ጋሞ ዞን ውስጥ ታስረው ይገኛሉ የተባሉ ከ80 በላይ ሰዎች እንዲለቀቁ ቤተሰቦቻቸው ጠየቁ
newsare.net
በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ ከዜይሴ ብሔረሰብ ቀበሌዎች የልዩ ወረዳ አደረጃጀት ጥያቄ ጋራ በተያያዘ ግጭት ታስረው እስር ቤት የቀሩ 80 ሰዎች በፖሊስና በፍርድ ቤጋሞ ዞን ውስጥ ታስረው ይገኛሉ የተባሉ ከ80 በላይ ሰዎች እንዲለቀቁ ቤተሰቦቻቸው ጠየቁ
በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ ከዜይሴ ብሔረሰብ ቀበሌዎች የልዩ ወረዳ አደረጃጀት ጥያቄ ጋራ በተያያዘ ግጭት ታስረው እስር ቤት የቀሩ 80 ሰዎች በፖሊስና በፍርድ ቤት ምልልልስ በመጉላላት ላይ መኾናቸውን የታሳሪ ቤተሰቦችና አንድ የፓርላማ አባል ገለጹ። ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ “ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ማፍረስ” የሚል ክስ መስርቶባቸዋል። የቤተሰብ አባላቱ ግን፣ ግለሰቦቹ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ከመጠየቅ በስተቀር የሠሩት ወንጀል የለም ሲሉ መከራከሪያ አቅርበዋል። የአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር አምሳሉ ሀንኮ፣ በወረዳው ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰረ ሰው የለም፣ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ስለ ጉዳዩ አቤቱታ ቀርቦለት ክትትል በማድረግ ላይ መኾኑን ገልጿል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡ Read more