Ethiopia



አዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራውያን ከለላ ጠያቂዎች አፋር ክልል ሊሰፍሩ ነው ተባለ

አዲስ አበባ የሚገኙ ከለላ ጠያቂ ኤርትራውያንን በመመዝገብ፣ አፋር ክልል ውስጥ በሚዘጋጅ መጠለያ ጣቢያ ለማስፈር ማቀዱን የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገ

ዓዲግራት ከተማ ሁለት ከንቲባ ተሾመባት 

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከትላንት በስቲያ ለዓዲግራት ከተማ «ከንቲባ» የሾመ ሲኾን፣ በዶ.ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ዛሬ
የአሜሪካ ድምፅ

ዓዲግራት ከተማ ሁለት ከንቲባ ተሾመባት 

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከትላንት በስቲያ ለዓዲግራት ከተማ «ከንቲባ» የሾመ ሲኾን፣ በዶ.ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ዛሬ ባካሄደው የምክር ቤት ጉባኤ ደግሞ ሌላ «ከንቲባ» ለከተማዋ መሾሙን አስታውቋል። በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሾሙት አቶ ዓለም አረጋዊ ሲኾኑ፣ በዶ.ር. ደብረጽዮን የተሾሙት ደግሞ አቶ ረዳኢ ገብረእግዚኣብሄር ናቸው። ሁለቱንም ተሿሚዎች አነጋግረናል።

ሦስት በመብት ላይ የሚሠሩ ድርጅቶች መታገድ ትችት አስከተለ

ሁለት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሦስት ታዋቂ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶችን ማገዱን አጥብቀው ተቃወሙ። አምነስቲ
የአሜሪካ ድምፅ

ሦስት በመብት ላይ የሚሠሩ ድርጅቶች መታገድ ትችት አስከተለ

ሁለት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሦስት ታዋቂ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶችን ማገዱን አጥብቀው ተቃወሙ። አምነስቲና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል በተናጥል ባወጧቸው መግለጫዎች፣ በሰብአዊ መብት ዙርያ በሚሠሩ የሲቪል ማኅበራት ላይ የመንግሥት ዛቻና ማስፈራርያ መበርታቱን ተናግረዋል። አምነስቲ መንግሥት እግዱን እንዲያነሳ ጠይቋል። የማዕከል ዋና ዲሬክተር አቶ ያሬድ ሃይለማርያም፣ ድርጅቶቹ ከመታገዳቸው አስቀድሞም ቢኾን በሰብአዊ መብት ዙርያ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበራትና አመራሮቻቸው ላይ በመንግሥት የጸጥታ አካላት ዛቻና ማስፈራርያ ይደርስ እንደነበር ጠቁመዋል። ከኢትዮጵያ መንግሥት ምላሽ አላገኘንም።

ሥራ አቋርጠው የነበሩ የህክምና ባለሞያዎችና ሠራተኞች ወደ ሥራ መመለሳቸውን ገለጹ

በታጠቁ ዘራፊዎች ምክኒያት የደኅንነት ስጋት ስለገባቸው ባለፈው ሳምንት ሰኞ ሥራ ማቆማቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸው የነበሩ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝ ሆስፒታ
የአሜሪካ ድምፅ

ሥራ አቋርጠው የነበሩ የህክምና ባለሞያዎችና ሠራተኞች ወደ ሥራ መመለሳቸውን ገለጹ

በታጠቁ ዘራፊዎች ምክኒያት የደኅንነት ስጋት ስለገባቸው ባለፈው ሳምንት ሰኞ ሥራ ማቆማቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸው የነበሩ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የህክምና ባለሞያዎችና ሠራተኞች ሙሉ ለሙሉ ወደ መደበኛ ሥራቸውን ከተመለሱ አንድ ሳምንት እደኾናቸው ገለጹ። ከዩኒቨርስቲውና ከኮሌጁ አመራሮች ጋራ በተደረገ ውይይት የሆስፒታሉን ጥበቃ ለማጠናከር ስምምነት ላይ በመደረሱ ሥራ መጀመራቸውን ተናግረዋል። ከሆስፒታሉ አመራሮች ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

VOA60 Africa - At least 30 feared dead after landslides in eastern Uganda

Uganda: The government issued a national disaster alert Thursday after days of heavy rains caused flooding and landslides. Local officials say at least 30 people are feared dead after landslides Wednesday in Masugu village in eastern Bulambuli district.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - At least 30 feared dead after landslides in eastern Uganda

Uganda: The government issued a national disaster alert Thursday after days of heavy rains caused flooding and landslides. Local officials say at least 30 people are feared dead after landslides Wednesday in Masugu village in eastern Bulambuli district.

VOA60 America - Wrongfully detained Americans return from China

Three American citizens imprisoned for years by China have been released. The three were designated by the U.S. government as wrongfully detained. China announced Thursday that the United States had returned four people to China including three Beijing says w
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Wrongfully detained Americans return from China

Three American citizens imprisoned for years by China have been released. The three were designated by the U.S. government as wrongfully detained. China announced Thursday that the United States had returned four people to China including three Beijing says were «wrongfully imprisoned.»

VOA60 World - Israeli military strikes kill at least 17 Palestinians across Gaza Strip

Israeli military strikes killed at least 17 Palestinians across the Gaza Strip on Thursday, medics said, as forces stepped up aerial bombardments on central areas and pushed tanks deeper into the north and south of the enclave.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Israeli military strikes kill at least 17 Palestinians across Gaza Strip

Israeli military strikes killed at least 17 Palestinians across the Gaza Strip on Thursday, medics said, as forces stepped up aerial bombardments on central areas and pushed tanks deeper into the north and south of the enclave.

የማህሙድ አህመድ የስልሳ ዓመታት የሙዚቃ ሕይወት ጉዞ

ገና በአፍላ ዕድሜው ያደረበትን የሙዚቃ ፍቅር ይዞ አደባባይ የወጣው አንጋፋው ድምጻዊ ማህሙድ አህመድ ትውልድ ተሻግረው ዛሬም ድረስ እንደ አዲስ የሚሰሙ ሙዚቃ
የአሜሪካ ድምፅ

የማህሙድ አህመድ የስልሳ ዓመታት የሙዚቃ ሕይወት ጉዞ

ገና በአፍላ ዕድሜው ያደረበትን የሙዚቃ ፍቅር ይዞ አደባባይ የወጣው አንጋፋው ድምጻዊ ማህሙድ አህመድ ትውልድ ተሻግረው ዛሬም ድረስ እንደ አዲስ የሚሰሙ ሙዚቃዎችን እየተጫወተ እዚኽ ደርሷል። የኢትዮጵያን የሙዚቃ ባህል በዓለም አቀፍ የሙዚቃ መድረኮች ማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን፤ ሙዚቃውን የሚጫወቱ ቁጥራቸው የበዙ አውሮፓውያን እና አሜሪካውያን ሙዚቀኞችም አፍርቷል። ዩናይትድ ስቴትስን እና ካናዳን ጨምሮ በአንዳንድ ሀገሮች ዛሬ የሚከበረውን የምስጋና ቀን ክብረ በዓል ምክኒያት በማድረግ፣ በዋሽንግተን እና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን “ለዕድሜ ዘመን አገልግሎትህ፣ በድንቅ ሙዚቃ ሥራዎችህ ለሰጠኽን ደስታ እና ብሎም የባሕል አምባሳደር ሆነህ አገር ላስተዋወቅክበት ውለታህ እናመሰግናለን” ሊሉት ተሰናድተዋል። ማህሙድ እስካኹን ከኖረበት ዕድሜ፣ አብላጫው ያገለገለበትን መድረክ የሚሰናበትበት ይህን ልዩ ዝግጅት ‘አክብረን እንከበር’ የሚል ሥያሜ ሰጥተውታል። አቶ ፍስሃ ወልዴ የሥነ ሥርዐት አስተባባሪ ናቸው። ለዝግጅቱ መነሻ የሆናቸውን አጋጣሚ ጨምረው በመድረኩ የታሰበውን በመጠኑ ያጋሩናል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ጁባላንድ ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋራ ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን አስታወቀች

በሶማሊያ አንድ የፌዴራሉ ዓባል የሆነ ግዛት ከማዕከላዊ መንግሥት ጋራ ያለውን ግንኙነት ማቋረጡን ተከትሎ በሃገሪቱ የሚታየው የፖለቲካ ቀውስ ተባብሷል። በሶ
የአሜሪካ ድምፅ

ጁባላንድ ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋራ ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን አስታወቀች

በሶማሊያ አንድ የፌዴራሉ ዓባል የሆነ ግዛት ከማዕከላዊ መንግሥት ጋራ ያለውን ግንኙነት ማቋረጡን ተከትሎ በሃገሪቱ የሚታየው የፖለቲካ ቀውስ ተባብሷል። በሶማሊያ ከሚገኙ ስድስት የፌዴራሉ ዓባል ግዛቶች ውስጥ አንዷ የሆነችው በደቡብ የምትገኘው ጁባላንድ ከፌዴራል መንግሥቱ ጋራ ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን በይፋ አስታውቃለች፡፡  ይላል የግዛቲቱ ካቢኔ ስብሰባን ተከትሎ ዛሬ ከኪሲማዮ የወጣው መግለጫ፣ “ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋራ ያላትን የሥራ ግንኙነት ማቋረጧን ጁባላንድ ታስታውቃለች” ይላል።  ፑንትላንድም ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ከፌዴራል መንግሥቱ ጋራ ያላትን ግንኙነት ማቋረጧ ይታወሳል። ጁባላንድ መነጠሏን ያስታወቀችው፣ በሞቃዲሹ የሚገኝ ፍርድ ቤት በጁባላንድ መሪ ላይ የመያዢያ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ተከትሎ ነው። መሪዉ አህመድ ሞሃመድ ኢስላም ወይም አህመድ ማዶቤ የሃገሪቱን መረጃ ለውጪ ሃገር አሳልፈው ሠጥተዋል በሚል “የሃገር ክህደት” እና ሕገ መንግስቱን የሚፃረር ተግባር በመፈጸም ክስ ቀርቦባቸዋል። ጁባላንድ ባወጣችው መግለጫ የሶማሊያውን ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ “ሥልጣንን ካለ አግባብ በመጠቀም” ከሳለች፡፡ ፍርድ ቤቱም “ገለልተኝነት ይጎድለዋል”  ብላለች፡፡ ውዝግቡ የጀመረው ባለፈው ወር ሞቃዲሹ ላይ በተካሄደ ብሔራዊ የምክክር ስብሰባ ላይ ነበር። በስብሰባውም የፌዴራል መንግስት እና አንዳንድ ግዛቶች በመጪው ሰኔ 2017 የአካባቢ ምርጫ ለማካሄድ፣ በመስከረም ደግሞ የግዛቶች እና የፓርላማ ምርጫ ለማድረግ ተስማምተው ነበር። የጁባላንዱ መሪ ግን ምርጫውን በዛ ወቅት ለማካሄድ የሥልጣን ዘመንን ማራዘም ይጠይቃል በሚል ተቃውመዋል። አህመድ ማዶቤ በጁባላንድ ባለፈው ሰኞ በግዛቲቱ ፓርላማ በድጋሚ መሪ ሆነው ተመርጠዋል። የፌዴራል መንግስት ግን ድርጊቱን በማውገዝ በድጋሚ መመረጣቸውን እውቅና እንደማይሰጥ አስታውቋል። በሁለቱ ወገኖች መካከል ውጥረቱ ባየለበት ሁኔታ የፌዴራል መንግስቱ ወደ ጁባላንድ ሠራዊቱን ልኳል። በጁባላንድ የአፍሪካ ኅብረት ኃይል አካል የሆኑ የኢትዮጵያ እና የኬንያ ወታደሮች ይገኛሉ።

በዩጋንዳ በተከሰተ የመሬት ናዳ ቢያንስ 30 ሰዎች ሞተዋል ተባለ

በምሥራቃዊ ዩጋንዳ በተከሰተ የመሬት ናዳ ቢያንስ 30 የሚሆኑ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ባለሥልጣናቱ አክለውም የሟቾቹ ቁጥር ከተጠቀ
የአሜሪካ ድምፅ

በዩጋንዳ በተከሰተ የመሬት ናዳ ቢያንስ 30 ሰዎች ሞተዋል ተባለ

በምሥራቃዊ ዩጋንዳ በተከሰተ የመሬት ናዳ ቢያንስ 30 የሚሆኑ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ባለሥልጣናቱ አክለውም የሟቾቹ ቁጥር ከተጠቀሰውም ሊበልጥ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል። ላለፉት ጥቂት ቀናት በሀገሪቱ ከባድ ዝናብ ሲጥል የነበረ ሲሆን፣ ጎርፍ እና የመሬት ናዳ መከሰታቸውን የሚያሳዩ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ መንግሥት ብሔራዊ የአደጋ ማስጠንቀቂያ አውጇል። ከመዲናዋ ካምፓላ የአምስት ሰዓት ርቀት ላይ የምትገኘው ማሱጉ መንደር ትላንት ረቡዕ የመሬት ናዳው ከተከሰተባቸው መንደሮች አንዷ ስትሆን፣ በማኅበራዊ ሚዲያ የተጋሩ ምስሎች የአደጋውን አስከፊነት አሳይተዋል። የወርዳው ኮሚሽነር 30 ሰዎች ኅይወታቸው እንዳለፈ አስታውቀዋል። እስከአሁን የአንድ ሕፃንን ጨምሮ ስድስት አስከሬኖች መገኘታቸውንም ተናግረዋል። የአደጋውን ከባድነትና የሸፈነውን ስፋት በመመልከት በርካታ ሰዎች የደረሱበት እንደማይታወቅና ምናልባትም ናዳው ሥር ተቀብረው ሊሆን እንደሚችልም ስጋታቸውን ገልጸዋል። የዩጋንዳው ቀይ መስቀል ቃል አቀባይ በበኩሉ 13 አስከሬኖችን ማግኘታቸውንና አደጋውም በበርካታ መንደሮች መከሰቱን አስታውቀዋል።

«አቶ ጌታቸው ረዳ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ናቸው» - አቶ አማኑኤል አሰፋ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በእነ ዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራው ቡድን ባካሄደው ጉባኤ ከሥልጣን የተነሱ በመኾናቸው ፕሬዝደን
የአሜሪካ ድምፅ

«አቶ ጌታቸው ረዳ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ናቸው» - አቶ አማኑኤል አሰፋ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በእነ ዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራው ቡድን ባካሄደው ጉባኤ ከሥልጣን የተነሱ በመኾናቸው ፕሬዝደንትነታቸውን እንደማይቀበል፣ በቅርቡ በተካሄደው አወዛጋቢ የህወሓት ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ኾነው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ ተናገሩ። አቶ አማኑኤል ዛሬ መቐሌ ላይ በሰጡት መግለጫ አቶ ጌታቸውን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሲሉ ጠርተዋቸዋል። «የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት እና ወደ ኅበረተሰቡ የማቀላቀል ሥራ፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እየተሠራ አይደለም» ያሉት አቶ አማኑኤል ሂደቱን ተቃውመውታል። አቶ አማኑኤል ዛሬ ረቡዕ ኅዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ለብዙኀን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ህወሓትን በአመፅ ለመበተን ወጣቶች እያሰለጠኑ ናቸው ሲሉ ወንጅለዋል። በጉዳዩ ላይ ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ኮምዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ሆኖም የአስተዳደሩ ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ በቅርቡ፣ በሰጡት መግለጫ፣ በዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመራ የህወሓት ቡድን፣ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ሥራውን እንዳያከናውን ከማድረግ በተጨማሪ የወረዳ ምክር ቤቶች በመጠቀም በመንግሥት የተመደቡ አስተዳዳሪዎች እንዲነሱ እያደረገ ነው ፣ «ይህ መፈንቅለ መንግሥት” ነው » ሲሉ ከሰው ነበር። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ዕድሜ ጠገቡ የኒውዮርክ የምስጋና ቀን ሰልፍ ትዕይንት

አሜሪካውያን  በየዓመቱ አንድ መቶ ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በየዓመቱ በሚዘጋጀው የሜሲስ ምስጋና ቀን የሰልፍ ትዕይንት  ሲደሰቱ ኖረዋል። በነዚህ ዓመታት ውስጥ የ
የአሜሪካ ድምፅ

ዕድሜ ጠገቡ የኒውዮርክ የምስጋና ቀን ሰልፍ ትዕይንት

አሜሪካውያን  በየዓመቱ አንድ መቶ ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በየዓመቱ በሚዘጋጀው የሜሲስ ምስጋና ቀን የሰልፍ ትዕይንት  ሲደሰቱ ኖረዋል። በነዚህ ዓመታት ውስጥ የተቋረጠው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ብቻ ነበር። «ሜሲስ» በተባለው ታዋቂ ግዙፍ መደብር የሚዘጋጀው  ትዕይንት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሸማቾችን «የኛ» በሚል ስሜት ከመደብሩ ጋር ለማስተሳሰር ያለመ ዓመታዊ  በዓል ነው። የቪኦኤ ዘጋቢ ዶራ መኳር በኒው ዮርክ የሰልፉን ዝግጅት ተመልክታለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

ጭቆና እና ጥቃትን ተቋቁመው የሠሩ ጋዜጠኞች እውቅና ተሰጣቸው

ግጭቶችን ለተመለከቱ ዘገባዎች ከመሰማራት አንስቶ እስከ ሕጋዊ እንቅፋቶችና እሥራቶች፣ በመላው ዓለም በፕሬስ ነፃነት ላይ የተደቀነው አደጋ  እየጨመረ መጥቷል
የአሜሪካ ድምፅ

ጭቆና እና ጥቃትን ተቋቁመው የሠሩ ጋዜጠኞች እውቅና ተሰጣቸው

ግጭቶችን ለተመለከቱ ዘገባዎች ከመሰማራት አንስቶ እስከ ሕጋዊ እንቅፋቶችና እሥራቶች፣ በመላው ዓለም በፕሬስ ነፃነት ላይ የተደቀነው አደጋ  እየጨመረ መጥቷል። በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ የሠሩ አራት ጋዜጠኞች ባለፈው ሐሙስ በዓመታዊው ዓለም አቀፍ የፕረስ ነፃነት ሽልማት ላይ  እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ሊያም ስካት ከኒው ዮርክ የላከውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

በአፍሪካ የተፈናቃዮች ቁጥር በሦስት እጥፍ መጨመሩ ተገለጸ

በአፍሪካ የተፈናቃዮች ሰዎች ቁጥር በሦስት እጥፍ መጨመሩን እና 35 ሚሊዮን መድረሱን ዓለም አቀፉ የሀገር ውስጥ ተናቃዮች ተከታታይ ማዕከል ይፋ ያደረገው ዐዲስ
የአሜሪካ ድምፅ

በአፍሪካ የተፈናቃዮች ቁጥር በሦስት እጥፍ መጨመሩ ተገለጸ

በአፍሪካ የተፈናቃዮች ሰዎች ቁጥር በሦስት እጥፍ መጨመሩን እና 35 ሚሊዮን መድረሱን ዓለም አቀፉ የሀገር ውስጥ ተናቃዮች ተከታታይ ማዕከል ይፋ ያደረገው ዐዲስ ሪፖርት አመለከተ። ከእነዚህም ውስጥ ቁጥራቸው 32.5 ሚሊዮን የሚደርሱት በግጭት እና ሁከት ሳቢያ ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ የተገደዱ ናቸው። ትላንት ማክሰኞ የታተመው ሪፖርት አያይዞም፤ በአህጉሪቱ ያለውን በሃገር ውስጥ የመፈናቀል ፈተና ለመፍታት መንግሥታት የሚያደርጉትን ጥረት የሚበረታታ ቢሆንም፤ ‘በቂ አይደለም’ ብሏል። መሀመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ ያደረሰን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ታስረው የነበሩ መምህራን መፈታታቸውን ተናገሩ 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ በእስር ላይ የነበሩና 66 ይኾናሉ የተባሉ መምህራን መፈታታቸውን የዞኑ መምህራን ማኅበር ለአሜሪካ ድምጽ አስታወቀ
የአሜሪካ ድምፅ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ታስረው የነበሩ መምህራን መፈታታቸውን ተናገሩ 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ በእስር ላይ የነበሩና 66 ይኾናሉ የተባሉ መምህራን መፈታታቸውን የዞኑ መምህራን ማኅበር ለአሜሪካ ድምጽ አስታወቀ። የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ከእስር የተለቀቁ መምህራን፣ በእስር ላይ በነበሩበት ወቅት ድብደባ እንደተፈጸመባቸንና ሕክምና ተከልክለው እንደነበር ገለጹ። በኮሬ ዞን የሳርማሌ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ፣ ታሰሩ የተባሉ መምህራን ቁጥር በጣም አነስተኛ እንደነበር ገልጸው፣ «ሁሉም ከእስር ተለቀዋል» ብለዋል። ድብደባ ተፈጸመ የተባለውም ከ«እውነት የራቀ ነው» ብለዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

አፋር ክልል የሚገኙ መምህራን የሥራ ማቆም አድማ ላይ መኾናቸውን ተናገሩ

ክልሉ የተቋረጠ ሥራ የለም ሲል አስተባብሏ በአፋር ክልል ሃሪረሱ ዞን ዳዌ ወረዳ የደሞዝ ክፍያ እንደዘገየባቸውና ጥቅማ ጥቅም እንዳልተከፈላቸው ለአሜሪካ ድ
የአሜሪካ ድምፅ

አፋር ክልል የሚገኙ መምህራን የሥራ ማቆም አድማ ላይ መኾናቸውን ተናገሩ

ክልሉ የተቋረጠ ሥራ የለም ሲል አስተባብሏ በአፋር ክልል ሃሪረሱ ዞን ዳዌ ወረዳ የደሞዝ ክፍያ እንደዘገየባቸውና ጥቅማ ጥቅም እንዳልተከፈላቸው ለአሜሪካ ድምጽ የተናገሩ መምህራን፣ የሥራ ማቆም አድማ ላይ መኾናቸውን ተናገሩ። አድማ የተደረገው በ18 መደበኛ እና ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ባልታወቀ አማራጭ ት/ቤቶች ላይ መሆኑን የወረዳው መምህራን ማኅበር አስታውቋል። ክልሉ መጠነኛ የደመወዝ መዘግየት አጋጥሞት እንደነበር ለቪኦኤ ምላሽ የሰጠው፣ የአፋር ክልል መንግሥት የኮምዩኒኬሽንስ ቢሮ ፣ የወረዳ አመራሮች ከመምህራኑ ጋራ ውይይት ካደረጉ በኋላ የተቋረጠው የማማር ማስተማር እንቅስቃሴ ጥያቄው ከተነሳበት ከኅዳር 16 ቀን 2017ዓ.ም ጀምሮ ቀጥሏል ብሏል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን በተጓዳኝ ሥራዎች ላይ እየተሰማሩ ነው

በደመወዝ አለመከፈል፣ መዘግየትና መቆረጥ የተነሳ ችግር ውስጥ መግባታቸውን ለአሜሪካ ድምጽ የተናገሩ መምህራን፣ ኑሯቸውን ለመደጎም ጫማ መጥረግን ጨምሮ፣ ከ
የአሜሪካ ድምፅ

የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን በተጓዳኝ ሥራዎች ላይ እየተሰማሩ ነው

በደመወዝ አለመከፈል፣ መዘግየትና መቆረጥ የተነሳ ችግር ውስጥ መግባታቸውን ለአሜሪካ ድምጽ የተናገሩ መምህራን፣ ኑሯቸውን ለመደጎም ጫማ መጥረግን ጨምሮ፣ ከዘርፋቸው ውጪ በሆኑ ሌሎች ሥራዎች ላይ እየተሰማሩ መኾኑን ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ። ሦስት ዐዳዲስ ክልሎች ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ፣ ችግሮች እያጋጠሟቸው እንደሚገኙ ያረጋገጠው ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ፣ ችግሩ በበጀት እጥረት ምክንያት የተፈጠረ መኾኑን ለአሜሪካ ድምጽ አስታውቋል። የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበርም በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ መምህራን ችግር ላይ መኾናቸውን ጠቅሶ፣ መፍትሔ ለመፈለግም ከክልሎቹ ኃላፊዎች ጋራ መነጋገሩን አመልክቷል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

አውስትራሊያ አዳጊዎች ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ ልታደርግ ነው

የአውስትራሊያ የተወካዮች ም/ቤት ከ16 ዓመት በታች ያሉ አዳጊዎች ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚያግድ ሕግ አጸደቀ። ሕጉ በመቀጠል በሃገሪቱ የእንደራሴዎች
የአሜሪካ ድምፅ

አውስትራሊያ አዳጊዎች ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ ልታደርግ ነው

የአውስትራሊያ የተወካዮች ም/ቤት ከ16 ዓመት በታች ያሉ አዳጊዎች ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚያግድ ሕግ አጸደቀ። ሕጉ በመቀጠል በሃገሪቱ የእንደራሴዎች ም/ቤት (ሴኔት) ከጸደቀ በዓለም የመጀመሪያው ይሆናል። የተወካዮች ም/ቤቱ በ102 ድጋፍ እና 13 ተቃውሞ ድምጽ አጽድቆታል። በሃገሪቱ የሚገኙ ዋና ፓርቲዎች የደገፉት ሕግ፤ ቲክቶክ፣ ፌስቡክ፣ ስናፕቻት፣ ሬዲት፣ X እና ኢንስታግራም የመሰሉ መድረኮች አዳጊዎች ተጠቃሚ እንዳይሆኑ የማይከላከሉ ከሆነ እስከ 33 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ሕጉ በዚህ ሳምንት በሴኔቱም የሚጸድቅ ከሆነ፣ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎቹ የዕድሜ ገደቡን ተፈጻሚ የሚያደርጉበትን መላ ለመዘየድ አንድ ዓመት ይሰጣቸዋል። ከአንድ ዓመት ጊዜ በኋላ ግን ቅጣቱ ተፈጻሚ ይሆናል። የሃገሪቱ ዋና ዋና ፓርቲዎች ሕጉን በመደገፋቸው፣ በእንደራሴዎች ምክር ቤት  ሊጸድቅ እንደሚችል ይጠበቃል።

በቻይና ለረጅም ዓመታት ታስረው የነበሩ ሦስት አሜሪካውያን ተለቀቁ

በቻይና ለረጅም ዓመታት ታስረው የነበሩ ሦስት አሜሪካውያን መለቀቃቸውን ዋይት ሃውስ አስታውቋል። የባይደን አስተዳደር በመጨረሻዎቹ  የሥልጣን ዘመኑ ወራት ከ
የአሜሪካ ድምፅ

በቻይና ለረጅም ዓመታት ታስረው የነበሩ ሦስት አሜሪካውያን ተለቀቁ

በቻይና ለረጅም ዓመታት ታስረው የነበሩ ሦስት አሜሪካውያን መለቀቃቸውን ዋይት ሃውስ አስታውቋል። የባይደን አስተዳደር በመጨረሻዎቹ  የሥልጣን ዘመኑ ወራት ከቤጂንግ ጋራ የፈፀመው ዲፕሎማሲያዊ ስምምነት ነው ተብሏል። የአሜሪካ መንግሥት ማርክ ስዊዳን፣ ካይ ሊ እና ጃን ሊዩንግ የተባሉት ሦስቱ አሜሪካዊያን   ካለ አግባብ ተይዘው  ቆይተው አሁን ወደአገራቸው ለመመለስ በቅተዋል ሲል አስታውቋል። ቻይና በበኩሏ እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን የምናስተናግደው በሕጉ መሠረት ነው  ብላለች፡፡ ማርክ ስዊዳን ከአደንዛዥ ዕጽ ጋራ በተያያዘ በቀረበበት ክስ የሞት ቅጣት በመጠባበቅ ላይ የነበረ ሲሆን፣ ካይ ሊ እና ጃን ሊዩንግ ደግሞ በስለላ ተጠርጥረው ነበር የታሰሩት፡፡ በባይደን አስተዳደር የመጨረሻ ወራት ላይ ቤጂንግ ከአሜሪካ ጋራ የፈጸመችው ብዙም ያልተለመደ ዲፕሎማሲያዊ ስምምነት እንደሆነ ተነግሯል። አሜሪካውያኑ ከ3 እስከ 12 ዓመታት በቻይና እስር ቤቶች ማሳለፋቸውም ታውቋል።

VOA60 America - Millions of Americans travel for Thanksgiving holiday

The Thanksgiving holiday rush neared its full stride at U.S. airports on Wednesday, putting travelers' patience to the test. Security workers were expected to screen more than 2.8 million people on Tuesday and 2.9 million on Wednesday after handling more tha
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Millions of Americans travel for Thanksgiving holiday

The Thanksgiving holiday rush neared its full stride at U.S. airports on Wednesday, putting travelers' patience to the test. Security workers were expected to screen more than 2.8 million people on Tuesday and 2.9 million on Wednesday after handling more than 2.5 million people on Monday.

VOA60 World - International Criminal Court asked for arrest warrant for head of Myanmar’s military

Netherlands: In a video released Wednesday, the International Criminal Court’s chief prosecutor asked judges to issue an arrest warrant for the head of Myanmar’s military regime, Senior Gen. Min Aung Hlaing, for crimes committed against the country’s Ro
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - International Criminal Court asked for arrest warrant for head of Myanmar’s military

Netherlands: In a video released Wednesday, the International Criminal Court’s chief prosecutor asked judges to issue an arrest warrant for the head of Myanmar’s military regime, Senior Gen. Min Aung Hlaing, for crimes committed against the country’s Rohingya Muslim minority.

VOA60 Africa - Voters line up in Namibia in presidential and parliamentary elections

Namibia: Voters waited in long queues outside polling stations in the capital Windhoek on Wednesday morning to cast ballots for a new president and parliament in what could be a tough election to win for the ruling SWAPO party.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Voters line up in Namibia in presidential and parliamentary elections

Namibia: Voters waited in long queues outside polling stations in the capital Windhoek on Wednesday morning to cast ballots for a new president and parliament in what could be a tough election to win for the ruling SWAPO party.

በሚያንማር መሪዎች ላይ የእስር ማዘዣ እንዲወጣ ተጠየቀ

የዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት ዋና ዐቃቤ ሕግ፣ የችሎቱ ዳኞች የሚያንማር ወታደራዊ አገዛዝ መሪ ላይ የእስር  ትዕዛዝ እንዲያወጡ ጠይቀዋል። ትዕዛዙ እንዲወጣ የ
የአሜሪካ ድምፅ

በሚያንማር መሪዎች ላይ የእስር ማዘዣ እንዲወጣ ተጠየቀ

የዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት ዋና ዐቃቤ ሕግ፣ የችሎቱ ዳኞች የሚያንማር ወታደራዊ አገዛዝ መሪ ላይ የእስር  ትዕዛዝ እንዲያወጡ ጠይቀዋል። ትዕዛዙ እንዲወጣ የተጠየቀው በሚያንማር በሚገኙ የሮሄንጂያ ሙስሊም ሕዳጣን ማኅበረሰብ ላይ መፈናቀል እና ሰቆቃን ጨምሮ የሰብአዊ ወንጀል ተፈጽሟል በሚል ነው። እ.አ.አ በ2021 በኦን ሳን ሱ ቺ ላይ መፈንቅለ መንግሥት አካሂደው ሥልጣን የተቆናጠጡት ጀኔራል ሚን ኦንግ ላይንግ፣ በሮሄንጂያ ሙስሊም ሕዳጣን ማኅበረሰብ ላይ መፈናቀል እና ሰቆቃ ፈጽመዋል የሚል ክስ ይቀርብባቸዋል። ጀኔራሉ፤ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የዘር ማጽዳት ተብሉ ከተገለጸው ዘመቻ ለማምለጥ ወደ ጎረቤት ባንግላዴሽ እንዲሸሹ አስገድደዋል የሚል ክስ ይቀርብባቸዋል። ዘመቻው መጠነ ሰፊ የመድፈር ጥቃት፣ ግድያ እና መኖሪያ ቤቶችን ማቃጠልን የጨመረ ነው ተብሏል። በባንግላዴሽ በሚገኝ የስደተኞች ካምፕ ሆነው መግለጫ የሰጡት፣ የዓለም አቀፉ ወንጀል ችሎት ዋና ዐቃቤ ሕግ ካሪም ካን፣ በሚያንማር መሪዎች ላይ ተጨማሪ የእስር ትዕዛዞች እንዲወጡ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል።

የሀዋሳ ከተማ የነዳጅ እጥረትና የተጠቃሚዎች ምሬት

በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ሕገ ወጥ የነዳጅ ንግድ በመስፋፋቱ በከተማዋ ለቀናት የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ተጠቃሚዎች ቅሬታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ። በከተማ
የአሜሪካ ድምፅ

የሀዋሳ ከተማ የነዳጅ እጥረትና የተጠቃሚዎች ምሬት

በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ሕገ ወጥ የነዳጅ ንግድ በመስፋፋቱ በከተማዋ ለቀናት የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ተጠቃሚዎች ቅሬታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ። በከተማው በተለይም በማደያ በ93 ብር ገደማ የሚሸጠው አንድ ሊትር ቤንዚን በአሳቻ ሰዓት ከማደያ እየወጣ በድብቅ እስከ 250 እየተሸጠ መኾኑን ገልጸዋል። የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ፣ በሕገ ወጥ መንገድ ተሰማርተው ነዳጅ ሲሸጡ እና ሲያዘዋወሩ ተገኙ ያላቸውን 34 ሰዎች ማሰሩን አስታውቋል። እጥረቱ የተከሰተው በአቅርቦት ማነስ እና በሕገ ወጥ ንግድ ምክኒያት መኾኑንም ገልጿል። በተጨማሪም ሁለት የንግድ እና ገበያ ልማት ባለሞያዎች መታሰራቸውንም የተናገሩት ምክትል ኮሚሽነር ካሳ ጫቦ፣ አምስት ፖሊሶች ደግሞ የጹሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ጨምረው ተናግረዋል። የክልሉ አድማ በታኝ ፖሊስ በከተማው የሚገኙ ማደያዎችን እየተቆጣጠረ ሲኾን በክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የሚመራ የቁጥጥርና ክትትል ቡድን መቋቋሙን የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስ ገልጸዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

«የዋጋ ንረትን ለማስተካከል ያግዛል» የተባለው አዲሱ የብሄራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ

የኢትዮጵያ መንግሥት ከባንክ በሚበደረው የገንዘብ መጠንና የጊዜ ገደብ በሚመለከት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ገደብ መቀመጡ በሀገሪ
የአሜሪካ ድምፅ

«የዋጋ ንረትን ለማስተካከል ያግዛል» የተባለው አዲሱ የብሄራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ

የኢትዮጵያ መንግሥት ከባንክ በሚበደረው የገንዘብ መጠንና የጊዜ ገደብ በሚመለከት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ገደብ መቀመጡ በሀገሪቱ የተከሰተውን የዋጋ ንረት ሊያረጋጋ ይችላል ሲሉ የንግድና ምጣኔ ሐብት ባለሞያዎች ተናገሩ። በ2000 ዓ/ም ተሻሽሎ እስካኹን በሥራ ላይ ያለው፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዐዋጅ፣ መንግሥት በፈለገው መጠን ገንዘብ እንዲበደር የሚፈቅድ በመኾኑ «ገንዘብ ያለገደብ ገበያ ላይ እንዲዘዋወርና የኑሮ ውድነት እንዲንር አስተዋፆ አድርጓል» የሚሉት ባለሙያዎቹ ኾኖም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት እየተደረገበት የሚገኘው፣ ረቂቅ አዋጅ መንግሥት ከባንኩ በሚወስደው ብድር ላይ የመጠን ገደብ የሚያስቀምጥ አንቀጽ መካተቱ ተገቢ ነው" ብለው ያምናሉ።

እስራኤል እና ሄዝቦላ ተኩስ አቆሙ

እስራኤል እና ሄዝቦላ ከዛሬ ረቡዕ ማለዳ ጀምሮ የተኩስ አቁም አድርገዋል። በሁለቱ መካከል የተደረሰው የተኩስ ማቆም በጋዛም ሌላ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲ
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል እና ሄዝቦላ ተኩስ አቆሙ

እስራኤል እና ሄዝቦላ ከዛሬ ረቡዕ ማለዳ ጀምሮ የተኩስ አቁም አድርገዋል። በሁለቱ መካከል የተደረሰው የተኩስ ማቆም በጋዛም ሌላ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈጸም መንገድ እንደሚከፍት የአሜሪካ እና የፈረንሳይ መሪዎች ተስፋ አድርገዋል። የተኩስ አቁሙ ዜና እንደተሰማ በጦርነቱ ምክንያት ደቡባዊ ሌባኖስን ለቀው እንዲወጡ የተደረጉ ነዋሪዎች ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው በመኪና ሲተሙ ተስተውሏል። የእስራኤል ሠራዊት ግን ሰዎች ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ወደ ተላለፈባቸው መንደሮች እንዳይመለሱ አሳስቧል። አሜሪካ እና ፈረንሣይ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲሆን ቁልፍ ሚና መጫወታቸው ሲነገር፣ የእስራኤል የፀጥታ ካቢኔም ትላንት ማምሻውን አጽድቆታል። የአሜሪካው ፕሬዝደነት ጆ ባይደን ተኩስ ማቆሙ በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን “ሁከት ለማስቆም ወሳኝ እርምጃ ነው” ብለዋል። የኢራን ተቀጥላ የሆኑት፣ ሌባኖስ የሚገኘው ሄዝቦላ እና ጋዛ የሚገኘው ሐማስ “ትልቅ ዋጋ ከፍለዋል” ሲሉ አክለዋል ባይደን። ስምምነቱ “ቋሚ የተኩስ ማቆም እንዲሆን ተደርጎ የተነደፈ ነው” ብለዋል ባይደን። ሄዝቦላ እስራኤልን ማጥቃቱን ለማቆም በመስማማቱ “ሐማስ ግልጽ የሆነ አማራጭ ቀርቦለታል። ያለው ብቸኛ መውጫ መንገድ አሜሪካውያንን ጨምሮ ያገታቸውን ሰዎች መልቀቅ ነው” ሲሉ ተናግረዋል ባይደን። በመጪዎቹ ቀናት አሜሪካ ከቱርክ፣ ግብጽ፣ ካታር፣ እስራኤል እና ከሌሎችም ጋራ በመሆን በጋዛ ተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ ግፊት እንደሚያደርጉ ባይደን ጠቁመዋል።  

በአማራ ክልል ተመላሽ ፍልሰተኞች ለዳግም ፍልሰት መዳረጋቸውን ገለጹ

ከተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ወደ አማራ ክልል ተመልሰው የነበሩ ሰዎች ለዳግም ፍልሰት መዳረጋቸውን ተናገሩ። ቪኦኤ ያነጋገራቸው፣ ደቡብና ሰሜን ወሎ
የአሜሪካ ድምፅ

በአማራ ክልል ተመላሽ ፍልሰተኞች ለዳግም ፍልሰት መዳረጋቸውን ገለጹ

ከተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ወደ አማራ ክልል ተመልሰው የነበሩ ሰዎች ለዳግም ፍልሰት መዳረጋቸውን ተናገሩ። ቪኦኤ ያነጋገራቸው፣ ደቡብና ሰሜን ወሎ የሚገኙ ከስደት ተመላሾች፣ መንግሥት ሊያቋቁማቸውን የገባውን ቃል ባለመጠበቁ፣ በድጋሚ ለመሄድ ዝግጅት ላይ መኾናቸውን ተናግረዋል። በተጨማሪም በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ተንቀሳቅሰው መሥራት አለመቻላቸው ችግሩን እንዳባባሰው ገልጸዋል። የአማራ ክልል ሥራና ሥልጠና ቢሮ ከክልሉ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚደረገው ፍልሰት መባባሱን አረጋግጦ፣ ተመላሾችን ለማቋቋም የአቅም ውስንነት መኖሩን አስታውቋል። ዝርዝሩን ከተያይዘው ፋይል ይከታተሉ።

የአቶ ታዬ ደንደአን ተጨማሪ የመከላከያ ምስክር ለመስማት ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ 

የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ደ’ኤታ አቶ ታዬ ደንደአ መከላከያ ምስክሮች የመጥሪያ ትዕዛዝ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው፣ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደ
የአሜሪካ ድምፅ

የአቶ ታዬ ደንደአን ተጨማሪ የመከላከያ ምስክር ለመስማት ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ 

የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ደ’ኤታ አቶ ታዬ ደንደአ መከላከያ ምስክሮች የመጥሪያ ትዕዛዝ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው፣ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሕገ-መንግስትና ሕገ-መንግሥት ሥርዓት ችሎት፣ የተከሳሹን ቀሪ የመከላከያ ምስክሮችን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። “የሰላም ሚኒስቴር ደ’ኤታ ኾነው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ ፀረ ሰላም ኀይሎች ጋራ በመተሳሰር ለጥፋት ተልእኮ በኅቡእ ተንቀሳቅሰዋል፤” በሚል ክስ የተመሠረተባቸው አቶ ታዬ ደንዳአ ቀሪ ምስክሮቻቸውን እንዲያቀርቡ መጥሪያ ለመጻፍ፣ ለዛሬ ኅዳር 17፣ 2017 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቶ የነበረ ሲኾን፣ ፍርድ ቤቱ ለምስክሮቹ መጥሪያ እንዲጻፍ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ተከሳሹ ከዚህ ቀደም የምስክሮቻቸው ማንነት በይፋ እንዳይገለጽ በጠየቁት መሰረት መጥሪያ እንዲጻፍ ትዕዛዝ የተሰጠው ለማን እንደኾነ በፍርድ ቤቱ በይፋ አልተገለጸም። አቶ ታዬ ጠበቃ የማግኘት መብት መነፈጋቸውን ጨምሮ በእስር ቤት እንደተፈጸመባቸው የገለጹት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አጣርቶ ለፍርድ ቤት እንዲያቀርብ ጥቅምት ስምንት ትዕዛዝ ተሰጥቶት ነበር። በሌላ በኩል በዛሬው ችሎትም ያለጠበቃ የቀረቡት አቶ ታዬ፣ ከዚህ ቀደም አቅርበዋቸው የነበሩትን ዐቃቤ ሕግ ክስ ሳይ መሰርትባቸው ለወራት እንዳቆያቸዉ፣ ቤተሰባቸዉ ላይ እንግልቶች መድረሱንና፣ የጥብቅና አገልግሎት ሊሰጧቸው የነበሩ ጠበቆችን የሀገሪቱ ደህንነት መሥሪያ ቤት በማስፈራራት የሕግ ድጋፍ እንዳያገኙ መከልከላቸውን በተመለከተ ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልጸው በድጋሚ አቤቱታ አቅርበዋል። ለተከሳሹ አቤቱታ ምላሽ የሰጡት የፍርድ ቤቱ የመሐል ዳኛም ‘ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ይህን ጉዳይ እንዲያጣራ ትእዛዝ ማስተላለፉን ገልፀዉ፣ ኮሚሽኑም ይህንኑ የማጣራት ሥራውን በ30 ቀን ጨርሶ እንደሚያቀርብ ምላሽ መስጠቱን" አስታውሰዋል። ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በሱዳን ጦርነት የሟቾቹ ቁጥር ከተገመተውም በላይ እንደሆነ አዲስ ጥናት አመለከተ

በሱዳን ጦርነት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ብዛት ከዚህ በፊት ከተገመተው ሊበልጥ እንደሚችል አንድ ዐዲስ ጥናት አመለከተ። ግጭቱ 11 ሚሊዮን ሰዎችን ከመኖሪያቸው ሲ
የአሜሪካ ድምፅ

በሱዳን ጦርነት የሟቾቹ ቁጥር ከተገመተውም በላይ እንደሆነ አዲስ ጥናት አመለከተ

በሱዳን ጦርነት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ብዛት ከዚህ በፊት ከተገመተው ሊበልጥ እንደሚችል አንድ ዐዲስ ጥናት አመለከተ። ግጭቱ 11 ሚሊዮን ሰዎችን ከመኖሪያቸው ሲያፈናቅል፣ በዓለም አስከፊ የተባለውን ረሃብ ማስከተሉን ጥናቱ ጠቁሟል። ሄንሪ ሪጅዌል የላከው ዘገባ ነው። ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በኬኒያ የንብ ርባታ ማኅበረሰቦች የአየር ንብረት ለውጡን እንዲቋቋሙ እየረዳ ነው

የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ጥበቃ መርሃ ግብር በሞቃታማ አካባቢዎች የሚኖሩ ማኅበረሰቦች በዓለም ሙቀት መጨመር ከሁሉም በላይ ተጎጂዎች መሆናቸውን ይናገ
የአሜሪካ ድምፅ

በኬኒያ የንብ ርባታ ማኅበረሰቦች የአየር ንብረት ለውጡን እንዲቋቋሙ እየረዳ ነው

የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ጥበቃ መርሃ ግብር በሞቃታማ አካባቢዎች የሚኖሩ ማኅበረሰቦች በዓለም ሙቀት መጨመር ከሁሉም በላይ ተጎጂዎች መሆናቸውን ይናገራል፡፡ ተደጋጋሚ ድርቅ እና የጎርፍ መጥለቅለቅ እንደ እርሻ እና የእንስሳት እርባታ ያለውን የኖረ መተዳደሪያቸውን የማይቻል አድርገውታል። በኬንያ ያሉ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች ታዲያ እንደነዚህ ያሉ ማህበረሰቦች ተለዋዋጭ የአየር ሁኔታን ለመቋቋም እንዲረዳቸው፣ እንደ ንብ እርባታ የመሳሰሉ በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ አማራጭ መተዳደሪያዎችን እንዲያዳብሩ በመርዳት ላይ ናቸው። ጁማ ማጃንጋ ከጋርሰን፣ ኬንያ ዘግቦበታል፡፡ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

VOA60 America - Trump pledges immediate tariffs on goods from Mexico, Canada and China

President-elect Trump pledged Monday to quickly impose tariffs on China, Mexico and Canada – the country’s top three trade partners. In a post on his Truth Social account Trump said he will impose a 25 percent tariff on all products coming into the U.S. f
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Trump pledges immediate tariffs on goods from Mexico, Canada and China

President-elect Trump pledged Monday to quickly impose tariffs on China, Mexico and Canada – the country’s top three trade partners. In a post on his Truth Social account Trump said he will impose a 25 percent tariff on all products coming into the U.S. from Mexico and Canada.

VOA60 World - Heavy rains make temporary shelters uninhabitable for displaced people in Gaza

Heavy rains and falling temperatures are making tents and other temporary shelters uninhabitable for displaced people in Gaza. As of Monday, nearly 10,000 tents in the coastal enclave had been swept away by flooding, according to officials
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Heavy rains make temporary shelters uninhabitable for displaced people in Gaza

Heavy rains and falling temperatures are making tents and other temporary shelters uninhabitable for displaced people in Gaza. As of Monday, nearly 10,000 tents in the coastal enclave had been swept away by flooding, according to officials

የሕንዱ ግዙፍ የታዳሽ ኃይል ማመንጫ አዳኒ በዩናይትድ ስቴትስ በጉቦ ቅሌት ተወነጀለ

የሕንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ የታዳሽ የኃይል ምንጭ ግንባታ እቅድ ዋና ደጋፊ የሆኑት ቢሊየነሩ ጓታም አዳኒ፤ በዓለም ግዙፉ ይሆናል ለተባለው የታዳሽ
የአሜሪካ ድምፅ

የሕንዱ ግዙፍ የታዳሽ ኃይል ማመንጫ አዳኒ በዩናይትድ ስቴትስ በጉቦ ቅሌት ተወነጀለ

የሕንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ የታዳሽ የኃይል ምንጭ ግንባታ እቅድ ዋና ደጋፊ የሆኑት ቢሊየነሩ ጓታም አዳኒ፤ በዓለም ግዙፉ ይሆናል ለተባለው የታዳሽ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክታቸው የፈረንሳዩን ቶታል ኢነርጂ እና የካታር ኢንቨስትመንት ባለስልጣንን አጋርነት አግኝተዋል። በተለየ ዓይን የሚያዩት የኩባንያቸው ዋነኛው ውጥን ‘አዳኒ ግሪን’ የተባለው በሕንዷ የምዕራብ ጉጅራት ግዛት የሚገኘው ፕሮጀክት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2030 ሲጠናቀቅ 50 ጊጋ ዋት ኃይል ማለትም ሕንድ በእቅድ ከያዘችው አጠቃላይ የንፁህ ኃይል ምርት ‘አንድ አስረኛውን ያህል ያመነጫል’ ተብሎ ይጠበቃል። ይሁን እንጂ ያ እቅድ አሁን፤ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ አዳኒ እራሳቸው፣ የወንድማቸው ልጅ እና የኩባንያቸው ዋና ድሬክተር ሳጋር አዳኒ፤ እንዲሁም መራሄ ድሬክተሩ ቭኔት ኤስ ጃይን፤ ለህንድ ኃይል የሚያቀርብ የተቋራጭ ሥራ ኮንትራት ለማግኘት የ265 ሚሊዮን ዶላር ጉቦ በመስጠት እና የአሜሪካ ባለ ኃብቶችን በማሳሳት ወንጀሎች በቀረቡባቸው ክሶች መሰናክል ገጥሞታል። የክሱ ዜና እንደተሰማም፣ የአዳኒ ግሪን የዎል ስትሪት ገበያ የአክሲዮን (ስቶክ) ዋጋ 36 በመቶ በማሽቆልቆሉ፣ ከገበያ ዋጋው 9ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር አጥቷል። ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የቀረበበትን ክስ ‘መሠረተ ቢስ’ ሲል ውድቅ ያደረገው ‘አዳኒ ግሩፕ’ በበኩሉ ይህንን ለመቀልበስ ‘ሁሉንም የሕግ አማራጮች እጠቀማለሁ’ ብሏል ። ይሁን እንጂ ሁኔታው ለታዳሽ ኃይል ግንባታ ፕሮጀክቱ ማቀላጠፊያ የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ገንዘብ የማሰባሰብ ጥረቱን ያወሳስበዋል ተብሎ ተገምቷል።

‘የስኳር በሽታ’ በእርግጥ ምንድነው?

በልማድ አጠራር ‘የስኳር በሽታ’ በመባል የሚታወቀው ይህ የሕመም ዓይነት ሊያስከትል የሚችላቸውን ውስብስብ የጤና ችግሮች ለመከላከል ወይም ለማስቀረት ይቻል
የአሜሪካ ድምፅ

‘የስኳር በሽታ’ በእርግጥ ምንድነው?

በልማድ አጠራር ‘የስኳር በሽታ’ በመባል የሚታወቀው ይህ የሕመም ዓይነት ሊያስከትል የሚችላቸውን ውስብስብ የጤና ችግሮች ለመከላከል ወይም ለማስቀረት ይቻል ይሆን? ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተደረሰባቸው ያሉ ከበሽታው ጋር የተዛመዱ ሁኔታዎች ካሁን ቀደም ስለሕመሙ ይታመኑ የነበሩ እውነታዎችን ጭምር በእጅጉ እየቀየሩ መሆናቸው ይነገራል። "ለመሆኑ ከስኳር በሽታ ሙሉ በሙሉ ሊዳን ይችላል?” ለሚለው ጥያቄ መልሱ “አዎንም፣ አይደለምም፤ ነው” የሚሉን ሞያዊ ትንታኔውን የሰጡን የውስጥ ደዌ እና የኢንዶክሪኖሎጂ ልዩ ሕክምና ባለ ሞያው ዶ/ር አቤል ተካ ናቸው። ”‘ኢንሱሊን’ የተባለውን ሰውነት የሚያመነጨውን ንጥረ ነገር የሰውነት አካላት በአግባቡ መጠቀም የማይችሉበት ሁኔታ እንዴት እንደሚፈጠር በወጉ መረዳት፤ የተለያዩ ውስብስብ ችግሮች የሚያስከትለውን የስኳር በሽታ ምንነት ለመረዳትም ሆነ፤ በሽታውን ለማከም በሚሰጠው ሕክምና እና ሕመምተኛው በራሱ ሊያደርጋቸው በሚችላቸው ጥረቶች አመርቂ ውጤት ለማግኘት ወሳኝ ነው” ይላሉ። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በደቡብ ሱዳን ከ2 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል

በደቡብ ሱዳን 2 ሚሊዮን የሚደርሱ ህጻናት እና 1 ሚሊዮን ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች ለከፋ የምግብ እጦት እየተጋለጡ መሆኑን ገልጾ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አ
የአሜሪካ ድምፅ

በደቡብ ሱዳን ከ2 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል

በደቡብ ሱዳን 2 ሚሊዮን የሚደርሱ ህጻናት እና 1 ሚሊዮን ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች ለከፋ የምግብ እጦት እየተጋለጡ መሆኑን ገልጾ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስጠንቅቋል። ደካማ የንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ የንፅህና አጠባበቅ እና የበሽታ መስፋፋት ቀውሱን ማባባሱን ቀጥሏል። ሺላ ፖኒ ከጁባ ከደቡብ ሱዳን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በጀልባ መገልበጥ አደጋ ከ20 በላይ ፍልሰተኞች ማዳጋስካር የባህር ዳርቻ ላይ ሞቱ

ፍልሰተኞች የያዙ ሁለት ጀልባዎች ማዳጋስካር ባህር ዳርቻ ላይ ተገልብጠው 24 ፍልሰተኞች ህይወታቸው ማለፉን የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌይስ አስታ
የአሜሪካ ድምፅ

በጀልባ መገልበጥ አደጋ ከ20 በላይ ፍልሰተኞች ማዳጋስካር የባህር ዳርቻ ላይ ሞቱ

ፍልሰተኞች የያዙ ሁለት ጀልባዎች ማዳጋስካር ባህር ዳርቻ ላይ ተገልብጠው 24 ፍልሰተኞች ህይወታቸው ማለፉን የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌይስ አስታወቁ። ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ሶማሊያውያን መኾናቸው ተገልጿል፡፡ በሃሩን ማሩፍ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Get more results via ClueGoal