የሀዋሳ ከተማ የነዳጅ እጥረትና የተጠቃሚዎች ምሬት
newsare.net
በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ሕገ ወጥ የነዳጅ ንግድ በመስፋፋቱ በከተማዋ ለቀናት የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ተጠቃሚዎች ቅሬታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ። በከተማየሀዋሳ ከተማ የነዳጅ እጥረትና የተጠቃሚዎች ምሬት
በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ሕገ ወጥ የነዳጅ ንግድ በመስፋፋቱ በከተማዋ ለቀናት የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ተጠቃሚዎች ቅሬታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ። በከተማው በተለይም በማደያ በ93 ብር ገደማ የሚሸጠው አንድ ሊትር ቤንዚን በአሳቻ ሰዓት ከማደያ እየወጣ በድብቅ እስከ 250 እየተሸጠ መኾኑን ገልጸዋል። የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ፣ በሕገ ወጥ መንገድ ተሰማርተው ነዳጅ ሲሸጡ እና ሲያዘዋወሩ ተገኙ ያላቸውን 34 ሰዎች ማሰሩን አስታውቋል። እጥረቱ የተከሰተው በአቅርቦት ማነስ እና በሕገ ወጥ ንግድ ምክኒያት መኾኑንም ገልጿል። በተጨማሪም ሁለት የንግድ እና ገበያ ልማት ባለሞያዎች መታሰራቸውንም የተናገሩት ምክትል ኮሚሽነር ካሳ ጫቦ፣ አምስት ፖሊሶች ደግሞ የጹሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ጨምረው ተናግረዋል። የክልሉ አድማ በታኝ ፖሊስ በከተማው የሚገኙ ማደያዎችን እየተቆጣጠረ ሲኾን በክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የሚመራ የቁጥጥርና ክትትል ቡድን መቋቋሙን የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስ ገልጸዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። Read more