ትውልደ ኬኒያዊ አሜሪካዊ ሁላዳ ሞማኒ ሂልስሊ ለሚኒሶታ ምክር ቤት ተመረጠች
newsare.net
ሁልዳህ ሞማኒ ሂልስሊ የመጀመሪያ ኬንያዊ ተወላጅ በመሆን ለሚኒሶታ ምክር ቤት በመመረጥ ታሪክ ሰርታለች። ይህ ድሏም የጽናት፣ ቆራጥነት እና የአሜሪካን ህልምትውልደ ኬኒያዊ አሜሪካዊ ሁላዳ ሞማኒ ሂልስሊ ለሚኒሶታ ምክር ቤት ተመረጠች
ሁልዳህ ሞማኒ ሂልስሊ የመጀመሪያ ኬንያዊ ተወላጅ በመሆን ለሚኒሶታ ምክር ቤት በመመረጥ ታሪክ ሰርታለች። ይህ ድሏም የጽናት፣ ቆራጥነት እና የአሜሪካን ህልም እውን ለማድረግ ማረጋገጫ እንደሆነ ገልጻለች። ሂልስሊ ለመጀመሪያ ጊዜ በምክር ቤቱ በተገኘችበት ወቅት ለቪኦኤ ስትናገር “በጣም ተደስቻለሁ” «ዛሬ ለአዲስ ህግ አውጪዎች የመጀመርያ ማብራርያ የሚሰጥበት ቀን ነው፣ እና በዚህ የሚኒሶታ ካፒቶል ውስጥ እንደ አፍሪካዊ ስደተኛ ሴት መቆም ትልቅ ክብር ነው። አሁን በጣም ጓጉቻለሁ።» ብላለች፡፡ ይህ ስኬት በቀላሉ አልመጣም የምትለው ሂልስሊ ወደ ሚኔሶታ የክልል ምክር ቤት የሄደችበት መንገድ በበርካታ ትግሎች የታጀበ እንደሆነ ተናግራለች፡፡ ይህም ቤተሰቦቿን ከሃገር ለማስወጣት ተቃርቦ ከነበረው የስደተኛ ስርዓትትን መፋለም የደረሰ ነው፡፡ በኋላም ይህ ትግሏ በማህበረሰቡና በቀድሞው ሴናተር ፖል ዌልስቶን ድጋፍ እርሷና ለቤተሰቦቿ መጀመርያ የመኖርያ ፍቃድ በኋላ ደግሞ ዜግነት እንዲያገኙ እንዳስቻላት ትናገራለች፡፡ ያገኘችው ድል የኬንያ ሚድያዎችን ትኩረት የሳበ ሲሆን በትውልድ አካባቢዋም ደስታቸውን እየገለጡ ነው፡፡ ሂልስሊ ለኬንያና አሜሪካ ታዳጊዎችም አርዓያ ለመሆን እንደምትሰራም ተናግራለች፡፡ Read more