዛሬው ዕለት ሞስኮ ላይ ጥቃት አደረሰች ።ጦርነቱ ከጀመረበት ከአውሮፓዊያኑ 2022 ወዲህ በሩሲያ መዲና ላይ ከደረሱት የድሮን ጥቃቶች ሁሉ ግዙፉ እንደሆነ የተነገረለት ጥቃት በሶስት የከተማዋ የአየር ማረፊያዎች  በረራዎች እንዲታጠፉ አድርጓል ፣ በትንሹ በአንድ ሰው ላይም ጉዳት አድርሷል። የሩስያ አየር መከላከያዎች በሌሎች የምዕራብ ሩሲያ ክልሎች ውስጥ በሶስት ሰዓት ውስጥ ሌሎች 36 ሰው አልባ አይሮፕላኖች ማምከናቸውን  የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። «በሩሲያ ፌዴሬሽን ግዛት ላይ የኪየቭ  አገዛዝ  መደበኛ አይሮፕላን መሳይ  ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ያደረገው ሙከራ ከሽፏል» ብሏል ሚኒስቴሩ። የሩስያ ፌደራል አየር ትራንስፖርት ኤጀንሲ የዶሞዴዶቮ፣ ሼሬሜትዬቮ እና ዡኮቭስኪ አውሮፕላን ማረፊያዎች ቢያንስ 36 በረራዎችን ማጠፋቸውን ፣ በአሁኑ ሰዓት ግን ማረፊያዎቹ  ስራቸውን መቀጠላቸውን አስታውቋል። በሞስኮ ቀጠና  አንድ ሰው  እንደተጓዳም ተነግሯል። ሞስኮ እና ቀጠናው ቢያንስ 21 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርበት፣ ከኢስታንቡል ጋር የሚስተካከል ፣ አውሮፓ ውስጥ ካሉት ትላልቅ «ሜትሮፖሊታን» አካባቢዎች አንዱ ነው። ሩሲያ በበኩሏ በአንድ ሌሊት  145 ሰው አልባ አይሮፕላኖችን እንዳስወነጨፈች ዩክሬን ተናግራለች። የኪየቭ አስተዳደር  የአየር መከላከያዎቹ  ከእነዚህ ውስጥ 62ቱን ማምከኑን አስታውቋል። በተጨማሪም ዩክሬን በሩሲያ ብራያንስክ ግዛት የጦር መሳሪያዎች ማከመቻ  ላይ ጥቃት ማድረሷን አስታውቃለች። 14ሰው አልባ አውሮፕላኖች በክልሉ ተመተው መውደቃቸውም  ተነግሯል። የሞስኮ ጦር ከጦርነቱ መጀመሪያ ወዲህ  ፈጣን ግስጋሴ ማሳየቱን እና ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ ፣ ለ2 ዓመት ከግማሽ የዘለቀው የዩክሬን ጦርነት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እየደረሰ መሆኑን አንዳንድ ባለስልጣናት ይናገራሉ።  በጥር ወር ስልጣን የሚረከቡት ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት በ24 ሰአት ውስጥ በዩክሬን ሰላም ማምጣት እንደሚችሉ ቢናገሩም ይህን ለማድረግ እንዴት እንደሚችሉ ግን ጥቂት ዝርዝሮችን ብቻ አጋርተዋል። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ትራምፕን ( እንኳን ደስ ያለዎት!) ለማለት በደወሉበት ወቅት የቴስላ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የትራምፕ ደጋፊ የሆኑት ኢሎን ማስክ ጥሪውን መቀላቀላቸውን የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ማስክ ለዩክሬን መከላከያ ጥረት ወሳኝ የሆኑ የስታርሊንክ የሳተላይት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሚሰጠውን የስፔስ ኤክስ ባለቤት ናቸው (ሮይተርስ)።

ትውልደ ኬኒያዊ አሜሪካዊ ሁላዳ ሞማኒ ሂልስሊ ለሚኒሶታ ምክር ቤት ተመረጠች 

ሁልዳህ ሞማኒ ሂልስሊ የመጀመሪያ ኬንያዊ ተወላጅ በመሆን ለሚኒሶታ ምክር ቤት በመመረጥ ታሪክ ሰርታለች። ይህ ድሏም የጽናት፣ ቆራጥነት እና የአሜሪካን ህልም
የአሜሪካ ድምፅ

ትውልደ ኬኒያዊ አሜሪካዊ ሁላዳ ሞማኒ ሂልስሊ ለሚኒሶታ ምክር ቤት ተመረጠች 

ሁልዳህ ሞማኒ ሂልስሊ የመጀመሪያ ኬንያዊ ተወላጅ በመሆን ለሚኒሶታ ምክር ቤት በመመረጥ ታሪክ ሰርታለች። ይህ ድሏም የጽናት፣ ቆራጥነት እና የአሜሪካን ህልም እውን ለማድረግ ማረጋገጫ እንደሆነ ገልጻለች።  ሂልስሊ ለመጀመሪያ ጊዜ በምክር ቤቱ በተገኘችበት ወቅት ለቪኦኤ ስትናገር “በጣም ተደስቻለሁ”  «ዛሬ ለአዲስ ህግ አውጪዎች የመጀመርያ ማብራርያ የሚሰጥበት ቀን ነው፣ እና በዚህ የሚኒሶታ ካፒቶል ውስጥ እንደ አፍሪካዊ ስደተኛ ሴት መቆም ትልቅ ክብር ነው። አሁን በጣም ጓጉቻለሁ።» ብላለች፡፡  ይህ ስኬት በቀላሉ አልመጣም የምትለው ሂልስሊ ወደ ሚኔሶታ የክልል ምክር ቤት የሄደችበት መንገድ በበርካታ ትግሎች የታጀበ እንደሆነ ተናግራለች፡፡  ይህም ቤተሰቦቿን ከሃገር ለማስወጣት ተቃርቦ ከነበረው የስደተኛ ስርዓትትን መፋለም የደረሰ ነው፡፡ በኋላም ይህ ትግሏ በማህበረሰቡና በቀድሞው ሴናተር ፖል ዌልስቶን ድጋፍ እርሷና ለቤተሰቦቿ መጀመርያ የመኖርያ ፍቃድ በኋላ ደግሞ ዜግነት እንዲያገኙ እንዳስቻላት ትናገራለች፡፡  ያገኘችው ድል የኬንያ ሚድያዎችን ትኩረት የሳበ ሲሆን በትውልድ አካባቢዋም ደስታቸውን እየገለጡ ነው፡፡ ሂልስሊ ለኬንያና አሜሪካ ታዳጊዎችም አርዓያ ለመሆን እንደምትሰራም ተናግራለች፡፡ 

እስራኤል በጋዛ ባደረሰችው የአየር ጥቃት 14 ሰዎች ተገደሉ 

የጋዛ ሲቪል መከላከያ ኤጀንሲ ዛሬ እንዳስታወቀው የእስራኤል የአየር ጥቃት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ በአንድ ሌሊት 14 ፍልስጤማውያንን መግደሉን ሲገልጽ  የእ
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል በጋዛ ባደረሰችው የአየር ጥቃት 14 ሰዎች ተገደሉ 

የጋዛ ሲቪል መከላከያ ኤጀንሲ ዛሬ እንዳስታወቀው የእስራኤል የአየር ጥቃት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ በአንድ ሌሊት 14 ፍልስጤማውያንን መግደሉን ሲገልጽ  የእስራኤል ጦር በበኩሉ በሰሜዊ ግዛት በደርዘን የሚቆጠሩ ታጣቂዎችን መግደሉን አስታውቋል፡፡  በደቡባዊ ካን ዩኒስ አካባቢ የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያንን በሚኖሩብባቸው ድንኳኖች ላይ በደረሰ የአየር ጥቃት ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ ቢያንስ 9 ሰዎች መሞታቸውን የሲቪል መከላከያ ቃል አቀባይ ማህሙድ ባሳል ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል።  የፍልስጤም ቀይ ጨረቃም ጉዳቱን አረጋግጦ 11 ሰዎች በጥቃቱ ቆስለው ወደ ናስር ሆስፒታል መወሰዳቸውን ገልጿል።  በጋዛ ከተማ በአል-ቱፋህ ወረዳ “በሺህ ለሚቆጠሩ ተፈናቃዮች” መጠለያነት በሚያገለግለው ትምህርት ቤት ላይ በደረሰ ሁለተኛ የአየር ጥቃትም  ህጻናትን ጨምሮ አምስት ሰዎች ሲገደሉ  22 ያህሉ መቁሰላቸውንም ቃል አቀባዩ ተግረዋል፡፡  በቅርብ ወራት ውስጥ የእስራኤል  ጦር የፍልስጤም ታጣቂዎች መሽገውባቸዋል ያላቸውን  በርካታ ወደ መጠለያ የተቀየሩ ትምህርት ቤቶችን እየደበደበ ነው፡፡  ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ጦር ሰራዊቱ በሰሜን ጋዛ ጃባሊያ አካባቢ “በደርዘን የሚቆጠሩ አሸባሪዎችን” መግደሉን የገለፀ ሲሆን ሃማስ እንደገና እንዳይሰባሰብ ከአንድ ወር በላይ የአየር እና የምድር ዘመቻ ሲያካሂድ መቆየቱን ገልጿል፡፡  የእስራኤል ወታደሮች በግዛቱ ደቡብ ራፋህ በተባለው አካባቢ በርካታ ታጣቂዎችን መግደላቸውንም ጦሩ አክሎ ገልጿል።  ወታደሮቹ በአሁኑ ወቅት በሁለት ግንባር ጦርነት ውስጥ ይገኛሉ ያለው የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ከሄዝቦላህ እና በጋዛ ከሀማስ ጋር እየተፋለሙ ይገኛሉ ብሏል። ሃማስ እና ሂዝቦላ በዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታንያ፣ የአውሮፓ ህብረት እና ሌሎች በአሸባሪነት የተፈረጁ ናቸው፡፡ 

በፓኪስታን በደረሰ የቦንብ ጥቃት 26 ሰዎች ተገደሉ 

በፓኪስታን ደቡብ ምዕራብ ባሎቺስታን ግዛት በተጓዦች በተጨናነቀው የባቡር ጣቢያ ውስጥ አጥፍቶ ጠፊ ባደረሰው የቦንብ ጥቃት ቢያንስ 26 ሰዎች ሲገደሉ ከ60 በላይ
የአሜሪካ ድምፅ

በፓኪስታን በደረሰ የቦንብ ጥቃት 26 ሰዎች ተገደሉ 

በፓኪስታን ደቡብ ምዕራብ ባሎቺስታን ግዛት በተጓዦች በተጨናነቀው የባቡር ጣቢያ ውስጥ አጥፍቶ ጠፊ ባደረሰው የቦንብ ጥቃት ቢያንስ 26 ሰዎች ሲገደሉ ከ60 በላይ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ተገለጸ።  ከፍተኛ የፖሊስ መኮንን የሆኑት መሀመድ ባሎክ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በኩቴታ ግዛት ዋና ከተማ የተከሰተው ኃይለኛ ፍንዳታ የደረሰው «100 የሚጠጉ ሰዎች» ይገኙበት በነበረው የባቡሩ የተሳፋሪ መቆያ ስፍራ ነው፡፡  ከተገደሉትና ከቆሰሉት መካከል ቢያንስ ግማሽ ያህሉ  የፓኪስታን ጦር ሰራዊት አባላት ሲሆኑ የጥቃቱም ቀዳሚ ኢላማ እንደነበሩም ፖሊስ እና የሆስፒታል ባለስልጣናት ተናግረዋል።  ጥቃቱ የደረሰበት ግዛት መንግስት ቃል አቀባይ ሻሂድ ሪንድ እንደተናገሩት ከተጎዱት መካከል ቢያንስ 10 ሰዎች “በጣም አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ናቸው” ብለዋል ።   የአማፂ ቡድን የሆነው የባሎክ የነጻነት ጦር፣  የፓኪስታን ወታደራዊ አባላትን ኢላማ አድርጓል ለተባለው ጥቃት ኃላፊነቱን ወስዷል።   ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሻሪፍ በኩዌታ የተፈጸመውን የቦምብ ጥቃት በማውገዝ “ከንጹሃን ዜጎች ግድያ ጀርባ ያሉትን ለመቅጣት ቃል ገብተዋል” ሲል ፅህፈት ቤታቸው ኢስላማባድ ውስጥ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።   ባለፈው ሳምንት በግዛቲቱ ማስቱንግ ከተማ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ቢያንስ 9 ሰዎች ሲሞቱ ከግማሽ በላይ የሚሆኑትም ተማሪዎች ነበሩ። ጥቃቱ ያነጣጠረውም የፖሊዮ ክትባቶችን የሚሰጡ ሰራተኞችን በሚያጓጉዝ የፖሊስ መኪና ላይ ነበር።   

የትረምፕ መመረጥ ኔቶ እና አውሮፓ ላይ ምን አንድምታ ይኖረዋል?

አውሮፓዊያኑ የዩናይትድ ስቴትስ አጋሮች ዶናልድ ትረምፕ መመረጣቸው በጸጥታ እና ኢኮኖሚያቸው ላይ ምን ዓይነት አንድምታ እንደሚኖረው እየተነጋገሩ ናቸው፡፡
የአሜሪካ ድምፅ

የትረምፕ መመረጥ ኔቶ እና አውሮፓ ላይ ምን አንድምታ ይኖረዋል?

አውሮፓዊያኑ የዩናይትድ ስቴትስ አጋሮች ዶናልድ ትረምፕ መመረጣቸው በጸጥታ እና ኢኮኖሚያቸው ላይ ምን ዓይነት አንድምታ እንደሚኖረው እየተነጋገሩ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው የትረምፕ አስተዳደር ዘመን ከአውሮፓ ኅብረት እና ከሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ ) አባል ሀገሮች ጋራ በተደጋጋሚ በጎላ አለመግባባት የታየበት ነበር፡፡ የአሜሪካ ድምጹ ሄንሪ ሪጅዌል ሩስያ ዩክሬይን ላይ የከፈተችው ወረራ ስለውቂያኖስ ተሻጋሪው ኅብረት የአውሮፓ ሀገሮች ያላቸውን ስጋት ይበልጡን ያጎላው መሆኑን ጠቅሶ ከለንደን ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል፡፡

የአንተኒ ብሊንከን መግለጫ በትግራይ ፓርቲዎች ተቃውሞ ገጠመው

የትግራይ ክልልን መነሻ አድርጎ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ተስፋፍቶ የነበረውን ግጭት ያስቆመው፣ የፕሪቶሪያ ተኩስን በዘላቂነት የማቆም የሰላም ስምምነ
የአሜሪካ ድምፅ

የአንተኒ ብሊንከን መግለጫ በትግራይ ፓርቲዎች ተቃውሞ ገጠመው

የትግራይ ክልልን መነሻ አድርጎ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ተስፋፍቶ የነበረውን ግጭት ያስቆመው፣ የፕሪቶሪያ ተኩስን በዘላቂነት የማቆም የሰላም ስምምነት ሁለተኛ ዓመትን አስመልክተው መግለጫ ያወጡት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊነክን፤ “ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንደተመለሱ አድርገው መግለፃቸው ተገቢ አይደለም ሲሉ” ሦስት ፓርቲዎች ተቃውሞ አቀረቡ። ህወሓት ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ ከጦርነቱ በፊት በትግራይ ክልል ሥር ከነበሩትና ምዕራብ ትግራይ በሚል ከሚጠሩት አካባቢዎች የተፈናቀሉት ሰዎች እስከ አኹን ወደ ቀያቸው እንዳልተመለሱ ገልጿል። ተፈናቃዮች ለመመለስ፣ መተማመን ለመገንባት እና በክልሉ ፀጥታ ለማስፈን በስምምነቱ መሰረት ከኢትዮጵያ መከላከያ ውጭ ያሉ ኃይሎች መውጣት ይገባቸዋል ሲል አስታውቋል። ፓርቲው በፌስቡክ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ፣ የዩናይትድ ስቴት ስምምነቱ እንዲተገበር የምታደርገውን ጥረት አድንቆ፣ የችግሩን ምንጭ ተረድቶ ጵላባት ለመስጠ አስቸኳይ የፖለቲካ ውይይት ያስፈልጋል ብሏል። ሌሎች ሁለት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎችም ቅሬታቸውን ገልጸዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የፍርድ ሂደታቸው መጓተቱ እንደሚያሳስባቸው እነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው ገለፁ

በእግድ ላይ የሚገኘውን የእነ አቶ ዮሃንስ ቧያለው የሽብር ክስ ሂደት ለማስቀጠል ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጠው፣ ዐቃቤ ሕግ ክሱን አሻሽሎ
የአሜሪካ ድምፅ

የፍርድ ሂደታቸው መጓተቱ እንደሚያሳስባቸው እነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው ገለፁ

በእግድ ላይ የሚገኘውን የእነ አቶ ዮሃንስ ቧያለው የሽብር ክስ ሂደት ለማስቀጠል ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጠው፣ ዐቃቤ ሕግ ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ በከፍተኛው ፍርድ ቤት በተሰጠው ብይን ላይ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበውን የይግባኝ ውሳኔ ለመጠባበቅ ነው። ተከሳሾቹ በበኩላቸው የፍርዱ ሂደት መጓተቱ አሳስቦናል ሲሉ በዛሬው ችሎት ላይ ቅሬታ አሰምተዋል፡፡ በሌላ በኩል፣ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ በመጣስ ማረሚያ ቤት ህክምና እንዳናገኝ ከልክሎናል ሲሉ አቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን፣ ማረሚያ ቤቱ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ሩሲያ ዩክሬንን በሚሳይል ድሮን እና ቦምቦች ደበደበች

ሩሲያ ዩክሬን ውስጥ ዛሬ ዓርብ በኦዴሳ፣ ካርኪቭ እና ኪቭ ክልሎችን ኢላማ በማድረግ በድሮኖች፣ ሚሳይሎች እና ቦምቦች በፈጸመችው የአንድ ሌሊት ጥቃት አንድ ሰው
የአሜሪካ ድምፅ

ሩሲያ ዩክሬንን በሚሳይል ድሮን እና ቦምቦች ደበደበች

ሩሲያ ዩክሬን ውስጥ ዛሬ ዓርብ በኦዴሳ፣ ካርኪቭ እና ኪቭ ክልሎችን ኢላማ በማድረግ በድሮኖች፣ ሚሳይሎች እና ቦምቦች በፈጸመችው የአንድ ሌሊት ጥቃት አንድ ሰው ሲሞት በትንሹ 25 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ጥቃቱ በመኖሪያ ሕንፃዎች እና መሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ዛሬ ዓርብ በካርኪቭ የሩስያ ቦምብ ጥቃት የተመታ አንድ ባለ 12 ፎቅ የመኖሪያ ህንጻ የታችኞቹን ሶስት የፎቅ ክፍሎች አውድሟል፡፡ ኦዴሳ ውስጥ በሩሲያ ድሮኖች ከተመቱ የመኖሪያ ሕንፃዎች አንዱ በእሳት የተቀጣጠለ ሲሆን የ46 ዓመቱን ሰው ገድሎ ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎችን ያቆሰለ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ የዩክሬን ሀይሎች አራት ሚሳይሎችን እና በግምት 60 የሚጠጉ ድሮኖችን መትተው ማውረዳቸውን ገልጸው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሩሲያ ላይ የተጠናከረ የጋራ ርምጃ እንዲወስድ አሳስበዋል። ዜሌንስኪ ይህንን መልእክት ያስተላለፉት ቡዳፔስት ውስጥ በአውሮፓ የፖለቲካ ማህበረሰብ ስብሰባ ላይ ከአውሮፓ መሪዎች ጋር በተገናኙበት ወቅት ነው፡፡ የዩክሬንን መከላከያ ለማጠናከር የሚያስችሉ አዳዲስ ስምምነቶችን ከአውሮፓ መሪዎች ያገኙ መሆኑም ተመልክቷል፡፡ የዶናልድ ትረምፕ እና የቭላድሚር ፑቲን ወዳጅ ናቸው የተባሉት የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን በቅርቡ የአሜሪካ ምርጫ ባሸነፉት ትረምፕ አሜሪካውያን ለዩክሬን የሚሰጡት ድጋፍ ሊቆም እንደሚችል እና አውሮፓም በጦርነቱ ውስጥ የራሷን ተሳትፎ እንደገና እንድታጤነው ሀሳብ አቅርበዋል። የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ካሪን ዣን ፒየር እና የፔንታጎን ቃል አቀባይ ሳብሪና ሲንግን ጨምሮ የአሜሪካ ባለስልጣናት ፕሬዝዳንት ባይደን ስልጣን እስኪያዛውሩ ድረስ ለዩክሬን ዕርዳታ መስጠት እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡ ቀደም ሲል ለዩክሬን ደህንንነት ከተፈቀደው ውስጥ በግምት 2 ቢሊዮን ዶላር እና ተጨማሪ የ4 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያዎች አሁንም እንዳሉ መሆናቸውን የፔንታገን ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡

VOA60 Africa - Botswana's Duma Boko sworn-in as new president

Botswana: Opposition leader Duma Boko was inaugurated president Friday following a historic election that removed the former ruling Botswana Democratic Party from power for the first time in 58 years.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Botswana's Duma Boko sworn-in as new president

Botswana: Opposition leader Duma Boko was inaugurated president Friday following a historic election that removed the former ruling Botswana Democratic Party from power for the first time in 58 years.

ትረምፕ የመጀመሪያዋን ሴት የኋይት ሃውስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሰየሙ

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለድል ያበቃቸውን የምርጫ ቅስቅሳ ዘመቻቸውን በዋና ሥራ አስኪያጅነት የመሩትን ሱዚ ዊልስን ኋይት ሃውስ ጽ/ቤት ኃላፊ አድር
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ የመጀመሪያዋን ሴት የኋይት ሃውስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሰየሙ

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለድል ያበቃቸውን የምርጫ ቅስቅሳ ዘመቻቸውን በዋና ሥራ አስኪያጅነት የመሩትን ሱዚ ዊልስን ኋይት ሃውስ ጽ/ቤት ኃላፊ አድርገው ሰይሟቸዋል፡፡ ሱዚ ዊልሰን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ተደማጭነት ያለውን ቦታ እንዲመሩ የተመደቡ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነዋል። ዊልሰን ትረምፕ ሥረዓት ያለው የምርጫ ቅስቀሳ እንዲያካሂዱ በማድረግ ባማረ ውጤት የተጠናቀቀውን ምርጫ በመምራት ለትረምፕ ቅርበት ባለቸው በብዙዎቹ የውስጥም ሆነ የውጭ ሰዎች ዘንድ የተደነቁ መሆናቸው ተነግሯል፡፡ ይሁን እንጂ ትረምፕ ባላፈው ረቡዕ ጧት ድላቸውን ሲያከብሩ ማይክራፎኑን ይዞ በመናገር ለመታየት እንኳ ፍላጎት አላሳዩም ተብሏል፡፡ የዊልሰን ሹመት እንደ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ለትረምፕ የመጀመሪያቸው ትልቅ ውሳኔ ሲሆን የመጭውን አስተዳደር ወሳኝ ፈተና ሊያመልክት የሚችል ውሳኔ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ዊልሰን ይዘው የሚመጡት ፌደራል መንግስት የሥራ ልምድ ባይኖራቸውም ከተመራጩ ፕሬዝዳንት ጋር የቀረበ ግንኙነት እንዳላቸው ተነግሯል፡፡

አምስተዳርም ውስጥ በእስራኤል የእግር ኳስ ደጋፊዎች ላይ በተካሄደ ጥቃት 5 ሰዎች ሰዎች ተጎዱ

አምስተርዳም ውስጥ በአያክስ እና ማካቢ ቴል አቪቭ መካከል በተደረገው የእግር ኳስ ጨዋታ በእስራኤል ደጋፊዎች ላይ ባነጣጠረ ፀረ-ሴማዊ ጥቃት የተጎዱ አምስት ሰ
የአሜሪካ ድምፅ

አምስተዳርም ውስጥ በእስራኤል የእግር ኳስ ደጋፊዎች ላይ በተካሄደ ጥቃት 5 ሰዎች ሰዎች ተጎዱ

አምስተርዳም ውስጥ በአያክስ እና ማካቢ ቴል አቪቭ መካከል በተደረገው የእግር ኳስ ጨዋታ በእስራኤል ደጋፊዎች ላይ ባነጣጠረ ፀረ-ሴማዊ ጥቃት የተጎዱ አምስት ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን የአምስተርዳም ፖሊስ ዛሬ ዓርብ አስታውቋል። ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ 62 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ፖሊስ ገልጿል፡፡ የእስራኤል እና የኔዘርላንድ መሪዎች እንዲሁም የተለያዩ የአይሁድ ማህበረሰብ ቡድኖች ጥቃትና ሁከቱን ሲያወግዙ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ለዚሁ ጉዳይ በፍጥነት ወደ ኔዘርላንድ ተጉዘዋል፡፡ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በአምስተርዳም በእስራኤል ዜጎች ላይ የደረሰውን ጥቃት አውግዘው የኔዘርላንድ ባለስልጣናት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል፡፡ የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲክ ስኩፍ “በእስራኤላውያን ላይ የሚደረገው ጸረ ሴማዊ ጥቃት በፍጹም ተቀባይነት የለውም” ብለዋል፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ግጭቶች የተነሳ የተባባሰው ዓለም አቀፍ ውጥረት የእስራኤል ቡድኖችን በሚያካትቱ ጨዋታዎች ላይ የደህንነት ስጋቶችን እየፈጠረ መምጣቱ ተነግሯል። የአምስተርዳም ፖሊስ ዝርዝር መረጃ ባይሰጥም በተለያዩ ቦታዎች የተፈጸሙ የጥቃት ድርጊቶችን መመርመር መጀመሩን አስታውቋል፡፡ በከተማው ውስጥ ባሉ የአይሁድ ተቋማትና ከፍተኛ አይሁዳውያን በሚኖሩባቸው ቦታዎች የደህንነት ጥበቃዎች መጠናከራቸው ተመልክቷል፡፡ የአምስተርዳም ከንቲባ ፌምኬ ሃልሴማ ግጭት ሊከሰት ይችላል በሚል ፍልስጤማውያንን የሚደግፉ የተቃውሞ ሰልፎች በስታዲየሙ አካባቢ እንዳይካሄዱ የከለከሉ ቢሆንም በከተማው በርካታ አካባቢዎች ሁከቱ መቀስቀሱን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘግባ አመልክቷል፡፡ በአውሮፓ ሊግ ጨዋታ አያክስ ማካቢ ቴል አቪቭን 5-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ የወለድ መጠንን ዝቅ አደረገ

የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ (Federal Reserve) ለኢኮኖሚው ቁልፍ የሆነውን የወለድ ምጣኔ ትናንት ሐሙስ በሩብ ነጥብ ዝቅ እንዲል አድርጓል፡፡ ውሳኔው በአንድ ወቅት ከፍ
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ የወለድ መጠንን ዝቅ አደረገ

የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ (Federal Reserve) ለኢኮኖሚው ቁልፍ የሆነውን የወለድ ምጣኔ ትናንት ሐሙስ በሩብ ነጥብ ዝቅ እንዲል አድርጓል፡፡ ውሳኔው በአንድ ወቅት ከፍተኛ የዋጋ ንረት እያሽቆለቆለ መምጣቱን ተከትሎ አሜሪካውያንን ካስቆጣው የዋጋ ንረትና ግሽበት ጋራ የተያያዘ ሲሆን የቀድሞው ፕሬዝደንት ትረምፕን በዚህ ሳምንቱ ምርጫ እንዲያሸነፉ የረዳቸው መሆኑን ተመልክቷል፡፡ የወለድ ምጣኔው ቅነሳ በመስከረም ወር በግማሽ ነጥብ የቀነሰውን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ ማዕከላዊ ባንኩ ውሳኔው የሥራ ቅጥር ገበያውን ለመደገፍ፣ የዋጋ ንረንት ለመዋጋት እና አሁን ከባንኩ እቅድ 2 ከመቶ በላይ በመጠኑ ያለፈውን የግሽበቱን መጠን ለመቆጣጠር ያለመ ነው ብሏል፡፡ ባንኩ ለአራት አስርት ዓመታት እየከፋ የመጣውን የዋጋ ግሽበት ለመቋቋም የወለድ መጠኑን ከአንድ ዓመት በላይ ከፍ አድርጎ መቆየቱ ተገልጿል፡፡ ዓመታዊ የዋጋ ግሽበቱ እኤአ በ2022 አጋማሽ 9.1 ከመቶ ደርሶ የነበረ ሲሆን ባላፈው መስከረም በሶስት ዓመት ተኩል ውስጥ ዝቅተኛ ሆኖ ወደ ተመዘገበው 2.4 ከመቶ ዝቅ ብሏል፡፡ የሀሙሱ ውሳኔ በአራት አስርት ዓመታት ውስጥ 5.3 ከመቶ ደርሶ የነበረውን የወለድ መጠን ወደ ወደ 4.6 ከመቶ ዝቅ አድርጎታል፡፡ ማዕከላዊ ባንኩ የቅርብ ጊዜውን ስብሰባ ባጠናቀቀበት ወቅት በሰጠው መግለጫ “የሥራ አጠነት መጠኑ ከፍ ብሏል ቢሆንም መጠኑ ዝቅተኛ ነው” ብሏል፡፡

በጋዛ ጦርነት ከሞቱት 70 ከመቶ የሚጠጉት ሴቶችና ህጻናት ናቸው – ተመድ

ባለፈው ዓመት በጋዛ ግጭት መሞታቸው ከተረጋገጠ ሰዎች መካከል 70% የሚጠጉት ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸውን ዛሬ ዓርብ የወጣው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መ
የአሜሪካ ድምፅ

በጋዛ ጦርነት ከሞቱት 70 ከመቶ የሚጠጉት ሴቶችና ህጻናት ናቸው – ተመድ

ባለፈው ዓመት በጋዛ ግጭት መሞታቸው ከተረጋገጠ ሰዎች መካከል 70% የሚጠጉት ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸውን ዛሬ ዓርብ የወጣው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ቢሮ ዘገባ አመልክቷል። የመንግሥታቱ ድርጅት ዘገባ “ይህ የዓለም ዓቀፍ የሰብአዊ ህግ መሰረታዊ መርሆችን ስልታዊ በሆነ መንገድ የጣሰ ነው” ሲልም ድርጊቱን አውግዟል፡፡ የሟቾቹ ቁጥር፣ ከአንድ ዓመት በፊት በጀመረው የእስራኤል ሀማስ ጦርነት፣ የመጀመሪያዎቹን ሰባት ወራት የሚሸፍን መሆኑን ባለ 32 ገጹ የመንግሥታቱ ድርጅት ዘገባ አመልክቷል፡፡ በዚህ ሰባት ወር ጊዜ ውስጥ፣ በመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብት ቢሮ የተረጋገጠው የሟቾች ቁጥር 8 ሺሕ 119 ሲሆን፣ ይህ የፍልስጤም የጤና ባለሥልጣናት በ13 ወራት ግጭት ከ43ሺሕ በላይ ነው ሲሉ ከጠቀሱት ቁጥር በእጅጉ ያነሰ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የድርጅቱ ዘገባ በጦርነቱ ከተገደሉት መካከል አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ህጻናትና ሴቶች ናቸው የሚለውን የጤና ባለሥልጣናቱን ዘገባ ይደግፋል፡፡ የድርጅቱ ዘገባ “የዓለም አቀፍ ህግን ጥሰዋል ሊባሉ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ገለልተኛ የፍትህ ምርመራ እንደሚያስፈልግ እና ማስረጃዎች ለተጠያቂነት ሲባል መጠበቅ እንደሚገባቸው” በመጠቆም አጽንኦት ሰጥቷል። እ.ኤ.አ ጥቅምት 2023 በደቡብ እስራኤል 1ሺሕ 200 የሚጠጉ ሰዎችን የገደለው እና ከ250 በላይ ሰዎችን አግቶ የወሰደውን የሃማስ ጥቃት ተከትሎ የአጸፋ ርምጃ መወሰድ መጀመሯን የገለጸችው እስራኤል የሰለማዊ ዜጎችን ጉዳት ለመቀነስ እየሞከረች መሆኑን ትናገራለች፡፡ ሀማስ ሰላማዊ ሰዎችን እንደ ሰብአዊ ጋሻ እየተጠቀመበት ነው ስትልም እስራኤል ሀማስን ትከሳለች፡፡ ጥቃቱ “ተመጣጣኝ አለመሆኑን” በገለጸው የድርጅቱ ዘገባ ከተረጋገጡ ሟቾች መካከል፣ ትንሹ ተጎጂ የአንድ ቀን ወንድ ልጅ ሲሆን፣ ትልቋ ደግሞ የ97 ዓመት ባልቴት እንደነበሩ ተገልጿል፡፡ ዘገባው አክሎም ይህም በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ያስከተለውን ሰፊ ተጽእኖ አጉልቶ ያሳያል ብሏል፡፡ ዘገባው በእስራኤል በተካሄዱ 88 ከመቶ በሚሆኑ ጥቃቶች ከአምስት ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች የተገደሉ መሆኑን ገልጾ ከተጎጂዎች መካከል 44 ከመቶ የሚሆኑት ህጻናት መሆናቸውን አመልክቷል፡፡

የአውሮፓ መሪዎች ለትረምፕ የደስታ መግለጫ ላኩ፣ ስለቀጣዩ የአትላንቲክ ተሻጋሪ ግንኙነት ስጋት አላቸው

በአውሮፓ ያሉ የአሜሪካ አጋሮች ሁለተኛው የሥልጣን ዘመናቸው በውቂያኖስ ተሻጋሪው ሕብረት ላይ ምን አንድምታ እንደሚያስከትል በስፋት ስጋት ቢኖራቸውም ባለፈ
የአሜሪካ ድምፅ

የአውሮፓ መሪዎች ለትረምፕ የደስታ መግለጫ ላኩ፣ ስለቀጣዩ የአትላንቲክ ተሻጋሪ ግንኙነት ስጋት አላቸው

በአውሮፓ ያሉ የአሜሪካ አጋሮች ሁለተኛው የሥልጣን ዘመናቸው በውቂያኖስ ተሻጋሪው ሕብረት ላይ ምን አንድምታ እንደሚያስከትል በስፋት ስጋት ቢኖራቸውም ባለፈው ማክሰኞ በተካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ላሸነፉት ለቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ የ«እንኳን ደስ ያለዎ» መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ሄንሪ ሪጅዌል ከለንደን ያደረሰንን ዘገባ ከተያይዘው ፋይል ይከታተሉ።

እስራኤላውያን በፕሬዝዳንት ትራምፕ መመረጥ የተሰማቸውን ደስታ ገለጡ

እስራኤላውያን እና ፍልስጤማውያን ዶናልድ ትራምፕ በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸንፈው የመመረጣቸውን ዜና በደስታ መቀበላቸውን እየገለጡ ነው። ከ
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤላውያን በፕሬዝዳንት ትራምፕ መመረጥ የተሰማቸውን ደስታ ገለጡ

እስራኤላውያን እና ፍልስጤማውያን ዶናልድ ትራምፕ በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸንፈው የመመረጣቸውን ዜና በደስታ መቀበላቸውን እየገለጡ ነው። ከሁለቱ ወገኖች በኩል ትላንት ረቡዕ በተሰሙት አስተያየቶች፤ እስራኤላውያን ከሃማስ፣ ሄዝቦላ እና ኢራን ጋር እያካሄዱ ባሉት ጦርነት ይረዱናል የሚል ተስፋ ማድረጋቸውን ሲገልጡ፤ ፍልስጤማውያን በበኩላቸው ነጻ የፍልስጤም ግዛት በሚመሰረትበት ሁኔታ ላይ አንዳንድ አዳዲስ ሃሳቦችን ያመጡ ይሆናል የሚል ተስፋ አሳድረዋል። ሊንዳ ግራድስቲን ከኢየሩሳሌም ያጠናቀረችውን ዘገባ ዝርዝር ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ሪፐብሊካኖቹ ሕገ መወሰኛውን ከአራት ዓመታት በኋላ ተቆጣጥረዋል

በአሜሪካ ምርጫ የሪፐብሊካን ፓርቲው የሕግ መወሰኛ ሸንጎውን ወይም ሴኔት በበላይነት ተቆጣጥሯል። ይህም በድጋሚ ፕሬዝደንታዊ ፉክክሩን ላሸነፉት ዶናልድ ትረ
የአሜሪካ ድምፅ

ሪፐብሊካኖቹ ሕገ መወሰኛውን ከአራት ዓመታት በኋላ ተቆጣጥረዋል

በአሜሪካ ምርጫ የሪፐብሊካን ፓርቲው የሕግ መወሰኛ ሸንጎውን ወይም ሴኔት በበላይነት ተቆጣጥሯል። ይህም በድጋሚ ፕሬዝደንታዊ ፉክክሩን ላሸነፉት ዶናልድ ትረምፕ፣ ያቀዷቸውን የሕግ ለውጦች ለማድረግ ቁልፍ የሆነ መሣሪያ ይሰጣቸዋል። የቪኦኤ የኮንግረስ ዘጋቢ ካትሪን ጂፕሰን የላከችው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

እስያውያን የትራምፕ ሁለተኛ አገዛዝን በስጋት እየተጠባበቁ ነው

እስያውያን የዩናይትድ ስቴትስ አጋሮች ዶናልድ ትራምፕ በማክሰኞው ዕለት ምርጫ ሙሉ ለሙሉ በማሸንፋቸው የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት እየላኩ ይገኛሉ፡፡ ይሁን
የአሜሪካ ድምፅ

እስያውያን የትራምፕ ሁለተኛ አገዛዝን በስጋት እየተጠባበቁ ነው

እስያውያን የዩናይትድ ስቴትስ አጋሮች ዶናልድ ትራምፕ በማክሰኞው ዕለት ምርጫ ሙሉ ለሙሉ በማሸንፋቸው የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት እየላኩ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ ብዙ እስያውያን ‘ቅድሚያ አሜሪካን’ የተሰኘው የውጭ ፖሊሲያቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ስጋት አጭሮባቸዋል፡፡ የአሜሪካ ድምጹ ቢል ጋሎ ከሲኦል ደቡብ ኮሪያ ያደረሰንን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በጦርነትና የአየር ንብረት ለውጥ ምክኒያት ረሃብ እየተስፋፍ መኾኑን ተመድ አስታወቀ

ጦርነትና የአየር ንብረት ለውጥ አኹንም በመላው ዓለም እየተስፋፋ ላለው ረሃብ ምክኒያት መኾናቸውን በተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት። አዲ
የአሜሪካ ድምፅ

በጦርነትና የአየር ንብረት ለውጥ ምክኒያት ረሃብ እየተስፋፍ መኾኑን ተመድ አስታወቀ

ጦርነትና የአየር ንብረት ለውጥ አኹንም በመላው ዓለም እየተስፋፋ ላለው ረሃብ ምክኒያት መኾናቸውን በተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት። አዲስ አበባ ውስጥ ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ በተጠናቀቀው ዓለምን ከረሃብ  ነጻ የማድረግ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት፣የድርጅቱ ዋና ሓላፊ ጌራልድ ሙሌር፣  ረሃብ የዓለምን ሕዝብ እየጎዳ ያለው የበለፅጉት ሃገራት ከዓመት ገቢያቸዉ በየዓመቱ ለአዳጊ ሀገራት ሊያደርጉ የሚገባቸዉን ድጋፍ ባለመስጠታቸውና በአዳጊ ሀገራትም የፖለቲካ ውሳኔ  ባለመኖሩ መኾኑን ገልፀዋል። የአፍሪካ ኅብረት በበኩሉ ከአራቱ አንዱ አፍሪቃው ለረሃብ ችግር የተጋለጠ መሆኑን ገልፆ፣ ግጭት አሁንም ለረሃብ መስፋፋት ምክንያት እንደሆነ ተናግሯል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ካምላ ሃሪስ በፕሬዝደንታዊ ምርጫው ትረምፕ ማሸነፋቸው ተቀበሉ

በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ተመራጩን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ዘንድ በስልክ «እንኳን ደስ ያለዎ» ብለዋቸዋል፡፡ ምክትል ፕሬዝደ
የአሜሪካ ድምፅ

ካምላ ሃሪስ በፕሬዝደንታዊ ምርጫው ትረምፕ ማሸነፋቸው ተቀበሉ

በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ተመራጩን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ዘንድ በስልክ «እንኳን ደስ ያለዎ» ብለዋቸዋል፡፡ ምክትል ፕሬዝደንት ካምላ ሃሪስም በምርጫው መሸነፋቸውን ተቀብለዋል፡፡ የኋይት ሀውስ ዘጋቢያችን ፓትሲ  ዊዳኩስዋራ  ሃሪስ ትላንት ረቡዕ ንግግር ካደረጉበት ከዋሽንግተኑ ሐዋርድ ዩኒቨርስቲ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ደስታም ሐዘንም ያስተናገደው የትረምፕ ምርጫ ድል

የአሜሪካውያን ፈቃድ በመሆኑ፣ የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ወደ ዋይት ሃውስ ይመለሳሉ። ለሁለት በተከፈለችው ሃገር፣ ምርጫውን የማሸነፋቸውን ዜና አ
የአሜሪካ ድምፅ

ደስታም ሐዘንም ያስተናገደው የትረምፕ ምርጫ ድል

የአሜሪካውያን ፈቃድ በመሆኑ፣ የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ወደ ዋይት ሃውስ ይመለሳሉ። ለሁለት በተከፈለችው ሃገር፣ ምርጫውን የማሸነፋቸውን ዜና አሜሪካውያን በደስታም፣ በሃዘንም ተቀብለውታል። ቬሮኒካ ባልዴራስ ኢግሌስያስ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

በደቡብ ሶማሊያው ጦርነት ቢያንስ 11 የመንግሥት ኃይሎች ተገደሉ

ሶማሊያ ውስጥ በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል በትላንት  በተደረገ ከባድ ጦርነት ቢያንስ 11 የሶማሌ ክልል እና የፌደራል መንግስት ሃይሎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት አ
የአሜሪካ ድምፅ

በደቡብ ሶማሊያው ጦርነት ቢያንስ 11 የመንግሥት ኃይሎች ተገደሉ

ሶማሊያ ውስጥ በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል በትላንት  በተደረገ ከባድ ጦርነት ቢያንስ 11 የሶማሌ ክልል እና የፌደራል መንግስት ሃይሎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ጦርነቱ የተካሄደው ከጁባላንድ ግዛት ኪስማዮ በስተደቡብ ምዕራብ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዋያንታ አካባቢ የመንግስት ሃይሎች ታጣቂዎቹ ይሰባሰባሉ በተባለበት ቦታ ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ ነው። ከመገናኛ ብዙኃን ጋር መነጋገር ያልተፈቀደላቸውና ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሦስት ባለሥልጣናት፣ 11 የክልልና የመንግሥት ወታደሮች ሲገደሉ ከ20 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል። በግጭቱ ከ20 በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን ከባለስልጣናቱ አንዱ ተናግረዋል። ባለፈው አመት የሶማሊያ ሃይሎች በተመሳሳይ አካባቢ ባደረጉት ዘመቻ የአልሸባብ ምክትል አሚር ነበር የተባለውን ግለሰብ መግደላቸውን የክልሉ ባለስልጣናት ገልጸዋል። አምና በአልሸባብ ታጣቂዎች ላይ በዋይንታ አካባቢ “ራስን በጋራ መከላከል” በተሰኘው የአሜሪካ ጦር የአየር ጥቃት ሶስት ተዋጊዎች ተገድለዋል።  

Get more results via ClueGoal