የውጭ ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሠሩ የሚፈቅደው ዐዋጅ ጸደቀ
newsare.net
የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ እንዲሳተፉ የሚፈቅደው “የባንክ ሥራ ረቂቅ ዐዋጅ” በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጸድቋል። ውሳኔው የሀገር ውስጥ ባየውጭ ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሠሩ የሚፈቅደው ዐዋጅ ጸደቀ
የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ እንዲሳተፉ የሚፈቅደው “የባንክ ሥራ ረቂቅ ዐዋጅ” በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጸድቋል። ውሳኔው የሀገር ውስጥ ባንኮችን ከውድድር ውጭ በማድረግ ከዘርፉ ሊያስወጣቸው እንደሚችል የምክር ቤቱ አባላት ስጋታቸውን አንፀባርቀዋል። የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በሰጡት ምላሽ፣ የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ እንዲሠሩ መፈቀዱ የሀገር ውስጥ ባንኮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አይኖረውም ብለዋል፡፡ የምጣኔ ሀብት ጉዳዮች ተንታኝ ዶ/ር አብዱል መናን መሐመድም፣ የባንክ ዘርፉን ለውጭ ባንኮች ክፍት ማድረግ፣ ለሀገር ውስጥ ባንኮች ስጋት አይኾንም ይላሉ፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። Read more