ቲክ ቶክ ለጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ እንደሚል አሳወቀ
newsare.net
በዋሽንግተን የሚገኘው የፌደራል ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ትላንት አርብ ታዋቂው የማኅበራዊ መገናኛ መተግበሪያ ቲክ ቶክ የተወሰነ ድርሻውን ቻይናዊ ላልሆነ ባለቲክ ቶክ ለጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ እንደሚል አሳወቀ
በዋሽንግተን የሚገኘው የፌደራል ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ትላንት አርብ ታዋቂው የማኅበራዊ መገናኛ መተግበሪያ ቲክ ቶክ የተወሰነ ድርሻውን ቻይናዊ ላልሆነ ባለቤት እንዲሸጥ አሊያም በቀጣይ ወር ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እንዲዘጋ የሚያስገድድ ህግ አፀድቋል። ፍርድ ቤቱ ቲክ ቶክ ለብሔራዊ ደኅንነት አደጋ እንዳለው በፌዴራል መንግሥት የቀረቡት “አሳማኝ”ክርክሮችን ለውሳኔው መሰረት መሆናቸውን አስታውቋል። የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ቲክ ቶክ የተጠቃሚዎቹ ግላዊ መረጃዎችን በብዛት በመሰብሰቡ፣እንዲሁም የቻይና መንግስት የሚቆጣጠረ ባይትዳንስ ኩባንያ መተዳደሩ ለአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት ልዩ አደጋ ያመጣል በሚል ተከራክሯል። ቲክቶክ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ብይን ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ እንደሚል ወዲያውኑ ምላሽ ሰጥቷል። ኩባንያው በድረ-ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫም “ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአሜሪካውያንን የመናገር መብት በመጠበቅ ረገድ የተረጋገጠ ታሪክ አለው፤ እናም በዚህ አስፈላጊ ህገ-መንግስታዊ ጉዳይ ላይም ይኸንኑ ያደርጋሉ ብለን እንጠብቃለን” ብሏል። የፍርድቤቱ ውሳኔ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በአለምአቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሆነ እድገት ያስመዘገበውን፤ እና 170 ሚሊዮን የሚደርሱ አሜሪካውያን በመደበኛነት የሚጠቀሙትን የማኅበራዊ መገናኛ እንዲቋረጥ ሊያደርግ የሚችል ሲሆን በተለይም በመተግበሪያው ላይ የተለያዩ ይዘቶችን ለሚያቀርቡ እና ኑሯቸውን በመተገበሪያው የሚደግፉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካውያንን ከተመልካቾቻቸው የሚያቆራርጥ ነው። መጭው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም የቲክቶክ እገዳን ሲደግፉ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ሃሳባቸውን በመቀየር ስራ ሲጀምሩ የመጀመሪያው እርምጃቸው መተግበሪያውን ማዳን እንደሚሆን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ይህን ለማድረግ ምን ዓይነት አማራጮች ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ግልጽ አይደለም። Read more