የሶሪያ አማጽያን በፍጥነት ከተሞችን መቆጣጠራቸውን ቀጥለዋል
newsare.net
የሶሪያ አማጽያን የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን የ24 ዓመት አገዛዝ ለመደምሰስ በምዕራባዊ ሶሪያ ሆምስ ግዛት ዙሪያ ግስጋሴያቸውን አበርትተው ቀጥለዋል። አማየሶሪያ አማጽያን በፍጥነት ከተሞችን መቆጣጠራቸውን ቀጥለዋል
የሶሪያ አማጽያን የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን የ24 ዓመት አገዛዝ ለመደምሰስ በምዕራባዊ ሶሪያ ሆምስ ግዛት ዙሪያ ግስጋሴያቸውን አበርትተው ቀጥለዋል። አማጽያኑ ከሳምንት በፊት አሌፖን ዘልቀው ከገቡበት ጊዜ አንስቶ፣ በመላ ሀገሪቱ ያሉ የመንግስት መከላከያዎች በአስደናቂ ፍጥነት መፈራረስ መጀመራቸው ተሰምቷል። አማጽያኑ ሰሜን አሌፖን እና በመሃላዊ ሀማ እንዲሁም በምሥራቅ ዲር አል ዞርን ከመያዛቸው በተጨማሪ፤ ከደቡባዊ ሱዋይዳ እና ዴራ ተነስተው አርብ ዕለት ሁለቱን ከተሞች መቆጣጠራቸውን የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን ለጥፈዋል። ሩሲያ ዜጎቿ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ትላንት አርብ ስታሳስብ በተመሳሳይ ኢራን ዲፕሎማቿን ከነቤተሶቦቻቸው ከሶሪያ ማስወጣቷን የኢራን ባለስልጣናት አስታውቀዋል። Read more