የውጭ ምንዛሪ ልውውጥ የሚያከናውኑት የግል ኩባንያዎች
newsare.net
በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ልውውጥ በገበያ ዋጋ እንዲወሰን የወጣውን ፖሊሲ ተከትሎ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት እየሰፋ መምጣቱን የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ባለሞየውጭ ምንዛሪ ልውውጥ የሚያከናውኑት የግል ኩባንያዎች
በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ልውውጥ በገበያ ዋጋ እንዲወሰን የወጣውን ፖሊሲ ተከትሎ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት እየሰፋ መምጣቱን የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ባለሞያዎች ተናግረዋል፡፡ ይኹን እንጂ በጥቁር ገበያውና በመደበኛው የባንክ ምንዛሪ መካከል ያለው ልዩነት ተስፋና ስጋት መፍጠሩንም ባለሞያዎቹ ገልጸዋል፡፡ ከባንኮች በተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ግብይት አገልግሎት እንዲሰማሩ ብሄራዊ ባንክ ፈቃድ ከሰጣቸው አምስት የግል ኩባንያዎች መካከል አንዱ የኾነው የኢትዮ ፎሬክስ አክስዮን ማኅበር መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ ፖሊሲው አዎንታዊ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ የምጣኔ ሀብቱ ባለሞያው አቶ ያሬድ ኃይለመስቀል በበኩላቸው ለውጥ መኖሩን ቢቀበሉም የውጭ ምንዛሬው ዘለቄታዊ በኾነ መንገድ ሊቀረፍ የሚችለው የጥቁር ገበያው ተፈላጊነት እየቀነሰ ሲመጣ፣ ለውጡ በውጭ ንግድ ምርቶች ሲደገፍና ከገቢ ሸቀጦች ጋራ ሲገናዘብ ብቻ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ /ዝርዝሩን ከተያይዘው ፋይል ይከታተሉ/ Read more