በዐድዋ ከተማ አንዲት አዳጊን አግተው በመግደል ጥፋተኛ የተባሉ ሁለት ተከሳሾች ሞትና ዕድሜ ልክ ተፈረደባቸው
newsare.net
ትግራይ ክልል ውስጥ ዐድዋ ከተማ፣ አንዲት አዳጊን አግተው በመውሰድ መግደላቸው በፍርድ ቤት ተረጋግጦ “ጥፋተኛ” የተባሉ ሁለት ተከሳሾች፣ አንደኛው በሞት አንበዐድዋ ከተማ አንዲት አዳጊን አግተው በመግደል ጥፋተኛ የተባሉ ሁለት ተከሳሾች ሞትና ዕድሜ ልክ ተፈረደባቸው
ትግራይ ክልል ውስጥ ዐድዋ ከተማ፣ አንዲት አዳጊን አግተው በመውሰድ መግደላቸው በፍርድ ቤት ተረጋግጦ “ጥፋተኛ” የተባሉ ሁለት ተከሳሾች፣ አንደኛው በሞት አንደኛው ደግሞ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ፣ ዛሬ ኅዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም. የዋለው ችሎት ፈረደ። በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን ዐድዋ ከተማ መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ ከቤት ወጥታ የቋንቋ ትምሕርት ወደ ምትከታተልበት ትምሕርት ቤት በማምራት ላይ የነበረችን አንዲት አዳጊ፣ በተለምዶ ባጃጅ ተብሎ በሚጠራ ባለ ሦስት እግር ተሽከካሪ በመጠቀም አግተው ወስደዋታል፣ በኋላም ገድለዋታል በሚል ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት ተከሳሾች ዛሬ ተፈርዶቻቸዋል። የመቐለ ዞን ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኞ ኅዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም. በዋለው ችሎት፣ የ16 ዓመት አዳጊ ማኅሌት ተኽላይን በመግደል ተከሰውና ጥፋተኛ ተብለው የፍርድ ውሳኔያቸውን ለመጠባበቅ ለዛሬ ተቀጥረው ከነበሩት ሁለት ተከሳሾች፣ አንደኛው የ24 ዓመት ዓወት ነጋሲ ሓጎስ ሞት ሲፈረድበት፣ ሁለተኛው የ20 ዓመቱ ናሆም ፍፁም ኃይሉ ደግሞ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። Read more