Ethiopia



ከመንገድ ዳር ዛፎቹ ጋር በፍቅር የወደቀው በጎ ፈቃደኛ

ዋለልኝ መኮንን ይባላል። ተወልዶ ያደገው ድሬዳዋ ከዚራ ሰፈር ነው። ቀድሞ በዛፎች ይታወቅ የነበረው የከተማዋ መሃል አካባቢ ገላጣ መኾን የፈጠረበት ቁጭት አካ

በኮሬ ዞን ከ60 በላይ መምህራን ከደሞዝ መቆረጥ ጋራ በተያያዘ መታሰራቸው ተገለጸ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ ከፍላጎታቸው ውጪ ደሞዝ መቆረጡን በመቃወም ሥራ የማቆም አድማ ያደረጉ 66 መምህራን መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸውና መ
የአሜሪካ ድምፅ

በኮሬ ዞን ከ60 በላይ መምህራን ከደሞዝ መቆረጥ ጋራ በተያያዘ መታሰራቸው ተገለጸ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ ከፍላጎታቸው ውጪ ደሞዝ መቆረጡን በመቃወም ሥራ የማቆም አድማ ያደረጉ 66 መምህራን መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸውና መምህራን ተናገሩ። የሳርማሌ ወረዳ አስተዳደር፣መምህራንን በማሳመፅ ተጠርጥረው የታሰሩ መኖራቸውን አረጋግጧል።

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ የደረሰው ርእደ መሬት በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተጽእኖ አስከተለ

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ደጋግሞ የደረሰው ርዕደ መሬት በት/ቤቶች ላይ ጉዳት በማድረሱ ከ600 በላይ ተማሪዎች ዛፍ ጥላ ስር ለመማር መገደዳቸውን የወረዳ
የአሜሪካ ድምፅ

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ የደረሰው ርእደ መሬት በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተጽእኖ አስከተለ

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ደጋግሞ የደረሰው ርዕደ መሬት በት/ቤቶች ላይ ጉዳት በማድረሱ ከ600 በላይ ተማሪዎች ዛፍ ጥላ ስር ለመማር መገደዳቸውን የወረዳው የትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ በርዕደ መሬቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ት/ቤቶች ውስጥ በዋናነት በሚጠቀሱት የሳቡሬ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የደረሰው ቁሳዊ ጉዳት የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተጽእኖ ከማሳደሩ ባሻገር በመቶዎች ለሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጥ ምክንያት መሆኑን ገልጿል፡፡ /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

የኢትዮጵያ መንግሥት 582 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ተጨማሪ የበጀት ጥያቄ አቅርቧል

የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ በመንግሥት የቀረበውን ተጨማሪ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ፣ ከዓለም የገንዘብ
የአሜሪካ ድምፅ

የኢትዮጵያ መንግሥት 582 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ተጨማሪ የበጀት ጥያቄ አቅርቧል

የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ በመንግሥት የቀረበውን ተጨማሪ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ፣ ከዓለም የገንዘብ ተቋማትና ከሌሎችም ምንጮች ከሚገኘው ገንዘብ ውስጥ ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ የበጀት ጥያቄ እንደሚቀርብ የገንዘብ ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወሳል፡፡ መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ተከትሎ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ተጨማሪ በጀት በመመደብ የሚወስዳቸው ርምጃዎች የሚኖራቸውን ተፅዕኖ በአሉታዊና አዎንታዊነት የሚመለከቱ ባለሞያዎች አሉ። የአሁኑ ተጨማሪ በጀት ስለሚኖረው ተፅዕኖ የማክሮ ኢኮኖሚ ባለሞያው ዶ/ር ቴዎድሮስ መኮንን፣ አዲሱ የበጀት ጭማሪ የውጭ ገቢዎች ላይ የተመሰረተ በመኾኑ በዋጋ ንረት ላይ የጎላ ተፅዕኖ እንደማይኖረው ያብራራሉ፡፡ /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/  

በዶናልድ ትረምፕ ድጋሚ መመረጥ የምሁራን እይታ

የዶናልድ ትረምፕ  በድጋሚ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ኾነው መመረጣቸው እንዳስገረማቸው በርካታ የውጭ ሀገር ምሁራን  ተናገሩ። «የአሜሪካ መራጮችንና ትልቅ ቦታ
የአሜሪካ ድምፅ

በዶናልድ ትረምፕ ድጋሚ መመረጥ የምሁራን እይታ

የዶናልድ ትረምፕ  በድጋሚ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ኾነው መመረጣቸው እንዳስገረማቸው በርካታ የውጭ ሀገር ምሁራን  ተናገሩ። «የአሜሪካ መራጮችንና ትልቅ ቦታ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች  በውል አልተረዳንም  ነበር» የሚል ስሜት እንዲሰማቸው  ማድረጉንም አመልክተዋል። ተመራጩ ፕሬዝደንት በሚቀጥለው አስተዳደራቸው ምን ዓይነት የውጭ ፖሊሲ እንደሚከተሉ እስካሁን በብዛት በግልጽ ባይታወቅም ጉዳዩን የሚከታተሉ አንድ ኢትዮጵያዊ ተንታኝ ተመራጩ ፕሬዝደንት  ከተለመደው ወጣ ያለውን የውጭ ፖሊሲ አካሄዳቸውን «አሁንም ይቀጥላሉ» ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል ። ትረምፕ የዓለም አቀፍ ፖለቲካ አካሄዳቸው  በሁለትዮሽ ግንኙነቶች  ላይ የተመሰረተ እንደሚኾን የገለጹ ተንታኞች  በተለይም የአፍሪካ ቀንድን በሚመለከት የሚከተሉት መንገድ የአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅምን በማስጠበቅ ላይ የተቃኘ  እንደሚሆን  ይናገራሉ፡፡ የሐዋሳው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዴዎስ እና የቪኦኤ ዋይት ሃውስ ዘጋቢ ፖትሲ ውዳኩስዋራን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

ቻይና ኢኮኖሚዋን ለማነቃቃት መግቢያ ቪዛ የማያስፈልጋቸው ሀገሮችን ቁጥር ልታሳድግ ነው

ቻይና የቱሪዝም እና የንግድ ተጓዦችን ቁጥር በማሳደግ የተቀዛቀዘውን ኢኮኖሚዋን ለማነቃቃት ለዘጠኝ ተጨማሪ ሀገራት ዜጎች ካለቪዛ እንዲገቡ ልትፈቅድ መሆኗን
የአሜሪካ ድምፅ

ቻይና ኢኮኖሚዋን ለማነቃቃት መግቢያ ቪዛ የማያስፈልጋቸው ሀገሮችን ቁጥር ልታሳድግ ነው

ቻይና የቱሪዝም እና የንግድ ተጓዦችን ቁጥር በማሳደግ የተቀዛቀዘውን ኢኮኖሚዋን ለማነቃቃት ለዘጠኝ ተጨማሪ ሀገራት ዜጎች ካለቪዛ እንዲገቡ ልትፈቅድ መሆኗን  አስታወቀች፡፡ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን ዛሬ ዓርብ እንዳስታወቁት እአአ ከህዳር 30 ጀምሮ ከቡልጋሪያ፣ ሮማኒያ፣ ማልታ፣ ክሮኤሺያ፣ ሞንቴኔግሮ፣ ሰሜን መቄዶኒያ፣ ኢስቶኒያ፣ ላቲቪያ እና ጃፓን ተጓዦች ለሠላሳ ቀናት ቆይታ ያለ ቪዛ  ሊገቡ ይችላሉ። ይህ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ያለቪዛ መግባት የተፈቀደላቸውን ሀገራት ቁጥር ወደ 38 ያሳድገዋል። ከዚህ ቀደም ከቪዛ ነጻ ፈቃድ የነበራቸው ሦስት ሀገራት ብቻ ሲሆኑ የእነሱም ፈቃድ  በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ተሰርዞ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ የጃፓን ከቪዛ ነጻ ሀገራቱ ውስጥ መጨመር፣ ቻይና በታይዋን ጉዳይ ከቶኪዮ በተደረጉ ጠንከር ያሉ ንግግሮች የተነሳ  ሻክሮ የነበረውን ግንኙነት ለማሻሻል እየፈለገች መሆኗን ሊጠቁም እንደሚችል ተነግሯል፡፡ ጃፓን ከወረርሽኙ  በፊት ከቪዛ ነፃ ከሚገቡት ሶስት ሀገራት አንዷ ነበረች፡፡  የጃፓን የካቢኔ ፀሃፊ ዮሺማሳ ሃያሺ እንደገና እንዲጀመር መንግሥታቸው  በተደጋጋሚ ሲወተውት እንደነበረ ገልጸዋል፡፡ ቻይና ከቪዛ ነፃ የመግባት ሂደትን በየደረጃው በማስፋፋት የአውሮፓ ሀገራትን ጨምራ በቅርቡ የተማሪዎችና እና የምሁራን ጉብኝቶችን በማሻሻል የህዝብ ለህዝብ ልውውጥ ላይ ትኩረት አድርጋለች። ታይላንድ እና ሌሎች ሀገራት ቱሪዝምን ለማበረታታት ለቻይና ተጓዦች ከቪዛ ነጻ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ አድርገዋል፡፡ በዚህ ዓመት ከሀምሌ እስከ መስከረም በነበሩት ሦስት ወራት  8፡2 ሚሊዮን የውጭ ዜጎች ቻይና የገቡ ሲሆን  4፡9 ሚሊዮን የሚሆኑት ከቪዛ ነጻ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባው አመልክቷል፡፡

የመካከለኛው ምሥራቅ የባይደን ልዩ መልዕክተኛ ግጭቶቹን ለማብቃት በተያዘው ድርድር  ‘ተሥፋ አለኝ’ አሉ

በመካከለኛው ምስራቅ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ልዩ መልዕክተኛ በትላንትናው ዕለት ሲናገሩ ምንም እንኳን በእስራኤል ሰሜናዊ ድንበር እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ቢ
የአሜሪካ ድምፅ

የመካከለኛው ምሥራቅ የባይደን ልዩ መልዕክተኛ ግጭቶቹን ለማብቃት በተያዘው ድርድር  ‘ተሥፋ አለኝ’ አሉ

በመካከለኛው ምስራቅ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ልዩ መልዕክተኛ በትላንትናው ዕለት ሲናገሩ ምንም እንኳን በእስራኤል ሰሜናዊ ድንበር እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ቢቀጥል እና የጋዛው ጦርነት ፍጻሜ ባይታይም፤ ግጭቱን ለማስቆም ከሄዝቦላህ ጋር የሚደረገውን ድርድር አስመልክቶ ያላቸውን ተስፋ ገልጠዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የዩናይትድ ስቴትስ እንደራሴዎች ምክር ቤት ትላንት ማምሻው ላይ በወሰደው ርምጃ ወደ እስራኤል ሊላክ የነበረ የተወሰነ መጠን ያለው ጦር መሳሪያ እንዳይላክ አግዷል። ርምጃውን የተቃወሙ ወገኖች በበኩላቸው ውጊያውን ያራዝመዋል ብለዋል።

«ድህነትን መቀነስ የፍልሰት ቀውስን ለማስታገስ ያስችላል» ሲሉ ባለሙያዎች ተናገሩ

በዓለም ለሚታየው የፍልሰት ቀውስ ድህነትና ረሃብ ዋና ምክንያቶች እንደሆኑ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በብራዚል በተካሄደው የቡድን 20 ሃገራት ጉባኤ ጎን የተናገሩ
የአሜሪካ ድምፅ

«ድህነትን መቀነስ የፍልሰት ቀውስን ለማስታገስ ያስችላል» ሲሉ ባለሙያዎች ተናገሩ

በዓለም ለሚታየው የፍልሰት ቀውስ ድህነትና ረሃብ ዋና ምክንያቶች እንደሆኑ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በብራዚል በተካሄደው የቡድን 20 ሃገራት ጉባኤ ጎን የተናገሩት ባለሙያዎች፣ ውጤታማ የሆኑ የማኅበራዊ ደኅንነት መጠበቂያ መንገዶች (ሴፍቲ ኔት) መኖር ሰዎች መኖሪያቸውን ለቀው ለመሰደድ የሚያበቋቸውን መንስሄዎች ለማስቆም ይረዳሉ። የቪኦኤ የስደት ጉዳዮች ዘጋቢ አሊን ቤሮስ ከሪዮ ደ ጃኔሮ የላከችው ዘገባ ነው።

ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት በኔታኒያሁና የሃማስ መሪዎች ላይ የእስር ማዘዣ አወጣ

የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት /ICC/ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትራቸው ዮአቭ ጋላንት እና የሃማስ ባለሥልጣ
የአሜሪካ ድምፅ

ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት በኔታኒያሁና የሃማስ መሪዎች ላይ የእስር ማዘዣ አወጣ

የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት /ICC/ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትራቸው ዮአቭ ጋላንት እና የሃማስ ባለሥልጣናትን በጦር ወንጀሎች እና በሰብአዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች በመክሰስ ዛሬ ሐሙስ የእስር ማዘዣ አውጥቶባቸዋል፡፡ የእስር ማዘዣው የወጣው ለ13 ወራት በዘለቀው የጋዛ ጦርነት በእስራኤል በተፈጸሙ የጦር ወንጀሎች እና እኤአ በጥቅምት 2023 ሀማስ በእስራኤል ላይ ባደረሳቸው የጦር ወንጀሎች እና በሰብዓዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች  ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ኔታንያሁ እና ጋላንት ሆን ብለው የጋዛን ሲቪሎች እንደ ምግብ፣ ውሃ እና መድሀኒት የመሳሰሉ አስፈላጊ አቅርቦቶችን መከልከላቸውን ሲገልጽ የሃማሱን መሪ መሀመድ ዲፍን ደግሞ እኤአ በጥቅምት 2023 በተፈጸመ ግድያ፣ አግቶ መሰወር፣ ማሰቃየት እና የፆታዊ ጥቃት ወንጀሎች ከሷል። ሃማስ ውሳኔውን ነቅፎታል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኒታኒያሁ ፍርድ ቤቱ በእርሳቸው ላይ ያወጣውን የእስር ማዘዣ አውግዘው፣ እስራኤል “የማይረባ እና የሐሰት ድርጊቶችን ስለምትጸየፍ አትቀበለውም” ብለዋል። ውሳኔው ኔታንያሁ እና ሌሎቹም በዓለም አቀፍ  ወንጀል ተፈላጊ ተጠርጣሪዎች ሆነው እንዲገለሉ ስለሚያደርግ ጦርነቱን ለማስቆም እና ለተኩስ አቁም ድርድር የሚደረገውን ጥረት የበለጠ እንደሚያወሳስበው የአሶሲየትድ ፕሬስ ዘገባው አመልክቷል። ይሁን እንጂ እስራኤል እና ዋና አጋሯ ዩናይትድ ስቴትስ የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አባላት ስላልሆኑ እና ሁለቱ የሃማስ ባለስልጣናት ቀደም ሲል በግጭቱ ስለተገደሉ የውሳኔ ተግባራዊ አንድምታ ውስን ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማውገዝ እስራኤል ከሃማስ ራሷን የመከላከል መብቷን እንደሚደግፉ ገለጸዋል። የመብት ተሟጋች ቡድኖች የዓለም አቀፉ  ፍርድ ቤት ውሳኔ በግጭት የተሳተፉትን አካላት በሙሉ ወደተጠያቂነት ለማምጣት ትልቅ ርምጃ ነው ሲሉ አድንቀዋል፡፡

የቀድሞ የትግራይ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታትና  ወደ ኅብረተሰቡ የማዋሐድ ሥራ ዛሬ ተጀመረ

በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ዛሬ በይፍ በተጀመረው፣ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት፣ ወደ ኅብረተሰቡ መልሶ የማዋሐድና የማቋቋም ሥራ 320 የቀድ
የአሜሪካ ድምፅ

የቀድሞ የትግራይ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታትና  ወደ ኅብረተሰቡ የማዋሐድ ሥራ ዛሬ ተጀመረ

በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ዛሬ በይፍ በተጀመረው፣ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት፣ ወደ ኅብረተሰቡ መልሶ የማዋሐድና የማቋቋም ሥራ 320 የቀድሞ ተዋጊዎች ትጥቃቸውን አስረክበው፣ ማሰልጠኛ ተቋማት ገቡ። በማሰልጠኛ ተቋማቱም ስድስት ቀናትን በሥልጠና እንደሚያሳልፉ፣ በዛሬው ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የብሔራዊ ተሐድሶ ኮምሽን ምክትል ኮምሽነር ብርጋዴር ጀነራል ደርቤ መኩሪያ ተናግረዋል።  

መርካቶ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው እየተመለሰ ነው

በኢትዮጵያ ትልቁ በሆነው በመርካቶ ገበያ በተለይ ከሰኞ ጀምሮ ሲተገበር የነበረው ሱቅ የመዝጋት አድማ ዛሬ በአብዛኛው ቆሟል፡፡ የቪኦኤ ዘጋቢ ወደገበያ ስፍራ
የአሜሪካ ድምፅ

መርካቶ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው እየተመለሰ ነው

በኢትዮጵያ ትልቁ በሆነው በመርካቶ ገበያ በተለይ ከሰኞ ጀምሮ ሲተገበር የነበረው ሱቅ የመዝጋት አድማ ዛሬ በአብዛኛው ቆሟል፡፡ የቪኦኤ ዘጋቢ ወደገበያ ስፍራው ተጉዞ ባደረገው ቅኝት  እንደተመለከተው፣ ሱቆች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተከፍተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለሥልጣናት፣ ችግሩን ለመቅረፍ ከመርካቶ ነጋዴዎች ጋራ ከትላንት በስትያ ውይይት አድርገዋል፡፡ ሆኖም ዛሬ ሱቆች የተከፈቱ ቢሆኑም፣ ብዙም ግብይት አይስተዋልም፡፡ ለዚህም ምክንያቱ፣ ሸማቾችም ወደ ገበያው ብዙም ጎራ አለማለታቸው እንደሆነ አስተያየታቸውን የሰጡ ነጋዴዎች ተናግረዋል፡፡

በዐዲሱ የሶማሊያ ተልዕኮ የሚካተቱ ሀገራት ገና እንዳልተለዩ  አፍሪካ ኅብረት አስታወቀ

በመጭው ጥር ወር በሚሰማራው የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍና የማረጋጋት ተልዕኮ በሶማሊያ፣ በምህጻሩ ኤዩሶም የሚካተቱ አገራት የትኛዎቹ እንደሆኑ ገና አለመወሰኑ
የአሜሪካ ድምፅ

በዐዲሱ የሶማሊያ ተልዕኮ የሚካተቱ ሀገራት ገና እንዳልተለዩ  አፍሪካ ኅብረት አስታወቀ

በመጭው ጥር ወር በሚሰማራው የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍና የማረጋጋት ተልዕኮ በሶማሊያ፣ በምህጻሩ ኤዩሶም የሚካተቱ አገራት የትኛዎቹ እንደሆኑ ገና አለመወሰኑን ኅብረቱ አስታወቀ። የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ ፣ ትላንት ኅዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፣ በተልዕኮው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸውን ሀገራት ጥያቄ በመቀበል ሂደት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ኮሚሽነሩ፣ ካለፈው ሰኞ ኅዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተከበረ ያለውን አራተኛውን የአፍሪካ ኅብረት የድህረ ግጭት መልሶ ግንባታና ልማት ሳምንት አስመልክተው ከጋዜጠኞች ጋራ ባደረጉት ቆይታ ላይ የተገኘው እስክንድር ፍሬው ተከታዩን ልኳል።

ትረምፕ ለጠቅላይ ዐቃቤ ህግነት ያጯቸው ማት ጌትስ ራሳቸውን አገለሉ

በተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለጠቅላይ አቃቤ ህግነት የታጩት ሪፐብሊካኑ የቀድሞ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ማት ጌትስ ራሳቸውን ከ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ ለጠቅላይ ዐቃቤ ህግነት ያጯቸው ማት ጌትስ ራሳቸውን አገለሉ

በተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለጠቅላይ አቃቤ ህግነት የታጩት ሪፐብሊካኑ የቀድሞ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ማት ጌትስ ራሳቸውን ከእጩነቱ አገለሉ፡፡ ጌትስ ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ ኤክስ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ “ትላንት ከህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት ጋር ጥሩ ስብሰባዎችን አድርጌ ነበር። ለሰጡኝ መልካም አስተያየትና ብዙዎች ላሳዩኝ ድጋፍ አደንቃለሁ፡፡ ወቅቱ ከባድ የነበረ ቢሆንም የኔ ለቦታው መታጨት የፕሬዚዳንት ትረምፕ እና ቫንስ ሽግግርን ወሳኝ የሥራ ትኩረት የሚከፋፍል እየሆነ መምጣቱ ግልጽ ነው” ብለዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የሥነ ምግባር ኮሚቴ ትላንት ረቡዕ ተሰብስቦ እሳቸውን በሚመለከት እያጠናቀቀ ያለውን የምርምራ ሪፖርት ይፋ በማድረግ ላይ ሊስማማ አልቻለም፡፡ ጌትስ እኤአ ጥር 20  2025  ሥራውን በሚጀምረው አዲሱ አስተዳደር የሀገሪቱ ከፍተኛ የህግ አስከባሪ ባለስልጣን ለመሆን በትረምፕ ከመመረጣቸው በፊት ከጾታዊ ምግባረ ብልሹነት እና ሱስ አስያዥ እፅ በድብቅ ከመጠቀም ጋር የተያያዘ ክስ ቀርቦባቸዋል። ሁለት የዜና ማሰራጫዎች፣ ኤቢሲ ኒውስ እና ዋሽንግተን ፖስት፣ ጌትስ በኮሚቴው ፊት ለቀረቡ ሁለት ሴቶች እኤአ ከሀምሌ 2017 እስከ ጥር 2019 መጨረሻ በድምሩ ከ10,000 ዶላር በላይ መክፈላቸውን የሚያሳዩ ሰነዶችን የምክር ቤቱ ኮሚቴ ማግኘቱን ዘግበዋል። የ42 ዓመቱ ጌትስ  ለምክር ቤቱ አባልነት ለአምስተኛ ጊዜ የተመረጡ ቢሆንም በትረምፕ ለዐቃቤ ህግነት መታጨታቸውን ከሰሙ በኋላ ከምክር ቤት አባልነታቸው መልቀቃቸው ይታወቃል፡፡

VOA60 World - Gaetz withdraws name as Trump’s attorney general nominee

Republican former Congressman Matt Gaetz faced a House ethics investigation and media reports on allegations of sexual misconduct and illicit drug use, all of which Gaetz has denied.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Gaetz withdraws name as Trump’s attorney general nominee

Republican former Congressman Matt Gaetz faced a House ethics investigation and media reports on allegations of sexual misconduct and illicit drug use, all of which Gaetz has denied.

«ሩሲያ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉር አቋራጭ ሚሳይል ተኩሳብናለች» - ዩክሬን

ሩሲያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2022 ወረራ ከከፈተች ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉር አቋራጭ የባለስቲክ ሚሳይል እንደተኮሰችባት ዩክሬን ዛሬ ሐሙስ አስታወቀች
የአሜሪካ ድምፅ

«ሩሲያ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉር አቋራጭ ሚሳይል ተኩሳብናለች» - ዩክሬን

ሩሲያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2022 ወረራ ከከፈተች ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉር አቋራጭ የባለስቲክ ሚሳይል እንደተኮሰችባት ዩክሬን ዛሬ ሐሙስ አስታወቀች፡፡ የዩክሬን የአየር ሃይል ከድምጽ በአምስት እጥፍ ይፈጥናል የተባለውን “ሃይፐርሶኒክ ሚሳይል እና ሰባት ክሩዝ ሚሳይሎችን ያካተተው መጠነ ሰፊ የሚሳይል ጥቃት የተተኮሰው ከሩሲያ አስትራካን ክልል ነው” ብሏል፡፡ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮኖች) እና መድፎች የካተተው የሚሳይል ጥቃቱ የኢንዱስትሪ ስፍራዎችን ጨምሮ ዩክሬን ያሉ የተለያዩ ይዞታዎች ላይ ያነጣጠረ እንደነበረ ተነግሯል፡፡ የዩክሬን ባለሥልጣናት በሩሲያ የአየር ጥቃት በዲኒፕሮ ፔትሮቭስክ ክልል በሚገኝ የኢንዱስትሪ አካባቢ ከባድ ጉዳት መድረሱን ዛሬ ሐሙስ ተናግረዋል። ሩሲያ ስለ ዩክሬን መግለጫ ወዲያኑ አስተያየት አልሰጠችም፡፡ ኒውክሊየር ጦር ቦምብ መሸከም የሚችለው የሩሲያ አህጉር አቋራጩ የረዥም ርቀት ሚሳይል (ICBM) የተተኮሰው ዩናይትድ ስቴትስ እና ብሪታንያ ዩክሬን ሩሲያ ድንበር ውስጥ ዘልቃ ዒላማዎችን ለማጥቃት የረጅም ርቀት ሚሳይሎቻቸውን እንድትጠቀም ከፈቀዱ ከቀናት በኋላ ነው። ዩናይትድ ስቴትስ የዩክሬን ወታደሮች እየገፋ የመጣውን የሩሲያ እግረኛ ሠራዊት መክተው ለመመለስ እንዲችሉ ለመርዳት የሚቀበሩ ፈንጂዎችን ለመላክ ማቀዷን የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስተን ትላንት ረቡዕ አስታውቀዋል፡፡ ሥልጣናቸው ሊያበቃ የሁለት ወር ጊዜ የቀራቸው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የቀደመውን አቋማቸውን ቀይረው ዩክሬን ዋሽንግተን የተሰጠቻትን የረዥም ርቀት ሚሳይሎችን ተጠቅማ ወደሩሲያ ግዛት ዘልቃ እንድታጠቃ የፈቀዱ ሲሆን ይሄኛው ውሳኔ በቅርብ ቀናት ውስጥ ሁለተኛው የአሜሪካ ፖሊሲ ለውጥ መሆኑ ተመልክቷል።

አሜሪካ የተመድ የጋዛ ተኩስ አቁም ውሳኔን ውድቅ አደረገች

ዩናይትድ ስቴትስ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት በጋዛ ቋሚ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ታጋቾች እንዲለቀቁ በመጠየቅ ትላንት ረቡዕ ያሳለፈው ውሳ
የአሜሪካ ድምፅ

አሜሪካ የተመድ የጋዛ ተኩስ አቁም ውሳኔን ውድቅ አደረገች

ዩናይትድ ስቴትስ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት በጋዛ ቋሚ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ታጋቾች እንዲለቀቁ በመጠየቅ ትላንት ረቡዕ ያሳለፈው ውሳኔ የተገለጸበት ቋንቋ “ለሀማስ የተሳሳተ መልዕክት ያስተላልፋል” በሚል ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷን በመጠቀም ውድቅ አደርጋዋለች፡፡ በመንግሥታቱ ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል አምባሳደር ሮበርት ዉድ “የተኩስ አቁምን ከታጋቾች መለቀቅ ጋር ማገናኘት ለዘላቂ ሰላም አስፈላጊ ነው” ሲሉ የፍልስጤም መልዕክተኛን ጨምሮ ተቺዎች ግን አሜሪካ የውሳኔ ሃሳቡን ውድቅ ማድረጓ   ጦርነትን ትደግፋለች ማለት ነው ሲሉ ከሰዋል። አምባሳደር ሮበርት ውድ ድምጽ ከተሰጠ በኋላ በሰጡት ቃል «ዩናይትድ ስቴትስ ይህ ውጤት እንዳይመጣ ለማድረግ ለሳምንታት በቅን ልቦና ሠርታለች» ብለዋል፡፡ አምባሳደሩ አክለውም “በድርድሩ ጊዜ ሁሉ ግልፅ አድርገናል፣ ታጋቾቹ ሳይለቀቁ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የተጠየቀውን የተኩስ አቁም መደገፍ አልቻልንም፣ ምክንያቱም ይህ ምክር ቤት ቀደም ሲል ባደረገው ጥሪ መሠረት ፣ የጦርነቱ በዘላቂነት ማብቃት ከታጋቾቹ መፈታት ጋር አብሮ መምጣት አለበት። እነዚህ ሁለት አስቸኳይ ግቦች የማይነጣጠሉ ናቸው” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስን አቋም ግልጽ አድርገዋል፡፡ በተመረጡ 10 የፀጥታው ምክር ቤት አባላት የቀረበውና ውድቅ የተደረገው የውሳኔ ሃሳብ፣ አስቸኳይ የተኩስ አቁም በሁሉም ወገኖች እንዲከበር እና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ታጋቾች እንዲፈቱ የሚጠይቅ ነው፡፡ በእስራኤል ዘንድ ግን አሸባሪዎችን እንዳይቀጡ የሚያደርግ ውሳኔ ተደርጎ ተወስዷል። ለ14 ወራት በዘለቀው የእስራኤል እና የሃማስ ግጭት አሜሪካ ጋዛን በተመለከተ የወሰደችው ይህ አቋም አራተኛው ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጦርነቱን ማስቆም ባለመቻሉ ዓለም አቀፍ ቁጣ እየጨመረ መሆኑ ተነግሯል፡፡ የፍልስጤም ምክትል አምባሳደር ማጅድ ባሚያ ለምክር ቤቱ ባሰሙት ንግግር «ረቂቅ ውሳኔ የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ የተደረገ ሙከራ እንጂ አደገኛ መልዕክት የሚያስተላልፍ አይደለም» ብለዋል፡፡ አስከትለውም "ይልቁኑ አደገኛው እስራኤል እናንተ ራሳችሁ በምትቃወሙት እቅዷ መግፋት እንደምትችል መልዕክት የሚያስተላልፈው ይህ ድምጽን በድምጽ የመሻር ርምጃ ነው፡፡ የምናስተላልፋቸው መልዕክቶች ትርጉም አላቸው፡፡ ይሄኛው በመጥፎ ጊዜ የተላለፈ መጥፎ መልዕክት ነው፡፡እስራኤል ለገደለቻቸው ፍልስጤም ሲቪሎች ተጠያቂ ነች። ከዚህ ኃላፊነት ነጻ መሆን አይቻልም›› ብለዋል። ይህ በእንዲህ አንዳለ የዩናይትድ ስቴትስ ልዑክ አሞስ ሆችስቴይን ዛሬ ሐሙስ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋራ እንደሚገናኙ ይጠበቃል። ሆችስቴይን በዚህ ሳምንት የሄዝቦላ ታጣቂዎች አጋር ናቸው የሚባሉትን የፓርላማ አፈ-ጉባዔ ናቢህ ቤሪን ጨምሮ ከሊባኖስ ባለሥልጣናት ጋራ ገንቢ በሆኑ ንግግሮች፣ መሻሻሎች መታየታቸውን ገልጸዋል፡፡

ኬንያ ከሕንዳዊው ባለጸጋ ጋራ የገባችውን የአውሮፕላን ማረፊያና የኃይል ስምምነት ሰረዘች

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ሀገራቸው ከህንዳዊው ባለጸጋ ጋውታም አዳኒ ጋራ የገባችውን ብዙ ሚሊዮን ዶላሮች የሚፈጅ የአውሮፕላን ማረፊያ ማስፋፊያ እና የ
የአሜሪካ ድምፅ

ኬንያ ከሕንዳዊው ባለጸጋ ጋራ የገባችውን የአውሮፕላን ማረፊያና የኃይል ስምምነት ሰረዘች

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ሀገራቸው ከህንዳዊው ባለጸጋ ጋውታም አዳኒ ጋራ የገባችውን ብዙ ሚሊዮን ዶላሮች የሚፈጅ የአውሮፕላን ማረፊያ ማስፋፊያ እና የሃይል ምንጭ ግንባታ ስምምነቶችን መሰረዛቸውን ዛሬ ሐሙስ አስታወቁ። ሩቶ ይህን ያስታወቁት ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው ሳምንት በእስያ ከሚገኙት ባለጸጎች በአንዱ ላይ የጉቦ እና የማጭበርበር ክስ መመስረቷን ካስታወቀች በኋላ ነው፡፡ ፕሬዝዳንቱ ውሳኔው የተላለፈው “በእኛ የምርመራ ተቋማት እና አጋር ሀገራት በቀረበው አዲስ መረጃ ላይ ተመስርቶ ነው” ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ  ዩናይትድ ስቴትስን ለይተው አልገለጹም፡፡ የአዳኒ ቡድን በዋና ከተማዋ ናይሮቢ የሚገኘውን የኬንያ ዋና አውሮፕላን ማረፊያ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት በመፈራረም ሂደት ላይ ሲሆን፣ በስምምነቱ መሠረት ተጨማሪ ማኮብኮቢያ እና መናኻሪያ በመገንባት በምትኩ ለ30 ዓመታት አየር መንገዱን የማስተዳደር ሥራ እንዲወስድ የታሰበ  ስምምነት ነው፡፡ ብዙ የተተቸው ስምምነት በኬንያ ጸረ-አዳኒ ተቃውሞን የቀሰቀሰ ሲሆን «የሥራ ሁኔታ ማሽቆልቆል እና አንዳንድ ቦታዎችም ላይ ከሥራ መፈናቀልን ያመጣል» ያሉ የአውሮፕላን  ማረፊያ ሠራተኞችን የሥራ ማቆም አድማ አስከትሏል፡፡ የአዳኒ ቡድን የምሥራቅ አፍሪካ የንግድ መናኻሪያ በሆነችው ኬንያ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን ለመዘርጋት የሚያስችል ስምምነት አግኝቷል። የኃይል ሚኒስትሩ ኦፒዮ ዋንዴ ለፓርላማው ኮሚቴ በሰጡት ቃል «በኬንያ በኩል ይህንን ስምምነት በመፈረም ሂደት ምንም አይነት የጉቦ ወይም የሙስና አድራጎት አልተፈጸመም» ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ አቃቤ ህግ በዚህ ሳምንት በመሠረተው ክስ አዳኒ ህንድ ውስጥ የሚገነባው  ግዙፍ የጸሐይ ሓይል ፕሮጀክት በጉቦ የተመቻቸ ነው የሚል ውንጀላ የቀረበበት ሲሆን ይህንኑ በግንባታ ፕሮጄክቱ መዋእለ ነዋይ ካፈሰሱ ባለሃብቶች ደብቆ   አጭበርብሯቸዋል  ብሏል፡፡ አዳኒ  የሀሰት የፋይናንስ መረጃዎችን በማቅረብ ለማጭበርበር አሲረዋል ተብለው ተከሰዋል፡፡

VOA60 World - Israeli airstrikes in Gaza kill 15 people

Gaza: Israeli airstrikes killed 15 people, including five children and three women, Wednesday afternoon, according to an AP journalist who counted the bodies taken to Al-Awda and Al-Aqsa Martyrs hospitals in central Gaza.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Israeli airstrikes in Gaza kill 15 people

Gaza: Israeli airstrikes killed 15 people, including five children and three women, Wednesday afternoon, according to an AP journalist who counted the bodies taken to Al-Awda and Al-Aqsa Martyrs hospitals in central Gaza.

የኢትዮጵያን ብዙኀን መገናኛ ዐዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ዐዋጅ ከፍተኛ ትችት ቀረበበት

በርካታ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣ የሲቪክ ተቋማትና የጋዜጠኞች ሞያ ማኅበራት የመገናኛ ብዙኅን ዐዋጅ ማሻሻያ ረቂቁን ተቃወሙ። የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚ
የአሜሪካ ድምፅ

የኢትዮጵያን ብዙኀን መገናኛ ዐዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ዐዋጅ ከፍተኛ ትችት ቀረበበት

በርካታ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣ የሲቪክ ተቋማትና የጋዜጠኞች ሞያ ማኅበራት የመገናኛ ብዙኅን ዐዋጅ ማሻሻያ ረቂቁን ተቃወሙ። የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባዘጋጀው ውይይት ላይ የተገኙ በአብዛኛው ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቋማት ተወካዮች፣ ረቂቁ በነባሩ ዐዋጅ የተደነገጉ የመገናኛ ብዙኅን ነጻነቶችን ወደ ኋላ የሚመልስ መኾኑን ጠቅሰው፣ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።   የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኅን ባለሥልጣን በበኩሉ፣ “ማሻሻያው ነጻነትን የሚገድብ ሳይኾን የሕግ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ያለመ ነው" ሲል ትችቱን ተከላክሏል።

የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሠራተኞች በዘራፊዎች ምክኒያት ሥራ ማቆማቸውን ገለጹ

ባህር ዳር ከተማ ዙሪያ የሚገኘው ጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና ባለሞያዎችና ሠራተኞች በአካባቢው ይገኛሉ ባሏቸው ታጣቂ ዘራፊዎች ይደርስብናል
የአሜሪካ ድምፅ

የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሠራተኞች በዘራፊዎች ምክኒያት ሥራ ማቆማቸውን ገለጹ

ባህር ዳር ከተማ ዙሪያ የሚገኘው ጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና ባለሞያዎችና ሠራተኞች በአካባቢው ይገኛሉ ባሏቸው ታጣቂ ዘራፊዎች ይደርስብናል ባሉት ዘረፋና ምክኒያት ሥራ ማቆማቸውን ገለጹ። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸውና ለደኅንነታቸው ስለሚሰጉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ሁለት የሕክምና ባለሞያዎች፣ በተለያዩ ጊዜያት የታጠቁ ዘራፊዎች ወደ ሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ዘልቀው በመግባት ሠራተኞቹን በሽጉጥ በማስፈራራት ዘረፋ ማካሄዳቸውን ገልጸው ከሰኞ ኅዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ ሥራቸውን እንዳቆሙ ተናግረዋል። ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸውን እንዳንጠቅስና ድምጻቸውን እንድንቀይር የጠየቁን አንድ የሆስፒታሉ የጤና ባለሞያ፣ ከአምስት ወራት ወዲህ በተደጋጋሚ የታጠቁ ድንገተኛ ዘራፊዎች ወደ ሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ በመግባት ዝርፊያ እንደሚፈፅሙ ገልጸዋል። ማክሰኞ ኅዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም. የሆስፒታሉን ዳይሬክተር ጨምሮ ሌሎች አምስት ሐኪሞች ግቢው ውስጥ እንደተዘረፉም ተናግረዋል። የሆስፒታሉ ሠራተኞች ለሚመለከተው አካል ጠንካራ የጸጥታ ኃይል እንዲመደብላቸው በተደጋጋሚ ቢጠይቁም መልስ ማግኘት እንዳልቻሉ ገልጸዋል። ለተሻለ ሕክምና ከምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቸና ወረዳ ታካሚ በበኩላቸው የሕክምና ባለሞያዎቹ አድማ ላይ በመኾናቸው ምክኒያት ፣ ከሰኞ ጀምሮ እስከ ዛሬ አገልግሎት ባለማግኘት እየተጉላሉ መኾኑን በተመሳሳይ የደኅንነት ስጋት ምክኒያት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ ታካሚ ተናግረዋል። የጥበበ ጊዮን አጠቃላይ ሆስፒታል በቀን ወደ 3 ሺሕ ታካሚዎችን እንደሚያስተናግድ የሆስፒታሉ አመራሮች ይገልጻሉ። ከዚህ በተጨማሪ በዩንቨርስቲው በሕክምናና ሳይንስ ኮሌጅ የሚማሩ ተማሪዎችም የተግባር ትምሕርት ይወስዱበታል። በዩንቨርስቲው በሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ የአምስተኛ ዓመት ተማሪ መኾኑን የገለጸልንና በደኅንነት ስጋት ምክንያት ስሙ እንዳይጠቀስ ድምጹም እንዲቀየር የጠየቅ አንድ ተማሪ ከሰኞ ጀምሮ የሕክምና ተማሪዎች የተግባር ትምህርት እየወሰዱ እንዳልሆነ ተናግሯል። “ሆስፒታሉ አጥር የለውም። ጠባቂዎቹም ዱላ ይዘው ነው የሚጠብቁት ሲል ቅሬታውን ያቀረበ አንድ በተመሳሳይ ምክንያት ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የሕክምና ባለሞያ መደበኛ የፀጥታ ኃይል ካልተመደበ በቀር ሥራ መሥራት አስቸጋሪ እንደኾነ ጠቁሟል። በባህር ዳር ዩንቨርስቲ በጥበቃ ሥራ የተሰማራና በደኅንነት ስጋት ምክንያት ስሙ እንዳይጠቀስ ድምጹም አየር ላይ እንዳይውል የገለጸልን ግለሰብ፣ የጠበቃ ሥራ የሚሠሩት ያለጦር መሳሪያ በመኾኑ ችግሮች ሲፈጠሩ ምላሽ መስጠት አለመቻላቸውን ገልጿል። በባህር ዳር ዩንቨርስቲ የጸጥታና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ፣ ኢንስፔክተር ሀብታሙ መለሰ የሆስፒታሉ ሠራተኞች በምሽት በታጠቁ ኃይሎች ዘረፋ እንደሚፈፀምባቸው አረጋግጠዋል። አክለውም፣ በአማራ ክልል ባለፈው ዓመት ከታወጀው አስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጋራ በተያያዘ ከጸጥታ ኃይሉ ውጭ የጦር መሳሪያ መያዝ የሚከለክል ዐዋጅ በመታወጁ የዩንቨርስቲው ጠባቂዎች የጦር መሳሪያ እንደማይዙ ገልጸዋል። በዚኽም ምክኒያት ወደ ግቢው ታጥቆ የሚመጣውን ማንኛውንም ዘራፊ ለመከላከል አዳጋች እንደሚኾንባቸው ተናግረዋል። ችግሩ ለመፍታትም ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋራ እየተነጋገሩ መኾኑን አስረድተዋል። ሆስፒታሉን በበላይነት የሚያስተዳድረው ባህር ዳር ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር መንገሻ አየነ ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው በሆስፒታሉ ውስጥ ዝርፊያ መከሰቱን አምነው ፣ዛሬ ጸጥታና ደህንነቱን ከሚመራው ተቋምና ከኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋራ ተወያይተው ችግሮችን ለመፍታት ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን ገልፀዋል። የጥበበ ጊዮን አጠቃላይ ሆስፒታል በኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ : በቀድሞው የሱማሊያው ፕሬዝዳንት መሀመድ አብድላሂ መሀመድ « ፋርማጆ »በ2010 ዓ.ም የተመረቀ ትልቅ ሆስፒታል ነው

የሰባት ዓመት አዳጊ አግተው ገንዘብ የጠየቁ ሦስት ወጣቶች 11 ዓመት እስር ተፈረደባቸው

በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ወልመራ ወረዳ ሆለታ ከተማ፣ የሰባት ዓመት አዳጊን አግተው በሚሊዮን የሚቆጠር የማስለቀቂያ ቤዛ ጠይቀዋል በሚል ፍርድ ቤት ጥፋ
የአሜሪካ ድምፅ

የሰባት ዓመት አዳጊ አግተው ገንዘብ የጠየቁ ሦስት ወጣቶች 11 ዓመት እስር ተፈረደባቸው

በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ወልመራ ወረዳ ሆለታ ከተማ፣ የሰባት ዓመት አዳጊን አግተው በሚሊዮን የሚቆጠር የማስለቀቂያ ቤዛ ጠይቀዋል በሚል ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ያላቸው ሦስት ወጣቶች፣ 11 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈረደባቸው። የዞኑ ዐቃቤ ሕግና ከፍርደኞቹ የአንደኛው እህት ግለሰቦቹ ጥፋታቸውን በፍርድ ቤት ፊት ማመናቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

ትረምፕ አፍ ለማስያዝ ተከፈለ ከተባለው ገንዘብ ጋር በተያያዘ የተፈረደባቸው ክስ ጉዳይ እጣ ምን ይሆን?

የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከ2016ቱ ምርጫ በፊት ሊጎዳቸው የሚችል መረጃ እንዳይወጣ ለማድረግ ከገንዘብ ወጭ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን አጭበርብረዋል በሚ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ አፍ ለማስያዝ ተከፈለ ከተባለው ገንዘብ ጋር በተያያዘ የተፈረደባቸው ክስ ጉዳይ እጣ ምን ይሆን?

የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከ2016ቱ ምርጫ በፊት ሊጎዳቸው የሚችል መረጃ እንዳይወጣ ለማድረግ ከገንዘብ ወጭ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን አጭበርብረዋል በሚል ተወንጅለው፤ ባለፈው የግንቦት ወር በተካሄደው የክስ ሂደት ቁጥራቸው 34 በሚደርሱ ከባድ ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል። የቅጣት ውሳኔያቸውም የምርጫው ሂደት እስኪጠናቀቅ ድረስ እንዲዘገይ ተደርጎ ነበር። አሁን እርሳቸው ተመራጭ ፕሬዚዳንት በመሆናቸው፤ የክስ ጉዳዮቹን በተመለከተ የሚቀጥለው ምን እንደሆን ግልጽ አይደለም። ቲና ትሪን ያደረሰችንን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ኢራን ዓለም አቀፍ ግፊቶችን ችላ በማለት የኒውክሊየር መርሃ ግብሯን ገፍታበታለች

ኢራን የኒውክሊየር መርሃ ግብሯን እንድትገታ የቀረቡላትን ዓለም አቀፍ ጥያቄዎች ወደ ጎን በመተው የዩሬኒየም ክምችቷን ለጦር መሣሪያ ማምረቻ ወደተቃረበ ደረጃ
የአሜሪካ ድምፅ

ኢራን ዓለም አቀፍ ግፊቶችን ችላ በማለት የኒውክሊየር መርሃ ግብሯን ገፍታበታለች

ኢራን የኒውክሊየር መርሃ ግብሯን እንድትገታ የቀረቡላትን ዓለም አቀፍ ጥያቄዎች ወደ ጎን በመተው የዩሬኒየም ክምችቷን ለጦር መሣሪያ ማምረቻ ወደተቃረበ ደረጃ እያሳደገች ነው ሲል የተባበሩት መንግሥታት የኒውክሊየር ተቆጣጣሪ ተቋም ሚስጥራዊ ዘገባ አመለከተ፡፡ ትላንት ማክሰኞ አሶሲየትድ ፕሬስ ያገኘው የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ተቆጣጣሪ  ተቋም ዘገባ፣ ኢራን የዩሬኒየም ክምችቷን ወደ 60 ከመቶ ከፍ ማድረጓን አመልክቷል፡፡ ዘገባው እንዳመለከተው እ.ኤ.አ ጥቅምት 26 ኢራን 182.3 ኪሎ ግራም ዩሬኒየም ክምችት የነበራት ሲሆን  በነሀሴ ወር ከወጣው ሪፖርት ወዲህ የ17.6 ኪሎ ግራም  ጭማሪ አሳይቷል። የዩራኒየም መጠኑ ክምችት 60 ከመቶ ደረሰ ማለት ወደ ሙሉ የኒውክሌር ጦር መሳሪያነት ለመቀየር ያስፈልጋል ለተባለው የ90 ከመቶ መስፈርት ጥቂት የሚቀረው መሆኑ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡ ኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብሯ ለጦር መሣሪያነት ሳይሆን ለልማት ዓላማ የሚውል መሆኑን ትናገራለች፡፡ የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኅይል ቁጥጥር  ተቋም ግን መርሃ ግብሩ በድብቅ ለጦር መሣሪያ ማምረቻ እንደማይውል ዋስትና እንደማይሰጥ አስጠንቅቋል። ሪፖርቶቹ በቅርብ ወራት ውስጥ እስራኤል እና ኢራን በቅርቡ የሚሳይል ጥቃትን የተለዋወጡ ሲሆን ከአንድ አመት በላይ በዘለቀው የጋዛ ጦርነት እስራኤል እና በኢራን የሚደገፈው ሃማስ ውጊያ ወሳኝ ደረጃ መድረሱን አመልክተዋል፡፡ ምንም እንኳ ኢራን ከዓለም ኃያላን ሀገራት ጋር የገባችው የኒውክሊየር ስምምነት እልባት ያላገኘ ቢሆንም የፕሬዝዳንት ትረምፕ ዳግም መመረጥ የተወሳሰበውን ጉዳይ በምን መልኩ ሊፈታው እንደሚችል ጥያቄ አስነስቷል፡፡ በዩናትይትድ ስቴትስ፣ በእንግሊዝ፣ በፈረንሣይ እና በጀርመን የሚመሩ ምዕራባውያን ሃገራት በቅርቡ በሚካሄደው የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኅይል ተቋም ቦርድ ስብሰባ ላይ ለስምምነቱ አለመሳካት ኢራንን ለመውቀስ አቅደዋል፡፡ ይህም ለተጨማሪ የኒውክሊየር መርሃ ግብሮች መባባስ ስጋት ሊሆን እንደሚችል አስግቷል፡፡

በእስራኤል ጥቃት 17 ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ ጤና ባለሥልጣናት ተናገሩ

በጋዛ ሰርጥ ዛሬ ረቡዕ  እስራኤል በተከታታይ ባደረሰቻቸው ጥቃቶች በትንሹ 17 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን የጋዛ የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል። በአንደኛ
የአሜሪካ ድምፅ

በእስራኤል ጥቃት 17 ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ ጤና ባለሥልጣናት ተናገሩ

በጋዛ ሰርጥ ዛሬ ረቡዕ  እስራኤል በተከታታይ ባደረሰቻቸው ጥቃቶች በትንሹ 17 ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን የጋዛ የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል። በአንደኛው የእስራኤል ጥቃት በሰሜን ጋዛ ጃባሊያ አካባቢ የሚገኝ መኖሪያ ቤት በመመታቱ ቢያንስ 12 ሰዎች ተገድለዋል። በሰሜን ጋዛ ከሃማስ ታጣቂዎች ጋራ በተደረገ ውጊያ ከወታደሮቹ አንዱ መገደሉና አንደኛው መቁሰሉን የእስራኤል ጦር ዛሬ ረቡዕ አስታውቋል። በደቡባዊ ሊባኖስ፣ የእስራኤል ኃይሎች እና የሂዝቦላህ ታጣቂዎች ለተከታታይ ወራት በተባባሰ ውጊያ ላይ ሲኾኑ  የሊባኖስ ጦር ከወታደሮቹ አንዱ በእስራኤል ተኩስ መገደሉን እና የእስራኤል ወታደሮች በሊባኖስ ጦር ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ዛሬ አስታውቋል። የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ረቡዕ፣ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በሊባኖስ የተባበሩት መንግሥታት ተልእኮ አካል የኾኑት የፈረንሳይ ወታደሮች ተተኩሶባቸዋል፡፡ መግለጫው አክሎም “ወታደሮቹ እንደልብ ተዘዋውረው ተልእኮቸውን የመፈጸም ነጻነታቸው ሊጠበቅ እንደሚገባ” አሳስቧል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ልኡክ አሞስ ሆችስቴይን በእስራኤል እና በኢራን በሚደገፈው በሂዝቦላ መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት የሚያቆም የተኩስ አቁም ስምምነት ሊደረስ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ትላንት ማክሰኞ ገልጸዋል፡፡ «ይህን ግጭት ለማቆም ተጨባጭ እድል አለን» ያሉት ሆችስቴይን የሄዝቦላህ ታጣቂዎች አጋር ናቸው የተባሉትን ሸምጋዩን የፓርላማ አፈ-ጉባዔ ናቢህ ቤሪን ጨምሮ፣ ከሊባኖስ ባለስልጣናት ጋር «በጣም ገንቢ ውይይት» አድርገናል ብለዋል። «የሊባኖስ መንግሥት እና ሂዝቦላህ ባለፈው ሳምንት በቀረበው ሀሳብ ተስማምተዋል፣ ሁለቱም በይዘቱ ላይ አንዳንድ አስተያየቶችን ሰጥተዋል» ሲሉ የቤሪ ረዳት የሆኑት አሊ ሀሰን ካሊል ከትላንት በስትያ ሰኞ ለሮይተርስ ተናግረዋል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረስም እስራኤል በሂዝቦላህ ላይ ወታደራዊ ዘመቻዋን እንደምትቀጥል ተናግረዋል። ኔታንያሁ ለእስራኤል ፓርላማ ባደረጉት ንግግር  «ዋናው ነገር  በወረቀት ላይ የሚሰፍረው (ስምምነት) አይደለም» ብለዋል።

የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ወደ ኅብረተሰቡ የማዋሐድ ሥራ ነገ እንደሚጀምር ተገለጸ

ወደ 75 ሺሕ የሚጠጉ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት፣ ወደ ኅብረተሰቡ መልሶ የማዋሐድና የማቋቋም ሥራ ነገ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሀድ
የአሜሪካ ድምፅ

የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ወደ ኅብረተሰቡ የማዋሐድ ሥራ ነገ እንደሚጀምር ተገለጸ

ወደ 75 ሺሕ የሚጠጉ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት፣ ወደ ኅብረተሰቡ መልሶ የማዋሐድና የማቋቋም ሥራ ነገ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን፣ ዛሬ አስታወቀ። በኢትዮጵያ መንግሥት በእና በህወሓት መካከል፣ ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ-ፕሪቶርያ ላይ የተደረገውን ተኩስ የማቆም የሰላም ስምምነት ተከትሎ፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት፣ ወደ ኅብረተሰቡ መልሶ የማዋሐድና በማቋቋም መርሐ ግብር ከሁለት ዓመት መዘግየት በኋላ ነገ እንደሚጀምር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስታውቋል። ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን፣ ዛሬ ኅዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ፣ ለዚህ ሥራ ሲባል በክልሉ የቀድሞ ተዋጊዎችን ተቀብሎ ለማሠልጠን የሚያስችሉ በመቐለ፣ በዕዳጋ ሐሙስና በዓድዋ ከተሞች ሦስት ማዕከላት መከፈታቸውን ተናግረዋል፡፡ ሒደቱም፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን ካሉበት የጦር እዝ በማላቀቅ ወደ ማዕከላት ማሰባሰብ፣ ማሰልጠን፣ ወደ ኅብረተሰቡ መቀላቀልና መልሶ ማቋቋምን እንደሚያካትት ኮሚሽነሩ ገልጸው፣ ይህንንም ነገ፣ ኅዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም መቐለ በሚገኘው የማሰልጠኛ ማዕከል እንደሚጀመር ጠቁመዋል።   ኮሚሽነሩ፣ “በምዕራፍ አንድ የትግበራ መርሐ ግብር ፣ በዚህ ሳምንት ከትግራይ ክልል 75 ሺሕ የቀድሞ ተዋጊዎችን የሚያካትት ሥራ እንጀምራለን፡፡ በዚህ ዙር በአብዛኛው የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሴቶችና በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ትግበራውን እንጀምራለን፡፡” ብለዋል። የቀድሞ ተዋጊዎችን በአራት ወራት ለማቋቋም ከኢትዮጵያ መንግሥት አንድ ቢሊዮን ብር፣ ከዓለም አቀፍ ለጋሾች ደግሞ 60 ሚሊዮን ዶላር በጀት መገኘቱን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡ ወደ መቐለ ማሰልጠኛ ማዕከል የሚገቡት የመጀመሪያዎቹ 320 የቀድሞ ተዋጊዎች፣ ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ እስከ ነገ ሙሉ ቀን የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተገኙበት፣ ትጥቅ የማስረከብ እንደሚያከናውኑም ኮሚሽነሩ አክለው ገልፀዋል። ስለጉዳዩ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርና ከጸጥታው ዘርፍ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡ /የዚህ ዘገባ ዝርዝር በምሽቱ የራዲዮ ፕሮግራም ይቀርባል/  

በዘንድሮው የአሜሪካ ምርጫ የአፍሪካውያን ተቀዳሚ ትኩረት ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ እንደነበረ ተገለጸ

“ዩስ አፍሪካ ኢንስቲትዩት” የተሰኘ ተቋም ከምርጫው በፊት በሠራው የዳሰሳ ጥናት ኢትዮጵያውያን ጨምሮ አፍሪካውያን በዘንድሮው ምርጫ የኢኮኖሚ፣ የስደተኝነት
የአሜሪካ ድምፅ

በዘንድሮው የአሜሪካ ምርጫ የአፍሪካውያን ተቀዳሚ ትኩረት ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ እንደነበረ ተገለጸ

“ዩስ አፍሪካ ኢንስቲትዩት” የተሰኘ ተቋም ከምርጫው በፊት በሠራው የዳሰሳ ጥናት ኢትዮጵያውያን ጨምሮ አፍሪካውያን በዘንድሮው ምርጫ የኢኮኖሚ፣ የስደተኝነትና የጤና ፖሊሲዎች በምርጫው ትኩረት የሰጧቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች እንደነበሩ የተቋሙ ፕሬዘዳንት ዶክተር ታዲዮስ በላይ ተናግረዋል። በዚህ የዳሰሳ ጥናት ከ2ሺሕ በላይ በዩናይትድ ስቴትስ እና በአህጉሪቱ የሚኖሩ አፍሪካውያን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ተብሏል፡፡

በትረምፕ መመረጥ የተበረታቱ አይሁድ ሰፋሪዎች ዌስት ባንክን ወደ ራሳቸው እንደሚቀላቅሉ ተስፋ አድርገዋል

በዌስት ባንክ የሚኖሩ የአይሁድ ሰፋሪዎች ዶናልድ ትረምፕ መመረጣቸውና ማይክ ሃካቢን በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር አድርገው መሾማቸውን በደስታ ተቀብለውታ
የአሜሪካ ድምፅ

በትረምፕ መመረጥ የተበረታቱ አይሁድ ሰፋሪዎች ዌስት ባንክን ወደ ራሳቸው እንደሚቀላቅሉ ተስፋ አድርገዋል

በዌስት ባንክ የሚኖሩ የአይሁድ ሰፋሪዎች ዶናልድ ትረምፕ መመረጣቸውና ማይክ ሃካቢን በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር አድርገው መሾማቸውን በደስታ ተቀብለውታል። ዌስት ባንክን ወደ ራሳቸው ለመቀላቀል እና በጋዛ ውስጥ ሳይቀር የሰፈራ መንደር ለመገንባት ተስፋ እንዳላቸው ይናገራሉ። የቪኦኤ ዘጋቢ ሊንዳ ግራንድስቴን ከዌስት ባክን ከዱሚም የሰፋሪዎች መንደር ያጠናቀረችውን ዘገባ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ም/ቤት ያለመከሰስ መብታቸውን የተነሳው አቶ ሰዒድ አሊ መታሰራቸውን ፖሊስ አስታወቀ

ከኮሪደር ልማት ጋራ በተያያዘ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ ጠዋት ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል አቶ ሰዒድ አሊ፣ ዛሬ ከ
የአሜሪካ ድምፅ

በአዲስ አበባ ም/ቤት ያለመከሰስ መብታቸውን የተነሳው አቶ ሰዒድ አሊ መታሰራቸውን ፖሊስ አስታወቀ

ከኮሪደር ልማት ጋራ በተያያዘ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ ጠዋት ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል አቶ ሰዒድ አሊ፣ ዛሬ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ጀምሮ መታሰራቸውን ፖሊስ አስታወቀ። የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር፣ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ “ግለሰቡ ያለመከሰስ መብታቸው ከተነሳ በኋላ፣ ዛሬ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ ከመኖርያ ቤታቸው በአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው በፖሊስ ኮሚሽኑ ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል ” ብለዋል። አክለውም፣  “ጉዳዩ በምርመራ ላይ ያለ በመኾኑ ዝርዝር ሁኔታውን ከዚኽ በላይ ለመግለጽ እንቸገራለን። የምርመራ  ሥራው ከተጠናቀቀ ለሚዲያም ለሕዝብም እናሳውቃለን” ብለዋል። የአቶ ሰዒድን ያለመከሰስ መብት መነሳት በተመለከተ፣ የምክር ቤቱ የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ለምክር ቤቱ በጹሑፍ ባቀረቡት የውሳኔ ሐሳብ፣ አቶ አቶ ሰዒድ አሊ በሙስና ወንጀል በመጠርጠራቸው የወንጀል ምርመራ መዝገብ በዐቃቤ ሕግ ተከፍቶባቸው እንደነበር አስታውቀዋል። በዚኹ በንባብ በቀረበውና በከተማው አስተዳደር መገናኛ ብዙኃን ላይ በተላለፈው የውሳኔ ሐሳብ፣ አቶ ሰኢድ ከማል፣ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በነበሩበት ወቅት የኮሪደር ልማቱን ምክንያት በማድረግ፣ አኹን በእስር ላይ ከሚገኙ አራት የልደታ ክፍለ ከተማ ሠራተኞችና  ከግል ባለሀብት ጋራ በመመሳጠር የመንግሥት ሀብትን ለግል ጥቅም እንዲውል አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው የወንጀል ምርመራ ሲደረግባቸው መቆየቱ ተገልጿል። ፍትሕ ሚኒስቴር በሚኒስትሯ ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ የምክር ቤት አባሉ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ  የጠየቁበትን ደብዳቤ ኮሚቴው በጥልቀት መመልከቱን ሰብሳቢው ለምክር ቤቱ በንባብ አሰምተዋል።  በተጨማሪም ኮሚቴው የወንጀል ምርመራ መዝገቡን ከመረመረና፣ ከዐቃቤ ሕግ ጋራ በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በኋላ፣ የምክር ቤት አባሉን የሕግ ከለላ ለማንሳት የሚያስችል በቂ አመላካች ኹኔታ አለ ብሎ በማመኑ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የውሳኔ ሐሳብ ማቅረቡን ገልጿል።  በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ መሰረትም የምክር ቤት አባሉ ያለመከሰስ መብት ተነስቷል። ከውሳኔው በኋላ የምክር ቤት አባሉን ለማግኘት ጥረት ስናደርግ የቆየን ቢኾንም፣ በኋላ ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከፖሊስ ለማወቅ ችለናል።

በመርካቶ ገበያ ትላንት የተጀመረው ሱቅ የመዝጋት አድማ ዛሬም ቀጥሏል

መንግሥት እያካሄደ ባለው የደረሰኝ ቁጥጥርና ቅጣት ምክንያት፣ ነጋዴዎች ከትላንት ጀምሮ መደብሮቻቸውን በመዝጋት ፣ አድማ ላይ መኾናቸውን የሱቅ ባለንብረቶች
የአሜሪካ ድምፅ

በመርካቶ ገበያ ትላንት የተጀመረው ሱቅ የመዝጋት አድማ ዛሬም ቀጥሏል

መንግሥት እያካሄደ ባለው የደረሰኝ ቁጥጥርና ቅጣት ምክንያት፣ ነጋዴዎች ከትላንት ጀምሮ መደብሮቻቸውን በመዝጋት ፣ አድማ ላይ መኾናቸውን የሱቅ ባለንብረቶች ተናግረዋል። ከአድማው በተጨማሪ ከመጋዘን እቃ የማሸሽ ተግባርም መኖሩን የገለፁት ነጋዴዎቹ፣ በዚህም ምክንያት ገበያ መቀዛቀዙን ገልፀዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ በበኩላቸው፣ “ቁጥጥሩ የተጀመረው በርካታ ሕገ ወጥ አሠራሮች ስላሉ ነው” ሲሉ ዛሬ በተካሔደው የከተማው ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል፡፡

VOA60 America - US envoy says end to Israel-Hezbollah conflict 'within our grasp'

U.S. envoy Amos Hochstein said Tuesday in Lebanon that conclusion to conflict between Israel and Iran-backed Hezbollah “is now within our grasp." The Lebanese government and Hezbollah agreed to a U.S. cease-fire proposal on Monday. There was no immediate co
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - US envoy says end to Israel-Hezbollah conflict 'within our grasp'

U.S. envoy Amos Hochstein said Tuesday in Lebanon that conclusion to conflict between Israel and Iran-backed Hezbollah “is now within our grasp." The Lebanese government and Hezbollah agreed to a U.S. cease-fire proposal on Monday. There was no immediate comment from Israel.

VOA60 World - Russian President Vladimir Putin signs revised nuclear doctrine

Russia: President Vladimir Putin on Tuesday signed a revised nuclear doctrine declaring that a conventional attack on Russia by any nation that is supported by a nuclear power will be considered a joint attack on his country.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Russian President Vladimir Putin signs revised nuclear doctrine

Russia: President Vladimir Putin on Tuesday signed a revised nuclear doctrine declaring that a conventional attack on Russia by any nation that is supported by a nuclear power will be considered a joint attack on his country.

ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬይን የምትሰጠውን ዕርዳታ መጠን ስታደርግ ’ጂ-20’ ቡድን ውስጥ ልዩነቶች እየታዩ ነው

 የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሥልጣን ዘመን ሊያበቃ በቀረው የሁለት ወራት ዕድሜ ውስጥ አስተዳደራቸው ዩክሬይን የሩሲያን ወረራ ለመከላከል ለያዘችው ጥረት የሚሰ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬይን የምትሰጠውን ዕርዳታ መጠን ስታደርግ ’ጂ-20’ ቡድን ውስጥ ልዩነቶች እየታዩ ነው

 የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሥልጣን ዘመን ሊያበቃ በቀረው የሁለት ወራት ዕድሜ ውስጥ አስተዳደራቸው ዩክሬይን የሩሲያን ወረራ ለመከላከል ለያዘችው ጥረት የሚሰጠውን የገንዘብ፣ የወታደራዊ እና የዲፕሎማሲያዊ ድጋፎች አሳድጓል። ሃያ የዓለም ሃገራት የተካተቱበትን የቡድን  20 የመሪዎች ጉባኤ እያስተናገደች ባለችው የብራዚሏ የባሕር ዳርቻ ከተማ ሪዮ ዲ ጄኔሮ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ለዩክሬን የሚሰጠውን ድጋፍ አስመልክቶ “ብርቱ” ግፊት እያደረጉ መሆናቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ደኅንነት ጉዳዮች ምክትል አማካሪ ጃን ፋይነር በትላንትናው ዕለት ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ሩስያ ባለፈው ሳምንት መገባደጂያ በዩክሬይን የፈጸመችውን የአየር ድብደባ ተከትሎ፤ ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች በሞስኮ ላይ ጠንካራ ትችት እንዲሰነዘር ግፊት እያደረጉ ነው። የሰሞኑም የሩስያ የአየር ጥቃት ለወራት ከታዩት ሁሉ ግዙፉ መሆኑ ተመልክቷል። ባለስልጣናቱ አክለውም የሩስያ  ጥቃት ማየል ‘ከአውሮፓ የሚሻገር ያለመረጋጋት ተጽእኖ ሊያስከትል እንደሚችል’ አስጠንቅቀዋል። በሩስያዋ የከርስክ ግዛት የዩክሬን ኃይሎች የተቆጣጠሩትን አካባቢ ለማስለቀቅ   ከ10 ሺሕ ላይ የሚሆኑ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሞስኮ መግባታቸውን ዩናይትድ ስቴትስ እና ዩክሬን በወሩ መጀመሪያ ላይ ማስታወቃቸው ይታወሳል።  ሆኖም የመጨረሻው የመሪዎች መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ ግፊት ያደረገችበትን አገላለጽ አላካተተም። መግለጫው ሩስያ የወሰደችውን እርምጃ ሳያወግዝ፤ ዩክሬን ውስጥ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ በሰው ልጆች ላይ በሚደርሰው ስቃይ እና በአለም አቀፍ ኢኮኖሚ ላይ ባስከተለው አሉታዊ ተፅእኖ ላይ ትኩረት አድርጓል። የመካከለኛውን ጦርነት አስመልክቶም በጋዛ እና በሊባኖስ የተኩስ አቁም እንዲደረስ እና እስራኤል እና ፍልስጤም ነጻ ሃገር ሆነው በሰላም የሚኖሩበት የሁለት-አገሮች መፍትሄ የተባለው ይሳካ ዘንድ የሚያስፈልገውን ቁርጠኝነት ጠይቋል። የእስራኤልን ራስን የመከላከል መብት በተመለከተ ያለው የለም። ፋይነር አክለውም፤ በቡድኑ ከታቀፉት አገሮች ስብጥር አንጻር አለም አቀፍ ግጭቶችን አስመልክቶ ሁሉም የሚስማሙበት ሃሳብ መቅረጽ ቀላል አለመሆኑን አምነዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ለኪቭ የምትሰጠውን ወታደራዊ ዕርዳታ ያሳደገችው ዩናይትድ ስቴትስ፤ ዩክሬን አሜሪካ-ሰራሹን የረዥም ርቀት ሚሳይሎች በሩሲያ ድንበር ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን ለመምታት እንድትጠቀምበት ፍቃድ መስጠቷን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ባለስልጣናትን ጠቅሰው የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ቡድን 20 - ባብዛኛው ተመሳሳይ እይታ የሚጋሩት የሰባቱ የዓለም ባለ ጸጋ ሃገሮች ካሉበት ቡድን 7 በተጨማሪ፤ ሩስያን፣ ቻይናን፤ እንዲሁም በደቡቡ  የዓለም ንፍቀ ክበብ የሚገኙት አንዳንድ በማደግ ላይ ያሉ ሃገራት ያጠቃልላል።

የውጭ ምንዛሪ ልውውጥ የሚያከናውኑት የግል ኩባንያዎች

በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ልውውጥ በገበያ ዋጋ እንዲወሰን የወጣውን ፖሊሲ ተከትሎ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት እየሰፋ መምጣቱን የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ባለሞ
የአሜሪካ ድምፅ

የውጭ ምንዛሪ ልውውጥ የሚያከናውኑት የግል ኩባንያዎች

በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ልውውጥ በገበያ ዋጋ እንዲወሰን የወጣውን ፖሊሲ ተከትሎ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት እየሰፋ መምጣቱን የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ባለሞያዎች ተናግረዋል፡፡ ይኹን እንጂ በጥቁር ገበያውና በመደበኛው የባንክ ምንዛሪ መካከል ያለው ልዩነት ተስፋና ስጋት መፍጠሩንም ባለሞያዎቹ ገልጸዋል፡፡ ከባንኮች በተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ግብይት አገልግሎት እንዲሰማሩ ብሄራዊ ባንክ ፈቃድ ከሰጣቸው አምስት የግል ኩባንያዎች መካከል አንዱ የኾነው የኢትዮ ፎሬክስ አክስዮን ማኅበር መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ ፖሊሲው አዎንታዊ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ የምጣኔ ሀብቱ ባለሞያው አቶ ያሬድ ኃይለመስቀል በበኩላቸው ለውጥ መኖሩን ቢቀበሉም የውጭ ምንዛሬው ዘለቄታዊ በኾነ መንገድ ሊቀረፍ የሚችለው የጥቁር ገበያው ተፈላጊነት እየቀነሰ ሲመጣ፣ ለውጡ በውጭ ንግድ ምርቶች ሲደገፍና ከገቢ ሸቀጦች ጋራ ሲገናዘብ ብቻ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ /ዝርዝሩን ከተያይዘው ፋይል ይከታተሉ/

“ከፊሊፒንስ ጋራ ያለን  አጋርነት ከአስተዳደሮች መለዋወጥም የሚሻገር ነው" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር ተናገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን፣ ቻይና በፊሊፒንስ ላይ የወሰደችውንና ‘አደገኛ’ ያሉትን ድርጊት አውግዘው፤ በአወዛጋቢው የደቡብ ቻይ
የአሜሪካ ድምፅ

“ከፊሊፒንስ ጋራ ያለን  አጋርነት ከአስተዳደሮች መለዋወጥም የሚሻገር ነው" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር ተናገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን፣ ቻይና በፊሊፒንስ ላይ የወሰደችውንና ‘አደገኛ’ ያሉትን ድርጊት አውግዘው፤ በአወዛጋቢው የደቡብ ቻይና ባህር የፊሊፒንስ ኃይሎች ጥቃት ቢደርስባቸው፤ ‘ዩናይትድ ስቴትስ ከሀገራቸው ወታደራዊ የትብብር ስምምነት ያላትን ማኒላን ትከላከላለች’ ሲሉ ቀደም ሲል ያሰሙትን ማስጠንቀቂያ አጽንኦት ሰጥተው ደግመዋል። አዲሱን የ500 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ እገዛ ጨምሮ፣ አገራቸው ለፊሊፒንስ የምትሰጠው ጠንካራ ወታደራዊ ድጋፍ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደርም ይቀጥል እንደሆን፤ በፊሊፒንሷ ፓላዋ ግዛት በሥራ ጉብኝት ላይ ባሉበት ወቅት የተጠየቁት ኦስቲን  የሚቀጥለውን የአስተዳደር እርምጃ መገመት እንደማይችሉ ተናግረዋል። ሆኖም በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ጠንካራ ጥምረት በአገሮቹ ውስጥ የሚደረጉትን “የአስተዳደሮች መለዋወጥ ተሻግሮ ይቀጥላል" የሚለውን እምነታቸውን ገልጸዋል።

በሶማሊላንድ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲው መሪ አሸነፉ

በሶማሊላንድ ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው መሐመድ አብዱላሂ ኢሮ ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ አብዲን ማሸነፋቸውን የምርጫ ኮሚ
የአሜሪካ ድምፅ

በሶማሊላንድ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲው መሪ አሸነፉ

በሶማሊላንድ ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው መሐመድ አብዱላሂ ኢሮ ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ አብዲን ማሸነፋቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ ዛሬ ማክሰኞ አስታወቀ፡፡ ገለልተኛ ታዛቢዎች ምርጫውን «ሰላማዊ »ሲሉ ገልጸውታል፡፡ የብሔራዊ ፓርቲው የዋዳኒ ፕሬዚደንታዊ እጩ አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ (ኢሮ) 63 ነጥብ 92 ከመቶውን የመራጭ ድምጽ ያገኙ ሲሆን ፕሬዚደንት ቢሂ 34 ነጥብ 81 ከመቶ፡ ሦስተኛው እጩ 0 ነጥብ 74 ከመቶውን ማግኘታቸውን የሶማሊላንድ ብሔራዊ የምርጫ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሴ ሀሰን ዩሱፍ ሐርጌሳ ላይ ይፋ አድርገዋል፡፡ የ69 ዓመቱ ኢሮ ለአምስት ዓመት ሶማሊላንድን ሊመሩ እ አ አ ታሕሳስ 13 ቀን ቃለ መሐላ ይፈጽማሉ፡፡ ብሐራዊ የምርጫ ኮሚሽኑ የምርጫውን ውጤት እንዲያጸድቅ ለከፍተኛ ፍርድ ቤቱ እንደሚያቀርበው ተመልክቷል፡፡ የሶማሊላንድ ምርጫ እአአ በ2022 ዓም ሊካሂድ ታቅዶ የነበረ ሲሆን በፖለቲካ ልዩነቶች የተነሳ እስካሁን ዘግይቷል፡፡ እአአ በ2017 በተካሄደው በቀደመው ምርጫ የዋዳኒ ፓርቲውን መሪ አሸንፈው ስልጣን የያዙት ቢሂ የምርጫውን ውጤት አከብራለሁ ብለዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ለተመራጩ ፕሬዚደንት የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክት አስተላልፉል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩ ባወጣው አጭር መግለጫ «ተመራጩ ፕሬዚደንት እና ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ መሐመድ ያሳዩትን ዲሞክራሲያዊ አመራር ኢትዮጵያ ታደንቃለች » ብሏል፡፡ የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሀሰን ሼክ መሐሙድም ለተመራጩ ፕሬዚደንት የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ፕሬዚደንት መሐሙድ ለሶማሊያ ሕዝብ እድገት እና አንድነት ወሳኝ ለሆነው እርቀ ሰላም የሚደረገው ንግግር እንዲጠናቀቅ ቁርጠኛነታቸው ያሳወቁ መሆኑን የሶማሊያ መንግሥት የዜና ማሰራጫ ዘግቧል፡፡ በሶማሊያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲም በበኩሉ ምርጫውን አስመልክቶ ለሶማሊላንድ ሕዝብ እና ለተመራጩ ፕሬዚደንት እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት መልዕክት አስተላልፏል፡፡ ኤምባሲው በኤክስ ገጹ ባወጣው ጽሁፍ «የሶማሊላንድ አስደናቂ የምርጫዎች እና የሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተሞክሮ ለቀጣናው ብቻ ሳይሆን አልፎም አርአያ የሚሆን ነው» ብሏል፡፡

የእግር ጉዞ ማዘውተር ለአንጎል ጤና የሚያስገኘው የላቀ ጠቀሜታ

የእግር ጉዞ፣ የቤት ውስጥ ሥራ አለያም ሌሎች መሰል ቀላል የአካል እንቅስቃሴዎችን አዘውትሮ ማድረግ ለአንጎል ጤና ከፍ ያለ ጥቅም የሚያገኝ መሆኑን በቅርቡ ይፋ
የአሜሪካ ድምፅ

የእግር ጉዞ ማዘውተር ለአንጎል ጤና የሚያስገኘው የላቀ ጠቀሜታ

የእግር ጉዞ፣ የቤት ውስጥ ሥራ አለያም ሌሎች መሰል ቀላል የአካል እንቅስቃሴዎችን አዘውትሮ ማድረግ ለአንጎል ጤና ከፍ ያለ ጥቅም የሚያገኝ መሆኑን በቅርቡ ይፋ የተደረገ አንድ የሳይንሳዊ ምርምር ጽሑፍ አመለከተ። የአንጎልን አሠራር ማቀላጠፍ እና የዓመታት ወጣትነት ማጎናጸፍ መቻሉ ተገልጿል። ሞያዊ ትንታኔውን የሰጡን ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ የነርቭና የአእምሮ ሃኪም፣ እንዲሁም በባሮ የነርቭ ሕክምና ተቋም መምህር እና ተመራማሪ ናቸው። ፕሮፌሰር ዮናስ ካሁን ቀደም ቀላል የአካል እንቅስቃሴዎች ዕድሜያቸው ከሰባ ዓመት በላይ የሆኑ አረጋውያን በተመሳሳይ ቀላል የአካል እንቅስቃሴ በማድረግ ብቻ ከመጃጀት ጋራ ተያይዘው የሚመጡ በሽታዎችን በመከላከል የሚረዱ መሆናቸውን ያረጋገጠ ለከፍተኛ እውቅና የበቃ ሳይንሳዊ የምርምር ሥራ አካሂደዋል። ሞያዊ ትንታኔውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Get more results via ClueGoal