ዩክሬይን ሞስኮ ውስጥ የሩስያን ጄኔራል ለገደለው የቦምብ ፍንዳታ ኃላፊነት ወሰደች
newsare.net
የሩስያ የኑክሌር ባዮሎጅካዊ እና ኬሚካል መከላከያ ኃይል ዘርፍ አዛዥ የነበሩት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ ዛሬ ማክሰኞ ሞስኮ ውስጥ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ተገድለዩክሬይን ሞስኮ ውስጥ የሩስያን ጄኔራል ለገደለው የቦምብ ፍንዳታ ኃላፊነት ወሰደች
የሩስያ የኑክሌር ባዮሎጅካዊ እና ኬሚካል መከላከያ ኃይል ዘርፍ አዛዥ የነበሩት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ ዛሬ ማክሰኞ ሞስኮ ውስጥ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ተገድለዋል፡፡ ዩክሬን ጄኔራሉን በሚኖሩበት ሕንጻ ደጃፍ መንገድ ላይ በቆመ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ (ስኩተር) ላይ እንዳይታይ ተደርጎ በተጠመደ ቦምብ መግደሏን አስታውቃለች፡፡ ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ እና ረዳታቸው የተገደሉት በደቡብ ምስራቅ ሞስኮ ከሚገኘው መኖሪያቸው ወደ ሥራ ለመሄድ እየወጡ በነበረበት ወቅት መሆኑን የሩሲያ የምርመራ ቡድን አስታውቋል፡፡ ፍንዳታው ከተፈፀመበት ቦታ የወጣው ቪዲዮ የተቃጠለ የህንጻው የፊት ለፊት ገጽታ፣ የተሰባበሩ ጡቦች እና መስኮቶችን ያሳያል። የቦምብ ጥቃቱ የደረሰው ኪሪሎቭን ለሦስት አመታት በዘለቀው ጦርነት የሩስያ ሃይሎች በዩክሬን ላይ ተጠቅመውታል በተባለው የኬሚካል ጦር መሣሪያ እጃቸው አለበት በሚል የዩክሬን አቃቤ ሕግ ክስ ከመሰረተባቸው ከአንድ ቀን በኋላ መሆኑ ነው። ብሪታንያን እና ካናዳን ጨምሮ በርካታ ሀገሮች ኪሪሎቭን በጦርነቱ ከነበራቸው ሚና ጋራ በተያያዘ ባለፈው ጥቅምት ማዕቀብ ጥለውባቸው ነበር፡፡ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የዩክሬን የደኅንነት አገልግሎት ባለሥልጣን ከጥቃቱ ጀርባ ኤጀንሲው እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ ባለሥልጣኑ ኪሪሎቭን “የጦር ወንጀለኛው ሙሉ በሙሉ ሕጋዊ ኢላማ” ነበር ሲሉም ተናግረዋል፡፡ የሩሲያ የዜና ማሰራጫዎች ቦምቡ በርቀት መቆጣጠሪያ እንደፈነዳ ዘግበዋል፡፡ ዋናው የሩሲያ መንግሥት የምርመራ ተቋም በበኩሉ የጄኔራል ኪሪሎቭን ሞት የሽብርተኝነት ምርመራ የከፈተበት መሆኑን አስታውቋል፡፡ የሩሲያ ባለሥልጣናት «ዩክሬንን እንቀጣታለን» ሲሉ ዝተዋል፡፡ Read more