Ethiopia



የአቶ ታዬ ደንደአን ተጨማሪ የመከላከያ ምስክር ለመስማት ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ 

የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ደ’ኤታ አቶ ታዬ ደንደአ መከላከያ ምስክሮች የመጥሪያ ትዕዛዝ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው፣ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደ

በአማራ ክልል ተመላሽ ፍልሰተኞች ለዳግም ፍልሰት መዳረጋቸውን ገለጹ

ከተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ወደ አማራ ክልል ተመልሰው የነበሩ ሰዎች ለዳግም ፍልሰት መዳረጋቸውን ተናገሩ። ቪኦኤ ያነጋገራቸው፣ ደቡብና ሰሜን ወሎ
የአሜሪካ ድምፅ

በአማራ ክልል ተመላሽ ፍልሰተኞች ለዳግም ፍልሰት መዳረጋቸውን ገለጹ

ከተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ወደ አማራ ክልል ተመልሰው የነበሩ ሰዎች ለዳግም ፍልሰት መዳረጋቸውን ተናገሩ። ቪኦኤ ያነጋገራቸው፣ ደቡብና ሰሜን ወሎ የሚገኙ ከስደት ተመላሾች፣ መንግሥት ሊያቋቁማቸውን የገባውን ቃል ባለመጠበቁ፣ በድጋሚ ለመሄድ ዝግጅት ላይ መኾናቸውን ተናግረዋል። በተጨማሪም በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ተንቀሳቅሰው መሥራት አለመቻላቸው ችግሩን እንዳባባሰው ገልጸዋል። የአማራ ክልል ሥራና ሥልጠና ቢሮ ከክልሉ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚደረገው ፍልሰት መባባሱን አረጋግጦ፣ ተመላሾችን ለማቋቋም የአቅም ውስንነት መኖሩን አስታውቋል። ዝርዝሩን ከተያይዘው ፋይል ይከታተሉ።

በሱዳን ጦርነት የሟቾቹ ቁጥር ከተገመተውም በላይ እንደሆነ አዲስ ጥናት አመለከተ

በሱዳን ጦርነት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ብዛት ከዚህ በፊት ከተገመተው ሊበልጥ እንደሚችል አንድ ዐዲስ ጥናት አመለከተ። ግጭቱ 11 ሚሊዮን ሰዎችን ከመኖሪያቸው ሲ
የአሜሪካ ድምፅ

በሱዳን ጦርነት የሟቾቹ ቁጥር ከተገመተውም በላይ እንደሆነ አዲስ ጥናት አመለከተ

በሱዳን ጦርነት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ብዛት ከዚህ በፊት ከተገመተው ሊበልጥ እንደሚችል አንድ ዐዲስ ጥናት አመለከተ። ግጭቱ 11 ሚሊዮን ሰዎችን ከመኖሪያቸው ሲያፈናቅል፣ በዓለም አስከፊ የተባለውን ረሃብ ማስከተሉን ጥናቱ ጠቁሟል። ሄንሪ ሪጅዌል የላከው ዘገባ ነው። ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በኬኒያ የንብ ርባታ ማኅበረሰቦች የአየር ንብረት ለውጡን እንዲቋቋሙ እየረዳ ነው

የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ጥበቃ መርሃ ግብር በሞቃታማ አካባቢዎች የሚኖሩ ማኅበረሰቦች በዓለም ሙቀት መጨመር ከሁሉም በላይ ተጎጂዎች መሆናቸውን ይናገ
የአሜሪካ ድምፅ

በኬኒያ የንብ ርባታ ማኅበረሰቦች የአየር ንብረት ለውጡን እንዲቋቋሙ እየረዳ ነው

የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ጥበቃ መርሃ ግብር በሞቃታማ አካባቢዎች የሚኖሩ ማኅበረሰቦች በዓለም ሙቀት መጨመር ከሁሉም በላይ ተጎጂዎች መሆናቸውን ይናገራል፡፡ ተደጋጋሚ ድርቅ እና የጎርፍ መጥለቅለቅ እንደ እርሻ እና የእንስሳት እርባታ ያለውን የኖረ መተዳደሪያቸውን የማይቻል አድርገውታል። በኬንያ ያሉ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች ታዲያ እንደነዚህ ያሉ ማህበረሰቦች ተለዋዋጭ የአየር ሁኔታን ለመቋቋም እንዲረዳቸው፣ እንደ ንብ እርባታ የመሳሰሉ በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ አማራጭ መተዳደሪያዎችን እንዲያዳብሩ በመርዳት ላይ ናቸው። ጁማ ማጃንጋ ከጋርሰን፣ ኬንያ ዘግቦበታል፡፡ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

VOA60 America - Trump pledges immediate tariffs on goods from Mexico, Canada and China

President-elect Trump pledged Monday to quickly impose tariffs on China, Mexico and Canada – the country’s top three trade partners. In a post on his Truth Social account Trump said he will impose a 25 percent tariff on all products coming into the U.S. f
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Trump pledges immediate tariffs on goods from Mexico, Canada and China

President-elect Trump pledged Monday to quickly impose tariffs on China, Mexico and Canada – the country’s top three trade partners. In a post on his Truth Social account Trump said he will impose a 25 percent tariff on all products coming into the U.S. from Mexico and Canada.

VOA60 World - Heavy rains make temporary shelters uninhabitable for displaced people in Gaza

Heavy rains and falling temperatures are making tents and other temporary shelters uninhabitable for displaced people in Gaza. As of Monday, nearly 10,000 tents in the coastal enclave had been swept away by flooding, according to officials
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Heavy rains make temporary shelters uninhabitable for displaced people in Gaza

Heavy rains and falling temperatures are making tents and other temporary shelters uninhabitable for displaced people in Gaza. As of Monday, nearly 10,000 tents in the coastal enclave had been swept away by flooding, according to officials

የሕንዱ ግዙፍ የታዳሽ ኃይል ማመንጫ አዳኒ በዩናይትድ ስቴትስ በጉቦ ቅሌት ተወነጀለ

የሕንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ የታዳሽ የኃይል ምንጭ ግንባታ እቅድ ዋና ደጋፊ የሆኑት ቢሊየነሩ ጓታም አዳኒ፤ በዓለም ግዙፉ ይሆናል ለተባለው የታዳሽ
የአሜሪካ ድምፅ

የሕንዱ ግዙፍ የታዳሽ ኃይል ማመንጫ አዳኒ በዩናይትድ ስቴትስ በጉቦ ቅሌት ተወነጀለ

የሕንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ የታዳሽ የኃይል ምንጭ ግንባታ እቅድ ዋና ደጋፊ የሆኑት ቢሊየነሩ ጓታም አዳኒ፤ በዓለም ግዙፉ ይሆናል ለተባለው የታዳሽ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክታቸው የፈረንሳዩን ቶታል ኢነርጂ እና የካታር ኢንቨስትመንት ባለስልጣንን አጋርነት አግኝተዋል። በተለየ ዓይን የሚያዩት የኩባንያቸው ዋነኛው ውጥን ‘አዳኒ ግሪን’ የተባለው በሕንዷ የምዕራብ ጉጅራት ግዛት የሚገኘው ፕሮጀክት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2030 ሲጠናቀቅ 50 ጊጋ ዋት ኃይል ማለትም ሕንድ በእቅድ ከያዘችው አጠቃላይ የንፁህ ኃይል ምርት ‘አንድ አስረኛውን ያህል ያመነጫል’ ተብሎ ይጠበቃል። ይሁን እንጂ ያ እቅድ አሁን፤ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ አዳኒ እራሳቸው፣ የወንድማቸው ልጅ እና የኩባንያቸው ዋና ድሬክተር ሳጋር አዳኒ፤ እንዲሁም መራሄ ድሬክተሩ ቭኔት ኤስ ጃይን፤ ለህንድ ኃይል የሚያቀርብ የተቋራጭ ሥራ ኮንትራት ለማግኘት የ265 ሚሊዮን ዶላር ጉቦ በመስጠት እና የአሜሪካ ባለ ኃብቶችን በማሳሳት ወንጀሎች በቀረቡባቸው ክሶች መሰናክል ገጥሞታል። የክሱ ዜና እንደተሰማም፣ የአዳኒ ግሪን የዎል ስትሪት ገበያ የአክሲዮን (ስቶክ) ዋጋ 36 በመቶ በማሽቆልቆሉ፣ ከገበያ ዋጋው 9ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር አጥቷል። ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የቀረበበትን ክስ ‘መሠረተ ቢስ’ ሲል ውድቅ ያደረገው ‘አዳኒ ግሩፕ’ በበኩሉ ይህንን ለመቀልበስ ‘ሁሉንም የሕግ አማራጮች እጠቀማለሁ’ ብሏል ። ይሁን እንጂ ሁኔታው ለታዳሽ ኃይል ግንባታ ፕሮጀክቱ ማቀላጠፊያ የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ገንዘብ የማሰባሰብ ጥረቱን ያወሳስበዋል ተብሎ ተገምቷል።

‘የስኳር በሽታ’ በእርግጥ ምንድነው?

በልማድ አጠራር ‘የስኳር በሽታ’ በመባል የሚታወቀው ይህ የሕመም ዓይነት ሊያስከትል የሚችላቸውን ውስብስብ የጤና ችግሮች ለመከላከል ወይም ለማስቀረት ይቻል
የአሜሪካ ድምፅ

‘የስኳር በሽታ’ በእርግጥ ምንድነው?

በልማድ አጠራር ‘የስኳር በሽታ’ በመባል የሚታወቀው ይህ የሕመም ዓይነት ሊያስከትል የሚችላቸውን ውስብስብ የጤና ችግሮች ለመከላከል ወይም ለማስቀረት ይቻል ይሆን? ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተደረሰባቸው ያሉ ከበሽታው ጋር የተዛመዱ ሁኔታዎች ካሁን ቀደም ስለሕመሙ ይታመኑ የነበሩ እውነታዎችን ጭምር በእጅጉ እየቀየሩ መሆናቸው ይነገራል። "ለመሆኑ ከስኳር በሽታ ሙሉ በሙሉ ሊዳን ይችላል?” ለሚለው ጥያቄ መልሱ “አዎንም፣ አይደለምም፤ ነው” የሚሉን ሞያዊ ትንታኔውን የሰጡን የውስጥ ደዌ እና የኢንዶክሪኖሎጂ ልዩ ሕክምና ባለ ሞያው ዶ/ር አቤል ተካ ናቸው። ”‘ኢንሱሊን’ የተባለውን ሰውነት የሚያመነጨውን ንጥረ ነገር የሰውነት አካላት በአግባቡ መጠቀም የማይችሉበት ሁኔታ እንዴት እንደሚፈጠር በወጉ መረዳት፤ የተለያዩ ውስብስብ ችግሮች የሚያስከትለውን የስኳር በሽታ ምንነት ለመረዳትም ሆነ፤ በሽታውን ለማከም በሚሰጠው ሕክምና እና ሕመምተኛው በራሱ ሊያደርጋቸው በሚችላቸው ጥረቶች አመርቂ ውጤት ለማግኘት ወሳኝ ነው” ይላሉ። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በደቡብ ሱዳን ከ2 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል

በደቡብ ሱዳን 2 ሚሊዮን የሚደርሱ ህጻናት እና 1 ሚሊዮን ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች ለከፋ የምግብ እጦት እየተጋለጡ መሆኑን ገልጾ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አ
የአሜሪካ ድምፅ

በደቡብ ሱዳን ከ2 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል

በደቡብ ሱዳን 2 ሚሊዮን የሚደርሱ ህጻናት እና 1 ሚሊዮን ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች ለከፋ የምግብ እጦት እየተጋለጡ መሆኑን ገልጾ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስጠንቅቋል። ደካማ የንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ የንፅህና አጠባበቅ እና የበሽታ መስፋፋት ቀውሱን ማባባሱን ቀጥሏል። ሺላ ፖኒ ከጁባ ከደቡብ ሱዳን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በጀልባ መገልበጥ አደጋ ከ20 በላይ ፍልሰተኞች ማዳጋስካር የባህር ዳርቻ ላይ ሞቱ

ፍልሰተኞች የያዙ ሁለት ጀልባዎች ማዳጋስካር ባህር ዳርቻ ላይ ተገልብጠው 24 ፍልሰተኞች ህይወታቸው ማለፉን የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌይስ አስታ
የአሜሪካ ድምፅ

በጀልባ መገልበጥ አደጋ ከ20 በላይ ፍልሰተኞች ማዳጋስካር የባህር ዳርቻ ላይ ሞቱ

ፍልሰተኞች የያዙ ሁለት ጀልባዎች ማዳጋስካር ባህር ዳርቻ ላይ ተገልብጠው 24 ፍልሰተኞች ህይወታቸው ማለፉን የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌይስ አስታወቁ። ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ሶማሊያውያን መኾናቸው ተገልጿል፡፡ በሃሩን ማሩፍ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ዓለም ለትረምፕ የንግድ ጦርነት ተጽእኖ ዝግጅት ላይ ነው

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ በተለይም በቻይና ላይ ከፍተኛ ታሪፍ ለመጣል በመዛታቸው ምክንያት፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ሃገራት የኢኮኖሚ አለመረጋጋት
የአሜሪካ ድምፅ

ዓለም ለትረምፕ የንግድ ጦርነት ተጽእኖ ዝግጅት ላይ ነው

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ በተለይም በቻይና ላይ ከፍተኛ ታሪፍ ለመጣል በመዛታቸው ምክንያት፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ሃገራት የኢኮኖሚ አለመረጋጋት ሊከተል ይችላል በሚል ስጋት በሚል ዝግጅት ላይ ናቸው። መንግሥታትና የንግድ ድርጅቶች ለሁኔታው በምን መልኩ ምላሽ እንደሚሰጡ ግራ የተጋቡ ይመስላል። የቪኦኤው ቢል ጋሎ ከሶል፣ ደቡብ ኮሪያ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መስከረም አበራ የአንድ ዓመት ከ4 ወር እስር ተፈረደባት

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት በመስከረም አበራ ላይ የ1 ዓመት ከ4 ወር እስር መፍረዱን ጠበቃዋ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡ “በኮምፒውተር ተጠ
የአሜሪካ ድምፅ

መስከረም አበራ የአንድ ዓመት ከ4 ወር እስር ተፈረደባት

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት በመስከረም አበራ ላይ የ1 ዓመት ከ4 ወር እስር መፍረዱን ጠበቃዋ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡ “በኮምፒውተር ተጠቅማ በኅብረተሰብ መካከል አመጽ፣ ሁከት እና ግጭት ለማነሳሳት ሞክራለች” በሚል ጥፋተኛ በተባለችባቸው ሁለት ወንጀሎች እንደተፈረደባት ጠበቃዋ ተናግረዋል። ዛሬ የቅጣት ውሳኔው ከተሰጠበት የክስ መዝገብ ሌላ፣ በአማራ ክልል ካለው የፀጥታ መደፍረስ ጋራ በተገናኘ ደግሞ በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ ስር ከሌሎች 50 ተከሳሾች ጋራ የሽብር ክስ የተመሰረተባት መስከረም አበራ፣ ከሚያዝያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ትገኛለች፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

ህወሓት ችግሩን ካልፈታ ፌደራል መንግሥት ክልሉን እንደሚረከብ መግለጹን አቶ ጌታቸው ተናገሩ

የህወሓት አመራሮች በውስጣቸው ያለውን በመፍታት ያዋጣል የሚሉትን መንገድ የማያቀርቡ ከኾነ፣ ብልጽግና የክልሉን አስተዳደር ራሱ ሊይዘው እንደሚችል ማሳሰቢ
የአሜሪካ ድምፅ

ህወሓት ችግሩን ካልፈታ ፌደራል መንግሥት ክልሉን እንደሚረከብ መግለጹን አቶ ጌታቸው ተናገሩ

የህወሓት አመራሮች በውስጣቸው ያለውን በመፍታት ያዋጣል የሚሉትን መንገድ የማያቀርቡ ከኾነ፣ ብልጽግና የክልሉን አስተዳደር ራሱ ሊይዘው እንደሚችል ማሳሰቢያ መስጠቱን፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። ትላንት እሁድ ለክልሉ ብዙኅን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ በክልሉ ባለፉት ሦስት ወራት ተኩል ከ28 ኩንታል በላይ ወርቅ ወደ ፌዳራል መንግሥት ገቢ የገለጹት አቶ ጌታቸው «የክልሉ መንግሥት ከዚህ ውስጥ ያገኘው ገቢ የለም» ብለዋል።

ፍልሰተኞች ያሳፈሩ ጀልባዎች ማዳጋስካር ባሕር ዳርቻ ላይ ተገልብጠው ቢያንስ 22 ሶማሊያውያን መሞታቸው ተገለጸ

ፍልሰተኞችን የያዙ ሁለት ጀልባዎች በማዳጋስካር ባህር ዳርቻ ተገልብጠው 22 ሶማሊያውያን ህይወታቸው ማለፉን የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌይስ አስታ
የአሜሪካ ድምፅ

ፍልሰተኞች ያሳፈሩ ጀልባዎች ማዳጋስካር ባሕር ዳርቻ ላይ ተገልብጠው ቢያንስ 22 ሶማሊያውያን መሞታቸው ተገለጸ

ፍልሰተኞችን የያዙ ሁለት ጀልባዎች በማዳጋስካር ባህር ዳርቻ ተገልብጠው 22 ሶማሊያውያን ህይወታቸው ማለፉን የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌይስ አስታወቁ። የማዳጋስካር የወደብ፣ የባህር እና የወንዞች ባለሥልጣን አደጋውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ጀልባዎቹ ከሶማሊያ ተነስተው፣ ወደፈረንሳይ የህንድ ውቅያኖስ ግዛት ማዮት ጉዞ የጀመሩት ጥቅምት 23 ቀን ነበር። ሆኖም ቅዳሜ ኅዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ፣ ዓሣ አጥማጆች የመጀመሪያውን ጀልባ በኖሲ ኢራንጃ አቅራቢያ ባሕሩ ላይ በንፋስ እና በባሕሩ እንቅስቃሴ እየተገፋ ሲንሳፈፍ ማግኘታቸውን የወደቡ ባለሥልጣናት አመልክተዋል። ጀልባው ላይ ተሳፍረው ከነበሩት ሰዎች ውስጥ 10 ወንዶችን እና 15 ሴቶችን ጨምሮ በድምሩ የ25 ሰዎችን ህይወት ማዳን ቢቻልም፣ የሰባት ተሳፋሪዎች ህይወት ግን ማለፉን ባለሥልጣኑ አስታውቀዋል። 38 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረው ሁለተኛው ጀልባ ማዳጋስካር ወደብ ላይ መድረስ መቻሉን ያመለከተው  መስሪያ ቤቱ፣ 23 ሰዎችን በህይወት ማትረፍ መቻሉን ቢያስታውቅም፣ ምን ያክል ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ግን አልገለጸም። የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስትር አዌይስ በበኩላቸው ከማዳጋስካር አቻቸው እንዳገኙ የገለጹትን መረጃ ጠቅሰው፣ እስካሁን 22 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ መረጋገጡን ተናግረዋል። «በጀልባዎቹ ላይ ወደ 70 የሚጠጉ ሶማሊያውያን ነበሩ። ከነሱ ውስጥ 22ቱ ህይወታቸው አልፏል» ያሉት አዌይስ፣ አንደኛው ጀልባ 38 ሌላኛው ጀልባ 32 ፍልሰተኞችን አሳፍሮ እንደነበር አመልክተዋል። ባለፉት አሰርት ዓመታት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከፍ ያለ የኑሮ ደረጃ ወዳላት እና የፈረንሳይ የድጎማ ሥርዓትም ተጠቃሚ ወደሆነቸው ወደማዮት ባሕር አቋርጠው ለመግባት መሞከራቸው ተመልክቷል፡፡

የ29ኛው አየር ንብረት ጉባዔ ድርድሮች

በ29ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባዔ፣ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን ችግሮች ለመቋቋም 1.3 ትሪሊየን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ገልጻ ብት
የአሜሪካ ድምፅ

የ29ኛው አየር ንብረት ጉባዔ ድርድሮች

በ29ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባዔ፣ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን ችግሮች ለመቋቋም 1.3 ትሪሊየን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ገልጻ ብትሟገትም፣ የበለጸጉ ሀገራት በዓመት 300 ቢሊየን ዶላር ብቻ ለመስጠት ቃል ገብተዋል። የድርድሩ ሂደት ምን ይመስል ነበር? ታዳጊ ሀገራትስ በራሳቸው ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል? (ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ፋይል ያገኛሉ)

በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ተጽዕኖ እያሳረፉ ነው

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ተጽዕኖ መፍጠራቸውን በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ ይገልጻሉ፡፡ በአዲስ አበባ ዙርያ በአ
የአሜሪካ ድምፅ

በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ተጽዕኖ እያሳረፉ ነው

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ተጽዕኖ መፍጠራቸውን በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ ይገልጻሉ፡፡ በአዲስ አበባ ዙርያ በአካባቢ ጥበቃ ስራ የተሰማራው ሀብታሙ አዳነ በጸጥታ ችግሩ ምክንያት እንደልብ ተዘዋውሮ ለመስራት ባለመቻሉ ስራቸውን እስከማቆም የደረሱ ሰዎች ስለመኖራቸው ይናገራል፡፡  በአርባምንጭ ዩንቨርስቲ በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ መምህር የሆኑት ዶክተር አዲሱ ፍቃዱ በበኩላቸው ግጭት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች አብረው እንደማይሄዱ ገልጸው በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶችም በብዝሃ ህይወት ሃብቷና ለቱሪስቶች በማስጎብኘት ገቢ የምታገኝባቸው በነበሩ ፓርኮችና የዱር እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡   በዚህ ዙርያ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ

በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ተጽዕኖ እያሳረፉ ነው 

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ተጽዕኖ መፍጠራቸውን በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ ይገልጻሉ፡፡ በአዲስ አበባ ዙርያ በአ
የአሜሪካ ድምፅ

በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ተጽዕኖ እያሳረፉ ነው 

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ተጽዕኖ መፍጠራቸውን በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ ይገልጻሉ፡፡ በአዲስ አበባ ዙርያ በአካባቢ ጥበቃ ስራ የተሰማራው ሀብታሙ አዳነ በጸጥታ ችግሩ ምክንያት እንደልብ ተዘዋውሮ ለመስራት ባለመቻሉ ስራቸውን እስከማቆም የደረሱ ሰዎች ስለመኖራቸው ይናገራል፡፡  በአርባምንጭ ዩንቨርስቲ በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ መምህር የሆኑት ዶክተር አዲሱ ፍቃዱ በበኩላቸው ግጭት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች አብረው እንደማይሄዱ ገልጸው በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶችም በብዝሃ ህይወት ሃብቷና ለቱሪስቶች በማስጎብኘት ገቢ የምታገኝባቸው በነበሩ ፓርኮችና የዱር እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡   በዚህ ዙርያ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ

ኢራን ከሶስት የአውሮፓ ኃያላን ሀገሮች ጋር ስለ ኒውክሌር ትነጋገራለች

የተባበሩት መንግስታት የአቶሚክ ተቆጣጣሪ ቡድን በቴህራን ላይ ውሳኔ ካሳለፈ ጥቂት ቀናት በኋላ፣ ኢራን ስለ አወዛጋቢው የኒውክሌር መርሃ ግብር ከሶስት የአውሮ
የአሜሪካ ድምፅ

ኢራን ከሶስት የአውሮፓ ኃያላን ሀገሮች ጋር ስለ ኒውክሌር ትነጋገራለች

የተባበሩት መንግስታት የአቶሚክ ተቆጣጣሪ ቡድን በቴህራን ላይ ውሳኔ ካሳለፈ ጥቂት ቀናት በኋላ፣ ኢራን ስለ አወዛጋቢው የኒውክሌር መርሃ ግብር ከሶስት የአውሮፓ ኃያላን ሀገራት ጋር ፣ በመጭው ዓርብ እኤአ ኖቬምበር 29 በጄኔቭ ለመነጋገር ማቀዷን የጃፓኑ ኪዮዶ የዜና ወኪል ዛሬ እሁድ ዘግቧል፡፡ ኢራን በብሪታንያ፣ በፈረንሣይ፣ በጀርመን እና በዩናይትድ ስቴትስ ለቀረበው የውሳኔ ሃሳብ፣ የመንግስት ባለስልጣናት “የተለያዩ እርምጃዎች” በማለት የጠሩትን ፣ ዩራኒየምን የሚያበለጽጉ በርካታ አዳዲስና ዘመናዊ የማብለያ ማሽኖችን በማንቀሳቀስ ምላሽ ሰጥታለች፡፡ ኪዮዶ “የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን መንግስት ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በዐለ ሲመት ከመድረሱ  ከጥር ወር በፊት ለኒውክለር ውዝግብ እልባት ሊሰጥ  እየፈለገ ነው” ብለዋል፡፡ አንድ የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣን፣ ስብሰባው በመጪው ዓርብ እንደሚካሄድ አረጋግጠው «ቴህራን የኒውክሌር ጉዳይ ሁልጊዜም በዲፕሎማሲ መፈታት አለበት ብላ ታምናለች፣ ኢራን ከድርድር ወጥታ አታውቅም።» ብለዋል፡፡ የስዊዘርላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በሪፖርቱ ለተጠቀሱት ሀገራት ጥያቄዎችን አስተላልፈዋል። እ.ኤ.አ. በ2018 በወቅቱ የነበረው የትረምፕ አስተዳደር ኢራን እኤአ 2015 ከስድስት ኃያላን ሀገራት ጋር ገብታ ከነበረው የኒውክሌር ስምምነት በመውጣት ከባድ ማዕቀቦችን ጥሏል፡፡  በዚህ የተነሳ ቴህራን የስምምነቱን ገደብ በመጣስ፣ የዩራኒየም ክምችቶችን እንደገና በመጨመር እና በጥራት በማበልጸግ ፣ የላቀ የኒውክለር ኃይል ለማመንጨት ፈጣንና ዘመናዊ የማብለያ ማሽኖችን በመትከል የተለያዩ እምርጃዎችን ወስዳለች፡፡  ስምምነቱን ለማደስ በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር እና በቴህራን መካከል የተደረገው ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት አልተሳካም ፡፡ ይሁን እንጂ ትረምፕ ባለፈው መስከረም የምርጫ ቅስቀሳቸው ላይ  «ስምምነት መፍጠር አለብን ምክንያቱም የሚያስከትለው ነገር የማይቻል ነው፣ ስምምነት ማድረግ ይኖርብናል» ብለዋል፡፡  

እስራኤል ኤምሬትስ ውስጥ የተሰወሩት ረቢ ተገድለው ተገኙ አለች

በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ውስጥ ደብዛቸው ጠፍቶ ተሰውረው የቆዩት ሞልዶቫዊ እስራኤላዊ የሃይማኖት መምህር (ረቢ) ተገድለው መገኘታቸውን የእስራኤል ጠቅላይ ሚ
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል ኤምሬትስ ውስጥ የተሰወሩት ረቢ ተገድለው ተገኙ አለች

በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ውስጥ ደብዛቸው ጠፍቶ ተሰውረው የቆዩት ሞልዶቫዊ እስራኤላዊ የሃይማኖት መምህር (ረቢ) ተገድለው መገኘታቸውን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት ዛሬ እሁድ አስታወቀ፡፡  ጽህፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ ድርጊቱ “ዘግናኝ እና ፀረ ሴማዊ የሽብር ክስተት ነው” ብሏል፡፡ ዝቪ ኮጋን የተባሉት የአይሁድ ሀይማኖት መምህር መሰወራቸው የተሰማው ባለፈው ሀሙስ ሲሆን ታግተው ይሆናል የሚል ጥርጣሬ እንደነበር ተሰምቷል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት መግለጫ “የእስራኤል መንግሥት ፍትህ ለመሻት ለግድያው ተጠያቂ በሆኑ ወንጀለኞች ላይ ማናቸውንም መንገድ በመጠቀም እርምጃ ይወስዳል” ብሏል፡፡  የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ግድያውን አውግዘው የኢምሬት ባለሥልጣናት ስለወሰዱት ፈጣን እምርጃ አመስግነዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ አክለውም “ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ ያለመታከት ይሰራሉ” የሚል እምነት አለኝ ብለዋል።፡  የኮጋን መሰወር የተሰማው በጥቅምት ወር ኢራን እና እስራኤል የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን ተከትሎ ኢራን እስራኤል ላይ የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ እየዛተች ባለችበት ወቅት መሆኑ ተመልክቷል። የእስራኤል መግለጫ ኢራንን ባይጠቅስም የኢራን የስለላ አገልግሎት ከዚህ ቀደም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አፈናዎችን መፈጸሙን ጠቅሶ አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል። ምዕራባውያን ባለስልጣናት ኢራን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ውስጥ የስለላ ስራዎችን እንደምትሠራ እና በመላ ሀገሪቱ የሚኖሩ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናውያንን በቅርብ ትከታተላለች ብለው ያምናሉ። ምንም እንኳን ቴህራን ብታስተባብልም ኢራን እ.ኤ.አ. በ2013 እንግሊዛዊውን ኢራናዊ አባስ ያዝዲን ዱባይ ውስጥ አፍኖ በመግደል ተጠርጥራለች፡፡   እ.ኤ.አ. በ2020 ኢራናዊውን ጀርመናዊ ጃምሺድ ሻርማድን ከዱባይ አግታ ወደ ቴህራን የወሰደች መሆኗም ተነግሯል፡፡  ሻርማድ ባላፈው ጥቅምት ወር ኢራን ውስጥ የሞት ቅጣት ተፈጽሞበታል።  

በሄይቲ የወረበሎቹ ቡድን ከዓለም አቀፉ ሰላም አስከባሪ አይሏል

በሄይቲ የወሮበሎች ጥቃትን ለመግታት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈው ተልእኮ ውጤት ባለማሳየቱ የሀገሪቱ ዜጎች ተስፋ እየደበዘዘ መሆኑ ተነገረ፡፡ 
የአሜሪካ ድምፅ

በሄይቲ የወረበሎቹ ቡድን ከዓለም አቀፉ ሰላም አስከባሪ አይሏል

በሄይቲ የወሮበሎች ጥቃትን ለመግታት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈው ተልእኮ ውጤት ባለማሳየቱ የሀገሪቱ ዜጎች ተስፋ እየደበዘዘ መሆኑ ተነገረ፡፡  የኬንያ ፖሊሶች የወሮበሎች ጥቃትን ለመቀልበስ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈው ተልዕኮ አካል ሆነው ሄይቲ ሲደርሱ የነበረው ተስፋ ከፍተኛ እንደነበር ቢገለጽም፣ የወንበዴዎች ጥቃቶች የሀገሪቱን ዋና ከተማ እንቅስቃሴዎች ሽባ አድርገዋቸዋል፡፡ የወረበሎቹ ቡድኖች በሚያደርጓቸው የተቀናጁ ጥቃቶች  85 ከመቶ የሚሆነውን የዋና ከተማውን ክፍል በመቆጣጠር ከፍተኛ መፈናቀልና ሞት እያስከተሉ መሆኑ ተነግሯል፡፡  አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ቀውስ ውስጥ ከገባችው ሄይቲ ጋር ተጋፍጠዋል፡፡  ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ በዋና ከተማዋ 150 ሰዎች ሲገደሉ ወደ 20ሺ የሚሆኑት መኖሪያቸውን ለቀው ተሰደዋል፡፡  በዚህ የአውሮፓውያኑ ዓመት እስካሁን ወደ 4,500 ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል፡፡  

የሱዳን ጦር የሴናር ዋና ከተማን ተቆጣጠርኩ አለ

የሱዳን ጦር ላለፉት አምስት ወራት በፈጥኖ ደራሹ ጦር ቁጥጥር ሥር የነበረችውና ከካርቱም በስተደቡብ የምትገኘውን ቁልፏን የሴናር ክፍለ ግዛት ዋና ከተማ ሲንጃ
የአሜሪካ ድምፅ

የሱዳን ጦር የሴናር ዋና ከተማን ተቆጣጠርኩ አለ

የሱዳን ጦር ላለፉት አምስት ወራት በፈጥኖ ደራሹ ጦር ቁጥጥር ሥር የነበረችውና ከካርቱም በስተደቡብ የምትገኘውን ቁልፏን የሴናር ክፍለ ግዛት ዋና ከተማ ሲንጃን ትላንት ቅዳሜ መቆጣጠሩን አስታወቀ፡፡  ሲንጃ ለ19 ወራት በዘለቀው ጦርነት የምስራቅ እና መካከለኛው ሱዳን አካባቢዎችን በሚያገናኝ ቁልፍ መንገድ ላይ የምትገኝ ስትራቴጅካዊ ከተማ ናት። ሲንጃ “ከአሸባሪው ሚሊሻ ነፃ ወጥታለች” ያለው የሱዳን ጦር ሠራዊት  መግለጫ ከተማዪቱ “ወደ ሀገሯ እቅፍ ተመልሳለች” ብሏል፡፡ የሠራዊቱ አዛዥ ጀኔራል አብዱል ፋታህ አልቡርሃን ትላንት ቅደሜ ከካርቱም በስተሰሜን 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደ ምትገኘው ሴናር ከተማ በመሄድ ጉብኝት ማድረጋቸውንና ድሉን ማክበራቸውን በሠራዊቱ የሚመራው መንግሥት የማስታወቂያ መንግሥት ተናግረዋል፡፡  የፈጥኖ ደራሹ ጦር ባለፈው ሰኔ በሰነዘረው ድንገኛ ጥቃት የክፍለ ግዛቲቱን ሁለቱን ከተሞች መቆጣጠሩ ሲገለጽ ወደ 726ሺ ሰለማዊ ሰዎች እንደተፈናቀሉ የተባበሩት መንግስትታት ድርጅትን ጠቅሶ ኤኤፍፒ ዘግቧል ፡፡  

ሁለት ጀልባዎች ሰጥመው ከ20 በላይ የሶማሊያ ፍልሰተኞች ሞቱ

የሶማሊያ ባለስልጣናት፣ ባለፈው ሳምንት ከ20 በላይ የሚሆኑ የሶማሊያ ፍልሰተኞች፣  በማዳጋስካር የባህር ዳርቻ በሰጠሙ ሁለት የጀልባ አደጋዎች መሞታቸውን አስ
የአሜሪካ ድምፅ

ሁለት ጀልባዎች ሰጥመው ከ20 በላይ የሶማሊያ ፍልሰተኞች ሞቱ

የሶማሊያ ባለስልጣናት፣ ባለፈው ሳምንት ከ20 በላይ የሚሆኑ የሶማሊያ ፍልሰተኞች፣  በማዳጋስካር የባህር ዳርቻ በሰጠሙ ሁለት የጀልባ አደጋዎች መሞታቸውን አስታወቁ። ፍልስተኞቹ ወደ 70 የሚጠጉ ፍልሰተኞችን በጫኑ ሁለት ጀልባዎች ይጓዙ እንደነበር ተገልጿል። የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌስ ዛሬ እሁድ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት 22 ፍልሰተኞች ሲሞቱ 48ቱ መትረፋቸውን የማዳጋስካር ባለስልጣናት የእንደነገሯቸው አስታውቀዋል።  የተረፉትን ፍልሰተኞቹን ያዳኗቸው ኖሲ ኢራንጃ ደሴት የሚገኙ የማዳጋስካር ዓሣ አጥማጆች መሆናቸውም ተነግሯል፡፡ በሕይወት የተረፉትን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አዌስ ተናግረዋል። ጀልባዎቹ ከየት እንደተነሱ እና የመጨረሻ መዳረሻቸውን በተመለከተ አዌስ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። የአሜሪካ ድምፅ የአፍሪካ ቀንድ አገልግሎት ያነጋገራቸው የምስራቅ፣ የአፍሪካ ቀንድ እና ደቡብ አፍሪካ ፍልስተኞች ቢሮ ነገሩን እንደሚያውቁ ገልጸው በጉዳዩ ላይ ከሶማሊያ ባለስልጣናት ጋር እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።  

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድጋፍ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ ማህበረሰብ እንዴት ይደርሳል?

በአዘርባጃን ዋና ከተማ፣ ባኩ በተካሄደው 29ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባዔ፣ የበለጸጉ ሀገራት፣ ታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ ያለውን
የአሜሪካ ድምፅ

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድጋፍ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ ማህበረሰብ እንዴት ይደርሳል?

በአዘርባጃን ዋና ከተማ፣ ባኩ በተካሄደው 29ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባዔ፣ የበለጸጉ ሀገራት፣ ታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ ያለውን ጉዳት መቋቋም የሚያስችላቸውን የገንዘብ ድጋፍ እንዲሰጡ ጥረት ተካሂዷል። ለመሆኑ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በአየር ንብረት ለውጥ ክፉኛ እየተጎዱ ያሉ ሀገራት ከዚህ የገንዘብ ድጋፍ ምን ያክል ተጠቃሚ ይሆናሉ? በደቡብ ኢትዮጵያ፣ ጎፋ ዞን ሐምሌ ወር ላይ ከዚህ በፊት ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ተከታታይ የመሬት መንሸራተት አደጋ  ህይወታቸውን ማጣታቸው ከተረጋገጠው 243 ሰዎች መካከል የአቶ ሰለሞን ሶማም ታላቅ እህት እና ሌሎች 13 የቤተሰባቸው አባላት ይገኙበታል።  በአደጋው ምክንያት አሁንም ድንጋጤ እና ሐዘን ላይ መሆናቸውን የሚገልጹት አቶ ሰለሞን አርሶ አደር ናቸው። ከአባታቸው በወረሱት ማሳ ባቄላ፣ በቆሎ፣ እና ጤፍም ያመርቱ ነበር። አሁን ግን ተፈናቃይ ናቸው። በእድሜያቸው አይተውት የማያውቁት መሆኑን የሚገልጹት አስደንጋጭ አደጋ የደረሰው፣ በደን ምንጣሬ እና መሬት ያለእረፍት በተደጋጋሚ በመታረሱ ምክንያት የአየር ንብረቱ በመለወጡ ነው ብለውም ያምናሉ።   በኦሮሚያ ክልል፣ ቦረና ዞንም እንዲህ ለአምስት ተከታታይ ወቅቶች ዝናብ ባለመዝነቡ በተከሰተው ድርቅ ሰዎች ለረሃብ ተጋልጠዋል፣ የሕዝቡ ዋና መተዳደሪያ የሆኑ ከብቶች በብዛት አልቀዋል፣ ሚሊየኖችም ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። አቶ ሊበን ጎዳና በዞኑ ያቤሎ ከተማ ውስጥ ነዋሪ ሲሆኑ፣ በስድስት እና በሰባት አመት ይከሰት የነበረው ድርቅ አሁን በአመት እና በሁለት አመት የሚመጣ በመሆኑ በነዋሪው ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ያመለክታሉ።   አቶ ሊበን አክለው በተደጋጋሚ ለድርቅ እና ሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎች ተጋላጭ የሆነው የቦረና ማህበረሰብ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት፣ የማህበረሰቡ የአኗኗር ዘይቤን ከመቀየር አንስቶ በርካታ ድጋፍ ሊደረግ እንደሚገባ ያምናሉ።    እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርስባቸውን ጉዳት ለመቋቋም የሚያስችል መሠረተ ልማት እንደሌላቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያመለክታል። የገንዘብ ድጋፍ ከተገኘ ግን የሚሊየኖችን ህይወት ለማዳን እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶችን ለመዘርጋት እንደሚቻልም ይገልጻል።  በአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ የተካሄደው 29ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ቁልፍ እና አንገብጋቢ ጉዳይም ይህ ነበር። በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳትን እያስተናገዱ ባሉ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሀገራት እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ እንዲያስችል፣ ቃል የተገባው የገንዘብ ድጋፍ እንዲጨምር እና ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ። ቢኒያም ያዕቆብ በዓለም አቀፉ የአካባቢ እና ልማት ተቋም ከፍተኛ ጥናት አጥኚ ሲሆኑ በጉባዔው ላይ ታዳጊ ሀገራትን ወክለው ይደራደራሉ። የበለጸጉ ሀገራት የታሰበውን የገንዘብ ድጋፍ ለመስጠት ስምምነት ላይ ቢደርሱም፣ ታዳጊ ሀገራት ገንዘቡን ለማግኘት እንደ የዓለም ባንክ ወይም የአየር ንብረት ፈንድ ያሉ ተቋማት ማመልከቻዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።  ከዚህ በፊት በታየው ልምድ ግን ብዙዎቹ ታዳጊ ሀገራት ይህ ገንዘብ ለማግኘት የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን በሚፈለገው መሥፈርት እና ጊዜ ለማቅረብ እንደሚቸገሩ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ዶክተር ይተብቱ ሞገስ የደን ስነ-ምህዳር ባለሙያ ናቸው።  የታዳጊ ሀገራት አቅም ውሱንነት በአዘርባጃን ከተነሱ የድርድር አጀንዳዎች መካከል አንዱ መሆኑን አቶ ቢኒያም ያመለክታሉ።  ታዳጊ ሀገራት ካሉባቸው የውስጥ ችግር በተጨማሪ የበለጸጉ ሀገራት ገንዘቡን የሚለቁበት መንገድ ውስብስብ መሆንም ሌላው ችግር ነው። በመሆኑም ዶክተር ይተብቱ ኢትዮጵያ ይህን ውስብስብ አሰራር ተረድተው መረጃዎችን በፍጥነት ማጠናከር የሚችሉ ተቋማት እንዲቋቋሙ ይመክራሉ። የበለጸጉ ሀገራት እንዲሰጡ በሚጠበቀው የገንዘብ ድጋፍ ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረስ ከተቻለ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ታዳጊ ሀገራት በገንዘቡ መጠቀም የሚያስችል ብቅት ማሳየት ይጠበቅባቸዋል። እስከዛው ለአየር ንብረት መዛባት እምብዛም አስተዋፅኦ የሌላቸው የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች በተደጋጋሚ ከሚያጠቃቸው የድርቅ እና የጎርፍ አደጋ ለመላቀቅ በተስፋ ይጠብቃሉ። 

የማኅጸን ግድግዳ መውረድ ምንድነው?

የማኅጸን በር ወይም ግድግዳ ውልቃት ተብሎ በተልምዶ የሚጠራው በኢትዮጵያ በብዛት የማይታወቅ እና ትኩረት ያልተሰጠው ነገር ግን በብዙ እናቶች ላይ የሚከሰት የ
የአሜሪካ ድምፅ

የማኅጸን ግድግዳ መውረድ ምንድነው?

የማኅጸን በር ወይም ግድግዳ ውልቃት ተብሎ በተልምዶ የሚጠራው በኢትዮጵያ በብዛት የማይታወቅ እና ትኩረት ያልተሰጠው ነገር ግን በብዙ እናቶች ላይ የሚከሰት የጤና ችግር ነው። በእንግሊዘኛ አጠራሩ ፕሮላፕስ ተብሎ የሚጠራውና በሴቷ የመራቢያ አካላት ውስጥ ያሉ ጡንቻዎች በመላላት ወደ ውጭ የሚወጣው የማኅጸን በር ወይም ግድግዳ አብዛኛውን ጊዜ ከወሊድ በኋላ ከባድ ስራ በመስራት፣ ለረጅም ሰዓት በማማጥ፣ በቂ የሆነ ህክምና ካለማግኘት እና በመሳሰሉት ምክንያቶች እንደሚከሰት ባለሞያዎች ይገልጻሉ። ብዙ ሴቶችም ጉዳዩን አቅልለው በማየት የህክምና አገልግሎት ሳያገኙ ለአመታት ከችግሩ ጋር አብረው እንደሚኖሩ ጥናቶች ያሳያሉ። በዚህ የተነሳም ተደጋጋሚ ለሆነ ኢንፌክሽኖች (የሰውነት መቆጣት)፣ በጊዜ ሂደት የሽንት ማምለጥ፣ እና ይባስ ብሎም እንደማኅጸን ካንሰር ላሉ የከፉ የጤና ችግሮች ተጋላጭ እንደሚሆኑ በተለያየ ጊዜ የተሰሩ ጥናቶች አመላክተዋል። ኤደን ገረመው በዚህ ችግር ተጠቂ የነበሩ አንዲት እናት፣ የጤና ባለሞያ እና በዚህ ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚሰራ ተቋምን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች።

በአርጀንቲና እግር ኳስ ጉዳይ ፕሬዝዳንቱና ማኅበሩ እየተወዛገቡ ነው

ማራዶና እና ሊዮኔል ሜሲን የመሳሰሉ የዓለም ኮከብ ተጫዋቾችን ባፈራችውና ሦስት ጊዜ  እግር ኳስ ሻምፒዮና የሆነችው አርጀንቲና ፕሬዝዳንት ሃቪየር ሚሌ እና የእ
የአሜሪካ ድምፅ

በአርጀንቲና እግር ኳስ ጉዳይ ፕሬዝዳንቱና ማኅበሩ እየተወዛገቡ ነው

ማራዶና እና ሊዮኔል ሜሲን የመሳሰሉ የዓለም ኮከብ ተጫዋቾችን ባፈራችውና ሦስት ጊዜ  እግር ኳስ ሻምፒዮና የሆነችው አርጀንቲና ፕሬዝዳንት ሃቪየር ሚሌ እና የእግር ኳስ ማኅበሩ ፕሬዚዳንት ክላውዲዮ ታፒያ በቡድኖች አደረጃጀት ጉዳይ እየተወዛገቡ ነው፡፡ የእግር ኳስ ክለቦች የንግድ ድርጅቶችን መልክ ይዘው እንዲዋቀሩ ይፈቅድላቸው ወይስ አይፈቀድላቸው የሚለው ዋነኛው የውዝግቡ መንስኤ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ፕሬዝዳንት ሚሌ ክለቦቹ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አደረጃጀትን ተከትለው ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ወይም ማኅበር ሆነው በንግድ መልክ እንዲደራጁ ቢፈልጉም የእግር ኳስ ማህበሩ ፕሬዚዳንት አይደግፉትም፡፡   የእግር ኳሱ ፕሬዚዳንት ታፒያ ክለቦች በአባሎቻቸው ባለቤትነት  መተዳደራቸውን እንዲቀጥሉ የሚፈልጉ ሲሆን ለአክሲዮን መቅረብም ሆነ ለባለሀብቶች መሸጥ የለባቸውም ባይ ናቸው፡፡ የአርጀቲና ፕሬዝዳንት «የበለጠ ኢንቨትመንት ያመጣል፣ የአሠራር ቅልጥፍናንም ይጨምራል» በሚል ክለቦች በአባሎቻቸው ይሁንታ ወደ ንግድ ድርጅትነት እንዲቀየሩ የሚያስችሉ ህጎችን ቢያወጡም፣ የእግር ኳስ ማህበሩ ግን በዚያ መልኩ የተደራጁ ክለቦችን እንደማይቀበል ከወዲሁ አስታውቋል፡፡ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን  (ፊፋ) እና የደቡብ አሜሪካ የእግር ኳስ ፌደሬሽን የአርጀንቲና መንግሥት በእግር ኳስ ጉዳይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እንደማይቀበሉት በመግለጽ አስጠንቅቀዋል፡፡ ተችዎች የአርጀንቲና እግር ኳስ በሙስና፥ በደካማ አሠራርና ገና ብቅ ያሉ ወጣት ተጫዋቾችን አስቀድሞ በመሸጥ ላይ ያተኮረ ነው ሲሉ ይከሡታል፡፡ የእግር ኳስ ፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት እ አ አ እስከ 2028 በኃላፊነት እንዲቀጥሉ የተመረጡ በመሆናቸው ሁኔታውን የበለጠ አስቸጋሪ ማድረጉ ተጠቅሷል፡፡ የአርጀንቲና ፕሬዝዳንት በማኅበሩ አሠራር ላይ ምርመራ እንደሚደረግ የተናገሩ ሲሆን የስፖርት ማህበሩ ከመንግስት የሚያገኛቸው አንዳንድ ጥቅማ ጥቅሞችም እንዲቀነሱ አድርገዋል፡

ዩክሬን በሩሲያ የተተኮሰው ሚሳይል ከድምጽም የፈጠነ ነው   አለች

ትላንት ሀሙስ የዩክሬይን ከተማ ዲኒፕሮ  የመታው የሩስያ ሚሳይል “ለ15 ደቂቃ የተምዘገዘገ ሲሆን እኤአ ባላፈው መጋቢት 11 ከተተኮሰው የሚፈጥን ነው” ሲል የኪየ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩክሬን በሩሲያ የተተኮሰው ሚሳይል ከድምጽም የፈጠነ ነው   አለች

ትላንት ሀሙስ የዩክሬይን ከተማ ዲኒፕሮ  የመታው የሩስያ ሚሳይል “ለ15 ደቂቃ የተምዘገዘገ ሲሆን እኤአ ባላፈው መጋቢት 11 ከተተኮሰው የሚፈጥን ነው” ሲል የኪየቭ ከፍተኛ የስለላ ድርጅት ዛሬ ዓርብ ተናግሯል፡፡ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ትላንት ሀሙስ እንደተናገሩት ሞስኮ “ኦሬሽኒክ” ተብሎ በሚጠራውና ከድምጽ በአምስት እጥፍ ይፈጥናል በተባለው አዲስ የ“ሃይፐርሶኒክ መካከለኛ ርቀት ተጓዥ ባለስቲክ ሚሳይል የዩክሬንን ወታደራዊ ተቋም አጥቅቷል ብለዋል፡፡ «ይህ የሩስያ ሚሳይል ወደ አስትራካን ክልል ከተተኮሰበት ጊዜ አንስቶ በዲኒፕሮ ከተማ ላይ ጉዳት እስካሳደረበት ጊዜ ድረስ የፈጀው የበረራ ጊዜ 15 ደቂቃ ነበር» ሲል የዩክሬን ዋና የመረጃ ዳይሬክቶሬት ባወጣው መግለጫው ተናግሯል። ሚሳይሉ እያንዳንዳቸው ስድስት ፈንጂዎችን የሚተፉ  ስድስት ወንጫፊዎች  የታጠቀ ሲሆን በመጨረሻው የመወንጨፊያ ሰዓትም ያሳየው ፍጥነት ከድምጽ በ11 እጥፍ የፈጠነ ነበር “ብሏል፡፡ የደህንነት ማዕከሉ አክሎም መሣሪያው “‹ከድር› ሚሳይል ተብለው ከሚጠሩ አዳዲሶቹ የሩሲያ ሀገር አቋራጭ ሚሳይሎች መካከል ሳይሆን አይቀርም” ብሏል። ኪቭ መጀመሪያ ላይ “ሩሲያ አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳይል ተኩሳለች” ብትልም የአሜሪካ ባለስልጣናት እና ኔቶ ግን፣ ፑቲን መሣሪያውን እንደ መካከለኛ ርቀት ባለስቲክ ሚሳይል አድርገው የገለጹበትን መንገድ ተጠቅመዋል፡፡ የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ለጥቃቱ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ትላንት ሃሙስ አሳስቧል። ኔቶ በሞስኮ ጥቃት ላይ ለመምከር በብራሰልስ በሚገኘው የሕብረቱ ዋና መሥሪያ ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያደርግ የኔቶ ምንጭ ዛሬ አስታውቋል፡፡

በኮሬ ዞን ከ60 በላይ መምህራን ከደሞዝ መቆረጥ ጋራ በተያያዘ መታሰራቸው ተገለጸ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ ከፍላጎታቸው ውጪ ደሞዝ መቆረጡን በመቃወም ሥራ የማቆም አድማ ያደረጉ 66 መምህራን መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸውና መ
የአሜሪካ ድምፅ

በኮሬ ዞን ከ60 በላይ መምህራን ከደሞዝ መቆረጥ ጋራ በተያያዘ መታሰራቸው ተገለጸ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ ከፍላጎታቸው ውጪ ደሞዝ መቆረጡን በመቃወም ሥራ የማቆም አድማ ያደረጉ 66 መምህራን መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸውና መምህራን ተናገሩ። የሳርማሌ ወረዳ አስተዳደር፣መምህራንን በማሳመፅ ተጠርጥረው የታሰሩ መኖራቸውን አረጋግጧል።

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ የደረሰው ርእደ መሬት በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተጽእኖ አስከተለ

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ደጋግሞ የደረሰው ርዕደ መሬት በት/ቤቶች ላይ ጉዳት በማድረሱ ከ600 በላይ ተማሪዎች ዛፍ ጥላ ስር ለመማር መገደዳቸውን የወረዳ
የአሜሪካ ድምፅ

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ የደረሰው ርእደ መሬት በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተጽእኖ አስከተለ

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ደጋግሞ የደረሰው ርዕደ መሬት በት/ቤቶች ላይ ጉዳት በማድረሱ ከ600 በላይ ተማሪዎች ዛፍ ጥላ ስር ለመማር መገደዳቸውን የወረዳው የትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ በርዕደ መሬቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ት/ቤቶች ውስጥ በዋናነት በሚጠቀሱት የሳቡሬ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የደረሰው ቁሳዊ ጉዳት የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተጽእኖ ከማሳደሩ ባሻገር በመቶዎች ለሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጥ ምክንያት መሆኑን ገልጿል፡፡ /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

የኢትዮጵያ መንግሥት 582 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ተጨማሪ የበጀት ጥያቄ አቅርቧል

የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ በመንግሥት የቀረበውን ተጨማሪ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ፣ ከዓለም የገንዘብ
የአሜሪካ ድምፅ

የኢትዮጵያ መንግሥት 582 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ተጨማሪ የበጀት ጥያቄ አቅርቧል

የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ በመንግሥት የቀረበውን ተጨማሪ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ፣ ከዓለም የገንዘብ ተቋማትና ከሌሎችም ምንጮች ከሚገኘው ገንዘብ ውስጥ ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ የበጀት ጥያቄ እንደሚቀርብ የገንዘብ ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወሳል፡፡ መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ተከትሎ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ተጨማሪ በጀት በመመደብ የሚወስዳቸው ርምጃዎች የሚኖራቸውን ተፅዕኖ በአሉታዊና አዎንታዊነት የሚመለከቱ ባለሞያዎች አሉ። የአሁኑ ተጨማሪ በጀት ስለሚኖረው ተፅዕኖ የማክሮ ኢኮኖሚ ባለሞያው ዶ/ር ቴዎድሮስ መኮንን፣ አዲሱ የበጀት ጭማሪ የውጭ ገቢዎች ላይ የተመሰረተ በመኾኑ በዋጋ ንረት ላይ የጎላ ተፅዕኖ እንደማይኖረው ያብራራሉ፡፡ /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/  

ከመንገድ ዳር ዛፎቹ ጋር በፍቅር የወደቀው በጎ ፈቃደኛ

ዋለልኝ መኮንን ይባላል። ተወልዶ ያደገው ድሬዳዋ ከዚራ ሰፈር ነው። ቀድሞ በዛፎች ይታወቅ የነበረው የከተማዋ መሃል አካባቢ ገላጣ መኾን የፈጠረበት ቁጭት አካ
የአሜሪካ ድምፅ

ከመንገድ ዳር ዛፎቹ ጋር በፍቅር የወደቀው በጎ ፈቃደኛ

ዋለልኝ መኮንን ይባላል። ተወልዶ ያደገው ድሬዳዋ ከዚራ ሰፈር ነው። ቀድሞ በዛፎች ይታወቅ የነበረው የከተማዋ መሃል አካባቢ ገላጣ መኾን የፈጠረበት ቁጭት አካባቢውን ወደ አረንጓዴነት እንዲቀይር አድርጎታል። ዋለልኝ ለ14 ዓመታት ያለማውን ይኽን ስፍራ የጎበኘው ዘጋቢያችን ዐዲስ ቸኮል በተከታዩ ዘገባ ቦታውን ያስቃኘናል።

በዶናልድ ትረምፕ ድጋሚ መመረጥ የምሁራን እይታ

የዶናልድ ትረምፕ  በድጋሚ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ኾነው መመረጣቸው እንዳስገረማቸው በርካታ የውጭ ሀገር ምሁራን  ተናገሩ። «የአሜሪካ መራጮችንና ትልቅ ቦታ
የአሜሪካ ድምፅ

በዶናልድ ትረምፕ ድጋሚ መመረጥ የምሁራን እይታ

የዶናልድ ትረምፕ  በድጋሚ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ኾነው መመረጣቸው እንዳስገረማቸው በርካታ የውጭ ሀገር ምሁራን  ተናገሩ። «የአሜሪካ መራጮችንና ትልቅ ቦታ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች  በውል አልተረዳንም  ነበር» የሚል ስሜት እንዲሰማቸው  ማድረጉንም አመልክተዋል። ተመራጩ ፕሬዝደንት በሚቀጥለው አስተዳደራቸው ምን ዓይነት የውጭ ፖሊሲ እንደሚከተሉ እስካሁን በብዛት በግልጽ ባይታወቅም ጉዳዩን የሚከታተሉ አንድ ኢትዮጵያዊ ተንታኝ ተመራጩ ፕሬዝደንት  ከተለመደው ወጣ ያለውን የውጭ ፖሊሲ አካሄዳቸውን «አሁንም ይቀጥላሉ» ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል ። ትረምፕ የዓለም አቀፍ ፖለቲካ አካሄዳቸው  በሁለትዮሽ ግንኙነቶች  ላይ የተመሰረተ እንደሚኾን የገለጹ ተንታኞች  በተለይም የአፍሪካ ቀንድን በሚመለከት የሚከተሉት መንገድ የአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅምን በማስጠበቅ ላይ የተቃኘ  እንደሚሆን  ይናገራሉ፡፡ የሐዋሳው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዴዎስ እና የቪኦኤ ዋይት ሃውስ ዘጋቢ ፖትሲ ውዳኩስዋራን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

ቻይና ኢኮኖሚዋን ለማነቃቃት መግቢያ ቪዛ የማያስፈልጋቸው ሀገሮችን ቁጥር ልታሳድግ ነው

ቻይና የቱሪዝም እና የንግድ ተጓዦችን ቁጥር በማሳደግ የተቀዛቀዘውን ኢኮኖሚዋን ለማነቃቃት ለዘጠኝ ተጨማሪ ሀገራት ዜጎች ካለቪዛ እንዲገቡ ልትፈቅድ መሆኗን
የአሜሪካ ድምፅ

ቻይና ኢኮኖሚዋን ለማነቃቃት መግቢያ ቪዛ የማያስፈልጋቸው ሀገሮችን ቁጥር ልታሳድግ ነው

ቻይና የቱሪዝም እና የንግድ ተጓዦችን ቁጥር በማሳደግ የተቀዛቀዘውን ኢኮኖሚዋን ለማነቃቃት ለዘጠኝ ተጨማሪ ሀገራት ዜጎች ካለቪዛ እንዲገቡ ልትፈቅድ መሆኗን  አስታወቀች፡፡ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን ዛሬ ዓርብ እንዳስታወቁት እአአ ከህዳር 30 ጀምሮ ከቡልጋሪያ፣ ሮማኒያ፣ ማልታ፣ ክሮኤሺያ፣ ሞንቴኔግሮ፣ ሰሜን መቄዶኒያ፣ ኢስቶኒያ፣ ላቲቪያ እና ጃፓን ተጓዦች ለሠላሳ ቀናት ቆይታ ያለ ቪዛ  ሊገቡ ይችላሉ። ይህ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ያለቪዛ መግባት የተፈቀደላቸውን ሀገራት ቁጥር ወደ 38 ያሳድገዋል። ከዚህ ቀደም ከቪዛ ነጻ ፈቃድ የነበራቸው ሦስት ሀገራት ብቻ ሲሆኑ የእነሱም ፈቃድ  በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ተሰርዞ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ የጃፓን ከቪዛ ነጻ ሀገራቱ ውስጥ መጨመር፣ ቻይና በታይዋን ጉዳይ ከቶኪዮ በተደረጉ ጠንከር ያሉ ንግግሮች የተነሳ  ሻክሮ የነበረውን ግንኙነት ለማሻሻል እየፈለገች መሆኗን ሊጠቁም እንደሚችል ተነግሯል፡፡ ጃፓን ከወረርሽኙ  በፊት ከቪዛ ነፃ ከሚገቡት ሶስት ሀገራት አንዷ ነበረች፡፡  የጃፓን የካቢኔ ፀሃፊ ዮሺማሳ ሃያሺ እንደገና እንዲጀመር መንግሥታቸው  በተደጋጋሚ ሲወተውት እንደነበረ ገልጸዋል፡፡ ቻይና ከቪዛ ነፃ የመግባት ሂደትን በየደረጃው በማስፋፋት የአውሮፓ ሀገራትን ጨምራ በቅርቡ የተማሪዎችና እና የምሁራን ጉብኝቶችን በማሻሻል የህዝብ ለህዝብ ልውውጥ ላይ ትኩረት አድርጋለች። ታይላንድ እና ሌሎች ሀገራት ቱሪዝምን ለማበረታታት ለቻይና ተጓዦች ከቪዛ ነጻ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ አድርገዋል፡፡ በዚህ ዓመት ከሀምሌ እስከ መስከረም በነበሩት ሦስት ወራት  8፡2 ሚሊዮን የውጭ ዜጎች ቻይና የገቡ ሲሆን  4፡9 ሚሊዮን የሚሆኑት ከቪዛ ነጻ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባው አመልክቷል፡፡

የመካከለኛው ምሥራቅ የባይደን ልዩ መልዕክተኛ ግጭቶቹን ለማብቃት በተያዘው ድርድር  ‘ተሥፋ አለኝ’ አሉ

በመካከለኛው ምስራቅ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ልዩ መልዕክተኛ በትላንትናው ዕለት ሲናገሩ ምንም እንኳን በእስራኤል ሰሜናዊ ድንበር እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ቢ
የአሜሪካ ድምፅ

የመካከለኛው ምሥራቅ የባይደን ልዩ መልዕክተኛ ግጭቶቹን ለማብቃት በተያዘው ድርድር  ‘ተሥፋ አለኝ’ አሉ

በመካከለኛው ምስራቅ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ልዩ መልዕክተኛ በትላንትናው ዕለት ሲናገሩ ምንም እንኳን በእስራኤል ሰሜናዊ ድንበር እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ቢቀጥል እና የጋዛው ጦርነት ፍጻሜ ባይታይም፤ ግጭቱን ለማስቆም ከሄዝቦላህ ጋር የሚደረገውን ድርድር አስመልክቶ ያላቸውን ተስፋ ገልጠዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የዩናይትድ ስቴትስ እንደራሴዎች ምክር ቤት ትላንት ማምሻው ላይ በወሰደው ርምጃ ወደ እስራኤል ሊላክ የነበረ የተወሰነ መጠን ያለው ጦር መሳሪያ እንዳይላክ አግዷል። ርምጃውን የተቃወሙ ወገኖች በበኩላቸው ውጊያውን ያራዝመዋል ብለዋል።

«ድህነትን መቀነስ የፍልሰት ቀውስን ለማስታገስ ያስችላል» ሲሉ ባለሙያዎች ተናገሩ

በዓለም ለሚታየው የፍልሰት ቀውስ ድህነትና ረሃብ ዋና ምክንያቶች እንደሆኑ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በብራዚል በተካሄደው የቡድን 20 ሃገራት ጉባኤ ጎን የተናገሩ
የአሜሪካ ድምፅ

«ድህነትን መቀነስ የፍልሰት ቀውስን ለማስታገስ ያስችላል» ሲሉ ባለሙያዎች ተናገሩ

በዓለም ለሚታየው የፍልሰት ቀውስ ድህነትና ረሃብ ዋና ምክንያቶች እንደሆኑ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በብራዚል በተካሄደው የቡድን 20 ሃገራት ጉባኤ ጎን የተናገሩት ባለሙያዎች፣ ውጤታማ የሆኑ የማኅበራዊ ደኅንነት መጠበቂያ መንገዶች (ሴፍቲ ኔት) መኖር ሰዎች መኖሪያቸውን ለቀው ለመሰደድ የሚያበቋቸውን መንስሄዎች ለማስቆም ይረዳሉ። የቪኦኤ የስደት ጉዳዮች ዘጋቢ አሊን ቤሮስ ከሪዮ ደ ጃኔሮ የላከችው ዘገባ ነው።

ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት በኔታኒያሁና የሃማስ መሪዎች ላይ የእስር ማዘዣ አወጣ

የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት /ICC/ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትራቸው ዮአቭ ጋላንት እና የሃማስ ባለሥልጣ
የአሜሪካ ድምፅ

ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት በኔታኒያሁና የሃማስ መሪዎች ላይ የእስር ማዘዣ አወጣ

የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት /ICC/ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትራቸው ዮአቭ ጋላንት እና የሃማስ ባለሥልጣናትን በጦር ወንጀሎች እና በሰብአዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች በመክሰስ ዛሬ ሐሙስ የእስር ማዘዣ አውጥቶባቸዋል፡፡ የእስር ማዘዣው የወጣው ለ13 ወራት በዘለቀው የጋዛ ጦርነት በእስራኤል በተፈጸሙ የጦር ወንጀሎች እና እኤአ በጥቅምት 2023 ሀማስ በእስራኤል ላይ ባደረሳቸው የጦር ወንጀሎች እና በሰብዓዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች  ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ኔታንያሁ እና ጋላንት ሆን ብለው የጋዛን ሲቪሎች እንደ ምግብ፣ ውሃ እና መድሀኒት የመሳሰሉ አስፈላጊ አቅርቦቶችን መከልከላቸውን ሲገልጽ የሃማሱን መሪ መሀመድ ዲፍን ደግሞ እኤአ በጥቅምት 2023 በተፈጸመ ግድያ፣ አግቶ መሰወር፣ ማሰቃየት እና የፆታዊ ጥቃት ወንጀሎች ከሷል። ሃማስ ውሳኔውን ነቅፎታል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኒታኒያሁ ፍርድ ቤቱ በእርሳቸው ላይ ያወጣውን የእስር ማዘዣ አውግዘው፣ እስራኤል “የማይረባ እና የሐሰት ድርጊቶችን ስለምትጸየፍ አትቀበለውም” ብለዋል። ውሳኔው ኔታንያሁ እና ሌሎቹም በዓለም አቀፍ  ወንጀል ተፈላጊ ተጠርጣሪዎች ሆነው እንዲገለሉ ስለሚያደርግ ጦርነቱን ለማስቆም እና ለተኩስ አቁም ድርድር የሚደረገውን ጥረት የበለጠ እንደሚያወሳስበው የአሶሲየትድ ፕሬስ ዘገባው አመልክቷል። ይሁን እንጂ እስራኤል እና ዋና አጋሯ ዩናይትድ ስቴትስ የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አባላት ስላልሆኑ እና ሁለቱ የሃማስ ባለስልጣናት ቀደም ሲል በግጭቱ ስለተገደሉ የውሳኔ ተግባራዊ አንድምታ ውስን ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማውገዝ እስራኤል ከሃማስ ራሷን የመከላከል መብቷን እንደሚደግፉ ገለጸዋል። የመብት ተሟጋች ቡድኖች የዓለም አቀፉ  ፍርድ ቤት ውሳኔ በግጭት የተሳተፉትን አካላት በሙሉ ወደተጠያቂነት ለማምጣት ትልቅ ርምጃ ነው ሲሉ አድንቀዋል፡፡

የቀድሞ የትግራይ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታትና  ወደ ኅብረተሰቡ የማዋሐድ ሥራ ዛሬ ተጀመረ

በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ዛሬ በይፍ በተጀመረው፣ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት፣ ወደ ኅብረተሰቡ መልሶ የማዋሐድና የማቋቋም ሥራ 320 የቀድ
የአሜሪካ ድምፅ

የቀድሞ የትግራይ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታትና  ወደ ኅብረተሰቡ የማዋሐድ ሥራ ዛሬ ተጀመረ

በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ዛሬ በይፍ በተጀመረው፣ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት፣ ወደ ኅብረተሰቡ መልሶ የማዋሐድና የማቋቋም ሥራ 320 የቀድሞ ተዋጊዎች ትጥቃቸውን አስረክበው፣ ማሰልጠኛ ተቋማት ገቡ። በማሰልጠኛ ተቋማቱም ስድስት ቀናትን በሥልጠና እንደሚያሳልፉ፣ በዛሬው ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የብሔራዊ ተሐድሶ ኮምሽን ምክትል ኮምሽነር ብርጋዴር ጀነራል ደርቤ መኩሪያ ተናግረዋል።  

Get more results via ClueGoal