ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ልታካሂድ ነው
newsare.net
ከሶማሊያ ተገንጥላ በራስ ገዝ አስተዳደር የምትመራው እና በዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ውስጥ የምትገኘው ሶማሌላንድ፣ በአፍሪካ ቀንድ ውጥረት በነገሰበት ወቅት ረቡሶማሌላንድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ልታካሂድ ነው
ከሶማሊያ ተገንጥላ በራስ ገዝ አስተዳደር የምትመራው እና በዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ውስጥ የምትገኘው ሶማሌላንድ፣ በአፍሪካ ቀንድ ውጥረት በነገሰበት ወቅት ረቡዕ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች። እ.አ.አ ከ1991 ጀምሮ እራሷን እንደ ነፃ ሀገር የምትቆጥረው ሶማሌላንድ የራሷ ገንዘብ፣ ፓስፖርት እና የጦር ሠራዊት ቢኖራትም፣ እስካሁን ከዓለም ሀገራት እውቅና አላገኘችም። አሁን ደግሞ በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ለተነሳው ከፍተኛ ውዝግብ ምክንያት የሆነች ሲሆን፣ አለመረጋጋት በሰፈነበት ቀጠና ግጭት ሊቀሰቅስ ይችላል የሚል ዓለም አቀፍ ስጋት ፈጥሯል። የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ በጥር ወር ከኢትዮጵያ ጋር በተፈራረሙት ስምምነት፣ 20 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው የቀይ ባህር ዳርቻ የባህር በር ለሌላት ኢትዮጵያ ለመስጠት ቃለ የገቡ ሲሆን፣ በምትኩ ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ እውቅና እንደምትሰጥ ተናግረዋል። ይህ ስምምነት በአዲስ አበባ በኩል ያልተረጋገጠ ሲሆን፣ የስምምነቱ ሙሉ ዝርዝርም ለህዝብ ይፋ አልተደረገም። ሆኖም የመግባቢያ ሰነዱ ሶማሊያን ያስቆጣ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ ጋር የሚካሄደው እና እየጨመረ የሄደው የቃላት እና ወታደራዊ ፍጥጫ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ አሳስቧል። የቡሂ ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡት ፕሬዝዳንታዊ እጩዎች፣ አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ እና ፋይሳል አሊ ዋራቤ፣ መግባቢያ ሰደዱ ላይ ቅሬታ ባያቀረቡም፣ ቡሂ ሶማሌላንድ ውስጥ መከፋፈል በመፍጠር፣ በግጭት እና በዋጋ ንረት ይከሷቸዋል። Read more