Ethiopia



በሱሉልታ በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ሁለት ፖሊሶች ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ትላንት ጠዋት በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት፣ የወረዳው ፖሊስ አዛዥና አንድ ፖሊስ መገደላቸው

የልጆች መጽሐፍት ያሳተሙት እናትና ልጅ

በውጭ ሀገር የተወለዱ አዳጊ ልጆች፣ በሚኖሩበት ሀገር ውስጥ በሳይንሱ ዘርፍ እንዲሳተፉና ውክልና እንዲኖራቸው ሁለት የልጆች መጻሕፍት ተጽፈዋል። ጸሐፊዋ ነዋ
የአሜሪካ ድምፅ

የልጆች መጽሐፍት ያሳተሙት እናትና ልጅ

በውጭ ሀገር የተወለዱ አዳጊ ልጆች፣ በሚኖሩበት ሀገር ውስጥ በሳይንሱ ዘርፍ እንዲሳተፉና ውክልና እንዲኖራቸው ሁለት የልጆች መጻሕፍት ተጽፈዋል። ጸሐፊዋ ነዋሪነታቸውን በቨርጂኒያ ግዛት ያደረጉት፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለሞያዋ የኔነሽ ሸዋነህ ሲኾኑ የ13 ዓመት ልጃቸውም ከሌላ ተባባሪ ጸሐፊ ጋራ በመኾን የልጆች መጽሐፍ አሳትሟል። እናትና ልጅን አነጋግረናል ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ትረምፕ የሦሪያን ጉዳይ በሩቁ ማየት የመረጡ ይመስላል፣ ይሳካ ይሆን?

አማጽያን ፕሬዝደንት በሻር አል አሳድን ከሥልጣን ማስወገዳቸውን ተከትሎ ዶናልድ ትረምፕ በሦሪያ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው ፍንጭ አሳይተዋል
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ የሦሪያን ጉዳይ በሩቁ ማየት የመረጡ ይመስላል፣ ይሳካ ይሆን?

አማጽያን ፕሬዝደንት በሻር አል አሳድን ከሥልጣን ማስወገዳቸውን ተከትሎ ዶናልድ ትረምፕ በሦሪያ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው ፍንጭ አሳይተዋል። ይሁን እንጂ የአሜሪካ ድምጿ የዋይት ሀውስ ቢሮ ኃላፊ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ በዘገባዋ እንዳመለከተችው ተመራጩ ፕሬዝዳንት፤ የእስራኤልን ደህንነት ማስጠበቅ፣ ኢራንን ማግለል እና እንዲሁም ከሩሲያ፣ ቱርክ እና ሌሎች ጋራ የሚኖራትን ግንኙነት ጨምሮ ዩናይትድ ስቴትስ ከአሏት ግቦች ጋራ ማጣጣም ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት እና ጁባላንድ መካከል ውጊያ ተቀሰቀሰ

በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት እና በጁባላንድ የክልል አስተዳደር መካከል ለሳምንታት የቆየው የፖለቲካ ልዩነት እና ውጥረት ተባብሶ፣ በደቡብ ሶማሊያ ግጭት ተቀስ
የአሜሪካ ድምፅ

በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት እና ጁባላንድ መካከል ውጊያ ተቀሰቀሰ

በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት እና በጁባላንድ የክልል አስተዳደር መካከል ለሳምንታት የቆየው የፖለቲካ ልዩነት እና ውጥረት ተባብሶ፣ በደቡብ ሶማሊያ ግጭት ተቀስቅሷል። ግጭቱ የተካሄደው፣ በቅርቡ የፌደራል ኃይሎች በተሰማሩባት ራስካምቦኒ የተሰኘች ከተማ ነው። ሁለቱም ወገኖች ግጭቱን በመቀስቀር እርስ በእርስ የተወነጃጀሉ ሲሆን፣ ምን ያክል ጉዳት እንደደረሰ እስካሁን በውል አልታወቀም። በሁለቱ ወገኖች መካከል ውዝግቡ የተቀሰቀሰው በቅርቡ በጁባላንድ የተደረገውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተከትሎ ሲሆን የፌደራል መንግስቱ ሕገወጥ ነው በማለት ውድቅ አድርጎታል። በፌደራሉ አመራር እና በክልሉ አስተዳደሪዎች መካከል እየተካረረ የሄደው የፖለቲካ ውዝግብ ተባብሶ፣ ረቡዕ እለት በፌደራል መንግስቱ ወታደሮች እና በጁባላንድ ኃይሎች መካከል ከፍተኛ ውጊያ መካሄዱ ተገልጿል። በአካባቢው የስልክ መስመር በመቋረጡ ዝርዝር መረጃ ማግኘት ባይቻልም፣ በጁባላንድ የሚገኙ የጸጥታ ኃይሎች የመጀመሪያውን ጥቃት የፈፀሙት የፌደራል ኃይሎች ናቸው በማለት ይከሳሉ። የጁባላንድ ምክትል የደህንነት ሚኒስትር ኤደን አህመድ ሃጂ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ «ከሞቃዲሾ ወደ ራስካምቦኒ የመጡት የፌደራል ኃይሎች በጁባላንድ ኃይሎች ላይ ጥቃት ፈፅመዋል። ጥቃቱ የጀመረው በድሮን ሲሆን፣ ውጊያው እየተካሄደ ያለው ከከተማ ወጣ ብሎ ነው። ግጭቱ ተስፋፍቶ አሁንም እንደቀጠለ ነው። የመንግሥት ኃይሎች አንድ ክፍል እጁን ሰጥቷል» ብለዋል። ጁባላንድ በርካታ የፌደራል መንግስት ወታደሮች እጃቸውን መስጠታቸውን የምትገልፅ ሲሆን፣ የክልሉ ባለስልጣናትም የፌደራል ኃይሎች የሚጠቀሟቸውን ሰው አልባ አሮፕላኖች የሰጡ ሀገራትን ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን ብለዋል። «የሁለቱም ወገኖች ወታደሮች በአንድ መከላከያ ኃይል ውስጥ የሚገኙ ወንድማማቾች ሆነው ሳለ፣ ዛሬ እርስ በእርስ መተኳኮሳቸው በጣም ያሳዝናል» ያሉት የጁባላንድ የደህንነት ሚኒስትር፣ «የሶማሊያ ፌደራል መንግስት ኃላፊነት ነው። የሶማሊያን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያገለግሉ ጦር መሳሪያዎች እና ተሽከርካሪዎች በሕዝብ ላይ ለጥቅም መዋላቸው የሚያሳዝን ነገር ነው» ሲሉ ፌደራል መንግስቱን ወንጅለዋል። የሶማሊያ ፌደራል መንግስት መከላከያ ሚኒስትር በበኩሉ «ያልተጠበቀ ጥቃት» ሲል የገለፀውን ጥቃት፣ በፌደራል ወታደሮች ቁጥጥር ስር በሚገኘው ስፍራ እና ለሰራዊቱ ድጋፍ የሚሰጡ የአካባቢው ሰራተኞች ላይ በማድረስ የጁባላንድ ኃይሎችን ከሷል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫም የፌደራል ኃይሎች በአካባቢው የሰፈሩት፣ የአፍሪካ ህብረት ኃይሎች በቅርቡ የለቀቁትን ወታደራዊ ካምፕ ለመረከብ እና በአልሻባብ ላይ የጸረ ሽብር ዘመቻዎች ለማዘጋጀት መሆኑን ገልጿል። ሆኖም ሁለቱም ወገኖች የሚያቀቧቸውን ክሶችም ሆነ ውጊያው በምን ያክል መጠን እየተካሄደ መሆኑን በገለልተኛ አካል ማረጋገጥ አልተቻለም። የሶማሊያ መንግስት በቅርቡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ራስካምቦኒ ከተማ ውስጥ ያሰፈረ ሲሆን፣ ጁባላንድ ድርጊቱ የክልሉን ደህንነት እና አስተዳደር ለማዳከም የተደረገ ነው ብሏል። የፌደራል ባለስልጣናቱ ግን፣ ወታደሮቹ የሰፈሩት ከአፍሪካ ህብረት መውጣት ጋር ተያይዞ በቦታው የነበሩት የኬንያ ኃይሎች ስፍራውን በመልቀቃቸው ነው ሲል ይከራከራል። ጁባላንድ በራስካምቦኒ ከተማ የስልክ አገልግሎቶችን ያቋረጠ ሲሆን፣ የፀጥታ አካላትንም በአካባቢው አሰማርቷል። የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድን «ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም» የምትከሰው እና የፌደራል መንግስቱ ሕገመንግስቱን ጥሷል የምትለው ጁባላን ከፌደራል መንግስቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን ሕዳር 19፣ 2017 ዓ.ም አስታውቃለች። ፓርላማው ያሳለፈውን ሕገመንግስታዊ ማሻሻያ እንደማትቀበልም ገልጻለች። አንድ ቀን ቀደም ብሎ ሞቃዲሾ የሚገኝ ፍርድ ቤት፣ «አህመድ ማዶቤ» በሚል ስያሜ የሚታወቁትን የጁባላንድ መሪ አህመድ ሞሃመድ ኢስላም፣ በሀገር ክህደት እና የሀገር ሚስጥርን ለውጭ ሀገር በማጋራት ሕገመንግስትን የሚፃረር ድርጊት ፈፅመዋል በማለት የእስር ትዕዛዝ አውጥቶባቸዋል። ውዝግቡ የተቀሰቀሰው አህመድ ማዶቤ በጥቅምት ወር በሞቃዲሾ ከተካሄደው ብሔራዊ የምክክር ምክርቤት ስብሰባ አቋርጠው ከወጡ እና በሕዳር ወር ምርጫ በማካሄድ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ከተመረጡ በኃላ ነው። ክልሉ ቀጥተኛ ምርጫ ማካሄዱን የተቃወመው የፌደራል መንግስት ሂደቱን ውድቅ አድጓል። በወቅቱ የፌደራል መንግስት እና አንዳንድ የክልል አመራሮች የአካባቢ ምርጫዎችን በሰኔ ወር፣ የክልል ፓርላማ እና ፕሬዝዳንታዊ ምርጫዎችን ደግሞ በመስከረም 2018 ዓ.ም ለማካሄድ ተስማምተው ነበር። ጁባላንድ ግን ይህን ስምምነት አልተቀበለችውም።

በሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳ

ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ታግደው የነበሩ፣ በሰብአዊ መብት ጥበቃ ዙሪያ የሚሠሩ ድርጅቶች ዛሬ እግዳቸው ተነስቷል። በኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበ
የአሜሪካ ድምፅ

በሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳ

ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ታግደው የነበሩ፣ በሰብአዊ መብት ጥበቃ ዙሪያ የሚሠሩ ድርጅቶች ዛሬ እግዳቸው ተነስቷል። በኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በኅዳር ወር ውስጥ በቀናት ልዩነት እግድ ተጥሎባቸው የነበሩት፣ የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ)፣ የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች እና ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ የተባሉ ድርጅቶች ናቸው፡፡ ለእግዱ ምክንያት ተብሎ የተጠቀሰው ደግሞ፣ ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል፣ እንዲሁም የአገርንና የሕዝብን ጥቅም የሚጎዳ ተግባር አከናውነዋል የሚል ነበር፡፡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ፣ እግድ በተጣለባቸው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ “በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔ” እንደሚሰጥ ኅዳር 19 መግለጫ በሰጡበት ወቅት ገልጸው የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ታኅሣሥ 2 እግዱ መነሳቱ ታውቋል፡፡ ታግደው ከነበሩት ድርጅቶች አንዱ የኾነው የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች ዋና ዳይሬክተር አቶ አምሃ መኮንን፣ እግዱ መነሳቱን የሚገልጽ ደብዳቤ ከማስጠንቀቂያ ጋራ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

“ሱዳን ትልቁን ሰብአዊ ቀውስ የተሸከመች ሀገር ሆናለች” - ዓለም አቀፍ ነፍስ አድን ኮሚቴ

በሱዳን በጦር ሠራዊቱ እና በፈጥኖ ደራሽ ኅይሎች መካከል ለ20 ወራት የዘለቀውን አስከፊ ጦርነት ተከትሎ “እስከዛሬ ከተመዘገቡት ሁሉ ትልቁን ሰብአዊ ቀውስ የተሸ
የአሜሪካ ድምፅ

“ሱዳን ትልቁን ሰብአዊ ቀውስ የተሸከመች ሀገር ሆናለች” - ዓለም አቀፍ ነፍስ አድን ኮሚቴ

በሱዳን በጦር ሠራዊቱ እና በፈጥኖ ደራሽ ኅይሎች መካከል ለ20 ወራት የዘለቀውን አስከፊ ጦርነት ተከትሎ “እስከዛሬ ከተመዘገቡት ሁሉ ትልቁን ሰብአዊ ቀውስ የተሸከመች ሀገር ሆናለች” ሲል የዓለም ነፍስ አድን ኮሚቴ አመለከተ፡፡ በተቃናቃኞቹ ጀኔራሎች መካከል በቀጠለው ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ 12 ሚሊዮን የሚሆኑት ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የተቋሙ ዘገባ ጠቅሷል፡፡ ወደ ዘጠኝ ሚሊዮን የሚጠጉት በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ መሠረተ ልማቶች በወደሙባቸው አካባቢዎች የሠፈሩ ሲሆን የጅምላ ረሃብ ሥጋትም ተጋርጦባቸዋል። ዓለም አቀፉ ድርጅት በሱዳን ወደ 26 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ለከባድ ረሃብ መጋለጡን ገልጾ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ሰብአዊ ቀውስ ገጥሟታል ብሏል፡፡ “ከዓለም ሕዝብ ከአንድ ከመቶ ያነሰ የሕዝብ ብዛት ያላት ሱዳን በዓለም የሰብአዊ ርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ተረጅዎች መካከል 10 በመቶውን ትሸፍናለች” ሲል እአአ የአጣዳፊ ርዳታ ፈላጊዎችን የሚከታተለውና መሠረቱን በኒው ዮርክ ያደደረገው ድርጅት እአአ በቀጣዩ 2025 የአጣዳፊ ሁኔታ ክትትል በሚያስፈልጋቸው ቀውሶች ዘገባው አስታውቋል፡፡ የዓለም ነፍስ አድን ኮሚቴ ዘገባ በየዓመቱ ለሰብአዊ ቀውስ ተጋላጭነት ከፍተኛ ሥጋት ያለባቸውን 20 ሀገራት ለይቶ በማጉላት የሚያሳይ ሲሆን ሱዳን ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በቀዳሚነት ደረጃ ላይ እንደምትገኝ አመልክቷል፡፡ በሀገሪቱ በጠቅላላው 30.4 ሚሊዮን ሰዎች በሰብአዊ እርዳታ ፈላጊዎች መሆናቸውን የገለጸው ኮሚቴው የተረጅዎችን ቁጥር መመዝገብ ከጀመረ ወዲህ ይህ “ከምንጊዜውም ትልቁ የሰብአዊ ቀውስ” መሆኑን ገልጿል። ኮሚቴው በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም ወደ 305 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የሰብአዊ እርዳታ የሚሹ መሆኑን ዘግቧል፡፡ ከእነዚህ 82 ከመቶ የሚሆኑት በኃይል በተያዙት የፍልስጤም ግዛቶች፣ ሚያንማር፣ ሦሪያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሊባኖስ በመሳሰሉት ክትትል ያስፈልጋቸዋል ተብለው በተመዘገቡ የቀውስ አካባቢዎች እንደሚገኙ ዘገባው አመልክቷል፡፡ የዓለም ነፍስ አድን ኮሚቴ ኃላፊ ዴቪድ ሚሊባንድ ‘ዓለም እሳት ላይ ነች’ ይህ በመቶ ሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች የዕለት ተዕለት እውነታ እንደሆነ ግልጽ ነው።” ብለዋል፡፡ ሚሊባንድ አክለውም «ዓለማችን በሁለት ካምፖች እየተከፈለች ነው፤ ባልተረጋጋ እና ግጭት ባለበት ቦታ በተወለዱት እና በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ የመኖር እድል ባላቸው መካከል» ማለታቸውን ኤኤፍፒ ጠቅሷል፡፡

የአሳድ ውድቀት ሩሲያ በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ የነበራትን ዋና አጋር አሳጥቷታል

ከስልጣናቸው የተባረሩት የሶሪያ ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ ሞስኮ መግባታቸውን በመግለፅ፣ የሩሲያ መንግስት መገናኛ ብዙሃን ሞስኮ ለአሳድ ጥገኝነት መስጠቷ
የአሜሪካ ድምፅ

የአሳድ ውድቀት ሩሲያ በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ የነበራትን ዋና አጋር አሳጥቷታል

ከስልጣናቸው የተባረሩት የሶሪያ ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ ሞስኮ መግባታቸውን በመግለፅ፣ የሩሲያ መንግስት መገናኛ ብዙሃን ሞስኮ ለአሳድ ጥገኝነት መስጠቷን ዘግበዋል። አሳድ በስልጣን ላይ እያሉ ታጣቂዎችን ለማሸነፍ ባደረጉት ትግል ክሬምሊን ቁልፍ የመንግስታቸው ደጋፊ የነበረች ሲሆን፣ ሞስኮ በሶሪያ የነበራትን፣ ከጥቂት ቀናት በፊት የማይነቃነቅ ይመስል የነበረ የበላይነት መልሶ ለማግኘት ግን አዳጋች ሊሆንባት ይችላል። ሪካርዶ ማርኪና በዚህ ዙሪያ ያደረሰንን ዘገባ፣ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ከአሰቃቂው የባሕር ላይ አደጋ የተረፉት ፍልሰተኞች ይናገራሉ

ከአንድ ወር በፊት፣ በአብዛኛው ሶማሊያውያን ፍልሰተኞች የተሳፈሩባቸውንና ወደ ማዮት ደሴት በማቅናት ላይ የነበሩ ሁለት ጀልባዎችን፣ የጀልባዎቹ አዛዦች የሆ
የአሜሪካ ድምፅ

ከአሰቃቂው የባሕር ላይ አደጋ የተረፉት ፍልሰተኞች ይናገራሉ

ከአንድ ወር በፊት፣ በአብዛኛው ሶማሊያውያን ፍልሰተኞች የተሳፈሩባቸውንና ወደ ማዮት ደሴት በማቅናት ላይ የነበሩ ሁለት ጀልባዎችን፣ የጀልባዎቹ አዛዦች የሆኑት ሕገ ወጥ አስተላላፊዎች መሃል ባሕሩ ላይ ጥለዋቸው በመሄዳቸው፣ ቢያንስ 27 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአፍሪካ ቀንድ አገልግሎት ባልደረባ ሃሩን ማሩፍ፣ ከአደጋው የተረፉትን አነጋግሮ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የጦር አካል ጉዳተኞች ከመቐለ ወደ ዓዲግራት የሚወስደውን መንገድ በተቃውሞ ዘግተው ዋሉ

በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊ የጦር አካል ጉዳተኞች ዛሬ ማክሰኞ ታኅሣስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. የክልሉ ዋና ከተማ መቐለን ከዓዲግራትና ሌሎች ከተሞች የሚያገናኘውን የ
የአሜሪካ ድምፅ

የጦር አካል ጉዳተኞች ከመቐለ ወደ ዓዲግራት የሚወስደውን መንገድ በተቃውሞ ዘግተው ዋሉ

በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊ የጦር አካል ጉዳተኞች ዛሬ ማክሰኞ ታኅሣስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. የክልሉ ዋና ከተማ መቐለን ከዓዲግራትና ሌሎች ከተሞች የሚያገናኘውን የተሽከርካሪ ማለፊያ መስመር በተቃውሞ ዘግተውት ዋሉ። የጦር አካል ጉዳተኞቹ፣ “በትጥቅ ማስፈታትና የመልሶ ማቋቋም ሂደት ላይ ከሌሎች ሙሉ አካል ካላቸው የቀድሞ ተዋጊዎች ጋራ ተመድበናል በቂ ህክምናም እያገኘን አይደለም፣ አመራሮውቹ ረስተውናል” የሚሉና ሌሎች ተቃውሞዎችን በማስማት ከመቐለ ከተማ ሰላሳ ኪሎሜትር በምትርቀው አጉላዕ በተባለች ከተማ ላይ መንገድ ዘግተው ውለዋል። ከትግራይ የጸጥታ ኃይሎች አመራር ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ ጋራ በጉዳዩ ላይ ከተወያዩ በኋላ መንገዱ ተከፍቷል።

ጋና የገጠማትን የኢኮኖሚ ቀውስ ለመፍታት ተመራጩ ፕሬዝደንት የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ ተጠየቀ

የቀድሞ የጋና ፕሬዝደንት እና የተቃዋሚ መሪው ጃን ማሃማ ባለፈው ቅዳሜ በተደረገው ምርጫ ማሸነፋቸውን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ ሰኞ አስታውቋል። ማሃማ ወ
የአሜሪካ ድምፅ

ጋና የገጠማትን የኢኮኖሚ ቀውስ ለመፍታት ተመራጩ ፕሬዝደንት የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ ተጠየቀ

የቀድሞ የጋና ፕሬዝደንት እና የተቃዋሚ መሪው ጃን ማሃማ ባለፈው ቅዳሜ በተደረገው ምርጫ ማሸነፋቸውን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ ሰኞ አስታውቋል። ማሃማ ወደ ሥልጣን የመመለሳቸው ጉዳይ የተደበላለቁ አስተያየቶችን በማስተናገድ ላይ ነው። አንዳንዶች ማሃማት በአዲስ መልክ ለማስተዳደር በመመለሳቸው ደስታቸውን ሲገልጹ፣ ሌሎች ደግሞ የጋናን የኢኮኖሚ ተግዳሮቶች የመፍታት አቅማቸው ላይ ጥያቄ አላቸው። የቪኦኤው ሰናኑ ቶድ ከአክራ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በሶሪያ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር አቋም ከእስላማዊ መንግስት ከፍተኛ የመልሶ ማጥቃት በኋላም አልተለወጠም

የደማስቆ ውድቀት፣ በጦርነት በተናጠች ሀገር ውስጥ እስላማዊ መንግሥት እንዳያንሰራራ ለማድረግ፣ ከአጋሮች ጋር ተባብረው ሲሰሩ የቆዩ የአሜሪካ ወታደሮች ቀጣ
የአሜሪካ ድምፅ

በሶሪያ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር አቋም ከእስላማዊ መንግስት ከፍተኛ የመልሶ ማጥቃት በኋላም አልተለወጠም

የደማስቆ ውድቀት፣ በጦርነት በተናጠች ሀገር ውስጥ እስላማዊ መንግሥት እንዳያንሰራራ ለማድረግ፣ ከአጋሮች ጋር ተባብረው ሲሰሩ የቆዩ የአሜሪካ ወታደሮች ቀጣይ እጣ፣ ምን ሊሆን እንደሚችል ስጋት አሳድሯል። በፔንታገን የቪኦኤ ዘጋቢ ካርላ ባብ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የታገዱት የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ህልውናቸው አደጋ ላይ መውደቁን መሪዎቹ ገለጹ

ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ከታገዱት ሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሁለቱ አመራሮች የድርጅታቸው ሕልውና አደጋ ላይ መውደቁን ተናገሩ። የመብቶችና ዴሞክራ
የአሜሪካ ድምፅ

የታገዱት የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ህልውናቸው አደጋ ላይ መውደቁን መሪዎቹ ገለጹ

ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ከታገዱት ሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሁለቱ አመራሮች የድርጅታቸው ሕልውና አደጋ ላይ መውደቁን ተናገሩ። የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) እና የሕግ ባለሞያዎች ለሰብአዊ መብቶች የተባሉ ሁለቱ የሲቪል ማኅበራት ድርጅት መሪዎች የባንክ ሂሳባቸው በመታገዱ ምክኒያት፣ ለሠራተኞች ደሞዝ መክፈልን ጨምሮ ምንም ዐይነት እንቅስቃሴ ማድረግ ባለመቻላቸው ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ገለጹ። ከኢትዮጵያ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ይኹንና ኅዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም. የተቋሙ ምክትል ዲሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ፣ እየተከናወነ ነው ያሏቸው የማጣራት ሥራ ሲጠናቀቅ ውጤቱ እንደሚገለጽ በቅርቡ መናገራቸው ይታወሳል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ሰሞነኞቹ የጋና እና የናሚቢያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫዎች  

በጋና ምርጫ የቀድሞው ፕሬዚደንት ጆን ድራሃሚ ማሃማ አሸነፉ፡፡ የገዢው ፓርቲ ዕጩ ተፎካካሪ የሆኑት ምክትል ፕሬዚደንቱም መሸነፋቸውን ተቀብለዋል፡፡ ናሚቢ
የአሜሪካ ድምፅ

ሰሞነኞቹ የጋና እና የናሚቢያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫዎች  

በጋና ምርጫ የቀድሞው ፕሬዚደንት ጆን ድራሃሚ ማሃማ አሸነፉ፡፡ የገዢው ፓርቲ ዕጩ ተፎካካሪ የሆኑት ምክትል ፕሬዚደንቱም መሸነፋቸውን ተቀብለዋል፡፡ ናሚቢያ የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዚደንት መርጣለች፡፡ ሰሜኑን እና ደቡቡን የሀገሪቱን ክፍል የሚለየውን የቅኝ አገዛዝ ዘመን አጥር ለማስወገድ እንደሚሰሩ አዲስ ተመራጯ ፕሬዚደንት ኔቱምቦ ናንዲ ኢንዳይትዋህ ቃል ገብተዋል፡፡ «Red Line» ወይም ቀዩ መስመር ተብሎ የሚጠራው 1000 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ እርዝማኔ ያለው አጥር የታጠረው ከሰሜኑ የናሚቢያ ክፍል ወደ ደቡቡ የግብርና ውጤቶች በተለይ የቀንድ ከብቶች እና ሥጋ እንዳይገባ ለመቆጣጠር መሆኑን ከዋና ከተማዋ ክዊንድሆክ በቪታሊዮ አንጉላ ያጠናቀረው ዘገባ ያወሳል፡፡ በሳምንታዊው አፍሪካ ነክ ርዕሶች ፕሮግራም ተካትተዋል፡፡

የአሳድ መንግሥት መውደቅ እና ቀጣዩ የሶሪያ ዕጣ ፈንታ 

የሶሪያው የበሽር አል አሳድ መንግሥት መውደቁን ተከትሎ ሶሪያውያን ደስታቸውን ጉዳዩን የሚከታተሉ ባለሞያዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው፡፡ የዩናትይድ ስቴት
የአሜሪካ ድምፅ

የአሳድ መንግሥት መውደቅ እና ቀጣዩ የሶሪያ ዕጣ ፈንታ 

የሶሪያው የበሽር አል አሳድ መንግሥት መውደቁን ተከትሎ ሶሪያውያን ደስታቸውን ጉዳዩን የሚከታተሉ ባለሞያዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው፡፡ የዩናትይድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕም የአምባገነኑን መንግሥት መውደቅ አስመልክተው ትላንት እሁድ አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ በመካከለኛው ምሥራቅ ካላት ስልታዊ ጥቅም አንጻር ከፊቷ የተደቀነውን የሶሪያ የወደፊት እጣ ፈንታ በቅርበት እንድምትከታተል ይጠበቃል፡፡ ኤድዋርድ ዪሬኒያን ከካይሮ ፡ ሄዘር መርዶክ ከኢስታንቡል እንዲሁም ቬሮኒካ ባልዴራስ ኢግሊሲያስ ያጠናቀሯቸውን የአሜሪካ ድምጽ ዘገባዎች በማጣመር የተሰናዳው ዘገባ ዝርዝር አለው፡፡    

VOA60 Africa - Ghana: Supporters celebrate John Mahama's electoral victory

Ghana: Former President John Dramani Mahama won a historic comeback election victory Sunday after Saturday’s election. Ghana's ruling New Patriotic Party candidate, Vice President Mahamudu Bawumia, conceded defeat
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Ghana: Supporters celebrate John Mahama's electoral victory

Ghana: Former President John Dramani Mahama won a historic comeback election victory Sunday after Saturday’s election. Ghana's ruling New Patriotic Party candidate, Vice President Mahamudu Bawumia, conceded defeat

VOA60 America - US strikes dozens of ISIS targets in Syria

​ After the fall of Syrian President Bashar al-Assad, the U.S. Central Command said its forces conducted dozens of airstrikes on Islamic State targets in central Syria on Sunday. U.S. President Joe Biden called the demise of Assad's regime a “fundamental
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - US strikes dozens of ISIS targets in Syria

​ After the fall of Syrian President Bashar al-Assad, the U.S. Central Command said its forces conducted dozens of airstrikes on Islamic State targets in central Syria on Sunday. U.S. President Joe Biden called the demise of Assad's regime a “fundamental act of justice.”

VOA60 World - Hundreds of displaced Syrians return from Lebanon to Syria

Hundreds of displaced Syrians were returning from Lebanon to Syria on Monday, with dozens of cars lining up at the border crossing. President Bashar Assad’s government fell on Sunday after rebel fighters entered Damascus following a stunning advance.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Hundreds of displaced Syrians return from Lebanon to Syria

Hundreds of displaced Syrians were returning from Lebanon to Syria on Monday, with dozens of cars lining up at the border crossing. President Bashar Assad’s government fell on Sunday after rebel fighters entered Damascus following a stunning advance.

በደጋ ዳሞት ወረዳ ከ30 በላይ ሲቪሎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የአማራ ክልል መንግሥትና ነዋሪዎች ተናገሩ 

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ፣ «ፈረስ ቤት» በተባለች ከተማ ኅዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም የፋኖ ታጣቂዎች ፈጸሙት በተባለ ጥቃት 37 ሲቪሎች መገ
የአሜሪካ ድምፅ

በደጋ ዳሞት ወረዳ ከ30 በላይ ሲቪሎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የአማራ ክልል መንግሥትና ነዋሪዎች ተናገሩ 

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ፣ «ፈረስ ቤት» በተባለች ከተማ ኅዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም የፋኖ ታጣቂዎች ፈጸሙት በተባለ ጥቃት 37 ሲቪሎች መገደላቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ። በሌላ በኩል የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የሟች ቤተሰቦችና የከተማው ነዋሪዎች፣ የወረዳውን አስተዳዳሪ ጨምሮ ከ30 በላይ የወረዳው አመራሮች በአካባቢው ይንቀሳቀሳሉ ባሏቸው የፋኖ ታጣቂዎች መገደላቸውን ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ ሰዎቹ የተገደሉት ሐሙስ ኅዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ነው ብለዋል። ላለፉት ሁለት ወራት በፋኖ ቁጥጥር ሥር እንደነበሩ አንድ ስማቸውን እንዲጠቀስ ያልፈልጉ የመንግሥት አንድ ግለሰብ ፣ ግድያው ሲፈጸም በቦታው ነበርኩ ብለዋል። አንድ ሌላ ግለሰብ ደግሞ፣ የቅርብ ቤተሰባቸው አባል እንደተገደለባቸው ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ ከፋኖ ታጣቂዎች መረጃን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ከፌደራልና ከክልል ባለሥልጣናትም መረጃን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የትላንቱ የአዲስ አበባ ከተማ ላይ የተሰማው ተኩስና የሰሞኑ የሠላም ስምምነት ጥያቄ አስነስቷል

በአዲስ አበባ ከተማ ትላንት የተሰማውን ተኩስ በተመለከተ መንግሥት ግልጽ መረጃ እንዲሰጥ ኢዘማ ጠየቀ። ተኩሱ የተፈፀመው “ወደ ተሃድሶ ሥልጠና በሚጓዙ የቀድ
የአሜሪካ ድምፅ

የትላንቱ የአዲስ አበባ ከተማ ላይ የተሰማው ተኩስና የሰሞኑ የሠላም ስምምነት ጥያቄ አስነስቷል

በአዲስ አበባ ከተማ ትላንት የተሰማውን ተኩስ በተመለከተ መንግሥት ግልጽ መረጃ እንዲሰጥ ኢዘማ ጠየቀ። ተኩሱ የተፈፀመው “ወደ ተሃድሶ ሥልጠና በሚጓዙ የቀድሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አባላት ነው” ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ ለተፈጠረው ድንጋጤና መረበሽ ይቅርታ ጠይቋል፡፡ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ በተያያዘ፣ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ቅርፅ እና ይዘት ለሕዝብ ግልፅ እንዲደረግም ኢዜማ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የተመድ የጸጥታው ም/ቤት በሦሪያ ጉዳይ ሊወያይ ነው

የሦሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በሦሪያ ሁኔታ ላይ ዛሬ ሰኞ በዝግ ይ
የአሜሪካ ድምፅ

የተመድ የጸጥታው ም/ቤት በሦሪያ ጉዳይ ሊወያይ ነው

የሦሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በሦሪያ ሁኔታ ላይ ዛሬ ሰኞ በዝግ ይወያያል። ለ14 ዓመታት በዘለቀው የሦሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት ለአሳድ ወታደራዊ ድጋፍ ስትሰጥ የቆየችው ሩሲያ፣ በተለይ የመንግሥታቱ ድርጅት በጎላን ተራሮች አካባቢ በነበረው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ሊኖረው ስለሚችለው ተፅእኖ ውይይት እንዲደረግ ጠይቃለች። እስራኤል ትላንት እሁድ ኅዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም.  የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቁጥጥር በሚያደርጉበት የጎላን ተራሮች ላይ ወታደሮቿን ያሰማራች ሲኾን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ ርምጃው ለእስራኤላውያን ደህንነት አስፈላጊ ነው ብለዋል። በቀጣይ ሦሪያን ማን እንደሚራ እና ለአምስት አስርት ዓመታት ከዘለቀው የአሳድ ቤተሰብ አገዛዝ በኋላ ሀገሪቱ ለዓመታት ከነበረችበት ጦርነት እንዴት እንደምታገግም ግን እስካሁን ግልፅ አይደለም።  የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአሳድ ጥገኝነት ለመስጠት መወሰናቸውን ገልጸው፣ ፑቲን ከአሳድ ጋራ ለመገናኘት ግን እቅድ እንደሌላቸው አመልክተዋል። አሳድ በአሁኑ ሠዓት ስለሚገኙበት ቦታም አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። ሆኖም የሩሲያ የዜና ማሰራጫዎች ዕሁድ እለት፣ አሳድ ከነቤተሰቦቻቸው ሞስኮ መግባታቸውን ዘግበዋል። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በበኩላቸው ሠኞ ዕለት በሰጡት መግለጫ፣ ቻይና በሦሪያ ያለውን ሁኔታ እየተከታተለች መሆኗን ገልፀው «የሶሪያ የወደፊት እጣ ፈንታ ሊወሰን የሚገባው በሶሪያ ሕዝብ ብቻ ነው» ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንም እሁድ ዕለት ባወጡት መግለጫ፣ አሜሪካ ሁኔታውን በቅርብ እንደምትከታተል እና በቀጠናው ካሉ አጋሮቿ ጋራ አብራ እንደምትሠራ አመልክተዋል። 

በቅርቡ ሕይወታቸው ያለፈው ካፒቴን መሐመድና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቆይታቸው በወዳጆቻቸው አንደበት 

በቅርቡ በሞት የተለዩት የ94 ዓመቱ ካፒቴን መሐመድ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በደርግ የሥልጣን ዘመን ከውድቀት ከታደጉት ሰዎች አንዱና ጠንካራ አመራር እንደ
የአሜሪካ ድምፅ

በቅርቡ ሕይወታቸው ያለፈው ካፒቴን መሐመድና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቆይታቸው በወዳጆቻቸው አንደበት 

በቅርቡ በሞት የተለዩት የ94 ዓመቱ ካፒቴን መሐመድ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በደርግ የሥልጣን ዘመን ከውድቀት ከታደጉት ሰዎች አንዱና ጠንካራ አመራር እንደነበሩ በወቅቱ አብረዋቸው ያገለገሉ ባልደረባቸውና ወዳጃቸው ምስክርነታቸውን ሰጥተውላቸዋል። ሐረር ከተማ የተወለዱት ካፕቴን መሐመድ ፣ ከ1972 እስከ ከ1986 ዓ. የዋና ሥራ አስፈጻሚነት ኃላፊነታቸውን ጨምሮ ለ30 ዓመታት አየር መንገዱን አገልግለዋል። የአፍሪካ አቪዬሽን ማኅበር ፕሬዝዳንትም በመኾን ከሀገራቸው አልፈው ለአፍሪካ አየር መንገድ አስተዋጾ አድርገዋል። የአየር መንገዱ የቀድሞ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች፣ በወቅቱ የነበረው የካፒቴን መሐመድ አስተዋጾ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጠው እንደኾነ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የአየር መንገድ ሥራ አስኪያጅና የካፒቴን መሐመድ አለቃ የነበሩት ካናዳ የሚገኙት ኮለኔል ሥምረት መድኽኔ፣ «ትውውቃችን የድሮ ነበር ሲሉ» ስለሟች ወዳጃቸውም በወቅቱ ስለነበረው የአየር መንገዱም ኹኔታ አጫውተውናል። የአየር መንገዱ የገበያና ኦፕሬሽን ዲሬክተር በመኾን ያገለገሉት የ90 ዓመቱ ካፕቴን አሰፋ አምባዬም ብዙ ዓመታትን ወደ ኋላ መልሰው፣ በወቅቱ ሊዘጋ ተቃርቦ የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከያሉበት ተሰብስበው እንዴት ሊታደጉት እንደቻሉ ተርከውልናል። «ከአየር መንገዱ ውጪ ኑሮም ሕይወትም አልነበረንም» ሲሉ የቀደመውን ጊዜያቸውን በትውስታ አጋርተውናል። የካፒቴን መሐመድ ልጅ አቶ ካሊድ መሀመድ ስለ አባታቸው፣ የአቪዬሽን አማካሪ አቶ ዮናታን መንክር ካሳም ስለቀድሞው የድርጅቱ መሪ የሚያውቁትን አካፍለውናል።

በደቡብ ሊባኖስ በተደረገ ውጊያ አራት ወታደሮቿ መሞታቸውን እስራኤል አስታወቀች

በደቡብ ሊባኖስ በተደረገ ውጊያ አራት ወታደሮች መገደላቸውን የእስራኤል ጦር ዛሬ ሰኞ አስታውቋል። ወታደሮቹ ከአንድ ብርጌድ የተውጣጡ መሆናቸውን ያመለከተው
የአሜሪካ ድምፅ

በደቡብ ሊባኖስ በተደረገ ውጊያ አራት ወታደሮቿ መሞታቸውን እስራኤል አስታወቀች

በደቡብ ሊባኖስ በተደረገ ውጊያ አራት ወታደሮች መገደላቸውን የእስራኤል ጦር ዛሬ ሰኞ አስታውቋል። ወታደሮቹ ከአንድ ብርጌድ የተውጣጡ መሆናቸውን ያመለከተው ወታደራዊ መግለጫ፣ መቼ እና በምን ሁኔታ እንደተገደሉ ግን አላብራራም። የእስራኤል ጦር ይህን ያስታወቀው በእስራኤል እና ሊባኖን በሚገኘው የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን መካከል የተኩስ አቁም ከተደረገው ከሁለት ሳምንታት በኋላ ነው። የሊባኖስ ጦር በበኩሉ ሰኞ እለት ባወጣው መግልጫ፣ እስራኤል ባካሄደችው የአየር ጥቃት በደቡብ ሊባኖስ በሚገኝ የጦር መከላከያ ኬላ አቅራቢያ አንድ መኪና በመምታት አንድ ሰው ሲገድል፣ አራት ወታደሮች ማቁሰሉን አስታውቋል። የእስራኤል ባለሥልጣናት ከየመን ተነስቷል ብለው እንደሚያምኑ የገለጹት ጥቃትም በመካከለኛው እስራኤል በምትገኘው ያቭኔ ከተማ የሚገኝ የመኖሪያ ህንፃ ላይ እንዳረፈ ያስታወቁ ሲሆን፣ ስለደረሰው ጉዳት ግን የተገለፀ ነገር የለም። ሁለቱም ወገኖች ወታደሮቻቸውን ከደቡብ ሊባኖስ ድንበር ለማራቅ ያደረጉት ስምምነት ጦርነቱን በከፍተኛ ደረጃ ቢቀንሰውም፣ አሁንም በአካባቢው ጥቃቶች ይፈፀማሉ። 

የደቡብ ኮሪያ አቃቤ ህግ የቀድሞ የመከላከያ አዛዥ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ

የደቡብ ኮሪያ አቃቤ ህግ ባለፈው ሳምንት የወጣውንና በአጭሩ የተቀጨውን ወታደራዊ ሕግ እንዲያውጁ ለፕሬዚዳንት ዮን ሱክ ዮል ሀሳብ ያቀረቡትን የቀድሞ የመከላከ
የአሜሪካ ድምፅ

የደቡብ ኮሪያ አቃቤ ህግ የቀድሞ የመከላከያ አዛዥ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ

የደቡብ ኮሪያ አቃቤ ህግ ባለፈው ሳምንት የወጣውንና በአጭሩ የተቀጨውን ወታደራዊ ሕግ እንዲያውጁ ለፕሬዚዳንት ዮን ሱክ ዮል ሀሳብ ያቀረቡትን የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር  በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡ የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር ኪም ዮንግ ዩን ዛሬ እሁድ በገዛ ፈቃዳቸው በሴኡል አቃቤ ህግ ቢሮ ቀርበው በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል፡፡  ከወታደራዊ ህጉ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ የመጀመርያው ሰውም ሁነዋል፡፡  እስሩ የመጣው ፕሬዘዳንት ዮን ከስልጣን እንዲነሱ በፓርላማ በተቃዋሚዎች የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ ከሆነ በኋላ ነው፡፡ ዋናው ተቃዋሚ ዴሞክራቲክ ፓርቲ በዩን ላይ አዲስ የክስ መቃወሚያ እንደሚያዘጋጅም ተናግሯል።  አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የህግ አስከባሪ ባለስልጣን የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ኪም ዮንግ ዩን በሴኡል ማቆያ ጣቢያ በአቃቤ ህግ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ለአሶሽየትድ ፕሬስ ገልጸዋል፡፡  ኪም በፕሬዘዳንት ዮን ወታደራዊ ህግ ላይ ዋና ሰው የነበሩ ሲሆን ህጉ ለመጽደቅ ቀርቦ በነበረበት ወቅትም የምክር ቤቱን ህንፃ  በወታደሮች እንዲከበብና ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች በላዩ ላይ እንዲያንዣብቡ አድርገው እንደነበርም ተገልጿል፡፡  ምክርቤቱ አዋጁን በሙሉ ድምጽ ውድቅ ካደረገ በኋላም ወታደራዊ ሃይሎች ምክር ቤቱን ለቀው ወጥተዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ሃሙስ እለት ኪም ያቀረቡትን የስራ መልቀቂያ ጥያቄ በፕሬዘዳንቱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ የሃገር ውስጥ ሚድያ ሪፖርቶቹ ዛሬ ፖሊስ የኪምን የቀድሞ ቢሮ እና መኖሪያ ቤት እንደፈተሸ ተናግረዋል። አሶሼትድ ፕሬስ ለተጨማሪ መረጃ  ወደ ሴኡል አቃቤ ህግ ቢሮዎች እና የፖሊስ ኤጀንሲ ላደረጋቸው ተደጋጋሚ ጥሪዎች ምላሽ አላገኘም። 

ትራምፕ ከዘለንስኪ ጋር ከነበራቸው ውይይት በኋላ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ 

የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጩ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፈረንሳይ ፓሪስ ከዩክሬንና ፈረንሳይ ፕሬዘዳንቶች ጋር ካደረጉት አጭር ስብሰባ በኋላ ከአንድ ሽህ ቀና
የአሜሪካ ድምፅ

ትራምፕ ከዘለንስኪ ጋር ከነበራቸው ውይይት በኋላ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ 

የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጩ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፈረንሳይ ፓሪስ ከዩክሬንና ፈረንሳይ ፕሬዘዳንቶች ጋር ካደረጉት አጭር ስብሰባ በኋላ ከአንድ ሽህ ቀናት በላይ የሆነውን ጦርነት ለማቆም ኪየቭ “ስምምነት ማድረግ ትፈልጋለች” በማለት በዩክሬን አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ዛሬ እሁድ አሳስበዋል፡፡ ትሩዝ ሶሻል በተባለው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባወጡት ጽሁፍ መጀመርያም መከሰት አልነበረበትም ባሉት ጦርነት ኬቭና ሞስኮ በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ወታደሮቻቸውን ማጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ግጭቱን ለማቆም እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ባደረጉበት በዚህ መልዕክታቸው «አፋጣኝ የተኩስ ማቆም እና ድርድር መጀመር አለበት፣ ብዙ ህይወት ያለ ምክንያት እየጠፋ ነው ፣ ብዙ ቤተሰቦችንም አጥፍቷል» ብለዋል። የትራምፕ አስተያየት የመጣው ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እና ከፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ቅዳሜ ተገናኝተው ዘለንስኪ “ገንቢ” ያሉትን ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው፡፡ በእለቱ ዘለንስኪ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ማንኛውም የሰላም ስምምነት ለዩክሬናውያን “ፍትሃዊ መሆን አለበት” ሩሲያ እና ፑቲን ወይም ሌሎች ወራሪዎች የመመለስ እድል ሊኖራቸውም አይገባም ብለዋል፡፡ ዘለንስኪ ዛሬ በማህበራዊ ሚድያ ባጋሩት መረጃ ደግሞ የሞስኮ ወረራ ከጀመረበት እአአ የካቲት 24፣ 2022 እስካሁ ድረስ ሃገራቸው 43ሽ ወታደሮችን ማጣቷንና 370ሽ የሚሆኑት መቁሰላቸውን አስታውቀዋል፡፡ ሁለቱም ሩሲያ እና ዩክሬን የሟቾችን ቁጥር ይፋ ለማድረግ ፈቃደኞች አልነበሩም፣ ነገር ግን የምዕራባውያን ባለስልጣናት ባለፉት ጥቂት ወራት በምስራቅ ዩክሬን ውስጥ የተካሄደው የጦርነት በሁለቱም ወገኖች ላይ ከፍተኛውን ኪሳራ ያስከተለ ሲሆን በየወሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሚሞቱና እንደሚቆስሉ ይናገራሉ፡፡

የጋና ገዥ ፓርቲ እጩ በፕሬዘዳንታዊ ምርጫው ተሸነፉ 

በጋና በተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የገዥው 'ኒው ፓትሪዎቲክ ፓርቲ'  የወከሉት ምክትል ፕሬዘዳንት ማሃማዱ ባዉሚያ ተሸንፈዋል፡፡ በሃገሪቱ የተንሰራፋው ኢኮ
የአሜሪካ ድምፅ

የጋና ገዥ ፓርቲ እጩ በፕሬዘዳንታዊ ምርጫው ተሸነፉ 

በጋና በተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የገዥው 'ኒው ፓትሪዎቲክ ፓርቲ'  የወከሉት ምክትል ፕሬዘዳንት ማሃማዱ ባዉሚያ ተሸንፈዋል፡፡ በሃገሪቱ የተንሰራፋው ኢኮኖሚያዊ ችግርን ተከትሎ መራጮች ላይ የነበረው ስጋት ለሽንፈታቸው ምክንያት ተደርጎ ተወስዷል፡፡  ትላንት የተካሄደው ምርጫ ሽንፈት ተከትሎ ለሁለት የምርጫ ጊዜ በፕሬዘዳንት ናና አኮ ፋዶ አማካኝነት ሃገሪቱን የመራትና በዋጋ ንረት እና እዳን በጊዜው ያለመክፈል የከፋ ኢኮኖሚያዊ ችግር ውስጥ ሃገሪቱን ከቷታል በሚል የሚወቀሰው የገዥው ፓርቲ የስልጣን ጊዜ የሚያበቃ ይሆናል፡፡  ባውሚያ  “የጋና ህዝብ ተናግሯል፣ ህዝቡ በዚህ ጊዜ ለለውጥ ድምጽ ሰጥቷል እናም በትህትና እናከብራለን« ሲሉ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡  ምርጫውን ላሸነፉት የተቃዋሚው ‘ናሽናል ዲሞክራቲክ ኮንግረስ’ እጩ እና የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆን ማሃማን ደውለው እንኳን ደስ ያለዎት ማለታቸውንም ተናግረዋል፡፡ ተመራጩ ማሃማም የስልክ ጥሪው እንደደረሳቸው በX የማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ አረጋግጠዋል፡፡  የማሃማ ደጋፊዎች አክራ ከሚገኘው የፓርቲው የምርጫ ቅስቀሳ ዋና መሥሪያ ቤት ውጭ ተሰብስበው ደስታቸውን እየገለጹ ነው፡፡   ማሃማ የፕሬዚዳንትነቱን ቦታ »ወሳኝ" በሆነ ሁኔታ ማሸነፋቸውንና ፓርቲያቸውም በሃገሪቱ ፓርላማ ምርጫ ማሸነፉንም ምክትል ፕሬዘዳንቱ ባውሚያ ተናግረዋል፡፡   በዲሞክራሲያዊ መረጋጋት ታሪክ  ባላት ጋና ሁለቱ ዋና ዋና ፓርቲዎች 'ኒው ፓትሪዎቲክ ፓርቲ' እና ‘ናሽናል ዲሞክራቲክ ኮንግረስ’ ሃገሪቱ ወደ መድበለ ፓርቲ ፖለቲካ ከተመለሰች እኤአ በ1992 በኋላ እየተፈራረቁ መርተዋል፡፡ 

አማጽያን የሶርያን መንግስት መቆጣጠራቸውንና የአሳድ አገዛዝ ማክተሙ ተገለጸ 

በፍጥነት ከተሞችን እየተቆጣጠሩ የመጡት አማጽያን ዋና ከተማዋን ደማስቆን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ የሶርያ መንግስት ወድቋል፡፡ ህዝቡም አደባባይ በመውጣት የአ
የአሜሪካ ድምፅ

አማጽያን የሶርያን መንግስት መቆጣጠራቸውንና የአሳድ አገዛዝ ማክተሙ ተገለጸ 

በፍጥነት ከተሞችን እየተቆጣጠሩ የመጡት አማጽያን ዋና ከተማዋን ደማስቆን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ የሶርያ መንግስት ወድቋል፡፡ ህዝቡም አደባባይ በመውጣት የአሳድ ቤተሰብ የ50 አመታት የበረታ አገዛዝ ማክተሙን አስመልክቶ ደስታውን እየገለጠ ይገኛል፡፡  የሶሪያ መንግስት ቴሌቪዥን ፕሬዚደንት በሽር አላሳድ ከስልጣን መወገዳቸውንና እና ሁሉም እስረኞች ተፈተዋል ሲሉ አማጽያኑ በቡድን ሁነው የሰጡትን የቪዲዮ መግለጫ አቅርቧል።  መግለጫውን ያነበበው ሰው 'ዘኦፕሬሽን ሩም ቱ ኮንከር ደማስቆ'  በመባል ከሚታወቀው የተቃዋሚ ቡድን ሲሆን ሁሉም አማፂ ተዋጊዎች እና ዜጎች «የነጻዋ የሶሪያ መንግስት» ተቋማትን እንዲጠብቁ ሲል ጥሪ አቅርቧል።  ይህ መግለጫ የወጣው የሶሪያ ተቃዋሚዎች የጦር አበጋዝ መሪ አሳድ ሀገሪቱን ለቀው ወዳልታወቀ ቦታ መሄዳቸውን ካስታወቁ ከሰዓታት በኋላ ነው፡፡ የሸሹትም በሀገሪቱ ፈጣን የሆነ ግስጋሴን ያደረጉ አማጽያን ደማስቆ ገብተናል ከማለታቸው ቀድመው ነው ተብሏል፡፡  ብዙ የመዲናዋ ነዋሪዎች በሽር አላ አሳድ በሀገሪቱ ላይ ያላቸውን ስልጣን ያጡበትን ፍጥነት ማመን አቅቷቸዋል፡፡ 14 ዓመታት በሚጠጋው የእርስ በርስ ጦርነት፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን የአገሪቱን ግማሽ ሕዝብ የሚሆነውን 23 ሚሊዮን ህዝብም አፈናቅሏል እንዲሁም በርካታ የውጭ ኃይሎችን ጦርነቱን እንዲቀላቀሉ አድርጓል፡፡ የሶሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ጋዚ ጃላሊ መንግስት እጁን ለተቃዋሚዎች ለመዘርጋት እና የሽግግር መንግስት ለመመስረት ዝግጁ ነው ሲሉ በቪዲዮ መግለጫ ተናግረዋል፡፡  በኋላም ለሳዑዲ የቴሌቭዥን ጣቢያ ለአል አረቢያ አሳድ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ የት እንዳሉ እንደማያውቁ ተናግረዋል። ቅዳሜ መገባደጃ ላይ ከአሳድ ጋር የነበራቸው ግንኙነት እንደተቋረጠም ገልጸዋል፡፡  አሳድ በጦርነቱ ወቅት እ.ኤ.አ. በ2013 በዋና ከተማው ዳርቻ ላይ የተፈፀመውን የኬሚካል ጦር መሳሪያ ጥቃት ጨምሮ በጦር ወንጀሎች እና በሰብአዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ይከሰሳሉ፡፡ 

ፎቢያ የሚሰኘው መሰረት የለሽ ጽኑ ፍርሃት ምንድነው?

ብዙ ሰዎች በከፍታ ስፍራ፣ በጠባብ ቦታዎች፣ አሊያም ደግሞ ተሳቢ እንሥሳት ሲያዩ ምቾት አይሰማቸውም። ይሁን እንጂ አንዳንዶች ደግሞ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎ
የአሜሪካ ድምፅ

ፎቢያ የሚሰኘው መሰረት የለሽ ጽኑ ፍርሃት ምንድነው?

ብዙ ሰዎች በከፍታ ስፍራ፣ በጠባብ ቦታዎች፣ አሊያም ደግሞ ተሳቢ እንሥሳት ሲያዩ ምቾት አይሰማቸውም። ይሁን እንጂ አንዳንዶች ደግሞ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ ሲገኙ በከፍተኛ ፍርሃት ሲሰቃዩ ይስተዋላል። እንዲህ ያለውን ስሜት የጤና ባለሙያዎች መሰረት የለሽ ጽኑ ፍርሃት ወይም በእንግሊዘኛ አጠራሩ ፎቢያ ይሉታል። በዚህ ዙሪያ የተሰናዳውን ዘገባ፣ የባለሞያ ምክር እና የግለሰቦች አስተያየት ከሳምንቱ ኑሮ በጤነንት መሰናዶ ይከታተሉ።

አውሎ ንፋስ ዳራ በእንግሊዝ ከባድ የኃይል መቆራረጥ አስከተለ

በዩናይትድ ኪንግደም ዳራ የተሰኘ አውሎ ንፋስ ሀገሪቱን በከባዱ በመምታቱ ከገና በፊት በመደረግ ላይ ያሉ ጉዞውች ላይ  መስተጓጎል አስከትሏል።  በተጨማሪም አ
የአሜሪካ ድምፅ

አውሎ ንፋስ ዳራ በእንግሊዝ ከባድ የኃይል መቆራረጥ አስከተለ

በዩናይትድ ኪንግደም ዳራ የተሰኘ አውሎ ንፋስ ሀገሪቱን በከባዱ በመምታቱ ከገና በፊት በመደረግ ላይ ያሉ ጉዞውች ላይ  መስተጓጎል አስከትሏል።  በተጨማሪም አውሎ ንፋሱ በዩናይትድ ኪንግደም በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ዛሬ ቅዳሜ ማለዳ ያለ ኃይል  አቅርቦት አስቀርቷቸዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የአየር ትንበያ ቢሮ የዌልስን እና የደቡብ ምዕራብ እንግሊዝን ክፍሎች የሚሸፍን ከባድ አውሎ ንፋስ ከአርብ ሌሊት  እስከ ቅዳሜ ንጋት ድረስ እንደሚከሰት የሚያመላክት  ቀይ ማንቂያ አውጥቶ ነበር። በተመሳሳይ መንግስት አርብ ዕለት ማማሻውን በድምጽ በላከው ማስጠንቀቂያ ሦስት ሚሊየን የሚደርሱ ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ አሳሰቦ ነበር። ዳራ በዚህ በክረምት ወር የተከሰተ አራተኛው ከፍተኛ አውሎ ንፋስ ነው። አውሎ ንፋሱን ተከትሎ በእንግሊዝ ዛሬ ቅዳሜ እና ነገ እሁድ ከፍተኛ ዝናብ እንደሚዘንብ ይጠበቃል። በዚህ የተነሳም በመላው ዩናይትድ ኪንግደም ከመቶ በላይ የጎርፍ ማስጠንቀቂያዎች ወጥተዋል። በሰሜን ምዕራብ እንግሊዝ አንድ ግለሰብ መኪና ውስጥ ሳለ ዛፍ ወድቆበት ሕይወቱ ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል። በአውሎ ንፋሱ የተነሳም ከግላስጎው ወደ ኤድንብራ ስኮትላንድ እንዲሁም ካምብሪጅ እና በምሥራቅ እንግሊዝ ስታንስቴድ አውሮፕላን ማረፊያ መካከል ያለውን ጨምሮ በተለያዩ የባቡር ጉዞዎች ተቋርጠዋል ወይም ታግደዋል።

በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ተቋረጠ

ዛሬ ቅዳሜ በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋም በፌስቡክ ገጹ ላይ ዛሬ ቅዳሜ ኀዳር 28/2017 አስታውቋ
የአሜሪካ ድምፅ

በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ተቋረጠ

ዛሬ ቅዳሜ በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋም በፌስቡክ ገጹ ላይ ዛሬ ቅዳሜ ኀዳር 28/2017 አስታውቋል። አገልግሎቱ ለኤሌክትሪክ መቋረጡ ምክንያት የሲስተም ችግር መሆኑንም ባሰፈረው አጭር መግለጫ ጠቁሟል። «የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው።» በማለት ዜጎች በትዕግስት እንዲጠብቁ አሳሰቧል። ስለጉዳዩ የአሜሪካ ድምጽ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እየሞከረ ነው።

የሶሪያ አማጽያን በፍጥነት ከተሞችን መቆጣጠራቸውን ቀጥለዋል

የሶሪያ አማጽያን የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን የ24 ዓመት አገዛዝ ለመደምሰስ በምዕራባዊ ሶሪያ ሆምስ ግዛት ዙሪያ ግስጋሴያቸውን አበርትተው ቀጥለዋል። አማ
የአሜሪካ ድምፅ

የሶሪያ አማጽያን በፍጥነት ከተሞችን መቆጣጠራቸውን ቀጥለዋል

የሶሪያ አማጽያን የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን የ24 ዓመት አገዛዝ ለመደምሰስ በምዕራባዊ ሶሪያ ሆምስ ግዛት ዙሪያ ግስጋሴያቸውን አበርትተው ቀጥለዋል። አማጽያኑ ከሳምንት በፊት አሌፖን ዘልቀው ከገቡበት ጊዜ አንስቶ፣ በመላ ሀገሪቱ ያሉ የመንግስት መከላከያዎች በአስደናቂ ፍጥነት መፈራረስ መጀመራቸው ተሰምቷል። አማጽያኑ ሰሜን አሌፖን እና በመሃላዊ  ሀማ እንዲሁም በምሥራቅ ዲር አል ዞርን ከመያዛቸው በተጨማሪ፤ ከደቡባዊ ሱዋይዳ እና ዴራ ተነስተው አርብ ዕለት ሁለቱን ከተሞች መቆጣጠራቸውን የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን ለጥፈዋል። ሩሲያ ዜጎቿ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ትላንት አርብ  ስታሳስብ  በተመሳሳይ ኢራን ዲፕሎማቿን ከነቤተሶቦቻቸው ከሶሪያ ማስወጣቷን የኢራን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ዩክሬን ከዴንማርክ ኤፍ 16 ተዋጊ ጄቶችን መረከቧን አስታወቀች

ዴንማርክ ለሁለተኛ ጊዜ የኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች ወደ ለዩክሬን መለገሷን ፕሬዚዳንት ቮሎደሚር ዘለንስኪ አስታውቀዋል። በተጨማሪም ዛሬ ቅዳሜ ፕሬዚዳንቱ  ወደ ፓሪ
የአሜሪካ ድምፅ

ዩክሬን ከዴንማርክ ኤፍ 16 ተዋጊ ጄቶችን መረከቧን አስታወቀች

ዴንማርክ ለሁለተኛ ጊዜ የኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች ወደ ለዩክሬን መለገሷን ፕሬዚዳንት ቮሎደሚር ዘለንስኪ አስታውቀዋል። በተጨማሪም ዛሬ ቅዳሜ ፕሬዚዳንቱ  ወደ ፓሪስ በመጓዝ በፈረንሳይ ከከፍተኛ ፖለቲከኞች እና ታላላቅ ሹማምንቶች ጋር ተገናኝተዋል። ዘለንስኪ በቴሌግራም በላኩት መልዕክታቸው ዴንማርክን ያወደሱ ሲሆን በሌሎች አጋሮቻቸው ዘንድ  ቁርጠኝነት ባለመኖሩ ማዘናቸውን ገልጸዋል። “በዴንማርክ የተለገሱን የመጀመሪያዎቹ አውሮፕላኖች ህዝቦቻችንን እና መሠረተ ልማቶቻችንን ለመታደግ በሩስያ ላይ ሚሳኤሎችን እየጣሉ ነው።”  ያሉ ሲሆን አያይዘውም  “አሁን የአየር ኃይላችን  ይበልጥ ተጠናክሯል፤ ሁሉም አጋሮች ይህን ያህል ቁርጠኝነት ቢኖራቸው ኖሮ የሩሲያን ሽብር ማቆም በቻልን ነበር” ብለዋል።   የዘለንስኪ መግለጫ የወጣው ሩሲያ በዛፖሬዢያ ግዛት በፈጸመችው ጥቃት አስር ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የሀዘን አዋጅ በታወጀበት በዚህ ወቅት ነው። የአካባቢውን አገልግሎት መስጫ ተቋም ላይ ያረፈው የሩሲያ ጥቃት  ሁለት ህጻናትን ጨምሮ 24 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የአካቢው ሀገረ ገዥ ኢቫን ፌዶሮቭ አስታውቀዋል። ዘለንስኪ ከጥቃቱ ጋር አያይዘው ንግግር ባደረጉበት ወቅት የሩሲያው ፕሬዚዳንት ‘እውነተኛ ሰላም’ አይሹም ሲሉ ወንጅለዋል። በጎርጎርሳውያኑ 2019 ከደረሰው ከባድ የእሳት ቃጠሎ በኋላ የኖትር ዳም ካቴድራል እድሳትን  እና በድጋሚ ለጎብኚዎች ክፍት መሆንን ለማክበር በፓሪስ በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ የታደሙት ዘለስኪይ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ጨምሮ ከሌሎች የዓለም መሪዎች ጋር ዛሬ ቅዳሜ ይገናኛሉ። በስነ ስርዓቱ ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ይታደማሉ ተብሎ ከሚጠበቁ እንግዶች መካከል አንዱ ናቸው።  የአውሮፓ መሪዎች መጪውን መሪ  ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው እና ሥስት ዓመታት በፈጀው ወረራ ላይ ለዩክሬን ድጋፍ ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ለማሳመን ይፈልጋሉ ። በመርሃግብሩ ላይ  ትራምፕ ከዘለንስኪ ጋር ይገናኙ እንደሆነ እስካሁን ድረስ ግልጽ አልተደረገም።  

ቲክ ቶክ ለጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ እንደሚል አሳወቀ

በዋሽንግተን የሚገኘው የፌደራል ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ትላንት አርብ ታዋቂው የማኅበራዊ መገናኛ መተግበሪያ ቲክ ቶክ የተወሰነ ድርሻውን ቻይናዊ ላልሆነ ባለ
የአሜሪካ ድምፅ

ቲክ ቶክ ለጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ እንደሚል አሳወቀ

በዋሽንግተን የሚገኘው የፌደራል ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ትላንት አርብ ታዋቂው የማኅበራዊ መገናኛ መተግበሪያ ቲክ ቶክ የተወሰነ ድርሻውን ቻይናዊ ላልሆነ ባለቤት እንዲሸጥ አሊያም በቀጣይ  ወር ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እንዲዘጋ የሚያስገድድ ህግ አፀድቋል። ፍርድ ቤቱ ቲክ ቶክ ለብሔራዊ ደኅንነት አደጋ እንዳለው በፌዴራል መንግሥት የቀረቡት “አሳማኝ”ክርክሮችን ለውሳኔው መሰረት መሆናቸውን አስታውቋል። የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ቲክ ቶክ የተጠቃሚዎቹ ግላዊ መረጃዎችን በብዛት በመሰብሰቡ፣እንዲሁም የቻይና መንግስት የሚቆጣጠረ ባይትዳንስ ኩባንያ መተዳደሩ  ለአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት ልዩ አደጋ ያመጣል በሚል ተከራክሯል። ቲክቶክ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ብይን ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ እንደሚል ወዲያውኑ ምላሽ ሰጥቷል። ኩባንያው በድረ-ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫም “ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአሜሪካውያንን የመናገር መብት በመጠበቅ ረገድ የተረጋገጠ ታሪክ አለው፤ እናም በዚህ አስፈላጊ ህገ-መንግስታዊ ጉዳይ ላይም ይኸንኑ ያደርጋሉ ብለን እንጠብቃለን” ብሏል። የፍርድቤቱ ውሳኔ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በአለምአቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሆነ እድገት ያስመዘገበውን፤ እና  170 ሚሊዮን የሚደርሱ አሜሪካውያን በመደበኛነት የሚጠቀሙትን የማኅበራዊ መገናኛ  እንዲቋረጥ ሊያደርግ የሚችል ሲሆን በተለይም በመተግበሪያው ላይ የተለያዩ ይዘቶችን ለሚያቀርቡ እና ኑሯቸውን በመተገበሪያው የሚደግፉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካውያንን  ከተመልካቾቻቸው የሚያቆራርጥ ነው። መጭው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም የቲክቶክ እገዳን ሲደግፉ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ሃሳባቸውን በመቀየር ስራ ሲጀምሩ የመጀመሪያው እርምጃቸው መተግበሪያውን ማዳን እንደሚሆን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ይህን ለማድረግ ምን ዓይነት አማራጮች ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ግልጽ አይደለም።

የቆዳ ውጤቶች ንድፍ ባለሞያዋ ሩት 

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የቆዳ እና ሌጦ ምርት ቢኖራትም ከዘርፉ ብዙም ተጠቃሚ አይደለችም። ለዚህም  ፈጠራ የታከለባቸው የቆዳ ምርቶችን ዲዛይን የሚነድፉ 
የአሜሪካ ድምፅ

የቆዳ ውጤቶች ንድፍ ባለሞያዋ ሩት 

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የቆዳ እና ሌጦ ምርት ቢኖራትም ከዘርፉ ብዙም ተጠቃሚ አይደለችም። ለዚህም  ፈጠራ የታከለባቸው የቆዳ ምርቶችን ዲዛይን የሚነድፉ ተወዳዳሪ ባለሙያዎች በበቂ ደረጃ አለመኖራቸው አንዱ ምክንያት እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡  ሆኖም አሁን  የዘርፉ ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ብቅ ብቅ እያሉ ነው። ሩት ግርማይ ከነዚህ አንዷ ናት። በይበልጥ አፍሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ ቀለም ያላቸውን መልዕክት አዘል ቦርሳዎች ዲዛይን በማድረግ ለገበያ ታቀርባለች፡፡  በአፍሪካ ደረጃ በተካሔዱ 2 ተከታታይ በቆዳ ውጤቶች ንድፍ (ዲዛይን) ውድድሮችን አሸንፋለች፡፡  ሩት ግርማይ ከአሜሪካ ድምጽ ጋራ የነበራትን ቆይታ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

በኮንጎ  ህይወት እየቀጠፈ ባለው በሽታ ላይ አስቸኳይ ርምጃ እንዲወሰድ ዶክተሮች እየወተወቱ ነው 

የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቢያንስ የ79 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎ
የአሜሪካ ድምፅ

በኮንጎ  ህይወት እየቀጠፈ ባለው በሽታ ላይ አስቸኳይ ርምጃ እንዲወሰድ ዶክተሮች እየወተወቱ ነው 

የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቢያንስ የ79 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያጠቃውን ዐዲስ በሽታ ምንነት ለመለየት እየታገለ መኾኑን አስታወቀ። የደቡባዊ አፍሪካ «የዶክተሮች ማኅበር ለሰብዓዊ መብት» የተባለው ስብስብ፣ በሽታው ወደ ሌሎች ሀገራት እንዳይዛመት አካባቢያዊ ትብብር እንደሚያስፈልግ አሳስቧል። ኮሎምበስ ማቭሁንጋ ከዚምባብዌ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

«አስራኤል በፍልስጥኤማዊያን ላይ የዘር ማጥፋት ፈፅማለች» አምነስቲ ኢንተርናሽናል 

እስራኤል ጋዛ ውስጥ በፍልስጥኤም ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት አድራጎት ፈፅማለች ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ወንጅሏታ
የአሜሪካ ድምፅ

«አስራኤል በፍልስጥኤማዊያን ላይ የዘር ማጥፋት ፈፅማለች» አምነስቲ ኢንተርናሽናል 

እስራኤል ጋዛ ውስጥ በፍልስጥኤም ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት አድራጎት ፈፅማለች ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ወንጅሏታል። አምነስቲ ግጭት እየቀጠለ ባለበት ሁኔታ እንዲህ ዓይነት ውንጀላ ሲያቀርብ ይህ የመጀመሪያው ነው።እስራኤል ክሱን አጥብቃ አጣጥላለች። ሄንሪ ሪጅዌል ከለንደን ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

አዲሱ የቀረጥ እቅድ በአሜሪካውያን ገበሬዎች እና የምጣኔ ሃብት አዋቂዎች ዓይን 

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ከሦስቱ የዩናይትድ ስቴትስ ዋነኛ የንግድ ሸሪኮች ወደ አገራቸው በሚገቡ ምርቶ
የአሜሪካ ድምፅ

አዲሱ የቀረጥ እቅድ በአሜሪካውያን ገበሬዎች እና የምጣኔ ሃብት አዋቂዎች ዓይን 

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ከሦስቱ የዩናይትድ ስቴትስ ዋነኛ የንግድ ሸሪኮች ወደ አገራቸው በሚገቡ ምርቶች ላይ ቀረጥ እጥላለሁ’ ሲሉ ዝተዋል። የአሜሪካ ድምጹ ኬኔ ፋራቦው ያደረሰን ዘገባ ትረምፕ በውሳኔያቸው ከጸኑ ርምጃው ሊያስከትል የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ይፈትሻል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

Get more results via ClueGoal