ዩክሬን ከዴንማርክ ኤፍ 16 ተዋጊ ጄቶችን መረከቧን አስታወቀች
newsare.net
ዴንማርክ ለሁለተኛ ጊዜ የኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች ወደ ለዩክሬን መለገሷን ፕሬዚዳንት ቮሎደሚር ዘለንስኪ አስታውቀዋል። በተጨማሪም ዛሬ ቅዳሜ ፕሬዚዳንቱ ወደ ፓሪዩክሬን ከዴንማርክ ኤፍ 16 ተዋጊ ጄቶችን መረከቧን አስታወቀች
ዴንማርክ ለሁለተኛ ጊዜ የኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች ወደ ለዩክሬን መለገሷን ፕሬዚዳንት ቮሎደሚር ዘለንስኪ አስታውቀዋል። በተጨማሪም ዛሬ ቅዳሜ ፕሬዚዳንቱ ወደ ፓሪስ በመጓዝ በፈረንሳይ ከከፍተኛ ፖለቲከኞች እና ታላላቅ ሹማምንቶች ጋር ተገናኝተዋል። ዘለንስኪ በቴሌግራም በላኩት መልዕክታቸው ዴንማርክን ያወደሱ ሲሆን በሌሎች አጋሮቻቸው ዘንድ ቁርጠኝነት ባለመኖሩ ማዘናቸውን ገልጸዋል። “በዴንማርክ የተለገሱን የመጀመሪያዎቹ አውሮፕላኖች ህዝቦቻችንን እና መሠረተ ልማቶቻችንን ለመታደግ በሩስያ ላይ ሚሳኤሎችን እየጣሉ ነው።” ያሉ ሲሆን አያይዘውም “አሁን የአየር ኃይላችን ይበልጥ ተጠናክሯል፤ ሁሉም አጋሮች ይህን ያህል ቁርጠኝነት ቢኖራቸው ኖሮ የሩሲያን ሽብር ማቆም በቻልን ነበር” ብለዋል። የዘለንስኪ መግለጫ የወጣው ሩሲያ በዛፖሬዢያ ግዛት በፈጸመችው ጥቃት አስር ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የሀዘን አዋጅ በታወጀበት በዚህ ወቅት ነው። የአካባቢውን አገልግሎት መስጫ ተቋም ላይ ያረፈው የሩሲያ ጥቃት ሁለት ህጻናትን ጨምሮ 24 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የአካቢው ሀገረ ገዥ ኢቫን ፌዶሮቭ አስታውቀዋል። ዘለንስኪ ከጥቃቱ ጋር አያይዘው ንግግር ባደረጉበት ወቅት የሩሲያው ፕሬዚዳንት ‘እውነተኛ ሰላም’ አይሹም ሲሉ ወንጅለዋል። በጎርጎርሳውያኑ 2019 ከደረሰው ከባድ የእሳት ቃጠሎ በኋላ የኖትር ዳም ካቴድራል እድሳትን እና በድጋሚ ለጎብኚዎች ክፍት መሆንን ለማክበር በፓሪስ በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ የታደሙት ዘለስኪይ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ጨምሮ ከሌሎች የዓለም መሪዎች ጋር ዛሬ ቅዳሜ ይገናኛሉ። በስነ ስርዓቱ ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ይታደማሉ ተብሎ ከሚጠበቁ እንግዶች መካከል አንዱ ናቸው። የአውሮፓ መሪዎች መጪውን መሪ ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው እና ሥስት ዓመታት በፈጀው ወረራ ላይ ለዩክሬን ድጋፍ ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ለማሳመን ይፈልጋሉ ። በመርሃግብሩ ላይ ትራምፕ ከዘለንስኪ ጋር ይገናኙ እንደሆነ እስካሁን ድረስ ግልጽ አልተደረገም። Read more