Ethiopia



የቀድሞ የከባድ ሚዛን ሻምፒዮን ማይክ ታይሰን በጃክ ፖል ተሸነፈ 

ትላንት ምሽት በቴክሳስ በተካሄደውና የቀድሞው ታዋቂ ቦክሰኛ ማይክ ታይሰንን በድጋሚ ወደ ቀለበት በመለሰው የከባድ ሚዛን ፍልሚያ ጃክ ፖል በነጥብ አሸናፊ ሁኗ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እስራኤል በጋዛ ያደረሰችው ጥቃት 'የዘር ማጥፋት' ስለመሆኑ ለማጣራት ምርመራ እንዲደረግ ጠየቁ

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ  ፣ እስራኤል በጋዛ ያደረሰችው ጥቃት ዘር ማጥፋት መሆኑን ለማረጋገጥ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ  አቀረ
የአሜሪካ ድምፅ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እስራኤል በጋዛ ያደረሰችው ጥቃት 'የዘር ማጥፋት' ስለመሆኑ ለማጣራት ምርመራ እንዲደረግ ጠየቁ

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ  ፣ እስራኤል በጋዛ ያደረሰችው ጥቃት ዘር ማጥፋት መሆኑን ለማረጋገጥ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ  አቀረቡ ።ይህ ይፋ የተደረገው  ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ  ኢዮቤልዩ በዓል አስቀድሞ  እንደሚለቀቅ ከተነገረለት አዲስ መጽሐፍ ላይ ቀድመው በወጡ ቅንጫቢ አንቀጾች  ላይ ነው።   ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት  ፍራንሲስ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በወሰደችው እርምጃ ጋር ተያይዞ ባለው  የዘር ማጥፋት ውንጀላ ዙሪያ ማጣሪያ እንዲደረግ  ሲያሳስቡ ይህ የመጀመሪያቸው ነው። በአውሮፓዊያኑ መስከረም ላይ እስራኤል በጋዛ እና ሊባኖስ ያደረሰችው ጥቃት “የሞራል ህግ የጣሰ” ፣ ተመጣጣኝ ያልሆነ መሆኑን እንዲሁም የእስራኤል  ወታደሮች ከጦርነት ህግጋት እንተደተሻገሩ ተናግረዋል። በሄርናን ሬይስ አልካይድ የተዘጋጀው እና ከጳጳሱ ጋር በተደረገ ቃለ ምልልስ ላይ የተመሰረተው መፅሃፍ “ተስፋ ፣ ተስፋ አይቆርጥም። መንፈሳዊ ፍኖት ወደ ተሻለ ዓለም« የሚል ርዕስ ሲኖረው ፣ ከጳጳሱ የአውሮፓዊያኑ 2025 ኢዮቤልዩ በዓለ ሲመት በፊት የፊታችን ማክሰኞ ይለቀቃል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን አንድ ዓመት የሚዘልቅ  ኢዮቤልዩ በዓል  በማስመልከት ከ30 ሚሊዮን በላይ ምዕመናንን  ወደ ሮም ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል። »አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት በጋዛ ውስጥ የተፈጸመው ድርጊት የዘር ማጥፋት ባህሪያት አሉት « ሲሉ ጳጳሱ  መናገራቸውን ፣ የመጽሃፉን ቅንጭብ ዋቢ ያደረገው ፣ ዛሬ ለንባብ የበቃው  የጣሊያን ዕለታዊ ጋዜጣ  ላ ስታምፓ ዘግቧል። »በህግ ባለሙያዎች እና በዓለም አቀፍ አካላት ከተቀረጹት ልዩ  ፍቺዎች ጋር የሚስማማ መሆኑን ለማረጋገጥ በጥንቃቄ መመርመር አለብን"  ሲሉም አክለዋል። ባለፈው ዓመት ርዕሳነ ሊቀ ጳጳስ  ፍራንሲስ በጋዛ ከሚገኙት የእስራኤል ታጋቾች እና በጦርነቱ ውስጥ ከሚኖሩ ፍልስጤማውያን ዘመዶች ጋር በተናጥል የተገናኙ ሲሆን  ፣ የቫቲካን ዲፕሎማቶች ከመጠቀም የሚታቀቧቸውን  “ሽብርተኝነት” እና እንደ ፍልስጤማዊያኑ ሁሉ  “የዘር ማጥፋት” የሚሉትን ቃላት በመጠቀማቸው የጋለ ክርክር ቀስቀሰዋል።  ባለፈው ሳምንት ከእስር ከተፈቱት የእስራኤል ታጋቾች ልኡካን  እና ጫና ሲፈጥሩ ከቆዩ ቤተሰቦቻቸው ጋር  የተገናኙት ሊቀ ጳጳሱ በቅርቡ በሚለቀቀው መጽሃፍ ላይ የኤዲቶሪያል ቁጥጥር አላቸው። ጦርነቱ የጀመረው የታጣቂው የሃማስ ቡድን በአውሮፓዊያኑ ጥቅምት  7፣ 2023 እስራኤልን ካጠቃ በኃላ  ሲሆን ፣ በወቅቱ 1,200 ሰዎች ገድሎ  250 ሰዎችን አሁንም የተወሰኑት  ወደ ሚገኙበት  ጋዛ አፍኖ  ወስዷል ።  በጋዛ የጤና ባለስልጣናት መረጃ መሰረት ፣ የእስራኤል ዓመት የተሻገረ  ወታደራዊ ዘመቻ ከ 43,000 በላይ ሰዎችን ገድሏል ። ምንም እንኳን ከሟቾቹ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች እና ህጻናት ናቸው ።  መረጃው  በሲቪሎች እና በተዋጊዎች መካከል ልዩነትን አላስቀመጠም (AP)።

የሶማሊያው ሚኒስትር ለአውሮፓ ዲፕሎማቶች ከባድ ማስጠንቀቂያ ላኩ

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  በቅርቡ በሶማሌላንድ ምርጫ ላይ አስተያየት ለሰጡ  በሀገሪቱ ለሚገኙ የአውሮፓ ዲፕሎማቶች ከባድ ማስጠንቀቂያ ላኩ። አህመድ
የአሜሪካ ድምፅ

የሶማሊያው ሚኒስትር ለአውሮፓ ዲፕሎማቶች ከባድ ማስጠንቀቂያ ላኩ

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  በቅርቡ በሶማሌላንድ ምርጫ ላይ አስተያየት ለሰጡ  በሀገሪቱ ለሚገኙ የአውሮፓ ዲፕሎማቶች ከባድ ማስጠንቀቂያ ላኩ። አህመድ ሙአሊም ፊቂ ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን ምርጫ የታዘቡ የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች ሶማሌላንድን እንደ አንድ የተለየ ሀገር ሳይሆን እንደ ሶማሊያ አንድ ክልል መጥራት እንዳለባቸው ተናግረዋል። ፊቂ በሶማሊያ የዴንማርክ አምባሳደር ስቲን ሶን አንደርሰንን በሶማሌላንድ ሃርጌሳ በነበሩበት ወቅት ስለ ሰጡት አስተያየት ለማነጋገር እንዳስጠሯቸው ገልጸዋል። የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ አንደርሰን በአውሮፓዊያኑ ህዳር 19 በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲቀርቡ ተነግሯቸዋል። የሶማሌላንድ የማስታወቂያ ሚኒስትር አሊ ሀሰን መሀመድ የፊቂን እርምጃ  “ምቀኝነት” ሲሉ ተችተዋል። አሊ ፊቂን “በሶማሊላንድ ህዝብ እድገት ምክንያት ቅናት አድሮባቸዋል” ሲል ከሰዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢ ቡድን (IEOM) በሶማሊላንድ ውስጥ ስላለው ምርጫ ያዘጋጀውን ግምገማ አትሟል። ምርጫው የተመዘገቡ መራጮች  የመምረጥ መብታቸውን መተግበር እንዲችሉ ባስቻለ  በአብዛኛው የተረጋጋና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መከናወኑን ታዛቢዎቹ ተናግረዋል። ምንም እንኳን የምርጫ ታዛቢዎቹ  በተሻለ ስልጠና ሊፈቱ የሚችሉ የአሰራር እና የአስተዳደር አለመጣጣም እንከኖችን ቢያስተውሉም ፣ ምንም አይነት ከባድ የህግ ጥሰት ወይም የምርጫ ብልሹ አሰራሮችን  እንዳልተመለከቱ ተናግረዋል። የሶማሌላንድ ምርጫ ኮሚሽን የቀደሙት ውጤቶችን ከአውሮፓዊያኑ ህዳር 21 በፊት ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ።  

በጋቦን ወታደራዊውን አገዛዝ ለማስወገድ አብላጫ መራጮች ድምጻቸውን መስጠታቸውን የቀደሙ ዘገባዎች አመላከቱ

በጋቦን የተከናወነው ህዝበ ውሳኔ ቀደምት ውጤቶች  ፣ከተመዘገቡት 860,000 መራጮች አብዛኛው  ወታደራዊ አገዛዝን የሚቋጨውን  አዲስ ሕገ መንግሥት ለመደገፍ ድምጽ
የአሜሪካ ድምፅ

በጋቦን ወታደራዊውን አገዛዝ ለማስወገድ አብላጫ መራጮች ድምጻቸውን መስጠታቸውን የቀደሙ ዘገባዎች አመላከቱ

በጋቦን የተከናወነው ህዝበ ውሳኔ ቀደምት ውጤቶች  ፣ከተመዘገቡት 860,000 መራጮች አብዛኛው  ወታደራዊ አገዛዝን የሚቋጨውን  አዲስ ሕገ መንግሥት ለመደገፍ ድምጽ መስጠታቸውን የሀገሪቱ መንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ  ዘገባዎች አመልክተዋል። የቅዳሜው ህገ-መንግስታዊ ህዝበ ውሳኔ ውጤት ፣ ለ60 ዓመታት በሀገሪቱ ውስጥ የቆየውን የቦንጎ ቤተሰብ ስርወ መንግስት ያስወገደውን የሽግግር ወታደራዊ መንግስት  ዘመን ሊደመድም ይችላል። ይፋዊ የቆጠራ ውጤቱ በቅርቡ ይፋ ይሆናል ይጠበቃል። ባለስልጣናት እንደሚሉት ፣ የአዲሱ ህገ መንግስት መጽደቅ ፣ በአውሮፓዊያኑ  ነሐሴ 30 የጋቦን መሪዎች ካለ ደም መፋሰስ ፣ የመካከለኛው አፍሪካዊቷን ሀገር ከፖለቲካ ባርነት ነጻ እንዳረገ በሚናገሩለት መፈንቅለ መንግስት ስልጣን የተቆጣጠሩት ፣ ጄኔራል ብሪስ ክሎቴር ኦሊጊ ንጊዩሜ ከገቧቸው  ዐበይት ቃል ኪዳኖች መካከል አንዱ ነው።   ሰርጌ ዜንግ አንጎ የጋቦን ዜጎች በህዝበ ውሳኔው ወቅት አዲስ ህገ-መንግስት እንዲፀድቁ የምርጫ ቅስቀሳ ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲ የብሔራዊ ህብረት  ስራ አስፈፃሚ ናቸው። አዲሱ ሕገ መንግሥት እንደ ቦንጎ ዘመን ሥልጣን ከአባት ወደ ልጅ የሚተላለፍበትን ሌላኛ የፖለቲካ ሥርወ መንግሥት(ውርርስ)  ማንኛውንም ዕድል እንደሚገታ ተናግረዋል። ነገር ግን ተቃዋሚዎች እና ሲቪል ማህበረሰቦች የሕገ መንግሥቱ ረቂቅ ወታደራዊው ገዥ ጄኔራል ንጉዌማን ለፕሬዚዳንትነት እንዳይወዳደሩ መከልከል ነበረበት ብለዋል።  በወታደራዊ አመራሮች  ህገ መንግስቱ የተዘጋጀው  ለፕሬዚዳንቱ ከልክ ያለፈ ስልጣን ለመስጠት ፣  ንጉዌማ በስልጣን ላይ እንዲቆዩ  ለማድረግ እንደሆነም አክለዋል። የጋቦን ተቃዋሚዎች እና የሲቪል ማህበራት የህዝበ ውሳኔውን ውጤት በፍርድ ቤት እንደሚቃወሙ ቢናገሩም ተጨማሪ ዝርዝር መግለጫ አልሰጡም። የጋቦን መንግስት የቅዳሜው ህዝበ ውሳኔ ነፃ፣ ፍትሃዊ እና ግልጽ ነበር ብሏል። አዲሱ ህገ መንግስት ከቦንጎ የአባት እና ልጅ የስልጣን  ዘመን በተለየ የግለሰቦችን ነፃነት ያስከብራል ሲሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል። የአፍሪካ ህብረት እና የመካከለኛው አፍሪካ ምጣኔ ሀብት  እና የገንዘብ ማህበረሰብ ፤ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እንደተናገሩት የምርጫ ጣቢያዎች ዘግይተው በመከፈታቸው ዘግይቶ  ከተጀመረው ድምጽ አሰጣጥ ሂደት  ምርጫው ሰላማዊ እና ግልፅነት የተሞላበት ነበር። የህዝበ ውሳኔው ውጤት ውጤት ይፋ ከሆነ  በኋላ ፣ ጋቦን በየካቲት ወር የምርጫ ህጎቿን በማዘጋጀት ፣ የምርጫ አስተዳደር አካልን ትፈጥራለች ተብሎ ይጠበቃል ።  በነሐሴ 2025 የአውሮፓዊያኑ ዘመን ደግሞ ሁለት አመት ያስቆጠረውም ሽግግር ጊዜ  ለመቋጨት  ፕሬዚዳንታዊ፣ የፓርላማ እና የአካባቢ ምርጫዎችን ታከናውናለች። ወታደራዊው ገዥ ንጉሜ  ለወደፊቱ በሚደረጉ ምርጫዎች ላይ ዕጩ ስለመሆናቸው ይፋ ባያደርጉም በዚህ ህዝበ ውሳኔ ላይ ያለው ህገ መንግስት ግን ለፕሬዚዳንትነት ከመወዳደር አይከለክላቸውም።

ትራምፕ የነዳጅ ኢንዱስትሪ ሥራ አስፈፃሚን ለኃይል መስሪያ ቤቱ ጸሐፊነት መረጡ

በቅርቡ ስልጣን የሚረከቡት  ዶናልድ ትራምፕ አዲሱን አስተዳደራቸውን እያዋቀሩ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት ፣ የነዳጅ መስክ አገልግሎት ድርጅት መስራች የሆኑት  
የአሜሪካ ድምፅ

ትራምፕ የነዳጅ ኢንዱስትሪ ሥራ አስፈፃሚን ለኃይል መስሪያ ቤቱ ጸሐፊነት መረጡ

በቅርቡ ስልጣን የሚረከቡት  ዶናልድ ትራምፕ አዲሱን አስተዳደራቸውን እያዋቀሩ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት ፣ የነዳጅ መስክ አገልግሎት ድርጅት መስራች የሆኑት  ክሪስ ራይትን የ ዩናእትድ ስቴትስን  የኃይል መስሪያቤት እንዲመሩ መርጠዋል። የሽግግር ቡድኑ የፕሬዚደንቱን ምርጫ  ቅዳሜ ከሰዓት በኃላ ይፋ አድርጓል ። አርብ እለት ትራምፕ  ፣ የአገር ውስጥ ጉዳይ መስሪያቤትን እንዲመሩ በመረጧቸው  የቀድሞው የሰሜን ዳኮታ ግዛት አስተዳዳሪ  ዳግ በርገም የሚመራ አዲስ ብሔራዊ የኃይል ምክር ቤት ይፋ አድርገዋል። በአዲሱ ኃላፊነታቸው መሰረት በርገም በኃይል ማመንጨት ፍቃድ ፣ምርት ፣ ስርጭት ፣ቁጥጥር እና ማጓጓዝ ላይ የሚሳተፉትን  ሁሉንም አስፈፃሚ ቅርንጫፍ ተቋማት የሚያካልል  ቡድንን እንደሚመሩ   ትራምፕ በመግለጫቸው አስታውቀዋል ። የብሔራዊ  ኃይል  ምክር ቤት ሊቀመንበር እንደመሆናቸው ፣ በርገም  በብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱም መቀመጫ  እንደሚኖራቸው  ተመራጩ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል። ራይት ፣ ኮሎራዶ ላይ መሰረት ያደረገው ፣ ሊበርቲ ኢነርጂ የተሰኘ ኩባንያ ዋና ኃላፊ ቢሆኑም ፣ የፖለቲካ ልምድ ግን የላቸውም ። ነዳጅ ማመንጨትን  ጨምሮ ለነዳጅ ዘይት እና ጋዝ ኢንዱስትሪ ተሟጋች በመሆናቸውም ይታወቃሉ። በአውሮፓዊያኑ  2019 ፣ አደገኛ አለመሆኑን ለማሳየት ፈሳሽ ነዳጅ እስከመጠጣት ደርሰዋል ። በመጋቢት 2024 የአውሮፓዊያኑ ዘመን ይፋ የተደረገው የአሜሪካ  ኃይል መረጃ አስተዳደር ሪፖርት እንደሚያሳየው ፣ ሀገሪቱ ላለፉት ስድስት ተከታታይ ዓመታት  በማንኛውም ጊዜ ከማንኛውም ሀገር የበለጠ ድፍድፍ ዘይት አምርታለች። ወርሃዊ የአሜሪካ ድፍድፍ ዘይት ምርት መጠን በአውሮፓዊያኑ ታህሳስ 2023 ከ13.3 ሚሊዮን በርሜል የደረሰ ሲሆን ፣ ይህም በወረሃዊው የምርት መጠን ልኬት  ከፍተኛው  ሆኖ ተመዝግቧል(AP)። 

እስራኤል ደቡባዊ ቤሩትን በአየር ደበደበች 

የእስራኤል ጦር ሃይል ነዋሪዎች ከአካባቢው ለቀው እንዲወጡ ካስጠነቀቀ ትንሽ ቆይታ በኋላ በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ደቡባዊ ክፍል ፍንዳታ ሲከሰት የሚያሳዩ የ
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል ደቡባዊ ቤሩትን በአየር ደበደበች 

የእስራኤል ጦር ሃይል ነዋሪዎች ከአካባቢው ለቀው እንዲወጡ ካስጠነቀቀ ትንሽ ቆይታ በኋላ በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ደቡባዊ ክፍል ፍንዳታ ሲከሰት የሚያሳዩ የተንቀሳቃሽ ምስሎች ወጥተዋል፡፡  የሂዝቦላ ታጣቂ ዋና ይዞታ እንደሆነ በሚነገርለት በዚህ አካባቢ እስራኤል ከማክሰኞ እለት ጀምሮ ተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሰች ይገኛል፡፡  ጥቃቱ ከመፈጸሙ ጥቂት ቀደም ብሎ የእስራኤል ወታደራዊ ቃል አቀባይ አቪሻይ አድራኢ በሃሬት ህሪክ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎችን ለቀው እንዲወጡ በ X የማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ጥረ አስተላልፈው ነበር፡፡  የሊባኖስ መንግስት ብሄራዊ የዜና ወኪል (ኤን ኤን ኤ) በበኩሉ «ጠላት»  ሲል በገለጻት እስራኤል በሃሬት ሂሪክ አቅራቢያ የደረሰውን ጨምሮ ሶስት የአየር ጥቃቶች ደርሰዋል ብሏል፡፡  እስራኤል በደቡባዊ ቤይሩት ላይ ተደጋጋሚ የአየር ድብደባ መፈጸሟን ተከትሎ በርካታ ንፁሀን ዜጎች ከአካባቢው እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል፡፡    ሂዝቦላ በበኩሉ በሰሜናዊ እስራኤል የሚገኘው የእግረኛ ጦር ሻለቃ ዋና መሥሪያ ቤት ላይ ያነጣጠረ ሁለት የሮኬት ጥቃቶችን ሌሊት ላይ ማድረሱን ገልጿል።  የሊባኖስ ባለስልጣናት ሂዝቦላ እና እስራኤል የተኩስ ልውውጥ ከጀመሩበት ካለፈው አመት ጥቅምት ጀምሮ ከ3,440 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ አስታውቀዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የሊባኖስ መንግስት መገናኛ ብዙሃን የእስራኤል የምድር ጦር ሃይሎች በሊባኖስ ውጊያ ከጀመሩ ከስድስት ሳምንታት በኋላ ወደ ሊባኖስ ጠልቀው መግባታቸውንና ከሂዝቦላህ ታጣቂዎች ጋር ከፍተኛ ውጊያ ካደረጉ በኋላ እንዳፈገፈጉ ዘግበዋል። ሪፖርቶቹ ዛሬ ጥዋት የእስራኤል ወታደሮች በደቡብ ሊባኖስ በምትገኘው ቻማ መንደር በእስራኤል ድንበር አቅራቢያ የሚገኝ ስትራቴጂካዊ ኮረብታ መያዛቸውንና ቆይተው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡  የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች የቤይሩትን ደቡባዊ ሰፈሮች እና ሌሎች አካባቢዎችን እየደበደቡ ባሉበት ወቅትም የሊባኖስ እና የሂዝቦላህ ባለስልጣናት ጦርነቱን ለማቆም በዩናይትድ ስቴትስ የቀረበውን ረቂቅ ሀሳብ እያጤኑ እንደነበረ ተገልጿል፡፡

በህንድ በሆስፒታል በተነሳ እሳት አስር ህጻናት ሞቱ 

በሰሜናዊ ህንድ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ በአራስ ሕፃናት ከፍተኛ እንክብካቤ ክፍል ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ አስር አዲስ የተወለዱ ሕፃናትን ሲሞቱ 16 ሌሎች ደ
የአሜሪካ ድምፅ

በህንድ በሆስፒታል በተነሳ እሳት አስር ህጻናት ሞቱ 

በሰሜናዊ ህንድ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ በአራስ ሕፃናት ከፍተኛ እንክብካቤ ክፍል ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ አስር አዲስ የተወለዱ ሕፃናትን ሲሞቱ 16 ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል ሲሉ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡  አርብ አመሻሽ ላይ በህንድ ኡታር ፕራዴሽ ግዛት በጃንሲ ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥየእሳት አደጋው በተከሰተበት ወቅት 55 ጨቅላ ህጻናት ህክምና እየተደረገላቸው ነበር ተብሏል፡፡  የእሳት አደጋ መከላከል ባለሙያዎችም አደጋው ከተከሰተ ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ የህይወት ማዳን ስራ መጀመራቸውንና ይህም የህይወት አድኑን ጥረት አዘግይቶታል ሲሉ የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡  በህንድ ውስጥ የእሳት ቃጠሎ የተለመደ መሆኑን የገለጸው የአሶሽየትድ ፕረስ ዘገባ የግንባታ ህጎች እና የደህንነት ደንቦች ብዙ ጊዜ በቤት ገንቢዎች እና በነዋሪዎች ይጣሳሉ ብሏል፡፡. ይህም በሀገሪቱ ካለው ደካማ የጥገና ስርዓት እና የእሳት አደጋ መከላከያ መሳሪያዎች እጥረት ጋር ተዳምሮ በእሳት አደጋ ለሚከሰት ሞት ምክንያት ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡ 

የቡድን 20 ሃገራት በአየር ንብረት ለውጥ ዙርያ ከስምምነት እንዲደረስ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ ተመድ አሳሰበ 

የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ሃላፊ  ለታዳጊ ሃገራት በሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ዙርያ በኮፕ 29  እየተደረጉ ያሉ ድርድሮች ገና ረጅም መንገድ እንደሚቀራ
የአሜሪካ ድምፅ

የቡድን 20 ሃገራት በአየር ንብረት ለውጥ ዙርያ ከስምምነት እንዲደረስ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ ተመድ አሳሰበ 

የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ሃላፊ  ለታዳጊ ሃገራት በሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ዙርያ በኮፕ 29  እየተደረጉ ያሉ ድርድሮች ገና ረጅም መንገድ እንደሚቀራቸው አስጠንቅቀዋል፡፡  በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ተደራዳሪዎቹ ልዩነታቸው በማጥበብ ከስምምነት ለመድረስ እየተነጋገሩ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በቀጣዩ ሳምንት በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ ከሚደረገው የሚንስትሮች ስብሰባ አስቀድሞ ከስምምነት ለመድረስ ፍላጎት ቢኖርም በዋና ዋና ጉዳዮች ግን አሁንም ከስምምነት መድርስ አልተቻለም ተብሏል፡፡  የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ሀላፊ ሲሞን ስቲል የዓለማችን ታላላቅ ኢኮኖሚዎች እና ከፍተኛ ብክለትን የሚያካትቱ የቡድን 20 ሀገራት መሪዎች ሰኞ በብራዚል ሲገናኙ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡት ተማጽነዋል።  ለአለም አቀፍ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀቶች ተጎጅ የሆኑት አንዳንድ ታዳጊ ሀገራት ከአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመቋቋምና ወደ ታዳሽ ሃይል እንዲሸጋገሩ  1.3 ትሪሊዮን ዶላር ዓመታዊ ድጋፍ ጠይቀዋል፡፡   ይህ አሃዝም አሜሪካን፣ የአውሮፓ ህብረት እና ጃፓንን ጨምሮ ለጋሾች ከሚከፍሉት 10 እጥፍ በላይ ነው። 

«ኢላን መስክ ሉዓላዊነታችንን ሊያከብሩ ይገባል» የጣሊያን ፕሬዝደንት

ጣሊያን ወደ ሀገሯ የሚጓዙ ፍልሰተኞች ውሳኔ እስከሚሰጣቸው አልቤኒያ በሚገኙ የእስር ካምፖች ለማቆየት ያወጣችው እቅድ የሕጋዊነት ጉዳይ መሰናክል አጋጥሞታል
የአሜሪካ ድምፅ

«ኢላን መስክ ሉዓላዊነታችንን ሊያከብሩ ይገባል» የጣሊያን ፕሬዝደንት

ጣሊያን ወደ ሀገሯ የሚጓዙ ፍልሰተኞች ውሳኔ እስከሚሰጣቸው አልቤኒያ በሚገኙ የእስር ካምፖች ለማቆየት ያወጣችው እቅድ የሕጋዊነት ጉዳይ መሰናክል አጋጥሞታል። ሮም ላይ ጉዳዩን የተመለከቱት ዳኞች ጉዳዩን ወደ አውሮፓ ሕብረት ፍርድ ቤት መርተውታል። አህጉራዊው ችሎት ውሳኔውን ለመስጠት ወራት ወይም ዓመታት ሊወስድ እንደሚችል ጠቅሶ ሄንሪ ሪጅዌል ከለንደን ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ የተካሄደውን ምርጫ አወደሰች

የኢትዮጵያ መንግስት በያዝነው ሳምንት ቦሶማሌላንድ የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አወደሰ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ
የአሜሪካ ድምፅ

ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ የተካሄደውን ምርጫ አወደሰች

የኢትዮጵያ መንግስት በያዝነው ሳምንት ቦሶማሌላንድ የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አወደሰ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ “’ምርጫው በሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ መንገድ’ በመካሄዱ ኢትዮጵያ የሶማሌላንድን ሕዝብ እንኳን ደስ አለህ ትላለች” ብሏል። መግለጫው በተጨማሪም “ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫ” በማካሄዱ ለሶማሌላንድን ብሄራዊ ምርጫ ኮሚሽን ያለውን አድናቆት ገልጧል። «ይህ ሂደት የሶማሌላንድን አስተዳደር እና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መጎልበት የሚያንፀባርቅ ነው» ሲልም አክሏል። የኢትዮጵያ እና የሶማሌላንድ ጠንካራ ግንኙነት ለዓመታት የዘለቀ ሲሆን፤ እየተገባደደ ባለው የአውሮፓውያኑ 2024 መጀመሪያ ላይ ኢትዮጵያን ከሶማሌላንድ 20 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የባህር ዳርቻ በሊዝ መከራየት የሚያስችል እና በምላሹ ለሶማሌላንድ ሉአላዊ እውቅና የሚያስገኝ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን የሃርጌሳ ባለስልጣናት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ይሁንና ሶማሌላንድን የግዛቷ አካል አድርጋ የምትመለከተው ሶማሊያ ‘ሉዓላዊነቴን ጥሷል’ ስትል በሁለቱ እገኖች የተፈረመውን ስምምነት አውግዛለች። ሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ በበኩላቸው ስምምነቱን ‘ትክክለኛ ነው’ ሲሉ ይከላከላሉ። የሶማሌላንዱ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ ጉሌይድ አህመድ ጃማ በሰጡት አስተያየት እንደጠቆሙት፤ የወቅቱ የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ በምርጫው ካሸነፉ የመግባቢያ ሰነዱን ተግባራዊ ያደርጋሉ። ቅሬታ እንዳላቸው የገለጡ ተቃዋሚ ቡድኖችም በበኩላቸው ስምምነቱን መቀበላቸው ተመልክቷል።

ትረምፕ የደህንነት ተቋማትን እንዲመሩ የረጅም ጊዜ ደጋፊዎቻቸውን አጭተዋል

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ የአሜሪካ ማዕከላዊ የምርመራ ቢሮ (ሲአይኤ) እንዲመሩ ያጩት፣ የረጅም ጊዜ አጋራቸውና ደጋፊያቸው የነበሩ ግለሰብን ነው። የ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ የደህንነት ተቋማትን እንዲመሩ የረጅም ጊዜ ደጋፊዎቻቸውን አጭተዋል

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ የአሜሪካ ማዕከላዊ የምርመራ ቢሮ (ሲአይኤ) እንዲመሩ ያጩት፣ የረጅም ጊዜ አጋራቸውና ደጋፊያቸው የነበሩ ግለሰብን ነው። የአሜሪካ የደህንነት ተቋማትን እንዲመሩ ያጩት ደግሞ የመንግሥት ሥልጣን ልምድ የሌላቸውንና፣ ተቋማቱን ሊያምሱ ይችላሉ ተብሎ የሚሰጉ ግለሰብን ነው። የቪኦኤ የብሔራዊ ደህንነት ዘጋቢ ጀፍ ሰልዲን ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የቀድሞው የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አህመድ ሲላንዮ አረፉ

የቀድሞው የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አህመድ ሞሃመድ ሞሃሙድ ሲላንዮ ዛሬ አርብ በ88 ዓመታቸው ሃርጌሳ ውስጥ ማረፋቸውን የሶማሌላንድ ቴሌቭዥን አስታወቀ። እንደ
የአሜሪካ ድምፅ

የቀድሞው የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አህመድ ሲላንዮ አረፉ

የቀድሞው የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አህመድ ሞሃመድ ሞሃሙድ ሲላንዮ ዛሬ አርብ በ88 ዓመታቸው ሃርጌሳ ውስጥ ማረፋቸውን የሶማሌላንድ ቴሌቭዥን አስታወቀ። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2010 በከፍተኛ የሕዝብ ድምፅ ለአምስት አመት የስልጣን ዘመን የተመረጡት ሲላንዮ፤ የሥራ ዘመናቸው ለተከሉት ሁለት ዓመታት ከተራዘመ በኋላ፤ በአሁኑ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ እስከ ተተኩበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር 2017 ድረስ አገልግለዋል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1982 የተመሰረተውን እና በኢትዮጵያ መንግስት ይደገፍ የነበረውን የሶማሌ ብሔራዊ ንቅናቄ የተቀላቀሉት ሲላንዮ የአማፂ ድርጅት መርተዋል። በመጀመሪያው የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት የቀድሞው አማጺ መሪ አብዲራህማን አሊ ቱር እስከተኩበት ጊዜ ድረስም አማጺ ቡድኑን ለበርካታ አመታት መርተዋል። ሲላንዮ የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት መሪዎች ጋር ውይይት ጀምረው ነበር። ከአሁኑ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ የመጀመሪያ የስልጣን ዘመን፤ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር 2014 አንስቶ በሁለቱ ወገኖች መካከል ተከታታይ ውይይቶች ቢካሄዱም፤ ጥረቶቹ በሙሉ ለስኬት ሳይበቁ ቀርተዋል። የሲላንዮ ዜና እረፍት የተሰማው ሶማሌላንድ አራተኛውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ካካሄደች ሁለት ቀናት በኋላ መሆኑ ነው። የህልፈታቸው መንስኤ ይፋ አልተደረገም። የቀድሞው የሶማሌላንድ መሪ የቀብር ሥነ ስርአታቸው ሰኞ እንደሚደሚፈጸም በዜና ዕረፍታቸው ተጠቅሷል።

በዩናይትድ ስቴትስ የምርጫ ታሪክ ዳግም ወደ ዋይት ሃውስ ለመመለስ ዕድል ያገኙት ሁለተኛው ፕሬዝዳንት

ባለፈው ማከኞው ምርጫ በከፍተኛ ድምጽ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን፤ የእንደራሴዎች ምክር ቤቱን ከእጁ ያስገባውን እና እስካሁን በተቆጠረውም ድምጽ የተወካዮች ምክር ቤ
የአሜሪካ ድምፅ

በዩናይትድ ስቴትስ የምርጫ ታሪክ ዳግም ወደ ዋይት ሃውስ ለመመለስ ዕድል ያገኙት ሁለተኛው ፕሬዝዳንት

ባለፈው ማከኞው ምርጫ በከፍተኛ ድምጽ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን፤ የእንደራሴዎች ምክር ቤቱን ከእጁ ያስገባውን እና እስካሁን በተቆጠረውም ድምጽ የተወካዮች ምክር ቤቱን ውጤት በአብላጫ ድምጽ እየመራ ያለው የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ ያሁኑ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የካቢኔ አባሎቻቸውንና ከፍተኛ አማካሪዎቻቸውን ከወዲሁ ይፋ ማድረግ ይዘዋል። ዳግም ወደ ዋይት ሃውስ የሚመለሱበትን ያልተጠበቀ ከፍተኛ ድምጽ ያገኙትን የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕን ለዚህ ስኬት ያበቁት ምክኒያቶች የፖለቲካ አዋቂዎችን እና የሌሎችን ትኩረት በተመሳሳይ ስበዋል። በማናቸውም ሁኔታዎች በሙሉ ልባቸው ትራምፕን በመደገፍ ከሚታወቁት የፓርቲያቸው አጥባቂ ደጋፊዎች፤ ለሁለቱም ፓርቲዎች ወገንተኝነት እስከ ከሌላቸው መራጮች እና ብሎም በዲሞክራት ፓርቲ ደጋፊነታቸው እስከሚታወቁ በርካቶች ድረስ፤ በተመሳሳይ ድምጻቸውን ለትረምፕ ለመስጠት የወሰኑባቸው እነኚህ ሁኔታዎች፤ ያልጠበቁት የገጠማቸውን የተፎካካሪው ፓርቲ ደጋፊዎች ጨምሮ ብዙዎችን ለውይይት መጋበዛቸው አልቀረም። በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን የሕግ መምህሩንና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኙን ዶ/ር ተሻገር ወርቁን አነጋግረናል። ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡  

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳሕለ ወርቅ ዘውዴ በበጎ ፈቃድ በተሰባሰቡ ሴቶች ተመሰገኑ

በበጎ ፈቃድ በተሰባሰቡ ሴቶች ጉዳይ ላይ በሚሠሩ ሀገር በቀል መሪዎች ዛሬ በምስጋና የተሸኙት የቀድሞ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ ሴቶችን የ
የአሜሪካ ድምፅ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳሕለ ወርቅ ዘውዴ በበጎ ፈቃድ በተሰባሰቡ ሴቶች ተመሰገኑ

በበጎ ፈቃድ በተሰባሰቡ ሴቶች ጉዳይ ላይ በሚሠሩ ሀገር በቀል መሪዎች ዛሬ በምስጋና የተሸኙት የቀድሞ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ ሴቶችን የማብቃት ጅምር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠየቁ። በሴቶች የተጀመሩ ሥራዎች ድጋፍ ሊደረግባቸው እንደሚገባ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቷ በንግግራቸው በሴቶች ላይ ካተኮሩ ንግግሮች ውጭ የሰጡት አስተያየት የለም። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የዝግጅቱ ታዳሚዎች፤ በመንግሥት በኩል ተገቢውን አሸኛኘት ስላልተሰጣቸው ቅር እንደተሰኙ ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በአየር ንብረት ጉባዔው የ1.3 ትሪሊየን ዶላር አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት እንዲጸድቅ ግፊት እየተደረገ ነው

በቅርቡ አዲስ በተሾሙት የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ እየተመራ፣ በአዘርባይጃን ዋና ከተማ ባኩ እየተካሄደ ባለው 29ኛው ዓለም አቀፍ የአየ
የአሜሪካ ድምፅ

በአየር ንብረት ጉባዔው የ1.3 ትሪሊየን ዶላር አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት እንዲጸድቅ ግፊት እየተደረገ ነው

በቅርቡ አዲስ በተሾሙት የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ እየተመራ፣ በአዘርባይጃን ዋና ከተማ ባኩ እየተካሄደ ባለው 29ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይ በመሳተፍ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ልዑክ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከባድ ጉዳት እየደረሰባቸው ላሉ ያላደጉ ሀገራት ለመስጠት ቃል የተገባው የገንዘብ ድጋፍ ወደ 1.3 ትሪሊየን ዶላር ያድጋል ብሎ እንደሚጠብቅ፣ በድርድሩ ላይ ተሳታፊ የሆኑት የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያ አቶ ያሬድ አበራ ገልጸዋል። «የአፍሪካ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትሮች ጉባዔ የወቅቱ ሊቀመንበር የኾነችው ኢትዮጵያ ከሌሎች ታዳጊ ሀገራት ሀገራት ጋራ በመሆን የገንዘብ ድጋፉ ስምምነት ላይ እንዲደርስ ጥረት እያደረገች ነው» ያሉት አቶ ያሬድ፣ ከከርሰ ምድር የሚወጣ ኃይል አጠቃቀምን ለመቀነስ እና የዓለምን ሙቀት ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ግን አሁንም አዳጋች መሆኑን አመልክተዋል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም. ፓሪስ ላይ በተካሄድው 21ኛው ጉባዔ የዓለም ሀገራት በፈረሙት የፓሪስ ስምምነት የዓለም ሙቀትን 1.5 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ላይ ለመገድብ ተስማምተው ነበር። ይህንንም ለማሳካት እ.አ.አ በ2030 ሙቀት ማመቅ የሚችሉ የጋዝ አይነቶችን በ43 ከመቶ ለመቀነስ እና በ2050 ዓለምን ከካርበንዳይኦክሳይድ የፀዳ ለማድረግ ቃል ገብተዋል። ባለፉት 40 ዓመታት ባልታየ ድርቅ ሲሰቃይ የነበረው የአፍካ ቀንድ አካባቢ ባለፈው ዓመት የተከሰተው ከፍተኛ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ ከ1.6 ሚሊየን በላይ ሰዎች እንዲፈናቀሉ አድርጎ የነበረ ሲሆን ከእነዚኽ ውስጥ 396 ሺሕ የሚሆኑት የሚገኙት ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን አክሽን አጌንስት ሀንገር የተሰኘው በአፍሪካ ቀንድ ረሃብን ለማጥፋት የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ርዳታ ሰጪ መረጃ ያመለክታል። ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የሚያከትለው ተደጋጋሚ የጎርፍ አደጋም መንገዶችን እና ቤቶችን ከማጥለቅለቁ እና ነዋሪዎችን ከማፈናቀሉ በተጨማሪ የውሃ ምንጮች እንዲበቀሉ እንዲሁም የጤና ተቋማት እንዲወድሙ በማድረጉ፣ በክልሉ ለበሽታ ተጋላጭነት ጨምሯል። በአየርን ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱት እነዚህ ተደራራቢ ጉዳቶችን እያስተናገደች ያለችው ኢትዮጵያ በአየርን ንብረት ለውጥ ተጠቂ ከሆኑ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር የጋራ አቋም በመያዝ በዓለም አቀፍ ጉባዔው ድምፃቸውን እያሰሙ ነው። /ከአቶ ያሬድ አበራ ጋራ የተደረገውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።/    

ለቋሚ ደመወዝተኞች የሥራ ግብር እንዲቀነስ ተጠየቀ

በኢትዮጵያ የብር የመግዛት አቅም መዳከምን ተከትሎ ቋሚ ደመወዝተኞችን የኑሮ ሁኔታው እየፈተናቸው መሆኑ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ገለጸ፡፡
የአሜሪካ ድምፅ

ለቋሚ ደመወዝተኞች የሥራ ግብር እንዲቀነስ ተጠየቀ

በኢትዮጵያ የብር የመግዛት አቅም መዳከምን ተከትሎ ቋሚ ደመወዝተኞችን የኑሮ ሁኔታው እየፈተናቸው መሆኑ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ገለጸ፡፡ የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ መንግሥት የሥራ ግብር መቀነስን ጨምሮ የኑሮ ጫናውን የሚያቃልሉ ኢኮኖሚያዊ ርምጃዎች እንዲወስድ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድን በደብዳቤ መጠየቃቸውን ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሃብት መምህር የሆኑት ዶክተር አጥላው ዓለሙ በበኩላቸው «መንግሥት የሥራ ግብር መቀነስን ጨምሮ ቋሚ ደመወዝተኞች ተጨማሪ ገቢ የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይኖርበታል» ብለዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከገንዘብ ሚንስቴር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ ነገር ግን የገንዘብ ሚንስትር ደኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ በቅርቡ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ መንግሥት የደመወዝ ጭማሪ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ጫናውን ለማቃለል እየሠራ ስለመሆኑ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡  

ተመራጩ ፕሬዚደንት ፈጥነው የአገር ውስጥ ፖሊሲዎች ለውጥ እንደሚተገብሩ ይጠበቃል 

ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ኋይት ሐውስን የሚረከቡት ገና የፊታችን ጥር ወር ሲመጣ ነው፡፡ ቢሆንም ከወዲሁ በቀጣዮቹ አራት ዓመታት
የአሜሪካ ድምፅ

ተመራጩ ፕሬዚደንት ፈጥነው የአገር ውስጥ ፖሊሲዎች ለውጥ እንደሚተገብሩ ይጠበቃል 

ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ኋይት ሐውስን የሚረከቡት ገና የፊታችን ጥር ወር ሲመጣ ነው፡፡ ቢሆንም ከወዲሁ በቀጣዮቹ አራት ዓመታት ለሚተገብሯቸው የአገር ውስጥ ፖሊሲዎች መሠረትን መጣል እና ዕቅዶች ማውጣት ጀምረዋል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ የዋሽንግተን ከፍተኛ ዘጋቢ ካሮሊን ፕረሱቲ ዘገባ ዝርዝር አለው፡፡

የሶማሊላንድ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች ውጤቱን እንዲቀበሉ ጥሪ ቀረበ 

በሶማሊላንድ ምርጫ የድምፅ ቆጠራው በቀጠለበት ባሁኑ ወቅት ሶስቱ ፕሬዝዳንታዊ እጩዎች እና ደጋፊዎቻቸው የምርጫውን ውጤት ይቀበሉ ዘንድ ምዕራባውያን ዲፕሎማ
የአሜሪካ ድምፅ

የሶማሊላንድ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች ውጤቱን እንዲቀበሉ ጥሪ ቀረበ 

በሶማሊላንድ ምርጫ የድምፅ ቆጠራው በቀጠለበት ባሁኑ ወቅት ሶስቱ ፕሬዝዳንታዊ እጩዎች እና ደጋፊዎቻቸው የምርጫውን ውጤት ይቀበሉ ዘንድ ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች እያሳሰቡ ነው። «ለዲሞክራሲያዊ ሂደቱ የሚሰጡትን ድጋፍ ለማጽናት» በተለያዩ ከተሞች ያሉ 30 የምርጫ ጣቢያዎችን መጎብኘታቸውንም ዲፕሎማቶቹ ተናግረዋል። ባለሥልጣናቱ በበኩላቸው በሚቀጥለው ሳምንት አንዳንድ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤቶች ይታወቃሉ ብለው ያምናሉ።

ደቡብ ሱዳን ወደዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለማምራት ተጨባጭ እርምጃ  እንድትወስድ  የመንግሥታቱ ድርጅት ተልዕኮ ጠየቀ

  በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል ‘አንሚስ’ በመባል የሚታወቀው የተባበሩት መንግስታት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ፣ ‘ያልተጠበቀ’ በተባለ እርምጃ የሃገሪቱ የፖለቲ
የአሜሪካ ድምፅ

ደቡብ ሱዳን ወደዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለማምራት ተጨባጭ እርምጃ  እንድትወስድ  የመንግሥታቱ ድርጅት ተልዕኮ ጠየቀ

  በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል ‘አንሚስ’ በመባል የሚታወቀው የተባበሩት መንግስታት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ፣ ‘ያልተጠበቀ’ በተባለ እርምጃ የሃገሪቱ የፖለቲካ መሪዎች ለሰላም ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ እርምጃ እንዲወስዱ አሳሰበ። ‘አንሚስ’ በደቡብ ሱዳን ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል መሻሻል እየተመዘገበ መሆኑን የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ መኖሩን ጠይቋል። ሺላ ፖኒ ከጁባ ያደረሰችንን ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፡፡

እስራኤል ደማስቆን ከአየር ደበደበች

እስራኤል በሶሪያ መዲና ደማስቆ ሁለት ሥፍራዎችን ከአየር መደብደቧን የሶሪያ መንግሥት የዜና አገልግሎት አስታውቋል። በድብደባው 15 ሰዎች ተገድለዋል። ሌሎች
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል ደማስቆን ከአየር ደበደበች

እስራኤል በሶሪያ መዲና ደማስቆ ሁለት ሥፍራዎችን ከአየር መደብደቧን የሶሪያ መንግሥት የዜና አገልግሎት አስታውቋል። በድብደባው 15 ሰዎች ተገድለዋል። ሌሎች 16 ሰዎች መጎዳታቸውንም ዜና አገልግሎቱ አስታውቋል። በጥቃቱ  አንዱ ኢላማ የነበረው 'እስላማዊ ጂሃድ’ የተሰኘ የፍልስጤማውያን ቡድን ይጠቀምበት የነበረ ቢሮ መሆኑ ታውቋል። ማዘኽ እና ኩድሳያ በተሰኙ ሥፍራዎች የሚገኙ ሁለት ሕንጻዎች የአየር ጥቃት ደርሶባቸዋል። ማዘኽ በተሰኘው ሥፍራ የሚገኝ ባለ 5 ፎቅ ሕንጻ በሚሳይል ተመትቶ ፈርሶ ማየቱን የአሶሲዬትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ ከሥፍራው ዘግቧል። የእስራኤል ሠራዊት “ሽብርተኛ” ሲል በጠራው ድርጅትና አባላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን  አስታውቋል። ‘እስላማዊ ጂሃድ’ የተሰኘው ቡድን ባለፈው ዓመት እ.አ.አ የጥቅምት 7 ቀን በእስራኤል ላይ ጥቃት በተሰነዘረበት ወቅት ተሳታፊ ነበር ሲል የእስራኤል ሠራዊት ያስታውቃል። በጥቃቱ 1ሺሕ 200 ሰዎች ሲገደሉ 250 የሚሆኑ ደግሞ ታግተው ወደ ጋዛ ተወስደው ነበር። ሠራዊቱ አስፈላጊ ሁኖ ሲያገኘው በ ‘እስላማዊ ጂሃድ’ ላይ እርምጃ እንደሚወስድም  አስታውቋል። እስራኤል ጋዛ ላይ ባደረሰችው ጥቃት እስከ አሁን በአብዛኛው ሴቶች እና ሕፃናት ጨምሮ  ከ43 ሺሕ በላይ ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጤማውያኑ የጤና ባለሥልጣናት ያስታውቃሉ። ባለሥልጣናቱ  በሚሰጧቸው አሐዞች ተዋጊዎችንና ሲቪሎችን ለይተው እንደማያቀርቡ የአሶሶዬትድ ፕረስ ዘገባ አያይዞ አመልክቷል።

የአውሮፓ ኮሚሽን ሜታ ላይ የ840 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ጣለ

የፌስቡክ እናት ኩባንያ ሜታ ‘ማርኬትፕሌስ’ የተሰኘውን የማስታወቂያ አገልግሎት ከማኅበራዊ መገናኛው ፌስቡክ ጋራ አስተሳስሮ በማቅረብ በሌሎች የማስታወቂያ
የአሜሪካ ድምፅ

የአውሮፓ ኮሚሽን ሜታ ላይ የ840 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ጣለ

የፌስቡክ እናት ኩባንያ ሜታ ‘ማርኬትፕሌስ’ የተሰኘውን የማስታወቂያ አገልግሎት ከማኅበራዊ መገናኛው ፌስቡክ ጋራ አስተሳስሮ በማቅረብ በሌሎች የማስታወቂያ አገልግሎቶች ላይ ፍትሃዊ ያልሆነ ጫና አሳድሯል፣ በዚህም የአውሮፓ ኅብረትን ህግ ጥሷል በሚል የኅብረቱ ኮሚሽን የ840.24 ዶላር መቀጫ እንዲከፍል አዟል። ሜታ የፌስቡክ ማርኬትፕሌስ ያልተገባ ጥቅም እንዲያገኝ አድርጓል ሲል ኮሚሽኑ አስታውቋል። ሜታ በበኩሉ ቅጣቱን ይግባኝ እንደሚል አስታውቆ፣ እስከዛው ግን የተጠቀሱትን ችግሮች በተመለከት አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚሻና ህጉን በማክበር እንደሚሰራ አስታውቋል። ፌስቡክ፣ ማርኬትፕሌስ የተሰኘውን የማስታወቂያ አገልግሎት ከማኅበራዊ ሚዲያው ጋራ በማገናኘት ያልተገባ ጥቅም አግኝቷል በሚል ነበር ኩሚሽኑ ከሁለት ዓመታት በፊት ሜታ ላይ ክስ የመሠረተው። ፌስቡክ ማርኬትፕሌስን የጀመረው በእ.አ.አ 2016 ሲሆን ከአንድ ዓመት በኋላም በበርካታ የአውሮፓ ሃገራት አገልግሎቱን አስፋፍቷል። ኮሚሽኑ ሜታ የማርኬትፕሌስ አገልግሎትን ለፌስቡክ ተጠቃሚዎች ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ አቅርቧል ሲል፣ ሜታ በበኩሉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ማርኬትፕሌስን የመጠቀምም ሆነ ያለመጠቀም አማራጭ አላቸው ይላል። የአውሮፓ ኅብረትን ሕግን የሚጥሱ ኩባንያዎች ከአጠቃላይ ገቢያቸው 10 ከመቶ መቀጫ ይጣልባቸዋል።

ሙሴቪኒን ሰድቧል የተባለው ወጣት በፍ/ቤት ጥፋተኛ ተባለ

የዩጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ በሕዝብ ፊት ይገረፉ የሚል መልዕክት በቲክቶክ ያስተላለፈው የ21 ዓመት ወጣት በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብሏል። ኢማኑዌል ናቡ
የአሜሪካ ድምፅ

ሙሴቪኒን ሰድቧል የተባለው ወጣት በፍ/ቤት ጥፋተኛ ተባለ

የዩጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ በሕዝብ ፊት ይገረፉ የሚል መልዕክት በቲክቶክ ያስተላለፈው የ21 ዓመት ወጣት በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብሏል። ኢማኑዌል ናቡጎዲ፤ ሙሴቪኒ በፍ/ቤት ሲዳኙ የሚያሳይ ሐሰተኛ ቪዲዮ አቀናብሮ አጋርቷል በሚልና፣ “ፕሬዝደንቱን በመስደብና በጥላቻ ንግግር” ክስ ፍርድ ቤት ቀርቧል። ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ ኢማኑዌል በሰባት ዓመት እሥራት እንዲቀጣ ጠይቋል። ኢማኑዌል ባለፉት ሁለት ቀናት ፕሬዝደንቱንና ቤተሰባቸውን ተሳድበዋል በሚል በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ በፍ/ቤት ከተወሰነባቸው አራት ግለሰቦች አንዱ ነው። ሃገሪቱን ለ38 ዓመታት የመሩትን ሙሴቪኒ በቲክቶክ ሰድቧል የተባለ ሌላ የ21 ዓመት ወጣት ባለፈው ሐምሌ በስድስት ዓመት እሥር ተቀጥቷል። ዓለም አቀፍ ሽልማት ያገኘው ሌላው ደራሲ ካክዌንዛ ሙሴቪኒን እና ልጃቸውን ተሳድቧል በሚል ከሦስት ዓመታት በፊት በቁጥጥር ውሎ ነበር። በስደት ጀርመን የሚገኘው ካክዌንዛ በአንድ ወር እስር ቆይታው ወቅት ስቃይ እንደደረሰበት ተናግሯል።

የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የጠየቀው ኢራናዊ ሕይወቱን አጠፋ

አራት የፖለቲካ እስረኞች የማይፈቱ ከኾነ ራሱን እንደሚገድል በ X ማኅበራዊ መድረክ ላይ ያስታወቀው ኢራናዊ ጋዜጠኛና የመብት ተሟገች ሕይወቱ ማለፉን ቤተሰቦቹ
የአሜሪካ ድምፅ

የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የጠየቀው ኢራናዊ ሕይወቱን አጠፋ

አራት የፖለቲካ እስረኞች የማይፈቱ ከኾነ ራሱን እንደሚገድል በ X ማኅበራዊ መድረክ ላይ ያስታወቀው ኢራናዊ ጋዜጠኛና የመብት ተሟገች ሕይወቱ ማለፉን ቤተሰቦቹ አስታውቀዋል። የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ አገዛዝ ተቃዋሚና የቀድሞው የቪኦኤ ጋዜጠኛ ኪያኑሽ ሳንጃሪ ትላንት ረቡዕ ምሽት ላይ ነበር አራቱ የፖለቲካ እስረኞች የማይለቀቁና ይህንንም የፍትህ አካላት የማያስታውቁ ከሆነ ራሱን እንደሚያጠፋ ያስታወቀው። ሳንጃሪ ነፍሱን በምን መንገድ እንዳጠፋ ግልጽ ባይሆንም፣ ትላንት ምሽት ከአንድ ሕንፃ ላይ ወደ ታች ሲመለከት የተነሳውን ፎቶ አጋርቶ ነበር። “ማንም ሰው ሐሳቡን በመግለጹ ምክንያት መታሰረ የለበትም። ሕይወቴ ከዚህ መልዕክት በኋላ ሊያልፍ ይችላል። የምንሞተው ለሞት ካለን ፍቅር ሳይሆን ለሕይወት ካለን ፍቅር የተነሳ ነው” ሲልም ጽፏል። በአንድ ወቅት ለአሜሪካ ድምጽ ይሠራ የነበረው ሳንጃሪ በእ.አ.አ 2015 ዕድሜያቸው የገፉ እናቱን ለመንከባከብ ወደ ሃገሩ ተመልሷል። በተደጋጋሚ ሲያዝና የፍርድ ቤት መጥሪያ ይደርሰው እንደነበርም የመብት ተሟጋቾች ይገልጻሉ። ሳንጃሪ መሞቱ እንደተሰማ የሰብአዊ መብት ቡድኖች ሐዘናቸውን ገልፀዋል። “የቀድሞ የቪኦኤ ጋዜጠኛና ሃገር ወዳዱ ኪያኑሽ ሳንጃሪ  በኢራን አገዛዝ እስርና ጭቆና ምክንያት ለሞት በቅቷል።በመሞቱም ጥልቅ ሐዘን ተሰምቶኛል” ሲሉ የቪኦኤ ዲሬክተር  ማይክል አብራሞዊትዝ መልዕክታቸውን በ X ላይ አስፍረዋል።    

ሶማሌላንድ ምርጫ እያካሄደች ነው

ከሶማሊያ ተለይታ የራስ-ገዝ አስተዳደር የመሰረተችው ሶማሌላንድ ዛሬ ረቡዕ ምርጫ እያካሄደች ነው። በአፍሪካ ቀንድ ያለው ውጥረት እያየለ ባለበት ወቅት በሚካሄ
የአሜሪካ ድምፅ

ሶማሌላንድ ምርጫ እያካሄደች ነው

ከሶማሊያ ተለይታ የራስ-ገዝ አስተዳደር የመሰረተችው ሶማሌላንድ ዛሬ ረቡዕ ምርጫ እያካሄደች ነው። በአፍሪካ ቀንድ ያለው ውጥረት እያየለ ባለበት ወቅት በሚካሄደው በዚህ ምርጫ፣ መራጮች ከሦስት ፕሬዝዳንታዊ እጩዎች መካከል አንዱን ይመርጣሉ። በሶማሌላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም፣ ማንም ቢያሸንፍ ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ያላቸው መልካም ግንኙነት እንደሚቀጥል ተስፋቸውን ገልጸዋል።  (ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ)

ከ20 በላይ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በእስር ላይ እንደሚገኙ ቤተሰቦችና የመብት ድርጅት ገለጸ

ሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋራ በተያያዘ፣ ታስረው ከነበሩ ከነበሩ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል 21 እስረኞች አኹንም በእስር ላይ እንደሚ
የአሜሪካ ድምፅ

ከ20 በላይ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በእስር ላይ እንደሚገኙ ቤተሰቦችና የመብት ድርጅት ገለጸ

ሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋራ በተያያዘ፣ ታስረው ከነበሩ ከነበሩ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል 21 እስረኞች አኹንም በእስር ላይ እንደሚገኙ፣ ጉዳያቸውን ሲከታተል የቆየው 'ሂዩማን ራይትስ ፈርስት’ የተባለ የመብት ተሟጋች ድርጅት አስታወቀ። የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች በበኩላቸው፣ ቤተሰቦቻቸው በምህረት እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው በኋላ፣ በመረጃ ስህተት ምክንያት ሊለቀቁ እንዳልቻሉ ተናግረዋል። ፍትህ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ የታሳሪዎቹ ጉዳይ በቅርቡ መታየት እንደሚጀምር አስታውቋል። ዶር. ኢትባረክ ተፈሪ የተባሉ አስተያየት ሰጪ በእስር ላይ ይገኛሉ ከተባሉት 21 ሰዎች መካከል አንዱ ጥቅምት 25፣ 2013 ዓ.ም የታሰሩት ወንድማቸው እንደሚገኙበት ገልፀው፣ በተያዘው የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት በምሕረት እንዲለቀቁ ውሳኔ አግኝተው እንደነበር ይናገራሉ። ቃሊቲ የሚገኙ እስረኛ ወንድማቸውን ስም ቢጠቀስ ለወንድማቸው ደኅንነት እንደሚሰጉ የገለጹት፣ ድ.ር. ይትባረክ፣ በመረጃ ስሕተት ምክኒያት የምሕረቱ ተጠቃሚ አለመኾናቸውን ተናግረዋል። ሌላው አስተያየት ሰጪ አቶ ጉዑሽ ትርፈ ለ30 አመታት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባል ሆኖ የሠራ ወንድማቸው፣ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በተቀሰቀሰ ማግስት፣ ከሥራ ምድቡ ተይዞ መታሰሩንና ላለፉት አራት ዓመታት በእስር ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ወንድማቸው በአዲስ አበባ፣ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ታስሮ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ ጉዑሽ፣ በይቅርታ እንዲፈታ ከተወሰነለት በኋላ፣ በመረጃ ስህተት ምክንያት አለመፈታቱን ጠቅሰዋል፡፡ ወደ ተለያዩ የፌደራል እና የክልል መስሪያ ቤቶች እየተመላለስን አመልክተናል የሚሉት አስተያየት ሰጪው፣ ሆኖም እስካሁን ውጤት አልተገኘም ባይ ናቸው፡፡ ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋራ ተያይዞ የታሰሩ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጉዳይን ላለፉት አራት አመታት ሲከታተል መቆየቱን የተናገረው ‘ሂዩማን ራይትስ ፈርስት’ የተባለ ኢትዮጵያዊ የመብት ተሟጋች ድርጅት፣ እስካሁን ያልተፈቱ ታሳሪዎች መኖራቸውን አስታውቋል። የድርጅቱ ምክትል ዲሬክተር አቶ መብርሂ ብርሃነ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር በአዲሱ አመት መግቢያ ላይ፣ በርካታ ታሳሪዎችን በምህረት መልቀቁን አድንቀው፣ ሆኖም፣ አሁንም በምህረት ያልተለቀቁ መኖራውን በምርመራ ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።    ስለዚህ ጉዳይ በአሜሪካ ድምፅ የተጠየቀው የፍትህ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ የታሳሪዎቹ ጉዳይ በቅርቡ መታየት እንደሚጀምር አስታውቋል።  በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስር የሚገኘው የይቅርታና ምህረት ቦርድ ጽ/ቤት፣ ኃላፊ ተወካይ  ወይኒ ገብረሚካኤል፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ፣ “በቅርቡ ቦርዱ ሲሰበሰብ ጉዳያቸው ይታያል፣ ለቤተሰቦቻቸውም ይኸው መረጃ ተነግሯቸዋል” ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ከመከላከያ ሚኒስቴር አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረትም አልተሳካም፡፡ ቤተሰቦቻችን እስካሁን አልተፈቱም ካሉን አስተያየት ሰጪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ጉዑሽ ትርፈ፣ ስለ ኹኔታው ለማስረዳት ወደ ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የፀጥታ ዘርፍ ፅ/ቤት ብንሔድም፣ ሰሚ አላገኘንም፣ በአግባቡም አልተስተናገድንም ብለዋል፡፡ በቅሬታው ዙርያ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ቃለአቀባይ አቶ ረዳኢ ሓለፎም አስተያየት ለማግኘት ብንጥርም፣ የእጅ ስልካቸው ስለማይነሳ ለዛሬ አልተሳካም፡፡ አቶ መብርሂ ብርሀነ በበኩላቸው፣ የታሳሪዎቹ ጉዳይ በአስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡   የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ባለፈው አመት መጨረሻ ላይ ባወጣው መግለጫ፣ የ 2017 አዲስ አመትን አስመልክቶ ጉዳያቸው በወታደራዊ ፍርድ ቤቶች ታይቶ እስከ ሞት ቅጣት የሚደርስ ፍርድ የተወሰነባቸው 178 የሰራዊት አባላት በምህረት እንዲለቀቁ መንግስት መወሰኑን አመልክቷል፡፡ /ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

ጋሞ ዞን ውስጥ ታስረው ይገኛሉ የተባሉ ከ80 በላይ ሰዎች እንዲለቀቁ ቤተሰቦቻቸው ጠየቁ

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ ከዜይሴ ብሔረሰብ ቀበሌዎች የልዩ ወረዳ አደረጃጀት ጥያቄ ጋራ በተያያዘ ግጭት ታስረው እስር ቤት የቀሩ 80 ሰዎች በፖሊስና በፍርድ ቤ
የአሜሪካ ድምፅ

ጋሞ ዞን ውስጥ ታስረው ይገኛሉ የተባሉ ከ80 በላይ ሰዎች እንዲለቀቁ ቤተሰቦቻቸው ጠየቁ

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ ከዜይሴ ብሔረሰብ ቀበሌዎች የልዩ ወረዳ አደረጃጀት ጥያቄ ጋራ በተያያዘ ግጭት ታስረው እስር ቤት የቀሩ 80 ሰዎች በፖሊስና በፍርድ ቤት ምልልልስ በመጉላላት ላይ መኾናቸውን የታሳሪ ቤተሰቦችና አንድ የፓርላማ አባል ገለጹ። ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ “ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ማፍረስ” የሚል ክስ መስርቶባቸዋል። የቤተሰብ አባላቱ ግን፣ ግለሰቦቹ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ከመጠየቅ በስተቀር የሠሩት ወንጀል የለም ሲሉ መከራከሪያ አቅርበዋል። የአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር አምሳሉ ሀንኮ፣ በወረዳው ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰረ ሰው የለም፣ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ስለ ጉዳዩ አቤቱታ ቀርቦለት ክትትል በማድረግ ላይ መኾኑን ገልጿል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

ባይደን እና ትራምፕ በዋይት ኃውስ ተገናኙ

ባለፈው ሳምንት ምርጫውን ካሸነፉ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ወደ ዋሽንግተን የተመለሱት የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ከፕሬዝደንት ጆ ባይደን ጋራ ዋይ
የአሜሪካ ድምፅ

ባይደን እና ትራምፕ በዋይት ኃውስ ተገናኙ

ባለፈው ሳምንት ምርጫውን ካሸነፉ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ወደ ዋሽንግተን የተመለሱት የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ከፕሬዝደንት ጆ ባይደን ጋራ ዋይት ኃውስ ውስጥ ተገናኝተው እጅ ለእጅ ተጨባብጠዋል።  ጆ ባይደን ትረምፕን ወደ ዋይት ኃውስ የጋበዟቸው ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ለማድረግ ሲሆን በዛም እንደደረሱ “ዶናልድ እንኳን ደስ አለህ” ብለዋቸዋል። «መጪው ፕሬዝዳንት እና የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ፣ እንኳን ደስ አልዎት። እንዳልነው በቀጣይ  ሰላማዊ ሽግግር ለማድረግ በጉጉት እየጠበቅን ነው። የሚፈልጉትን ለማድረግ የምንችለውን እያደረግን ነው፣ እናም የተወሰነውን አሁን ለመነጋገር እድል እናገኛለን።» ትራምፕ በበኩላቸው ባይደን ላደረጉላቸው አቀባበል አመስግነው፣ «በአንዳንድ ነገሮች የፖለቲካው ዓለም አስደሳች አይደለም። ዛሬ ግን አስደሳች ነው። ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግር መደርጉን አደንቃለሁ። ከዚህ በዋላ በሚቻለው ሁሉ የተረጋጋ ሽግግር ይሆናል። በጣም ደስ የሚያሰኝ ነው። አመሰግናለሁ» ሲሉ ፖለቲካ አስቸጋሪ መሆኑን ግን ደግሞ በተደረገላቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።  ትራምፕ ዛሬ ጠዋት አውሮፕላናቸው ሜሪላንድ በሚገኘው  ጆይንት ቤዝ አንድሩስ የአየር ኃይል ወታደራዊ ቅጥር ያረፈ ሲሆን፣ በካፒቶል የሚገኙ የሪፐብሊካን አባላትንም አግኝተው ንግግር አድርገዋል። ትረምፕ ከአራት ዓመታት በፊት በምርጫው በተረቱበት ወቅት ባይደንን ወደ ዋይት ሃውስ አልጋበዙም። በባይደን በዓለ ሹመት ላይም አልተገኙም።

የመገናኛ ብዙኃን ዐዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ በመብት ተሟጋቾችና ሞያ ማኅበራት ተቃውሞ ገጠመው

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ዐዋጅ ቁጥር 1238/2013ን ለማሻሻል ከሁለት ሣምንታት በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ ዐዋጅ ፣ በሥራ ላይ የሚገኘው የ
የአሜሪካ ድምፅ

የመገናኛ ብዙኃን ዐዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ በመብት ተሟጋቾችና ሞያ ማኅበራት ተቃውሞ ገጠመው

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ዐዋጅ ቁጥር 1238/2013ን ለማሻሻል ከሁለት ሣምንታት በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ ዐዋጅ ፣ በሥራ ላይ የሚገኘው የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ጥበቃ የሚሰጣችውን ነጻነቶች የሚገድብና የሚዲያ ተቆጣጣሪውን አካል በአስፈፃሚው አካል ተፅዕኖ ውስጥ የሚከት ነው ሲሉ 14 የሰብአዊ መብት ድርጅቶችና የጋዜጠኞች የሞያ ማኅበራት ተቃውሞ አቀረቡ። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የሴኔት ዲሞክራቶች የፌዴራል ዳኞችን ለመሾም ጥድፊያ ላይ ናቸው 

በአሜሪካ የሕግ መወሰኛው ም/ቤት (ሴኔት) አብላጫ ድምጽ ያላቸው ዲሞክራቶች ትረምፕ ሥልጣናቸውን ከመረከባቸው በፊት የፌዴራል ዳኞችን ለመሾም በመጣደፍ ላይ ናቸ
የአሜሪካ ድምፅ

የሴኔት ዲሞክራቶች የፌዴራል ዳኞችን ለመሾም ጥድፊያ ላይ ናቸው 

በአሜሪካ የሕግ መወሰኛው ም/ቤት (ሴኔት) አብላጫ ድምጽ ያላቸው ዲሞክራቶች ትረምፕ ሥልጣናቸውን ከመረከባቸው በፊት የፌዴራል ዳኞችን ለመሾም በመጣደፍ ላይ ናቸው።  ባለፈው ሳምንት ምርጫ ውጤት መሰረት ከእ.አ.አ ጥር 3  ቀን 2025 ዓ.ም. ጀምሮ ሪፐብሊካኖቹ ሴኔቱን በበላይነት ከመቆጣጠራቸውና ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕም ሥልጣናቸውን ከመረከባቸው በፊት፣ ዲሞክራቶቹ በፕሬዝደንት ጆ ባይደን  የታጩትን 30 የፌዴራል ዳኞች ለመሾም በመረባረብ ላይ ሲኾኑ፣ ምን ያህሉን እጩዎች ማጽደቅ እንደሚችሉ ግን ግልጽ አይደለም ተብሏል።  ሴኔቱ ትላንት በሰጠው ድምጽ 51 ለ 44 በሆነ ውጤት የቀድሞዋ አቃቤ ሕግ ኤፕሪል ፔሪን በኢሊኖይ ግዛት የፌዴራል ዳኛ አድርጎ መርጧል።  ጆ ባይደን ካቀረቡት 30 እጩዎች ውስጥ 16ቱ በሴኔቱ የሕግ ኮሚቴ የተገመገሙ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ 14 እጩዎችም በኮሚቴው ይፈተሻሉ ተብሏል።  የአሜሪካ ሕገ መንግሥት በፕሬዝደንቱ የሚቀርቡትን እጩ የፌዴራል ዳኞች ገምግሞ የማጽደቅ ሥልጣኑን ለሴኔቱ ሰጥቷል። የታቻለውን ያህል ዳኞች እንደሚሾሙ በሴኔቱ የዲሞክራቲክ ፓርቲው መሪ ቻክ ሹመር አስታውቀዋል።  ዶናልድ ትረምፕ በአራት ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸው 234 የፌዴራል ዳኞችን የሾሙ ሲኾን፣ በዚህም የፍትህ አካሉን ቀኝ ዘመም እንዲሆን አድርገዋል ተብሏል። በተጨማሪም በጠቅላይ ፍ/ቤቱ የወግ አጥባቂ ዳኞችን በመሾም ስድስት ለሦስት የበላይነት እንዲኖራቸው አድርገዋል።  ባይደን በበኩላቸው በሥልጣን ዘመናቸው 214 ዳኞችን ሴኔቱ እንዲያጸድቅ አድርገዋል። በተጨማሪም ለዘብተኛ የሆኑትን ኬታንጂ ብራውን ጃክሰንን በጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኝነት ሾመዋል።     

በሶማሊላንድ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ በመካሄድ ላይ ነው 

በአፍሪካ ቀንድ ያለው ውጥረት በቀጠለበት ሁኔታ፣ ከሶማሊያ ተገንጥላ ራሷን በማስተዳደር ላይ ባለችው  ሶማሊላንድ ዛሬ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ በመካሄድ ላይ ነው። 
የአሜሪካ ድምፅ

በሶማሊላንድ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ በመካሄድ ላይ ነው 

በአፍሪካ ቀንድ ያለው ውጥረት በቀጠለበት ሁኔታ፣ ከሶማሊያ ተገንጥላ ራሷን በማስተዳደር ላይ ባለችው  ሶማሊላንድ ዛሬ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ በመካሄድ ላይ ነው።  ሶማሊላንድ ከእ.አ.አ 1991 ጀምሮ ከሶማሊያ ተገንጥላ ራሷን በማስተዳደር ላይ ስትሆን፣ በሽብር ከምትናጠው ሶማሊያ አንጻር የሰላምና መርረጋጋት ደሴት ተደርጋ ትታያለች፡፡ ሆኖም ግን ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እውቅና አልተሰጣትም።  በሃርጌሳ በመቶ የሚቆጠሩ ድምጽ ሰጪዎች ጎሕ ከመቅደዱ በፊት በድምጽ መስጪያ ጣቢያዎች ተሰልፈው ተስተውለዋል። በሌሎችም የሃገሪቱ ክፍሎች ሙቀቱ ከማየሉ በፊት በማለዳ ድምጽ ለመስጠት የወጡ ሰዎች ታይተዋል።  የወቅቱ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሂ፣ ተቀናቃኛቸው አብድራህማን ሞሃመድ እንዲሁም ሌላው ተፎካካሪ ፋይሳል አሊ ዋራቤ በማለዳ ድምጻቸውን ሰጥተዋል፡፡  ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋራ የባሕር በር አጠቃቀምን በተመለከተ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሟን ተከትሎ፣ በሶማሊያና በኢትዮጵያ መካከል ውጥረት በመስፈኑ ባልተረጋጋው ቀጠና ሌላ ግጭት እንዳይነሳ ተሰግቷል።  ፕሬዝደንት ቢሂ ኢትዮጵያ በምትኩ ለሶማሊላንድ እውቅና ትሰጣለች ቢሉም፣ የኢትዮጵያ መንግስት ይህን አላረጋገጠም። የስምምነቱ ዝርዝርም እስከ አሁን  ይፋ አልሆነም።  የቢሂ ተቀናቃኞች ስምምነቱን ሲነቅፉ አይስተዋሉም።  ከእ.አ.አ 2017 ጀምሮ በሥልጣን ላይ የቆዩት ቢሂ፣ በድጋሚ የሚመረጡ ከሆነ ስምምነቱን እንደሚያስቀጥሉ ይናገራሉ።   

የሱዳን ሉዐላዊ ም/ቤት የቻድ ድንበር መሻገሪያ ክፍት መሆኑ እንደሚቀጥል አስታወቀ

የምግብና ሌሎችንም ዕርዳታዎችን ለማድረስ እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የቻድ ድንበር መሻገሪያን ክፍት ማድረጉን እንደሚቀጥል የሱዳን ሉዐላዊ ም/ቤት ዛሬ አስታው
የአሜሪካ ድምፅ

የሱዳን ሉዐላዊ ም/ቤት የቻድ ድንበር መሻገሪያ ክፍት መሆኑ እንደሚቀጥል አስታወቀ

የምግብና ሌሎችንም ዕርዳታዎችን ለማድረስ እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የቻድ ድንበር መሻገሪያን ክፍት ማድረጉን እንደሚቀጥል የሱዳን ሉዐላዊ ም/ቤት ዛሬ አስታውቋል። አድሬ በሚል የሚታወቀው የድንበር መተላለፊያ በዳርፉር እና ኮርዶፋን ለሚገኙና ለረሃብ ለተጋለጡ ሰዎች ዕርዳታ ለማድረስ አስፈላጊ መሆኑን የረድኤት ድርጅቶች ይገልጻሉ። የመንግስት አካላት በበኩላቸው ድንበሩን ከፍቶ ማቆየት ለፍጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሣሪያ ማስተላለፊያነት እንዲያገለግል ያደርጋል በሚል ተቃውመውታል። በሃገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚገኙ ከ25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለቸነፈር የተጋለጡ መሆናቸውን እንዲሁም በዳርፉር በሚገኝ አንድ መጠለያ ረሃብ መግባቱን ባለሙያዎች አስታውቀዋል። በሱዳን ሁለቱ ተፋላሚ ጀኔራሎች “ወሳኝ” ብለው የሚገልጹትን ወታደራዊ ድል በመሻታቸው፣ ፖለቲካዊ መፍትሄ የመገኘቱን ዕድል አጥብቦታል። ጦርነቱ ከፈነዳበት ሚያዚያ 2016 ወዲህ 11 ሚሊዮን ሠዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዓለም አስከፊው መፈናቀል ሲል ገልጾታል።

የዓለም ሙቀት መጨመር የኮፕ 29 ቁልፍ የመወያያ ነጥብ ሆኖ ቀጥሏል

አብዛኛው ኢኮኖሚዋ ከከርሰ ምድር በሚወጣ ኃይል ላይ በተመሰረተው አዘርባጃን ዋና ከተማ፣ ባኩ ውስጥ ትላንት ሰኞ በተጀመረው 29ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት
የአሜሪካ ድምፅ

የዓለም ሙቀት መጨመር የኮፕ 29 ቁልፍ የመወያያ ነጥብ ሆኖ ቀጥሏል

አብዛኛው ኢኮኖሚዋ ከከርሰ ምድር በሚወጣ ኃይል ላይ በተመሰረተው አዘርባጃን ዋና ከተማ፣ ባኩ ውስጥ ትላንት ሰኞ በተጀመረው 29ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባዔ ላይ የዓለም መሪዎች የበካይ ጋዞች ልቀትን ቁጥጥር ማድረግ የሚያስችል እርምጃ እንዲወሰድ እየጠየቁ ነው። (ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ያገኛሉ)

ከኢትዮጵያ ለመውጣት የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ ኤርትራውያን ገለጹ

በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራውያን፣ የመውጫ ቪዛ ለማግኘት የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ ገለጹ። ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ ኤርትራውያን፣ ወደ ሌሎች ሀገ
የአሜሪካ ድምፅ

ከኢትዮጵያ ለመውጣት የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ ኤርትራውያን ገለጹ

በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራውያን፣ የመውጫ ቪዛ ለማግኘት የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ ገለጹ። ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ ኤርትራውያን፣ ወደ ሌሎች ሀገራት ለመሄድ ሲፈልጉ፣ የመውጫ ቪዛ ለማስመታት እስከ 4 ሺህ ዶላር ድረስ እንደሚጠየቁ ገልጸዋል፡፡ የክፍያው ምክንያት ግልፅ እንዳልኾነና ወጥነትም እንደሌለው የተናገሩት ኤርትራውያኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የክፍያውን መጠን ዳግም እንዲመለከተው ጠይቀዋል፡፡  የኢሚግሬሽና ዜግነት አገልግሎት በበኩሉ፣ እየተጠየቀ ያለው ክፍያ፣ ለመውጫ ቪዛ ሳይሆን፣ በሕገወጥ መንገድ ለቆዩበት ጊዜ የሚወሰን ቅጣት ነው ብሏል፡፡ በህገወጥ መንገድ፣ በሀገሪቱ ውስጥ እየኖሩ ያሉ የውጭ ሀገራት ዜጎች፣ በተቋሙ ተመዝግበው ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ እንዲይዙም ጠይቋል፡፡  (ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ)

ዐቃቤ ሕግ የ51 የሽብር ተከሳሾችን ክስ አሻሽሎ ቀረበ

  ዐቃቤ ሕግ፣ በእነዶር. ወንድወሰን አሰፋን የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል የተከሰሱትን 51 ተከሳሾች ክስ ዛሬ አሻሽሎ ቀረበ።  ተከሳሾቹ ከዚህ ቀደም ክሱ እን
የአሜሪካ ድምፅ

ዐቃቤ ሕግ የ51 የሽብር ተከሳሾችን ክስ አሻሽሎ ቀረበ

  ዐቃቤ ሕግ፣ በእነዶር. ወንድወሰን አሰፋን የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል የተከሰሱትን 51 ተከሳሾች ክስ ዛሬ አሻሽሎ ቀረበ።  ተከሳሾቹ ከዚህ ቀደም ክሱ እንዲሻሻል ያቀረቡትን ጥያቄ ዐቃቤ ሕግ ባለመቀበል አቤቱታ አቅርቦበት የነበረ ቢኾንም፣ ፍርድ ቤቱ ክሱ እንዲሻሻል የሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ ዛሬ ክሱን አሻሽሎ ቀርቧል።   (ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ)

Get more results via ClueGoal