በእስራኤል ጥቃት 17 ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ ጤና ባለሥልጣናት ተናገሩ
newsare.net
በጋዛ ሰርጥ ዛሬ ረቡዕ እስራኤል በተከታታይ ባደረሰቻቸው ጥቃቶች በትንሹ 17 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን የጋዛ የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል። በአንደኛበእስራኤል ጥቃት 17 ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ ጤና ባለሥልጣናት ተናገሩ
በጋዛ ሰርጥ ዛሬ ረቡዕ እስራኤል በተከታታይ ባደረሰቻቸው ጥቃቶች በትንሹ 17 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን የጋዛ የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል። በአንደኛው የእስራኤል ጥቃት በሰሜን ጋዛ ጃባሊያ አካባቢ የሚገኝ መኖሪያ ቤት በመመታቱ ቢያንስ 12 ሰዎች ተገድለዋል። በሰሜን ጋዛ ከሃማስ ታጣቂዎች ጋራ በተደረገ ውጊያ ከወታደሮቹ አንዱ መገደሉና አንደኛው መቁሰሉን የእስራኤል ጦር ዛሬ ረቡዕ አስታውቋል። በደቡባዊ ሊባኖስ፣ የእስራኤል ኃይሎች እና የሂዝቦላህ ታጣቂዎች ለተከታታይ ወራት በተባባሰ ውጊያ ላይ ሲኾኑ የሊባኖስ ጦር ከወታደሮቹ አንዱ በእስራኤል ተኩስ መገደሉን እና የእስራኤል ወታደሮች በሊባኖስ ጦር ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ዛሬ አስታውቋል። የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ረቡዕ፣ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በሊባኖስ የተባበሩት መንግሥታት ተልእኮ አካል የኾኑት የፈረንሳይ ወታደሮች ተተኩሶባቸዋል፡፡ መግለጫው አክሎም “ወታደሮቹ እንደልብ ተዘዋውረው ተልእኮቸውን የመፈጸም ነጻነታቸው ሊጠበቅ እንደሚገባ” አሳስቧል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ልኡክ አሞስ ሆችስቴይን በእስራኤል እና በኢራን በሚደገፈው በሂዝቦላ መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት የሚያቆም የተኩስ አቁም ስምምነት ሊደረስ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ትላንት ማክሰኞ ገልጸዋል፡፡ «ይህን ግጭት ለማቆም ተጨባጭ እድል አለን» ያሉት ሆችስቴይን የሄዝቦላህ ታጣቂዎች አጋር ናቸው የተባሉትን ሸምጋዩን የፓርላማ አፈ-ጉባዔ ናቢህ ቤሪን ጨምሮ፣ ከሊባኖስ ባለስልጣናት ጋር «በጣም ገንቢ ውይይት» አድርገናል ብለዋል። «የሊባኖስ መንግሥት እና ሂዝቦላህ ባለፈው ሳምንት በቀረበው ሀሳብ ተስማምተዋል፣ ሁለቱም በይዘቱ ላይ አንዳንድ አስተያየቶችን ሰጥተዋል» ሲሉ የቤሪ ረዳት የሆኑት አሊ ሀሰን ካሊል ከትላንት በስትያ ሰኞ ለሮይተርስ ተናግረዋል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረስም እስራኤል በሂዝቦላህ ላይ ወታደራዊ ዘመቻዋን እንደምትቀጥል ተናግረዋል። ኔታንያሁ ለእስራኤል ፓርላማ ባደረጉት ንግግር «ዋናው ነገር በወረቀት ላይ የሚሰፍረው (ስምምነት) አይደለም» ብለዋል። Read more