የቡድን 20 ሃገራት በአየር ንብረት ለውጥ ዙርያ ከስምምነት እንዲደረስ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ ተመድ አሳሰበ
newsare.net
የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ሃላፊ ለታዳጊ ሃገራት በሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ዙርያ በኮፕ 29 እየተደረጉ ያሉ ድርድሮች ገና ረጅም መንገድ እንደሚቀራየቡድን 20 ሃገራት በአየር ንብረት ለውጥ ዙርያ ከስምምነት እንዲደረስ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ ተመድ አሳሰበ
የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ሃላፊ ለታዳጊ ሃገራት በሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ዙርያ በኮፕ 29 እየተደረጉ ያሉ ድርድሮች ገና ረጅም መንገድ እንደሚቀራቸው አስጠንቅቀዋል፡፡ በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ተደራዳሪዎቹ ልዩነታቸው በማጥበብ ከስምምነት ለመድረስ እየተነጋገሩ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በቀጣዩ ሳምንት በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ ከሚደረገው የሚንስትሮች ስብሰባ አስቀድሞ ከስምምነት ለመድረስ ፍላጎት ቢኖርም በዋና ዋና ጉዳዮች ግን አሁንም ከስምምነት መድርስ አልተቻለም ተብሏል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ሀላፊ ሲሞን ስቲል የዓለማችን ታላላቅ ኢኮኖሚዎች እና ከፍተኛ ብክለትን የሚያካትቱ የቡድን 20 ሀገራት መሪዎች ሰኞ በብራዚል ሲገናኙ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡት ተማጽነዋል። ለአለም አቀፍ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀቶች ተጎጅ የሆኑት አንዳንድ ታዳጊ ሀገራት ከአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመቋቋምና ወደ ታዳሽ ሃይል እንዲሸጋገሩ 1.3 ትሪሊዮን ዶላር ዓመታዊ ድጋፍ ጠይቀዋል፡፡ ይህ አሃዝም አሜሪካን፣ የአውሮፓ ህብረት እና ጃፓንን ጨምሮ ለጋሾች ከሚከፍሉት 10 እጥፍ በላይ ነው። Read more