Ethiopia



ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ዲፕሎማሲያዊ ግፊት ለማድረግ በመካከለኛው ምሥራቅ ይገኛሉ

በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረገ ግፊት ለማድረግ እንዲሁም ባሻር አል-አሳድ ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ የተፈጠረውን ችግር በቅርብ ለመመልከት የፕሬዝደንት

ደሴ ላይ ይገነባል ለተባለው ሆስፒታል ከሕዝብ ተሰብስቦ ገቢ አልተደረገም የተባለ ገንዘብ ክርክር አስነሳ

ደሴ ከተማ ላይ ሊገነባ ለታቀደው፣ “ወሎ ተርሸሪ ኬር የልእለ ህክምናና ትምህርት ማዕከል” ግንባታ ከሕዝብ የተሰበሰበው ገንዘብ በአግባቡ ገቢ እንዳልተደረገ የ
የአሜሪካ ድምፅ

ደሴ ላይ ይገነባል ለተባለው ሆስፒታል ከሕዝብ ተሰብስቦ ገቢ አልተደረገም የተባለ ገንዘብ ክርክር አስነሳ

ደሴ ከተማ ላይ ሊገነባ ለታቀደው፣ “ወሎ ተርሸሪ ኬር የልእለ ህክምናና ትምህርት ማዕከል” ግንባታ ከሕዝብ የተሰበሰበው ገንዘብ በአግባቡ ገቢ እንዳልተደረገ የፌደራል ዋና ኦዲተር አስታወቀ። ኦዲተር መሥሪያ ቤቱ ባቀረበው ሪፖርት፣ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱን ተጠያቂ አድርጓል። የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ በበኩላቸው፣ ለፕሮጀክቱ ገቢ ማሰባሰቢያ እንዲኾን በሚል የርዳታ ገንዘብ ለማሰባሰቢያ የተበተኑት ኩፖኖችና የሎተሪ ትኬቶችን መልሶ ለመሰብሰብ የተለያዩ ችግሮች ስላጋጠሟቸው ገንዘቡን መሰብሰብ እንዳልቻሉ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። በውዝግቡ ዙሪያ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የኢትዮጵያና የሶማሊያ ስምምነት በተንታኞች እይታ

በያዝነው ሳምንት በሶማሊያና ኢትዮጵያ መሪዎች መካከል አንካራ ላይ የተፈጸመውን ስምምነት አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የአፍሪካ ኅብረት እንዲሁም ኢጋድ በመ
የአሜሪካ ድምፅ

የኢትዮጵያና የሶማሊያ ስምምነት በተንታኞች እይታ

በያዝነው ሳምንት በሶማሊያና ኢትዮጵያ መሪዎች መካከል አንካራ ላይ የተፈጸመውን ስምምነት አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የአፍሪካ ኅብረት እንዲሁም ኢጋድ በመልካም ተቀብለውታል። በስምምነቱ መሠረት ሁለቱ ወገኖች አንዱ የሌላውን የግዛት አንድነት እና ሉዐላዊነት ያከብራል። በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኝት ጥያቄ በተመለከተ በጋራ እንደሚሠሩበት ተመልክቷል። በሌላ በኩል የአንካራው ስምምነት፣ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚኾን አላመላከተም። ሃሩን ማሩፍ ስምምነቱ በሁለቱም ሃገራት እንዲሁም ከሶማሊላንድ ጋራ በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ላይ የሚኖረውን አንድምታ በተመለከተ ሁለት ተንታኞችን አነጋግሯል። እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።

በትረምፕ አስተዳደር ለውጭ ርዳታ በሚመደብ ገንዘብ የኦዲት ቁጥጥር እንደሚኖር ተንታኞች ተነበዩ

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ጥር 20 ቀን ሥልጣን በሚረከበው የተመራጩ ፕሬዝደንት ትረምፕ አስተዳደር የውጭ ርዳታን በሚመለከት የሚነሱ ሁለት ቁልፍ ጥያቄዎች አ
የአሜሪካ ድምፅ

በትረምፕ አስተዳደር ለውጭ ርዳታ በሚመደብ ገንዘብ የኦዲት ቁጥጥር እንደሚኖር ተንታኞች ተነበዩ

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ጥር 20 ቀን ሥልጣን በሚረከበው የተመራጩ ፕሬዝደንት ትረምፕ አስተዳደር የውጭ ርዳታን በሚመለከት የሚነሱ ሁለት ቁልፍ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እነሱም በአኹኑ ወቅት «ዩናይትድ ስቴትስ ምን ያህል ገንዘብ ለውጭ ርዳታ ታወጣለች? ርዳታው የሚሰጠው ለማን ነው? » የሚሉት ናቸው፡፡ የአሜሪካ ድምጿ ቬሮኒካ ኢግሊሲያስ ባልዴራስ የሚያገኙት ርዳታ እንደሚቀነስ የሚጠበቁትን እና የርዳታ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚችሉትን የሚያስቃኝ ዘገባ አጠናቅራለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነታቸው መሻከሩን የሚያመለክቱ ቃላትን መለዋወጥ ጀምረዋል

ከሰሞኑ የኤርትራው ፕሬዝደንት ስለ ኢትዮጵያ ያደረጉት ንግግር እና በኢትዮጵያ በኩል የተሰማው ምላሽ፣ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ የሻከረው የሁለቱ አገራት
የአሜሪካ ድምፅ

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነታቸው መሻከሩን የሚያመለክቱ ቃላትን መለዋወጥ ጀምረዋል

ከሰሞኑ የኤርትራው ፕሬዝደንት ስለ ኢትዮጵያ ያደረጉት ንግግር እና በኢትዮጵያ በኩል የተሰማው ምላሽ፣ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ የሻከረው የሁለቱ አገራት ግንኙነት መቋረጡን የሚያመለክት ነው ሲሉ የቀጣናዊ ጉዳዮች ተንታኞች ተናግረዋል። በዚኽ ጉዳይ ላይ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የሩሲያ የጋዝ አቅርቦት ይቋረጣል በሚል ሥጋት ውስጥ የገባችው ሞልዶቫ የአስቸኳይ ጊዜ ዐወጀች

የሞልዶቫ ፓርላማ ሩሲያ በያዝነው የክረምት ወር የአውሮፓ ኅብረት እጩ ወደሆነችው ሀገር ትልክ የነበረውን የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት ልታቋርጥ ትችላለች በሚል ሥጋ
የአሜሪካ ድምፅ

የሩሲያ የጋዝ አቅርቦት ይቋረጣል በሚል ሥጋት ውስጥ የገባችው ሞልዶቫ የአስቸኳይ ጊዜ ዐወጀች

የሞልዶቫ ፓርላማ ሩሲያ በያዝነው የክረምት ወር የአውሮፓ ኅብረት እጩ ወደሆነችው ሀገር ትልክ የነበረውን የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት ልታቋርጥ ትችላለች በሚል ሥጋት በኃይል አቅርቦቱ ዘርፍ ተፈጻሚ የሚኾን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ አጽድቋል። 101 መቀመጫዎች ያሉት የሞልዶቫ ምክር ቤት ከመጭው ሰኞ አንስቶ የሚጀምር እና ለ60 ቀናት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ለማጽደቅ ድምጽ ሰጥቷል። በዐዋጁም መሠረት ሞስኮ ለትልቁ የሞልዶቫ የጋዝ ማመንጫ ‘ኩሲዩርጋን’ የምታቀርበውን የጋዝ አቅርቦት የምታቋርጥ ከኾነ “አይቀሬ ፈተና” ይደቅናል ያሉትን ሁኔታ ይመራል። የኩሲዩርጋን የኃይል ማመንጫ በሩሲያ ዘመሙ የትራኒስትሪያ ግዛት ይገኛል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2022 መገባደጃ ሩሲያ ከሞልዶቫ በምትዋሰነው ዩክሬን የከፈተችውን ጥቃት ተከትሎ የኩሲዩርጋን የኃይል ማመንጫ ሥራ ተቋርጦ ነበር።

«ዩናይትድ ስቴትስ እና ቱርክ በሦሪያ ጉዳይ የሚስማሙባቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ» - ብሊንከን

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን ዛሬ አርብ ከቱርኩ አቻቸው ጋራ አንካራ ላይ ተገናኝተው ከተነጋገሩ በኋላ በሰጡት አስተያየት ነው፤
የአሜሪካ ድምፅ

«ዩናይትድ ስቴትስ እና ቱርክ በሦሪያ ጉዳይ የሚስማሙባቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ» - ብሊንከን

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን ዛሬ አርብ ከቱርኩ አቻቸው ጋራ አንካራ ላይ ተገናኝተው ከተነጋገሩ በኋላ በሰጡት አስተያየት ነው፤ በዐዲሱ የሦሪያ መንግሥት እውን ኾነው ማየት በሚፈልጓቸው ጉዳዮች ዙሪያ የሚስማሙባቸው በርካታ ጉዳዮች መኖራቸውን ተናግረዋል። ብሊንከን እና የቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሃካን ፊዳን በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሁለቱ ሀገራት በሦሪያ “ሁሉን አቀፍ እና ከወገንተኝነት የጸዳ፤ የህዳጣን ማኅበረሰቦችን እና የሴቶችን መብት የሚያስከብር፣ ለሕዝብ ተቋማት ጥበቃ መረጋገጥ የሚቆምና እና ሕዝብ የሚያስፈልገውን እንዲያገኝ ለማድረግ የሚሠራ ጊዜያዊ መንግሥት እንዲቋቋም ይፈልጋሉ” ብለዋል። ብሊንከን አክለው እንደገለጹት፤ ሁለቱ ሀገራት ጊዜያዊው የሦሪያ መንግሥት ከቀድሞው የሦሪያ ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ መንግሥት የተራረፉ ማናቸውም የኬሚካል ጦር መሳሪያ ዐይነቶችን ፈልጎ እንዲያወድም ይሻሉ። ሦሪያ በጎረቤቶቿ ላይ ስጋት የማትደቅን እና ጊዜያዊው አመራሯም ከአክራሪ ቡድኖች ጋራ  ያለውን ግንኙነት እንዲያቋርጥ የሚፈልጉ መሆናቸውን ብሊንከን ተናግረዋል። በተለይም እስላማዊውን አሸባሪ ቡድን - አይሲስን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚደረገውን ጥረት መቀጠል አስፈላጊ መሆኑንም ሁለቱ ባለ ሥልጣናት ጨምረው ገልጸዋል።  የሦሪያው እስላማዊ አማጺ ቡድን ባደረሰው ብርቱ ጥቃት ለ54 አመታት የዘለቀው የአሳድ ቤተሰብ የጭቆና አገዛዝ ማብቃት የፈጠረውን ሁኔታ ተከትሎ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ያቀኑት ብሊንከን፤ የጉዟቸው ሁለተኛ መዳረሻ ካደረጓት አንካራ ላይ ፊዳንን አግኝተው ከማነጋገራቸው አስቀድሞ፤ ትላንት ሃሙስ ከቱርኩ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ጋር መነጋገራቸው ታውቋል። ብሊንከን ዮርዳኖስ ላይም ከንጉስ አብዱላህ ሁለተኛ ቢን አል-ሁሴን እና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አይማን ሳፋዲ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።    

VOA60 Africa - Niger junta suspends BBC radio for three months

The junta suspended BBC radio for three months, accusing the British broadcaster of airing «erroneous information likely to destabilize social peace and undermine the morale of the troops» fighting militants. The junta also said it was «fili
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Niger junta suspends BBC radio for three months

The junta suspended BBC radio for three months, accusing the British broadcaster of airing «erroneous information likely to destabilize social peace and undermine the morale of the troops» fighting militants. The junta also said it was «filing a complaint» against Radio France Internationale.

VOA60 America - Calmer winds, rising humidity help California firefighters battling the Franklin Fire

Calmer winds and rising humidity in Southern California helped firefighters contain the Franklin Fire, officials said Thursday, as they climb through steep canyons to battle a blaze that’s driven thousands out of Malibu. The fire has destroyed four homes an
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Calmer winds, rising humidity help California firefighters battling the Franklin Fire

Calmer winds and rising humidity in Southern California helped firefighters contain the Franklin Fire, officials said Thursday, as they climb through steep canyons to battle a blaze that’s driven thousands out of Malibu. The fire has destroyed four homes and at least six others have been damaged.

VOA60 World - Blinken: US, Turkey share 'broad agreement' on Syria

U.S. Secretary of State Antony Blinken said there was “broad agreement” between Turkey and the United States on what they would like to see in Syria following the ouster of President Bashar Assad.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - Blinken: US, Turkey share 'broad agreement' on Syria

U.S. Secretary of State Antony Blinken said there was “broad agreement” between Turkey and the United States on what they would like to see in Syria following the ouster of President Bashar Assad.

አዲሱ የትረምፕ አስተዳደር ስደተኞችን ከሀገር የሚያስወጣበትን ዘመቻ በጦር ሠራዊቱ ለመደገፍ እየተሰናዳ ነው

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ማረጋገጫ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞች ከሀገር ለማስወጣት የወጠኑት ዘመቻ በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ከ
የአሜሪካ ድምፅ

አዲሱ የትረምፕ አስተዳደር ስደተኞችን ከሀገር የሚያስወጣበትን ዘመቻ በጦር ሠራዊቱ ለመደገፍ እየተሰናዳ ነው

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ማረጋገጫ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞች ከሀገር ለማስወጣት የወጠኑት ዘመቻ በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ከሁሉ ግዙፉ ይሆናል ሲሉ ቃል ገብተዋል። ይሁንና አተገባበር እና ሕጋዊነቱ ጥያቄዎችን ያስነሳል። የአሜሪካ ድምጿ የኢሚግሬሽን ጉዳዮች ዘጋቢ አሊን ባሮስ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ሠራዊት በእነዚህ እቅዶች ሊሳተፍ የሚችልበትን መንገድ ትቃኛለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

ትረሞፕ ኬሪ ሌክን ለቪኦኤ ዲሬክተርነት አጩ

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ፖለቲከኛ እና የቀድሞ ጋዜጠኛ የነበሩትን ኬሪ ሌክ በመንግሥት ለሚደገፈውና ዓለም አቀፍ ስርጭት ላለው የአሜሪካ ድምጽ ዲሬክ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረሞፕ ኬሪ ሌክን ለቪኦኤ ዲሬክተርነት አጩ

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ፖለቲከኛ እና የቀድሞ ጋዜጠኛ የነበሩትን ኬሪ ሌክ በመንግሥት ለሚደገፈውና ዓለም አቀፍ ስርጭት ላለው የአሜሪካ ድምጽ ዲሬክተርነት እንዲሾሙ ማጨታቸውን ትላንት ረቡዕ አስታውቀዋል። ትረምፕ ‘ትሩዝ ሶሻል’ በተሰኘው ማኅበራዊ መድረካቸው ላይ እንዳስታወቁት፣ ኬሪ ሌክ የቪኦኤ ዲሬክተር ኾነው እንደሚሾሙ አስታውቀዋል። ኬሪ ሌክ የትረምፕ የቅርብ የፖለቲካ አጋርና አሪዞና በሚገኘው የፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ደግሞ የቀድሞ ዜና አቅራቢ ነበሩ። ሌክ ለ27 ዓመታት በጋዜጠኝነት የሠሩ ሲሆን፣ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2021 ዓ.ም ለአሪዞና አገረ ገዢነት ለመወዳደር ሲሉ ሥራቸውን አቁመዋል። በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ለአሜሪካ ሴኔት ተወዳድረው ያልተሳካላቸው ሌክ፣ በምርጫ ዘመቻዎቻቸው አሪዞና “የአሜሪካ ትቅደም ፖሊሲዎች ተምሳሌት” መሆን አለባት ብለዋል። ‘ዩ ኤስ ኤጀንሲ ፎር ግሎባል ሚዲያ’ (USAGM) በመባል ለሚታወቀውና ለአሜሪካ ድምጽ እና ለሌሎችም በመንግሥት ለሚደገፉ የሥርጭት ጣቢያዎች እናት ድርጅት ለኾነው መንግሥታዊ ተቋም ዋና ሥራ አስፈጻሚ በቅርቡ እንደሚሾሙ ትረምፕ ትላንት ረቡዕ ጨምረው አስታውቀዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው በፕሬዝደንቱ የሚታጭ ሲኾን፣ በሕግ አውጪው ሸንጎ ወይም ሴኔት መጽደቅ ይኖርበታል። ለዋና ሥራ አስፈጻሚነት የሚመርጡት ግለሰብ ኬሪ ሌክን እንደሚሾሙና ሁለቱ ሹሞች በቅርበት እንደሚሠሩም ትረምፕ ጨምረው አስታውቀዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው ‘ዩ ኤስ ኤጀንሲ ፎር ግሎባል ሚዲያ’ (USAGM) በተቀመጠለት ተልዕኮ መሠረት ነጻ ብዙሃን መገናኛዎች ውስን ወደሆኑባቸው ሃገራት ተአማኒና ትክክለኛ የጋዜጠኝነት ሥራዎች መሰራጨታቸውን ያረጋግጣል። የቪኦኤ የወቅቱ ዲሬክተር ማይክ አብራሞዊትዝ ዛሬ ሐሙስ ማለዳ ለድርጅቱ ሠራተኞች በላኩት የኢሜይል መልዕክት፣ ኬሪ ሌክን በተመለከተ የወጣውን መረጃ ረቡዕ ምሽት መመልከታቸውንና፣ በማኅበራዊ መድረክ ላይ ከወጣው ውጪ ሌላ ተጨማሪ መረጃ እንዳልተሰጣቸው አስታውቀዋል። “በዩ ኤስ ጂ ኤምም ሆነ በቪኦኤ የሚደረጉ የሥልጣን ሽግግሮችን በመልካም እቀበላለሁ” ያሉት አብራሞዊትዝ፣ የቪኦኤን ዲሬክተር ሹመት በተመለከተ “ከአዲሱ አስተዳደር ጋራ ለመተባበርና የሽግግር ሂደቱንም ለመከተል እሻለሁ” ብለዋል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጥር 2020 ዓ.ም የኤጀንሲውን አስተዳደር እንደገና ስለማዋቀር የወጣው ሕግ የዩ ኤስ ጂ ኤም ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሥሩ ያሉ ኃላፊዎችን የመቅጠርና የማባረር ሥልጣን ተሰጥቶታል። ነገር ግን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ታኅሣሥ 2020 ዓ.ም. ላይ በሁለቱም ፓርቲዎች በጋራ በወጣው ሕግ መሠረት፣  ዋና ሥራ አስፈጻሚው ወይም አስፈጻሚዋ ኃላፊዎቹን ለመቀየር የ’ዓለም አቀፍ ሥርጭት አማካሪ ቦርድ’ የተባለው አካል በድምጽ ብልጫ መወሰን አለበት፡፡ ቦርዱ የውጪ ጉዳይ ምኒስትሩ እና በፕሬዝደንቱ የሚሾሙ ስድስት ዓባላት ሲኖሩት፣ እያንዳንዱ ዓባልም የተለያየ የአገልግሎት ዘመን አለው። የቦርዱ ኃላፊነትም የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሥርጭት ጣቢያዎቹን የኤዲቶሪያል ነጻነትና ሃቀኛ የሆነ መርህን እንዲያከብሩና እንዲያረጋግጡ እንዲሁም ጋዜጠኝነት የሚጠይቀው ከፍተኛ መመዘናዎች መሟላታቸውን ማረጋገጥ ነው። ኬሪ ሌክ በX ማኅበራዊ መድረክ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ለቪኦኤ ኃላፊነት በመታጨታቸው ክብር እንደሚሰማቸው አስታውቀዋል። ቪኦኤ “እጅግ አስፈላጊ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋም ነው” ያሉት ሌክ “ዲሞክራሲንና እውነትን” የሚያበረታታ ተቋምም ነው ሲሉ አክለዋል። “በእኔ አመራር ቪኦኤ በተልዕኮው የላቀ አፈጻጸም ይኖረዋል። የአሜሪካንን ስኬትም ለዓለም ያሳውቃል” ብለዋል ሌክ። ቪኦኤ የኬሪ ሌክን አስተያየት ለማግኘት በዘመቻ ድህረ ገጻቸው ላይ በሚገኘው የሚዲያ ክፍል አማካይነት ሞክሯል። ይህ ዜና እስከታተመበት ሰዓት ምላሽ ማግኘት አልቻለም። ቪኦኤ በሳምንት 354 ሚሊዮን ለሚሆኑ አድማጮቹ በ49 ቋንቋዎች የሚያሰራጭ ሲሆን፣ የወቅቱ ዲሬክተር የሆኑት ማይክ አብራሞዊትዝ የፍሪደም ሃውስ የቀድሞ ፕሬዝደንትና በዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ለ 24 ዓመታት አዘጋጅ ነበሩ።

በላሊበላ ከተማ ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

በአማራ ክልል በግጭት ውስጥ ያሉ ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ ተካሂደ፡፡ ሰልፈኞቹ በአካባቢው ባ
የአሜሪካ ድምፅ

በላሊበላ ከተማ ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

በአማራ ክልል በግጭት ውስጥ ያሉ ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ ተካሂደ፡፡ ሰልፈኞቹ በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የቱሪዝም እንቅስቃሴው ተስተጓጉሏል፤ የከፋ ድህነት እየተስተዋለ ነው ብለዋል፡፡ ሰልፉ በመንግሥት ትእዛዝና አስገዳጅነት እንጅ በሕዝብ ፍላጎት የተዘጋጀ አይደለም ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ የተናገሩም አሉ፡፡ የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ሰልፉን ከአጎራባች ወረዳዎች ጋራ በመተባበር ማዘጋጀቱን አስታውሶ በፈቃደኘነት እንጅ በአስገዳጅ ትእዛዝ የተሳተፈ የለም ሲሉ ትችቱን አስተባብለዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የሀዲያ ሚዲያ ዩቲይብ ባለቤት በሁለት ክስ ነፃ ሲባል አንዱን እንዲከላከል ተወሰነ

በእስር ላይ የሚገኘው የሀዲያ ሚዲያ ሃውስ ዩቲዩብ ባለቤት አቶ መለስ አብርሀም ከቀረቡበት ሦስት ክሶች በሁለቱ «ነጻ» ሲባል ፣ ርእሰ መስተዳደሩ በመተቸ
የአሜሪካ ድምፅ

የሀዲያ ሚዲያ ዩቲይብ ባለቤት በሁለት ክስ ነፃ ሲባል አንዱን እንዲከላከል ተወሰነ

በእስር ላይ የሚገኘው የሀዲያ ሚዲያ ሃውስ ዩቲዩብ ባለቤት አቶ መለስ አብርሀም ከቀረቡበት ሦስት ክሶች በሁለቱ «ነጻ» ሲባል ፣ ርእሰ መስተዳደሩ በመተቸት በሚለው በአንዱ ክስ እንዲከላከል ብይን ተሰጠ። የመከላከያ ምስክሮቹን እንዲያሰማም የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትላንት ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ባስቻለው ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ተከሳሹ በዋስ እንዲለቀቅ ፍርድ ቤት ቢወስንም፣ አኹንም በእስር ላይ እንደሚገኝ ወንድሙ ለአሜሪካ ድምጽ ገልጿል። ከክልሉና ከዞኑ ባለሥልጣናት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የኢትዮጵያና የሶማሊያ ሥምምነት የጦርነት ሥጋትን እንደቀነሰላቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ

ኢትዮጵያና ሶማሊያ በመካከላቸው ተፈጥሮ የነበረውን ውጥረት መፍትሄ ለመስጠት የደረሱበትን ሥምምነት፣ ለሁለቱ ሀገራትና ለቀጣናው ሠላምና መረጋጋት እንዲሁም
የአሜሪካ ድምፅ

የኢትዮጵያና የሶማሊያ ሥምምነት የጦርነት ሥጋትን እንደቀነሰላቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ

ኢትዮጵያና ሶማሊያ በመካከላቸው ተፈጥሮ የነበረውን ውጥረት መፍትሄ ለመስጠት የደረሱበትን ሥምምነት፣ ለሁለቱ ሀገራትና ለቀጣናው ሠላምና መረጋጋት እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንደሚኖረው ከአዲስ አበባ ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡንን ነዋሪዎች አስተያየት ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የኢትዮጵያውያንና ሶማሌያውያን አስተያየት

ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ተለይታ የራስ-ገዝ አስተዳደር ከመሰረተችው ሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ጋራ በተፈራረመችው አወዛጋቢ የባህር በር ግንኙነት ስምምነት ምክንያት አ
የአሜሪካ ድምፅ

የኢትዮጵያውያንና ሶማሌያውያን አስተያየት

ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ተለይታ የራስ-ገዝ አስተዳደር ከመሰረተችው ሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ጋራ በተፈራረመችው አወዛጋቢ የባህር በር ግንኙነት ስምምነት ምክንያት አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ ገብተው የነበሩት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አለመግባባታቸውን በስምምነት ለመፍታት ትላንት ረቡዕ ተፈራርመዋል። ስምምነቱን በተመለከተ፣ በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩና የመቋድሾ ነዋሪዎችን ጠይቀናል። አስተያየታቸውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።    

የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ኢትዮጵያ እራሷን ከሶማሊያ ከገነጠለቸው የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ጋራ በተፈራረመችው አወዛጋቢ የባህር በር ስምምነት ምክንያት አንድ ዓመ
የአሜሪካ ድምፅ

የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ኢትዮጵያ እራሷን ከሶማሊያ ከገነጠለቸው የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ጋራ በተፈራረመችው አወዛጋቢ የባህር በር ስምምነት ምክንያት አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ የዘለቀውን ዲፕሎማሲያዊ ውዝግባቸውን ለመፍታት ትላንት ረቡዕ ተስማምተዋል፡፡ በቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ሸምጋይነት የተካሄደውን ሦስተኛ ዙር ድርድር ተከትሎ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መህሙድ እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አንዳቸው የሌላውን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ተስማምተዋል። “የአንካራው ስምምነት” ተብሎ በተሰየመው ስምምነት መሰረት፣ “የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ መሪዎች አንዳቸው ለሌላው ሉዓላዊነት፣ አንድነት፣ ነፃነት እና የግዛት አንድነት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ሕግ የተደነገገውን የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር እና የአፍሪካ ኅብረት ድንጋጌዎችን ለማክበር እና ለዚህም ያላቸውን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ” ተስማምተዋል፡፡ መግለጫው አክሎም ፣ “በተጨማሪም ሁለቱ መሪዎች በወዳጅነት እና በመከባበር መንፈስ ልዩነቶችን እና አወዛጋቢ ጉዳዮችን በመተው እና በመተጋገዝ የጋራ ብልጽግናን ለማስፈን በትብብር ለመቀጠል ተስማምተዋል” ብሏል። “ሶማሊያ በአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለከፈሉት መስዋዕትነት እውቅና ትሰጣለች። የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ የግዛት አንድነትን በማክበር ከተረጋገጠው የኢትዮጵያ የባህር ተደራሽነት ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ሊገኙ እንደሚችሉ አምነዋል።” ሲልም መግለጫው አክሏል፡፡ ሁለቱ መሪዎች ተቀራርበው በመሥራት የጋራ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውን የንግድ ሥርዐቶች በሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት፣ የኮትንራት፣ የኪራይ እና ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ጨምሮ በሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ሉዓላዊ ሥልጣን ሥር የኢትዮጵያ ፌደራል ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ ከባህርና ወደ ባህር የሚያደርስ በር ተደራሽነት ለማረጋገጥ ተስማምተዋል፡፡ ሁለቱ ሀገሮች “እኤአ በየካቲት 2025 መጨረሻ በቱርክ አመቻችነት በአራት ወራት ውስጥ ተጠናቅቆ ለመፈረም ዝርዝር የአፈጻጸም ነጥቦች ላይ የሚደረገውን ድርድር በቅን ልቦና ለመጀመር ወስነዋል” ሲል መግለጫው ገልጿል። ስምምነቱን ያደራደሩት ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ሁለቱን ወገኖች አድንቀዋል። /በዚህ ጉዳይ ላይ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

VOA60 Africa - Somalia, Ethiopia agree to end dispute

Ethiopia and Somalia agreed on Wednesday to hold “technical talks” to resolve a dispute sparked by Ethiopia’s deal for sea access with the breakaway region of Somaliland, according to a statement following talks in Turkey.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 Africa - Somalia, Ethiopia agree to end dispute

Ethiopia and Somalia agreed on Wednesday to hold “technical talks” to resolve a dispute sparked by Ethiopia’s deal for sea access with the breakaway region of Somaliland, according to a statement following talks in Turkey.

VOA60 America - Trump named Time magazine's «Person of the Year»

President-elect Trump was named Time magazine's «Person of the Year» on Thursday. Time bestowed the «Person of the Year» title on Trump once before, in 2016.
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 America - Trump named Time magazine's «Person of the Year»

President-elect Trump was named Time magazine's «Person of the Year» on Thursday. Time bestowed the «Person of the Year» title on Trump once before, in 2016.

VOA60 World - South Korea: Thousands protest outside the National Assembly calling for President Yoon Suk Yeol to be impeached

South Korea: Thousands of people protest outside the National Assembly, calling for President Yoon Suk Yeol to be impeached over his recent brief imposition of martial law. The demonstration comes just hours after Yoon vowed to fight «until the very las
የአሜሪካ ድምፅ

VOA60 World - South Korea: Thousands protest outside the National Assembly calling for President Yoon Suk Yeol to be impeached

South Korea: Thousands of people protest outside the National Assembly, calling for President Yoon Suk Yeol to be impeached over his recent brief imposition of martial law. The demonstration comes just hours after Yoon vowed to fight «until the very last minute» in a defiant address.

የሶማሊያ ፌዴራል ኃይል ከጁባላንድ አፈገፈገ

የሶማሊያ ወታደሮች በከፊል ራስ ገዝ ከሆነችው ከጁባላንድ ኃይሎች ጋራ ትላንት ከተጋጩ በኋላ ከያዙት ሥፍራ ለቀው ማፈግፈጋቸውን ሞቃዲሾ ዛሬ ሐሙስ አስታውቃለች
የአሜሪካ ድምፅ

የሶማሊያ ፌዴራል ኃይል ከጁባላንድ አፈገፈገ

የሶማሊያ ወታደሮች በከፊል ራስ ገዝ ከሆነችው ከጁባላንድ ኃይሎች ጋራ ትላንት ከተጋጩ በኋላ ከያዙት ሥፍራ ለቀው ማፈግፈጋቸውን ሞቃዲሾ ዛሬ ሐሙስ አስታውቃለች፡፡ ግጭት የማይለያት ሶማሊያ በአምስት ከፊል ራስ ገዝ በሆኑ ክልሎች ማለትም፣ ፑንትላንድ፣ ጁባላንድ፣ ጋልሙዱግ፣ ሂርሸበሌ፣ እና ደቡብ ምዕራብ በተሰኙ ክልሎች የተዋቀረች ናት፡፡ በአህመድ ማዶቤ የሚመሩት የጁባላንድ ኃይሎች ራስ ካምቦኒ በተባለ ሥፍራ ትላንት ረቡዕ ለበርካታ ሰዓታት ከፌዴራል መንግሥት ኃይሎች ጋር ተታኩሰው እንደነበር የመንግሥት እና ወታደራዊ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። “የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት የሶማሊያውያን፣ በተለይም የሃገሪቱ ጦር ሠራዊት ደም እንዳይፈስ መከላከል ግዴታው ነው፣ በመሆኑም ሠራዊቱ ከታችኛው ጁባ ለቆ እንዲወጣ ታዟል” ሲል መንግሥት ባወጣው መግለጫው አስታውቋል። መግለጫው ዝርዝር ጉዳዮችን አላነሳም። ለግጭቱ የማዶቤን ኃይሎች ተጠያቂ አድርጓል። ሠራዊቱ ከአል ሻባብ ኃይሎች ውጪ የትጥቅ ግጭት እንዲያደርግ መመሪያ አልተሰጠውም ሲል አክሏል መግለጫው። ማዶቤ ባለፈው ጥቅምት የተደረገውን የሃገሪቱን ብሔራዊ የምክክር ም/ቤት ጉባኤ ረግጠው ከወጡና ምርጫ በማካሄድ የጁባላንድ ፕሬዝደንት ሆነው በድጋሚ ከተመረጡ በኋላ በሁለቱ ወገኖች በኩል ውጥረቱ ተባብሷል። ስብሰባው የፌዴራል መንግሥት እና አንዳንድ ግዛቶች በመጪው ሰኔ 2017 የአካባቢ ምርጫ ለማካሄድ፣ በመስከረም ደግሞ የግዛቶች እና የፓርላማ ምርጫ ለማድረግ ስምምነት ላይ ቢደርስም፣ ማዶቤ ግን በተጠቀሰው ወቅት ምርጫ ለማካሄድ የሥልጣን ዘመንን ማራዘም ይጠይቃል በሚል ተቃውመው ነበር።

በቱኒዚያ ባሕር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ አደጋ ቢያንስ ዘጠኝ ፍልሰተኞች ሞቱ

በቱኒዚያ ባሕር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ አደጋ ሕይወታቸው ያለፈ የዘጠኝ ፍልሰተኞችን አስከሬን ማግኘታቸውን የሃገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ከደረሰው አ
የአሜሪካ ድምፅ

በቱኒዚያ ባሕር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ አደጋ ቢያንስ ዘጠኝ ፍልሰተኞች ሞቱ

በቱኒዚያ ባሕር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ አደጋ ሕይወታቸው ያለፈ የዘጠኝ ፍልሰተኞችን አስከሬን ማግኘታቸውን የሃገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ከደረሰው አደጋ የተረፉ 27 ፍልሰተኞችን መታደጋቸውንና የስድስት ፍልሰተኞች ፍለጋ መቀጠሉን ባለሥልጣናቱ ጨምረው አስታውቀዋል። የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ወደ አውሮፓ በማቅናት ላይ የነበሩት ፍልሰተኞች ጀልባ በመስጠም ላይ መሆኗን ያየ አሳ አስጋሪ ለባለሥልጣናት ሁኔታውን በማሳወቁ የማዳን እንቅስቃሴ መጀመሩ ተነግሯል። ስምንት ሴቶችን ጨምሮ 42 ፍልሰተኞች ከሰሃራ በታች ካሉ ሃገራት የተነሱ መሆናቸውም ታውቋል። በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ብቻ በቱኒዚያ ባሕር ዳርቻ ከ600 እስከ 700 የሚደርሱ ፍልሰተኞች ሕይወት በጀልባ አደጋ ምክንያት ማለፉን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያና ሶማሊያ የደረሱበትን ሥምምነት “ካለ ምንም መዘግየት” ተግባራዊ እንዲያደርጉ የአፍሪካ ኅብረት ጠየቀ

ኢትዮጵያና ሶማሊያ በመካከላቸው ተፈጥሮ የነበረውን ውጥረት መፍትሄ ለመስጠት የደረሱበትን ሥምምነት “ካለ ምንም መዘግየት” ተግባራዊ እንዲያደርጉ የአፍሪካ
የአሜሪካ ድምፅ

ኢትዮጵያና ሶማሊያ የደረሱበትን ሥምምነት “ካለ ምንም መዘግየት” ተግባራዊ እንዲያደርጉ የአፍሪካ ኅብረት ጠየቀ

ኢትዮጵያና ሶማሊያ በመካከላቸው ተፈጥሮ የነበረውን ውጥረት መፍትሄ ለመስጠት የደረሱበትን ሥምምነት “ካለ ምንም መዘግየት” ተግባራዊ እንዲያደርጉ የአፍሪካ ኅብረት ጠየቀ። የሁለቱ ሃገራት መሪዎች “ጠቃሚ የሆነ ርምጃ” ወስደዋል፣ ያሉት የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት፣ ሆኖም ግን “የተስማሙባቸውን ጉዳዮች ካለመዘግየት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው” ሲሉ በX ማኅበራዊ መድረክ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል። የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ዋና ፀኅፊ ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው፣ “አስፈላጊ እርምጃ” ብለው የገለጹት ሥምምነት፣ “የሁለትዮሽ ጉዳዮችን በወዳጅነት መንፈስ መፍታትን ያሳየ ነው” ብለዋል። ኢትዮጵያ የሶማሊላንድን የባሕር ዳርቻ በኪራይ ለመያዝ ከአንድ ዓመት በፊት ሥምምነት መፈጸሟን ተከትሎ፣ ሉዐላዊነቷ እንደተደፈረ የምትገልጸው ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋራ ውጥረት ውስጥ ከርማለች፡፡ ሶማሊላንድ ለፈጸመችው ሥምምነት በአጸፋው ከኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊና ይፋዊ ዕውቅና እንደምታገኝ ብትገልጽም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህ እንደሚሆን ፈጽሞ አረጋግጦ አያውቅም። የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ መሪዎች ትላንት ረቡዕ ቱርክ ላይ ሰዓታት የፈጀ ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ “ታሪካዊ” ስትል የገለጸችው ሥምምነት በሁለቱ ሃገራት መካከል መፈረሙን አንካራ አስታውቃለች፡፡ የሥምምነቱ ዝርዝሮች በይፋ ባይገለጹም፣ ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሉዐላዊነት ባከበረ መልኩ የባሕር በር እንደምታገኝ ተመልክቷል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አለመግባባታቸውን ለመፍታት ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ፣ ከሶማሊያ ተለይታ የራስ-ገዝ አስተዳደር ከመሰረተችው ሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ጋራ በተፈረመ የመግባቢያ ስምምነት ምክኒያት ለአንድ ዓመት
የአሜሪካ ድምፅ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አለመግባባታቸውን ለመፍታት ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ፣ ከሶማሊያ ተለይታ የራስ-ገዝ አስተዳደር ከመሰረተችው ሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ጋራ በተፈረመ የመግባቢያ ስምምነት ምክኒያት ለአንድ ዓመት ገብተውበት የነበረውን ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ለማቆም ዛሬ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ ከሶማሊያ እና ከኢትዮጵያ መሪዎች ጋር አንካራ ላይ ያደረጉትን ሦስተኛ ዙር፣ ድርድር ተከትሎ የሶማሊያ መሪ ሀሰን ሼክ መሀሙድ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአንዳቸው የሌላውን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ተስማምተዋል። ኤርዶዋን የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድን እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን በፕሬዝዳንታዊው ቤተ መንግሥት ዛሬ ለየብቻ ተቀብለው ካነጋገሯቸው በኋላ ነው ስምምነቱ ይፋ የተደረገው። የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት በሰጠው መግለጫ የዛሬ ስብሰባው “ጠቃሚ” እና በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ለሚደረግ ውይይት መንደርደሪያ እንደሚኾን አስታውቆ ነበር። መሀሙድ አንካራ የገቡት ትላንት ማክሰኞ ሲኾን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ደግሞ ዛሬ ረቡዕ አንካራ መግባታቸውንና ከኤርዶዋን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ኤክስ ላይ ባወጣው ጽሑፍ አስታውቆ ነበር። የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ እና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን «ታሪካዊ» የመግባቢያ ስምምነት ከፈረሙበት እነደ አውሮፓውያን ከጥር 1 ቀን 2024 ጀምሮ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ውዝግብ ውስጥ ገብተው ቆይተዋል። የሶማሌላንድ ባለሥልጣናት ዲፕሎማሲያዊ እውቅና በአጸፋው ለማግኘት ለኢትዮጵያ 20 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የባሕር በር ለ50 ዓመታት በኪራይ እንደሚሰጥ በወቅቱ ተናግረዋል፡፡ የሶማሊያ መንግሥት ሥምምነቱን በጽኑ በመቃወም ውድቅ አድርጎ አምባሳደሩንም ጠርቶ እንደነበር ይታወሳል። ሶማሊያ ስምምነቱን “ሕጋዊ መሠረት የሌለው እና ተፈጻሚ ሊሆን የማይችል” ያለችው ሲሆን “በሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ላይ ግልጽ የሆነ ጥሰት ፈጽማለች" ብላ ኢትዮጵያን ስትከስ ቆይታለች። ኢትዮጵያ ለመግባቢያ ስምምነቱ ተገቢነት ብትሟገትም ለሶማሌላንድ ዕውቅና እንደምትሰጥ በይፋ አረጋግጣ ግን አታውቅም። ባለፈው ሐምሌ እና ነሀሴ ወራት በቱርክ የተካሄዱ ሁለት ዙር ንግግሮች በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ባይችሉም፣ በሦስተኛው ዙር ግን ውይይት ግን ሁለቱ ሀገራት አለመግባባታቸውን ለመፍታት ተስማምተዋል።

የልጆች መጽሐፍት ያሳተሙት እናትና ልጅ

በውጭ ሀገር የተወለዱ አዳጊ ልጆች፣ በሚኖሩበት ሀገር ውስጥ በሳይንሱ ዘርፍ እንዲሳተፉና ውክልና እንዲኖራቸው ሁለት የልጆች መጻሕፍት ተጽፈዋል። ጸሐፊዋ ነዋ
የአሜሪካ ድምፅ

የልጆች መጽሐፍት ያሳተሙት እናትና ልጅ

በውጭ ሀገር የተወለዱ አዳጊ ልጆች፣ በሚኖሩበት ሀገር ውስጥ በሳይንሱ ዘርፍ እንዲሳተፉና ውክልና እንዲኖራቸው ሁለት የልጆች መጻሕፍት ተጽፈዋል። ጸሐፊዋ ነዋሪነታቸውን በቨርጂኒያ ግዛት ያደረጉት፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለሞያዋ የኔነሽ ሸዋነህ ሲኾኑ የ13 ዓመት ልጃቸውም ከሌላ ተባባሪ ጸሐፊ ጋራ በመኾን የልጆች መጽሐፍ አሳትሟል። እናትና ልጅን አነጋግረናል ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በሱሉልታ በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ሁለት ፖሊሶች ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ትላንት ጠዋት በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት፣ የወረዳው ፖሊስ አዛዥና አንድ ፖሊስ መገደላቸው
የአሜሪካ ድምፅ

በሱሉልታ በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ሁለት ፖሊሶች ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ትላንት ጠዋት በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት፣ የወረዳው ፖሊስ አዛዥና አንድ ፖሊስ መገደላቸውን የሱሉልታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አበበ ወርቁ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። ሁለት ሌሎች ሰዎችም በታጣቂዎቹ ታግተው መወሰዳቸውን ተናግረዋል። የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች ግድያውን መፈፀማቸውን አምነዋል። “ሰዎቹን አግተን ሳይኾን ማርከን ወስደናቸዋል” ብለዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ትረምፕ የሦሪያን ጉዳይ በሩቁ ማየት የመረጡ ይመስላል፣ ይሳካ ይሆን?

አማጽያን ፕሬዝደንት በሻር አል አሳድን ከሥልጣን ማስወገዳቸውን ተከትሎ ዶናልድ ትረምፕ በሦሪያ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው ፍንጭ አሳይተዋል
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ የሦሪያን ጉዳይ በሩቁ ማየት የመረጡ ይመስላል፣ ይሳካ ይሆን?

አማጽያን ፕሬዝደንት በሻር አል አሳድን ከሥልጣን ማስወገዳቸውን ተከትሎ ዶናልድ ትረምፕ በሦሪያ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው ፍንጭ አሳይተዋል። ይሁን እንጂ የአሜሪካ ድምጿ የዋይት ሀውስ ቢሮ ኃላፊ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ በዘገባዋ እንዳመለከተችው ተመራጩ ፕሬዝዳንት፤ የእስራኤልን ደህንነት ማስጠበቅ፣ ኢራንን ማግለል እና እንዲሁም ከሩሲያ፣ ቱርክ እና ሌሎች ጋራ የሚኖራትን ግንኙነት ጨምሮ ዩናይትድ ስቴትስ ከአሏት ግቦች ጋራ ማጣጣም ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት እና ጁባላንድ መካከል ውጊያ ተቀሰቀሰ

በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት እና በጁባላንድ የክልል አስተዳደር መካከል ለሳምንታት የቆየው የፖለቲካ ልዩነት እና ውጥረት ተባብሶ፣ በደቡብ ሶማሊያ ግጭት ተቀስ
የአሜሪካ ድምፅ

በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት እና ጁባላንድ መካከል ውጊያ ተቀሰቀሰ

በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት እና በጁባላንድ የክልል አስተዳደር መካከል ለሳምንታት የቆየው የፖለቲካ ልዩነት እና ውጥረት ተባብሶ፣ በደቡብ ሶማሊያ ግጭት ተቀስቅሷል። ግጭቱ የተካሄደው፣ በቅርቡ የፌደራል ኃይሎች በተሰማሩባት ራስካምቦኒ የተሰኘች ከተማ ነው። ሁለቱም ወገኖች ግጭቱን በመቀስቀር እርስ በእርስ የተወነጃጀሉ ሲሆን፣ ምን ያክል ጉዳት እንደደረሰ እስካሁን በውል አልታወቀም። በሁለቱ ወገኖች መካከል ውዝግቡ የተቀሰቀሰው በቅርቡ በጁባላንድ የተደረገውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተከትሎ ሲሆን የፌደራል መንግስቱ ሕገወጥ ነው በማለት ውድቅ አድርጎታል። በፌደራሉ አመራር እና በክልሉ አስተዳደሪዎች መካከል እየተካረረ የሄደው የፖለቲካ ውዝግብ ተባብሶ፣ ረቡዕ እለት በፌደራል መንግስቱ ወታደሮች እና በጁባላንድ ኃይሎች መካከል ከፍተኛ ውጊያ መካሄዱ ተገልጿል። በአካባቢው የስልክ መስመር በመቋረጡ ዝርዝር መረጃ ማግኘት ባይቻልም፣ በጁባላንድ የሚገኙ የጸጥታ ኃይሎች የመጀመሪያውን ጥቃት የፈፀሙት የፌደራል ኃይሎች ናቸው በማለት ይከሳሉ። የጁባላንድ ምክትል የደህንነት ሚኒስትር ኤደን አህመድ ሃጂ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ «ከሞቃዲሾ ወደ ራስካምቦኒ የመጡት የፌደራል ኃይሎች በጁባላንድ ኃይሎች ላይ ጥቃት ፈፅመዋል። ጥቃቱ የጀመረው በድሮን ሲሆን፣ ውጊያው እየተካሄደ ያለው ከከተማ ወጣ ብሎ ነው። ግጭቱ ተስፋፍቶ አሁንም እንደቀጠለ ነው። የመንግሥት ኃይሎች አንድ ክፍል እጁን ሰጥቷል» ብለዋል። ጁባላንድ በርካታ የፌደራል መንግስት ወታደሮች እጃቸውን መስጠታቸውን የምትገልፅ ሲሆን፣ የክልሉ ባለስልጣናትም የፌደራል ኃይሎች የሚጠቀሟቸውን ሰው አልባ አሮፕላኖች የሰጡ ሀገራትን ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን ብለዋል። «የሁለቱም ወገኖች ወታደሮች በአንድ መከላከያ ኃይል ውስጥ የሚገኙ ወንድማማቾች ሆነው ሳለ፣ ዛሬ እርስ በእርስ መተኳኮሳቸው በጣም ያሳዝናል» ያሉት የጁባላንድ የደህንነት ሚኒስትር፣ «የሶማሊያ ፌደራል መንግስት ኃላፊነት ነው። የሶማሊያን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያገለግሉ ጦር መሳሪያዎች እና ተሽከርካሪዎች በሕዝብ ላይ ለጥቅም መዋላቸው የሚያሳዝን ነገር ነው» ሲሉ ፌደራል መንግስቱን ወንጅለዋል። የሶማሊያ ፌደራል መንግስት መከላከያ ሚኒስትር በበኩሉ «ያልተጠበቀ ጥቃት» ሲል የገለፀውን ጥቃት፣ በፌደራል ወታደሮች ቁጥጥር ስር በሚገኘው ስፍራ እና ለሰራዊቱ ድጋፍ የሚሰጡ የአካባቢው ሰራተኞች ላይ በማድረስ የጁባላንድ ኃይሎችን ከሷል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫም የፌደራል ኃይሎች በአካባቢው የሰፈሩት፣ የአፍሪካ ህብረት ኃይሎች በቅርቡ የለቀቁትን ወታደራዊ ካምፕ ለመረከብ እና በአልሻባብ ላይ የጸረ ሽብር ዘመቻዎች ለማዘጋጀት መሆኑን ገልጿል። ሆኖም ሁለቱም ወገኖች የሚያቀቧቸውን ክሶችም ሆነ ውጊያው በምን ያክል መጠን እየተካሄደ መሆኑን በገለልተኛ አካል ማረጋገጥ አልተቻለም። የሶማሊያ መንግስት በቅርቡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ራስካምቦኒ ከተማ ውስጥ ያሰፈረ ሲሆን፣ ጁባላንድ ድርጊቱ የክልሉን ደህንነት እና አስተዳደር ለማዳከም የተደረገ ነው ብሏል። የፌደራል ባለስልጣናቱ ግን፣ ወታደሮቹ የሰፈሩት ከአፍሪካ ህብረት መውጣት ጋር ተያይዞ በቦታው የነበሩት የኬንያ ኃይሎች ስፍራውን በመልቀቃቸው ነው ሲል ይከራከራል። ጁባላንድ በራስካምቦኒ ከተማ የስልክ አገልግሎቶችን ያቋረጠ ሲሆን፣ የፀጥታ አካላትንም በአካባቢው አሰማርቷል። የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድን «ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም» የምትከሰው እና የፌደራል መንግስቱ ሕገመንግስቱን ጥሷል የምትለው ጁባላን ከፌደራል መንግስቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን ሕዳር 19፣ 2017 ዓ.ም አስታውቃለች። ፓርላማው ያሳለፈውን ሕገመንግስታዊ ማሻሻያ እንደማትቀበልም ገልጻለች። አንድ ቀን ቀደም ብሎ ሞቃዲሾ የሚገኝ ፍርድ ቤት፣ «አህመድ ማዶቤ» በሚል ስያሜ የሚታወቁትን የጁባላንድ መሪ አህመድ ሞሃመድ ኢስላም፣ በሀገር ክህደት እና የሀገር ሚስጥርን ለውጭ ሀገር በማጋራት ሕገመንግስትን የሚፃረር ድርጊት ፈፅመዋል በማለት የእስር ትዕዛዝ አውጥቶባቸዋል። ውዝግቡ የተቀሰቀሰው አህመድ ማዶቤ በጥቅምት ወር በሞቃዲሾ ከተካሄደው ብሔራዊ የምክክር ምክርቤት ስብሰባ አቋርጠው ከወጡ እና በሕዳር ወር ምርጫ በማካሄድ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ከተመረጡ በኃላ ነው። ክልሉ ቀጥተኛ ምርጫ ማካሄዱን የተቃወመው የፌደራል መንግስት ሂደቱን ውድቅ አድጓል። በወቅቱ የፌደራል መንግስት እና አንዳንድ የክልል አመራሮች የአካባቢ ምርጫዎችን በሰኔ ወር፣ የክልል ፓርላማ እና ፕሬዝዳንታዊ ምርጫዎችን ደግሞ በመስከረም 2018 ዓ.ም ለማካሄድ ተስማምተው ነበር። ጁባላንድ ግን ይህን ስምምነት አልተቀበለችውም።

በሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳ

ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ታግደው የነበሩ፣ በሰብአዊ መብት ጥበቃ ዙሪያ የሚሠሩ ድርጅቶች ዛሬ እግዳቸው ተነስቷል። በኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበ
የአሜሪካ ድምፅ

በሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳ

ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ታግደው የነበሩ፣ በሰብአዊ መብት ጥበቃ ዙሪያ የሚሠሩ ድርጅቶች ዛሬ እግዳቸው ተነስቷል። በኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በኅዳር ወር ውስጥ በቀናት ልዩነት እግድ ተጥሎባቸው የነበሩት፣ የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ)፣ የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች እና ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ የተባሉ ድርጅቶች ናቸው፡፡ ለእግዱ ምክንያት ተብሎ የተጠቀሰው ደግሞ፣ ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል፣ እንዲሁም የአገርንና የሕዝብን ጥቅም የሚጎዳ ተግባር አከናውነዋል የሚል ነበር፡፡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ፣ እግድ በተጣለባቸው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ “በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔ” እንደሚሰጥ ኅዳር 19 መግለጫ በሰጡበት ወቅት ገልጸው የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ታኅሣሥ 2 እግዱ መነሳቱ ታውቋል፡፡ ታግደው ከነበሩት ድርጅቶች አንዱ የኾነው የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች ዋና ዳይሬክተር አቶ አምሃ መኮንን፣ እግዱ መነሳቱን የሚገልጽ ደብዳቤ ከማስጠንቀቂያ ጋራ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

“ሱዳን ትልቁን ሰብአዊ ቀውስ የተሸከመች ሀገር ሆናለች” - ዓለም አቀፍ ነፍስ አድን ኮሚቴ

በሱዳን በጦር ሠራዊቱ እና በፈጥኖ ደራሽ ኅይሎች መካከል ለ20 ወራት የዘለቀውን አስከፊ ጦርነት ተከትሎ “እስከዛሬ ከተመዘገቡት ሁሉ ትልቁን ሰብአዊ ቀውስ የተሸ
የአሜሪካ ድምፅ

“ሱዳን ትልቁን ሰብአዊ ቀውስ የተሸከመች ሀገር ሆናለች” - ዓለም አቀፍ ነፍስ አድን ኮሚቴ

በሱዳን በጦር ሠራዊቱ እና በፈጥኖ ደራሽ ኅይሎች መካከል ለ20 ወራት የዘለቀውን አስከፊ ጦርነት ተከትሎ “እስከዛሬ ከተመዘገቡት ሁሉ ትልቁን ሰብአዊ ቀውስ የተሸከመች ሀገር ሆናለች” ሲል የዓለም ነፍስ አድን ኮሚቴ አመለከተ፡፡ በተቃናቃኞቹ ጀኔራሎች መካከል በቀጠለው ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ 12 ሚሊዮን የሚሆኑት ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የተቋሙ ዘገባ ጠቅሷል፡፡ ወደ ዘጠኝ ሚሊዮን የሚጠጉት በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ መሠረተ ልማቶች በወደሙባቸው አካባቢዎች የሠፈሩ ሲሆን የጅምላ ረሃብ ሥጋትም ተጋርጦባቸዋል። ዓለም አቀፉ ድርጅት በሱዳን ወደ 26 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ለከባድ ረሃብ መጋለጡን ገልጾ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ሰብአዊ ቀውስ ገጥሟታል ብሏል፡፡ “ከዓለም ሕዝብ ከአንድ ከመቶ ያነሰ የሕዝብ ብዛት ያላት ሱዳን በዓለም የሰብአዊ ርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ተረጅዎች መካከል 10 በመቶውን ትሸፍናለች” ሲል እአአ የአጣዳፊ ርዳታ ፈላጊዎችን የሚከታተለውና መሠረቱን በኒው ዮርክ ያደደረገው ድርጅት እአአ በቀጣዩ 2025 የአጣዳፊ ሁኔታ ክትትል በሚያስፈልጋቸው ቀውሶች ዘገባው አስታውቋል፡፡ የዓለም ነፍስ አድን ኮሚቴ ዘገባ በየዓመቱ ለሰብአዊ ቀውስ ተጋላጭነት ከፍተኛ ሥጋት ያለባቸውን 20 ሀገራት ለይቶ በማጉላት የሚያሳይ ሲሆን ሱዳን ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በቀዳሚነት ደረጃ ላይ እንደምትገኝ አመልክቷል፡፡ በሀገሪቱ በጠቅላላው 30.4 ሚሊዮን ሰዎች በሰብአዊ እርዳታ ፈላጊዎች መሆናቸውን የገለጸው ኮሚቴው የተረጅዎችን ቁጥር መመዝገብ ከጀመረ ወዲህ ይህ “ከምንጊዜውም ትልቁ የሰብአዊ ቀውስ” መሆኑን ገልጿል። ኮሚቴው በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም ወደ 305 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የሰብአዊ እርዳታ የሚሹ መሆኑን ዘግቧል፡፡ ከእነዚህ 82 ከመቶ የሚሆኑት በኃይል በተያዙት የፍልስጤም ግዛቶች፣ ሚያንማር፣ ሦሪያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሊባኖስ በመሳሰሉት ክትትል ያስፈልጋቸዋል ተብለው በተመዘገቡ የቀውስ አካባቢዎች እንደሚገኙ ዘገባው አመልክቷል፡፡ የዓለም ነፍስ አድን ኮሚቴ ኃላፊ ዴቪድ ሚሊባንድ ‘ዓለም እሳት ላይ ነች’ ይህ በመቶ ሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች የዕለት ተዕለት እውነታ እንደሆነ ግልጽ ነው።” ብለዋል፡፡ ሚሊባንድ አክለውም «ዓለማችን በሁለት ካምፖች እየተከፈለች ነው፤ ባልተረጋጋ እና ግጭት ባለበት ቦታ በተወለዱት እና በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ የመኖር እድል ባላቸው መካከል» ማለታቸውን ኤኤፍፒ ጠቅሷል፡፡

የአሳድ ውድቀት ሩሲያ በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ የነበራትን ዋና አጋር አሳጥቷታል

ከስልጣናቸው የተባረሩት የሶሪያ ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ ሞስኮ መግባታቸውን በመግለፅ፣ የሩሲያ መንግስት መገናኛ ብዙሃን ሞስኮ ለአሳድ ጥገኝነት መስጠቷ
የአሜሪካ ድምፅ

የአሳድ ውድቀት ሩሲያ በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ የነበራትን ዋና አጋር አሳጥቷታል

ከስልጣናቸው የተባረሩት የሶሪያ ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ ሞስኮ መግባታቸውን በመግለፅ፣ የሩሲያ መንግስት መገናኛ ብዙሃን ሞስኮ ለአሳድ ጥገኝነት መስጠቷን ዘግበዋል። አሳድ በስልጣን ላይ እያሉ ታጣቂዎችን ለማሸነፍ ባደረጉት ትግል ክሬምሊን ቁልፍ የመንግስታቸው ደጋፊ የነበረች ሲሆን፣ ሞስኮ በሶሪያ የነበራትን፣ ከጥቂት ቀናት በፊት የማይነቃነቅ ይመስል የነበረ የበላይነት መልሶ ለማግኘት ግን አዳጋች ሊሆንባት ይችላል። ሪካርዶ ማርኪና በዚህ ዙሪያ ያደረሰንን ዘገባ፣ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ከአሰቃቂው የባሕር ላይ አደጋ የተረፉት ፍልሰተኞች ይናገራሉ

ከአንድ ወር በፊት፣ በአብዛኛው ሶማሊያውያን ፍልሰተኞች የተሳፈሩባቸውንና ወደ ማዮት ደሴት በማቅናት ላይ የነበሩ ሁለት ጀልባዎችን፣ የጀልባዎቹ አዛዦች የሆ
የአሜሪካ ድምፅ

ከአሰቃቂው የባሕር ላይ አደጋ የተረፉት ፍልሰተኞች ይናገራሉ

ከአንድ ወር በፊት፣ በአብዛኛው ሶማሊያውያን ፍልሰተኞች የተሳፈሩባቸውንና ወደ ማዮት ደሴት በማቅናት ላይ የነበሩ ሁለት ጀልባዎችን፣ የጀልባዎቹ አዛዦች የሆኑት ሕገ ወጥ አስተላላፊዎች መሃል ባሕሩ ላይ ጥለዋቸው በመሄዳቸው፣ ቢያንስ 27 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአፍሪካ ቀንድ አገልግሎት ባልደረባ ሃሩን ማሩፍ፣ ከአደጋው የተረፉትን አነጋግሮ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የጦር አካል ጉዳተኞች ከመቐለ ወደ ዓዲግራት የሚወስደውን መንገድ በተቃውሞ ዘግተው ዋሉ

በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊ የጦር አካል ጉዳተኞች ዛሬ ማክሰኞ ታኅሣስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. የክልሉ ዋና ከተማ መቐለን ከዓዲግራትና ሌሎች ከተሞች የሚያገናኘውን የ
የአሜሪካ ድምፅ

የጦር አካል ጉዳተኞች ከመቐለ ወደ ዓዲግራት የሚወስደውን መንገድ በተቃውሞ ዘግተው ዋሉ

በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊ የጦር አካል ጉዳተኞች ዛሬ ማክሰኞ ታኅሣስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. የክልሉ ዋና ከተማ መቐለን ከዓዲግራትና ሌሎች ከተሞች የሚያገናኘውን የተሽከርካሪ ማለፊያ መስመር በተቃውሞ ዘግተውት ዋሉ። የጦር አካል ጉዳተኞቹ፣ “በትጥቅ ማስፈታትና የመልሶ ማቋቋም ሂደት ላይ ከሌሎች ሙሉ አካል ካላቸው የቀድሞ ተዋጊዎች ጋራ ተመድበናል በቂ ህክምናም እያገኘን አይደለም፣ አመራሮውቹ ረስተውናል” የሚሉና ሌሎች ተቃውሞዎችን በማስማት ከመቐለ ከተማ ሰላሳ ኪሎሜትር በምትርቀው አጉላዕ በተባለች ከተማ ላይ መንገድ ዘግተው ውለዋል። ከትግራይ የጸጥታ ኃይሎች አመራር ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ ጋራ በጉዳዩ ላይ ከተወያዩ በኋላ መንገዱ ተከፍቷል።

ጋና የገጠማትን የኢኮኖሚ ቀውስ ለመፍታት ተመራጩ ፕሬዝደንት የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ ተጠየቀ

የቀድሞ የጋና ፕሬዝደንት እና የተቃዋሚ መሪው ጃን ማሃማ ባለፈው ቅዳሜ በተደረገው ምርጫ ማሸነፋቸውን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ ሰኞ አስታውቋል። ማሃማ ወ
የአሜሪካ ድምፅ

ጋና የገጠማትን የኢኮኖሚ ቀውስ ለመፍታት ተመራጩ ፕሬዝደንት የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ ተጠየቀ

የቀድሞ የጋና ፕሬዝደንት እና የተቃዋሚ መሪው ጃን ማሃማ ባለፈው ቅዳሜ በተደረገው ምርጫ ማሸነፋቸውን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ ሰኞ አስታውቋል። ማሃማ ወደ ሥልጣን የመመለሳቸው ጉዳይ የተደበላለቁ አስተያየቶችን በማስተናገድ ላይ ነው። አንዳንዶች ማሃማት በአዲስ መልክ ለማስተዳደር በመመለሳቸው ደስታቸውን ሲገልጹ፣ ሌሎች ደግሞ የጋናን የኢኮኖሚ ተግዳሮቶች የመፍታት አቅማቸው ላይ ጥያቄ አላቸው። የቪኦኤው ሰናኑ ቶድ ከአክራ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

በሶሪያ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር አቋም ከእስላማዊ መንግስት ከፍተኛ የመልሶ ማጥቃት በኋላም አልተለወጠም

የደማስቆ ውድቀት፣ በጦርነት በተናጠች ሀገር ውስጥ እስላማዊ መንግሥት እንዳያንሰራራ ለማድረግ፣ ከአጋሮች ጋር ተባብረው ሲሰሩ የቆዩ የአሜሪካ ወታደሮች ቀጣ
የአሜሪካ ድምፅ

በሶሪያ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር አቋም ከእስላማዊ መንግስት ከፍተኛ የመልሶ ማጥቃት በኋላም አልተለወጠም

የደማስቆ ውድቀት፣ በጦርነት በተናጠች ሀገር ውስጥ እስላማዊ መንግሥት እንዳያንሰራራ ለማድረግ፣ ከአጋሮች ጋር ተባብረው ሲሰሩ የቆዩ የአሜሪካ ወታደሮች ቀጣይ እጣ፣ ምን ሊሆን እንደሚችል ስጋት አሳድሯል። በፔንታገን የቪኦኤ ዘጋቢ ካርላ ባብ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የታገዱት የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ህልውናቸው አደጋ ላይ መውደቁን መሪዎቹ ገለጹ

ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ከታገዱት ሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሁለቱ አመራሮች የድርጅታቸው ሕልውና አደጋ ላይ መውደቁን ተናገሩ። የመብቶችና ዴሞክራ
የአሜሪካ ድምፅ

የታገዱት የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ህልውናቸው አደጋ ላይ መውደቁን መሪዎቹ ገለጹ

ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ከታገዱት ሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሁለቱ አመራሮች የድርጅታቸው ሕልውና አደጋ ላይ መውደቁን ተናገሩ። የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) እና የሕግ ባለሞያዎች ለሰብአዊ መብቶች የተባሉ ሁለቱ የሲቪል ማኅበራት ድርጅት መሪዎች የባንክ ሂሳባቸው በመታገዱ ምክኒያት፣ ለሠራተኞች ደሞዝ መክፈልን ጨምሮ ምንም ዐይነት እንቅስቃሴ ማድረግ ባለመቻላቸው ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ገለጹ። ከኢትዮጵያ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ይኹንና ኅዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም. የተቋሙ ምክትል ዲሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ፣ እየተከናወነ ነው ያሏቸው የማጣራት ሥራ ሲጠናቀቅ ውጤቱ እንደሚገለጽ በቅርቡ መናገራቸው ይታወሳል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Get more results via ClueGoal