Ethiopia



VOA60 World - Russian President Vladimir Putin signs revised nuclear doctrine

Russia: President Vladimir Putin on Tuesday signed a revised nuclear doctrine declaring that a conventional attack on Russia by any nation that is supported by a nuclear power will be considered a joint attack on his country.

በዘንድሮው የአሜሪካ ምርጫ የአፍሪካውያን ተቀዳሚ ትኩረት ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ እንደነበረ ተገለጸ

“ዩስ አፍሪካ ኢንስቲትዩት” የተሰኘ ተቋም ከምርጫው በፊት በሠራው የዳሰሳ ጥናት ኢትዮጵያውያን ጨምሮ አፍሪካውያን በዘንድሮው ምርጫ የኢኮኖሚ፣ የስደተኝነት
የአሜሪካ ድምፅ

በዘንድሮው የአሜሪካ ምርጫ የአፍሪካውያን ተቀዳሚ ትኩረት ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ እንደነበረ ተገለጸ

“ዩስ አፍሪካ ኢንስቲትዩት” የተሰኘ ተቋም ከምርጫው በፊት በሠራው የዳሰሳ ጥናት ኢትዮጵያውያን ጨምሮ አፍሪካውያን በዘንድሮው ምርጫ የኢኮኖሚ፣ የስደተኝነትና የጤና ፖሊሲዎች በምርጫው ትኩረት የሰጧቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች እንደነበሩ የተቋሙ ፕሬዘዳንት ዶክተር ታዲዮስ በላይ ተናግረዋል። በዚህ የዳሰሳ ጥናት ከ2ሺሕ በላይ በዩናይትድ ስቴትስ እና በአህጉሪቱ የሚኖሩ አፍሪካውያን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ተብሏል፡፡

በትረምፕ መመረጥ የተበረታቱ አይሁድ ሰፋሪዎች ዌስት ባንክን ወደ ራሳቸው እንደሚቀላቅሉ ተስፋ አድርገዋል

በዌስት ባንክ የሚኖሩ የአይሁድ ሰፋሪዎች ዶናልድ ትረምፕ መመረጣቸውና ማይክ ሃካቢን በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር አድርገው መሾማቸውን በደስታ ተቀብለውታ
የአሜሪካ ድምፅ

በትረምፕ መመረጥ የተበረታቱ አይሁድ ሰፋሪዎች ዌስት ባንክን ወደ ራሳቸው እንደሚቀላቅሉ ተስፋ አድርገዋል

በዌስት ባንክ የሚኖሩ የአይሁድ ሰፋሪዎች ዶናልድ ትረምፕ መመረጣቸውና ማይክ ሃካቢን በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር አድርገው መሾማቸውን በደስታ ተቀብለውታል። ዌስት ባንክን ወደ ራሳቸው ለመቀላቀል እና በጋዛ ውስጥ ሳይቀር የሰፈራ መንደር ለመገንባት ተስፋ እንዳላቸው ይናገራሉ። የቪኦኤ ዘጋቢ ሊንዳ ግራንድስቴን ከዌስት ባክን ከዱሚም የሰፋሪዎች መንደር ያጠናቀረችውን ዘገባ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ም/ቤት ያለመከሰስ መብታቸውን የተነሳው አቶ ሰዒድ አሊ መታሰራቸውን ፖሊስ አስታወቀ

ከኮሪደር ልማት ጋራ በተያያዘ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ ጠዋት ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል አቶ ሰዒድ አሊ፣ ዛሬ ከ
የአሜሪካ ድምፅ

በአዲስ አበባ ም/ቤት ያለመከሰስ መብታቸውን የተነሳው አቶ ሰዒድ አሊ መታሰራቸውን ፖሊስ አስታወቀ

ከኮሪደር ልማት ጋራ በተያያዘ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ ጠዋት ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል አቶ ሰዒድ አሊ፣ ዛሬ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ጀምሮ መታሰራቸውን ፖሊስ አስታወቀ። የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር፣ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ “ግለሰቡ ያለመከሰስ መብታቸው ከተነሳ በኋላ፣ ዛሬ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ ከመኖርያ ቤታቸው በአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው በፖሊስ ኮሚሽኑ ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል ” ብለዋል። አክለውም፣  “ጉዳዩ በምርመራ ላይ ያለ በመኾኑ ዝርዝር ሁኔታውን ከዚኽ በላይ ለመግለጽ እንቸገራለን። የምርመራ  ሥራው ከተጠናቀቀ ለሚዲያም ለሕዝብም እናሳውቃለን” ብለዋል። የአቶ ሰዒድን ያለመከሰስ መብት መነሳት በተመለከተ፣ የምክር ቤቱ የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ለምክር ቤቱ በጹሑፍ ባቀረቡት የውሳኔ ሐሳብ፣ አቶ አቶ ሰዒድ አሊ በሙስና ወንጀል በመጠርጠራቸው የወንጀል ምርመራ መዝገብ በዐቃቤ ሕግ ተከፍቶባቸው እንደነበር አስታውቀዋል። በዚኹ በንባብ በቀረበውና በከተማው አስተዳደር መገናኛ ብዙኃን ላይ በተላለፈው የውሳኔ ሐሳብ፣ አቶ ሰኢድ ከማል፣ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በነበሩበት ወቅት የኮሪደር ልማቱን ምክንያት በማድረግ፣ አኹን በእስር ላይ ከሚገኙ አራት የልደታ ክፍለ ከተማ ሠራተኞችና  ከግል ባለሀብት ጋራ በመመሳጠር የመንግሥት ሀብትን ለግል ጥቅም እንዲውል አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው የወንጀል ምርመራ ሲደረግባቸው መቆየቱ ተገልጿል። ፍትሕ ሚኒስቴር በሚኒስትሯ ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ የምክር ቤት አባሉ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ  የጠየቁበትን ደብዳቤ ኮሚቴው በጥልቀት መመልከቱን ሰብሳቢው ለምክር ቤቱ በንባብ አሰምተዋል።  በተጨማሪም ኮሚቴው የወንጀል ምርመራ መዝገቡን ከመረመረና፣ ከዐቃቤ ሕግ ጋራ በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በኋላ፣ የምክር ቤት አባሉን የሕግ ከለላ ለማንሳት የሚያስችል በቂ አመላካች ኹኔታ አለ ብሎ በማመኑ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የውሳኔ ሐሳብ ማቅረቡን ገልጿል።  በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ መሰረትም የምክር ቤት አባሉ ያለመከሰስ መብት ተነስቷል። ከውሳኔው በኋላ የምክር ቤት አባሉን ለማግኘት ጥረት ስናደርግ የቆየን ቢኾንም፣ በኋላ ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከፖሊስ ለማወቅ ችለናል።

በመርካቶ ገበያ ትላንት የተጀመረው ሱቅ የመዝጋት አድማ ዛሬም ቀጥሏል

መንግሥት እያካሄደ ባለው የደረሰኝ ቁጥጥርና ቅጣት ምክንያት፣ ነጋዴዎች ከትላንት ጀምሮ መደብሮቻቸውን በመዝጋት ፣ አድማ ላይ መኾናቸውን የሱቅ ባለንብረቶች
የአሜሪካ ድምፅ

በመርካቶ ገበያ ትላንት የተጀመረው ሱቅ የመዝጋት አድማ ዛሬም ቀጥሏል

መንግሥት እያካሄደ ባለው የደረሰኝ ቁጥጥርና ቅጣት ምክንያት፣ ነጋዴዎች ከትላንት ጀምሮ መደብሮቻቸውን በመዝጋት ፣ አድማ ላይ መኾናቸውን የሱቅ ባለንብረቶች ተናግረዋል። ከአድማው በተጨማሪ ከመጋዘን እቃ የማሸሽ ተግባርም መኖሩን የገለፁት ነጋዴዎቹ፣ በዚህም ምክንያት ገበያ መቀዛቀዙን ገልፀዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ በበኩላቸው፣ “ቁጥጥሩ የተጀመረው በርካታ ሕገ ወጥ አሠራሮች ስላሉ ነው” ሲሉ ዛሬ በተካሔደው የከተማው ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል፡፡

VOA60 America - US envoy says end to Israel-Hezbollah conflict 'within our grasp'

U.S. envoy Amos Hochstein said Tuesday in Lebanon that conclusion to conflict between Israel and Iran-backed Hezbollah “is now within our grasp." The Lebanese government and Hezbollah agreed to a U.S. cease-fire proposal on Monday. There was no immediate co
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - US envoy says end to Israel-Hezbollah conflict 'within our grasp'

U.S. envoy Amos Hochstein said Tuesday in Lebanon that conclusion to conflict between Israel and Iran-backed Hezbollah “is now within our grasp." The Lebanese government and Hezbollah agreed to a U.S. cease-fire proposal on Monday. There was no immediate comment from Israel.

ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬይን የምትሰጠውን ዕርዳታ መጠን ስታደርግ ’ጂ-20’ ቡድን ውስጥ ልዩነቶች እየታዩ ነው

 የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሥልጣን ዘመን ሊያበቃ በቀረው የሁለት ወራት ዕድሜ ውስጥ አስተዳደራቸው ዩክሬይን የሩሲያን ወረራ ለመከላከል ለያዘችው ጥረት የሚሰ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬይን የምትሰጠውን ዕርዳታ መጠን ስታደርግ ’ጂ-20’ ቡድን ውስጥ ልዩነቶች እየታዩ ነው

 የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሥልጣን ዘመን ሊያበቃ በቀረው የሁለት ወራት ዕድሜ ውስጥ አስተዳደራቸው ዩክሬይን የሩሲያን ወረራ ለመከላከል ለያዘችው ጥረት የሚሰጠውን የገንዘብ፣ የወታደራዊ እና የዲፕሎማሲያዊ ድጋፎች አሳድጓል። ሃያ የዓለም ሃገራት የተካተቱበትን የቡድን  20 የመሪዎች ጉባኤ እያስተናገደች ባለችው የብራዚሏ የባሕር ዳርቻ ከተማ ሪዮ ዲ ጄኔሮ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ለዩክሬን የሚሰጠውን ድጋፍ አስመልክቶ “ብርቱ” ግፊት እያደረጉ መሆናቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ደኅንነት ጉዳዮች ምክትል አማካሪ ጃን ፋይነር በትላንትናው ዕለት ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ሩስያ ባለፈው ሳምንት መገባደጂያ በዩክሬይን የፈጸመችውን የአየር ድብደባ ተከትሎ፤ ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች በሞስኮ ላይ ጠንካራ ትችት እንዲሰነዘር ግፊት እያደረጉ ነው። የሰሞኑም የሩስያ የአየር ጥቃት ለወራት ከታዩት ሁሉ ግዙፉ መሆኑ ተመልክቷል። ባለስልጣናቱ አክለውም የሩስያ  ጥቃት ማየል ‘ከአውሮፓ የሚሻገር ያለመረጋጋት ተጽእኖ ሊያስከትል እንደሚችል’ አስጠንቅቀዋል። በሩስያዋ የከርስክ ግዛት የዩክሬን ኃይሎች የተቆጣጠሩትን አካባቢ ለማስለቀቅ   ከ10 ሺሕ ላይ የሚሆኑ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሞስኮ መግባታቸውን ዩናይትድ ስቴትስ እና ዩክሬን በወሩ መጀመሪያ ላይ ማስታወቃቸው ይታወሳል።  ሆኖም የመጨረሻው የመሪዎች መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ ግፊት ያደረገችበትን አገላለጽ አላካተተም። መግለጫው ሩስያ የወሰደችውን እርምጃ ሳያወግዝ፤ ዩክሬን ውስጥ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ በሰው ልጆች ላይ በሚደርሰው ስቃይ እና በአለም አቀፍ ኢኮኖሚ ላይ ባስከተለው አሉታዊ ተፅእኖ ላይ ትኩረት አድርጓል። የመካከለኛውን ጦርነት አስመልክቶም በጋዛ እና በሊባኖስ የተኩስ አቁም እንዲደረስ እና እስራኤል እና ፍልስጤም ነጻ ሃገር ሆነው በሰላም የሚኖሩበት የሁለት-አገሮች መፍትሄ የተባለው ይሳካ ዘንድ የሚያስፈልገውን ቁርጠኝነት ጠይቋል። የእስራኤልን ራስን የመከላከል መብት በተመለከተ ያለው የለም። ፋይነር አክለውም፤ በቡድኑ ከታቀፉት አገሮች ስብጥር አንጻር አለም አቀፍ ግጭቶችን አስመልክቶ ሁሉም የሚስማሙበት ሃሳብ መቅረጽ ቀላል አለመሆኑን አምነዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ለኪቭ የምትሰጠውን ወታደራዊ ዕርዳታ ያሳደገችው ዩናይትድ ስቴትስ፤ ዩክሬን አሜሪካ-ሰራሹን የረዥም ርቀት ሚሳይሎች በሩሲያ ድንበር ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን ለመምታት እንድትጠቀምበት ፍቃድ መስጠቷን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ባለስልጣናትን ጠቅሰው የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ቡድን 20 - ባብዛኛው ተመሳሳይ እይታ የሚጋሩት የሰባቱ የዓለም ባለ ጸጋ ሃገሮች ካሉበት ቡድን 7 በተጨማሪ፤ ሩስያን፣ ቻይናን፤ እንዲሁም በደቡቡ  የዓለም ንፍቀ ክበብ የሚገኙት አንዳንድ በማደግ ላይ ያሉ ሃገራት ያጠቃልላል።

የውጭ ምንዛሪ ልውውጥ የሚያከናውኑት የግል ኩባንያዎች

በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ልውውጥ በገበያ ዋጋ እንዲወሰን የወጣውን ፖሊሲ ተከትሎ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት እየሰፋ መምጣቱን የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ባለሞ
የአሜሪካ ድምፅ

የውጭ ምንዛሪ ልውውጥ የሚያከናውኑት የግል ኩባንያዎች

በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ልውውጥ በገበያ ዋጋ እንዲወሰን የወጣውን ፖሊሲ ተከትሎ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት እየሰፋ መምጣቱን የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ባለሞያዎች ተናግረዋል፡፡ ይኹን እንጂ በጥቁር ገበያውና በመደበኛው የባንክ ምንዛሪ መካከል ያለው ልዩነት ተስፋና ስጋት መፍጠሩንም ባለሞያዎቹ ገልጸዋል፡፡ ከባንኮች በተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ግብይት አገልግሎት እንዲሰማሩ ብሄራዊ ባንክ ፈቃድ ከሰጣቸው አምስት የግል ኩባንያዎች መካከል አንዱ የኾነው የኢትዮ ፎሬክስ አክስዮን ማኅበር መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ ፖሊሲው አዎንታዊ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ የምጣኔ ሀብቱ ባለሞያው አቶ ያሬድ ኃይለመስቀል በበኩላቸው ለውጥ መኖሩን ቢቀበሉም የውጭ ምንዛሬው ዘለቄታዊ በኾነ መንገድ ሊቀረፍ የሚችለው የጥቁር ገበያው ተፈላጊነት እየቀነሰ ሲመጣ፣ ለውጡ በውጭ ንግድ ምርቶች ሲደገፍና ከገቢ ሸቀጦች ጋራ ሲገናዘብ ብቻ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ /ዝርዝሩን ከተያይዘው ፋይል ይከታተሉ/

“ከፊሊፒንስ ጋራ ያለን  አጋርነት ከአስተዳደሮች መለዋወጥም የሚሻገር ነው" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር ተናገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን፣ ቻይና በፊሊፒንስ ላይ የወሰደችውንና ‘አደገኛ’ ያሉትን ድርጊት አውግዘው፤ በአወዛጋቢው የደቡብ ቻይ
የአሜሪካ ድምፅ

“ከፊሊፒንስ ጋራ ያለን  አጋርነት ከአስተዳደሮች መለዋወጥም የሚሻገር ነው" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር ተናገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን፣ ቻይና በፊሊፒንስ ላይ የወሰደችውንና ‘አደገኛ’ ያሉትን ድርጊት አውግዘው፤ በአወዛጋቢው የደቡብ ቻይና ባህር የፊሊፒንስ ኃይሎች ጥቃት ቢደርስባቸው፤ ‘ዩናይትድ ስቴትስ ከሀገራቸው ወታደራዊ የትብብር ስምምነት ያላትን ማኒላን ትከላከላለች’ ሲሉ ቀደም ሲል ያሰሙትን ማስጠንቀቂያ አጽንኦት ሰጥተው ደግመዋል። አዲሱን የ500 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ እገዛ ጨምሮ፣ አገራቸው ለፊሊፒንስ የምትሰጠው ጠንካራ ወታደራዊ ድጋፍ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደርም ይቀጥል እንደሆን፤ በፊሊፒንሷ ፓላዋ ግዛት በሥራ ጉብኝት ላይ ባሉበት ወቅት የተጠየቁት ኦስቲን  የሚቀጥለውን የአስተዳደር እርምጃ መገመት እንደማይችሉ ተናግረዋል። ሆኖም በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ጠንካራ ጥምረት በአገሮቹ ውስጥ የሚደረጉትን “የአስተዳደሮች መለዋወጥ ተሻግሮ ይቀጥላል" የሚለውን እምነታቸውን ገልጸዋል።

በሶማሊላንድ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲው መሪ አሸነፉ

በሶማሊላንድ ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው መሐመድ አብዱላሂ ኢሮ ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ አብዲን ማሸነፋቸውን የምርጫ ኮሚ
የአሜሪካ ድምፅ

በሶማሊላንድ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲው መሪ አሸነፉ

በሶማሊላንድ ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው መሐመድ አብዱላሂ ኢሮ ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ አብዲን ማሸነፋቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ ዛሬ ማክሰኞ አስታወቀ፡፡ ገለልተኛ ታዛቢዎች ምርጫውን «ሰላማዊ »ሲሉ ገልጸውታል፡፡ የብሔራዊ ፓርቲው የዋዳኒ ፕሬዚደንታዊ እጩ አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ (ኢሮ) 63 ነጥብ 92 ከመቶውን የመራጭ ድምጽ ያገኙ ሲሆን ፕሬዚደንት ቢሂ 34 ነጥብ 81 ከመቶ፡ ሦስተኛው እጩ 0 ነጥብ 74 ከመቶውን ማግኘታቸውን የሶማሊላንድ ብሔራዊ የምርጫ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሴ ሀሰን ዩሱፍ ሐርጌሳ ላይ ይፋ አድርገዋል፡፡ የ69 ዓመቱ ኢሮ ለአምስት ዓመት ሶማሊላንድን ሊመሩ እ አ አ ታሕሳስ 13 ቀን ቃለ መሐላ ይፈጽማሉ፡፡ ብሐራዊ የምርጫ ኮሚሽኑ የምርጫውን ውጤት እንዲያጸድቅ ለከፍተኛ ፍርድ ቤቱ እንደሚያቀርበው ተመልክቷል፡፡ የሶማሊላንድ ምርጫ እአአ በ2022 ዓም ሊካሂድ ታቅዶ የነበረ ሲሆን በፖለቲካ ልዩነቶች የተነሳ እስካሁን ዘግይቷል፡፡ እአአ በ2017 በተካሄደው በቀደመው ምርጫ የዋዳኒ ፓርቲውን መሪ አሸንፈው ስልጣን የያዙት ቢሂ የምርጫውን ውጤት አከብራለሁ ብለዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ለተመራጩ ፕሬዚደንት የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክት አስተላልፉል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩ ባወጣው አጭር መግለጫ «ተመራጩ ፕሬዚደንት እና ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ መሐመድ ያሳዩትን ዲሞክራሲያዊ አመራር ኢትዮጵያ ታደንቃለች » ብሏል፡፡ የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሀሰን ሼክ መሐሙድም ለተመራጩ ፕሬዚደንት የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ፕሬዚደንት መሐሙድ ለሶማሊያ ሕዝብ እድገት እና አንድነት ወሳኝ ለሆነው እርቀ ሰላም የሚደረገው ንግግር እንዲጠናቀቅ ቁርጠኛነታቸው ያሳወቁ መሆኑን የሶማሊያ መንግሥት የዜና ማሰራጫ ዘግቧል፡፡ በሶማሊያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲም በበኩሉ ምርጫውን አስመልክቶ ለሶማሊላንድ ሕዝብ እና ለተመራጩ ፕሬዚደንት እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት መልዕክት አስተላልፏል፡፡ ኤምባሲው በኤክስ ገጹ ባወጣው ጽሁፍ «የሶማሊላንድ አስደናቂ የምርጫዎች እና የሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተሞክሮ ለቀጣናው ብቻ ሳይሆን አልፎም አርአያ የሚሆን ነው» ብሏል፡፡

የእግር ጉዞ ማዘውተር ለአንጎል ጤና የሚያስገኘው የላቀ ጠቀሜታ

የእግር ጉዞ፣ የቤት ውስጥ ሥራ አለያም ሌሎች መሰል ቀላል የአካል እንቅስቃሴዎችን አዘውትሮ ማድረግ ለአንጎል ጤና ከፍ ያለ ጥቅም የሚያገኝ መሆኑን በቅርቡ ይፋ
የአሜሪካ ድምፅ

የእግር ጉዞ ማዘውተር ለአንጎል ጤና የሚያስገኘው የላቀ ጠቀሜታ

የእግር ጉዞ፣ የቤት ውስጥ ሥራ አለያም ሌሎች መሰል ቀላል የአካል እንቅስቃሴዎችን አዘውትሮ ማድረግ ለአንጎል ጤና ከፍ ያለ ጥቅም የሚያገኝ መሆኑን በቅርቡ ይፋ የተደረገ አንድ የሳይንሳዊ ምርምር ጽሑፍ አመለከተ። የአንጎልን አሠራር ማቀላጠፍ እና የዓመታት ወጣትነት ማጎናጸፍ መቻሉ ተገልጿል። ሞያዊ ትንታኔውን የሰጡን ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ የነርቭና የአእምሮ ሃኪም፣ እንዲሁም በባሮ የነርቭ ሕክምና ተቋም መምህር እና ተመራማሪ ናቸው። ፕሮፌሰር ዮናስ ካሁን ቀደም ቀላል የአካል እንቅስቃሴዎች ዕድሜያቸው ከሰባ ዓመት በላይ የሆኑ አረጋውያን በተመሳሳይ ቀላል የአካል እንቅስቃሴ በማድረግ ብቻ ከመጃጀት ጋራ ተያይዘው የሚመጡ በሽታዎችን በመከላከል የሚረዱ መሆናቸውን ያረጋገጠ ለከፍተኛ እውቅና የበቃ ሳይንሳዊ የምርምር ሥራ አካሂደዋል። ሞያዊ ትንታኔውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

አሜሪካ ለፕሬዝዳንታዊ ሽግግር እየተዘጋጀች ነው

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሥልጣን ለመረከብ እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ሥልጣንን ከተሰናባቹ ወደ አዲሱ አስተዳደር የማሸጋገር ሂደት ከብርቱ ጥንቃቄ ጋ
የአሜሪካ ድምፅ

አሜሪካ ለፕሬዝዳንታዊ ሽግግር እየተዘጋጀች ነው

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሥልጣን ለመረከብ እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ሥልጣንን ከተሰናባቹ ወደ አዲሱ አስተዳደር የማሸጋገር ሂደት ከብርቱ ጥንቃቄ ጋራ በቅንጅት እየተካሄደ ነው። ባለሞያዎች የፌደራል መንግሥት በአሜሪካ ዲሞክራሲ ውስጥ ወሳኝ ለኾነው ለዚህ ጊዜ እንዴት እንደሚዘጋጅ ሐሳባቸውን ያካፍላሉ። የቪኦኤዋ ዘጋቢ ሳሌም ሰለሞን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ባይደን አማዞን ደንን በመጎብኘት ለአየር ንብረት ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት የሚያደርጉትን ጥረት ለማጉላት፤ ትላንት እሁድ ታሪካዊ የተባለውን ጉብኝት በማድረ
የአሜሪካ ድምፅ

ባይደን አማዞን ደንን በመጎብኘት ለአየር ንብረት ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት የሚያደርጉትን ጥረት ለማጉላት፤ ትላንት እሁድ ታሪካዊ የተባለውን ጉብኝት በማድረግ ወዳ ብራዚል አቅንተዋል፡፡ ይኸም የአማዞን ጥቅጥቅ ደንን የጎበኙ የመጀመሪያው በሥልጣን ላይ የሚገኙ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አድርጓቸዋል፡፡ ፕሬዘዳንቱ በሪዮ ዲጄኔሮ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በድህነት ቅነሳና በሌሎችም ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ለውይይት በሚቀርቡበት የዓለም ግዙፍ ምጣኔ ሃብት ያላቸው የቡድን 20 የመሪዎች በሚሳተፉበት ጉባኤ ላይ ይታደማሉ፡፡ የዋይት ኋውስ ቢሮ ዋና ሃላፊ ፓትሲ ዊዳስኩዋራ ያሰናዳችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዐዲስ ሥራ አስፈጻሚ ሲሰይም የተቃውሞ ድምጾችም ተደምጠዋል

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዐዲስ ሥራ አስፈጻሚ መረጠ። አምስት ፓርቲዎች ምርጫውን እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል። የጋራ ምክር ቤቱ ቅዳሜ እ
የአሜሪካ ድምፅ

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዐዲስ ሥራ አስፈጻሚ ሲሰይም የተቃውሞ ድምጾችም ተደምጠዋል

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዐዲስ ሥራ አስፈጻሚ መረጠ። አምስት ፓርቲዎች ምርጫውን እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል። የጋራ ምክር ቤቱ ቅዳሜ እና እሁድ ባደረገው ጠቅላላ ጉባዔ፣ ዐዲስ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መምረጡን እና የም/ቤቱን መተዳደሪያ ደንብ ማፅደቁን ዋና ጸሐፊው አቶ ደስታ ዲንቃ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ቀደም፣ የሥራ አስፈጻሚው ሥልጣን በማብቃቱ ምርጫ ቦርድ ጉባዔ እንዲጠራ የጠየቁ ስድስት ፓርቲዎች በበኩላቸው፣ ባለፉት ሁለት ቀናት በተካሔደው ጉባዔ የተላለፉ ውሳኔዎችን አንቀበልም ማለታቸውን የኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር መጋቢ ቢሉይ አብርሃም ኃይማኖት ገልፀዋል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የትራምፕ ካቢኔ ምርጫ ነባራዊውን ሁኔታ ይለውጣል ሲሉ የምክርቤት አባል ተናገሩ

ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የካቢኔ አባላት ምርጫዎች «አወዛጋቢ» መሆናቸውን በዲሞክራቲክ እና በሪፐብሊካን ፓርቲ አባላቶች
የአሜሪካ ድምፅ

የትራምፕ ካቢኔ ምርጫ ነባራዊውን ሁኔታ ይለውጣል ሲሉ የምክርቤት አባል ተናገሩ

ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የካቢኔ አባላት ምርጫዎች «አወዛጋቢ» መሆናቸውን በዲሞክራቲክ እና በሪፐብሊካን ፓርቲ አባላቶች እየገለጹ ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባዔ የሆኑት ሪፐብሊካኑ ማይክ ጆንሰን እሁድ እለት ለትችቶቹ በሰጡት ምላሽ፣ የአሜሪካ ሕዝብ ነባራዊውን ሁኔታ ለመለወጥ ድምፅ መስጠታቸውን አስታውሰው፣ አዲሶቹ የካቢኔ አባላት በምክርቤቱ እውቅና ከተሰጣቸው የሚጠብቃቸው ኃላፊነት እሱ መሆኑን ተናግረዋል። የአሜሪካ ድምጿ ቬሮኒካ ባልደራስ በዚህ ዙሪያ ያደረሰችንን ዘገባ፣ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ባይደን አማዞን ደንን በመጎብኘት የአየር ንብረት ለውጥ ትግል ቅርሳቸውን አከበሩ

ትላንት እሁድ በብራዚል ታሪካዊ ጉብኝት ያደረጉት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በአስተዳደር ዘመናቸው የአማዞን ደንን የጎበኙ የመጀመሪያው የአሜ
የአሜሪካ ድምፅ

ባይደን አማዞን ደንን በመጎብኘት የአየር ንብረት ለውጥ ትግል ቅርሳቸውን አከበሩ

ትላንት እሁድ በብራዚል ታሪካዊ ጉብኝት ያደረጉት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በአስተዳደር ዘመናቸው የአማዞን ደንን የጎበኙ የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሆነዋል፡፡ ጉብኝታቸውን ኋይት ሀውስ ፕሬዚደንቱ የአየር ንብረት ለውጥን በመታገል ያበረከቱት ክንዋኔ ታሪክ የተከበረበት ጉዞ ሲል ገልጾታል፡፡ ትላንት ከዓለም ግዙፉ የአማዞን ደን መግቢያ ላይ የሚገኘው አማዞኒያ ክፍለ ግዛት ዋና ከተማ ማናዉስ   የገቡት ባይደን በርሳቸው አስተዳደር ዩናይትድ ስቴትስ ለዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ በየዓመቱ 11 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት ያላትን ግብ አሳክታ ማለፏን አመልክተዋል፡፡ ባይደን በንግግራቸው ዓለማችንን ለመጠበቅ የምናደርገው ትግል ለቀጣይ ተውልዶች የሚተርፍ ትግል ነው ያሉት ጆ ባይደን  «ይህ  በሀገሮቻችንን በጠቅላላ  እና በሰው ዘር በሙሉ ላይ  የተጋረጠ ብቸኛው የህልውና አደጋ  ሊባል ይችላል»  ብለዋል፡፡ የአማዞኒያ ዋና ከተማ   ማናዉስ የምትገኘው የእስያ ፓሲፊክ የኢኮኖሚ ጉባኤ አስተናጋጅ በሆነቸው በፔሩ ዋና ከተማ ሊማ እና የቡድን ሃያ የመሪዎች ጉባኤ አስተናጋጇ ሪዮ ዲ ጃኒየሮ መሃል ሲሆን የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ባደረጉት አጭር ቆይታ ዩናይትድ ስቴትስ ለበርካታ የአየር ንብረት መርሓ ግብሮች የመደበቻቸውን ወጪዎች ይፋ አድርገዋል፡፡ ለአማዞን ደን ጥበቃ ፈንድ 50 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን አስታውቀዋል፡፡ ከአካባቢው ነባር ማህበረሰቦች መሪዎች ጋር የተወያዩት ባይደን ደኑን በሄሊኮፕተር እየተዘዋወሩ ጎብኝተዋል፡፡ በኤፔክ እና ቡድን ሃያ ጉባኤ ላይ የተገኙ እና ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ በርካታ የዲፕሎማሲ ምንጮች በቀጣዩ የፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር ዩናይትድ ስቴትስ የአየር ንብረት ጉዳዮችን በሚመለከት የምታደርጋቸው ጥረቶች በእጅጉ መቀነሳቸው አይቀርም የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡   

የቤይሩት የአየር ጥቃት ተከትሎ የቤይሩት ት/ቤቶች ተዘግተዋል

በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ማዕከላዊ አካባቢ ትላንት በደረሱት የአየር ጥቃቶች የሄዝቦላ ዋና ቃል አቀባዩን ጨምሮ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ዛሬ ሰኞ
የአሜሪካ ድምፅ

የቤይሩት የአየር ጥቃት ተከትሎ የቤይሩት ት/ቤቶች ተዘግተዋል

በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ማዕከላዊ አካባቢ ትላንት በደረሱት የአየር ጥቃቶች የሄዝቦላ ዋና ቃል አቀባዩን ጨምሮ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ዛሬ ሰኞ የከተማዋ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ተዘግቧል፡፡ በጥቃቶቹ ምክንያት የትምህርት ሚንስቴሩ ቤይሩት ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሁለት ቀናት እንዲዘጉ መወሰኑ ተገልጿል፡፡ ራስ አል ናባ በተባለው የቤይሩት አካባቢ የሄዝቦላ ቃል አቀባይ መሐመድ አፊፍ እና ሌሎች ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ሄዝቦላ እና የእስራኤል የጦር ኅይል አስታውቀዋል፡፡ እስራኤል ለወትሮው ግልጽ የሆነ ወታደራዊ ሚና የሌላቸውን የሄዝቦላ ከፍተኛ ባለስልጣናት አዘውትራ ኢላማ የማታደርግ ሲሆን በአየር ጥቃቶቿም በአብዛኛው የምታነጣጥረው ሄዝቦላ ታጣቂዎች በብዛት የሚገኙባቸውን የቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻ ሰፈሮችን መሆኑን ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል፡፡ ሆኖም የእስራኤል የመከላከያ ኃይሎች ባወጣው መግለጫ የሂዜቦላ ቃል አቀባዩን የገደለው ላይ ጥቃት ደንበኛ የስለላ መረጃ ተመሥርቶ የተወሰደ እርምጃ ነው ብሏል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ጋዛ ካን ዩኒስ ውስጥ እስራኤል በተፈናቃዮች መጠለያ ድንኳን ላይ ዛሬ ሌሊት ባደረሰችው ጥቃት ሁለት ሕጻናት እና ወላጆቻቸውን መግደሏን የፍልስጥኤም ባለስልጣናት አመልክተዋል፡፡ የጋዛ ህዝባዊ መከላከያ ተቋም ትላንት እሁድ ባወጣው መግለጫ እስራኤል «ቤት ላህላ» በተባለ ሰፈር የሚገኝ የመኖሪያ ህንጻ ላይ ባደረሰችው የአየር ድብደባ ህጻናት ጨምሮ ሠላሳ አራት ሰዎች መግደሏን አመልክቶ ብዛት ያላቸው ሰዎች ያሉበት ሁኔታ አለመታወቁን   አመልክቷል፡፡

ብሪታኒያ በሱዳን ጉዳይ የፀጥታ ምክር ቤት አባላትን እገዛ ልትጠይቅ ነው

የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ውጊያው አቁመው የርዳታ አቅርቦት እንዲገባ እንዲፈቅዱ የጠየቀችው ብሪታኒያ የተቀሩት የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት አባላት
የአሜሪካ ድምፅ

ብሪታኒያ በሱዳን ጉዳይ የፀጥታ ምክር ቤት አባላትን እገዛ ልትጠይቅ ነው

የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ውጊያው አቁመው የርዳታ አቅርቦት እንዲገባ እንዲፈቅዱ የጠየቀችው ብሪታኒያ የተቀሩት የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት አባላትን ድጋፍ እንደምትጠይቅ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴሯ አስታውቋል፡፡ ብሪታኒያ የወቅቱ የምክር ቤቱ ተረኛ ፕሬዝደንት ናት። ዛሬ ሰኞ የምክር ቤቱን ስብሰባ በሊቀመንበርነት የሚመሩት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ ዴቪድ ላሚ ሀገራቸው ና ሲየራሊዮን በጋራ ያቀረቡት ረቂቅ ውሳኔ ላይ ድምጽ ያሰጣሉ፡፡ ውሳኔው ከርዳታ አቅርቦት መግባት ሌላ ለሲቪሎች ደህንነት ጥበቃ እንዲሰጥም ይጠይቃል፡፡ ሚንስትሩ ብሪታኒያ ሱዳን እንድትረሳ እንደማትፈቅድ እና ርዳታዋንም በእጥፍ በማሳደግ ወደ285 ሚሊዮን ዶላር ከፍ እንድምታደርግ እንደሚያስታውቁ መግለጫው አመልክቷል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዴቪድ ላሚ ከዚህ በተጨማሪ እስራኤል ወደጋዛ የሚላከውን የሰብዓዊ ረድዔት አቅርቦት መገደቧን እንደሚነቅፉ መግለጫው አውስቶ በአስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ታጋቾቹ በሙሉ እንዲለቀቁ ይጠይቃሉ ብሏል፡፡ ዩክሬይንን በተመለከተም ሩስያ ያለው ዕውነታ እስከሚገባት ብሪታኒያ ከዩክሬን ጋር መቆሟን እንደምትቀጥል እንደሚናገሩ መግለጫው አመልክቷል፡፡

በወሲባዊ ውዝግብ የተጠመዱት ሁለቱ የተመራጩ ፕሬዝደንት እጩ ተሿሚዎች

በተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ከታጩት ዋና ዋና የካቢኔ ተሿሚዎች መካከል ሁለቱ   ከወሲባዊ ውንጀላዎች ጋራ በተያያዙ ውዝግቦች የተጠ
የአሜሪካ ድምፅ

በወሲባዊ ውዝግብ የተጠመዱት ሁለቱ የተመራጩ ፕሬዝደንት እጩ ተሿሚዎች

በተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ከታጩት ዋና ዋና የካቢኔ ተሿሚዎች መካከል ሁለቱ   ከወሲባዊ ውንጀላዎች ጋራ በተያያዙ ውዝግቦች የተጠመዱ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡ ትረምፕ ለመከላከያ ሚንስትርነት ያጯቸው የቀድሞው የፎክስ ኒውስ ቴሌቭዥን አቅራቢ ፒት ሄግሴት እና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እንዲሆኑ የመረጧቸው የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባል ማት ጌትዝ ከወሲባዊ አድራጎት ውንጀላዎች ጋራ በተያያዙ ውዝግቦች የተጠመዱ ሲኾኑ ሹመታቸው በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት መጽደቅ ላይ እክል ሊፈጥር እንደሚችል ተመልክቷል፡፡ ለመከላከያ ሚንስትርነት የታጩት የአርባ አራት ዓመቱ ፒት ሄግሴት እ.አ.አ በ2017 ዓ.ም በወሲባዊ ጥቃት ለወነጀለቻቸው ሴት መጠኑ ያልተገለጸ ገንዘብ መክፈላቸውን በሳምንቱ መጨረሻ ጠበቃቸው ቲም ፓርላቶር ገልጸው መሠረተ ቢስ ያሉት ውንጀላ አደባባይ እንዳይወጣ ለመከላከል መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የአርባ ሁለት ዓመቱ ማት ጌትዝ ደግሞ በተወካዮች ምክር ቤት አባልነት አራተኛቸው የሆነውን የሁለት ዓመት ዘመን እያጠናቀቁ ሳሉ   ባለፈው ሳምንት በድንገት ሥራቸውን ለቀዋል፡፡ ጌትዝ ከምክር ቤት አባልነት የለቀቁት ከአስራ ሰባት ዓመት ልጃገረድ ጋራ ወሲባዊ ግንኙነት በመፈጸም እና በድብቅ ሱስ አስያዥ መድሃኒቶች በመውሰድ በቀረቡባቸው ውንጀላዎች ዙሪያ የምክር ቤቱ የሥነ ምግባር ኮሚቴ የከፈተውን ምርምራ ሊያጠናቅቅ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት መሆኑ ተመልክቷል፡፡ አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት ጌትዝ በወሲባዊ ድርጊት በተሰማሩባቸው ሁኒታዎች ራቁት የተነሱ ፎቶዎችን ምክር ቤቱ አዳራሽ ውስጥ ለሰዎች ሲያሳዩ ነበር ብለው ተናግረውባቸዋል፡፡ ጌትዝ ክሱን ያስተባበሉ ሲሆን የፊዴራል መንግሥት ባለሥልጣናትም ክስ እንደማይመሰርቱባቸው በዚሁ ዓመት አስታውቀው እንደነበር አይዘነጋም፡፡ የፒት ሃግሴት ጠበቃ በበኩላቸው ካሊፎርኒያ ውስጥ ከተካሄደ የሪፐብሊካን ፓርቲ የሴቶች ዝግጅት በኋላ በሆቴል ክፍላቸው ከሴቲቱ ጋራ የነበረው ወሲባዊ ግንኙነት የተፈጸመው በሁለቱም ፍላጎት ነው ብለዋል፡፡

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እስራኤል በጋዛ ያደረሰችው ጥቃት 'የዘር ማጥፋት' ስለመሆኑ ለማጣራት ምርመራ እንዲደረግ ጠየቁ

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ  ፣ እስራኤል በጋዛ ያደረሰችው ጥቃት ዘር ማጥፋት መሆኑን ለማረጋገጥ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ  አቀረ
የአሜሪካ ድምፅ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እስራኤል በጋዛ ያደረሰችው ጥቃት 'የዘር ማጥፋት' ስለመሆኑ ለማጣራት ምርመራ እንዲደረግ ጠየቁ

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ  ፣ እስራኤል በጋዛ ያደረሰችው ጥቃት ዘር ማጥፋት መሆኑን ለማረጋገጥ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ  አቀረቡ ።ይህ ይፋ የተደረገው  ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ  ኢዮቤልዩ በዓል አስቀድሞ  እንደሚለቀቅ ከተነገረለት አዲስ መጽሐፍ ላይ ቀድመው በወጡ ቅንጫቢ አንቀጾች  ላይ ነው።   ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት  ፍራንሲስ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በወሰደችው እርምጃ ጋር ተያይዞ ባለው  የዘር ማጥፋት ውንጀላ ዙሪያ ማጣሪያ እንዲደረግ  ሲያሳስቡ ይህ የመጀመሪያቸው ነው። በአውሮፓዊያኑ መስከረም ላይ እስራኤል በጋዛ እና ሊባኖስ ያደረሰችው ጥቃት “የሞራል ህግ የጣሰ” ፣ ተመጣጣኝ ያልሆነ መሆኑን እንዲሁም የእስራኤል  ወታደሮች ከጦርነት ህግጋት እንተደተሻገሩ ተናግረዋል። በሄርናን ሬይስ አልካይድ የተዘጋጀው እና ከጳጳሱ ጋር በተደረገ ቃለ ምልልስ ላይ የተመሰረተው መፅሃፍ “ተስፋ ፣ ተስፋ አይቆርጥም። መንፈሳዊ ፍኖት ወደ ተሻለ ዓለም« የሚል ርዕስ ሲኖረው ፣ ከጳጳሱ የአውሮፓዊያኑ 2025 ኢዮቤልዩ በዓለ ሲመት በፊት የፊታችን ማክሰኞ ይለቀቃል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን አንድ ዓመት የሚዘልቅ  ኢዮቤልዩ በዓል  በማስመልከት ከ30 ሚሊዮን በላይ ምዕመናንን  ወደ ሮም ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል። »አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት በጋዛ ውስጥ የተፈጸመው ድርጊት የዘር ማጥፋት ባህሪያት አሉት « ሲሉ ጳጳሱ  መናገራቸውን ፣ የመጽሃፉን ቅንጭብ ዋቢ ያደረገው ፣ ዛሬ ለንባብ የበቃው  የጣሊያን ዕለታዊ ጋዜጣ  ላ ስታምፓ ዘግቧል። »በህግ ባለሙያዎች እና በዓለም አቀፍ አካላት ከተቀረጹት ልዩ  ፍቺዎች ጋር የሚስማማ መሆኑን ለማረጋገጥ በጥንቃቄ መመርመር አለብን"  ሲሉም አክለዋል። ባለፈው ዓመት ርዕሳነ ሊቀ ጳጳስ  ፍራንሲስ በጋዛ ከሚገኙት የእስራኤል ታጋቾች እና በጦርነቱ ውስጥ ከሚኖሩ ፍልስጤማውያን ዘመዶች ጋር በተናጥል የተገናኙ ሲሆን  ፣ የቫቲካን ዲፕሎማቶች ከመጠቀም የሚታቀቧቸውን  “ሽብርተኝነት” እና እንደ ፍልስጤማዊያኑ ሁሉ  “የዘር ማጥፋት” የሚሉትን ቃላት በመጠቀማቸው የጋለ ክርክር ቀስቀሰዋል።  ባለፈው ሳምንት ከእስር ከተፈቱት የእስራኤል ታጋቾች ልኡካን  እና ጫና ሲፈጥሩ ከቆዩ ቤተሰቦቻቸው ጋር  የተገናኙት ሊቀ ጳጳሱ በቅርቡ በሚለቀቀው መጽሃፍ ላይ የኤዲቶሪያል ቁጥጥር አላቸው። ጦርነቱ የጀመረው የታጣቂው የሃማስ ቡድን በአውሮፓዊያኑ ጥቅምት  7፣ 2023 እስራኤልን ካጠቃ በኃላ  ሲሆን ፣ በወቅቱ 1,200 ሰዎች ገድሎ  250 ሰዎችን አሁንም የተወሰኑት  ወደ ሚገኙበት  ጋዛ አፍኖ  ወስዷል ።  በጋዛ የጤና ባለስልጣናት መረጃ መሰረት ፣ የእስራኤል ዓመት የተሻገረ  ወታደራዊ ዘመቻ ከ 43,000 በላይ ሰዎችን ገድሏል ። ምንም እንኳን ከሟቾቹ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች እና ህጻናት ናቸው ።  መረጃው  በሲቪሎች እና በተዋጊዎች መካከል ልዩነትን አላስቀመጠም (AP)።

የሶማሊያው ሚኒስትር ለአውሮፓ ዲፕሎማቶች ከባድ ማስጠንቀቂያ ላኩ

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  በቅርቡ በሶማሌላንድ ምርጫ ላይ አስተያየት ለሰጡ  በሀገሪቱ ለሚገኙ የአውሮፓ ዲፕሎማቶች ከባድ ማስጠንቀቂያ ላኩ። አህመድ
የአሜሪካ ድምፅ

የሶማሊያው ሚኒስትር ለአውሮፓ ዲፕሎማቶች ከባድ ማስጠንቀቂያ ላኩ

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  በቅርቡ በሶማሌላንድ ምርጫ ላይ አስተያየት ለሰጡ  በሀገሪቱ ለሚገኙ የአውሮፓ ዲፕሎማቶች ከባድ ማስጠንቀቂያ ላኩ። አህመድ ሙአሊም ፊቂ ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን ምርጫ የታዘቡ የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች ሶማሌላንድን እንደ አንድ የተለየ ሀገር ሳይሆን እንደ ሶማሊያ አንድ ክልል መጥራት እንዳለባቸው ተናግረዋል። ፊቂ በሶማሊያ የዴንማርክ አምባሳደር ስቲን ሶን አንደርሰንን በሶማሌላንድ ሃርጌሳ በነበሩበት ወቅት ስለ ሰጡት አስተያየት ለማነጋገር እንዳስጠሯቸው ገልጸዋል። የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ አንደርሰን በአውሮፓዊያኑ ህዳር 19 በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲቀርቡ ተነግሯቸዋል። የሶማሌላንድ የማስታወቂያ ሚኒስትር አሊ ሀሰን መሀመድ የፊቂን እርምጃ  “ምቀኝነት” ሲሉ ተችተዋል። አሊ ፊቂን “በሶማሊላንድ ህዝብ እድገት ምክንያት ቅናት አድሮባቸዋል” ሲል ከሰዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢ ቡድን (IEOM) በሶማሊላንድ ውስጥ ስላለው ምርጫ ያዘጋጀውን ግምገማ አትሟል። ምርጫው የተመዘገቡ መራጮች  የመምረጥ መብታቸውን መተግበር እንዲችሉ ባስቻለ  በአብዛኛው የተረጋጋና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መከናወኑን ታዛቢዎቹ ተናግረዋል። ምንም እንኳን የምርጫ ታዛቢዎቹ  በተሻለ ስልጠና ሊፈቱ የሚችሉ የአሰራር እና የአስተዳደር አለመጣጣም እንከኖችን ቢያስተውሉም ፣ ምንም አይነት ከባድ የህግ ጥሰት ወይም የምርጫ ብልሹ አሰራሮችን  እንዳልተመለከቱ ተናግረዋል። የሶማሌላንድ ምርጫ ኮሚሽን የቀደሙት ውጤቶችን ከአውሮፓዊያኑ ህዳር 21 በፊት ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ።  

በጋቦን ወታደራዊውን አገዛዝ ለማስወገድ አብላጫ መራጮች ድምጻቸውን መስጠታቸውን የቀደሙ ዘገባዎች አመላከቱ

በጋቦን የተከናወነው ህዝበ ውሳኔ ቀደምት ውጤቶች  ፣ከተመዘገቡት 860,000 መራጮች አብዛኛው  ወታደራዊ አገዛዝን የሚቋጨውን  አዲስ ሕገ መንግሥት ለመደገፍ ድምጽ
የአሜሪካ ድምፅ

በጋቦን ወታደራዊውን አገዛዝ ለማስወገድ አብላጫ መራጮች ድምጻቸውን መስጠታቸውን የቀደሙ ዘገባዎች አመላከቱ

በጋቦን የተከናወነው ህዝበ ውሳኔ ቀደምት ውጤቶች  ፣ከተመዘገቡት 860,000 መራጮች አብዛኛው  ወታደራዊ አገዛዝን የሚቋጨውን  አዲስ ሕገ መንግሥት ለመደገፍ ድምጽ መስጠታቸውን የሀገሪቱ መንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ  ዘገባዎች አመልክተዋል። የቅዳሜው ህገ-መንግስታዊ ህዝበ ውሳኔ ውጤት ፣ ለ60 ዓመታት በሀገሪቱ ውስጥ የቆየውን የቦንጎ ቤተሰብ ስርወ መንግስት ያስወገደውን የሽግግር ወታደራዊ መንግስት  ዘመን ሊደመድም ይችላል። ይፋዊ የቆጠራ ውጤቱ በቅርቡ ይፋ ይሆናል ይጠበቃል። ባለስልጣናት እንደሚሉት ፣ የአዲሱ ህገ መንግስት መጽደቅ ፣ በአውሮፓዊያኑ  ነሐሴ 30 የጋቦን መሪዎች ካለ ደም መፋሰስ ፣ የመካከለኛው አፍሪካዊቷን ሀገር ከፖለቲካ ባርነት ነጻ እንዳረገ በሚናገሩለት መፈንቅለ መንግስት ስልጣን የተቆጣጠሩት ፣ ጄኔራል ብሪስ ክሎቴር ኦሊጊ ንጊዩሜ ከገቧቸው  ዐበይት ቃል ኪዳኖች መካከል አንዱ ነው።   ሰርጌ ዜንግ አንጎ የጋቦን ዜጎች በህዝበ ውሳኔው ወቅት አዲስ ህገ-መንግስት እንዲፀድቁ የምርጫ ቅስቀሳ ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲ የብሔራዊ ህብረት  ስራ አስፈፃሚ ናቸው። አዲሱ ሕገ መንግሥት እንደ ቦንጎ ዘመን ሥልጣን ከአባት ወደ ልጅ የሚተላለፍበትን ሌላኛ የፖለቲካ ሥርወ መንግሥት(ውርርስ)  ማንኛውንም ዕድል እንደሚገታ ተናግረዋል። ነገር ግን ተቃዋሚዎች እና ሲቪል ማህበረሰቦች የሕገ መንግሥቱ ረቂቅ ወታደራዊው ገዥ ጄኔራል ንጉዌማን ለፕሬዚዳንትነት እንዳይወዳደሩ መከልከል ነበረበት ብለዋል።  በወታደራዊ አመራሮች  ህገ መንግስቱ የተዘጋጀው  ለፕሬዚዳንቱ ከልክ ያለፈ ስልጣን ለመስጠት ፣  ንጉዌማ በስልጣን ላይ እንዲቆዩ  ለማድረግ እንደሆነም አክለዋል። የጋቦን ተቃዋሚዎች እና የሲቪል ማህበራት የህዝበ ውሳኔውን ውጤት በፍርድ ቤት እንደሚቃወሙ ቢናገሩም ተጨማሪ ዝርዝር መግለጫ አልሰጡም። የጋቦን መንግስት የቅዳሜው ህዝበ ውሳኔ ነፃ፣ ፍትሃዊ እና ግልጽ ነበር ብሏል። አዲሱ ህገ መንግስት ከቦንጎ የአባት እና ልጅ የስልጣን  ዘመን በተለየ የግለሰቦችን ነፃነት ያስከብራል ሲሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል። የአፍሪካ ህብረት እና የመካከለኛው አፍሪካ ምጣኔ ሀብት  እና የገንዘብ ማህበረሰብ ፤ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እንደተናገሩት የምርጫ ጣቢያዎች ዘግይተው በመከፈታቸው ዘግይቶ  ከተጀመረው ድምጽ አሰጣጥ ሂደት  ምርጫው ሰላማዊ እና ግልፅነት የተሞላበት ነበር። የህዝበ ውሳኔው ውጤት ውጤት ይፋ ከሆነ  በኋላ ፣ ጋቦን በየካቲት ወር የምርጫ ህጎቿን በማዘጋጀት ፣ የምርጫ አስተዳደር አካልን ትፈጥራለች ተብሎ ይጠበቃል ።  በነሐሴ 2025 የአውሮፓዊያኑ ዘመን ደግሞ ሁለት አመት ያስቆጠረውም ሽግግር ጊዜ  ለመቋጨት  ፕሬዚዳንታዊ፣ የፓርላማ እና የአካባቢ ምርጫዎችን ታከናውናለች። ወታደራዊው ገዥ ንጉሜ  ለወደፊቱ በሚደረጉ ምርጫዎች ላይ ዕጩ ስለመሆናቸው ይፋ ባያደርጉም በዚህ ህዝበ ውሳኔ ላይ ያለው ህገ መንግስት ግን ለፕሬዚዳንትነት ከመወዳደር አይከለክላቸውም።

ትራምፕ የነዳጅ ኢንዱስትሪ ሥራ አስፈፃሚን ለኃይል መስሪያ ቤቱ ጸሐፊነት መረጡ

በቅርቡ ስልጣን የሚረከቡት  ዶናልድ ትራምፕ አዲሱን አስተዳደራቸውን እያዋቀሩ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት ፣ የነዳጅ መስክ አገልግሎት ድርጅት መስራች የሆኑት  
የአሜሪካ ድምፅ

ትራምፕ የነዳጅ ኢንዱስትሪ ሥራ አስፈፃሚን ለኃይል መስሪያ ቤቱ ጸሐፊነት መረጡ

በቅርቡ ስልጣን የሚረከቡት  ዶናልድ ትራምፕ አዲሱን አስተዳደራቸውን እያዋቀሩ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት ፣ የነዳጅ መስክ አገልግሎት ድርጅት መስራች የሆኑት  ክሪስ ራይትን የ ዩናእትድ ስቴትስን  የኃይል መስሪያቤት እንዲመሩ መርጠዋል። የሽግግር ቡድኑ የፕሬዚደንቱን ምርጫ  ቅዳሜ ከሰዓት በኃላ ይፋ አድርጓል ። አርብ እለት ትራምፕ  ፣ የአገር ውስጥ ጉዳይ መስሪያቤትን እንዲመሩ በመረጧቸው  የቀድሞው የሰሜን ዳኮታ ግዛት አስተዳዳሪ  ዳግ በርገም የሚመራ አዲስ ብሔራዊ የኃይል ምክር ቤት ይፋ አድርገዋል። በአዲሱ ኃላፊነታቸው መሰረት በርገም በኃይል ማመንጨት ፍቃድ ፣ምርት ፣ ስርጭት ፣ቁጥጥር እና ማጓጓዝ ላይ የሚሳተፉትን  ሁሉንም አስፈፃሚ ቅርንጫፍ ተቋማት የሚያካልል  ቡድንን እንደሚመሩ   ትራምፕ በመግለጫቸው አስታውቀዋል ። የብሔራዊ  ኃይል  ምክር ቤት ሊቀመንበር እንደመሆናቸው ፣ በርገም  በብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱም መቀመጫ  እንደሚኖራቸው  ተመራጩ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል። ራይት ፣ ኮሎራዶ ላይ መሰረት ያደረገው ፣ ሊበርቲ ኢነርጂ የተሰኘ ኩባንያ ዋና ኃላፊ ቢሆኑም ፣ የፖለቲካ ልምድ ግን የላቸውም ። ነዳጅ ማመንጨትን  ጨምሮ ለነዳጅ ዘይት እና ጋዝ ኢንዱስትሪ ተሟጋች በመሆናቸውም ይታወቃሉ። በአውሮፓዊያኑ  2019 ፣ አደገኛ አለመሆኑን ለማሳየት ፈሳሽ ነዳጅ እስከመጠጣት ደርሰዋል ። በመጋቢት 2024 የአውሮፓዊያኑ ዘመን ይፋ የተደረገው የአሜሪካ  ኃይል መረጃ አስተዳደር ሪፖርት እንደሚያሳየው ፣ ሀገሪቱ ላለፉት ስድስት ተከታታይ ዓመታት  በማንኛውም ጊዜ ከማንኛውም ሀገር የበለጠ ድፍድፍ ዘይት አምርታለች። ወርሃዊ የአሜሪካ ድፍድፍ ዘይት ምርት መጠን በአውሮፓዊያኑ ታህሳስ 2023 ከ13.3 ሚሊዮን በርሜል የደረሰ ሲሆን ፣ ይህም በወረሃዊው የምርት መጠን ልኬት  ከፍተኛው  ሆኖ ተመዝግቧል(AP)። 

እስራኤል ደቡባዊ ቤሩትን በአየር ደበደበች 

የእስራኤል ጦር ሃይል ነዋሪዎች ከአካባቢው ለቀው እንዲወጡ ካስጠነቀቀ ትንሽ ቆይታ በኋላ በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ደቡባዊ ክፍል ፍንዳታ ሲከሰት የሚያሳዩ የ
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል ደቡባዊ ቤሩትን በአየር ደበደበች 

የእስራኤል ጦር ሃይል ነዋሪዎች ከአካባቢው ለቀው እንዲወጡ ካስጠነቀቀ ትንሽ ቆይታ በኋላ በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ደቡባዊ ክፍል ፍንዳታ ሲከሰት የሚያሳዩ የተንቀሳቃሽ ምስሎች ወጥተዋል፡፡  የሂዝቦላ ታጣቂ ዋና ይዞታ እንደሆነ በሚነገርለት በዚህ አካባቢ እስራኤል ከማክሰኞ እለት ጀምሮ ተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሰች ይገኛል፡፡  ጥቃቱ ከመፈጸሙ ጥቂት ቀደም ብሎ የእስራኤል ወታደራዊ ቃል አቀባይ አቪሻይ አድራኢ በሃሬት ህሪክ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎችን ለቀው እንዲወጡ በ X የማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ጥረ አስተላልፈው ነበር፡፡  የሊባኖስ መንግስት ብሄራዊ የዜና ወኪል (ኤን ኤን ኤ) በበኩሉ «ጠላት»  ሲል በገለጻት እስራኤል በሃሬት ሂሪክ አቅራቢያ የደረሰውን ጨምሮ ሶስት የአየር ጥቃቶች ደርሰዋል ብሏል፡፡  እስራኤል በደቡባዊ ቤይሩት ላይ ተደጋጋሚ የአየር ድብደባ መፈጸሟን ተከትሎ በርካታ ንፁሀን ዜጎች ከአካባቢው እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል፡፡    ሂዝቦላ በበኩሉ በሰሜናዊ እስራኤል የሚገኘው የእግረኛ ጦር ሻለቃ ዋና መሥሪያ ቤት ላይ ያነጣጠረ ሁለት የሮኬት ጥቃቶችን ሌሊት ላይ ማድረሱን ገልጿል።  የሊባኖስ ባለስልጣናት ሂዝቦላ እና እስራኤል የተኩስ ልውውጥ ከጀመሩበት ካለፈው አመት ጥቅምት ጀምሮ ከ3,440 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ አስታውቀዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የሊባኖስ መንግስት መገናኛ ብዙሃን የእስራኤል የምድር ጦር ሃይሎች በሊባኖስ ውጊያ ከጀመሩ ከስድስት ሳምንታት በኋላ ወደ ሊባኖስ ጠልቀው መግባታቸውንና ከሂዝቦላህ ታጣቂዎች ጋር ከፍተኛ ውጊያ ካደረጉ በኋላ እንዳፈገፈጉ ዘግበዋል። ሪፖርቶቹ ዛሬ ጥዋት የእስራኤል ወታደሮች በደቡብ ሊባኖስ በምትገኘው ቻማ መንደር በእስራኤል ድንበር አቅራቢያ የሚገኝ ስትራቴጂካዊ ኮረብታ መያዛቸውንና ቆይተው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡  የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች የቤይሩትን ደቡባዊ ሰፈሮች እና ሌሎች አካባቢዎችን እየደበደቡ ባሉበት ወቅትም የሊባኖስ እና የሂዝቦላህ ባለስልጣናት ጦርነቱን ለማቆም በዩናይትድ ስቴትስ የቀረበውን ረቂቅ ሀሳብ እያጤኑ እንደነበረ ተገልጿል፡፡

በህንድ በሆስፒታል በተነሳ እሳት አስር ህጻናት ሞቱ 

በሰሜናዊ ህንድ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ በአራስ ሕፃናት ከፍተኛ እንክብካቤ ክፍል ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ አስር አዲስ የተወለዱ ሕፃናትን ሲሞቱ 16 ሌሎች ደ
የአሜሪካ ድምፅ

በህንድ በሆስፒታል በተነሳ እሳት አስር ህጻናት ሞቱ 

በሰሜናዊ ህንድ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ በአራስ ሕፃናት ከፍተኛ እንክብካቤ ክፍል ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ አስር አዲስ የተወለዱ ሕፃናትን ሲሞቱ 16 ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል ሲሉ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡  አርብ አመሻሽ ላይ በህንድ ኡታር ፕራዴሽ ግዛት በጃንሲ ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥየእሳት አደጋው በተከሰተበት ወቅት 55 ጨቅላ ህጻናት ህክምና እየተደረገላቸው ነበር ተብሏል፡፡  የእሳት አደጋ መከላከል ባለሙያዎችም አደጋው ከተከሰተ ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ የህይወት ማዳን ስራ መጀመራቸውንና ይህም የህይወት አድኑን ጥረት አዘግይቶታል ሲሉ የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡  በህንድ ውስጥ የእሳት ቃጠሎ የተለመደ መሆኑን የገለጸው የአሶሽየትድ ፕረስ ዘገባ የግንባታ ህጎች እና የደህንነት ደንቦች ብዙ ጊዜ በቤት ገንቢዎች እና በነዋሪዎች ይጣሳሉ ብሏል፡፡. ይህም በሀገሪቱ ካለው ደካማ የጥገና ስርዓት እና የእሳት አደጋ መከላከያ መሳሪያዎች እጥረት ጋር ተዳምሮ በእሳት አደጋ ለሚከሰት ሞት ምክንያት ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡ 

የቀድሞ የከባድ ሚዛን ሻምፒዮን ማይክ ታይሰን በጃክ ፖል ተሸነፈ 

ትላንት ምሽት በቴክሳስ በተካሄደውና የቀድሞው ታዋቂ ቦክሰኛ ማይክ ታይሰንን በድጋሚ ወደ ቀለበት በመለሰው የከባድ ሚዛን ፍልሚያ ጃክ ፖል በነጥብ አሸናፊ ሁኗ
የአሜሪካ ድምፅ

የቀድሞ የከባድ ሚዛን ሻምፒዮን ማይክ ታይሰን በጃክ ፖል ተሸነፈ 

ትላንት ምሽት በቴክሳስ በተካሄደውና የቀድሞው ታዋቂ ቦክሰኛ ማይክ ታይሰንን በድጋሚ ወደ ቀለበት በመለሰው የከባድ ሚዛን ፍልሚያ ጃክ ፖል በነጥብ አሸናፊ ሁኗል፡፡  የ27 አመቱ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪ ሽልማት አሸናፊው ፖል እና በ58 አመቱ የቀድሞ የከባድ ሚዛን ሻምፒዮን ታይሰን መካከል የተደረገውን ፍልሚያ በአርሊንግተን በሚገኘው AT&T ስታዲየም በርካታ ተመልካቾች ታድመውበታል፡፡ በኔትፍሊክስም ፍልሚያው በቀጥታ ስርጭት ተላልፏል፡፡   በፍልሚያው ፖል ተፋላሚው ማይክ ታይሰን ላይ 78 ቡጢዎችን ያሳረፈ ሲሆን ታይሰን በበኩሉ  18 ቡጢዎችን ብቻ ተጋጣሚው ላይ ማሳረፍ መቻሉ ተገልጿል፡፤   «በመጀመሪያ ደረጃ ማይክ ታይሰን - እሱ ጋር መፋለም መቻሌ ለእኔ ክብር ነው» ሲል ፖል ከፍልሚያው በኋላ ተናግሯል።  የጉልበት መከላከያ ለብሶ ፍልሚያውን ያደረገው ማይክ ታይሰን ከውድድሩ በኋላ የእግር ጉዳት እንደነበረበት ገልጿል ነገር ግን ለውድድሩ ይህንን ምክንያት ማድረግ አልፈልግም ሲልም ተናግሯል፡፡   በ1980ዎቹ መገባደጃ እና በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ እጅግ አስፈሪ የከባድ ሚዛን ሻምፒዮኖች አንዱ የነበረው ማይክ ታይሰን ይህ በ20 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረገው ፕሮፌሽናል ፍልሚያ ነው፡፡ ወደ ቀለበቱ እንደገና ይመለስ እንደሆነ ሲጠየቅ ቁርጥ ያለ ምላሽ አልሰጠም። 

የቡድን 20 ሃገራት በአየር ንብረት ለውጥ ዙርያ ከስምምነት እንዲደረስ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ ተመድ አሳሰበ 

የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ሃላፊ  ለታዳጊ ሃገራት በሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ዙርያ በኮፕ 29  እየተደረጉ ያሉ ድርድሮች ገና ረጅም መንገድ እንደሚቀራ
የአሜሪካ ድምፅ

የቡድን 20 ሃገራት በአየር ንብረት ለውጥ ዙርያ ከስምምነት እንዲደረስ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ ተመድ አሳሰበ 

የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ሃላፊ  ለታዳጊ ሃገራት በሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ዙርያ በኮፕ 29  እየተደረጉ ያሉ ድርድሮች ገና ረጅም መንገድ እንደሚቀራቸው አስጠንቅቀዋል፡፡  በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ተደራዳሪዎቹ ልዩነታቸው በማጥበብ ከስምምነት ለመድረስ እየተነጋገሩ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በቀጣዩ ሳምንት በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ ከሚደረገው የሚንስትሮች ስብሰባ አስቀድሞ ከስምምነት ለመድረስ ፍላጎት ቢኖርም በዋና ዋና ጉዳዮች ግን አሁንም ከስምምነት መድርስ አልተቻለም ተብሏል፡፡  የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ሀላፊ ሲሞን ስቲል የዓለማችን ታላላቅ ኢኮኖሚዎች እና ከፍተኛ ብክለትን የሚያካትቱ የቡድን 20 ሀገራት መሪዎች ሰኞ በብራዚል ሲገናኙ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡት ተማጽነዋል።  ለአለም አቀፍ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀቶች ተጎጅ የሆኑት አንዳንድ ታዳጊ ሀገራት ከአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመቋቋምና ወደ ታዳሽ ሃይል እንዲሸጋገሩ  1.3 ትሪሊዮን ዶላር ዓመታዊ ድጋፍ ጠይቀዋል፡፡   ይህ አሃዝም አሜሪካን፣ የአውሮፓ ህብረት እና ጃፓንን ጨምሮ ለጋሾች ከሚከፍሉት 10 እጥፍ በላይ ነው። 

«ኢላን መስክ ሉዓላዊነታችንን ሊያከብሩ ይገባል» የጣሊያን ፕሬዝደንት

ጣሊያን ወደ ሀገሯ የሚጓዙ ፍልሰተኞች ውሳኔ እስከሚሰጣቸው አልቤኒያ በሚገኙ የእስር ካምፖች ለማቆየት ያወጣችው እቅድ የሕጋዊነት ጉዳይ መሰናክል አጋጥሞታል
የአሜሪካ ድምፅ

«ኢላን መስክ ሉዓላዊነታችንን ሊያከብሩ ይገባል» የጣሊያን ፕሬዝደንት

ጣሊያን ወደ ሀገሯ የሚጓዙ ፍልሰተኞች ውሳኔ እስከሚሰጣቸው አልቤኒያ በሚገኙ የእስር ካምፖች ለማቆየት ያወጣችው እቅድ የሕጋዊነት ጉዳይ መሰናክል አጋጥሞታል። ሮም ላይ ጉዳዩን የተመለከቱት ዳኞች ጉዳዩን ወደ አውሮፓ ሕብረት ፍርድ ቤት መርተውታል። አህጉራዊው ችሎት ውሳኔውን ለመስጠት ወራት ወይም ዓመታት ሊወስድ እንደሚችል ጠቅሶ ሄንሪ ሪጅዌል ከለንደን ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ የተካሄደውን ምርጫ አወደሰች

የኢትዮጵያ መንግስት በያዝነው ሳምንት ቦሶማሌላንድ የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አወደሰ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ
የአሜሪካ ድምፅ

ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ የተካሄደውን ምርጫ አወደሰች

የኢትዮጵያ መንግስት በያዝነው ሳምንት ቦሶማሌላንድ የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አወደሰ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ “’ምርጫው በሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ መንገድ’ በመካሄዱ ኢትዮጵያ የሶማሌላንድን ሕዝብ እንኳን ደስ አለህ ትላለች” ብሏል። መግለጫው በተጨማሪም “ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫ” በማካሄዱ ለሶማሌላንድን ብሄራዊ ምርጫ ኮሚሽን ያለውን አድናቆት ገልጧል። «ይህ ሂደት የሶማሌላንድን አስተዳደር እና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መጎልበት የሚያንፀባርቅ ነው» ሲልም አክሏል። የኢትዮጵያ እና የሶማሌላንድ ጠንካራ ግንኙነት ለዓመታት የዘለቀ ሲሆን፤ እየተገባደደ ባለው የአውሮፓውያኑ 2024 መጀመሪያ ላይ ኢትዮጵያን ከሶማሌላንድ 20 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የባህር ዳርቻ በሊዝ መከራየት የሚያስችል እና በምላሹ ለሶማሌላንድ ሉአላዊ እውቅና የሚያስገኝ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን የሃርጌሳ ባለስልጣናት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ይሁንና ሶማሌላንድን የግዛቷ አካል አድርጋ የምትመለከተው ሶማሊያ ‘ሉዓላዊነቴን ጥሷል’ ስትል በሁለቱ እገኖች የተፈረመውን ስምምነት አውግዛለች። ሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ በበኩላቸው ስምምነቱን ‘ትክክለኛ ነው’ ሲሉ ይከላከላሉ። የሶማሌላንዱ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ ጉሌይድ አህመድ ጃማ በሰጡት አስተያየት እንደጠቆሙት፤ የወቅቱ የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ በምርጫው ካሸነፉ የመግባቢያ ሰነዱን ተግባራዊ ያደርጋሉ። ቅሬታ እንዳላቸው የገለጡ ተቃዋሚ ቡድኖችም በበኩላቸው ስምምነቱን መቀበላቸው ተመልክቷል።

ትረምፕ የደህንነት ተቋማትን እንዲመሩ የረጅም ጊዜ ደጋፊዎቻቸውን አጭተዋል

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ የአሜሪካ ማዕከላዊ የምርመራ ቢሮ (ሲአይኤ) እንዲመሩ ያጩት፣ የረጅም ጊዜ አጋራቸውና ደጋፊያቸው የነበሩ ግለሰብን ነው። የ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ የደህንነት ተቋማትን እንዲመሩ የረጅም ጊዜ ደጋፊዎቻቸውን አጭተዋል

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ የአሜሪካ ማዕከላዊ የምርመራ ቢሮ (ሲአይኤ) እንዲመሩ ያጩት፣ የረጅም ጊዜ አጋራቸውና ደጋፊያቸው የነበሩ ግለሰብን ነው። የአሜሪካ የደህንነት ተቋማትን እንዲመሩ ያጩት ደግሞ የመንግሥት ሥልጣን ልምድ የሌላቸውንና፣ ተቋማቱን ሊያምሱ ይችላሉ ተብሎ የሚሰጉ ግለሰብን ነው። የቪኦኤ የብሔራዊ ደህንነት ዘጋቢ ጀፍ ሰልዲን ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የቀድሞው የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አህመድ ሲላንዮ አረፉ

የቀድሞው የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አህመድ ሞሃመድ ሞሃሙድ ሲላንዮ ዛሬ አርብ በ88 ዓመታቸው ሃርጌሳ ውስጥ ማረፋቸውን የሶማሌላንድ ቴሌቭዥን አስታወቀ። እንደ
የአሜሪካ ድምፅ

የቀድሞው የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አህመድ ሲላንዮ አረፉ

የቀድሞው የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አህመድ ሞሃመድ ሞሃሙድ ሲላንዮ ዛሬ አርብ በ88 ዓመታቸው ሃርጌሳ ውስጥ ማረፋቸውን የሶማሌላንድ ቴሌቭዥን አስታወቀ። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2010 በከፍተኛ የሕዝብ ድምፅ ለአምስት አመት የስልጣን ዘመን የተመረጡት ሲላንዮ፤ የሥራ ዘመናቸው ለተከሉት ሁለት ዓመታት ከተራዘመ በኋላ፤ በአሁኑ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ እስከ ተተኩበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር 2017 ድረስ አገልግለዋል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1982 የተመሰረተውን እና በኢትዮጵያ መንግስት ይደገፍ የነበረውን የሶማሌ ብሔራዊ ንቅናቄ የተቀላቀሉት ሲላንዮ የአማፂ ድርጅት መርተዋል። በመጀመሪያው የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት የቀድሞው አማጺ መሪ አብዲራህማን አሊ ቱር እስከተኩበት ጊዜ ድረስም አማጺ ቡድኑን ለበርካታ አመታት መርተዋል። ሲላንዮ የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት መሪዎች ጋር ውይይት ጀምረው ነበር። ከአሁኑ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ የመጀመሪያ የስልጣን ዘመን፤ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር 2014 አንስቶ በሁለቱ ወገኖች መካከል ተከታታይ ውይይቶች ቢካሄዱም፤ ጥረቶቹ በሙሉ ለስኬት ሳይበቁ ቀርተዋል። የሲላንዮ ዜና እረፍት የተሰማው ሶማሌላንድ አራተኛውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ካካሄደች ሁለት ቀናት በኋላ መሆኑ ነው። የህልፈታቸው መንስኤ ይፋ አልተደረገም። የቀድሞው የሶማሌላንድ መሪ የቀብር ሥነ ስርአታቸው ሰኞ እንደሚደሚፈጸም በዜና ዕረፍታቸው ተጠቅሷል።

በዩናይትድ ስቴትስ የምርጫ ታሪክ ዳግም ወደ ዋይት ሃውስ ለመመለስ ዕድል ያገኙት ሁለተኛው ፕሬዝዳንት

ባለፈው ማከኞው ምርጫ በከፍተኛ ድምጽ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን፤ የእንደራሴዎች ምክር ቤቱን ከእጁ ያስገባውን እና እስካሁን በተቆጠረውም ድምጽ የተወካዮች ምክር ቤ
የአሜሪካ ድምፅ

በዩናይትድ ስቴትስ የምርጫ ታሪክ ዳግም ወደ ዋይት ሃውስ ለመመለስ ዕድል ያገኙት ሁለተኛው ፕሬዝዳንት

ባለፈው ማከኞው ምርጫ በከፍተኛ ድምጽ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን፤ የእንደራሴዎች ምክር ቤቱን ከእጁ ያስገባውን እና እስካሁን በተቆጠረውም ድምጽ የተወካዮች ምክር ቤቱን ውጤት በአብላጫ ድምጽ እየመራ ያለው የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ ያሁኑ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የካቢኔ አባሎቻቸውንና ከፍተኛ አማካሪዎቻቸውን ከወዲሁ ይፋ ማድረግ ይዘዋል። ዳግም ወደ ዋይት ሃውስ የሚመለሱበትን ያልተጠበቀ ከፍተኛ ድምጽ ያገኙትን የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕን ለዚህ ስኬት ያበቁት ምክኒያቶች የፖለቲካ አዋቂዎችን እና የሌሎችን ትኩረት በተመሳሳይ ስበዋል። በማናቸውም ሁኔታዎች በሙሉ ልባቸው ትራምፕን በመደገፍ ከሚታወቁት የፓርቲያቸው አጥባቂ ደጋፊዎች፤ ለሁለቱም ፓርቲዎች ወገንተኝነት እስከ ከሌላቸው መራጮች እና ብሎም በዲሞክራት ፓርቲ ደጋፊነታቸው እስከሚታወቁ በርካቶች ድረስ፤ በተመሳሳይ ድምጻቸውን ለትረምፕ ለመስጠት የወሰኑባቸው እነኚህ ሁኔታዎች፤ ያልጠበቁት የገጠማቸውን የተፎካካሪው ፓርቲ ደጋፊዎች ጨምሮ ብዙዎችን ለውይይት መጋበዛቸው አልቀረም። በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን የሕግ መምህሩንና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኙን ዶ/ር ተሻገር ወርቁን አነጋግረናል። ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡  

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳሕለ ወርቅ ዘውዴ በበጎ ፈቃድ በተሰባሰቡ ሴቶች ተመሰገኑ

በበጎ ፈቃድ በተሰባሰቡ ሴቶች ጉዳይ ላይ በሚሠሩ ሀገር በቀል መሪዎች ዛሬ በምስጋና የተሸኙት የቀድሞ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ ሴቶችን የ
የአሜሪካ ድምፅ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳሕለ ወርቅ ዘውዴ በበጎ ፈቃድ በተሰባሰቡ ሴቶች ተመሰገኑ

በበጎ ፈቃድ በተሰባሰቡ ሴቶች ጉዳይ ላይ በሚሠሩ ሀገር በቀል መሪዎች ዛሬ በምስጋና የተሸኙት የቀድሞ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ ሴቶችን የማብቃት ጅምር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠየቁ። በሴቶች የተጀመሩ ሥራዎች ድጋፍ ሊደረግባቸው እንደሚገባ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቷ በንግግራቸው በሴቶች ላይ ካተኮሩ ንግግሮች ውጭ የሰጡት አስተያየት የለም። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የዝግጅቱ ታዳሚዎች፤ በመንግሥት በኩል ተገቢውን አሸኛኘት ስላልተሰጣቸው ቅር እንደተሰኙ ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በአየር ንብረት ጉባዔው የ1.3 ትሪሊየን ዶላር አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት እንዲጸድቅ ግፊት እየተደረገ ነው

በቅርቡ አዲስ በተሾሙት የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ እየተመራ፣ በአዘርባይጃን ዋና ከተማ ባኩ እየተካሄደ ባለው 29ኛው ዓለም አቀፍ የአየ
የአሜሪካ ድምፅ

በአየር ንብረት ጉባዔው የ1.3 ትሪሊየን ዶላር አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት እንዲጸድቅ ግፊት እየተደረገ ነው

በቅርቡ አዲስ በተሾሙት የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ እየተመራ፣ በአዘርባይጃን ዋና ከተማ ባኩ እየተካሄደ ባለው 29ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይ በመሳተፍ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ልዑክ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከባድ ጉዳት እየደረሰባቸው ላሉ ያላደጉ ሀገራት ለመስጠት ቃል የተገባው የገንዘብ ድጋፍ ወደ 1.3 ትሪሊየን ዶላር ያድጋል ብሎ እንደሚጠብቅ፣ በድርድሩ ላይ ተሳታፊ የሆኑት የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያ አቶ ያሬድ አበራ ገልጸዋል። «የአፍሪካ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትሮች ጉባዔ የወቅቱ ሊቀመንበር የኾነችው ኢትዮጵያ ከሌሎች ታዳጊ ሀገራት ሀገራት ጋራ በመሆን የገንዘብ ድጋፉ ስምምነት ላይ እንዲደርስ ጥረት እያደረገች ነው» ያሉት አቶ ያሬድ፣ ከከርሰ ምድር የሚወጣ ኃይል አጠቃቀምን ለመቀነስ እና የዓለምን ሙቀት ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ግን አሁንም አዳጋች መሆኑን አመልክተዋል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም. ፓሪስ ላይ በተካሄድው 21ኛው ጉባዔ የዓለም ሀገራት በፈረሙት የፓሪስ ስምምነት የዓለም ሙቀትን 1.5 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ላይ ለመገድብ ተስማምተው ነበር። ይህንንም ለማሳካት እ.አ.አ በ2030 ሙቀት ማመቅ የሚችሉ የጋዝ አይነቶችን በ43 ከመቶ ለመቀነስ እና በ2050 ዓለምን ከካርበንዳይኦክሳይድ የፀዳ ለማድረግ ቃል ገብተዋል። ባለፉት 40 ዓመታት ባልታየ ድርቅ ሲሰቃይ የነበረው የአፍካ ቀንድ አካባቢ ባለፈው ዓመት የተከሰተው ከፍተኛ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ ከ1.6 ሚሊየን በላይ ሰዎች እንዲፈናቀሉ አድርጎ የነበረ ሲሆን ከእነዚኽ ውስጥ 396 ሺሕ የሚሆኑት የሚገኙት ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን አክሽን አጌንስት ሀንገር የተሰኘው በአፍሪካ ቀንድ ረሃብን ለማጥፋት የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ርዳታ ሰጪ መረጃ ያመለክታል። ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የሚያከትለው ተደጋጋሚ የጎርፍ አደጋም መንገዶችን እና ቤቶችን ከማጥለቅለቁ እና ነዋሪዎችን ከማፈናቀሉ በተጨማሪ የውሃ ምንጮች እንዲበቀሉ እንዲሁም የጤና ተቋማት እንዲወድሙ በማድረጉ፣ በክልሉ ለበሽታ ተጋላጭነት ጨምሯል። በአየርን ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱት እነዚህ ተደራራቢ ጉዳቶችን እያስተናገደች ያለችው ኢትዮጵያ በአየርን ንብረት ለውጥ ተጠቂ ከሆኑ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር የጋራ አቋም በመያዝ በዓለም አቀፍ ጉባዔው ድምፃቸውን እያሰሙ ነው። /ከአቶ ያሬድ አበራ ጋራ የተደረገውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።/    

ለቋሚ ደመወዝተኞች የሥራ ግብር እንዲቀነስ ተጠየቀ

በኢትዮጵያ የብር የመግዛት አቅም መዳከምን ተከትሎ ቋሚ ደመወዝተኞችን የኑሮ ሁኔታው እየፈተናቸው መሆኑ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ገለጸ፡፡
የአሜሪካ ድምፅ

ለቋሚ ደመወዝተኞች የሥራ ግብር እንዲቀነስ ተጠየቀ

በኢትዮጵያ የብር የመግዛት አቅም መዳከምን ተከትሎ ቋሚ ደመወዝተኞችን የኑሮ ሁኔታው እየፈተናቸው መሆኑ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ገለጸ፡፡ የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ መንግሥት የሥራ ግብር መቀነስን ጨምሮ የኑሮ ጫናውን የሚያቃልሉ ኢኮኖሚያዊ ርምጃዎች እንዲወስድ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድን በደብዳቤ መጠየቃቸውን ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሃብት መምህር የሆኑት ዶክተር አጥላው ዓለሙ በበኩላቸው «መንግሥት የሥራ ግብር መቀነስን ጨምሮ ቋሚ ደመወዝተኞች ተጨማሪ ገቢ የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይኖርበታል» ብለዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከገንዘብ ሚንስቴር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ ነገር ግን የገንዘብ ሚንስትር ደኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ በቅርቡ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ መንግሥት የደመወዝ ጭማሪ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ጫናውን ለማቃለል እየሠራ ስለመሆኑ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡  

Get more results via ClueGoal