አሜሪካ የተመድ የጋዛ ተኩስ አቁም ውሳኔን ውድቅ አደረገች
newsare.net
ዩናይትድ ስቴትስ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት በጋዛ ቋሚ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ታጋቾች እንዲለቀቁ በመጠየቅ ትላንት ረቡዕ ያሳለፈው ውሳአሜሪካ የተመድ የጋዛ ተኩስ አቁም ውሳኔን ውድቅ አደረገች
ዩናይትድ ስቴትስ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት በጋዛ ቋሚ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ታጋቾች እንዲለቀቁ በመጠየቅ ትላንት ረቡዕ ያሳለፈው ውሳኔ የተገለጸበት ቋንቋ “ለሀማስ የተሳሳተ መልዕክት ያስተላልፋል” በሚል ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷን በመጠቀም ውድቅ አደርጋዋለች፡፡ በመንግሥታቱ ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል አምባሳደር ሮበርት ዉድ “የተኩስ አቁምን ከታጋቾች መለቀቅ ጋር ማገናኘት ለዘላቂ ሰላም አስፈላጊ ነው” ሲሉ የፍልስጤም መልዕክተኛን ጨምሮ ተቺዎች ግን አሜሪካ የውሳኔ ሃሳቡን ውድቅ ማድረጓ ጦርነትን ትደግፋለች ማለት ነው ሲሉ ከሰዋል። አምባሳደር ሮበርት ውድ ድምጽ ከተሰጠ በኋላ በሰጡት ቃል «ዩናይትድ ስቴትስ ይህ ውጤት እንዳይመጣ ለማድረግ ለሳምንታት በቅን ልቦና ሠርታለች» ብለዋል፡፡ አምባሳደሩ አክለውም “በድርድሩ ጊዜ ሁሉ ግልፅ አድርገናል፣ ታጋቾቹ ሳይለቀቁ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የተጠየቀውን የተኩስ አቁም መደገፍ አልቻልንም፣ ምክንያቱም ይህ ምክር ቤት ቀደም ሲል ባደረገው ጥሪ መሠረት ፣ የጦርነቱ በዘላቂነት ማብቃት ከታጋቾቹ መፈታት ጋር አብሮ መምጣት አለበት። እነዚህ ሁለት አስቸኳይ ግቦች የማይነጣጠሉ ናቸው” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስን አቋም ግልጽ አድርገዋል፡፡ በተመረጡ 10 የፀጥታው ምክር ቤት አባላት የቀረበውና ውድቅ የተደረገው የውሳኔ ሃሳብ፣ አስቸኳይ የተኩስ አቁም በሁሉም ወገኖች እንዲከበር እና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ታጋቾች እንዲፈቱ የሚጠይቅ ነው፡፡ በእስራኤል ዘንድ ግን አሸባሪዎችን እንዳይቀጡ የሚያደርግ ውሳኔ ተደርጎ ተወስዷል። ለ14 ወራት በዘለቀው የእስራኤል እና የሃማስ ግጭት አሜሪካ ጋዛን በተመለከተ የወሰደችው ይህ አቋም አራተኛው ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጦርነቱን ማስቆም ባለመቻሉ ዓለም አቀፍ ቁጣ እየጨመረ መሆኑ ተነግሯል፡፡ የፍልስጤም ምክትል አምባሳደር ማጅድ ባሚያ ለምክር ቤቱ ባሰሙት ንግግር «ረቂቅ ውሳኔ የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ የተደረገ ሙከራ እንጂ አደገኛ መልዕክት የሚያስተላልፍ አይደለም» ብለዋል፡፡ አስከትለውም "ይልቁኑ አደገኛው እስራኤል እናንተ ራሳችሁ በምትቃወሙት እቅዷ መግፋት እንደምትችል መልዕክት የሚያስተላልፈው ይህ ድምጽን በድምጽ የመሻር ርምጃ ነው፡፡ የምናስተላልፋቸው መልዕክቶች ትርጉም አላቸው፡፡ ይሄኛው በመጥፎ ጊዜ የተላለፈ መጥፎ መልዕክት ነው፡፡እስራኤል ለገደለቻቸው ፍልስጤም ሲቪሎች ተጠያቂ ነች። ከዚህ ኃላፊነት ነጻ መሆን አይቻልም›› ብለዋል። ይህ በእንዲህ አንዳለ የዩናይትድ ስቴትስ ልዑክ አሞስ ሆችስቴይን ዛሬ ሐሙስ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋራ እንደሚገናኙ ይጠበቃል። ሆችስቴይን በዚህ ሳምንት የሄዝቦላ ታጣቂዎች አጋር ናቸው የሚባሉትን የፓርላማ አፈ-ጉባዔ ናቢህ ቤሪን ጨምሮ ከሊባኖስ ባለሥልጣናት ጋራ ገንቢ በሆኑ ንግግሮች፣ መሻሻሎች መታየታቸውን ገልጸዋል፡፡ Read more