አውሎ ንፋስ ዳራ በእንግሊዝ ከባድ የኃይል መቆራረጥ አስከተለ
newsare.net
በዩናይትድ ኪንግደም ዳራ የተሰኘ አውሎ ንፋስ ሀገሪቱን በከባዱ በመምታቱ ከገና በፊት በመደረግ ላይ ያሉ ጉዞውች ላይ መስተጓጎል አስከትሏል። በተጨማሪም አአውሎ ንፋስ ዳራ በእንግሊዝ ከባድ የኃይል መቆራረጥ አስከተለ
በዩናይትድ ኪንግደም ዳራ የተሰኘ አውሎ ንፋስ ሀገሪቱን በከባዱ በመምታቱ ከገና በፊት በመደረግ ላይ ያሉ ጉዞውች ላይ መስተጓጎል አስከትሏል። በተጨማሪም አውሎ ንፋሱ በዩናይትድ ኪንግደም በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ዛሬ ቅዳሜ ማለዳ ያለ ኃይል አቅርቦት አስቀርቷቸዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የአየር ትንበያ ቢሮ የዌልስን እና የደቡብ ምዕራብ እንግሊዝን ክፍሎች የሚሸፍን ከባድ አውሎ ንፋስ ከአርብ ሌሊት እስከ ቅዳሜ ንጋት ድረስ እንደሚከሰት የሚያመላክት ቀይ ማንቂያ አውጥቶ ነበር። በተመሳሳይ መንግስት አርብ ዕለት ማማሻውን በድምጽ በላከው ማስጠንቀቂያ ሦስት ሚሊየን የሚደርሱ ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ አሳሰቦ ነበር። ዳራ በዚህ በክረምት ወር የተከሰተ አራተኛው ከፍተኛ አውሎ ንፋስ ነው። አውሎ ንፋሱን ተከትሎ በእንግሊዝ ዛሬ ቅዳሜ እና ነገ እሁድ ከፍተኛ ዝናብ እንደሚዘንብ ይጠበቃል። በዚህ የተነሳም በመላው ዩናይትድ ኪንግደም ከመቶ በላይ የጎርፍ ማስጠንቀቂያዎች ወጥተዋል። በሰሜን ምዕራብ እንግሊዝ አንድ ግለሰብ መኪና ውስጥ ሳለ ዛፍ ወድቆበት ሕይወቱ ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል። በአውሎ ንፋሱ የተነሳም ከግላስጎው ወደ ኤድንብራ ስኮትላንድ እንዲሁም ካምብሪጅ እና በምሥራቅ እንግሊዝ ስታንስቴድ አውሮፕላን ማረፊያ መካከል ያለውን ጨምሮ በተለያዩ የባቡር ጉዞዎች ተቋርጠዋል ወይም ታግደዋል። Read more