የተመድ የጸጥታው ም/ቤት በሦሪያ ጉዳይ ሊወያይ ነው
newsare.net
የሦሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በሦሪያ ሁኔታ ላይ ዛሬ ሰኞ በዝግ ይየተመድ የጸጥታው ም/ቤት በሦሪያ ጉዳይ ሊወያይ ነው
የሦሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በሦሪያ ሁኔታ ላይ ዛሬ ሰኞ በዝግ ይወያያል። ለ14 ዓመታት በዘለቀው የሦሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት ለአሳድ ወታደራዊ ድጋፍ ስትሰጥ የቆየችው ሩሲያ፣ በተለይ የመንግሥታቱ ድርጅት በጎላን ተራሮች አካባቢ በነበረው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ሊኖረው ስለሚችለው ተፅእኖ ውይይት እንዲደረግ ጠይቃለች። እስራኤል ትላንት እሁድ ኅዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቁጥጥር በሚያደርጉበት የጎላን ተራሮች ላይ ወታደሮቿን ያሰማራች ሲኾን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ ርምጃው ለእስራኤላውያን ደህንነት አስፈላጊ ነው ብለዋል። በቀጣይ ሦሪያን ማን እንደሚራ እና ለአምስት አስርት ዓመታት ከዘለቀው የአሳድ ቤተሰብ አገዛዝ በኋላ ሀገሪቱ ለዓመታት ከነበረችበት ጦርነት እንዴት እንደምታገግም ግን እስካሁን ግልፅ አይደለም። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአሳድ ጥገኝነት ለመስጠት መወሰናቸውን ገልጸው፣ ፑቲን ከአሳድ ጋራ ለመገናኘት ግን እቅድ እንደሌላቸው አመልክተዋል። አሳድ በአሁኑ ሠዓት ስለሚገኙበት ቦታም አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። ሆኖም የሩሲያ የዜና ማሰራጫዎች ዕሁድ እለት፣ አሳድ ከነቤተሰቦቻቸው ሞስኮ መግባታቸውን ዘግበዋል። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በበኩላቸው ሠኞ ዕለት በሰጡት መግለጫ፣ ቻይና በሦሪያ ያለውን ሁኔታ እየተከታተለች መሆኗን ገልፀው «የሶሪያ የወደፊት እጣ ፈንታ ሊወሰን የሚገባው በሶሪያ ሕዝብ ብቻ ነው» ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንም እሁድ ዕለት ባወጡት መግለጫ፣ አሜሪካ ሁኔታውን በቅርብ እንደምትከታተል እና በቀጠናው ካሉ አጋሮቿ ጋራ አብራ እንደምትሠራ አመልክተዋል። Read more