ትረምፕ ለጠቅላይ ዐቃቤ ህግነት ያጯቸው ማት ጌትስ ራሳቸውን አገለሉ
newsare.net
በተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለጠቅላይ አቃቤ ህግነት የታጩት ሪፐብሊካኑ የቀድሞ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ማት ጌትስ ራሳቸውን ከትረምፕ ለጠቅላይ ዐቃቤ ህግነት ያጯቸው ማት ጌትስ ራሳቸውን አገለሉ
በተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለጠቅላይ አቃቤ ህግነት የታጩት ሪፐብሊካኑ የቀድሞ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ማት ጌትስ ራሳቸውን ከእጩነቱ አገለሉ፡፡ ጌትስ ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ ኤክስ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ “ትላንት ከህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት ጋር ጥሩ ስብሰባዎችን አድርጌ ነበር። ለሰጡኝ መልካም አስተያየትና ብዙዎች ላሳዩኝ ድጋፍ አደንቃለሁ፡፡ ወቅቱ ከባድ የነበረ ቢሆንም የኔ ለቦታው መታጨት የፕሬዚዳንት ትረምፕ እና ቫንስ ሽግግርን ወሳኝ የሥራ ትኩረት የሚከፋፍል እየሆነ መምጣቱ ግልጽ ነው” ብለዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የሥነ ምግባር ኮሚቴ ትላንት ረቡዕ ተሰብስቦ እሳቸውን በሚመለከት እያጠናቀቀ ያለውን የምርምራ ሪፖርት ይፋ በማድረግ ላይ ሊስማማ አልቻለም፡፡ ጌትስ እኤአ ጥር 20 2025 ሥራውን በሚጀምረው አዲሱ አስተዳደር የሀገሪቱ ከፍተኛ የህግ አስከባሪ ባለስልጣን ለመሆን በትረምፕ ከመመረጣቸው በፊት ከጾታዊ ምግባረ ብልሹነት እና ሱስ አስያዥ እፅ በድብቅ ከመጠቀም ጋር የተያያዘ ክስ ቀርቦባቸዋል። ሁለት የዜና ማሰራጫዎች፣ ኤቢሲ ኒውስ እና ዋሽንግተን ፖስት፣ ጌትስ በኮሚቴው ፊት ለቀረቡ ሁለት ሴቶች እኤአ ከሀምሌ 2017 እስከ ጥር 2019 መጨረሻ በድምሩ ከ10,000 ዶላር በላይ መክፈላቸውን የሚያሳዩ ሰነዶችን የምክር ቤቱ ኮሚቴ ማግኘቱን ዘግበዋል። የ42 ዓመቱ ጌትስ ለምክር ቤቱ አባልነት ለአምስተኛ ጊዜ የተመረጡ ቢሆንም በትረምፕ ለዐቃቤ ህግነት መታጨታቸውን ከሰሙ በኋላ ከምክር ቤት አባልነታቸው መልቀቃቸው ይታወቃል፡፡ Read more