ቻይና ኢኮኖሚዋን ለማነቃቃት መግቢያ ቪዛ የማያስፈልጋቸው ሀገሮችን ቁጥር ልታሳድግ ነው
newsare.net
ቻይና የቱሪዝም እና የንግድ ተጓዦችን ቁጥር በማሳደግ የተቀዛቀዘውን ኢኮኖሚዋን ለማነቃቃት ለዘጠኝ ተጨማሪ ሀገራት ዜጎች ካለቪዛ እንዲገቡ ልትፈቅድ መሆኗንቻይና ኢኮኖሚዋን ለማነቃቃት መግቢያ ቪዛ የማያስፈልጋቸው ሀገሮችን ቁጥር ልታሳድግ ነው
ቻይና የቱሪዝም እና የንግድ ተጓዦችን ቁጥር በማሳደግ የተቀዛቀዘውን ኢኮኖሚዋን ለማነቃቃት ለዘጠኝ ተጨማሪ ሀገራት ዜጎች ካለቪዛ እንዲገቡ ልትፈቅድ መሆኗን አስታወቀች፡፡ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን ዛሬ ዓርብ እንዳስታወቁት እአአ ከህዳር 30 ጀምሮ ከቡልጋሪያ፣ ሮማኒያ፣ ማልታ፣ ክሮኤሺያ፣ ሞንቴኔግሮ፣ ሰሜን መቄዶኒያ፣ ኢስቶኒያ፣ ላቲቪያ እና ጃፓን ተጓዦች ለሠላሳ ቀናት ቆይታ ያለ ቪዛ ሊገቡ ይችላሉ። ይህ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ያለቪዛ መግባት የተፈቀደላቸውን ሀገራት ቁጥር ወደ 38 ያሳድገዋል። ከዚህ ቀደም ከቪዛ ነጻ ፈቃድ የነበራቸው ሦስት ሀገራት ብቻ ሲሆኑ የእነሱም ፈቃድ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ተሰርዞ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ የጃፓን ከቪዛ ነጻ ሀገራቱ ውስጥ መጨመር፣ ቻይና በታይዋን ጉዳይ ከቶኪዮ በተደረጉ ጠንከር ያሉ ንግግሮች የተነሳ ሻክሮ የነበረውን ግንኙነት ለማሻሻል እየፈለገች መሆኗን ሊጠቁም እንደሚችል ተነግሯል፡፡ ጃፓን ከወረርሽኙ በፊት ከቪዛ ነፃ ከሚገቡት ሶስት ሀገራት አንዷ ነበረች፡፡ የጃፓን የካቢኔ ፀሃፊ ዮሺማሳ ሃያሺ እንደገና እንዲጀመር መንግሥታቸው በተደጋጋሚ ሲወተውት እንደነበረ ገልጸዋል፡፡ ቻይና ከቪዛ ነፃ የመግባት ሂደትን በየደረጃው በማስፋፋት የአውሮፓ ሀገራትን ጨምራ በቅርቡ የተማሪዎችና እና የምሁራን ጉብኝቶችን በማሻሻል የህዝብ ለህዝብ ልውውጥ ላይ ትኩረት አድርጋለች። ታይላንድ እና ሌሎች ሀገራት ቱሪዝምን ለማበረታታት ለቻይና ተጓዦች ከቪዛ ነጻ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ አድርገዋል፡፡ በዚህ ዓመት ከሀምሌ እስከ መስከረም በነበሩት ሦስት ወራት 8፡2 ሚሊዮን የውጭ ዜጎች ቻይና የገቡ ሲሆን 4፡9 ሚሊዮን የሚሆኑት ከቪዛ ነጻ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባው አመልክቷል፡፡ Read more